💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
🌸ሱኒ ሰለፍይ የሆነች በተውሂድ የጠነከረች፣
የሱናዋ ቆንጆ ጀግናዋ በሱና ያጌጠች ሁሌም እሷ ውድ ነች!!🌸
ሐያእ (አይናፋርነት) ለሴት ልጅ ትልቁ ሀብቷና ውበቷ ነው!!



↪️ሐያእ በመሰረቱ ወንዱም ሴቱም ጋር ሊኖር የሚገባው ተወዳጅ ምርጥ ባህሪ ነው። በተለይ መልኩ ግን ሴቶች ዘንድ ወሳኝነት አለው። ይሁን እንጂ ሐያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር አላህ ካዘነላቸው ጥቂት እንስቶች በስተቀር ብን! ብሎ የጠፋ ይመስላል። ሴት ልጅ አይናፋርነት ከሌላት እንዲሁ ባህሪዋ ለባሏ እንኳ አይማርከውም፣ ምክንያቱም አይናፋርነት ለሴት ልጅ ከፈጣሪዋ የተሰጣት ልዩ ውበትና ግርማ ሞገሷ፣ ተፈጥሯአዊ የሆነ ስጦታዋ ነውና። ሀያእ (አይናፋርነት) የሚባለው ነገር ከብዙ ሴቶች ልብ ድራሹ ጠፍቶ በስመ ስልጣኔ ጋጠ-ወጥ ሴቶች አስባልቱን ከሞሉት ሰነባብቷል። እንዲያውም አንዳንዴ በተቃራኒው ሀያእ የሚባለው ነገር ከሴቶች ይልቅ ወንዶች ዘንድ ይስተዋላል።
"
↪️እህቴ ሆይ! ቁርኣን አንድን ነገር ሲጠቅስ ያለ ምክንያት አይደለም!። ይልቅ ከእኛ መተገበሩ ወይም መጠንቀቁ ተፍልጓል ማለት ነው። ለምሳሌ አላህ ስለ ነቢዩላህ ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ስደት ላይ ሆኖ የገጠመውን ሲተርክ እንዲህ በማለት የአንዲትን እንስት አካሄድ አውስቷል:-

فَجَاءَتْهُ إِحْدَاهُمَا تَمْشِي عَلَى اسْتِحْيَاءٍ

«ከሁለቱ አንደኛይቱም ከሐፍረት ጋር የምትሄድ ሆና መጣችው፡፡» አል-ቀሰስ 25

ሸይኽ ናሲሩ ሰዕዲ (ረሂመሁላህ) ይህን አንቀፅ ሲያብራሩ ተፍሲራቸው ላይ እንዲህ አሉ:- “ይህ የሚያመላክተው የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤት መሆኗን ነው፣ ምክንያቱም አይናፋርነት በላጭ ከሆነው ከመልካም ስነ-ምግባር ነው!፣ በተለይ በሴቶች ላይ።” [ተፍሲሩ ሰዕዲ]

↪️"ከሀፍረት ጋር የምትሄድ ሆነ…" በማለት አካሄዷን አውስቷል፣ አላህ ይህን አካሄድ አንቺም ከቤት የሚያስወጣሽ አስገዳጅ ነገር ሲኖር ተግባራዊ እንድታደርጊው ፈልጓል ማለት ነው። አለባበስሽ ሸሪዐው የሚፈልገው አይነት ሆኖ በጅልባብና ኒቃብ የተሰተርሽ ሆነሽ ብትወጪ እንኳን ይህ አይናፋርነት ፈፅሞ ሊለይሽ አይገባም!። ምክንያቱም ሀያእ ከፈጣሪሽ ዘንድ የተቸረሽ ትልቁ ሀብትሽና ውበትሽ ነው!።
"
↪️የነዚያ ጋጠ-ወጦች ጩሃት ሸንግሎሽ በስመ ስልጣኔና ግልፀኝነት ሀያእሽን አትልቀቂው የአንቺ የሙስሊሟ እንስት የፈጣሪዋ ትልቅ ችሮታ ነው!!። ሀያእ የሚባለውን የተፈጥሮ ስጦታሽንና ሀብትሽን ለማቆየት ምናምንቴዎችን ትተሽ ጓደኝነትሽን ሀያእ ካላቸው እህቶችሽ ጋር አድርጊው!። ጓደኛሽ ሀያእ ከሌላት ሙተነቂብ መሆኗ አለያም ከአንቺ በላይ እውቀት ስላላት አትሸንግልሽ!፣ ከቻልሽ ሀያእ እንዲኖራት ምከሪያት! ካልተስተካከለች ግን ራቂያትና ሀያእ ያላቸውንና ዲናቸው ጠንካራ የሆኑ እህቶችሽን ጓደኛ አድርጊ!።
"
↪️ወንድሜ ሆይ! ልታገባ ስታስብ ሀያእ ያላትን ሴት መምረጥ እንዳለብህ አትዘንጋ!። ልታገባት ያሰብካት ሴት ምናልባት ማሻ አላህ አለባበሷ ሸሪዐዊ የዲን እውቀቷም እንደዛው ሊሆን ይችላል፣ ግን ሀያእዋ እንዴት ነው?!። ምክንያቱም ሀያእ ትልቅ ዋጋ አለው!
በዚህ አስቸጋሪ ዘመን ሀያእ የሌላት እንስት ከራሷ የባሰ ሀያእ የሌለውን ትውልድ ቢሆን እንጂ ሀያእ ያለውን ትውልድ ልታፈራ አትችልም!!።

↪️ሀያእ እየጠፋ የመጣ የሙስሊም እንስቶች ትልቅ ሀብት ነው!! እህቴ ሆይ! ትልቁን ሀብትሽን ውበትሽን፣ የፈጣሪሽን ስጦታ ፈልገሽ አጥብቀሽ ያዢው!!

✍🏻ኢብን ሽፋ:

#ውዷ_እህቴ_በሀያዕሺ_በሂጃብሺ_ተዋቢ_አትዝረከረኪ_ቁጥብ_ሁኚ_ውድ_ትሆኛለሺ!!

የተለያዩ ት/ት ሰጪ ፅሁፎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ከሌሎት
#join ⤵️ ያድርጉና ይቀላቀሉ
https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ


↪️ ክፍል 2⃣1⃣ ↩️


↪️ ፅንስ ማስወረድ ያለው አደጋ
↪️ ሩህ ሳይነፋበት በፊት ማስወረድ
↪️ የምታስወርድ ሴት ቅጣት

🔻ሼር በማድረግ እህቶቻችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
💢ነብዩሏህ ዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላም)‼️


↪️«ነብዩሏህ ዩሱፍ (ዓለይሂ ሰላም) በወንድሞቹ ምቀኝነት ምክንያት ከአባታቸው ለይተው ተኩላ በላው ብልው ዋሻ ውስጥ ወረወሩት ከዚያም ሃያሉ አላህን በመጨነቅና በመጠበብ ለመነ፣ አላህም ዱዓውን ተቀብሎ ከእዚያ ከጭንቅ አወጣው ትልቅ ቦታም ላይ አደረሰው»!!



↪️ወንድሞቹ ቢበድሉትም አላህ ኑሮውን አሳመረለት!
ይሁን እንጅ ትልቅ ፈተና ቀርቦለት ነበር የአዚዙ ሚስት በሩን ዘግታ አባበለችው ለወንጀልም በጠራቸው ጊዜ እንዲህ ነበር ያለው:-
«በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)»።

وَرَاوَدَتْهُ الَّتِي هُوَ فِي بَيْتِهَا عَن نَّفْسِهِ وَغَلَّقَتِ الْأَبْوَابَ وَقَالَتْ هَيْتَ لَكَ ۚ قَالَ مَعَاذَ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ رَبِّي أَحْسَنَ مَثْوَايَ ۖ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ


↪️ያቺም እርሱ በቤቷ የነበረባት ሴት ከነፍሱ አባበለችው፡፡ ደጃፎቹንም ዘጋች፤ «ላንተ ተዘጋጅቼልሃለሁና ቶሎ ናም» አለችው፡፡ «በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (ያገዘኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም» አላት፡፡

📚ቅዱስ ቁራኣን ሱራ ዩሱፍ (23)

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
Kitabu Tewhid #6
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ


↪️ ክፍል 6⃣ ↩️


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አንዲት ሴት የባሏን ሐቅ እስካልተወጣች ደረስ የኢማንን ጣዕም አታገኝም።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አርበዒን 25ኛ ሐዲሥ
Ibnu Munewor
↪️አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር↩️


↪️ ሐዲሥ ቁጥር –2⃣5⃣


🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔺حفظه الله تعالى
https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
◾️فضل التسبيح والتحميد والتكبير


📌عَنْ أَبِي ذَرٍّ رضي الله عنه أَيْضًا، "أَنَّ نَاسًا مِنْ أَصْحَابِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالُوا لِلنَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم يَا رَسُولَ اللَّهِ ذَهَبَ أَهْلُ الدُّثُورِ بِالْأُجُورِ؛ يُصَلُّونَ كَمَا نُصَلِّي، وَيَصُومُونَ كَمَا نَصُومُ، وَيَتَصَدَّقُونَ بِفُضُولِ أَمْوَالِهِمْ. قَالَ: أَوَلَيْسَ قَدْ جَعَلَ اللَّهُ لَكُمْ مَا تَصَّدَّقُونَ؟ إنَّ بِكُلِّ تَسْبِيحَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَكْبِيرَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَحْمِيدَةٍ صَدَقَةً، وَكُلِّ تَهْلِيلَةٍ صَدَقَةً، وَأَمْرٌ بِمَعْرُوفٍ صَدَقَةٌ، وَنَهْيٌ عَنْ مُنْكَرٍ صَدَقَةٌ، وَفِي بُضْعِ أَحَدِكُمْ صَدَقَةٌ. قَالُوا: يَا رَسُولَ اللَّهِ أَيَأْتِي أَحَدُنَا شَهْوَتَهُ وَيَكُونُ لَهُ فِيهَا أَجْرٌ؟ قَالَ: أَرَأَيْتُمْ لَوْ وَضَعَهَا فِي حَرَامٍ أَكَانَ عَلَيْهِ وِزْرٌ؟ فَكَذَلِكَ إذَا وَضَعَهَا فِي الْحَلَالِ، كَانَ لَهُ أَجْرٌ".

📚 رَوَاهُ مُسْلِمٌ [رقم:1006].



#የዚክር_ምንዳዎች


አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ : “ከአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمጓዶች (ሱሓባዎች) ውስጥ የተወሰኑት ለነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ፦

↪️ሃብታሞች በአጅር (በምንዳ) በለጡን። ልክ እንደምንሰግደው ይሰግዳሉ፥ ልክ እንደምንጾመው ይጾማሉ፥ በተረፈው ገንዘባቸው ደግሞ ሰደቃ ያወጣሉ።

ከዚያም የአላህ መልዕክተኛ አሏቸው አላህ እናንተ ሰደቃ የምታወጡበት ነገር አላደረገላቹህምን ?

#ሁሉም_ተስቢሕ (ሱብሃነላህ) ሰደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁአክበር) ሰደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሓምዱሊላህ) ሰደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለላህ) ሰደቃ ነው፤ በመልካም ነገር ማዘዝ ሰደቃ ነው፤ ከመጥፎ ነገር መከልከል ሰደቃ ነው፤ ከባለቤቱ(ቷ) ጋር የሚደረግ ግብረስጋ ግንኙነትም
ሰደቃ ነው።


የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمጓዶች (ሱሓባዎች) አንድ ሰው ስሜቱን ተወጥቶ እንዴት አጅር ይኖረዋል ? የአላህ መልእክተኛም صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ፦ አያቹህ ግብረስጋ ግንኙነቱን በሓራም ቢያደርግ ወንጀል አይኖርበትምን ? ልክ እንደዚሁ በሓላል ከፈጸመው ለሱ አጅር አለው።”

📚 ሀዲሱን ሙስሊም ዘግቦታል

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
➧ከሴቶች ሁሉ አስጠሊታ ሴት ማለት ከወንዶች ሀያእ «አይናፋርነት የሌላት» የሆነችዋ ሴት ናት።
ዑመር አል ፋሩቅ
ምንጭ፦ ኢብኑ አቢ ሸይባህ (32503)
↪️ሁላችንም ለዲናችን ከዱንያችን በበለጠ ቦታ ሰጥተን እውቀትን እንማር !!

↪️የአላህ ዲን የምናውቀው እውቀትን በመፈልግ እንጅ አንረዳውም።

📖የአላህን ዲን ባወቅን ቁጥር አላህ እናውቃለን አላህን ካወቅን ደግሞ ለሱ ያለን ፍራቻ(ተቅዋ) ይጨምራል

↪️አላህን በትክክል ከፈራን ደግሞ በዱንያም በአኼራም ትልቅ ደስታን እናገኛለን።

🖇አላህ እውቀትን ለመማርም ሆነ ለማስተማር ያግራልን ።

https://t.me/https_Asselfya
https://t.me/https_Asselfya
Audio
◾️ተከታታይ የተንቢሀት ኪታብ ደርስ


↪️ ክፍል 2⃣2⃣ ↩️


↪️ ፅንስ ለማስወረድ መስፈርቱ
↪️ ፅንስ ማድወረጃ ክኒን መውሰድ
↪️ እርግዝና መከላከያ መጠቀም

🔻ሼር በማድረግ እህቶቻችን እናንቃ

🎙 አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
🔺حفظه الله تعالى!!!

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🔜ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️ ↪️ #ክፍል_ሶስት↩️ #የተከበርሽ_እህቴ_ሆይ! በአላህ ውዴታ ክብርና ልቅና የምትጎናጸፊበትን መንገድ ትኩረት ልትሰጭ ይገባል፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡- 📌إِنَّ أَكرَمَكُم عِندَ اللَّهِ أَتقَاكُم “አላህ ዘንድ በላጫችሁ…
ሙስሊሟ እህቴ ሆይ ሂጃብሺን አደራ❗️


↪️
#ክፍል_አራት↩️

↪️እነዚህ ከዚህ በላይ የጠቀስናቸው ህግጋቶች በተግባር ሊተገበሩና ሁልጊዜም ልናስታውሳቸው ፤ ቀልባችን እንዲለዝብና የአላህን ህግጋት እንድንቀበል የሚያደርጉ በአጠቃላይ ደረታችንን የሚያሰፉ፣ የሚያረጋጉ፣ ወደአላህ ህግጋት ፊታችንን እንድናዞርና በዱንያም ይሁን በአኼራ እድለኛ እንድንሆን የሚያግዙ መሰረታዊ ታላቅና
ጠንካራ ህግጋቶች እና ደንቦች ናቸው፡፡



↪️የተከበርሽውብ እህቴ ሆይ! ዲነል ኢስላም ሴቶች ከወንድ ጋር አይቀላቀሉ ፣ ሂጃብ ይልበሱ በማለት ትዕዛዝ ያስተላለፈው የሴቶችን ክብር ከባለጌዎች ለመከላከል ነው፡፡

ሴት በኢስላም ከማንኛውም ቆሻሻ የጠራች እንቁ ነች!! በዲኑ ህግና ስርዓት ለመስራት ዕድሉ የገጠመው ምን ትልቅ እድል አጋጠመው! ሁኔታውን ምን አላቀው! በረካውን ምን ከፍ አደረገው!
የአላህን ህግ መከተል ከተለያዩ ጥቅሞች ያግዳል ፤ መጥፎ ነገር ያስከትላል ብሎ መናገር በአላህ ላይ ያለእውቀት መናገር ነው የሚሆነው፡፡

ከሓጢያቶች ሁሉ ታላቁ ደግሞ በአላህ ላይ ያለእውቀት መናገር ነው ፡፡

አላህ በተከበረው ቁርዓን እንድህ ብሎ ተናግሯል፡-

📌وَأن تَقُولُواْ عَلَی اللَّهِ مَا لاَ تَعْلَمُونَ

“በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው በላቸው፡፡” አል አዕራፍ33


🔜የተከበርሽው እህቴ ሆይ! ሴቶችን በተመለከተ ከአላህ ኪታብ ባነበብሽ ጊዜ ደረትሽን አስፍተሸ በእርጋታና በጥሞና በማስተንተን አንብቢው፡፡ ምክንያቱም የምታነቢው ንግግር አንችን የፈጠረሽ ያስገኘሽ መስሚያ እና መመልከቻ ማለትም አምስቱን የስሜት ህዋሳት የሰጠሽ ጥንክርናን እና ብርታትን ያደረገልሽ ጌታ ንግግር ነው፡፡



የአላህ ንግግር እና የፍጡር ንግግር ልዩነቱ ልክ በእርሱ እና በፍጡሮች መካከል ያለውን ልዩነት ማለት ነው፡፡

ከአላህ በመጣው መመሪያ ላይ አደራ በልቦናሽ ውስጥ ያለመቀበል ስሜት እንዳታሳድሪ!!

【ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን!
ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!】

ኢንሻአላህ

ክፍል አምስት ይቀጥላል


https://t.me/https_Asselefya1
#ምርጫዬ__ሱኒ__ናት!!!
#ዛሬም__እንደ__ትናንት

የተገኘች ለታ
አቤት ያለ ደስታ
ሱኒይቱ ስጠኝ አንተ የኔ ጌታ

#ሳገኛት__ምኞቴ
ሳይኖርም ልዩነት በመካከላችን
በፍቅር ተሞልቶ የሱናው ቤታችን
ሷሊህ ሷሊህ ልጆች ሲሰጠን ጌታችን
ሱናን ስንከተል እስከ ልጆቻችን
በቁርኣን በሐዲስ ታንፃ ቀልባችን
ስንሰራ እኖራለን ለዛኛው ቤታችን !!


➣ዱንያ ላይ የወንድም ይሁን የሴት ህይወት ጥሩና መልካም እንዲሁም የተረጋጋ የሚሆነው ሷሊህ የሆኑ ባልና ሚስቶች ሲጠናዱና ሲጣመሩ ነው።
ጌታዬ አላህ ሆይ ! ሷሊህ አድርገህ ከሷሊ ባሪያህ ጋር አጣምረን!!

قال العلامة أحمد النجمي - رحمه الله - :
- فالرجل لا يتم حاله ولا تطيب له الحياة إلا بالزوجة الصالحة .
- والمرأة لا تطمئن ولا تطيب لها الحياة إلا بالزوج الصالح .[تأسيس الأحكام 172/4]
~ከሱኒዮች ሰፈር......

https://t.me/Asselefya1
https://t.me/Asselefya1