💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የኢማን ትርጉም
☑️ አርካኑል ኢማን

➰ክፍል ⑨➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ዘጠኝ ➽ትክክለኛ የቁርኣን ንባብ በሶስት ነገሮች ካልሆነ ሊሟላ አይችልም ➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬ ⓵ቁርኣንን ባማረ ሁኔታ በማንበብ እና በቻለው አቅም በቃሉ በመሸምደድ ⓶ መልዕክቱን በመገንዘብና በመረዳት كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ…
➽የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል አስር

➲ቁርኣንን በፍጥነት አንብቦ ከመጨረስ ነፍስህን በእርሷ የምትፈውስበት ፣ አስተንትነህ ትርጉሟን በደንብ ተገንዝበህ የምታነባት አንዲት አንቀጽ በላጭና በጣም ጠቃሚ ናት፡፡ለዚህ ነው ሰለፎቹ ወይም ቀደምት ደጋጎች በአንዲት አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን የሚያነጉት፡፡

ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው አንድ አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን አንግተዋል፡

إِن تُعَذِّبْهُمْ فَإِنَّهُمْ عِبَادُكَ ۖ وَإِن تَغْفِرْ لَهُمْ فَإِنَّكَ أَنتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

“ብትቀጣቸው እነርሱ ባሮችህ ናቸው፡፡ ለነርሱ ብትምርም አንተ አሸናፊው
ጥበበኛው ነህ” (ይላል)
አል ማኢዳህ፡118” አህመድ፡ 21328 አን ነሳኢይ፡1010 ኢብኑ ማጀህ፡1350

➢በትክክለኛ ሐዲስ አቡ ሰዒድ አል'ኹድርይ ረድየሏህ አንሁ የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡-አንድ ሶሃባ አንድን ግለሰብ “ቁልሁወሏሁ አሀድን” ደጋግሞ ሲቀራ አደመጠው፡፡ነገሩን እንደቀላል በመመልከት ከነጋ በኋላ ወደረሡል صلى الله عليه وسلم መጣና ነገራቸው፡፡ የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم ግን የሚከተለውን ተናገሩ፡-

"والذي نفسي بيده إنها لتعدل ثلث القرآن"
➧“ነፍሴ በእጁ በሆነው ጌታ እምላለሁ፡፡ እንሆ እርሷ የቁርኣንን አንድ ሶስተኛ
ትመዝናለች
፡፡” ቡኻሪ፡5013

➢ቁርኣንን ያለምንም መገንዘብና ማስተንተን እንዲሁ በስድ ከምታነብ ፣ አንዲትን አንቀጽ በደንብ እያስተነተንክ እና እያስተዋልክ ካነበብክ ነፍስህን እየፈወስክ ፣የልብህን በሽታ እያከምክ ፣ እምነትህን እና ተወኩልህን እያጠናከርክ ፣ ከአላህ ጋር ያለውን እውነተኛነትህንና የጠበቀ ግንኙነትህን በማደስ ከእርሷ ጋር ብቻህን በደስታ ማሳለፍህ የተሻለና በላጭ ነው፡፡

⓷ኛው በተከበረው ቁርኣን መስራት
ሀሰን አል'በስርይ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"أنزل القرآن ليعمل به ، ..."

➧“ቁርኣን የወረደው በእርሱ ሊሰሩበት ነው፤ …” ሚፍታሁ ዳሪ አስ ሳዓዳህ፡1/187

➠ቁርኣን የወረደው ልንሰራበት ፣ ከቁርኣን ባለቤቶች እንድንሆን ነው፡፡ አንድ ሰው
ሀርፉን ፣ አንቀጾችን ፣ ምዕራፎችን በማንበብና በመሀፈዝ ብቻ የቁርኣን ባለቤት ሊሆን አይችልም፡፡ ይልቁንም ትርጉሙን በመረዳትና በመገንዘብ በታላቁ ቁርኣን መስራት ይኖርበታ
ል፡፡

➭ከሶሃቦች ዘመን ቀጥሎ ከሚገኙት ታላላቅ ታብዒዮች መካከል አንዱ የሆኑት ኢማም ሀሰን አል'በስርይ - ረሂመሁሏህ - የዘመኑ ቁራኦችን (ቁርኣን አንባቢዎች) አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፡፡

➤“አንድ ሰው አንድንም ሐርፍ ሳልጥል ቁርኣንን አንብቤ አጠናቀቅሁ ይላል፡፡ይህን ሲናገር የእርሱ አላማ ሒፍዙንም ተጅዊዱንም አጥርቸና አረጋግጨ አነበብኩት ለማለት ፈልጎ ነው፡፡ ነገር ግን በአላህ ምዬ የምናገረው ሁሉንም ጥሎታል፡፡

ቁርኣን ላይ ያሉ ስነ-ምግባሮችና ተግባሮች ከእርሱ ላይ አይታዩም፡፡ አንዳንዶች በአንድ ትንፋሽ የቁርኣንን ምእራፎች አጠናቅቄ አነበብሁ ይላሉ፡፡ ወሏሂ እነዚህ ቁራኦች አይደሉም የቁርኣንን ህግ በተግባር የሚያውሉም ጥበበኞችም ፣ አላህን ፈሪዎችም አይደሉም፡፡ መቸ ነው እንደነዚህ አይነተ ሰዎች ቁራእ የሆኑት? እንደነዚህ አይነት ሰዎችን አላህ በሰዎች መካከል ቁጥራቸውን አያብዛው!” አዝ ዙህድ ሊብን አል ሙባረክ 793

➤ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የላኢላ ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ ክፍል⓸ ⓻ኛዉ መስፈርትመዉደድ፦ ሌላኛዉ መስፈርት ደግሞ ላኢላ ሃኢለሏህን ፣መልዕክቷን እንድሁም እሷን የተሸከሙ ሰዎችን መዉደድ ነዉ። ➠ላኢላ ሃኢለሏህ የሚል ሰዉ ከምንም በላይ አሏህን ይወዳል። ➠ከሰዎችም ከአሏህ ሌላ ባላጣዎችን የሚይዝ አለ።ልክ አሏህን እንደሚወዱት ይወዷቸዋል። እነዚያ ያመኑት…
➲የላኢላ_ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ⓹

➠7ኛው መስፈርት መዉደድ ከትላቱ የቀጠለ፦

ስለዚህ መስፈርቶች ስናወራ ዋናዉ የሚፈለገዉ ነገር በተጨባጭ መልዕክታቸዉን ማስገኛት እንጂ እንዲሁ በጭንቅላት ሸምዲዶ በምላስ መዘርዘሩ አይደለም። ስንት መስፈርቶቿን መቁጠር ሳይችል ላኢላ ሀኢለሏህን በሚገባ የሚያስገኝ አለ?!

➧ስንት በምላሱ እየዘረዘረ መሠረታዊ ነጥቦቿን የሚያጓዲል አለ?!


➠በጥቅሉ ከነዚህ መስፈርቶች የምንረዳዉ ከአስፈላጊ መስፈርቶች የተራቆተ ባዶ ላኢላ ሃኢለሏህ ዋጋ የሌለዉ መሆኑ ነዉ።

➧ታላቁ አሊም ኢብኑ_ ረጀብ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ ''በምላሱ ላኢላ ሃኢለሏህ እያለ ከዚያም አላህን በማመፀና ሸይጧንንና ስሜቱን የሚከተለዉማ በርግጥም ተግባሩ ንግግሩን አስተባብሎታል። ሸይጧንና ስሜቱን በመታዘዝ አሏህን ባመፀዉ ልክ የተዉሒዱን ሙላት አጓዲሎታል ። (ከአላህም የሆነ መመሪያ ሳይኖረዉ ስሜቱን ከተከተለ ሰዉ ይበልጥ የጠመመዉ ማነዉ?!)/ከሊመቱል ኢኽላስ፡28/

➧ሰዎች ለነዚህ መስፈርቶች ከሚኖራቸዉ አያያዝ አንፃር የተዉሒድ ጥንካሬቸዉ ይለያያል።

➩ኢብኑል ቀይም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦ ስለሆነም በተጨባጭ በሆነ መልኩ ከአሏህ በስተቀር እዉነተኛ አምላክ እንዴሌለ የመሠከረን አሏህ በእሳት ላይ እርም አድርጎታል። የዚችን ምስክርነት እዉነታ በሚገባ ያረጋገጠና በተግባር ያስገኛ ሰዉ እሳት ይገባል ማለት ዘበት ነዉ። የላቀዉ አላህም(እነዚያ በምስክርነታቸዉ የፀኑ ናቸዉ)ይላል።እናም ምስክርነት በይፍም፣በስዉርም፣ በልቡ በዉጩም የፀና ይሆናል ማለት ነዉ። ምክንያቱም ከሰዎች ዉስጥ ምስክርነቱ ሸሃዳዉ የሞተ የሆ አለ። ከነሱ ዉስጥ ደግሞ ምስክርነቱ የተኛ አለ_ሲቀሰቀስ የሚነቃ። ከዉስጣቸዉም የተጋደመ አለ። ከዉስጣቸዉም ለመቆም የቀረበ አለ።

➧ባጭሩ የላኢላ ሃኢለሏህ ምስክርነት ከቀልብ ዉስጥ፣ልክሩህ ከአካል ዉስጥ እዳላት ሁኔታነዉ። የሞተ ሩህ አለ።የታመመሩህ አለ። ወደ ሞት የቀረበ አለ። ወደ ህይወት የቀረበ አለ። ሌላ ደግሞ ለአካል ጥቅምና ደህንነት የሚተጋ ሩህ አለ።(አድዳኡ_ወድደዋእ፡302)

➧ከዚህ በመነሳት ህዝባችን በተጨባጭ ያለበት እዉነታ ስንቃኝ የሚታየዉ ነገር አሰፈሪ ነዉ።

➤ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉◉✍

✅ተዉሒዲ የሁለት ሃገር ስኬት ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ መፀሃፍ የተወሰዴ

✍️أم عثيمين
➢ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ወሳኝ ጥንቃቄ ለዲን ተማሪዎች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

✅ የምትማርበትን ኡስታዝ፦
☑️ አቂዳውንና
☑️ መንሀጁን ጠንቅቀህ እወቅ


➡️ ይህ እውቀት ስጋህ፣ ደምህና ህይወትህ ነውና ከማን እንደምትወስደው በትኩረት አጢን

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ስድስት ➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ወደ ምን አይነት ሰዎች ነበር የተላኩት? 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➲ሁሉም ነብይ ወደ የህዝቡ ሲላክ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ግን ባጠቃላይ ለአለማት እዝነት ተደርገው ነው የተላኩት።ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ህዝቦች እንደተላኩ ማወቃችን ወሳኝ ነጥብ ነው። ምክንያቱም…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫
እውነታው:አደጋዎቹና መዘዞቹ

➧ክፍል ሰባት


➠ልብ በሉ የአላህ ባሪያዎች እነዚህ አጋሪያን የአላህን ጌትነት ማመናቸው ወደ ነብያት ሁሉ ሀይማኖት ኢስላም አላስገባቸውም። ይህም የሆነው አምልኮን በጠቅላላ ለአንድ አላህ ብቻ ስላልፈጸሙ እና አላህንም ከእርሱ ውጭ ያሉትንም ያመልኩ ስለ ነበር ነው።

«ከአጋሪያን ተግባር ውስጥ የሚጠቃለለው ለእርሱ ብቻ የሚገባውን አምልኮ በእርሱ ላይ ሌላን ምንንም ማድረግ የማይችሉ፣ የማይጠቅሙ፣ የማይጎዱ፣ ጥቅምን ለራሳቸው ማምጣት የማይችሉ፣ እራሳቸውን ከጉዳት መከላከል የማይችሉትን ፍጡራን መገዛታቸው ነው። ለዚህም ማስረጃው የሚከተለው አንቀጽ ነው።

وَمَا يُؤْمِنُ أَكْثَرُهُم بِاللَّهِ إِلَّا وَهُم مُّشْرِكُونَ

➧አብዛኞቻቸውም፤ እነሱ (በአምልኮ የተውሒድ ክፍል) አጋሪዎች ሆነው እንጂ በአላህ ጌትነት አያምኑም።” [ዩሱፍ፡ 106]

የዚህ አንቀጽ ትንታኔ እንደሚያሳየው አብዛኛዎቹ አጋሪዎች የአላህን ጌትነት፣ ፈጣሪነት፣ ሲሳይን ለጋሽነት እና አስተናባሪነት ያጸድቁ እንደነበር ነው።

➲ግና አላህን በጌትነቱ እንደነጠሉት በአምላክነቱ አልነጠሉትም። ለብቸኛው ፈጣሪ የሚገባውን አምልኮ ከእርሱ ውጭ ለሆኑ ፉጡራን በማካፈል ነበር አምልኮ የሚፈጽሙት። የአላህን ጌትነት አምነው ተቀብለው በአምላክነቱ ላይ በማጋራታቸው ደግሞ “አማኝ” አላስባላቸውም።

«ለዚህች አንቀጽ ቁርኣን ተርጓሚ የሆኑትን ሶሐባዎች እና ታቢዒዮች የሰጡትን ትርጉም እንመልከት፡-

ኢብን ዐባስ (ረድየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ይላሉ፡- “ከኢማናቸው ውስጥ ሰማይን ማን ፈጠረው? ምድርን ማን ፈጠረው? ተራራን ማን ፈጠረው? (ተብለው) ከተጠየቁ አላህ ብለው ይመልሳሉ፣ እነሱ ግን አጋሪ ናቸው።

➲ኢክሪማ ደግሞ እንዲህ አሉ፡ “ማን ፈጠራችሁ፣ ሰማያትና ምድርን ማን ፈጠረ ብለህ ትጠይቃቸዋለህ? የእነሱም መልስ አላህ ይሆናል። ይህም ነው በአላህ ላይ ያላቸው እምነት። ከእርሱ (ከአላህ) ውጭ ግን ያመልካሉ።

➧ሙጃሂድ ደግሞ እንዲህ ይላሉ፡- “እምነታቸው አላህ ፈጠረን፣ ሲሳይ ይለግሰናል፣ ይገድለናል ብለው መናገራቸው ነው። ይህ ነው እምነታቸው ከእርሱ ውጭ እያመለኩ.....”

➲ዐብዱረሕማን ኢብን ዘይድ ኢብን አስለም ደግሞ “በአላህ ላይ አንድም የሚያጋራ የለም አላህ ጌታው፣ አላህ ፈጣሪው እና ሲሳይ ሰጪው መሆኑን እያወቀ እና እያመነ ቢሆን እንጂ።
◉
◉

◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📘ዝግጅት መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ።

✏️መጻፍ ካልቻልክ አንብብብ!!ማንበብ የተሻለ ሰው ያድርጋል።


ጆ ይ ን በ ማ ለ ት ተ ጠ ቃ ሚ ይ ሁኑ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

‏ ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ
‏ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝


قال النبي ﷺ :

" أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشراً ".

قال المحدث الألباني : حسن
📕السلسلة الصحيحة
1407

اللَّهُمَّ صَـــلِّ وَسَلِّــمْ وبارک عَلَـــى نَبِيـِّنَا محمد

اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ በሩሱሎች ማመን
☑️ በአላህ ውሳኔ ማመን
☑️ በመጨረሻው ቀን ማመን

➰ክፍል ⓾➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ እውነታው:አደጋዎቹና መዘዞቹ ➧ክፍል ሰባት ➠ልብ በሉ የአላህ ባሪያዎች እነዚህ አጋሪያን የአላህን ጌትነት ማመናቸው ወደ ነብያት ሁሉ ሀይማኖት ኢስላም አላስገባቸውም። ይህም የሆነው አምልኮን በጠቅላላ ለአንድ አላህ ብቻ ስላልፈጸሙ እና አላህንም ከእርሱ ውጭ ያሉትንም ያመልኩ ስለ ነበር ነው። «ከአጋሪያን ተግባር ውስጥ የሚጠቃለለው ለእርሱ ብቻ የሚገባውን አምልኮ በእርሱ ላይ ሌላን…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➳ ክፍል ስምንት

➲ዐብዱረሕማን ኢብን ዘይድ ኢብን አስለም ደግሞ “በአላህ ላይ አንድም የሚያጋራ የለም አላህ ጌታው፣ አላህ ፈጣሪው እና ሲሳይ ሰጪው መሆኑን እያወቀ እና እያመነ ቢሆን እንጂ። ኢብራሂም ምን እንዳሉ አታይምን

وَاجْعَلْنِي مِن وَرَثَةِ جَنَّةِ النَّعِيمِ◆وَاغْفِرْ لِأَبِي إِنَّهُ كَانَ مِنَ الضَّالِّينَ◆وَلَا تُخْزِنِي يَوْمَ يُبْعَثُونَ
➧ ትገዙት የነበራችሁትን አስተዋላችሁን? እናንተም የቀድሞዎቹ አባቶቻችሁም (የተግገዛችሁትን)። እነሱም (ጣዖቶቹ) ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር (እርሱ ወዳጄ ነው)። (እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው። እርሱም ይመራኛል።” [አሽሹዐራእ፡
75-77]

➧እንግዲህ ኢብራሂም ዳዕዋ ያደረጉላቸው ሰዎች አላህን እና ከእርሱ ውጭ ያሉትን ያመልኩ ነበር። ኢብራሂም “እነሱም (ጣዖቶቹ) ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማትጌታ ሲቀር (እርሱ ወዳጄ ነው)” አሉ።

➠ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (የተላኩባቸው ህዝቦች ነብዩ ዒሳን (ዐለይሂ-ስሰላም)፣እናታቸው መርየምን፣ ዑዘይርን፣ ላትን፣ ኡዛን፣ መናትን፣ ሺዕራን
፣ ፀሀይ እና ጨረቃን፣መላእክትን፣ ጂኖችን፣ ዛፎችን፣ ወዘተ በመጣራት በአላህ ላይ ያጋሩ ነበር፡


➳ላት የተባለው ይህ ግለሰብ ለሀጅ የሚመጡ ሰዎችን በሶ በማበስበስ ይመግብ እንደነበር ይነገርለታል፡፡

➳ሹዕራን የተባለው ከብዙ ኮከቦች አንዷ ሺዕራ ብለው ለይተው የሚያመልኳት ነበረች፡፡ አላህም እሷን እንዳያመልኩ እና
የሷ ጌታ መሆኑን እንዲህ ሲል ጠቆማቸው


وَأَنَّهُ هُوَ رَبُّ الشِّعْرَىٰ النجم: ٤٩

“እነሆ እርሱም የሺዕራ ጌታ ነው፡፡” አል ነጅም 49

➧ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ከአላህ ውጭ የሚመለኩትን በጠቅላላ አንዱን ከአንዱ ሳይለዩ መቃወማቸው እና አምልኮን ለብቸኛው አላህ ብቻ ይሁን ማለታቸው የሺርክን አስከፊነት እና ከባድነት የሚያሳይ ነው።

➠ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ ያየ ከአላህ ውጭ ያለን ማንንም ይሁን ማን ማምለክ ሺርክ እንደሆነ ይገነዘባል። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ሁሉንም ከአላህ ውጭ የሚፈጸም አምልኮ መቃወማቸው ፀሀይ እና ጨረቃን በሚያመልከው ሰው እና ዒሳን በሚያመልከው ሰው መሃል ልዩነት እንደሌለ እና ሁለቱም አጋሪያን እንደሆኑ ያስገነዝበናል። ይሄ ሺርክ ማለት ምን እንደሆነ ሰፋ ባለ ሁኔታ እንድንረዳ ያደርገናል።

➧አንድ ሙስሊም ነበዩላህ ኢሳ ዐለይሂ-ስሰላም አይመለኩ ሲል እኝህን ውድ የአላህ ነብይ ጠልቶ አይደለም። ነገር ግን የብቸኛው ፈጣሪ፣ የአንድ አምላክ አላህ ብቸኛ መብት፣ ከፍጡራን ለማንም ሊሰጥ ስለማይገባ ነው። ልክ እንደዚሁ በአላህ ላይ ማንም ከተጋራበት ትክክለኛ አምልኮ ተብሎም አይጠራም። የሚመለከው እንጨት፣ ፀሀይ፣ ጨረቃ፣ ጂን፣ ሙት፣ በህይወት ያለ፣ አላህ ዘንድ እንደ መልአክ እና ነብይ ታላቅ ቦታ ያለው ቢሆንም ጉዳዩን ከሺርክነት አያወጣውም። አምልኮ የአንድ አላህ ሐቅ ነውና።
ይህንንም አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል፡-

وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا الجن: ١٨

“እነሆ መስጊዶችም የአላህብቻ ናቸው። (በውስጣቸው) ከአላህ ጋር አንድንም አትገዙ።” አልጂን፡ 18]
◉

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ሀሳቡ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
الوقوع_فريسة_للآخرين_من_أسباب
<unknown>
ينبغي على الزوجين أن يملئ البيت بالعاطفة والمحبة

#مقطع صوتي
للشيخ سليمان الرحيلي وفقه الله


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➽የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አስር ➲ቁርኣንን በፍጥነት አንብቦ ከመጨረስ ነፍስህን በእርሷ የምትፈውስበት ፣ አስተንትነህ ትርጉሟን በደንብ ተገንዝበህ የምታነባት አንዲት አንቀጽ በላጭና በጣም ጠቃሚ ናት፡፡ለዚህ ነው ሰለፎቹ ወይም ቀደምት ደጋጎች በአንዲት አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን የሚያነጉት፡፡ ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሚከተለው አንድ አንቀጽ ቆመው ሌሊቱን…
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➳ክፍል ⓫

➤አንተ ቁርኣንን ታነባለህ ነገር ግን በትዕዛዞች፣በክልከላዎች በማስጠንቀቂያዎች፣ በተግሳጾች እና ማስታወሻዎች እንዲሁ ዝም ብለህ ታልፋለህ፡፡ ታዲያ ከቁርኣን ለአንተ ያለህ ድርሻ ወይም እጣ ምን ይሆን?
ኢብን መስዑድ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"إذا سمعت الله يقول: "يأيها الذين ءامنوا" فأرعها سمعك ، فإنه إما خير يأمر به أو شر ينهى عنه"

➧አላህ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ!” በማለት ሲጣራ ከሰማህ ጀሮህን ሰጠህ በደንብ አድምጥ፡፡ አንድም መልካም ሊያዝህ ነው ወይም መጥፎ ከሆነው ነገር ሊከለክልህ ነው፡፡” ተፍሲር ኢብኑ አቢ ሓቲም፡1/196

➭ነገር ግን ልክ ንግግሩ ለሌላ ሰው እንደሆነ ጀሮህን ሰጠህ የማታዳምጥ ወይም ነገሩ እንደማይመለከትህ ዝም ብለህ የምታልፍ ከሆነ ከቁርኣን እንዴት ልትጠቀም ትችላለህ? የቁርኣን አሻራ በአንተ ላይ እንዴት ሊያርፍ ይችላል?
ስለዚህ አንድ ሙስሊም ነፍሱን ሊታገል ፣ የተከበረውን ቁርኣን ለመቅራት ከላይ
የተጠቀሱትን ሶስት መስፈርቶች ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል፡፡

➧እነዚህን ሶስት መስፈርቶች በቀላሉ እንዲገነዘብ አላህ ቁርኣንን ገርና ቀላል
አድርጎታል፡፡


وَلَقَدْ يَسَّرْنَا الْقُرْآنَ لِلذِّكْرِ فَهَلْ مِن مُّدَّكِرٍ

ቁርኣንንም ለመገንዘብ በእርግጥ አገራነው፡፡ ተገንዛቢም አልለን? አል ቀመር 17

➲ኢብን አል'ቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"يسره للذكر ، ويسر ألفاظه للحفظ ، ومعانيه للفهم ، وأوامره ونواهيه للامتثال"

➽“ቁርኣንን ለማስታወስ ገር አደረገው ፣ በቃል ለመሸምደድ ቃላቶችን ገር አደረጋቸው፣ ትርጉማቸውን ለመገንዘብ ገር አደረገው ፤ ለመተግበር ያመች ዘንድ ትዕዛዝን እና ክልከላን ገር አደረጋቸው፡፡”
ሙኽተሶሩ ሰዋዒቅ አል ሙርሰላ፡ ገፅ 40

➠ይህ ቁርኣን ለደረቶች ፈውስ እንደሆነ በሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ግልጽ አደረገ፡፡

وَنُنَزِّلُ مِنَ الْقُرْآنِ مَا هُوَ شِفَاءٌ وَرَحْمَةٌ لِّلْمُؤْمِنِينَ ۙ وَلَا يَزِيدُ الظَّالِمِينَ إِلَّا خَسَارًا

ከቁርኣንም ለምእመናን መድኀኒትና እዝነት የኾነን እናወርዳለን፡፡ በዳዮችንም ከሳራን እንጂ ሌላ አይጨምርላቸውም፡፡
አል ኢስራዕ 82


هُوَ لِلَّذِينَ آمَنُوا هُدًى وَشِفَاءٌ ۖ
“እርሱ (ቁርኣን) ለእነዚያ ለአመኑት መምሪያና መፈወሻ ነው፡፡” ፉሲለት፡44

وَشِفَاءٌ لِّمَا فِي الصُّدُورِ وَهُدًى

“(ቁርኣን) በደረቶች ውስጥ ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድሓኒት (ሲሆን በእርግጥ መጣላችሁ)” ዩኑስ፡57

➧ቀታዳህ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"إن القرآن يدلكم على دائكم ودوائكم ، أما داؤكم فذنوبكم ، وأما دواؤكم فالاستغفار"

➤“ቁርኣን በሽታችሁንም መድሓኒታችሁንም ይጠቁማል፡፡ በሽታችሁ ወንጀሎቻችሁ ናቸው፡፡ መድሓኒታችሁ ደግሞ ኢስቲግፋት (አላህን ይቅርታ መጠየቅ) ነው፡፡” በይሓቂይ ሹዓብ አል ኢማን፡ አስበሃኒ አት ተርጊብ ወት ተርሂብ 221

➢ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1