💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➲እንስቶች ሆይ ይህንን የታላቅ ዓሊም ንግግር ስሙልኝ!!!

وقال شيخ العلامۃ صالح الفوزان حفظه الله

ومن النساء المسلمات من يستعملن النفاق ّفی الحجاب فإذا كُنَّ فی مجتمع يلتزم الحجاب احْتجبن وإذا كُنَّ في مجتمع لا يلتزم بالحجاب لم يحْتجِبْنَ

📌ከሴቶች መካከል በሒጃባቸው ንፍቅና የሚሰሩ አሉ ።

➧ሒጃብ የሚደረግበት አከባቢ ሲሆኑ ሒጃብ ያደርጋሉ ፣ ሒጃብ የማያደርጉ የሆኑ ማህበረሰብ ዘንድ ሲሆኑ ደግሞ ሒጃብ አያደርጉም !!

ومنهن من يحتجبن إذا كانت في مكان عامٍّ وإذا دخلت محلاً تجَّاريۃ أو مُسْتَشْفَٰی أو كانت تكلم أحدً صاغَۃِ الحُليِ أو أحدٌ خياطي الملابس النساءيۃ كشفت وجهها وذراعيها كأنها عند زوجها أو أحد محارمها فتقين الله يا من تفعلن ذالك

📖 تنبهات علی أحكام تختص بالمأمنات
للشيخ صالح الفوزان خفظه الله

📌 ማህበረሰብ በሚበዛበት ቦታ ላይ የሚሸፈኑ አሉ ፣ ከዛም ወደ ገበያ ቦታዎች እና ሆስፒታሎች ፣ ወይንም አንድን ወርቅን አንጣሪ ሳናግር ፣ ወይንም ደግሞ የሴቶችን ልብስ የሚሰፋን ሰውየ ስታናግር ፣ ፊቷን ፣ እጇን ጧቶቿን ፣ ትገልጣለች ።

📌ልክ ባሏ ዘንድ እና የሷ ቅርብ ቤተሰብ ዘንድ እንዳለች ሁላ ፊቷንም እጆቿንም ትገልጣለች ።
ይህንን የምታደርጊ እንስት ሆይ አሏህን ፍሪ ። ‼️‼️

እህቴ ሆይ የዝህ የትልቅ ዓሊም ምክር ላንቺ ነው በሒጃብሽ በኒቃብሽ ምን ያክል ጠንካራ ነሽ እስኪ ራስን ፈትሺ ።

📌አንዳንድ እህቶች ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ቤት ሲገቡ ሒጃብን እንዳለ ይረሱታል ይገላለጣሉ አሏሙስተዓን አሏህ ቀልቡን ይስጣቸው ።

📌እናም እህቴ ከነዝህ አይነት እንስቶች እንዳትሆኚ በሒጃብሽ ጠንክሪ ሒጃብሽ እዝህ ሀገር ብትመጪም እዛ ብትሆኚም እስከ እለተሞትሽ ዘውታሪ መሆን አለበት
።

ሒጃብን ያዘዘው አሏህ እንጅ የሱዑዲ መንግስት ብቻ አይደለም እዝህ ሀገራችን ብትመጪም በዛው መቀጠል አለብሽ እንጅ ቦሌ ስትደርሺ ሂጃቡን ጥለሽ በራቆትሽ ሀገርሽ አትግቢ ።

👉እንዲህማ ከሆነ ይህ ሙናፊቅነት ነው ሼይኹ እንዳሉት ማለት ነው ።

አሏህ ለእህቶቻችን በኒቃብ ላይ እስከ እለተሞት ድረስ ፅናቱን ይስጥልን እዝህ መጥተው ለሚያወልቁት ደግሞ አሏህ ልቦናን ይለግስልን ። አሚን

✍ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

https://t.me/abuUseyminabdurehman
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ④②➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏህ ወበረካቱህ

ያ ጀመዐ እንደት ናችሁ እኔ በጣም ሰላም ነኝ አልሐምዱሊላህ።

#ኑረዲን አል አረቢ
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሰላሳ ዘጠኝ 〰〰〰〰〰〰 ➧“ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን፣ መተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹ፣ በወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹ፣ የረሱል ምስለኔ አላጋውን ወራሹ፣ የልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ” “ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ፣ ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፣ እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር፣ ይላል እንዘይር ቀልቡን ሳያጠራ፣ የማያውቁ…
➧መንዙማ
➫➫➫➫

➭ክፍል አርባ
➛➛➛➛➛

➲“የሂዲ ሸህ ደግሞ ጋላቢው ነብር”
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➧አብዛሀኛዎቹ የሃገራችን የአውሊያእ ጀብዱዎች ከአሉ አሉ ባለፈ ይሄ ነው
የሚባል ማረጋገጫ የማይቀርብባቸው ተረቶች ናቸው
። ይህን የምለው ከራማን ለመቃወም አይደለም። በአላህ፣ በዲኑ እና በመልእክተኛው ላይ የሚዋሽ አካል ገበያ ለመፍጠር ሲል ድንበር በሚያልፍባቸው አካላት ላይ አይዋሽም ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ስለዚህ በደፈናው ባንቃወምም ያለ አስተማማኝ ሰነድ የሚወሩ ወጣ ያሉ ቂሷዎቻቸውን ያለተጨባጭ ማስረጃ ልንቀበል አይገባም። የት አለ ውሸታቸው ከተባለ
ለምሳሌ ያክል ይሄውና፡

“ሸህ ሙሀመድ ሸሪፍ የርጎየው ገበር፣
ሲመድህ ሙስጠፋን እያየ ነበር።”


➭ነብዩ صلى الله عليه وسلم መዲና ቀብር ውስጥ ነው ያሉት። ታዲያ እንዴት ነው የሚያያቸው? ከሞቱ በኋላ በህልም እንጂ ማንም በአካል አያያቸውም። ሌላ ውሸት ይሄውና!

“ረቢአል አወል የገባ ጊዜና፣
በሀኢሙ (እንስሳው) ሁላ ያቀርባል ምስጋና፣
ለመውሊድ አድርገን እያለ መውላና
”

➧ሐቅ የያዙ ሰዎች በሚያንቀላፉበት ምድር ውሸታሞች ይህን ያክል በድፍረት
ይሰብካሉ። መረጃ አጥቶ የሚልፈሰፈሰውን መውሊድ እንዲህ በቅጥፈት ሊያቆሙት የውሸት ክራንች ያቀብሉታል። አሁንም ሌላ ውሸት ይሄውና!


“ጌታው አባ ረህማ የአውልያ መምህር፣
ጨዋታው ነበረ ሰይድ ከድር ጋር፣
ሁሉም ከሀድራው ይቀስም ነበር።”

ኸዲር ሙተዋል። በየት አግኝቷቸው ነው ከሳቸው ጋር የሚጫወተው?


➲ጫት እና መንዙማ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➧ጫት ህዝባችንንም አገራችንንም ወደኋላ እየጎተተ ያለ አደገኛ አደንዛዥ ቅጠል
ነው። ከሁሉ በጣም የሚያሳዝነው ይህ እርኩስ ቅጠል በአውቆ አጥፊዎች፣ እውቀት በሌላቸው ሰዎች እና ከእስልምና ሃይማኖት ውጭ ባሉ ሰዎች ውስጥ እንደ ትልቅ የኢስላም አካል ተደርጎ መወሰዱ ነው።


➭የጫትን መጥፎነት ማወቅ የፈለገ በተጨባጭ አገራችን ላይ በተለይ ሙስሊሙ ላይ ያደረሰውን ጉዳት መመልከት ይችላል።እነዚህ መንዙማ ባዮች ግን ምን ያክል ጫትን እያንቆለጳጰሱ ዲናዊ ቅብ እንደሰጡት እንመልከት።

“ጁሉሱ ሰኣቲን ጥቂት ቃቅምና
ንገረው ለመውላህ እበሩ ቁምና”
“እነሱ ይበራሉ በመቶ ሃምሳ ጀት፣
እኛ ቀደም ናቸው በአንድ ዘርባ ጫት”
“ተአስር ሺህ መትረየስ አጥምዶ ተቆመ፣
ከሺህ ፈረሰኛ ተባብሮ ለጉሞ ከቆመ፣
ይበልጣል ደግበል አድቅቆ የቃመ፣
ጠላቱንም ጎድቶ ወዳጁን ጠቀመ።”


➛ሰውየው ጫት በመቃሙ እራሱን እና ለእርሱ ጥሩ የሚያስቡትን መልካም ወዳጆቹን ይጎዳል። በተገላቢጦሹ እውነተኛ ጠላቱ የሆነውን ሸይጧን አላማ በማሳካት ሸይጧንን ይጠቅመዋል። ከዚህ ውጭ ሰው ጫትን አይደለም አድቅቆ ቢቅም ጁስ አድርጎ ቢጠጣው እንኳን እራሱን መጥቀምም ይሁን ጠላቱን መጉዳት አይችልም።

“ፍየል ቅጠል በልታ ትወልዳለች መንታ፣
መቼም እርባን የለው በጫት የተመታ”
ይልቅ እራሱ ጤናውንም፣ ገንዘቡንም፣

➧ ዲኑንም በጫት ከሚያስመታ በጊዜ
ቢማር ይሻለው ነበር። በተረፈ “ጫት ቅመን በቀልባችን ነደፍናቸው” እያሉ የሚያሰሙት ከራ ተረተረት ነው። ይልቅ እርባና የሌለው ቅጠል እያኘከ የአላህን፣ የሚስቱን፣ የልጆቹን፣ የቤተሰቦቹን እና የፍጡራንን መብት ጀዝቦ የማያሟላው ነው።

◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➧አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል
!

➭ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ ለሌሎችም ሺር ያድጉት
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

▪️የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦

➧“ሲያነጋ በእኔ ላይ አስር ጊዜ ሰላዋት ያወረደ፤ ሲያመሽም አስር ጊዜ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የቂያማ (ትንሳኤ) ቀን ምልጃዬ (ሸፈዓዬ) ታገኘዋለች።”

📚 ጦብራኒ ዘግውታል አልባኒ ተርጊብ ወተርሂብ (1/273) ላይ ሶሂህ ብለውታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ኹጥባ_አልወለደም አልተወለደም።
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
📍خطبة الجمعة
📍የጁሙዓ ኹጥባ

🌐 لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

🌐 አልወለደም፤ አልተወለደምም፡፡

🕌 ደሴ አል አዝሐር መስጂድ

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/4361
t.me/abu_reyyis_arreyyis/4361
هداية المستفيد ክፍል 01
Voice changer with effects (https://play.google.com/store/apps/…
ክፍል አንድ 0⃣1⃣

📚 የኪታቡ ስም
ሒዳየቱል ሙስተፊድ ፊአህካሚ ተጅዊይድ
📚(هدايةالمستفيد في احكام التجويد)

📝 አዘጋጅ " ሸይኽ ሙሀመድ መህሙድ አቡ ሪማ በመባል የሚታወቁት

📝تأليف، (الشيخ محمد محمود المشهور بأبي ريمة)


📕የኪታቧን PDF ለማግኘት ⤵️⤵️

https://t.me/Asselefya1/3340

🎙 አቅራቢ በወንድም አቡ ሒበቲላህ

https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫ ➭ክፍል አርባ ➛➛➛➛➛ ➲“የሂዲ ሸህ ደግሞ ጋላቢው ነብር” 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➧አብዛሀኛዎቹ የሃገራችን የአውሊያእ ጀብዱዎች ከአሉ አሉ ባለፈ ይሄ ነው የሚባል ማረጋገጫ የማይቀርብባቸው ተረቶች ናቸው። ይህን የምለው ከራማን ለመቃወም አይደለም። በአላህ፣ በዲኑ እና በመልእክተኛው ላይ የሚዋሽ አካል ገበያ ለመፍጠር ሲል ድንበር በሚያልፍባቸው አካላት…
➲መንዙማ
➻➻➻➻➻

➧ክፍል አርባ አንድ
〰〰〰〰〰〰

“ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣
የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ
”

➲ኡመተል ኢስላምን ያሽመደመደው፣ ያጀዘበው፣ የአላህንም የፍጡራንንም ሀቅ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነው ይህን አደንዛዥ ቅጠል እንዲህ እያሉ ያስተዋውቁታል። አላህ ወንድም እና እህቶቻንን ከዚህ ሱስ ያውጣልን።

“ወጣቶች ዘፈኑ በስልት እያዜሙ፣
እያሉ ይጠሩሃል ሺሊላህ ኢማሙ፣
ይመጀኑብሃል ቂምሃ እየቃሙ፣

➧ጫት ኡማው ከጌታው ወይንም ከቤተሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነት አቆርፋጅ፣ አደንዛዥ ቅጠል፣ትውልድ ገዳይ፣ ቤተሰብ በታኝ፣ አገር አበላሽ፣ ተውልድ አኮላሽ ነው፡፡ በተለይ በተለይ ሙስሊሙን ከጎዱ top 5 ከሚባሉት ነገሮች ውስጥ ዋናው ነው፡፡ እንዲህ አይነት ደፋር መንዙማ ባዮች እና የሃይማኖት አባት ነን ባዮች ሙስሊሙን በተለይ ወጣቱን ለማደንዘዝ ጫትን የእስልምና አካል አድርገው ያቀርቡታል፡፡ አላህን ይፍሩ፡፡ እስልምና ከእንዲህ አይነት አደንዛዥ እፅ የፀዳ ነው፡፡

➛ሌሎች

“ቶሎ በል ቶሎ በል፣ አንድየ ቶሎ በል፣
እንደ ዘመኑ ሰው ነገ ዛሬ አትበል”

➠ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!!ተመልከቱ የዚህ መንዙማ ባይ ድፍረትና መሃይምነት። ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ይላሉ “ማንም ሙስሊም በወንጀል እና ዝምድናን በመቁረጥ ዱዓ እስካላደረገ ድረስ አላህ ከሶስት አንዱን ይሰጠዋል። ወይ የለመነው ይደርሰዋል፣ ወይ ለአኼራ ያዘገይለታል፣ ወይም አምሳያውን በላ ያነሳለታል”። አሁንም ነብዩ صلى الله عليه وسلم በዱዓ እንዳንቻኮል ነገረውናል። አላህን እንዲህ አድርጎ ከፍጡር ጋር በማመሳሰል መግለፅ ምን የሚሉት በሽታ ነው? አላህ አደብ እና እውቀት ይስጠን።

“አጫጭሱላቸው በሁለቱ ገል (ማጨሻ)፣
አንዱም የአብዶዮ ነው፣ አንዱም የኸድር”

➠ልብ በሉ ብዙ እናቶች እና አባቶች ቡና ይፈላ ይባል እና ቁርስ ጀባ ቃሃ ጀባ
እየተባለ እጣን ይጨሳል። እጣኑም ሲጨስ እንዲህ ከአላህ ውጭ ያሉን የሚጠሩበት ሁኔታ አለ። አንድ ሰው ቤቱ ላይ ቤቱ ጥሩ ሽታ እንዲኖረው ማጨስ ይችላል። ይህን የሚያጨሰው ግን ለጥፋት በመደገስ ከሆነ ከአላህ ጋር ነው የሚያጣላው።


“ተግርዶው ነው ወይ፣ ወይንስ ከቡኑ፣
ነው ወይንስ ከጫቱ፣ ወይስ ከጉዝ ጓዙ፣
ወይስ ከመጀን፣ ነው ወይንስ ከመጀን፣
ሌላውን በጮማ እኛን በጎመን፣ ወይንስ ከመጀን፣ ወይንስ ከወንድም፣ ወይንስ ከእህት፣
ሌላውን በጮማ እኛን በጎመን”


“እያረግክላቸው እያየሁህ (ኝ) ባይኔ፣
የበደል መሰለኝ አረ ምነው እኔ”
“ሲበሉ አልበላሁም፣ ሲለብሱ አለበስኩም፣
ሲያጌጡ አላጌጥኩም፣ ሲያገቡ አላገባሁ፣
ሲሰሩ አልሰራሁኝ፣ ሁል ጊዜ ሁል ጊዜ ሃያቴን ፈጀሁት።”

➧ሰይጣን ምን እንዳለ አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል

ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ

“(ሰይጣንም) “ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ። አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ሆነው አታገኛቸውም”
(አለ)።”
[አልአዕራፍ፡ 17]


وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ

“ጌታችሁም “ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና” በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ
)።” [ኢብራሂም፡ 7]
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➧አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!

➭ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ ለሌሎችም ሺር ያድጉት
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
◾️ሸህ ሷሊህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

✅ አንድ ሙስሊም ከሌሊት ሶላት ቁጥሩ ቢያንስም እንኳን ሁሌም የሚዘወትርበት የሆነ ድርሻ ሊኖረው ይገባል።

📚الملخص الفقهي(صـ ٩٣)
▪️ታላቁ አሊም ሼይኽ ዑሰይሚን ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦

➲እያንዳነዷ ሴት ያለ ዕውቀት ሷሊህ የሚባለው ደረጃ ላይ መድረስ እንደማትችል ልታውቅ ይገባል፣ ዕውቀት ስል ሸሪዓዊ ዕውቀትን ለማለት ፈልጌ ነው።

📝ደውሩ አልመረኣህ 7
Audio
የማለዳ የቁርዐን ግብዣየ

መሳጭ ቲላዋ
ያዳምጡ ይወዱታል


እናንተ የቁርዓን ህዝቦች ሆይ ‼️
🔻ቁርዐንን ማዳመጥ
🔻 ማንበብ አትሰላቹ
ዘወትር ልባችን ከቁርዐን ጋር ይሁን ❗️
አላህ ያግራልን ⁉️

ማን ይፈልጋል ቁርዐን ማዳመጥ

እስቲ እንያቹ ቤተስብ ሁኑ ⁉️
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

✅ አላህ እጅ እንዳለውና በዚህ ላይ የአህባሾች ማምታቻ

➰ክፍል ④③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➳ክፍል ስምንት ➲አራተኛው፡ - ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው ወደአላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች የትንሳኤ ቀን ባሪያው በአላህ ውዴታ የሚጎናጸፍበት በጀነት ድልብ ሀብት ሆኖ እንደሚቆየው የሸሪዓ መረጃዎች ሁሉ ይጠቁማሉ፡፡ ➧በቁርኣን ፣ ተግባር በኢማን ስም ከመግባቱ በተጨማሪ ኢማን እናተግባርን በማጣመር የሚገኘውን ምንዳ ፣ የሁኔታቸውን…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ዘጠኝ
〰〰〰〰〰

✅አምስተኛው፡ - ሰለፎቹ ባወቁት ለመስራት ተሸቀዳዳሚ ነበሩ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ይህን ደረጃ ከሚያብራሩ ነጥቦች መካከል፡ የሰለፎች አስደናቂ ባህሪያቸው ነው፡፡ሰለፎቹ ተግባርን በቋሚነት ለመፈጸም ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ ከረሡል صلى الله عليه وسلم የሰሙትን ፈጥነው ለመተግባር ይቸኩሉ ነበር፡፡

➭በዚህ ትርጉም ላይ ሰለፎቹ ምን ያክል ባወቁት ለመተግበር ፍላጎቱ እንደነበራቸው ብርቱ ትኩረት እንደሚሰጡ የሚገልጹ በርካታ መረጃዎች መጠዋል፡፡ከዚህ መካከል ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ተዘግቦ የሚገኘው ሐዲስ ነው፡፡ የረሡል صلى الله عليه وسلم ልጅ ፋጢማ ረድየላህ አንሃ አገልጋይ ፈልጋ ለአላህ መልእከተኛ ጥያቄ አቀረበች፡፡

▪️የአላህ መልክተኛም صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጧት፡- “ለአንች ከአገልጋይ የተሻለውን ልጠቁምሽ?” አሏት፡፡ (ለመተኛት) ወደፍራሽ በተጠጋሽ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሃን አሏህ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ፤ አሏሁ አክበር ሰላሳ ሶስት ጊዜ በይ” አሏት፡፡ ባለቤቷ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"فما تركتها منذ سمعتها من رسول الله صلى الله عليه وسلم"

“ከረሡል ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቸው አላውቅም” ከመካከላቸው አንዱ “አስቸጋሪ ሌሊት ላይ እንኳ ቢሆን? - ማለትም ሰው በሚዘነጋበት ሰኣት ላይ እንኳ ቢሆን? - ይህን ዚክር ረስቶት አያውቅም?” ፤ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን?!” - ይህ ሌሊት የታወቀ ጦርነት ነው - የሚል ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን” በማለት ምላሽ ሰጧል፡
፡ ቡኻሪ፡ 5362 ሙስሊም፡2727

➧ዓንበሳህ ብን አቢ ሱፍያን -ረሂመሁሏህ- በሞተበት በሽታ ላይ ሆኖ ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰማሁ ብላ የሚከተለውን ሐዲስ ነገረችኝ ብሎ ለእኔ አስተላልፎልኛል ይላል ዓምር ብን አውስ፡፡

"من صلى اثنتيني عشرة ركعة في يوم وليلة بني له بهن بيت في الجنة"

▪️“አስራ ሁለት ረከዓዎችን በሌሊትና በቀን የሰገደ ሰው በእነርሱ አማካኝነት በጀነት ቤት ይገነባለታል፡፡” ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ የሚከተለውን ተናግራለች ፡-
"فما تركتهن منذ سمعتهن من رسول الله"

➧“ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማሁ ጀምሬ (እነዚህን አስራ ሁለት ረከዓዎች) ትቻቸው አላውቅም” አንበሳህ ደግሞ በተመሳሳይ “ከኡሙ ሀቢባ ከሰማሁ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም”ይላል፡፡ ዓምር ብን አውስ ደግሞ “ከአንበሳህ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ኑዕማን ብን ሳሊም ደግሞ “ከዓምር ብን አውስ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል
፡፡ ሙስሊም፡728

➠ይህ ፍጥነትን እና በቋሚነት መፈጸምን ያጣመረ ታላቅ ወኔ ነው፡፡ ለስራ መፍጠን ፣ቋሚ ደምበኛ ለመሆን መሽቀዳደም፡፡

▪️ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ አቡሁረይራ ረዲየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"أوصاني خليلي بثلاث لا أدعهن حتى أموت: صوم ثلاث أيام من كل شهر ، وصالة الضحى ، ونوم على وتر"

➲“ወዳጀ እስከምሞት ድረስ የማልተዋቸው በሆኑ ሶስት ነገሮች አደራ አለኝ፡፡ ከየወሩ ሶስትቀናቶችን (እንድጾም) ፣ የዱሃ ሶላት (እንድሰግድ) ፤ ዊትር ሰግጀ እንድተኛ” ቡኻሪ፡1178
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w