💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
✍️ወሎ_ሁኖ_አያውቅም!!
----------------------------
በሀበሻ ታሪክ በዚህች ሀገር ክስተት፡
ባንዳ ሆኖ አያውቅም ወሎ በስህተት፡
ወደ ኋላ ሳይዞር ሳያወልቅ ጥምጣም፡
#ምሽግ_ሰባሪ_ነው_የወሎ_ሽርጣም፡
በሚዲያ ወጥተህ ጠላት ከመለመን፡
በገንዘብ ከመስራት ጠላትክን ከማመን፡
#የወሎን_ሳተና_ጀግንነቱን_እመን!?

------------------------------------------
▪️ወሎ_በጠላት_ፊት_አያቀረቅርም፡
ዘር ስለማይቆጥር ሰፈር አያፈቅርም፡
አቅራሪው ፎካሪው ፊኛ ቢወጥርም፡
ወሎ
#በባንዳነት አይጠረጠርም፡
ህዝቤ ድምፅ ይሆናል ለእነዚያን ወንድሞች፡
መቀበሪያ ላጡት
#የትግራይ ሙስሊሞች፡
የኢስላም ልጆችን እኖዳቸዋለን፡
ድሮስ ከነርሱ ጋር እኛ መች ፀብ አለን!!

----------------------------------------
የዚህች ሀገር ጠላት የታሪክ ጠባሳ፡
የጥቁር አሻራ ደግሞም የሀበሳ፡
በጭካኔ ድርጊት የግፍ ፍርደኛችን፡
አንተና እሱ ናችሁ የሀገር ባንዳችን፡
ጨክን የወሎ ልጅ ምረር እንደ ኮሶ፡
በየደረስክበት ንፁህ ደምህ ፈሶ፡
እንደት ትሆናለህ ሞትህ ተደግሶ፡
የፌስ ቡክ አርበኛ
#ባንዳ ነህ እያለህ፡
ጠላት ጋር አብሮ ደፍሮ እያስገደለህ፡
የቱ ነው ጠላትህ ስንቱን ትችላለህ፡
ህዝቤ ቂም አታውቅም
#ወሎ ትለያለህ፡
--------------------------------------------
ለፈሪ ፉከራ ለባንዳው ቀረርቶ፡
ይሸኘዋል እንጂ የሰራውን ሰርቶ፡
አያሸረግድም #ኤጁ ትጥቁን ፈቶ፡
ወሎ ሲጠናከር ተው አይንህን አትሽ፡
ባንዳው ራስህ ነህ ማንነትክን ፈትሽ፡

👉ወሎ____
ፍቅር ደግነት ጋር ልቡ ላይ ፀድቆበት፡
ውልደቱና እድገቱ ጀግንነት ሆኖበት፡
ሀብት እየዘረፈ የኖረ ሲለቅም፡
በፌስቡክ አርበኛ
#ወሎዬ አይናቅም፡
ቀርቦ አብሮት ያልኖረ ይህን ህዝብ አያውቅም፡
ወሎ ፍቅር እንጂ ጥላቻ አይሰንቅም፡
የራሱን ሀቅ እንጂ የሰው አይናፍቅም፡
ደፍሮ ለወረረው ርስቱን አይለቅም፡
ሀገር አፍራሽ ባንዳ ወሎ ሁኖ አያውቅም፡

------------------------------------------------
#ወሎ_ታሪክህ_ይመስክር!!
-------------------------------------------
✍️ኑረዲን_አል_አረብ

http://t.me/nuredinal_arebi
🌺‏أخـتي كريمة 🌺


➧ሂጃብሽ ጅልባብሽ  አላህ እንደሚወድልሽ ነው አለባበስሽ!!


➧ወይንስ ነፍስያሽ እንደፈለገችው ነው አለባበስሽ!!

➧እራስሽን ፈትሺ እህቴ ስሜትሽን መከተልን ተጠንቀቂ ካቺ ስሜት የጌታሽ ትዛዝ ይበልጣልና❗

https://t.me/https_Asselefya1
🥀ምክር ለእህቴ🥀

➧እስኪ ብልጥ ሁኚ!!

➷እህቴ ሆይ! ኧረ ተይ ፎቶሽን ታፔላ አታድርጊው!! ተይ ግን በየሚድያው ላይ አትበትኝው!! ተይ ግን ሞት አለብሽ ተይ ግን እህትዬ ተይ ራስሽን አታርክሺ!!

➷ውዴ  እስኪ ልጠይቅሽ ቁንጅናሽ ውበትሽ ከربنا ቅጣት ይከላከልልሻል!?እ መከላከል ይችላሉ!? ጅስምሽ እሳትን መቋቋም ይችላላ!!? لا وربي لا وربي በፍፁም ይቅር እህቴ ሁሉም ይቅርብሽ ልታይ ልታይ አትበይ!! ወንጀልን እንጂ አታተርፊም!!!

➷አንቺም ወንጀል ቀስመሽ ወንድሞችሽንም ፈትነሽ!! ተይ እህቴ ኸይር አይደለም ይቅርብሽ!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
▪️ إِن يَعْلَمِ ٱللَّهُ فِى قُلُوبِكُمْ خَيْرًۭا يُؤْتِكُمْ خَيْرًۭا مِّمَّآ أُخِذَ مِنكُمْ

«አላህ በልቦቻችሁ ውስጥ በጎን ነገር (እምነትን) ቢያውቅ ከእናንተ ከተወሰደባችሁ የተሻለን ይሰጣችኋል፡፡   ~Anfal

               https://t.me/https_Asselefya1
✍إِنَّ مَعَ ٱلْعُسْرِ يُسْرًۭا

➧ከችግር ጋር በእርግጥ ምቾት አልለ፡፡
Audio
ወንድማችን ኢትዮጵያዊው ጀማል ብዙ ቃሪኦች አሉን አልሀምዱሊላህ አላህ በያሉበት በድሎት በፀጋው ያኑርልን እንዲህ አይነቶችንም ብዝዝት ያድርግልን ሀያኩም አላህ ጀሚአን እንዴት ደስስስ ይላል !!!

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
ጦርነቱን በተመለከተ ጠቃሚ ዳሰሳ!!

✍️ኢብኑ ሙነወር እንደፃፈው...

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
♻️ወሎ_ነው_ሀገሬ__!! ▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴▴ ለሁሉም ግልፅ ይሁን፤ ወሎ ፍቅር እንጅ ክፋት አያቀውም፡ ሁሉም ዘመዱ ነው፤ ከማንም ይስማማል ሴራ ሸፍጥ የለውም፡ የአሏህ ውሳኔ እንጂ፤ የማንም ቀረርቶ የማንም ፉከራ አያሸንፈውም፡ በርግጥ ይገባኛል፤ ወሎየ ነኝ ስለው ውስን ሰው አይወድም፡ ግን ደግሞ ሀቅ ነው፤ እኔ ወሎዬ ነኝ ይህንን አልክድም፡ በተረዳሁት ልክ፤ #የዘረኝነት_ጥል ወሎ ገብቶ…
متن أصول الثلاثة ۱۰
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
❿

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
➧ችግሩ ብዙ ቤቶች ውስጥ አለ

ከስር የያዝኳት አረብኛ እንድህ ትላለች

بعض النساء إذا خرجت تعطرت وتزينت وإذا بقيت في منزلها تبصلت وتثومت...

➧አንዳንድ እህቶች ወደ ውጭ ሲወጡ ሽቶ ይቀባሉ ይዋባሉ፤ ቤታቸው ውስጥ ሲኖሩ ቀይ ሽንኩርት ና ነጭ ሽንኩርት ሽታ ይሸታሉ።

➧መዋብና ሽቶ መቀባት በቤት ውስጥ አጅነብይ ከሌለ ይፈቀዳል።

➧መዋብና መቆነጃጀት በተለይ ሽቶና መሰል ሽታ ያላቸው ነገሮችን ተቀብቶ ከቤት መውጣት ይከለከላል ።

Ibnu seid🖊
https://t.me/https_Asselefya1
✍️ግርም_የምትሉኝ_በተለይ_ሴቶች__!!

#ጠንከር_ያለ_ቃል_ተጠቅሜያለሁ_አውቄ_ነው።

#በክርስቲያኖች_ስብከት ስር
#እግዚአብሔር_ይመስገን በሚል #ቪዲወ_ስር
#ከኢስላም_ተቃራኒ_በሆነ_ሰው_ዩቲዩብና_ፌስቡክ_ስር_እየገባችሁ.....

አሏህ ይጠብቃችሁ
አሏህ ያቆያችሁ
ምናለበት ከናንተ ጋር በሆን የምትሉ #ሙስሊሞች በጤናችሁ ነወይ በአሏህ...!!

ኸረ ንቁ በተለይ በስደት የምትኖሩ ናችሁ በእንደዚህ አይነት የተልከሰከሰ ተግባር ላይ የምትሳተፉት...

አወ እኔ በስደት ላሉ ሙስሊም ወገኖቼ ብዙ ጊዜ ጠበቃ ሆኘ አውቃለሁ ።

በርግጥ ብዙ ጀግኖች በእምነታቸው የማይደራደሩ አሉ አውቃለሁ ግን ጂሎቹም እዛው ናቸው።

እንደ ሲነግሯቸውም አይሰሙምኮ አይሰሙም ወላሒ

የፓስተሩ ላይክ
የቄሱ የስብከት ሸር
የደብተራው የምርቃ ኮሜንት እንዳለ በሙስሊም የታጨቀ ነው።

እነሱም አስበው ሙስሊሙ አሏህ ያቆያችሁ ሲል #ላይካቸውን ያበዙላቸዋል ኸረ ንቁ ሙስሊሞች በአሏህ ወላሒ ሙስሊም ሆነው በካ*ፊ*ሮ*ች ኮሜንት ስር #ከኢስላም የሚያሶጡ ንግግሮች የሚናገሩ አሉ....

ወላሒ አስጠላችሁኝ ከአሁን በኋላ በተከታታይ እፅፋለሁ ኢንሻ አሏህ

ሙስሊሞች እርስ በርሳችሁ ተነቃቁ በአሏህ በአሏህ በአሏህ ልለምናችሁ

እምነታችሁን አክብሩ
ሀይማኖታችሁን አታዋርዱ
ያልተፈቀደ ነገር አትናገሩ
ለአሏህ ጠላቶች አታጎብድደለ

➻ሙስሊሙ ኢንተርቪው ሲደረግ #አልሀምዱ_ሊላህ ለማለት ያፍራል።

➻ወላሒ አንዳንዱ ሙስሊም ሆኖ #እግዚአብሔር_ያውቃል ሲል እንደት ይጨንቃል በአሏህ...!!

ካፊሩ ግን ሙስሊሞችን በሚሳደብበት ቻናል ስር ተከታታዩ አሽቃባጩ እረዳቱ #ሙስሊም_ነው #ኤጭ,,,,,,አሏህን ፍሩ

ንግግርም ከኢስላም ያሶጣልኮ #ጂሎች

#ወላሒ_ለነዚህ_አካላት_በየወሩ ተቆራጭ ገንዘብ የሚልኩት ብዙወች ናቸው

ይህ ምን አይነት ድንቁርና ነው!?

የሚገነባ መስጂድ ጠፋ
የሚረዳ ሙስሊም የለም!?
እየተንከራተተ የተቸገረው ተፈናቃይ #ሙስሊም ቤተሰብሽስ..!?

አዑዙ ቢላህ አሏህ ሒድያ ይክጣችሁ!!

በጣም በጣም አዝኛለሁ ወላሒ ቅጥል ነው ያደረጋችሁኝ በናንተ ምክንያት #ፅኑወቹን_ጠንካራወቹን_እንዳልጠላ_ፈራሁ_!!

ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂዑን

ሸር አድርጋችሁ አድርሱልኝ በዚህ ጉዳይ የምታውቁትን መረጃም አቀብሉኝ በሰፊው እፅፋለሁ።


http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
ኒቃብ መልበስ ከነገር አለሙ የሚያሰናብት አድርገው ለሚመለከቱ እንዲሁም ለሚሰብኩ ለውጪም ይሁኑ ለውስጥ ጠላቶችሽ ኒቃብሽን ለብሰሽ ለራስሽም ይሁን ለሌሎች መልካም ነገርን በማበርከት ላይ ፍጹም እንደማያቅብሽ በተግባር አሳያቸው።

አዎ!  በያቸው ኒቃቤ ውበቴን እንጂ አእምሮዬን አልሸፈነውም።


https://t.me/https_Asselefya1
ሙስሊሟ ሴት ሆይ ! አላህ (ሱ.ወ)በማህጸንሽ ውስጥ በፈጠረው ጽንስ አንች አመኔታ ተጥሎብሻል፤ ስለሆነም አትደብቂው ፤ አላህ እንዲህ ይላል ፦

وَلَا يَحِلُّ لَهُنَّ أَن يَكْتُمْنَ مَا خَلَقَ اللَّهُ فِي أَرْحَامِهِنَّ إِن كُنَّ يُؤْمِنَّ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ

♻️በአላህና በመጨረሻውም ቀን የሚያምኑ ቢኾኑ አላህ በማህፀኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ሊደብቁ ለነርሱ አይፈቀድላቸውም።


↑ጽንስን የማስወረድ ሸሪዓዊ ብይን... ከተንቢሀት የወሰድኩት

ኮፒ

https://t.me/https_Asselefya1
ማንነትክን በወሬ ሳይሆን በተግባር አሳይ!!

" الكلماتُ قد تكذب !
لكن التصرفات دائماً تقولُ الحقيقة "


ንግግር ሊዋሽ ይችላል
ድርጊት ግን ሁሌም እውነትን ይመሰክራል።


http://t.me/nuredinal_arebi
✅ ሰለፎች ከሚያደርጉት ዱአ ውስጥ አንዱ እንዲህ የሚል ነበር፦

【አላህ ሆይ፦ አንተን በመታዘዝ አልቀኝ አንተን በማመፅ አታዋርደኝ】ይሉ ነበር።
📚الداء و الدواء (٩٤)
‍ 📩ይድረስ👇
ኢንተርኔት ለምትጠቀሙ እህቶች‼️

♻️በኢንተርኔት ከንቱ ምኞት ትዳርዋን የተበላሸባት፤ ህይወቷን የጨለመባት እንስት አስተማሪ ታሪክ…

ወጉ ወዲህ ነው👇
ሚስት አላህ ይጠብቀንና በኢንተርኔት ሱስ የተጠመደች ናት። ባለቤትዋ ከዚህ ተግባርዋ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ቢመክራትም ልትቀበለው አልቻለችም። ብዙ ለመናት ብዙ አስመከራት "አሻፈረኝ" አለች። የምትጠቀምበትን ስልክ ሳይቀር ወስዶባታል። እሷም ሌላ ስልክ በመፈለግ ኢንተርኔት ላይ መዘውተሯን ቀጠለች።

በዚህ ጊዜ ባል አንድ ዘዴ ይዘይዳል👇
ወደ facebook በመግባት እንደ ሚባለው "fake acount" (የውሸት አድራሻ) በመክፈት ስሙን ይቀይርና ፕሮፋይሉ ላይ ሀብታምና ቆንጆ የሚመስል የወንድ ምስል ያስቀምጣል። ከዝያ በኋላ የሚስቱን የ facebook አድራሻ በመፈለግ ያናግራት ጀመረ።

👆ጨዋታው የተጀመረው እዚህ ቦታ ነበር
በሰላምታ የተጀመረው ንግግር ወደ ትውውቅ ይሸጋገርና ያለችበትን የኑሮ ሁኔታ ጨርሳ ትነግረዋለች። እሱ ግን እየዋሻት እሷን በምትፈልገው አይነት ራሱን እየገለፀ ያጫውታታል።
ባለ ትዳር እንደሆነችና ነገር ግን በትዳሯ ላይ ደስተኛ እንዳልሆነች ስትነግረው
"እንግዲያውስ ባልሽን ይፍታሽና ከእኔጋ እንደመር" ይላታል።
ባቀረበላት ሀሳብ ደስተኛ ሆና ከባልዋ ጋ በምን ዓይነት መልኩ መፋታት እንዳለባት መላ ይፈልጋሉ። እሱም "በቃ ሳትጎዳዱና ሳትጨቃጨቁ እንድትለያዩ ችግር በማይፈጥር መልኩ ባህሪሽን ቀይሪበት" ይላታል።

ባል ስራ ውሎ ማታ ሲገባ የሚስቱ ባህሪይ ከቀን ወደ ቀን እየተቀያየረ ይመጣል። ሚስት የማታውቀው ባል የፈጠረው ጨዋታ ነውና ቀን እያወራት ማታ ገብቶ ይታዘባታል። [አላህ ይጠብቀን]

ጨዋታው ሲጧጧፍ ባል ማታ ይገባና
"ሰሞኑ እያየሁብሽ ያለው ነገር እያስደሰተኝ አይደለም ምን ተፈጥሮ ነው?" ይላታል
"ምንም" ትለዋለች
"ንገሪኝ ችግርሽ ዝምታ መፍትሄ አይሆንም" ሲላት
"ምንም አልሆንኩም" ትለዋለች
"ሀሳብሽ በግልፅ ንገሪኝ ከእኔ መለየት ትፈልጊያለሽ ያልተመቸሽ ነገር አለ እንዴ?" ሲላት
"ቢሆን አይከፋኝም" ብላ ፍላጎትዋን ገለፀችለት።

ፍላጎቷን ግልፅ ካደረገች በኋላ ባልየው ቀጥታ ወደ ፈለገው ጨዋታ ይገባና ያናግራታል👇
"እንግዲህ መለያየታችን አይቀሬ ከሆነ አንቺም የሄድሽበት እንዲቀናሽ እኔም ቤቴና ንብረቴ ተበታትኖ ህይወቴ እንዳይበላሽ ከመሄድሽ በፊት ሁለተኛ ላግባና ልክ እንዳገባኋት ለእሷ አስረክበሽ ትሄጃለሽ" ይላታል።
  ሚስትም ያሳሰባት ሁለተኛ ማግባቱ አለ ማግባቱ ሳይሆን የእሷ መፈታት ነበርና "ምንም ችግር የለውም" ብላ ትስማማለች።

ባልየው በማግስቱ ወደ ሚስቱ ቤተሰቦች በመሄድ የተነጋገሩበት ነገር ያጫውታቸውና ሁለተኛ ሊያገባ መሆኑ ይነግራቸዋል።
ሁለተኛ ሚስት ፍለጋ ተ ጀ መ ረ

ባል ሊያገባት ሚስት ደግሞ አስረክባት የምትወጣዋ ሁለተኛ ሚስት በሁለቱም ብርቱ ፍለጋ "ትሆናለች፣ ትመጥናለች" የተባለችዋን አፈላልገው አገኙ።
ያዝ እንግዲህ……

የሁለተኛዋ ሚስት የኒካህ ቀጠሮ ይያዛል። ልብ በሉ ሁለተኛዋ እንደ መጣች የመጀመሪያዋ ተሸኝታ 👉ያ በኢንተርኔት መንፈስ ብቻ የምታውቀው ባልዋ ሊያገባት ነው።

የማይደርስ የለምና የኒካሁ ቀን ደረሰ። ባል ልክ የሁለተኛ ሚስቱ ኒካህ እንዳሰረ ያ ሚስቱን ሌላ ሰው መስሎ ያወራበት የነበረው የ facebook አድራሻ ዘግቶት ከኢንተርኔት መንደር ይወጣል።
لا إله إلا الله

የመጀመሪያዋ ሚስት ባልዋ ሌላ እንዳገባና ከባልዋ ተለያይታ አዲስ የተዋወቀችው ሰወዬ ልታገባው እንደሆነ ልታበስረው ስትገባ ያ በውሸት ሲያወራት የነበረው ባለ facebook አድራሻው ዘግቶ ከመንደሩ ጠፍቷል።

ዱንያ የት አትጥበባት?
"ምድር ዋጭኝ" ብትላት መች ልትውጣት? ህይወት ጨልሞባት፣ መኖር አስጠልቷት ራሷን እየረገመች አዝና ተክዛ ቁጭ ብላለች።

ባል አዲሷ ሙሽራው ጋ መቆየት ያለበትን ቆይቶ መጫወት ያለበትን ተጫውቶ ወደ ቀድሞ ሚስቱ ቤት ሲሄድ በሀዘን ተውጣ ተቀምጣለች።
"ምንድን ነው ሰላም አይደል እንዴ?" ሲላት
"ሰላም ነው" ትለዋለች
"ምን ሆንሽ?"  "ምንም"
ትቷት ይሄዳል።

አሁንም ተመልሶ ሲመጣ ሰውነቷ ከሳስቶ ፊቷ ተሸብሽቦ ያገኛታል
"ምንድን ነው የሆንሽው?"
"ምንም አልሆንኩም"
"ያስቀየምኩሽ ነገር አለ"
"ኧረ የለም"
"ሀሳብ መቀየር አስበሽ ነው?"
ፀጥ ረጭ አለች።

የዛኔ ባል አጠገቧ ቁጭ ብሎ እያፅናናት
"ምን ላርግ ታድያ? ከአንቺ መኖር እየፈለግሁ፣ ሳልጠላሽ፣ ሳላስከፋሽ በራስሽ ፍላጎት ያመጣሽው ሀሳብ ነው። እኔ ግን አሁንም ቢሆን የማከብርሽ የምወድሽ ባለቤቴ ነሽ። አንቺም ከእኔ የመለየት ፍላጎት ከሌለሽ ያመጣኋትም ሙስሊም እህትሽ ናት አብራችሁ ትኖራላችሁ። እሷም በቤቷ አንቺም በቤትሽ አብረን እንኑር።" አላት

በዚህ ሰዓት ካላይዋ ላይ የተጫናት ተራራ የተነሳላት በሚመስል መልኩ በደስታ ፈንጥዛ ባልዋን እየሳመችና እያመሰገነች እያለቀሰች ደስተኝነቷን ገለፀችለት።

በመጨረሻም ባልየው ባለ ሁለት ሲም ሆኖ ከሁለቱም ሚስቶቹ ጋ አብረው መኖር ጀመሩ።


NB: ታሪኩ ላይ የተጠቀሱ በሸሪዓ ክልከላ ያለባቸው ነጥቦች አሉ [ፎቶ መጠቀምና ውሸትን] ይመስል
ዘንግተናቸው ሳይሆን ከታሪኩ ብዙ ሰው ሊማር ይችላል ብለን ስላሰብን ነው።
ማስተላለፍ የተፈለገውም ባሎች እንዲህ እንዲያደርጉ ሳይሆን ሴቶች ከምንም ነገር በፊት ክብራቸውን (ትዳራቸውን) ማክበርና መታዘዝ እንዳለባቸው ለማስገንዘብ ነው።


ኮፒ!!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
‍ 📩ይድረስ👇 ኢንተርኔት ለምትጠቀሙ እህቶች‼️ ♻️በኢንተርኔት ከንቱ ምኞት ትዳርዋን የተበላሸባት፤ ህይወቷን የጨለመባት እንስት አስተማሪ ታሪክ… ወጉ ወዲህ ነው👇 ሚስት አላህ ይጠብቀንና በኢንተርኔት ሱስ የተጠመደች ናት። ባለቤትዋ ከዚህ ተግባርዋ እንድትቆጠብ በተደጋጋሚ ቢመክራትም ልትቀበለው አልቻለችም። ብዙ ለመናት ብዙ አስመከራት "አሻፈረኝ" አለች። የምትጠቀምበትን ስልክ ሳይቀር ወስዶባታል። እሷም…
ፁሁፍ ረጂም ነዉ ግንተመስጨ ያነበብኩት ገርሞኝ አይ እኛ ሴቶች ትገርሚኛለሁ ነንኮ ጉድ ሓቂቃ ተመከሩበት በተለይ ባለ ትዳሮች ጥንቃቄ አድርጉ ሓቂቃ!!
↪️የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች

👉ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ
1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:-


➧ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387]

➧ ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69]

➧ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946]

➧ ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ።

➧ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957]

2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ።


3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:-


👉አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣
👉አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣
👉የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው
👉እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?!

የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007)


የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor