💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
هدايات_القرآن_الكريم_للمرأة_المسلمة.pdf
3.8 MB
•••
- هِدَاياتُ القُرْآن الكريم لَلمرْأة المُسلمة

الشّـيخ عَبد الرّزاق البَدر حفِظه الله

ሴቶች ታነቧት ታስተነትኗት ዘንድ ግብዣዬ ነዉ 🌺


•━━━ ✽ • ✽ ━━━•
ሴቶች አበባ እና ጣፋጭ በጣም ይወዳሉ አሉ ! ባሎችዬ ስጦታ እየገዛችሁ ስጧቸዉ ! ስጦታ ፍቅርን ይጨምራል።

#በፍቅር እደሩልኝ


=
∙ አንዳንድ ሰዎች ግን የሰዉ መድሃኒት ናቸዉ። ከነሱ ጋር ስዓታት ታሳልፋለህ ሁሉ ነገር የተሻለ ሆኖ ይሰማሀል።

#صباح الخير
=
t.me/https_Asselefya1
🔖 ኪታቦች ሲፈልጉ ወደ "ሱቅ በደረቴ" ጎራ ይበሉ «ሁሉም አይነት ኪታብ» ከኛ ዘንድ ያገኛሉ።

╭┈──── ◖🇸🇦◗
╰┈➢
t.me/suk_bederete123

​ •┈┈•┈┈•⊰✿🇸🇦✿⊱•┈┈•┈┈•
ሳኡድ አረቢያ  ሁሉም ከተሞች እናቀርባለን
​
ሁለተኛ ማግባት…!?
|
~ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! በአሁኑ ጊዜ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት (ተዐዱድ) የሚፃፈውም የሚወራውም በዝቷል።

ይህ ርዕስ በኢስላም የተፈቀደ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጉዳዩን እጅግ ቀለል አድርገው ሲያቀርቡትና ሲያወሩት ይታያል።

አላህ ከ አንድ በላይ ማግባትን በ ቁርኣን የፈቀደው ከአንድ በላይ ማግባትን ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕን አብሮ በመደንገግ ነው።
«وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا»

«በየቲሞችም (ፍትሕን) አለማድረጋችሁን ብትፈሩ (ከሌሎቹ) ለእናንተ የተዋበላችሁን (ሴቶች) ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ በመካከላቸውም አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ የጨበጧትን (ባሪያ) ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡» ይላል።

ይህ አንቀጽ የንግግራችን ሁሉ መሰረት ነው። ፍቃዱ ከተሰጠ በኋላ ወዲያውኑ፦
"فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً"
(አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ) የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ ይመጣል።
«ብትፈሩ» (خِفْتُمْ) የሚለው ቃል ጥርጣሬንም ይጨምራል። ፍትሕን ስለማስፈኔ እርግጠኛ ካልሆንኩ ወይም ከተጠራጠርኩ፣ መንገዱ አንድ ብቻ ነው።አንድ ብቻ!
"فَوَاحِدَةً"
📌ፍትሕ እዚህ ላይ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
① የቁሳቁስ ፍትሕ፦
በሚስቶች መካከል በመኖሪያ ቤት፣ በቀለብ፣ በልብስ እና በሌሎችም ቁሳዊ ፍላጎቶች ላይ ፍጹም እኩልነትን ማሳየት።
② የጊዜ ፍትሕ፦
የማደሪያ ጊዜን በሚስቶች መካከል በእኩልነት መከፋፈል።ይህንን የፍትሕ ሚዛን መሳት የሚያስከትለው ቅጣት እጅግ ከባድ መሆኑን ነብያችን (ﷺ) አስጠንቅቀዋል፦
"مَنْ كَانَتْ لَهُ امْرَأَتَانِ فَمَالَ إِلَى إِحْدَاهُمَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَشِقُّهُ مَائِلٌ "
«ሁለት ሚስቶች ኖረውት ወደ አንደኛዋ (በአያያዝ) ያደላ ሰው፣ የቂያማ ቀን አንደኛው የሰውነቱ ክፍል ሽባ ሆኖ (ተዘምሞ) ይመጣል።»
📚(አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ እና ሌሎችም በሰሂህ ሰነድ ዘግበውታል)

እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ! በዚህ ከባድ ቅጣት ፊት እየቀለድን ነው? የአንዲትን ሀቅ በአግባቡ ሳንወጣ፣ ሁለተኛውን በደል ለመጨመር መሮጣችን ምን የሚሉት ነው።

ቆም ብለን እናስብ! ጉዳዩን የስሜት ማብረጃ ሳይሆን፣ ከባድ የዲን አደራ እንደሆነ እንገንዘብ።
📚ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
   "والأفضل مع قيامه بحق الواحدة الاقتصار عليها، وإنما أبيح التعدد لمن احتا؏ إليه ولم ‏يجاوز العدل"

«የተሻለውና በላጩ ሰውየው የአንዷን ሚስት መብት በአግባቡ የሚወጣ ከሆነ በአንዲት ላይ መብቃቃቱ ነው። ከአንድ በላይ ማግባት የተፈቀደው (አስገዳጅ)ፍላጎት ሲኖር እና ፍትሕን የማያጓድል ሲሆን ብቻ ነው።»
 
📚ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
   "ؼذا كان الإنسان لا يثق من نفسه بالعدل، أو يغلب على ظنه أنه لا يعدل، فإنه لا يجوز له أن يتزوج أك؍ع من واحدة، لقوله تعالى: (فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً)، فؼذا كان يخاف ألا يعدل، فإن التعدد يكون بالنسبة له حراماً."
«አንድ ሰው በራሱ ላይ ፍትሕን የማስፈን ብቃት እንደሌለው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ክልክል (ሀራም) ይሆንበታል። ምክንያቱም ጌታችን አላህ «አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ» ብሏል። ስለዚህ ፍትሕን መተግበር እንደሚፈራ ካወቀ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ሀራም ይሆናል።»

ንግግራቸው ግልጽ ነው፤ ፍትሕን የማስፈን ጥርጣሬ ካለ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ወደ ሀራምነት ይሸጋገራል።

📍ከአንድ በላይ ለማግባት ስታስብ ራስህን ልትጠይቃቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎች ይኖራሉ።ይህንን መንገድ ከማሰብህ በፊት፣ ልብህንና አቅምህን በእውነተኛነት ፈትሽ። የሰዎችን ግፊት ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታወችን ወደጎን ትተህ፣ በእጅጉ ከባድ በሆነው የፍትሕ ሚዛን ራስህን መዝን።

① የመነሻ ዓላማዬ ምንድን ነው?
• የምፈልገው ስሜቴን ለማርካት፣ በጓደኞቼ ፊት ለመፎከር…ወይንስ ከዚህ የጠለቀ፣ የቲሞችን ለመርዳት፣ ያላገቡ እህቶችን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ በፍትሕ ላይ የተመሰረተ ቤተሰብን ለማስፋት ያለኝ እውነተኛ የሸሪዓ ፍላጎት ነው?

② የመጀመሪያዋ ሚስቴ ሀቅ ሙሉ በሙሉ ተጠብቋል?
• አሁን ላለችው ሚስቴ ሙሉ መብቷን—በቀለብ፣ በጤና፣ በመልካም አኑዋኑዋር፣ በስሜታዊ ድጋፍ…በአግባቡ እየሰጠሁ ነው? በሷ ላይ ያለብኝን ሃላፊነት ሳልወጣ፣ ሌላ ከባድ ሃላፊነት ለመጨመር መሞከሬ በደል ላይ በደል መጨመር አይደለምን?

③ ሁለት ቤቶችን በእኩልነት የማስተዳደር የገንዘብ አቅሜ ምን ይመስላል?
• ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ቤተሰቦችን ያለ ምንም ችግር እና በእኩልነት ለማስተዳደር የሚያስችል የተረጋጋ ገቢ አለኝ? አንዷን እያብቃቃሁ ሌላኛዋን የማስርብ፣ ለአንዷ የተሻለ ቤት ሰጥቼ ሌላኛዋን በችግር የማኖር ከሆነ፣ የቂያማ ቀን ሽባ ሆኜ ከሚቀሰቀሱት እንደማልሆን ምን ዋስትና አለኝ?

④ ሁሉንም በእኩልነት የማስተናገድ የአካል፣ የጊዜ እና የስነ-ልቦና ዝግጁነት አለኝ?
• በሁለት ቤቶች መካከል ያለውን ውጣ ውረድ፣ የሁለቱንም ሚስቶች ስሜትና ፍላጎት የማስተናገድ የአዕምሮ ብስለትና ጥንካሬ አለኝ? በሚስቶች እና በልጆች መካከል የሚፈጠሩ ቅናቶችን እና አለመግባባቶችን በፍትሕና በጥበብ የመፍታት ብቃቱስ?

⑤ስለ ፍትሕ ምን ያህል ተምሬአለሁ?
• ቁርኣን እና ሐዲስ ስለ ፍትሕ የሚያስተምሩትን ትምህርት በጥልቀት አጥንቻለሁ? የዑለማዎችን ማብራሪያ አንብቤያለሁ? ፍትሕ ማለት በልብስና በምግብ እኩልነት ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ፊት፣ በንግግርና በአያያዝም ጭምር መሆኑን ተረድቻለሁ?

እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች ቆም ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። ምክኒያቱም ከአንድ በላይ ማግባት የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም፤ የጀግንነት መለኪያም አይደለም። በስሜት የሚወሰን ጊዜያዊ ፍላጎትም አይደለም። ይልቁንም፣ የቂያማ ቀን አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ከባድ አደራ እና ሃላፊነት ነው። ስለዚህ፣ ጉዳዩን ቀለል አድርገው ከሚያወሩ ሰዎች ንግግር በመራቅ፣ የዲኑን ጥልቅ አስተምህሮ እንረዳ።

አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን። ሃላፊነታችንን በአግባቡ የምንወጣና እርሱን በሚያስደስት መልኩ የምንኖር ያድርገን።
|•| t.me/AbuSufiyan_Albenan
𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
ሁለተኛ ማግባት…!? | ~ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! በአሁኑ ጊዜ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት (ተዐዱድ) የሚፃፈውም የሚወራውም በዝቷል። ይህ ርዕስ በኢስላም የተፈቀደ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጉዳዩን እጅግ ቀለል አድርገው ሲያቀርቡትና ሲያወሩት ይታያል። አላህ ከ አንድ በላይ ማግባትን በ ቁርኣን የፈቀደው ከአንድ በላይ ማግባትን ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕን አብሮ በመደንገግ ነው።…
በትኩረት በማንበብ ራሳችሁ ፈትሹ ያ ሸባብ !

👉ማግባት የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም።
👉የጀግንነት መለኪያ አይደለም።
👉በስሜት የሚወሰን ጊዜያዊ ፍላጎት አይደለም።
👉ይልቁንም የቂያም ቀን አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ከባድ አደራ ነዉ።

👆👆👆👆👆👆👆👆👆
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀምሌ ነዉእኮ .... እንረስ 🖐 በሬዎቹ ግን ሲያሳዝኑ ዝናቡ ዘነበባቸዉ ህእ¡
ጓደኛ እንደ መሰላል ነው ወይ ወደላይ ያወጣካል ወይ ወደታች ያስወርድካል ስለዚህ መሰላልክን ምረጥ!!

||
t.me/https_Asselefya1
~ ራስን መግዛት የሚጀምረዉ  ሃሳብን ከመቆጣጠርነዉ፣ የምታስበዉን  መቆጣጠር ካልቻልክ  የምታደርገዉን  ልትቆጣጠር አትችልም።

=
t.me/https_Asselefya1
እኔ አሁን ድረስ የሚቆጨኝ ፦  ከቤተሰብ ስንጣላ እነሱን የጎዳን እየመሰለን ምግብ አልበላም የምለዉ ነገር......    እኔጋ ብቻ ነዉ ግን ?

=
منقول