💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
ኢኽዋን ፣ ሱሩሪያ

የቢድዓ ሰዎች ግለሠቦች ላይ መናገር
➻ዉዷ እህቴ ሆይ

☞ ሰውነትሽ መሸፈንሽ ስልጣኔሽ ሲሆን መገላለጥሽ ደሞ በተቃራኒው መሀይምትሽ ነው!!
ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም!

➲ነብዩﷺ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦

➲‹‹ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እኔ ያላየኋቸው ወደፊት የሚመጡ! አንደኛቸው ለብሰው ያለበሱ(የለበሰቱ ልብስ ሰውነታቸውን የማይሸፍን) አካሄዳቸው እና እንቅስቃሲያቸው ወደ ፀያፍ ተግባር ያዘነበሉ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ሴቶች ናቸው።

➲እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም፡፡››

📚ሙስሊም ዘግበውታል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሰላሳ ሰባት ➲ስንታመም የሚያድነን ማን ነው? ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➠የሚከተለው የሺርክ መንዙማ ደግሞ በጉራጊኛ ቋንቋ ከአላህ ውጭ አቡል ጀበል የሚባለው ግለሰብ የእግርም ሆነ የእጅ ቁስላችንን ያድነናል ብለው የሚያምኑበት እና እሱን ሰውየውን በቀጥታ የሚለምኑበት ነው። ➴➴“አቡል ጀበል ሺሊላህ አቡል ጀበል ሺሊላህ፣ አሁን ትሆኝ እና መላ፣ …
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➳ክፍል ሰላሳ ስምንት
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር”
“ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር፣
ሲፈቱ መለኪይ ዛቱ የበሸር፣
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሺር ወአንዚር፣
ጎራ እማይጋርደው ይዟል መነጠር፣
ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር፣ ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ኸጢር”


➲ ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር፣
እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር፣ ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር” እጣው እንደ ነቢ...” እስኪ ይህን ድፍረት ተመልከቱ፡፡ “ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) አትጣሩ” ሲባሉ “ክብራቸውን አጎደፋችሁ፡፡


➩ እሳቸው እንደኛ ተራ ሰው አይደሉም” እያሉ ፈጥረው የሚወነጅሉ ሰዎች እዚህ ግን አንድን ተራ ምስኪን ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ጋር እያመሳሰለ ነው፡፡

➧እነዚህ ስንኞች በደካማ ፍጡሮች ላይ ድንበር ማለፍ፣ የጌታን ክብር ማጉደፍ፣ ፍጡሮችን ከፈጣሪ ጋር ማመሳሰል አለባቸው። በዚያ ላይ ያፈጠጡ ያገጠጡ ውሸቶች ታጭቀውባቸዋል። አላህ እሱ ላይ የሚዋሹ ሰዎችን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡-

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۗ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ

➬በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው እነሆ በደለኞች አይድኑም።” [አልአንዓም፡ 21]

➲ከኢልመል ገይብ ጋር የሚጋጩ ስንኞች ''ኢልመል ገይብ” ማለት የሩቅ እውቀት ማለት ነው። የሩቅ እውቀት በጠቅላላ የአላህ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ

«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡'' [አንነምል፡ 65]

عن ابن عمر رضي الله ‏عنهما ‏أن رسول الله صلى الله، عليه وسلم قال مفاتيح
الغيب ‏خمسة لا ‏يعلمها ‏ إلا الله، لا يعلم ما في غدٍ الا الله، ولا يعلم ما تغ؜ ‏
الأرحام ‏إلا الله، ولا يعلم متى يأتي المطر احد ‏إلا الله، ولا تدري نفس بأي ‏الأرض تموت، ولا يعلم متى تقم الساعة ‏ الا الله،


➩ከዐብደላህ ኢብን ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል “የሩቅ ሚስጥር ቁልፍ አምስት ናቸው። አላህ እንጂ ማንም የማያውቃቸው።

➧ ነገ ምን እንደሚከሰት አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። ሆድ ውስጥ (የተረገዘው) ምን እንደሆነ አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። አላህ እንጂ መቼ እንደሚዘንብ ማንም አያውቅም። ነፍስ የት እንደምትሞት ማንም አያውቅም። የምፅዓት ቀን መቼ እንደምትቆም አላህ እንጂ ማንም አያውቅም።”

➲ኢማሙ አል ቡኻሪ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم
) “የሩቅን ሚስጥር (ነገር) ከአላህ ውጭ የሚያውቅ የለም” ብለዋል። ኢማሙ ጠበራኒ ዘግበውታል።

አላህ ከመልክተኞቹ ለፈለገው የፈለገውን የሩቅ ሚስጥር ያሳውቃል። ይህ ሆኖ ሳለ እውነታው ተመልክቱ የሚከተሉት ስንኞች እንዴት ከእስልምና አስተምህሮት እንደሚጋጩ፡-

“አልዩ ሀይደር
ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር፣
ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር።”
ማን ነበር ጠያቂው? የታለስ ማስረጃው?


“ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን፣
መተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹ፣
በወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹ፣
የረሱል ምስለኔ አላጋውን ወራሹ፣
የልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ”
“ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ፣
ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፣
እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር፣

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
♦️ تلاوة من سورة المؤمنون
♦️ القارئ: #صالح_الفالح
•••━══❁✿❁══━•••
✅ ማራኪ ቲላዋ
✅ የቁርአን ግብዣ
♦️قال ابن القيم رحمه الله:

📌"إنَّ الكريم المحسن أشرح النَّاس صدرًا، وأطيبهم نفسًا، وأنعمهم قلبًا، والبخيل الذي ليس فيه إحسان أضيق النَّاس صدرًا، وأنكدهم عيشًا، وأعظمهم همًّا وغمًّا".

📚(زاد المعاد ج٢ ص٢٢
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
إنا لله وإنا إليه راجعون
اللهم أجرنا في مصيبتنا واخلفنا خيرا منها
توفي شيخنا العلامة صالح اللحيدان عضو هيئة كبار العلماء.

🔶 إن القلب ليحزن وإن العين لتدمع ولا نقول إلا ما يرضي ربنا.
🔹 أعظم الله أجركم يا أهل السنة
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሰባት ➛➛➛➛➛➛ ➲ሶስተኛው፡- በእውቀቱ ለማይሰራ ሰው የተላለፈ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ባወቁት የማይሰሩ ሰዎች ዛቻና ውግዘት በቁርኣንና በሐዲስ ደርሶባቸዋል፡፡ አላህበተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ◆كَبُرَ…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➳ክፍል ስምንት

➲አራተኛው፡ - ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው ወደአላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች የትንሳኤ ቀን ባሪያው በአላህ ውዴታ የሚጎናጸፍበት በጀነት ድልብ ሀብት ሆኖ እንደሚቆየው የሸሪዓ መረጃዎች ሁሉ ይጠቁማሉ፡፡

➧በቁርኣን ፣ ተግባር በኢማን ስም ከመግባቱ በተጨማሪ ኢማን እናተግባርን በማጣመር የሚገኘውን ምንዳ ፣ የሁኔታቸውን ታላቅነት እና ደረጃ በማብራራት አምሳ የሚሆኑ አንቀጾች መጠዋል፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን
፡፡” አን ነህል ፡97

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

“እነዚያም ያመኑት በጎ ስራዎችንም የሰሩት እነዚያ የጀነት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውሰጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡”
አል በቀራህ፡82

وَنُودُوا أَن تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
“ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡” አል አዕራፍ፡43

الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُون

“እነዚያ በመልካም ሁኔታ ላይ ሆነው መላእክት “ሰላም በእናንተ ላይ” እያሉ የሚገድሏው ናቸው፡፡ “ትሰሩት በነበራችሁት ስራ ጀነትን ግቡ” (ይባላሉ
)፡፡” አን ነህል፡32

➧በዚህ ትርጉም ላይ የመጡ አንቀጾች በርካታ ናቸው፡፡ ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው፡፡ ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"لن يدخل أحدا عمله الجنة"

➛“አንድ ሰው ስራው ፍጹም ጀነት ሊያስገባው አይችልም፡፡” ሶሃቦች “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንተም?!” በማለት ጠየቁ፡፡ “እኔም ብሆን ፤ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ ካልሸፈነኝ በቀር፡፡” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡ 5673 ሙስሊም፡2816

➲ተግባር ከጀነት ምክንያቶች አንዱ ምክንያት ነው፡፡ የዚህ ሐዲስ መንፈስ ፣ ጀነት የሚግገባው በአላህ እዝነት እንጅ በዱንያ ላይ የሰራው መልካም ስራ ለውጥ ሆኖት ጀነት ያስገባዋል ማለት አይደለም፡፡

➧ተግባር ለውጥ ወይም ቅያር ሆኖ ጀነት አያስገባም፡፡ ጀነት የሚገባው በአላህ እዝነት እና ችሮታ ነው፡፡ይልቁንም ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው፡፡ባሪያው የሚተገብረው መልካም ተግባርም ቢሆን በአላህ እዝነትና በአላህ ችሮታ ነው፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

۞ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ مَا زَكَىٰ مِنكُم مِّنْ أَحَدٍ أَبَدًا وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يُزَكِّي مَن يَشَاءُ ۗ

“በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ ባልጠራ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል
፡፡” አን ኑር፡21
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
እኛም የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን
إنا لله وإنا إليه راجعون

◾️ኡመተል ኢስላም ዛሬ አንድ የምድር ኮከቧን፣ አለኝ የምትለው ታላቅ አሊሟን፣ ሁነኛ መካሪዋና ገሳጯን አጥታለች። ታላቁ ኣሊም ሸህ ሷሊህ አሉሐይዳን ወደ አሔራ ሄደዋል።

إن القلب ليحزن وإن العين لتدمع ولا نقول إلا ما يرضي ربنا وإنا على فراقك يا شيخنا لمحزونون
اللهم ارض عنه واغفر له وارحمه واجعل قبره روضة من رياض الجنة واجعله في الفردوس الأعلى من الجنة اللهم اغفر له وارحمه واسكنه فسيح جناتك

➡️ የአላህን ዲን የተረዳ፣ ሀላሉና ሀራሙን ጠንቅቆ የሚያውቅና የሚያሳውቅ የአንድ አሊም ሞት ከአንድ ሺህ ኣቢድ ሞት ጋር አይስተካከልም።
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ④①➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

✅ የአንድ ዓሊም ሞት በእስልምና ውስጥ ቀንና ሌሊት ቢለያዩም በምንም ነገር ሊዘጋ የማይችል ቀዳዳ ነው።

📚[جامِع بيان العِلم وفضله -١\٥٩٥-]
Forwarded from Ř§Ů„Ů…ŮŽŮ†Ů‡ŘŹŮ السَّلفي لــيس لـه بَديل
ድንቅ መልስ
__
"ኒቃብሽ ብዙ በሮችን ይዘጋብሻል" አሏት
እሷም
"የጀሀነምን በር መዝጋቱ ይበቃኛል" አለቻቸዉ
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➳ክፍል ሰላሳ ስምንት ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➧የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር” “ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር፣ ሲፈቱ መለኪይ ዛቱ የበሸር፣ ተብሎ አላህ ዘንዳ በሺር ወአንዚር፣ ጎራ እማይጋርደው ይዟል መነጠር፣ ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር፣ ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ኸጢር” ➲ ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር፣ እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር፣ ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር”…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሰላሳ ዘጠኝ
〰〰〰〰〰〰

➧“ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን፣
መተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹ፣
በወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹ፣
የረሱል ምስለኔ አላጋውን ወራሹ፣
የልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ
”

“ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ፣
ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፣
እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር፣
ይላል እንዘይር ቀልቡን ሳያጠራ፣
የማያውቁ መስሎት የቀልቡን የሰድሩን


አላህ እንዲህ ይላል፡

إِنَّهُ عَلِيمٌ بِذَاتِ الصُّدُورِ

“እርሱ በደረቶች ውስጥ ያለውን ሁሉ ዐዋቂ ነውና።” [ሁድ፡ 5]

“ሰይድ ቡሽራ ገታ ቀምጣላው ገበር፣
ከልካይ የለበትም ሲዘልቅ እልፍኝ በር
ጨወታው ነበር ቀዷ ቀደር ጋር፣”


➲አዑዙ ቢላህ!! ሰዎቹ ድፍረታቸው የት እንደደረሰ ተመልከቱ። ጭራሽ ቀዷና
ቀደር እስከመቀያየር ስልጣን ነው የሚያንጋጥጡት። ሰዎቹ እዚሁ ላይ በቃ ካልተባሉ ለጥፋታቸው ለከት የላቸውም። ተናጋሪዎቹስ ሰውነታቸው ጥፋትን ተላምዷል።


➧ሙስሊም የሆነ ሰው ይህን ሲሰማ አይሰቀጥጠውም? በማዳመጡ ብቻ አላህ እንዳይጠይቀው አይፈራምን?
አላህ ከመልክተኞቹ ለወደደው ብቻ ነው የሩቅን ሚስጥር ያውም ከፊሉን
የሚሳውቀው።



عَالِمُ الْغَيْبِ فَلَا يُظْهِرُ عَلَىٰ غَيْبِهِ أَحَدًا⓺⓶إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا⓻⓶

“(እርሱ አላህ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው። በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም። ከመልክተኛ ለወደደው ቢሆን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)። እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል
። [አልጂን፡ 26-27]

➧ለምሳሌ ለነብዩ صلى الله عليه وسلم ቂያማ መቼ እንደሚከሰት አላሳወቃቸውም።ነገር ግን ምልክቶቿን አሳውቋቸዋል። ስለዚህ መልክተኞች እንኳን ከሩቅ ሚስጥር አላህ የወደደላቸው እና ከፊል የፈለገውን ብቻ ነው የሚያሳውቃቸው። እዚህስ?

“እነሸሁ ሀቢብ ጓደኛው ገበር፣
ከአርሽ እስከ ሰራ ይታየው ነበር፣
አላህ አርጎት ነበር የሚስጥር ሰፈር”
“እንደ ሁሴን ጂብሪል ደግሞ ማን ነበር፣
የከሽፉ መነጠር አይኑ ላይ ነበር፣
የፊቱን የኋላን ይናገር ነበር፣
ሁሉም ተገላልጦ ይታየው ነበር።”
“መጂት ሀጅ ቡሽራ የራቀው ገበር፣
አገላባጭ ነበር የቀዷ ደብተር፣
ለውሀል መህፉዝ አይቶ ነበር ሲናገር።”
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን።

➲ውሸቶች እና ተረተረቶች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭እነዚህ መንዙማ ባዮች “ወልይ” የሚሏቸውን ሰዎች በውሸት እና በተረተረቶች የሚክቡት ሰውን የነሱ (የሸሆቹ) ባሪያ ለማድረግ ነው። ሰዎቹን ከደረጃቸው በላይ ከፍ ከፍ በማድረግ ሰዎች እንዲያመልኳቸው በርን ለመክፈት የሚደረግ ጥረት ነው።ማንኛውም ሙስሊም ወሬን ማጣራት አለበት። አላህ እንዲህ ይላል


يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِن جَاءَكُمْ فَاسِقٌ بِنَبَإٍ فَتَبَيَّنُوا أَن تُصِيبُوا قَوْمًا بِجَهَالَةٍ فَتُصْبِحُوا عَلَىٰ مَا فَعَلْتُمْ نَادِمِينَ

➲“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነገረኛ ወሬን ቢያመጣላችሁ በስህተት ላይ ሆናችሁ ሕዝቦችን እንዳትጎዱና በሠራችሁት ነገር ላይ ተጸጸቾች እንዳትሆኑ አረጋግጡ።”
[አልሑጁራት፡ 6]

➠እነዚህ መንዙማ ባዮች ከላይ እንዳሳለፍነው አላህ እና መልክተኛው ላይ ሲዋሹ ምንም ያልመሰላቸው ሌሎች ግለሰቦች ላይ አይዋሹም አንልም። እነሱ “ወልይ” የሚሏቸው ላይ ድንበር አልፈው ያልሰሩትን ሰሩ እያሉ ሲናገሩ በሸሪዓ ሚዛን ወሬውን ልናጣራው ይገባል።

የሚከተሉት ስንኞች ቅጥፈቶች ናቸው።

“ጌታው ሀሰን ለሚ በራራ ነበር፣
ሙት የሚቀሰቅስ ጉድ ያለው ገበር፣
ለሰሚው ይአጅባል የሰሩት ነገር”
“የጌታው ስጦታ ስፍር የለው ቁጥር፣
ለሸህ አሊ ጎንደር፣ አድርጎት ነበር ባለመነጠር፣
ለበረካው ያህል ጥቂት ልናገር፣
አንዲት ላም ኮሬብ ላይ ስትበላ ሳር፣
እላይዋ ላይ ወጥታ በናትዎ ቀብር፣


ጎንደር ሆነው አዩዋት የሚያጅብ ነገር፣
ተዛ ተቆጡና ሸህ አሊ ጎንደር፣
ሆዷን ቢሏት ሞተች ወርውረው ጢጠር፣
ምነው አይባልም የወልይ ነገር፣
ለባለቤቲቱ ሰደዱላት ብር፣
አፉ በይኝ አሏት ሀቋም እንዳይቀር፣
እየው የአላህ ስራ ከባሮቹ ጋር”

➲“ምነው” የማይባለው አላህ ነው። ስለዚህ እንጠይቃለን፡- ማገናዘብ የማትችለውን ላም እንዴት ቀብር ላይ ወጣች ብለው ከጎንደር ወሎ ወርውረው ገደሏት? በዚህ መልኩ ነፍስ ማጥፋት ይፈቀዳል? ለነገሩ የብዙ “ወልዮች” ገድል በነፍስ ማጥፋት ታሪክ የተሞላ ነው።

➧ “እከሌ ወልይ እከሌ የሚባሉትን በመዐና ገደሏቸው”፣ “አርባውን አባወራ ድንጋይ አደረጉት”፣… አይነት ታሪኮች ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሪኮች እውነት ብለን ከተቀበልን እነዚህ ሰዎች ነፍሰ በላዎች ናቸው። ስለዚህ ልናከብራቸው ሳይሆን ልንፀየፋቸው ነው የሚገባን። ታሪኩን ውሸት ነው ብለን ከመለስን እንዲህ አይነት ተረት የሚያወሩ የዲን ነጋዴዎችን ልንርቅ ይገባል።
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➧አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!


➭ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ ለሌሎችም ሺር ያድጉት
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
وَدِيعٌ اليَمَنِي
<unknown>
بعيداً عن أيّ ضجيج.. أرح مسمَعك"

✅ ማራኪ ቲላዋ
✅ የቁርአን ግብዣ
➷"በተግባር የታጀበ እውቀት ፍሬ
እንዳለው ዛፍ ነው!


ተግባርን ያላካተተ እውቀት ደግሞ ፍሬ
እንደሌለው ዛፍ ነው "
[ ሼኽ ሳሊህ አል
ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ]

{ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻋﻠﻤﻨﺎ ﻣﺎ ﻳﻨﻔﻌﻨﺎ ﻭﺍﻧﻔﻌﻨﺎ ﺑﻤﺎ
ﻋﻠﻤﺘﻨﺎ ﺍﻧﻚ ﺍﻧﺖ ﺍﻟﻌﻠﻴﻢ ﺍﻟﺤﻜﻴﻢ}
➧ቁርአን ስትቀርበው ይበልጥ ላንተ ቅርብህ ይሆናል በውስጥህ ያለን ጭንቀት አስወግዶ ልብህን በደስታ ሀሴት ይሞላል!!!
(فضايل القران 297 )