💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞ ➖〰➖〰➖〰➖〰 ÂŤ ክፍል  ⓹ Âť ↷ከሙናፊቆች ጋር ተባብሮ መስራት ብይኑ↶ ◉ قال تعاى: { سَیَحۡلِفُونَ بِٱللَّهِ لَكُمۡ إِذَا ٱنقَلَبۡتُمۡ إِلَیۡهِمۡ لِتُعۡرِضُوا۟ عَنۡهُمۡۖ فَأَعۡرِضُوا۟ عَنۡهُمۡۖ إِنَّهُمۡ رِجۡسࣱۖ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُ جَزَاۤءَۢ بِمَا كَانُوا۟ یَكۡسِبُونَ…
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞
➖〰➖〰➖〰➖

«ክፍል  ⓺ Âť

ከሙናፊቆች ጋር መስራት ብይኑ ከትላት የቀጠለ!


⇘አላህ  ምእምናንን ወደ ከሐድ ዉሸታም ሙናፊቆች እንዳይዘነበሉ እነርሱን ጓደኛና ወዳጂ  አድርገዉ እንዳይዙ በጥብቅ ያስጠነቅቃል።

⇘አላህ የእርሱን ቃል አፍርሶ ከእነርሱ ጋር እነርሱ በአንቀፁና በተአምራቱ ሊያሾፉና ሲያላግጡ አብሮ የተቀመጠና ከእነርሱ ጋር የሆነ ሰዉ ከእነርሱ ምንም አይነት ልዩነት እንደሌለዉና ከእነርሱ ጋር እንደሆነ ሲናገር እንድህ ይላል፦

◉ قال تعالى:{ وَقَدۡ نَزَّلَ عَلَیۡكُمۡ فِی ٱلۡكِتَـٰبِ أَنۡ إِذَا سَمِعۡتُمۡ ءَایَـٰتِ ٱللَّهِ یُكۡفَرُ بِهَا وَیُسۡتَهۡزَأُ بِهَا فَلَا تَقۡعُدُوا۟ مَعَهُمۡ حَتَّىٰ یَخُوضُوا۟ فِی حَدِیثٍ غَیۡرِهِۦۤ إِنَّكُمۡ إِذࣰا مِّثۡلُهُمۡۗ إِنَّ ٱللَّهَ جَامِعُ ٱلۡمُنَـٰفِقِینَ وَٱلۡكَـٰفِرِینَ فِی جَهَنَّمَ جَمِیعًا }

⇘አላህ እንድህ ይላል፦
በእናንተም ላይ በመፀሀፉ ዉስጥ የአላህን አንቀፆች  በርሷ ሲካድበትና በርሷም  ሲላገጥበት በሰማችሁ ግዜ በሌላ ወሬ ዉስጥ እስከሚገቡ ድረስ ከእነርሱ ጋር አትቀመጡ።ማለትን በእርግጥ አወረደ። እናንተ ያን ግዜ  አምሳያዎቻቸዉ ናችሁኒ።አላህ መናፍቃንን እና ከሐደሐዎችን በሙሉ በገሀነብ ዉስጥ ሰብሳቢ ነዉ ።(አንኒሳዕ፡140)


⇲አላህ በዚህ አንቀፀ ላይ በታምራቶቹ በሚያሾፉት እና በሚያጋልጡት ጋር መቀማመጥና እነርሱን መዉደድ መጥፎ ተግባር ሲሰሊ አይቶ የማይከለክልን ሰዉ  ከእነርሱ ጋር እኩል ወንጀለኛ እና ጥፍተኛ አድርጎ ቆጥሮታል፣እዚት በዱኒያ ላል በአላህ አንቀፀ ለማሾፍና ለማላገጥ እንደተሰበሰቡትም ነገ በመጨረሻ ቀን አላህ በገሀነብ እሳት ዉስጥ ከከሐዲዎች ጋር ይሰበስባቸዋል።

    «ሙናፊቆችን  ማጋለጥ»
   〰〰〰〰〰〰〰〰

☞ የሙናፊቆች ቁጥር መዝገብ ማገላበጥ፤ ያላቸዉ መጥፎ አድራጎትና ተግባር ለሙእሚኖች ማሳወቅና  ሙእሚኖች ከእነዚህ መጥፎ ሰዎች ማስጠንቀቅ፣የእነሱን ድብቅ ሚስጥር እያወጡ ማጋለጥ፤እነርሱን ማዋረድና ማሳፈር አላህ እና መልዕክተኛዉ ﷺየተከተሉት መንገድ ነዉ።

☞አላህ በሱረቱ አት_ተዉባ (አል_ፋድሃ)አዋራጇ በመባል በምትጠራዉ ምእራፍና በሱረቱል በቀራህ ይባስ ብሎም በስማቸዉ ሱረቱል ሙናፊቁን /የመናፍቃኖ ምዕራፍ ተብላ በምትጠራዉ/ምእራፎች ላይ ሾለ እነሱ ምንነት  ማንነት አበጥሮና አንጠርጥሮ በዝርዝሮ ለሙእሚኖች አቅርቧል። መልዕክተኛዉንም ﷺ፦

قال تعالى: { یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ جَـٰهِدِ ٱلۡكُفَّارَ وَٱلۡمُنَـٰفِقِینَ وَٱغۡلُظۡ عَلَیۡهِمۡۚ وَمَأۡوَىٰهُمۡ جَهَنَّمُۖ وَبِئۡسَ ٱلۡمَصِیرُ }

☞አንተ ነብዩ ሆይ!  ከሐድዎችንና መናፍቃንን ታገል። በእነርሱም ላይ ጨክን። መኖሪያቸዉም ገሀነም ናት ። መመለሻይቱም ከፍች።( አት_ተዉባህ :73) በማለት  እነርሱን መዋጋትና መታገል እንዳለባቸዉ አዟቸዋል።

☞አላህ  በበቀራህ ምእራፍ ላይ ሾለ ሙእሚኖች አራት አያህ/አንቀፀ/ ሾለ ከሀድዎች 2አንቀፀ ሲጠቅስ ስለሙናፊቆች ግን  አስራ ሶስት አያህ ነዉ  ያብራራዉተ ይህም የሆነበት  የእነርሱን ብዛትና መጥፎነት አላህ ለሙእሚኖች ሊያብራራያ ሊተነትን ነዉ።

☞ምክንያቱም ሙናፊቆች በእስልምና ጥላ ሾር ሙስሊም መስለዉ  ተጠልለዉ፣የእስልምናን ባንድራ/አርማ/አዉለብልበዉ፤ በሙስሊም ምሽግ ተከልለዉ፣በሙስሊሞች መሳሪያ እስልምናንና ሙስሊሞችን የሚያጠቁና  የሚዋጉ ሙስሊም ህብረተሰብ በቀላሉ ሊቃወሟቸዉና ሊለያቸዉ የማይችሉ የእስልምናና የሙስሊሞች ጥላት በእስልምና ጉዳይ ስም የእስልምና ገዳይ አረመኔዎች ስለሆኑ ነዉ።

✎ሙስሊም የሆነ ሰዉ ሙናፊቆችን ማድረግ ያለበት ወደፊት ሳይሆን ወደ ኋላ፤ማሳደግ ሳይሆን ማሳነስ፣ማቅረብ ሳይሆኖ ማራቅ፤መዉደድ ሳይሆን መጥላት ፣ማሞገስ ሳይሆን ማዋረድ ነዉ።

✎ምክንያቱም ሙናፊቆች የአላህ እና የመልዕክተኛዉ ጠላቶች የምእምናን ባላጋራዎች ናቸዉ።ሙስሊም የሆነ ሰዉ ለሙናፊቆች ምንም አይነት እርዳታና ትብብር  ሊያደርግ አይፈቀድለትም።

📔ይቀጥላል ኢንሻ አላህ...........

↶↷↶↷↶↷↶↷↶↷↶↷↶
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
🛑👉አንድ ሴት ሰለፍይ ወይም ሷሊህ ደግ ናት ማለት ወንጀል የማትሰራ የማትሳሳት ጥቡቅ ናት ማለት አይደለም። ነገር ግን፦

☞ሲያስታውሷት ትነቃለች
☞ሲመክሯት ትቀበላለች
☞ከስህተቷ ትመለሳለች
☞ለወንጀሏ እስቲግፋር ትጠይቃለች።


𝐓𝐞❝ t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
አንዴ ጆሮ ስጪ!!

ሸይኽ ዶ/ር ሷሊህ አልፈዉዛን ሃፊዞሁላህ ይመክሩሻል……

ሙስሊሟ ሆይ!

ሒጃብ፤ ልባቸዉ የታመመ የሰዉ ውሾች ከሚወረውሯቸዉ የተመረዙ እይታዎች ይጠብቅሻል። የተነሳሱ መጥፎ ምኞቶችንም ያከስማል። ሒጃብሽን አጥበቀሽ ያዢ።
ሒጃብን የሚዋጉና አስፈላጊነቱን አቅልለዉ የሚያቀርቡትን እኩይ ተልእኮ ያላቸዉ ሰዎች አሉባልታዎች አታዳምጪ። ላንቺ መንገድን እንጂ እንደማይፈልጉም አትጠራጠሪ።

ላቅ ያለዉ ጌታሽ አላህ እንዳለዉ⬇️

ﻭَﻳُﺮِﻳﺪُ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺘَّﺒِﻌُﻦَ ﺍﻟﺸَّﻬَﻮَﺍﺕِ ﺃﻥ ﺗَﻤِﻴﻠُﻮﺍ ﻣَﻴْﺎﻻً ﻋَﻈِﻴﻤﺎً
{እነዚያም ስሜቶቻቸዉን የሚከተሉት (ከዉነት) ትልቅን መዘንበል እንድትዘነበሉ ይፈልጋሉ።}
ሱረት አልኒሳእ 27

🔘📚ተንቢሀት አላ አህካሚን ተኽተሱ ቢል ሙእሚናት ገፅ 46

⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱
https://t.me/alruqyehsheriyeh
⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰
«ማንኛዋም ሴት ባሏ በእሷ ተደስቶባት ከሞተች፤  ጀነት ገባች።» ረሱል  (ቲርሚዚይ ዘግበውታል!)
አክስት መሆን የሌለ ደስ ይላል ስሜቱ የምር የአክስትነት ሀቅ የምንወጣ ያድርገን!

ስደት ከመጣሁ የተወለዱ አሁን አድገዉ አክስቴ ሲሉ አፍቸዉ መጣፈጡ የምር ዉድ ወንድሞቼ አክስት ስላደረጋችሁኝ ደስ ብሎኛል አላህ ይጠብቃችሁ!!

=
ከሽፉ ሹቡሓት 010
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
🎈መትን ከሽፉ ሹቡሓት

【 ክፍል  ➉ 】

🎙«𝐁𝐲 𝐀𝐛𝐮 𝐑𝐞𝐲𝐲𝐢𝐬 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐢𝐦𝐚𝐦 »

          √ የኪታብ 𝕡𝕕𝕗↓↓
t.me/https_Asselefya1/13134
ወንድ ልጅ እናቱ ስትወልደው
የተሰማት ህመሞች ቢሰማው ኖሮ
ምንም ያህል ምክኒያቶች ቢገዝፉም
አንድም ቀን ሴትን ልጅ አያሳዝንም ነበር!።

t.me/abdu_rheman_aman
ከሽፉ ሹቡሓት 011
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢማም
🎈መትን ከሽፉ ሹቡሓት

【 ክፍል  ➀➀ 】

🎙«𝐁𝐲 𝐀𝐛𝐮 𝐑𝐞𝐲𝐲𝐢𝐬 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐢𝐦𝐚𝐦 »

          √ የኪታብ 𝕡𝕕𝕗↓↓
t.me/https_Asselefya1/13134
«ወላጂ ምን ያድርግሽ?»
➖➖➖➖➖➖➖➖

ተይ ልጄ ቀስ በይ እያሉ ሲመክሩሽ፣
አልሰማም አልሽና በሚድያ ሰክርሽ፣
ሙግት ትይዧለሽ አገባለሁ ብለሽ፣
በንግግር ብቻ ወንድ ልጅን አምነሽ፣
የወላጅን ልፋት እደቀላል አይተሽ፣

ቤተሰብ ለልጁ እደመይሳሳ አድርገሽ፣
ከለከሉኝ ብለሽ ደግሞ ታለቅሻለሽ፣
ይገርማል እህቴ ምነዉ ሶብር አጣሽ፣
የወጣሽበትን አላማ ዘነጋሸ?፣
የስደት እንግልት ድካሙን እረሳሽ፣

በተለይ በተለይ ገጠር የተወለድሽ፣
የአባትን ስቃይ መከራዉን ያየሽ፣
የእናትን ለቅሶ ዱዓዋን የሰማሽ፣
ተይ አታስከፊያቸዉ እህቴ ልንገርሽ፣

ዛሬ ብትማሪም ዛሬ ያወቅሽ መስሎሽ፣
ዘመናዉይነት ስልጣኔ መስሎሽ፣
ድምፅ መቀያየር ከተሜነት መስሎሽ፣
የተጓሺዉ ስደት ቤተሰብ ካስረሳሽ፣


↷ይቀጥላል ..........

✍️ሶላሁዲን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞 « t.me/selahudin_Islamic_knowlages
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
عمل المرأة من سبب ضياع الأولاد

الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
t.me/https_Asselefya1
ፈገግ እያላችሁ ተማሩበት ለብርዱ


«ባንች እንዳልሞት»
-----------------
በትግል ነው ለመኖር ስል፤
              የታገስኳት የሞት ሞቴን፡
ባታውቅ እንጂ፤
ለርሷ ስል ነው የሰዋሁት እኔነቴን፡
〰️〰️〰️〰️
የዘመኔን እኩሌታ፤
           ለሡ ፍቅር እንደ ባሪያ፡
ከላጤነት ለመላቀቅ፤
              ብትሆን ብዬ መከበሪያ፡
ሚስቴ ብዬ ያገባኋት፤
          ፊት ሰጥታኝ ነው መጀመሪያ፡
〰️〰️〰️〰️
ሳላውቅበት ያለ ቀመር፤
                   ተነጥፌ ስንከረፈፍ፡
ለሷ ደስታ እየባከንኩ፤
                     እንደ ንፍሮ ስጠነፈፍ፡
ለሰከንዶች ቢሆን እንኳን፤
                    ከውደታ ሳልዛነፍ፡
ከሷው ብሶ ብልጥ ሆና፤
                     ቆጠረችኝ እንደ ሰነፍ፡
〰️〰️〰️〰️
➥ታዲያ.....
------------
እችላለሁ ምንም አልል፤
              ይህን መልዕክት አቀብሏት፡
ምንም ብትል መልስ አልሰጥም፤
                           ይብላኝልሽ ብሏል በሏት፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መራር ፊቷን ት'ጠ'ብ'ና፤
                   ትል'ነቷን ትግደልበት፡
ከሸፋፋው እግሮቿ ስር፤
                       ጫማ አድርጋ ትሒድበት፡
〰️〰️〰️〰️〰️
በአፍታ መሳቅ፤
ባፍታ መናቅ መሰንበቻ ከመሰልኳት፡
በዱባ-ሞት እባካችሁ፤
በቁም ነገር ንገሩልኝ እንደተውኳት፡
〰️〰️〰️〰️〰️
በግርጭርጭ ፀባይሽ ልክ፤
                  ሁሌ አልኖርም በአግራሞት፡
ላንች ያለኝ ልዩ ቦታ፤
         ፈሶ አለቀ እንደ ሀሞት፡
በቃ ተይኝ ትቸሻለሁ፤
               ተናድጀ ባንች እንዳልሞት፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️
.....✍️ኑር ነኝ የፋሩቅ አባት
〰️〰️〰️〰️〰️
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi