💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን 〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰 ✅ ክፍል  ➃ ስለዚህ ጂብሪል ከራሱ ሳይሆን ከጌታ ተቀብሎ ነው ይዞት የወረደው። እንጂ ቁርኣኑ የአላህ ንግግር ለመሆኑማ እንዲህ ተነግሮናል’ኮ፡ { وَإِنۡ أَحَدࣱ مِّنَ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ٱسۡتَجَارَكَ فَأَجِرۡهُ حَتَّىٰ یَسۡمَعَ كَلَـٰمَ ٱللَّهِ } ከአጋሪዎቹም አንዱ ጥገኝነትን ከጠየቀህ…
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን
   〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰


✅  ክፍል  ➄

➴⇘በነገራችን ላይ ይሄ በቁርአን ላይ ያላቸዉ እምነት ቁርአን  ፍጡር ነው”  ከሚለው የሙዕተዚላ እምነት ጋር አንድ ነው። እንደሚታወቀው ጂብሪልም ይሁን ሙሐመድ ፍጡሮች ናቸው። የፍጡር ንግግር ፍጡር ነው። ስለዚህ ይሄ በእጃችን ላይ ያለው ቁርኣን ፍጡር ነው ማለት ነው፣ እንደነሱ እሳቤ። ታዲያ ይሄ እነ ኢማሙ አሕመድን ያንገላቱት ሙዕተዚላዎች እምነት አይደለምን?! ጁወይኒ እንደመሰከረው በዚህ ጉዳይ ላይ በአሽዐሪያና በሙዕተዚላ መካከል ያለው ልዩነት የአገላለፅና የስያሜ እንጂ በፅንሰ ሀሳብ አንድ ናቸው። [አልኢርሻድ፣ አልጁወይኒ፡ 116-117]
[አልመዋቂፍ፣ ኢጂ፡ 293-294]


➴⇘ ኢማሙ ማሊክ፣ ለይሥ ኢብኑ ሰዕድ፣ ሱፍያን ብኑ ዑየይና፣ አቡበክር ብኑ ዐያሽ፣ ወኪዕ ብኑ ጀራሕ፣ ኢብኑል ሙባረክ፣... ቁርኣን ፍጡር ነው የሚል ሰው ከሃዲ እንደሆነ አስረግጠው ከተናገሩ በርካታ ታላላቅ አኢማዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ናቸው። [ላለካኢ፡ ቁ. 412]

➴⇘ ቁርኣን የአላህ ንግግር ለመሆኑ ልቡ ላልተበከለ ሁሉ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ የለውም። የአላህ ንግግር የራሱ መገለጫ (ሲፋህ) ነው። የአላህ መገለጫዎችን ደግሞ ልክ እውቀቱን፣ መስማቱን፣ ማየቱን፣ መቻሉን፣… “ፍጡር ናቸው” እንደማንል ሁሉ መናገሩንም ፍጡር ነው ልንል አንችልም። ይሄ በጣም ግልፅ ነገር ነው። የአላህ ንግግር ፍጡር እንዳልሆነ ከሚጠቁሙ ማስረጃዎች አንዱ ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ማለታቸው ነው፡

▪إذا نزا أحدكم منزلا فليقل أعوذ بكلمات الله التامات من شر ما خلق ..


“አንዳችሁ የሆነ ቦታ ሲያርፍ ጊዜ ‘ሙሉ በሆኑት የአላህ ንግግሮች እሱ  ከፈጠራቸው ተንኮሎች እጠበቃለሁ’ ይበል።” [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 7054] 

↷⇘ይስተዋል! በፍጡር ጥበቃን መሻት ከኢስላም የሚያስወጣ ትልቅ ሺርክ ነው። ከለላየሚጠየቀው ከአላህ ብቻ ነውና። በአላህ ንግግሮች መጥጠበቅ ሺርክ ቢሆን ኖሮ ነብዩ صلى الله عليه وسلم” ሙሉ በሆኑት የአላህ ንግግሮች እጠበቃለሁ” እንድንል ባልመከሩን ነበር። በፍጡር መጥጠበቅ ጥፋት እንጂ ልማት የለውምና። ጌታችን እንዲህ ይላል፦

{ وَأَنَّهُۥ كَانَ رِجَالࣱ مِّنَ ٱلۡإِنسِ یَعُوذُونَ بِرِجَالࣲ مِّنَ ٱلۡجِنِّ فَزَادُوهُمۡ رَهَقࣰا }

እነሆም ከሰዎች የሆኑ ወንዶች ከጂኖች በሆኑ ወንዶች ይጠበቁ ነበር። መሸበርንም ጨመሯቸው። [አልጂን፡ 6]

➴⇘ እነዚህ የቢድዐ አቀንቃኞች ከመነሳታቸው በፊት ቁርኣን የአላህ ንግግር በመሆኑ ላይ አንድም ልዩነት አልነበረም። አቡበክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ፡- የሮማንና የፋርስን ጦርነት አስመልክቶ ሮማውያን ያሸንፋሉ ብለው ከመካ አጋሪዎች ጋር ተወራርደው ነበር። ሮማውያን ሲያሸንፉ ጊዜ አቡበክር የመካ ሙሽሪኮች ላይ ይህንን ጉዳይ የሚመለከተውን የቁርኣን መልእክት አነበቡላቸው።
(ሱረቱ ሩም ከአንቀፅ አንድ ጀምሮ ያለውን ማለት ነው።) “ይሄ ያንተ ንግግር ነው ወይስ የጓደኛህ (የሙሐመድ) ንግግር ነው?” ብለው ሙሽሪኮቹ ሲጠይቁ አቡበክር እንዲህ ብለው መለሱላቸው፡

▪ليس بكلامي ولا كلام صاحيبي  ولكنه كلام الله ؚز وجل....

“የኔ ንግግር አይደለም። የጓደኛዬ ንግግርም አይደለም። ነገር ግን የአላህ - ዐዘ ወጀል - ንግግር ነው።” [አሱና፣ ዐብደላህ ብኑ አሕመድ፡ ቁ. 116] በይሀቂ ሶሒሕ ብለውታል። [አልስማእ ወሲፋት፣ በይሀቂ፡ ቁ. 510

✍️ኢንሻ አላህ ይቀጥላል........

↷ወደ አቡ ሂበቲላህ ቻናል ይቀላቀሉ↶
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ለሚስትህ ፍቅርህን ግለጽላት አንቺም እንደዛዉ
abdu shikur abu fewzan
"ሚስትህን አፈቅርሻለሁ በላት፡፡

አፈቅርሻለሁ ብሎ መዋሸት እንዴት ይታያላ?"

🎙አብዱ ሽኩር አቡ ፈዉዛን

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur
☞ከትዝታ ሰፈር ማነዉ እነኚህ ጠብቆ ያደገ........
አባታችን አደምን አሏህ ከፈጠራቸው በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀሙት ነገር ምንድን ነው!?
Anonymous Quiz
22%
አለቀሱ
4%
ሳቁ
63%
አነጠሳቸው
11%
ተነጋገሩ
ማንነትክን በወሬ ሳይሆን በተግባር አሳይ ! ንግግር ሊዋሽ ይችላል ድርጊት ግን ሁሌም እውነትን ይመሰክራል።»

✍️
አንዳዴ ሰነፍ ሰዎች ሰንፈዉ ያሰንፍሉ¡¡

➬በየ ቀኑ ቂርአት እርማት ላይ የማዳም ስራ ሰለቸኝ ደከመኝ ሳይሉ የሚተጉ እህቶች አድናቂ ነኝ ጀግኖች ወላሂ የተባረከ ስራ ላይ ናችሁ ጠንክሩ ግዜዉ እንጠቀምበት ነገ ሀገር ሄደን በሰራሁት ኖሮ ብለን የምንለድምበት ሳይሆን ደግ እንኳን ሰራሁት ብለን የምንደሰትበት አሻራ ጥለን ለማለፍ ጠንክሮ መስራት ነዉ። "አላህ ያጠንክራችሁ"

✍️

https://t.me/https_Asselefya1
አንዳዴ....

ለመቅረብ ፈርተን ግን ቀስ ብለን ቀርበናቸዉ ብዙ ያሉብን ክፍተቶች ደካማ ጎኖች አርመዉን ሂወታችን ለመስተካከል ሰበብ የሚሆኑ ምርጥ ሰዎች አሉ!!

🌿
ተዉሒድ የገባችሁ መስሎኝ ነበር...
በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
☞ተዉሒድ የገባችሁ መስሎኝ ነበር...!!

🎙በ𝐔𝐬𝐭𝐚𝐳 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐌𝐮𝐧𝐞𝐰𝐨𝐫

↷↷↷↷↷⇊🍃⇊↶↶↶↶
http://t.me/https_Asselefya1
☞ምርጥ ሰዎች ሁለየም ምርጥ ናቸዉ። አላህ ከምርጦች ያድርገን!! አማን እደሩ¡¡
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን    〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰 ✅  ክፍል  ➄ ➴⇘በነገራችን ላይ ይሄ በቁርአን ላይ ያላቸዉ እምነት ቁርአን  ፍጡር ነው”  ከሚለው የሙዕተዚላ እምነት ጋር አንድ ነው። እንደሚታወቀው ጂብሪልም ይሁን ሙሐመድ ፍጡሮች ናቸው። የፍጡር ንግግር ፍጡር ነው። ስለዚህ ይሄ በእጃችን ላይ ያለው ቁርኣን ፍጡር ነው ማለት ነው፣ እንደነሱ እሳቤ። ታዲያ ይሄ እነ ኢማሙ አሕመድን…
👉እዉን ቁርአን የአላህ ንግግር አይደለምን
   〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖
〰

✅ ክፍል  ➅ የመጨረሻ

☛በይሀቂይ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ከዚህ የተለየ በሶሐባም በታቢዒዮችም ዘመን ከአንድም ሰው አልተገኘም።” [አልአስማእ ወሲፋት፡ ቁ. 562] ለዚህ ደግሞ “ከሰባ አመት በፊት የመልእክተኛውን صلى الله عليه وسلم ሶሐቦችና ከነሱም በታች ያሉትን ‘አላህ ፈጣሪ ነው። ከሱ ሌላ ያለ ፍጡር ነው፣ ቁርኣን ሲቀር። ቁርኣኑ የአላህ ንግግር ነው። ከሱ ወጥቷል፤ ወደሱም ይመለሳል’ እያሉ አግኝቻለሁ” የሚለው የታዋቂው ታቢዒይ ዐምር ብኑ ዲናር ንግግር ዋቢ መሆን ይችላል። ከሱፍያን ብኑ ዑየይናህ እና ከአቡበክር ብኑ ዐያሽም ተመሳሳይ ንግግር ተገኝቷል። [ሙኽተሶሩል ዑሉው፡ 164፣ 166]

☞በርካታ ቀደምት የኢስላም ሊቃውንት “ቁርኣን ፍጡር ነው አንልም” በማለታቸው
ሳቢያ ግድያ፣ ስቃይና እንግልት አስተናግደዋል። ቁርኣንና ሐዲሥን በሶሐቦች ግንዛቤ በመታገዝም ፈተናውን በፅናት ተወጥተዋል። ይህም ጉዳዩ ምን ያክል ቀላል እንዳልሆነ ነው የሚያሳየን። አንድ ድንቅ ምሳሌ እንውሰድማ።
በጊዜው በርካታ የሱና ዑለማዎችን ሲያንገላታ የነበረው ኸሊፋው አልዋሢቅ ወህኒ ካጎራቸው ሰዎች ውስጥ አንድ ሽማግሌ ትዝ ይሉትና “ያንን ሽማግሌ አምጡልኝ” ይላል። እጆቻቸው እንደታሰሩ ቀረቡ። ከፊቱ ሲቆሙ ሰላምታ አቀረቡለት። ኸሊፋው አልመለሰም።

☞ሽማግሌው፡ “የሙእሚኖች መሪ ሆይ! የአላህንም የመልእክተኛውንም صلى الله عليه وسلم አስተምህሮት በኔ ላይ ተግባራዊ
አላደረግክም። የላቀው አላህ፡ በሰላምታ  በተከበራችሁም ጊዜ ከርሷ ይበልጥ ባማረው (ሰላምታ) አክብሩ። ወይም (እሷኑ)  መልሷት ይላል። ነብዩም صلى الله عليه وسلم ሰላምታን በመመለስ አዘዋል” አሉት።

☛ኸሊፋው፡ “ወዐለይከ ሰላም” ካለ በኋላ ፈታኝ አድርጎ ያዘጋጀውን ኢብኑ አቢ ዱኣድን፡
“ጠይቀው!” በማለት ሽማግሌውን እንዲፈትን
አዘዘው።


☞ሽማግሌው፡ “የሙእሚኖች መሪ ሆይ! እኔ የተጠፈርኩ እስረኛ ነኝ። በእስር ላይ ውሃ ተከልክዬ በተየሙም ነው የምሰግደው። የታሰርኩበት ይፈታልኝ ዘንድ እዘዝልኝ። ውዱእ የማደርግበት ውሃም እዘዝልኝና አድርጌ ልስገድ። ከዚያ በኋላ ጠይቀኝ” አሉት። የታሰሩበት እንዲፈታላቸው አዘዘ። ውሃም አዘዘላቸውና ውዱእ አድርገው ሰገዱ። ከዚያም ለፈታኙ ኢብኑ አቢ ዱኣድ “ጠይቀው!” አለ። ሽማግሌው ግን የዋዛ አልነበሩም። “ጥያቄ ለኔ ይሁን። መልስእንዲሰጠኝ እዘዘው” አሉት።

☛ኸሊፋው፡ “ጠይቅ” አላቸው።

☞ሽማግሌው፡ እድሉን ሲያገኙ ኢብኑ አቢ ዱኣድን አጣደፉት። “እስኪ ንገረኝ። ይሄ
‘ቁርኣን ፍጡር ነው’ እያላችሁ ሰዎችን የምትጣሩበት ጉዳይ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የተጣሩበት ጉዳይ ነውን?” አሉት።
ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

☛ሸይኹ፡ “ጥሩ። ከሳቸውስ በኋላ አቡበክር ሲዲቅ የተጣሩበት ነገር ነውን?” አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ። (አይደለም ማለቱ ወዶ አይደለም። “አዎ” ካለ የከፋ መፋጠጥ
ስለሚከተለው ነው።)


☞ሸይኹ፡ “ጥሩ። ከነሱስ በኋላ ዑመር ብኑል ኸጧብ የተጣሩበት ነገር ነውን?”  አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

☛ሸይኹ፡ “መልካም። ከነሱስ በኋላ ዑሥማን ብኑ ዐፋን የተጣሩበት ነገር ነውን?” አሉት። ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

☞ሸይኹ፡ “መልካም። ከነሱስ በኋላ ዐልይ ብኑ አቢ ጧሊብ የተጣሩበት ነገር ነውን?”  ሲሉት ኢብኑ አቢ ዱኣድ፡ “አይደለም” አለ።

☛ሸይኹ፡ “የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ያልተጣሩበት ነገር፣ አቡ በክርም፣ ዑመርም፣ ዑሥማንም፣ ዐልይም - ረዲየላሁ ዐንሁም - ያልተጣሩበትን ነገር አንተትጣራበታለህን?

☞መቼም ‘ያውቁት ነበር’ ወይ ደግሞ ‘አያውቁትም ነበር’ ከማለት ውጭ ምርጫ የለህም። ‘ያውቁት ነበር ግን ሳይጣሩበት ዝም ብለዋል’ ካልክ እኛንም አንተንም እነሱን የበቃቸው ዝምታ ይበቃናል። ‘አይ አያውቁትም ነበር እኔ ግን አወቅኩት’  ካልክ አንተ ውዳቂ የውዳቂ ልጅ! አንድን ነገር ነብዩ صلى الله عليه وسلم እና ቅን ምትኮቻቸው - ረዲየላሁ ዐንሁም - ሳያውቁት አንተናባልደረቦችህልታውቁት ነውን?” አሉት።

☞ኸሊፋው፡ አፉን በልብሱ በማፈን እየሳቀ ተነሳ። ከዚያም እንዲህ አለ፦ “እውነቱን
ነው። ወይ ‘ያውቁት ነበር’ ወይ ደግሞ
‘አያውቁትም ነበር’ ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫ የለም።
‘ያውቁት ነበር ግን ሳይጣሩበት ዝም ብለዋል’ ካልክ እኛንም አንተንም እነሱን የበቃቸው ዝምታ ይበቃናል። ‘አይ አያውቁትም ነበር እኔ ግን አወቅኩት’ ካልክ አንተ ውዳቂ የውዳቂ ልጅ! አንድን ነገር ነብዩ صلى الله عليه وسلم እና ቅን ምትኮቻቸው - ረዲየላሁ ዐንሁም - ሳያውቁት አንተና ባልደረቦችህ ልታውቁት ነው?” አለ።[አሸሪዐህ፡ 53-54]

☞ልክ እንዲሁ ቁርኣን የአላህ ንግግር መሆኑን የሚያስተባብሉ ጠማሞችን እንዲሁም የአላህን መገለጫዎች (ሲፋት) የሚያራቁቱ የጀህሚያ ወራሾችን የሰለፎቹን ግንዛሬ በመጠቀም መፈናፈኛ ማሳጣት ይገባል። ይሄ ርእስ እጅግ በርካታ ህዝብ የተፈተነበት ጉዳይ በመሆኑ በምትችሉት ሁሉ በማሰራጨት የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በአላህ ስም እጠይቃለሁ። ወሶለላሁ ወሰለም ዐላ ነቢይና ወኣሊሂ ወሶሕቢሂ ወሰለም። ተፈፀመ።

✍️ተፃፈ በኢብኑ ሙነወር እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር 2005 ላይ ተፅፎ ዛሬ ሚያዚያ 14/2015 በመጠኑ ተነካክቶ የወጣ።


       ↶✍️↶  أم عثيمين بنت أعاغاو الولوية
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
👉ከኩሽና ርቆ እንዲች ያለች ቦታ ቂርአት ናፍቆናል......✍️ ጀሊሉ ነጃ በለን ከኩሽና....!

https://t.me/https_Asselefya1
➬ አላህ ሰለፍያህ ባል ከወፈቀሽ.........

𝐓𝐞 ≈ https://t.me/https_Asselefya1
"ኡስታዝ" ነው የሚለው እና ፀባዩ " ሸጋ" ነው የሚሉት ነገሮች የሚለያዩ ነገሮች ናቸው። ሁለቱም ባንድ ላይ ላይገኙ ይችላሉና አጣርተሽ ግቢ ለማለት ያክል ነው።
منقول
🌿✍️
قال الإمام ابن القيم رحمه الله :

‏من ك؍عت همومُه وغمومه
‏فلكثر من قـول :  ‏لا حـول ولا قـوة إلا باللـه.
‏ زاد المعاد 183/4

🍁 ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል :-
" ጭንቀቱና ትካዜው የበዛ ሰው ላ ሀውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂ : የሚለውን ዚክር ያብዛ "
ዛዱል መዓድ ( 4/183 )

𝐓𝐞~ t.me/https_Asselefya1
✍️ حياءُ المرأةِ حياتُها !

✮ የሴት ልጅ ሀያዕ አይናፋርነቷ ሂወቷ ነው።
መስፈርት ካልተሟላ 100አመት ቢሰጠዉ ኡማዉ አንድ ማድረግ አይቻልም!
ወንድም ሳዳት ከማል حفظه الله
👉መስፈርቱ ካልሟላ 100 አመት ቢሰጠውም ኡማውን አንድ ማድረግ አይችልም፡፡

🎙በወንድም ሳዳት ከማል حفظه الله

http://t.me/https_Asselefya1
☞ እህቴ ቂርአት ከበደኝ ብለሺ ከቂርአትቦታ እንዳትርቂ ጠበቅ አድርገሺ ያዢዉ አይዞሺ ታሸንፊዋለሺ!!የምን ተስፍ መቁረጥ  ቀርተሺ ያለፍሺዉን እንደት እንዳፍለሺዉ ዘወር ብለሺ አስቢና  ከዛ የጀመርሺዉን  ጠበቅ አድርገሺ ያዢዉ አይዞሺ ዉዷ!! ✍️𝐔𝐦𝐮 𝐔𝐬𝐞𝐲𝐦𝐢𝐧

𝐓𝐞 ~ t.me/https_Asselefya1