💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
متن أصول الثلاثة ۱۱
Abu Useymin
ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖

📚ኪታብ ኡሱሉ ሰላሳ

            ➧ክፍል 
➊➊

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1

@abuUseyminabdurehman
#ዘመን_መለወጫ።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ዘመን መለወጫ የለንም ወዳጄ፡
ኮተት አልፈልግም ዘወር በል ከደጄ፡
ሙሉ ፅድት ያለ ሐቅ ነው መንሀጄ፡
ከሉቃስ ዩሀንስ ከማርቆስ ክርስቶስ፡
ከሰውች ወደሰው ከቄርቆስ ቆሮንጦስ፡
ኸረ ለቀቅ አርገኝ አያልቅም ያንተ ጦስ?
ወደ ሰው መጠጋት ሙስሊሞች አንወድም፡
ከአንድ አምላክ በስተቀር ለማንም አንሰግድም፡
ለማርቆስ ለሉቃስ አናጎበድድም፡
ምንክንያቱም ሙታን ምንም አይፈይድም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ስለዚህ ራቂኝ ማነሽ እንቁጣጣሽ፡
ወደኛ አትጠጊ ዞር በይ እስከ ሻንጣሽ፡
እኛ እናውቅሻለን ከየት እንደመጣሽ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
በእስልምናችን የለም እንቁ ጣጣሽ፡
ዘመን መለወጫ የሽርክ ብጥስጣሽ፡
የድግምት የመተት ክፋት መተግበሪያ፡
የክፋት የሴራ ተንኮል መቀመሪያ፡
እውነታ የሌለሽ የኩፋር መመሪያ፡
እውነትን ሰርዘሽ ውሸት ማስተማሪያ፡
ሐቅን ባጢል ብለሽ ጥመት ማበጠሪያ፡
ውስጥሽ ውጭሽ ቦድ ግድግዳሽም ጣሪያ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ኢብሊስ የገነባሽ የጭፍሮቹ መተት፡
አማኞች አያውቁም እንድህ አይነት ኮተት፡
ሐቁ መመሪያችን ካላፀደቀልን፡
ውዱ ነብያችን ካልመሰከረልን።
በነሉቃስ ቀመር ተጓዥ አይደለንም፡
ዘመን መለወጫ ፈፅሞ የለንም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
የአመፅ የበደል የወንጀሎች ቅርጫ፡
የሸይጣን የአጋንንት የጥመት መፈንጫ፡
የመጥፎነት ማዕረግ የሙሽሪኮች ዋንጫ፡
ሽርክን ክህደትን በጥብጦ መጠጫ፡
ሙስሊሞች የለንም ዘመን መለወጫ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
[ ኑረዲን አል አረቢ 01/26/1443
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Audio
🎧تلاوة جميلة لخواتيم سورة المؤمنون

🎙 للقارئ صالح الفالح

https://t.me/https_Asselefya1
➧ልጅ መውለድን አብዙ ሲሳያችሁ ይበዛል

💭ሙሀመድ ሷሊህ አል ዑሰይሚን አሏህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ:-

➲"በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬን በማሳደር ልጆችን አታብዙ፤ ሲሳያችሁ ይጠባል ያለ ሰው በእርግጥም ግልጽ የሆነ ጥመትን ተጣሟል።

➲በአርሹ ጌታ እምላለሁ በዚህ ንግግራቸው ዋሽተዋል። ይልቁንም ልጅ ሲያበዙ አሏህ ሲሳያቸውን ያበዛላቸዋል።


➲ምክንያቱም በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ሪዝቋ በአላህ ላይ ያለ ቢኾን እንጂ፡፡ ወጪ ታደርግላቸው ዘንድ የልጆችህን ሲሳይ የሚከፍትልህ አሏህ ነው።


➲አብዛኛው ሰው ግን በጌታው ላይ መጥፎ ጥርጣሬ ያሳድራል፤ ፊት ለፊቱ ባለው በሚታየው ቁሳዊ ነገር ላይ ብቻ ይደገፋል፤ የወደፊቱንም አያይም፣ የጌታውንም ችሎታ አይመለከትም። ልጆች ቢበዙም ሲሳይን የሚለግሰው እሱ 7 ነው።ልጆችን አብዛ ሲሳይህ ይሰፋል።ትክክለኛው ይህ ነው ።"

📚ሸርህ ሪያዱሷሊሂን [1/91]


https://t.me/https_Asselefya1
➧የዕለቱ መልዕክት➛ወንድ ሁን!

ሴት ልጅ ትለምነኝ ትለማመጠኝ አትበል
ትታገልልኝ ላድክማት  ልፈትናት ልንቀባረርባት አትበል
!!

ወንድ ሁን አንዱ የውንድነት መገለጫህና ውበትህ የወንድነት መለያህ  ከላይ የተጠቀሰው በግልባጭ አንተጋ ሚገኙ ሲሆኑ ነው በቃ ወንድነሃ እነዚህ ያንተ ስራዎች ናቸው ወንድነት በፆታ ብቻ አይገለፅም በዋናነት ተግባሩ ነው ሚገልፀው!
!

ስለዚህ ቀድህ ተገኝ ለሴት ልጅ ተንበርከክጂ እንድትን በረከክልህ አትፍቀድ አሸንፍጂ አትሸነፍ  ቅደምጂ አትቀደም ኢማም ሁንላትጂ ኢማም  አትሁንልህ ፈጣን ቀልጣፋ ጂ ልፍስፍስ አትሁን ምራትጂ አትምራህ አስተዳድራትጂ አታስተዳድርህ አግባትጂ አታግባህ ለምናትጂ አትለምንህ  ምከራትጂ አትምከርህ አስተምራትጂ አታስተምርህ!!

ደግ ሁንላትጂ አትክፋባት ታዘዛትጂ አትገልምጣት እጄ አስገባኋትጂ እጄ አስገባሁት አትባል በቃ ወንድ ሁን ቀዳሚጅ ተቀዳሚ አትሁን ፈጣን እንጂ አዝግም አትሁን!

አስተዋይ እንጂ ዝፍቅ አትሁን ሚያስደስትንና ሚያስጠላን ራስህ ለይጂ ሰዎች እንዲለዩልህ አትፍቀድ ጧሊበተል ኢልምጂ ጃሂል አትሁን በቃ ቅደምምምምም  ይህ ነው በወንድ ላይ ሚያምረው ሚገልፀው ስለዚህ መገለጫዎችህን እወቅ ላንተ የሆኑትን ያልሆኑ ቦታ ላይ እንድታይ አትፍቀድ......!!

ኮፒ!

https://t.me/https_Asselefya1
➧ሀቢብቲ ያንቺ  መከናነቢያና ኒቃብሽ ⁈

በእምነትሽ ላይ ያለሽን እውቀት
የሚገልፅ ነው።  አለማወቅን መላቀቅሽንና
ብልጠትሽን እጅግ ውብ ዘመናዊነትሽን ያሳያል።


እንደመሸፋፈኛሽ አንደበትሽም ንቁና የተረጋጋ አሰተዋይ ሀቀኛ ይሆን ለማወቅ በምታደርጊው ጥረት ድክመትሽን ጃሂልነት  ያደረጉ ለሚቆነጥጡሽ ሰዎች በመልካም ባህሪ አዋቂነትሽን አሳያቸው።

አላህ በሰጠሽ እውቀት ላይ አመስጊኝ  ጭማሪን ታገኚ ዘንድ በተሰጠሽ ላይ አለማመሰገን አንድ ክህደት ነውና !!

وإذ تأذن ربكم لئن شكرتم لأزيدنكم ولئن كفرتم إن عذابي لشديد
ማወቅ ባለብሽ ነገር ላይ ጥረትን አድርጊ በጥረትሽ ላይ አላህ እንዲ ከፍትልሽ ዱዓ አድርጊ፣አስባቡንም  አድርሺ፣ስራሽን ፍፁም ለጌታሽ አጥሪ አላህ ለሹ ብሎ የታገሉትን አይጥልምና !

وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا
وَإِنَّ اللهَ لَمَعَ المُحْسِنِينَ
እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡

https://t.me/https_Asselefya1
➧ኢብኑ ተይሚያ የሱናዉ አንበሳ የሱንዮች መድረክ በቴሌግራም የሚተላለፉ ትምህርቶች ለመከታተል ከታች ባሉት አድራሻ ይቀላቀሉ!

↪️በግሩፓችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች፦

➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የጥያቄና መልስ ውድድር
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ

➲ወቅታዊ ምክሮች
➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
@IbnuTeymyaYesunawAmbesa
@IbnuTeymyaYesunawAmbesa

↪️በቻናላችን የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች

➲የአቂዳ ኪታቦች
➲የፊቅህ ግንዛቤዎች
➲የሱና ኡለማዎች ፈትዋ
➲ወቅታዊ ምክሮች

➲የቁርአን ቂርአትና ሌሎችም
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
➧ስራችን ሁለየ ለአላህ አጥርተን ከሰራን ምንግዜም ደስተኞች ነን። ነገር ግን የሰዉ ሙገሳ ፈልገን ለሰዉ ብለን ከሆነ ያ ሙገሳና ለሱ ብለን የሰራነዉ ዝም ሲሉን ሁለየ መጨናነቅ መጠበብ ነዉ። አደራ ስራን አጥርቶ በመስራት ላይ ነፍሳችንን እንታገል።

✍️Binet Aragaw

https://t.me/https_Asselefya1
➛መውደድ የቻለ ልብ መጥላትም ይችላል !!
➧ነፍስህን በከንቱ አታስጨንቃት!
እንዲያልፍህ የተፃፈ አያገኝክም
ሊያገኝክ የተፃፈ አያልፍክም...!!


➭ስለዚህ ነፍስህን አታስጨንቃት ጭንቀትም በሺታ ነው።
➲ልጆችን በመልካም ለማነፅ የሚረዱ መርሆዎች
 
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱
 
❶ለአንድ ህፃን እጅግ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ውስጥ የመጀመሪያው ስነ-ምግባሩን በመገንባት ላይ ትኩረት መስጠት ነው ።

➫ ልጅ የሚያድገው አሳዳጊው በልጅነቱ ባለማመደው ነገር ነው።

➬ቁጣን፣እንቢተኝነትን፣ችኩልነትንና ሌሎች መጥፎ ስነምግባሮችን እያየ ያደገ ልጅ በቀላሉ እነዚህን ስነ ምግባራቶች ይላበሳቸዋል።ትልቅ ሰው ሲሆንም ከራሱ ላይ ማስወገድ ይከብደዋል።
•┈┈┈┈•✿🌸✿•┈┈┈┈•     
📚ኢብኑል ቀይም (አላህ ይዘንላቸው)

➭
ተርቢያ
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
እስከ መቼ?
~
ነጋ ጠባ ስለ ብሄርህ የምታወራ፣ ጧት ማታ "ኦሮሞ፣ ኦሮሞ"፣ "አማራ፣ አማራ"፣ "ትግሬ፣ ትግሬ"፣ "አፋር፣ አፋር"፣ "ስልጤ፣ ስልጤ"፣ "ጉራጌ፣ ጉራጌ"፣ ... የምትዘምር፣ የምታለቅስ፣ ... ከሆነ መመዘኛህ ሁሉ ዘር ነው የሚሆነው። ዘር ተከትለህ ትወዳለህ። ዘር ለይተህ ትጠላለህ።
እወቅ! ያንተ ብሄር ከሌላው የሚለየው ቅንጣት ታክል ደረጃ የለውም። ደግሞም በለቅሶውም፣ በሰርጉም፣ በሀዘኑም፣ በፌሽታውም፣ በቤትም፣ በመስጂድም፣ በቡናውም፣ በጫቱም ላይ ሁሌ ስለብሄር ስታኝክ ልታፍር ይገባሃል። በብሄር አጀንዳ በተጠመድን ቁጥር በሌሎች ላይ ጥላቻ እየጨመርን ነው የምንሄደው። አንድ ሰው ዘረኝነት ልቡን ከተቆጣጠረው ሰውነቱን ያጣል። በመንጋ እንደሚጓዝ አውሬ ያለ ምክንያት ያልመሰለውን ሁሉ ይናከሳል። "ቆይ እኛ ቤት ትመጣለህ!" እንደሚል ህፃን ከደጃፉ ያገኘውን ሁሉ ያጠቃል። ደግሞም ሁሌ ሌላውን ብሄር እያብጠለጠልን ከሌላው አክብሮትን ልንጠብቅ አይገባም። Respect is a two-way street!
ወንድሜ ሆይ! ሰው ሁን። ጭንቅላትህን ካልተጠቀምክበት ላንገትህ ሸክም ሆኖ ቢንገታገት ምን ይሰራል?! ሰው ሰርቶ ሲለወጥ "ከኛ የሰበሰበው ገንዘብ ነው" አይነት ቅናት የወለደው ብሶት አታንቋር። ከቻልክ እንደሰው ሰርተህ ተለወጥ። ካልሆነልህን እራስህን በቅናት አታቃጥል። "ምቀኛ ከራሱ ማግኘት ይልቅ የሌላው ማጣት ነው የሚያሳስበው" ይባላል።
ዘረኝነት ተደጋግፈን እንዳንኖር የተጋረጠ እጅግ አደገኛ በሽታ ነው። በዚህ ዘመን በየቦታው ለሚደርሰው ግጭትና እልቂት ቀዳሚው ምክንያት ዘረኝነት ነው። ሌላው ቀርቶ በየመስጂዱ ሳይቀር እየገባ ሰዎችን ልብ ለልብ እያራራቀ ነው። ችግሩ በዚህ መጠን እንዲያውም ከተገለፀውም በከፋ ደረጃ ቢሆንም የዲን አስተማሪዎች ግን አብዛኞቹ ደራርበው ተኝተዋል። ከፈሎቹማ ጭራሽ የችግሩ አካል ናቸው። ጥቂቶች ደፍረው የሚናገሩ ከኖሩም አንዳንዶቻችን "እኛን ለመንካት ነው" ብለን ደርሰን የምናኮርፍ፣ ልባችን በጥላቻ የሚጓሽ ሆነናል። ይሄ በጣም የሚያሳፍር ነው።
ብቻ ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም። ጥንብ በሆነው ዘረኝነት የተነሳ ከማንወጣበት አዘቅት ውስጥ እየገባን ዝም ብሎ ማየት አያዋጣንም። ስለዚህ በቃ ልንል ይገባል። እስካሁን የደረሰብን ጉዳት ለመማር ከበቂ በላይ ነው። ነገ የነ ርዋንዳ አይነት እልቂት እንዳይገጥመን ጥርሳችንን ነክሰን ችግሩን ልንጋፈጠው ይገባል። ባግባቡ መወቃቀስ ባለመቻላችን ይሄው በድንቁርናው የሚኮፈስ፣ ድንዛዜውን "በክብር" ሰቅሎ የሚያሳይ ገራሚ ትውልድ መጥቶልናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor