💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
#የወላጆችህን_እርግማን_ተጠንቀቅ


‏قال الإمام مقبل ‎الوادعي رحمه الله፡–

رُبَّ دعوة من الوالدين تدمر الشخص و يخسر حياته و آخرته،

بسبب دعوة أمه، أو بسبب دعوة أبيه !

ሸይኽ ሙቅቢል ዒብኑ ሀዲ አሏህ ይዘንላቸውና እንድህ አሉ፡–

#በአባትህ_ፀሎት_ምክንያ_ ወይም_ #በእናትህ_ዱዐዕ_ምክንያት_በወላጆችህ ዱዐዕ ምክንያት የሰውየው ዱንያውም አኸይራውም ሊወድምበትና ሊከስርበት ይችላል፡፡
[[كتاب الرحلةالأخيرة - ٢٤٠]]

ስለዚህ ከወላጆቻችን እርግማን ልንጠነቀቅ ይገባል።
ከተቻለ እንድንረዳቸውና እንድናስደስታቸው አሏህ ዘንድ ትልቅ ሀላፊነት እና ትልቅ አጂር አለን

የመርዳት አቅም ካጣን ማስደሰት ካልተቻለ ግን በፍፁም በፍፁም የመከፋታቸው ምክንያት መሆን የለብንም!!


https://t.me/https_Asselefya1
ወዳጅህ /ሺ ከስህተት የሚያርምህ/ሺ ነው


ﻗَﺎﻝَ ﺍﺑﻦُ ﻗُﺪَﺍﻣَﺔ - ﺭَﺣِﻤﻪُ ﺍﻟﻠَّﻪ ፡–ﻗَﺪ ﻛَﺎﻥَ ﺍﻟﺴَﻠَﻒ ﻳُﺤِﺒُّﻮﻥَ ﻣَﻦ ﻳُﻨَﺒِّﻬُﻬﻢ ﻋَﻠَﻰ ﻋُﻴُﻮﺑَﻬُﻢ
ﻭﻧَﺤْﻦُ ﺍﻵﻥ ﺃﺑﻐَﺾُ ﺍﻟﻨَّﺎﺱِ ﺇﻟَﻴﻨَﺎ ﻣَﻦ ﻳُﻌﺮِّﻓَﻨﺎ ﻋُﻴﻮﺑَﻨﺎ ‏

ኢብኑቁዳማህ አሏህ ይዘንላቸው እንዲህ ይላሏ፡–
#ሰለፎቻችን_ስህተታቸው የሚያርማቸውን ሰው በጣም ይወዱ ነበር።

↪️እኛ ደግሞ በጣም የምንጠላው ሰው ስህተታችንን[የሚያርመንን] የሚያስታውሰንን ነው ።

‏[[ ﻣِﻨﻬَﺎﺝُ ﺍﻟﻘَﺎﺻِﺪﻳﻦ [[ﺻـ ١٩٦]]


https://t.me/Asselefya1
سئل الامام المحدث الشيخ الالباني رحمه الله تعالـــﮯ

السائل : هل يجوز التأمين عند الدعاء والخطيب يخطب؟

الشيخ : هذا لا يجوز .

السائل : نعم...
والصلاة على النبي - صلى الله عليه وسلم - .

الشيخ : لا يجوز لا صلاة ولا كلام ولا صلاة على الرسول

لقول النبي صلى الله عليه وسلم":
( إذا قلت لصاحبك يوم الجمعة والإمام يخطب أنصت فقد لغوت ) .
السائل : ويدخل فيها الدعاء؟
الشيخ : كل شيء .

[الامام الالباني رحمه الله]
📚المصــدر : الهدى والنور (٢٦٢)]
✍️
ቀደም ብዬ ወደ መስጂድ ለመግሪብ ሶላት እየሔድኩኝ ነው።እንደገባሁ ማሻ አሏህ ደስ የሚል ህፃን ልጂ ተመለከትኩ።
____ በባህሪዬ ከህፃን ልጂ ጋር መጫወት በጣም ከሚያስደስተኝ ነገር ውስጥ አንዱ ነው። _የልጁ ውበት እና ህፃንነቱ ከኔ ህፃን መውደድነት ጋር ሲዋሀድ የሆነ ስሜት ተሰማኝ ብቻየን በፈገግታ ድምቅ ከማለቴ ተነሳ መስጂዱ ውስጥ ሰው የለሌለ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር ።

#ከዚያ_የህፃኑ_አባት_ሶላት እየሰገደ ነበርና ህፃኑ #ባባ የሚል ድምፅ ሲያሰማ..!! ከአባቱ ጋር ሆኖ ምን ሆነ !?የሚል ጥያቄ ፈጠረብኝ!!።
ከውስን ቆይታ በኋላ አባቱ ከሶላት አሰላመተ ልክ እንዳሰላመተ ሮጦ በፈገግታ #ግንባሩን ሳም አደረገው ልጁ #አሁን ለምን ባባ እንዳለ ገባኝ #ለካም_ናፍቆት ነው። ልጁ የአባቱን ግንባር እንደሳመው #አባትዮው ከደስታው ብዛት የተነሳ ምኑን እንደሚስመው ግራ የተጋባ ይመስላል ከዚያም እቅፍ አድርጎ አንገቱን ሳም አደረገው #ያ_ሰላም
#ማሻ_አሏህ_ወላሒ_ቀናሁ::
ያማረ አባትነትና የደመቀ የልጂ ፍቅር እንደት ደስ ይላል በአሏህ!?
#ከትርዒቱ_በኋላ_ነፍሴ በጥያቄ ቀስፋ ያዘችኝ
#አንተ_ምን_እየሰራህ_ነው!?
#ለምን_አታገባም!?
#መውለድ_አያምርህምን!?
ብላ ስትሰቅዘኝ እንድህ ተቀኘሁላት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
#ወልደህ_እንድትስም__!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የልጂነት እድሜህ ውበትህ ሳይጠፋ፡
እርጂና ሳይመጣ አንገትክን ሳትደፋ፡
የአካልህ ላይ ፀጉር ነጭነት ሳይተፋ፡
የወጣትነትህ ውበትህ ሳይከስም፡
ባባ የሚል ሞገስ እንድታወጣ ስም፡
ሀላሉን ድፈረው ወልደህ እንድትስም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የሚል ተስፋ ለነፍሴ ማፅናኛ ሰጥቻት ቀሪውን በዝምታ ውጨ ተውኩት።

#ኑረዲን_ነኝ

https://t.me/Asselefya1

👉 #ወንድሜ ሆይ አግባ ወለድ ልጆች ውበት ናቸው መከበሪያ ናቸው #እህቴ ሆይ አግቢ ውለጅ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ወልዶ ከመሳም የበለጠ ልጆች እኮ #እማየ_እናቴ_የሚለውን የክብር ስም ያሰጥሻል እናትነት ክብር ነው ውድ እህቶቼ ትዳርን አትፍሩት የሱና ጎጇችሁን መስርቱ!!

http://t.me/nuredinal_arebi
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
◼️የጅሙአ ቀን ሰለዋትን እናብዛ


【إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا】
↪️ አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በመልእክተኛው ላይ ሶለዋት አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📚(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 56)

اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ


↪️ ክፍል 5⃣5⃣ ↩️


↪️የትዳር አስፈላጊነትና ጥቅም
↪️የጥሩ ትዳር መሰረቶች
↪️ከትዳር መሸሽና አደጋው


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ተዉሂድና የሺርክ አይነቶች

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/2968
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
📍محاضرة جديدة

📍አዲስ ሙሓደራ

🌐 موقف المؤمن عند الفتن

🌐 በፊትና ግዜ የሙዕሚን አቋም

🕌 ደሴ አል አዝሓር መስጂድ ሳምንታዊ ፕሮግራም

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◼️እውቀት እና ጅህልና‼️


የእውቀት አስፈላጊነትና አሳሳቢነት

እውቀት የሁለት ሀገር የስኬት ዋነኛው ቁልፍ

እውቀት ወደ አላህ መቃረቢያ ኢባዳ ስለመሆኑ

እውቀት መፈለግ ከነዋፊል ኢባዳ መብለጡ

የጅህልና አስከፊነትና አደገኝነት

ጅህልና የጨለማው የጀሀነም ጉዞ

♨️ጠቃሚ ነጥቦች የተወሳበት ምክር

🔻العلم قبل القول والعمل

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ


↪️ ክፍል 5⃣6⃣ ↩️


↪️ትዳር የሀብት ምንጭ
↪️ትዳር በኢስላም መነፅር

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
♨️ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️ ↪️ #ክፍል_ስምንት↩️ #ስምንተኛ፡ - አንዲት ሴት ለሆነ ጉዳይ ስትወጣ አጅነብይ የሆኑ ወንዶችን ዘወር ዘወር እያለች መመልከት የለባትም፡፡ ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡- ⫸【وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ…
🔜ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️


↪️
#ክፍል_ዘጠኝ↩️


↪️
#የተከበርሽው_እህቴ_ሆይ! ኢብን ሂባን የዘገበውን አቡሁረይራ ረድየሏሁ አንሁ ያስተላለፉትን ታላቅ ሐዲስ አስተውይ ፡

📌"إذا صلت المرأة خمسها ، وصامت شهرها ، وحصنت فرجها ، وأطاعت بعلها ،
دخلت من أي أبواب الجنة شاءت"
↪️“ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሶላት ከሰገደች ፤ ወሯን (ረመዷንን) ከጾመች ፤ ብልቷን ከጠበቀች ፤ ባሏን ከታዘዘች ፤ በፈለገችው የጀነት በሮች ትገባለች፡፡” ኢብኑ ሂባን፡ ጦበራኒይ አል ሙዕጀም አል ወሰጥ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ተርጊብ፡

📌وروى اإلمام أحمد من حديث عبد الرحمن بن عوف رضي الله عنه أن النبي صلى الله عليه وسلم قال: "إذا صلت المرأة خمسها وصامت شهرها وحفظت فرجها وأطاعت زوجها قيل لها ادخلي الجنة من أي أبواب الجنة شئت"

↪️“ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሶላት ከሰገደች ፤ ወሯን (ረመዷንን) ከጾመች ፤ ብልቷን ከጠበቀች ፤ ባሏን ከታዘዘች ፤ በፈለገችው የጀነት በሮች ትገባለች፡፡” አህመድ፡ ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አት ተርጊብ፡

ከመጥፎ ተጣሪዎች እርቃ በእነዚህ ታላላቅ ነብያዊ ምክሮች ተጠቃሚ በመሆንና ህይዎቷን በመምራት እድለኛ የሆነች ሴት እንኳን ደስ አላት!

#ሙስሊሟ እህቴ ሆይ! በዚህ ዘመን የኢስላም ጠላቶች ሂጃብሽን አስወልቀው ከተራ ዱርየዎች ተርታ ሊያሰልፉሽ ተዘጋጅተዋል፡፡ ለዚህ ተንኮላቸው ደግሞ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱት ቴሌቪዥኖች፣ ሞባይሎች ፣ ጋዜጦች እና የተለያዩ ሚዲያዎች ናቸው፡፡

🔷በመሆኑም አንዲት ሙስሊም ሴት አላህ ባዘዛት መሰረት ቀጥ ካለችና ሒጃቧን ባግባቡ ከለበሰች በኢማኗ ጥንካሬ የሚከሰቱ ውዝንብሮችን እና የሰይጣን ተንኮሎችን በአላህ ፈቃድ ትከላከላለች፡፡


↪️ከዚህ ቦታ የኡሙ ሰለማን ረድየሏህ አንሃ ጠንካራ ባህሪ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم ልብሱን በኩራት እየጎተተ ስለሚሄድ ወንድ ስለሚያጋጥመው ቅጣት በተናገሩ ጊዜ ኡሙ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ ሴቶች ምን ማድረግ እንዳለባቸው ስትጠይቅ “አንድ ስንዝር ታስረዝም” አሏት “እንደዛ ከሆነማ እግሮቻችን ይገለጣሉ” አለቻቸው፡፡

“በቃ አንድ ክንድ ታስረዝም ከዚህ በላይ እንዳትጨምር” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡ ቲርሚዚይ፡ ነሳኢይ፡ዘግበውታል

↪️ኢማኗ የደከመባት ሴት በተቃራኒው አንድ ስንዝር ወይም አንድ ክንድ ወይም ከዚያ በላይ እንደ ኢማኗ ድክመት አካሏን ትገልጣለች፡፡


↪️ለቅኑ ጎዳና እንዲመራሽ ፤ ግልጽም ከሆነ ስውር ፈተና እንዲጠብቅሽ ፤ እርሱን
በመታዘዝ ላይ እንዲያግዝሽ ፤ በሐቁ ላይ እንዲያጸናሽ አላህን እማጸናለሁ፡፡ እነሆ አላህ ዱዓን ሰሚና ተቀባይ ነውና ፡፡

【በዚህ ተጠናቀቀ 】

▪️ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ ከሚለው መፅሀፍ የተወሰደ

👉ውድ እህቴ ሆይ እኔም አልኩሺ ሂጃብሺን አደራ! ሂጃብሺ እኮ የመከበሪያሺ ፣የውበትሺ፣የኢማንሺ ፣የሀያዕሺ መለኪያ ነውና ጠብቂው ስረአቱን ጠብቀሺ ልበሺው ሂጃብ ከአላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ የተሰጠን ኒዕማ ፀጋ ነው!!

🖊ኡሙ ፋሩቅ


https://t.me/https_Asselefya1
Audio
የወንጀል አደገኝነት
ወንጀልን ማተናነስ
የቀልብ መጥቆር ምክንያት

📌عن أبي هريرة رضي الله عنه ،عن رسول الله ﷺ قال :
((إنَّ العَبْدَ إذَا أخْطَأ خَطِيئَةً نُكِتَتْ فِي قَلْبِهِ نُكْتَةٌ سَوْدَاءُ ، فَإذَا هُوَ نَزَعَ وَاسْتَغْفَرَ وَتَابَ سُقِلَ قَلْبُهُ ، وَإنْ عَادَ زِيدَ فِيهَا حَتَّى تَعْلُوَ قَلْبَهُ ، وَهُوَ الرَّانُ الَّذِي ذَكَرَ اللهُ :﴿كَلَّا بَلْ رَانَ عَلَى قُلُوبِهِم مَّا كَانُوا يَكْسِبُونَ﴾))
📚رواه الترمذي.

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️የተንቢሀት ኪታብ ደርስ


↪️ ክፍል 5⃣7⃣ ↩️


↪️ የትዳር ዋና ዋና አላማዎች
↪️ በትዳር የሚገኙ ዋና ጥቅሞች
↪️ ራስን በራስ ማርካት በተመለከተ


🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
❝በመሸነፍ ውስጥ ያለ ማሸነፍ❞


↪️"አላህን ፍራ" ለሚልህ ተሸነፍ። በአላህ ለሚገስፅህ ተሸነፍ። ከጥፋት እንድትመለስ፣ ወደ መልካም እንድትዞር ለሚጎተጉትህ አቀራረቡ ባያምርህም ተሸነፍ። ወንድሜ ሆይ! ለሐቅ እጅ መስጠት ሽንፈት አይደለም። ከመሰለህም ግዴለህም ተሸነፍ። ነፍስያህ እንደዚያ አስመስላ ብታቀርብብህም ነፍስያህን በመርታት አሸንፍ። አስተውል! ከመሙ ጫፍ ላይ ድል ያለበት ሽንፈት ማሸነፍ ነው።

..🖊𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐌𝐮𝐧𝐞𝐰𝐨𝐫 «𝐇𝐚𝐟𝐢𝐞𝐳𝐞𝐡𝐮𝐥𝐥𝐚𝐡»


https://t.me/Asselefya1
ኢማሙ ዓብኑል ጀውዚ ረሒመሁሏህ ይላሉ፡–ከሞተ በኋላ መልካም ስራው እንዳይቋረጥበት የፈለገ ሰው እውቀትን ያሰራጭ…!!

https://t.me/Asselefya1