💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Forwarded from ŮƒŮˆŮ†ŮŠ النساء السلفية
ቢስሚላሂ አሮህማኒሮሂም
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
የገላ ትጥበት ስርዓቶች
••••••••••••••••••••••••

♻️1⃣ ከሰዎች እይታ ተሰውሮ መታጠብ፦
የነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
ባለቤት መይሙና እንዳለችው
ነቢዩ ሸፍኛቸው ገላቸውን ታጠቡ"
[ቡኻሪ ዘግቦታል]

♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

♻️2⃣ውሃን አለማባከን፦
ጃቢር ኢብን አብደላህ ስለ ገላ ትጥበት
ተጠይቆ "አንድ ቁና ውሃ ይበቃሃል"
ብሎ መለሰ።
ጠያቂው " ይህማ አይበቃኝም" ሲል
ጃቢር " ከአንተ የተሻለና ፀጉራቸውም
የበዛው ሰው በቅቷቸዋል" በማለት
መለሰለት። {ቡኻሪና ሙስሊም}

♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

♻️3⃣ከገላ በፊት ፊትን መታጠብ፦
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
እንዲ ብለዋል "እኔ ስታጠብ
በመዳፎቼ ውሃ እየዘገንኩ ሶስት
ጊዜ ራሴ ላይ ካፈሰስኩ በኋላ
የተቀረውን ገላዬን እታጠባለሁ"
[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

♻️4⃣የፀጉርን ስር በውሃ ማዳረስ፦
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
እንዲ ብለዋል "ወንድ ልጅ ፀጉሩን
ፈቶ የፀጉር ስሩ እስኪደርስ ማጠብ
ሲኖርበት ሴት ግን ፀጉሯን መፍታት
አይኖርባትም ይልቁንስ ሶስት ጊዜ
ራሷ ላይ ከረጨች በቂዋ ነው" {አቡዳውድ}

♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

♻️5⃣ ባልና ሚስት አንድ ላይ ሆነው
መታጠብ ይችላሉ፦
አዒሻ እንዳለችው "እኔና ነቢዩ ዓለይሂ
ሰላቱ ወሰላም በአንድ እቃ አብረን
እንታጠብ ነበር።"[ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]

♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️

♻️6⃣በኩሬ ውሃ አለመታጠብ ፦
ነቢዩ እንዲ ብለዋል "በኩሬ ውሃ
ውስጥ አትፀዳዱ ሰውነታችሁንም
አትታጠቡ።" [አህመድ፣አቡዳውድ፣ኢብን ማጃህ
በይሃቂይና ኢብን ሂባን ዘግበውታል]
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
umu fulan
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
♻️ የውዱእ መስፈርቶች(شروط الوضوء)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺ከውዱእ በፊት መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶችና ቅድመ ሁኔታዎች

《ክፍል 1⃣6⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
♻️ የውዱእ ግዴታዎች(فروض الوضوء)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔺የመልእከወተኛው የውዱእ አደራረግ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ

《ክፍል 1⃣7⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ሰለፎች ከቁርአን የነበራቸው ትስስር
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹ቁርአን የቀልብ ድርቀትን ለመከላከል
🔹በቁርአን ህይወታችን ለመለወጥ
🔹ለቁርአን ልንሰጠው የሚገባ ትኩረት
🔘ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተወስቶበታል

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔊 زوج اقترض مـن زوجتـه ورفـض وفـائهـا كيـف تستــطيع أخـذ مـالهـا⛔
🎙للشــيخ/محمـد بـن صـالـح العثيمـــين رحمـه اللـه🍃
📲قناة فتَاوى العِشْرة الزّوجية:-
t.me/Fatawa_Aleshrah_Azzawjyya
📲 انشروا القناة رحمكم الله 👈🏻فالدال على الخير كفاعله...👍🏻
✳አኽላቅ ወል አዳብ ✳
••••••••••••••••••••

ጥቂት ኢስላማዊ ስርዓቶች
♻1⃣የቤት አገባብና አወጣጥ ስርአቶች

🔺አንደኛ. የቤቱን ሰው ማስፈቀድ፦

✅አንድ ሰው የራሱ ያልሆነን ቤት ከመግባቱ
በፊት ማስፈቀድ ግዴታው ሲሆን
የራሱ ቤት ሲገባም ቢያስፈቅድ
መልካም ነው።
አላህ እንዲ ይላል፦
يأيها الذين آمنوا لاتدخلو بيوتا غير بيوتكم
حتى تستأنسو وتسلمو علي أهلها ذالكم خير لكم
لعلكم تذكرون*⃣ فإن لم تجدو فيه أحدا
فلا تدخلوها حتى يؤذن لكم وإن قيل لكم
ارجعوا فرجعوا هو أزكا لكم ولله بما تعملون عليم*⃣ النور:٢٧-٢٨

➡<< እናንተ ያመናችሁ ሆይ!
እስከምታስፈቅዱና በባለ ቤቶቿ ላይ
ሰላምታን እስከምታቀርቡ ድረስ
ከቤቶቻችሁ ሌላ የኾኑን ቤቶች አትግቡ።
ይህ ለእናንተ መልካም ነው።
እናንተ ትገነዘቡ ዘንድ[ በዚህ ታዘዛችሁ]።
በውስጧም አንድንም ሰው ባታገኙ
ለእናንተ እስከሚፈቀድላችሁ ድረስ
አትግቧት።
ለእናንተ ተመለሱ ብትባሉም ተመለሱ።
እሱ ለእናንተ የተሻለ ነው።
አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ዐዋቂ
ነው።>>[ አል ኑር 27-28]
__________________________

➡️የኢብኑ መስዑድ ባለቤት ዘይነብ
እንዳሉት ኢብኑ መስዑድ ጉዳያቸውን
ጨርሰው ወዴ ቤት ሲመጡ በሚጠሉት
ሁኔታ ላይ ድንገት ብቅ ላለማለት
ሲሉ ወዴ በር ሲቀርቡ ድምፃቸውን
ያሰሙ ነበር።"

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

2⃣ሰላም ማለት፦
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
አንድን ሰውዬ በአግባቡ ባለማስፈቀዱ
ምክንያት ለአገልጋያቸው እንዲ ብለዋታል
✅በአግባቡ አላስፈቀደምና አሰላሙ አለይኩም
ልግባ? እንዲል ንገሪው"
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
3⃣ሲገባ የሚከተለውን ዚክር ማለት፦

↪️ቢስሚላሂ ወለጅና ወቢስሚላሂ
ኸረጅና ወአለሏሂ ረቢና ተወከልና"
🔶ትርጉሙም፡
{በአላህ ስም ገባን
በአላህ ስም ወጣን በጌታችን አላህ ተመካን}✔️
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

4⃣ጥርስን መፋቅ፦
<<ዐኢሻ እንዳስተላለፈችው ነቢዩ ሰላላሁ
ዓለይሂ ወሰለም ቤት ሲገቡ አስቀድመው
ጥርሳቸውት ይፍቁ ነበር። [ሙስሊም]
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

5⃣ ቀኝ እግርን ማስቀደም፦
ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም ለማንኛውም
መልካም ነገር ቀኝን ማስቀዴም ይወዱ ነበር።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

6⃣ ሲወጣ ይህን ዚክር ማለት፦

↪️ ቢስሚላሂ ተወከልቱ አለሏሂ ወላ ሀውለ
ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ"

➡️ትርጉሙም፡
[በአላህ ስም ፣ በአላህ እመካለሁ፣ ብልሃትም ሆነ ሃይል ያለ አላህ የለም።]
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
um Fulan

https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
بسم الله الرحمن الرحيم
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↪️ ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ እንዲ ይላል፦

♻️ሽርክ ያልተቀላቀለበት የጠራ ተውሂድ
ያለው ሰው፣እንደሱ ያልሆነው ይቅር
የማይለውን ከጥፋቱ ይቅር ይባላል።
በአላህ ላይ ጭራሽ ምንም ነገር
ያላጋራው ባለተውሒድ ምድርን
ሊሞላ የቀረቡ ወንጀሎችን ይዞ
ከጌታው ጋ ቢገናኝ ያንኑ በሚያክል
ምህረት ይገናኜዋል።
ይሄ ተውሂዱ ጎድሎ በሽርክ
ለተቀላቀለው አይገኝም።
ሽርክ ያልተቀላቀለበት የሆነው
ጥርት ያለው ተውሂድ ከሱጋር ወንጀል
አይቀርም ።

🔺ምክንያቱም ይሄ የጠራው ተውሂድ
ምድርን ሊሞሉ የቀረቡ ቢሆኑ እንኳን
ወንጀሎችን ለማጠብ ወሳኝ የሆነውን
የላቀውን አላህ በብቸኝነት መውደድን፣
ማክበርን፣ማላቅን፣ መፍራትን ተስፋ
ማድረግን፣ … ይዟልና ።
አዎ ቆሻሻ [ወንጀል] ሊያጋጥም
ይችላል። ነገር ግን ማፅጃው
ብርቱ ነው። [ኢጋሰቱል ለህፋን፡ 1/64]
~~~~~~~~~~~~
https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
↪️ቅዲሚያ ለተውሂድ እንላለን ምክንያቱም
ተውሒድ ከትዕዛዛት ሁሉ በላጭ ነውና↙️
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

↪️ የተውሂድን ታላቅነት ከሚያሳዩ ጠቋሚዎች
ውስጥ አንዱ ነቢዩ ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም
እንዲ ማለታቸው ነው፡

↪️ [ኑህ ሊሞት ሲል ለልጁ በላኢላሀ ኢለላህ
አዝሀለሁ።✔️
↪️ ሰባቱ ሰማያትና ሰባቱ መሬቶች
በአንዱ የሚዛኑ ክፍል ላይ ቢቀመጡ፣
↪️ ላኢላሃ ኢለላህ ደሞ በሌላኛው የሚዛኑ
ክፍል ላይ ብትቀመጥ፣ ላኢላሃ ኢለላህ
በነሱ ላይ ሚዛን ትደፋ ነበር።] ✔️
➡️[ ሸይኹል አልባኒይ ሶሒሕ ብሎታል]።

↪️[ተሕቂቁ ከሊመቲል ኢኽላስ፡57]


https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
➲ለራሱ የሚወደውን ለአንችም የሚወድልሽ ወንድማዊ ነሲሃ አስታውስ ማስታወስ ለሙዕሚኖች ይጠቅማቸዋልና ብሎ አላህ ሱብሃነሁ ወተአላ እንዳለው እኔም አንችን ለመምከር አቅምና ብቃቱ ባይኖረኝም ትንሽ ነገርን ላስታውስሽ ወደድኩ።

➲ውድ የዒማን እህቴ ሆይ !ያለንበት ዘመን ካለፉት ዘመን ሲነጻጸር የአላህ ሱብሃነሁ ወታዓላ ፍርሃት የቀለለበትና ፊትና የበዛበት ዘመን ውስጥ ነውና የምንገኘው አላህን በመፍራት ላይ አደራ እልሻለሁ።አላህን መፍራት የስኬት ቁልፍ ነው፣የአላህ ሱብሃነሁ ወታዓላም ኑዛዜ ነው ፣የአማኞችም መገለጫና መለያ ልዩ ባህሪ ነው።

➲በዚሁ አያይዤ ጌታሽን አላህ ሱብሃነሁ ወታዓላን ለመፍራትና ለመታዘዝ የሚጠቅሙሽን ጥቂት ነገሮችንም ልጠቁምሽ ውዷ እህቴ ሆይ!

➲ታላቁና ርህሩሁ ጌታሽን ለማወቅ የመጀመሪያው መስፈርት ዒልም(እውቀት)ን ከባለቤቶቹና ከእውነተኛ አሊሞችና ኡስታዞች መማርና ባወቅሽው እውቀት ተግባራዊ ማድረግ ነው።ይህንንም በማስመልከት ጌታችን አላህ እንድህ በማለት ነግሮናል..አላህን ተገቢውን ፍራቻ የሚፈሩት ኡለማዎቹ ናቸው" (ፋጢር፤28)

➲በሁለተኝነት አላህን ለመፍራትና ለማወቅ ከሚረዱሽ ነገሮች ውስጥ ጥሩ የሆነ አቀማማጭና ጓደኛን መምረጥ እንድሁም አብሮ መኖር ነው።

➲እህቴ ሆይ ጓደኛ ትልቅ ተጽዕኖን በልብሽ ውስጥ ይፈጥርብሻል።ከመልካም ጓደኞች ጋር ስትኖሪ ከአንደበትሽ መልካም ይወጣል፣አካልሽ ጥሩን ነገር ይተገብራል፣ኢማንሽ ይጨምራል፣ማንነትሽን ታይበታለሽ፣በጥቅሉ ውጫዊም ይሁን ውስጣዊ ተግባርና ንግግርሽ ያማረና የተስተካከለ ይሆናል።

➲በተቃራኒው ከመጥፎ ጓደኛና አቀማማጭ ጋር ከሆንሽ ከመጥፎ መከልከል ይከብድሻል፣ኢማንሽ ይቀንሳል፣ወደ ወንጀልና ወደ ቢድኣ የመውደቅ እድልሽ የሰፋ ነው የሚሆነው።ስለዚህ ጥቂትም ቢሆኑ ጥሩ ጓደኞችን ምረጭና የድንሽንም ሆነ የአኼራ ህይወትሽን በአላህ ፍቃድ አሳምሪን።

➲በሶስተኝነት አላህን ለመፍራትና ለማስታወስ ከሚጠቅሙሽ ውሥጥ ያወቅሽውንና የተገበርሽውን ለሙስሊሙ ማህበረሰብ አቅምሽ በፈቀደው ማስተማርና ዳዕዋ ማድረግሽ ነው።

➲ይህን ስራ ለመስራት ከላይ በመጀመሪያ እንደገለጽኩልሽ ዒልምና ተግባር ያስፈልገዋልና አደራ እንዳትዘነጊው።ዳዕዋ ለማዲረግና ለማስተማርም ትዕግስት ዋና ቁልፍ መሆኑን ተገንዝበሽ የምን ዕውቀት ተቀዳሚ ነው የሚለውን በመገንዘብና በማጤን በአላህ ታግዘሽ ጀምሪው አላህም ያግሽ።ባነበብሽው አላህ ተጠቃሚ ያድርግሽ የዛሬን አበቃሁ!

✍🏼 Ibnu Seid

https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ሰለፎችና ቁርአን የነበራቸው ትስስር
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

🔹አስደናቂው የቀደምቶች ታሪክ
🔹ቁርአን የቀልብ ድርቀትን ለመከላከል
🔹በቁርአን ህይወታችን ለመለወጥ
🔹ለቁርአን ልንሰጠው የሚገባ ትኩረት
🔹በቁርአን ቀልባችንን ለማከም
🔘ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች ተወስቶበታል

【ክፍል ②】
🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌ውዱእን የሚያበላሹ ነገራቶች
📌 (نواقض الوضوء)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ የውዱእ አፍራሾች
🔹የኡለማዎች ሒላፍና አመዛኙ አቋም በመረጃ የተዳሰሰበት

《ክፍል 1⃣8⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFgdAPPfoRzUemL4vw


https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
|#ውድሽ_የሱና_እህቴ!

~ደንሽ ላይ ጠንካራ ባህሪሽ ማራኪ,
~ኢልምን የምትወጂ ለሱ ተንበርካኪ,
~መንሀጅሽ የጠራ ከቢድአ ንክኪ,
~ሀያእን ተላባሻ ካልሆንሽ ዝርክራኪ,
~ውድ ነሽ ወላሂ አንቺ ነሽ ማራኪ!!!

~መልክሽን ካፈካሽ በጂልባብ በኒቃብ,
~የአላህን ትእዛዝ ከያዝሽው በአግባብ,
~አንቺኮ ነሽ ውዷ የሆንሽ ለሀቅ ዘብ,
~በራችን ክፍት ነው ላንች የሱና እርግብ,

كتبه: أخوكم أبو ماهر الأثري..

t.me/abu_mahir_al_assery
ቁርዓን ቂርዓት አማር ባህረዲን
አማር ባህረዲን
የነብያት አባት
ኢብራሂም አለይሂ ሰላም የተውሒድ ተጋድሎ፣
የጠላቶቹ ሴራ፣
አላህ ሴራቸውን በድል እንዴት እንደቀለበሰው፣
አላህ በነብያት ልጆች እንዴት እንደመነዳው በተከበረው ቃሉ ቁርአን እንዲህ ሲል ይነግረባል።
በጥሞና እናዳምጠው።
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌በመልካም ስነምግባር መዋብ
📌 (التحلي بالأخلاق المشروعة)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹እውነተኝነት 🔹ጥቡቅነት
🔹ቸርነት 🔹አይናፋርነት
🔹ጀግንነት 🔹አማናን መወጣት
🔹ቃል ኪዳንን መሙላትና ሌሎችም

《ክፍል 1⃣9⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ

https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
✅ ማግባትህ ካልቀረ ሰለፍይዋን አግባ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ እውነተኛ ሰለፍይ የሆነችን ሴት ያገባ ወንድ ምንኛ ታደለ❗️

♻️ስማማ ወንድሜ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻
🔹ሽቶህ የፈረንሳይ ቢሆን
🔹ጫማህ ከጣሊያን ቢገዛ
🔹ሰአትህ የስዊዘርላንድ ቢሆን
🔹መኪናህ ከጀርመን ቢመጣ
⏩ ሚስትህ ሰለፍይና ጣሊበል ኢልም ካልሆነች የህይወትን ደስታና ጣእም ሙሉውን አታገኝም።

✅ ለዛም ነው አንዳንዶቹ "ሰለፍይ የሆነችን ሚስት ያላገባ ወንድ ሁሌም ላጤ ነው" የሚሉት።

↪️ ሰለፍይዋን በማግባትህ ከምታገኛቸው ጥቅሞች ውስጥ በትንሹ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
◾️በዲንህ እንድትበረታ፣ ለአሔራህ እንድትለፋና በሱና ላይ እንድትጠናከር ታግዝሀለች።
◾️ሁሉ ነገሯ ያንተ ብቻ ነው። ካንተ ውጪ ማንም አይጨብጣትም፣ አያያትም፣ አይነካትም።
◾️የተለያዩ ቁሳ ቁሶችና ያላስፈላጊ ወጪ በመጠየቅ ብርህት አታባክንም።
◾️አጉል መዝናኛ፣ ትርፍ የሌለወወ ሽርሽርና ቅጥ ያጣ ደስታ በሚል ጊዜህን አትገልብህም።
◾️የትም ብትሄድና ከሷ ብትርቅ በልጆችህ፣ በገንዘብህና በፍራሽህ ጉዳይ ላይ ምንም ስጋት አይገባህም።
◾️ህመምህ ህመሟ፣ ጭንቅህ ጭንቋ፣ ስቃይህ ስቃይዋ፣ ደስታህ ደስታዋ አድርጋ ስለምታስብ ሁሌም ትሳሳልሀለች።
◾️ለልብህ መርጊያ፣ ለአይንህ ማረፊያ እንዲሁም ለቀልብህ ደስታ ትሆነሀለች።

💢 ይህች ናት ሰለፍይዋ እወቃት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ የሰለፍይ ሴት እጅግ ብዙ መገለጫና ባህርይ ቢኖራትም ከነዚህ ውስጥ በመጠኑ ልጠቁምህ

➲የማትጠራጠር ሁሌም በእርግጠኝነት የተሞላች
➲ሀሜት አታውቅም ምላሷን ጠባቂ ናት
➲ቶሎ አትናደድም ነገራቶችን በርጋት ምትቃኝ ናት
➲ትርፍና የማይጠቅም ከሆነ ነገር ሁሉ ትርቃለች
➲አዛኝ ናት ጭካኔን አታውቅም
➲ሩህሩህ ናት ደንዳና አይደለችም
➲ለእውቀት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች መሀይምነትን ትጠላለች
➲ባወቀችው ነገር ትሰራለች ሰዎችም በአደቡ ትመክራለች
➲ስነምግባሯ ያማረ ነው ጋጠወጥ አይደለችም
➲ጥቡቅ ናት የፈለገ ሁሉ አያገኛትም
➲ርካሽ ቦታ አትገኝም ክብሯን ትጠብቃለች
➲ባላት የምትብቃቃ ናት ሌሎችን አሻግራ አትመለከትም
➲ለዱንያ ብዙም አትጨነቅ በጌታዋ የምትተማመን ነች
➲እራሷን ጠባቂ ናት አትዝረከረክም
➲ንግግር አታበዛም ቁጥብ ናት
➲እውነተኛ ናት ውሸትን አትወድም
➲ጌታዋን ታወሳለች ዝንጉ አይደለችም
➲ዙረት አታበዛም በቤቷ ረጊ ናት
➲ለማንም አትገላለጥም ለባሏ ካልሆነ በቀር
➲ባሏን አክባሪ ናት አታዋርደውም
➲ሚስጥሩን ጠባቂ ናት ለማንም አሳልፋ አትሰጥም
➲የተረጋጋች ናት ቸኳላ አይደለችም
➲ጊዜዋ በኢባዳ እንጂ በወሬ በፊልም በድራማ አትገልም
➲ሰዎች ይናፍቋታል እንጂ መቸም አይሰለቿትም
➲በውይይት የምታምን እንጂ ግትር አይደለችም
➲ሰውን አክባሪ እንጂ ፈሪ አይደለችም
➲ሽርክ ቢድአና ኹራፋትን በጭራሽ አትቀርብም
➲በኒቃቧ ተሸፋኝ ናት ሰውን አትፈትንም
➲የአላህን ውሳኔ ወዳ ሶብር ታደርጋለች እንጂ አትበሳጭም
➲የባሏን ትእዛዝ ታከብራለች በፍፁም አታምፀውም
➲ለሰዎች መልካምን እንጂ መጥፎ አትመኝም
➲ለሌሎች ዱአ ታደርጋለች እንጂ አትመቀኝም
➲በተራ ምክንያት ትዳሯን ገደል አትከትም
➲ይቅር ባይና ሆደ ሰፊ ናት ቂም አትይዝም
➲አርቆ አሳቢ ናት ስሜታዊና ቅፅበታዊ አይደለችም
➲መነጫነጭ፣ መነታረክ፣ መኮሳተር፣ መከራከር አቶድም
➲በዲኗ ጉዳይ ከማንምና በምንም አትደራደርም
🔺ለወንድ ብላ ሀይማኖቷን አትቀይርም
🔺ለዱንያ ብላ ሱናዋን አትሸጥም
🔺ለትዳር ብላ ከመንሀጇ አትንሸራተትም
🔺ለስሜቷ ስትል ዲኗን አታሰድብም
🔺ለጥቅማ ጥቅም ስትል ክብሯን አሳልፋ አትሰጥም

▶️ ይህች ናት አግባ የምልህ

📝ልብ በል📝
💢ትዳር ከተስተካከለ እዚህ ምድር ላይ ካሉ ኒእማዎችና ፀጋዎች ውስጥ አንዱና ዋና ከሚባሉት የሚመደብ ሲሆን በተቃራኒው ከሆነ ደሞ ህይወትህ ምስቅልቅሉ የሚያወጣና ደስታን የሚነሳ ስለሆነ ከማግባትህ በፊት ማን ማግባት እንዳለብህ ቆም ብለህ አስብ።

↪️ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል።
【ٱلْخَبِيثَٰتُ لِلْخَبِيثِينَ】
💎መጥፎ ሴቶች ለመጥፎ ወንዶች የተገቡ ናቸው።
【وَٱلْخَبِيثُونَ لِلْخَبِيثَٰتِ】
💎መጥፎ ወንዶች ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡
【وَٱلطَّيِّبَٰتُ لِلطَّيِّبِينَ】
💎ጥሩዎቹ ሴቶች ለጥሩዎቹ ወንዶች የተገቡ ናቸው።
【 وَٱلطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَٰتِ】
💎ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡
📚ሱረቱ ኑር (26)

↪️ ለዚህም ነው በተጨማሪ ውዱ ነብያችን እንዲህ ያሉት፦
【"فاظفر بذات الدين تربت يداك"】
የዲን ባለ ቤቷን ምረጥ። እጅህ አፈር አፋሽ ይሁንን

👉 በአላህ ፍቃድ
ስለወንዶቹ
ይቀጥላል።

t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1670
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1670
بسم الله الرحمن الرحيم


ዛሬም እንዴ ጥንቱ መላዕክትና ጂን የሚያመልክ አለ
●●●●●●●●●●●●●●●●●●

🔺አላህ እንዲ ይላል፦
↪️ሁሉንም በሚሰበስባቸውና ከዚያም ለመላእክቱ፡
እነዚህ እናንተን ነበር የሚገዙት? በሚላቸው
ቀን አውሳ]። [መላዕክቱም]፡ ጥራት ይገባህ ከነሱ ይልቅ ረዳታችን አንተው ነህ።
ይልቁንም ጂንን ነበር የሚያመልኩት።
አብዛኞቻቸው በእነሱ አማኞች ናቸው ይላሉ"።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
[ሰበእ፡40-41]

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↪️እነሆም ከሰዎች የሆኑ ወንዶች
በወንድ ጅኖች ይጠበቁ ነበር።
መሼበርንም ጨመሯቸው።[ አል ጂን፡5]
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

🔻ዛሬም ተመሳሳይ እውነታ አለ።
አዲስ ቤት ሰርተው ሲገቡ የአካባቢው
➡️"ቆሌ" እንዳይጣላቸው ለመጠበቅ
ደም የሚያፈሱ አሉ።
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
🔺ከህመም ለመጠበቅ የተለያዩ መልክና
ስያሜዎች ያሏቸው ዶሮዎችን በላያቸው ላይ
አዙረው የሚለቁ ኋላም በቃላቸው
የሚያርዱ ሰዎች በሀገራችን በብዛት አሉ።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹በመንገድ ላይ ሲጓዙ አስፈሪ አካባቢ
ሲደርሱ ወይም ከፍ ያለ ዛፍ ሲያገኙ
ከስሩ ለበረካው ተቀምጠው የአካባቢውን
ቆሌና አድባር ከስጋት እንዲጠብቃቸው
የሚለማመጡ ብዙ ናቸው።

ታዲያ የሚያስቡትን አማን፣ የሚያልሙትን
ጤና ሊያገኙ ቀርቶ ሁሌ በስጋት ነው
የሚኖሩት። ሁሌ ምርኮኛ ሆነው ነው
የሚቀሩት።
♻️♻️♻️♻️♻️
um fulan


https://t.me/joinchat/V9ZPw81xGZVQYL_1
Audio
💢ተከታታይ የዱሩስ አልሙሂማ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
📌 الدروس المهمة لعامة الأمة

♻️በዛሬው ደርስ የተወሱ ነጥቦች
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
📌(እስላማዊ በሆኑ አደቦች ማጌጥ)
📌 (التأدب بأداب الإسلامية)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
🔹ሰላምታን ማብዛት
🔹ያስነጠሰን ማስደሰት
🔹የተቸገረን መርዳት
🔹የአበላል ስነስርአት
🔹የታመመን መጠየቅ
🔹የቤትና የመስጅድ አደቦችና ሌሎችም ተወስቶበታል

《ክፍል 2⃣0⃣》

🎙አቡ አብደሏህ ኢብኑ ኸይሩ


https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w