💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
➡️ ጥያቄዎቻችንን አይመልስልንም ብላችሁ ስሞታ ለምታቀርቡብኝ ወንድም እህቶች

🔘ሀቂቃ የምትጠይቁኝን ጥያቄዎች ሁሉ የምመልስበት አቅምና እውቀት ቢኖረኝ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ጠዋትም ማታ ብመልስላችሁ ደስታዬን አልችለውም ነበር። ግን ያን የማድረግ አቅሙም እውቀቱም የለኝም። እንደናንተው ገና ጅምር ላይ አሉ ከሚባሉ ተማሪዎች ውስጥ አንዱ ነኝ። የቢድአና የጥመት ባለቤቶች ሀቅን ለመቅበር፣ ማህበረሰባችንን በሽርክና በቢድአ ለማጨቃየት ከሚለፋት አንፃር በአቅሜ በምችለው ብንቀሳቀስና ለጥቂቶች እንኳን ቢሆን የኸይር ሰበብ ብሆን ብዬ እንጂ ሌላ የተለየ ነገር ኖሮኝ አይደለም። ይህ ስል እራሴን ለማተናነስና ዝቅ ብሎ መታየትን ፈልጌ እንዳልሆነ በደምብ በደምብ እወቁልኝ። አቅሜን ስለማውቀውና የሚያውቁኝ ሰዎች በደምብ ስለሚረዱኝ ነው። ይህ ማለት ግን የማውቀውን ከሱና ኡለማዎች በትክክል የተረዳሁትን ከዚህ በተሻለ መልኩ አጠናክሬ አቀርባለሁ ኢንሻአላህ። ይህ ነው እውነታው።

ግን እወቁ ቻናል የከፈተ ሁሉ፣ ብዙ ተከታይ ያለው ሁሉ፣ ያወቀውን የሚያሳውቅ ሁሉ ኣሊም ወይም ፈትዋ ሰጪ አድርጋችሁ አታስቡ። በከበደንና በጠናን ጉዳይ እንድንጠይቅ የታዘዝነው (أهل الذكر) ተብለው የተጠሩት የእውቀት ባለቤቶችን ነው። በዚሁ ላይ ለሰለፍይ ወንድም እህቶች የማሳስበው ፈትዋ ስትጠይቁ ሁለት ነጥቦችን በደምብ እንድታስታውሱ ነው።
①) ፈትዋ የምትጠይቁት አካል የእውቀት ባለቤት መሆኑን፣ በአቂዳውና በመንሀጁ የተስተካከለ መሆኑን አረጋግጡ። ሲጨንቃችሁ ላገኛችሁት ሁሉ እየጠየቃችሁ የጠሞ አጥማሚ ትክክል ያልሆነ ፈትዋ ተቀብላችሁ በመያዝ ገደል እንዳትገቡ።

②) ፈትዋ ስትጠይቁ ይቻላል ወይም አይቻልም ስትባሉ መረጃው በቁርአን በሀዲስ የተደገፈና መሆኑን አረጋግጡ። ሌላው ቢቀር ለዚህ ፈትዋ መረጃው ምንድ ነው ብላችሁ ጠይቁ። አንዳንዱ በመሰለኝ ከኪሱ በመምዘዝ ፈትዋ የሚሰጥ አይጠፋምና ጥንቃቄ አድርጉ። ስለዚህ ሁለት ነገር ላይ ትኩረት ይደረግ
👁‍🗨ፈትዋ ስትጠይቁ ለእውቀት ባለቤት ጠይቁ
👁‍🗨ለተሰጣችሁ ፈትዋ መረጃው ምንድ ነው በማለት አረጋግጡ።
Audio
የአላህ ባህሪዎችን በተመለከተ የኢማሞ አትቲርሚዚ እና የሌሎች አኢማዎች አቌም ...

https://t.me/Muhammedsirage
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ እውነታው፣ አደጋዎችና መዘዞቹ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል አራት ➧በሌላ ጎኑ ድል ለአሏህ፣ ለመልክተኛው እና ለአማኛች ነውና አሏህ ለነብዩሏህ ኑሕን (አለይሂ_ሰላም) በጣም ጥቂት ከሆኑ ተከታዮቻቸው ጋር ከእንስሳት ጥንድ ጥንድ በመሆን እዛች መርከብ ላይ ተጭነው በዚህ ምድራዊ ህይወት ከመስመጥ ተጠበቁ። በአላህ ፍቃድ የሚቀጥለው አለም ላይ ካለው አሳማሚ ቅጣት ተጠብቀው…
➲መንዙማ
➬➬➬➬➬

➢ክፍል አምስት

➧ልብ በሉ በዚህ ግዜ አማልክት ተብለውም አልተጠሩም። ሸይጧን ግቡን
ለማሳካት ሩቅ ነው የሚያልመው።ከዚያም ይህ ትውልድ አልፎ ሌላ ትውልድ ሲተካና፣እውቀትም ሲጠፋ “አባቶቻችሁ ዝናብ ሲቸግራቸው እነሱን ነበር የሚጠይቁት” ብሎ ታላቁ ወጥመዱ ውስጥ ከተታቸው። ከዚያም ተቀበሉት። በዚህም ምክንያት አላህ ለምድር ህዝቦች የመጀመርያውን መልክተኛ ኑሕን (ዐለይሂ-ስሰላም) ላከ።


➲ታላቁ መልክተኛ ኑሕ በቀንም በማታም፣ በድብቅም በግልፅም፣ በተለያየ ስልት ህዝባቸውን “ህዝቦቼ ሆይ! አላህን በብቸኝነት አምልኩት ከእርሱ ውጭ በሃቅ የሚመለክ የለምና” በማለት 950 አመት ተጣሩ። በጣም ጥቂቶች እንጂ ለጥሪያቸው መልካምን
መልስ አልሰጡም።


➠ነብየላህ ኑሕ 950 አመት ህዝቦቹን በቀንም በማታም በድብቅም በግልጽም ካስጠነቀቁ በኋላ የህዝቦቹ መልስ የሚከተለው ነበር

◀وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا

አሉም “አምላኮቻችሁን አትተዉ።ወድንም፣ ሱዋዕንም፣የጉሥንም፣የዑቅንም ነስርንም አትተው።” [ኑሕ፡ 23]

➧ይህን ጉድ ተመልከቱ። ብቸኛው ፈጣሪ፣ የሁሉ ቀላቢ፣ የፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ፣ ብቸኛ አምላክ አላህ በድንበር አላፊዎች እና የተፈጠሩለትን አላማ በረሱ ህዝቦች
“አማልክት” በተባሉ ፍጡራን ተተካ
። የአላህ መብት ተቆርሶ የተሰጣቸው አምስቱ ሰዎች ወድ፣ ሱዋዕ፣ የጉሥ፣ የዑቅ እና ነስር በመባል ይታወቃሉ።

➧አርእስቱን ስናጠቃልል የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ፍጡራንን ማንም ይሁን ማን መላኢካም ይሁን ነብይ አላህ ከሰጠው ደረጃ በላይ ከፍ ማድረግ አላህ ለጠላው ሺርክ ይዳርጋል። ፍጡራን ፍጡር ናቸው። ምንም ይሁኑ ማን ጉዳትን ከራሳቸው ላይ መከላከል አይችሉም። መጥቀምም መጉዳትም የሚችለው የፍጡራን ሁሉ መጠጊያ የሆነው አንድ አላህ ብቻ ነው ።

➳ እዚህ መጸሀፍ ላይ የምናየው የሺርክ ስንኞች አብዛኛዎቹ በነብዩ (صلى الله عليه وسلم(፣በወሊዮች እና ወልይ ናቸው ተብለው የሚታሰቡ ሰዎች ላይ ድንበር በማለፍ የተፈፀሙ ናቸው።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

➽መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

📚አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወደ ግሩፓችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
➧ጥልቅ ፍቅር
➭➭➭➭➭➭➭

➲በአንድ ወቅት ነብዩ መሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰላም) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከሗላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አደረገው ይይዙትና።


ድምፃቸውን ቀይረው "እኔ ማን ነኝ ?" ብለው ይጠይቁታል.....
ቢላልም
"ኡመር ነህ ?"
"አይደለሁም።"
"አቡበክር መሆን አለብህ?"
"አሁንም ተሳስተሃል።"
"በቃ ኡስማን ነህ።"
"አላወቅከኝም።"
"አሊ ነህ ማለት ነው?"
....እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል።

°
ከዚያ ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለቅቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት
"ቢላል ሆይ! በእውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ ?" ሲሉ ጠየቁት።
°

ቢላልም “የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ እንዳቀፉኝ መቆየትን ስለፈልግኩኝ እንጂ"ሲል መለሰላቸው።ምን አይነት ፍቅር ነው? ያ ረብ!
ፊዳክ አቢ ወኡሚ ወነፍሲ ያረሱሉሏህ!!
ያአሏህ የእሳቸውን ፊት በጀና ለማየት አብቃን!!!

🌹اللهــم صــــل وسلــــم
علـــى نبينـــا محمــــدﷺ🌹

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ የአህሉ ሱነቲ ወልጀመአ ስሞች
☑️ የአህሉ ሱነቲ ወልጀማአ እምነቶች

➰ክፍል ⑦➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የዱኒያዋ ሠለፍይ
ከሁረል ዐይን ትበልጣለች


👉በጀነት ውስጥ ሁረል አይን አለች
👉በዱንያ ደግሞ ሰለፍይ ሴት አለች

🌹በዱንያ ያለችው ሠለፍይ ጀነት ውስጥ ስትገባ ከሁረል አይኗ የበለጠ ውብ ትሆናለች

ምክንያቱም የዱኒያዋ ሠለፍዩዋ እህቴ ፦
ጀነትን ለማግኘት የአዱንያን ፈተና ችግርና መከራ ስለተወጣች ነው።

https://t.me/abumahi13
https://t.me/abumahi13
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የላኢላ_ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➢ክፍል ⓶ ⓶ኛ የቂን፦ ሌላኛዉ የላኢላ ሃኢለሏህ መስፈርት ምንም ሳያወላዉሉ እርግጠኛ ሆኖ መልዕክቷን ማመን ነዉ። በያዘችዉ መልዕክት እርግጠኛ ሆኖ ያላመነ ተጠራጣሪ ነዉ። ➲በልቡ የሚጠራጠር ሰዉ ደግሞ በምላሱ ላኢላ ሃኢለሏህ ማለቱ ፍፁም ፍይዳ የለዉም። በተነፈሰ ቁጥር ላኢላ ሀኢለሏህ ቢልም እንኳን።…
➲የላኢላ_ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➛ክፍል⓷

⓸ኛዉ መስፈርት እዉነት ብሎ ማመን፦የላኢላ ሃኢለሏህን መልዕክት እዉነት ብሎ ያላመነ አስተባባይ ነዉ። ላኢላ_ሃኢለሏህ ደግሞ እዉነት ብሎ ለተቀበለ ብቻ ነዉ የምትጠቅመዉ!!

➧ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም(አንድ ሰዉ ከልቡ እዉነት ብሎ'ከአሏህ በስተቀር እዉነተኛ አምላክ የለም። ሙሀመድም ባሪያዉና መልዕክተኛዉ ናቸዉ ብሎ የሚመሰክር የለም'በእሳት ላይ እሱን አሏህ እርም የሚያደርገዉ ቢሆንጂ ይላሉ። (ቡኻሪ 128)

⓹ኛዉ መስፈርት ኢኽላስ፦ይሄኛዉ የላኢላ ሀኢለሏህ መስፈርት ደግሞ አምልኮትን አሏህን ብቻ በማሰብ መፈፀምን የሚመለከት ነዉ። አምልኮን ለአሏህ ብቻ ሳያደርግ ለፈጣሪም ለፍጡርም የሚሰጥ አካል ላኢላ ሃኢለሏህ ከነ መሰረቷ ንዷታል። ቀድሞ ነገር ላኢላ ሃኢለሏህ ከማለት ይሄ ይሄ እንጂ ምን ተፈልጎ!? ጌታችን አሏህ እንዲህ ይላል፦

(አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ብቻ የሚያጠሩና ቀጥተኞችም ሆነዉ እንዲያመልኩትንጂ አልታዘዙም።)[አልበይናህ፡5]

➲ነብዩ ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም እንድህ ይላሉ፦ ላኢላ ሃኢለሏህ ያለን ሰዉ_ይህን ማለቱ (የአሏህን ፊት የሚያስብ ከሆነ አሏህ በእሳት ላይ እርም አድርጎታል) ይላሉ።(ቡኻሪ ፡425 ሙስሊም:1528)

⓺ኛዉ መስፈርት መቀበል፦በተጨማሪ የላኢላ ሃኢለሏህን መልዕክት ያለ ምንም ማመንታት አሚን ብሎ መቀበል ያስፈልጋል። ያለበለዚያ እንቢተኛ ነዉ ማለት ነዉ። መልዕክቷን ያለ መቀበል ፍቃደኛ ያልሆነ እምቢተኛ ትርጉሟን በጥንቃቄ ማወቁና እዉነት እንደሆነም እርግጠኛ ሆኖ መረዳቱ በምንም መልኩ ሊጠቅመዉ አይችልም። አጋሪዎች አስመልክቶ ጌታችን ምን እንደሚል እንመልከት፦(እነሱ 'ከአሏህ ሌላ እዉነተኛ አምላክ የለም'በተባሉ ግዜ ይንጠባረሩ ነበር።''አኛ ለአንድ እብድና ባለቅኔ ብለን አምላኮቻችንን የምንተዉ ሰዎች ነን? ይሉም ነበር [አስሷፍት35_36] እናም የላኢላ ሃኢለሏህ መልዕክት መረዳቱ፣የቂን ብሎ ማወቁ፣ እዉነት ብሎም ማመኑ ቢኖር፤ የያዘችዉን መልዕክት ለመቀበል ዝግጁ እስካልሆነ ድረስ ሰዉየዉ አማኝ አይባልም። አቡ ጧሊብና በርካታ አይሁዳዉያን የሙሐመድ ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም እዉነተኛ ነብይነት በተለያዩ አጋጣሚዎች ተናግረዋል። መልዕክቱን ስላልተቀበሉ ግን እንደ ሙስሊም አልታሰቡም።

➛ ኢንሻ አሏህ
ይቀጥላል


📚ተውሂድ የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፍ ከሚለው ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ኪታብ የተወሰደ
✍ام عثيمين

JOIN በማለት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ክፍል ስምንት 〰〰〰〰〰 ➭ልብን “ረቢዓ ቀልቢ” (የልቦናዬ (ለምለም) ጨፌ) በማለት ሲያወሳ ደረትን ደግሞ“ኑረ ሶድሪ” (የደረቴ ብርሃን) በማለት ገለጸው፡፡ ምክንያቱም ደረት ልቦናን ያቀፈ ወይም ያካበበ ነው፡፡ ደረት ሲያበራ በውስጥ ያለው አካል ሁሉ ያንጸባርቃል፡፡ ልብ ለመልካም ነገሮች ከተገጠመች የትሩፋቶች ሁሉ ምንጭ በመሆኗ “ረቢዕ”…
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ዘጠኝ

➽ትክክለኛ የቁርኣን ንባብ በሶስት ነገሮች ካልሆነ ሊሟላ አይችልም
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

⓵ቁርኣንን ባማረ ሁኔታ በማንበብ እና በቻለው አቅም በቃሉ በመሸምደድ

⓶ መልዕክቱን በመገንዘብና በመረዳት

كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ إِلَيْكَ مُبَارَكٌ لِّيَدَّبَّرُوا آيَاتِهِ وَلِيَتَذَكَّرَ أُولُو الْأَلْبَابِ

“(ይህ) ወደአንተ ያወረድነው ብሩክ መጽሐፍ ነው፡፡ አንቀጾቹን እንዲያስተነትኑና የአእምሮዎች ባለቤቶችም እንዲገሰጹ (አወረድነው
)፡፡” ሷድ 29

أَفَلَمْ يَدَّبَّرُوا الْقَوْلَ
◆የቁርኣንን ንግግሩንም አያስተነትኑምን?” አል ሙእሚኑን፡68

➢የአንድ ሙስሊም ሐሳብና ጭንቀት ቁርኣንን ማንበቡ ወይም የጀመረውን ምእራፍ መች እንደሚያጠናቅቅ ሳይሆን መቼ ነው የቁርኣንን ጽንሰ ሐሳብ የምገነዘበው? የአላህን ቃል መቼ ነው የምረዳው? መቼ ነው ከልቤ ላይ ሰርጾ የሚገባው? መቼ ነው በቁርኣን የምሰራው? መቼ ነው በቁርኣን እንደተወሱት እውነተኞች የምሆነው? መቼ ነው ከጸጸተኞች ፣ ከተመላሾች ፣ ከአስታዋሾች ፣ ከሰጋጆች ፣ አላህን ከሚታዘዙት ፣ሶደቃ ከሚሰጡት የምሆነው? የሚለው ነው አንድን ሙስሊም ሊያሳስበው የሚገባው፡፡

➧አጁርሪይ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“ንግግሩን የተገነዘበ ጌታውን ፣ የጌታውን ታላቅ ስልጣን እና ችሎታውን ይገነዘባል፡፡በሙእሚኖች ላይ የቸረውን ታላቅ ስጦታ ያውቃል፡፡ በእርሱ ላይ ያለበትን የዒባዳ ግዴታዎች ይርረዳል፡፡

➠ ዋጅብ የሆኑትን ነገሮች በነፍሱ ላይ አጥብቆ ይይዛል ፣ የተከበረው ጌታ ያስጠነቀቀውን ይጠነቀቃል ፣ እርሱ የወደደውን ይወዳል ፡፡ ባህሪው ይህ የሆነ ሰው ቁርኣንን ሲቀራ ከሌሎቹ ሲያደምጥ ለእርሱ ፈውስ ይሆንለታል ፣ ገንዘብ ባይኖረውም በእርሱ ብቻ ይብቃቃል፣ ይረካል ፤ ያለዘመድ ልቅናን ያገኛል ፤ ሌላው ብቸኝነት ሲሰማው እርሱ በሐሴት ይዋጣል፡፡


➧ቁርኣንን ለመቅራት ከፈት ሲያደርገው በምቀራው መች ነው የምገሰጸው? የሚለውን እንጅ መቼ ነው ይህን ቁርኣን የማጠናቅቀው?የሚለው የእርሱ አላማ አይሆንም፡፡ ፍላጎቱ የአላህን ንግግር መቸ ነው የምገነዘበው? በአላህ ንግግር መቸ ነው የምገሰጸው? መቸ ነው የማስተነትነው? የሚለው ይሆናል።ምክንያቱም ቁርኣንን ማንበብ ከአምልኮቶች አንዱ ነው፡፡

ስለዚህ ከሚዘነጉ ሰዎች አትሁን፡፡ ለዚህም መልካም ተግባር የሚገጥምህ አላህ መሆኑን ተገንዘብ፡፡
” አኽላቁ ሃመለቲ አል ቁርኣን ሊል አጁሪ፡ ገፅ10

➳ይህን ለማረጋገጥ ቁርኣንን በደንብ ያነባል ፣ ነፍሱን ይታገላል፡፡

➧ይህን አስመልክቶ ኢብን አል'ቀይም - ረሂመሁሏህ - “ሚፍታሁ ዳሪ አስ’ሰዓዳ”
በተባለው ኪታባቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“የቁርኣንን አንቀጽ በማስተንተንና በመገንዘብ ማንበብ ፣ ያለምንም መገንዘብና መረዳት አጠናቆ ከማንበብ የበለጠና የተሻለ ነው፡፡ ለልቦና በጣም ጠቃሚ ፣ ኢማን ለማግኘት ቀስቃሽ ፣ የቁርኣንን ጣፋጭነት ለመቅመስ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያለው ነው፡፡” ሚፍታሁ ዳሪ አስ ሰዓዳ፡1/172

➛ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉◉✍

📚አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋልና

https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

☑️ አህለሱናዎች
▪️ቀደርዮች
▪️ኸዋሪጆች
▪️ሙርጂአዎች
▪️አህባሾች
☑️ ብዙ የቢድአ ቡድኖች ተወስቶበታል

➰ክፍል ⑧➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የላኢላ_ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል⓷ ⓸ኛዉ መስፈርት እዉነት ብሎ ማመን፦የላኢላ ሃኢለሏህን መልዕክት እዉነት ብሎ ያላመነ አስተባባይ ነዉ። ላኢላ_ሃኢለሏህ ደግሞ እዉነት ብሎ ለተቀበለ ብቻ ነዉ የምትጠቅመዉ!! ➧ነብዩ ሰለሏህ አለይሒ ወሰለም(አንድ ሰዉ ከልቡ እዉነት ብሎ'ከአሏህ በስተቀር እዉነተኛ አምላክ የለም። ሙሀመድም…
➲የላኢላ ሃኢለሏህ መስፈርቶች ሰባት ናቸዉ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➳ ክፍል⓸

⓻ኛዉ መስፈርትመዉደድ፦ ሌላኛዉ መስፈርት ደግሞ ላኢላ ሃኢለሏህን ፣መልዕክቷን እንድሁም እሷን የተሸከሙ ሰዎችን መዉደድ ነዉ።

➠ላኢላ ሃኢለሏህ የሚል ሰዉ ከምንም በላይ አሏህን ይወዳል።

➠ከሰዎችም ከአሏህ ሌላ ባላጣዎችን የሚይዝ አለ።ልክ አሏህን እንደሚወዱት ይወዷቸዋል። እነዚያ ያመኑት ግን አሏህን በመዉደድ(ከእነርሱ)ይበልጥ የበረቱ ናቸዉ።
{አልበቀራህ፡165}

➧ከምንም በላይ አሏህን የወደደ ሰዉ ደግሞ እሱ ወዶና መርጦ የላካቸዉን ነብይ የሂወቱ መመሪያ አድርጎ ይከተላል።(''አሏህን የምትወዱ ከሆነ ተከተሉኝ አላህ ይወዳችኋዋልና'' በላቸዉ።(አል ኢምራን:31)

➻አላህ የሚወደዉን መዉደድ እንዲሁም የአሏህ ደጋግ ባሪያዎችን መዉደዲም ላኢላ ሃኢለሏህ ከሚል ሰዉ የሚጠበቁ ነገሮች ናቸዉ።

➧ነብዩም ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፦(ሶስት ነገሮች በዉስጡ ያሉበት ሰዉ የኢማንን ጥፍጥና አጣጥሟል ፦

⓵ኛው እሱ ዘንድ አሏህና መልዕክተኛዉ ከነሱ ዉጭ ካሉ ሁሉ ይበልጥ የተወደዱ ሊሆኑ ነዉ።

⓶ኛው አንድን ሰዉ ለአሏህ ሲል ብቻ ሊወዲ ነዉ።

⓷ኛው አላህ ከሱን ከክህደት ካተረፈዉ ቡሀላ ወደ ክህዴት መመለስን ልክ ከእሳት ዉስጥ መወርወርን የሚጠላዉን ያክል ሊጠላ ነዉ
።(ቡኻሪ 16፣ሙስሊም፣174)

➧ስለዚህ አሏህን የሚወድ ሰዉ ከምንም በላይ የአሏህን ፍላጎት ያስቀድማል።

➧አሏህ የሚወደዉን ይወዳል፣ የሚጠላዉንም ይጠላል።

➲የላኢላ ሃኢለሏህ አንኳር መልዕክት የሆነዉን ተዉሒድና የተዉሒድ ሰዎች እየጠሉ በምላስ ላኢላ ሃኢለሏህ ማስተጋባቱ ይጠቅማል ብሎ ማሰብ ዘበት ነዉ።

📚ተዉሒዲ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁሏህ መፀሃፍ የተወሰዴ!!

✍أم عثيمين

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
↪️አቢ ሙሳ አላህመልካም ስራውን ይውደድለትና እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንድህ ብለዋል

➡️ሶስት አይነት ሰዎች ጀነት አይገቡም!!
▪️አስካሪ መጠጥ አዘውታሪ
▪️ዝምድና ቆራጭ
▪️ሲህር እውነት ነው ባይ

📚رواه أحمد وٱبْنُ حِبّٓان في صحيحه
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➢ክፍል አምስት ➧ልብ በሉ በዚህ ግዜ አማልክት ተብለውም አልተጠሩም። ሸይጧን ግቡን ለማሳካት ሩቅ ነው የሚያልመው።ከዚያም ይህ ትውልድ አልፎ ሌላ ትውልድ ሲተካና፣እውቀትም ሲጠፋ “አባቶቻችሁ ዝናብ ሲቸግራቸው እነሱን ነበር የሚጠይቁት” ብሎ ታላቁ ወጥመዱ ውስጥ ከተታቸው። ከዚያም ተቀበሉት። በዚህም ምክንያት አላህ ለምድር ህዝቦች የመጀመርያውን መልክተኛ ኑሕን (ዐለይሂ…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ስድስት


➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ወደ ምን አይነት ሰዎች ነበር የተላኩት?
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰


➲ሁሉም ነብይ ወደ የህዝቡ ሲላክ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ግን ባጠቃላይ ለአለማት እዝነት ተደርገው ነው የተላኩት።ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ህዝቦች እንደተላኩ ማወቃችን ወሳኝ ነጥብ ነው።
ምክንያቱም ዛሬ አብዛኞች የነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ተከታዮች ነን እያሉ በተግባር ግን ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (የተዋጓቸውን የነ አቡ ጀህልን መንገድ ሲከተሉ ይታያሉና።

➧ከላይ “የሰው ልጆች እንዴት አላህ ላይ ማጋራት ጀመሩ” የሚለውን ዋና ነጥብ
አይተን ነበር። በነጥቡ ላይ የሺርክን አደገኝነት እና የመጀመርያው ሺርክ በምን ምክንያት እና በማን ሰባኪነት እንደተፈጸመ አይተናል። አሁን ደግሞ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለምን አይነት ሰዎች ተልከው እንደነበር ማወቃችን የሺርክ አደገኝነት አውቀን በአላህ ፍቃድ ከባድ ጥንቃቄ እንድናደርግ ያግዘናል፣ ይረዳናል።


➧ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (የተላኩባቸው ህዝቦች ሐጅ የሚፈጽሙ፣ ምጽዋት የሚለግሱ እና ሌሎችንም ስራዎች የሚተገብሩ ነበሩ። ግና ይህ ተግባራቸው እስልምና ውስጥ አላስገባቸውም። ምክንያቱም አምልኮ ሲፈጽሙ በአላህ ላይ አጋርን ይጨምሩ ነበርና። በዚህም ነው ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (የተጋደሏቸው።

ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (የተላኩባቸው ህዝቦች አላህ ብቸኛው የሁሉ ፈጣሪ፣ ሁሉን አስተናባሪ፣ ሲሳይ ሰጪ መሆኑን ያምኑ ነበር። ለዚህም የሚከተሉት የቁርኣን አንቀጾች ግለጽ ማስረጃ ናቸው።

وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَسَخَّرَ الشَّمْسَ وَالْقَمَرَ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት ማን እንደሆነ ብትጠይቃቸው “አላህ ነው” ይሉሃል። “ምስጋና ለአላህ ነው” በላቸው። ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም። አንከቦት 61

وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَهُمْ لَيَقُولُنَّ اللَّهُ ۖ فَأَنَّىٰ يُؤْفَكُونَ

ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው “በእርግጥ አላህ ነው” ይላሉ። ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ?አዙህሩፍ 87

قُل لِّمَنِ الْأَرْضُ وَمَن فِيهَا إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ●سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ●قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ●سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ●قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ●سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ فَأَنَّىٰ تُسْحَرُونَ
“ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትሆኑ (ንገሩኝ)” በላቸው።“በእርግጥ የአላህ ነው” ይሉሃል። “ታዲያ አትገሰጹምን?”በላቸው። “የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?” በላቸው። “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል። “እንግዲያ አትፈሩትምን?” በላቸው። የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው? የምታውቁ እንደሆናችሁ (መልሱልኝ)” በላቸው። “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል። “ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?” በላቸው። [አልሙእሚኑን፡ 84-89]

📚መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1