💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
017 ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
♦️አዲስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

▪️كتاب منهاج الفرقة الناجية والطائفة المنصورة

➲ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ

▪️ክፍል አስራ ሰባት
〰〰〰〰〰

♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➘➘➷➷➴➴➘➘➷
https://t.me/https_Asselefya1/3725

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/https_Asselefya1
➲ብዙ ሴቶች ስለትዳር ሲነሳ የሚያሳስባቸው፦
➧ ቬሎ እና ጫማ
➧ሂና ፕሮግራም
➧የሚጠራ ሰው ብዛት
➧ሜካፕ ባለሙያ
➧ደረጃ 1 "ኢስላሚክ" ዲጄ
➧ ካሜራ ማን
➧ ፎቶ ሽርሽር...እና መሰል ቅራቅንቦዎች ሲሆኑ

➲እውነተኛ ሙስሊም ሴት የሚያሳስባት ደግሞ

➛የባል የኢማን ደረጃ
➛ የባል የከስብ ምንጭ ሃላልነት
➛ ለሚጠብቃት ሃላፊነት የሚሆን እውቀት እና የመሳሰሉት እጅግ ወሳኝ ነጥቦች ናቸው።

➧ሴቶች ሆይ! አላህ ለቅራቅንቦ ከመጨነቅ ያውጣችሁ፥ ሁለተኛው ምድብ ላይ ያላችሁ አላህ ያጠንክራችሁ።

(ፉላን አል-ሐበሺ)
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
▪ይህ 🎙በወንድማችን አቡ ዑሰይሚን ሓፊዘሁላህ 30ጁዝ ሙሉ ቁርአን እጂግ ባማረናዉብ በሆነ ተቀርቶ የተጠናቀቀ ድምፀ ፍይሎች የሚገኝበትቻናል ነዉ!

➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛
➧ቁርአንን በትኩረት አዳምጥ!
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛
✅ቁርአን ስታዳምጥ፦

↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
➧ውስጥህ ይረካል!
➧ጭንቅህ ይወገዳል!
➧ኢማንህ ይጨምራል!
➧መንፈስህ ይታደሳል!
➧ቀልብህ ይረጥባል!
➧አላህ ይወድሀል!
➧ሸይጧን ይርቅሀል!
➧አይምሮህ ይደሰታል!
➧ትልቅ ወኔ ይሰማሀል!


🎙قارئ: عَبْدُالرَّحْمَٰنْ إِبْنُ زْنَابي الإتيوبي
↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/tilawaAbu_Useymin
https://t.me/tilawaAbu_Useymin
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የመልካም ሚስት ስብዕና ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➧ባሏን አፍቃሪ ➻➻➻➻➻➻ ▪️تزوّجوا الودود الولود ، فإني مكاثِرٌبكم الأمم يوم القيامة ➲"አፍቃሪ እና ወላድ የሆነችን ሴት አግቡ፣ ምክንያቱም እኔ የቂያማ ዕለት (ከሌሎቹ) ሕዝቦች ጋ እፎካከርባችኃለሁና። ስለሆነም አንዲት ሚስት ልጆችን ለመውለድ ጥረት ማድረግና ለዚህም የሚያስፈልጉ ሰበቦችንም ማድረስ ይጠበቅባታል።…
➲የመልካም ሚስት ስብዕና
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻

➭አላህን ከፈሩ
〰〰〰〰〰

➲የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ቀጥለው እንድህ አለ:-

▪️وَشَرُّنِسَائِكُمُ المُتَبَرِّجَاتُ

➛ከሴቶቻችሁ መካከል መጥፎዎቹ (ከባሎቻቸው ውጭ ላሉ አካላት) የሚገላለጡ ናቸው።

➧ይህ ማለት:- (በአግባቡ ሂጃቧን ሳትለብስ) ውበቷን አጋልጣ የምታሳይ፣ ተጋጊጣ፣ ሰውነቷን አጋልጣ፣ ተሺቀርቅራ፣ ሺቶ ተቀባብታና ተኳኩላ የሸይጣን ጋሻ ጃግሬ እና ማህበረሰቡን ለማበላሸት ላዘጋጀው ወጥመድና የጥፋት አላማ አጋዥ ልትሆን የምትወጣ ሴት ማለት ነው።

ይህ ባህሪ ተላብሳ ተገላልጣና ተጋጊጣ በዚህ መንገድ የምትወጣ ሴት በእውነቱ ካስተዋልነው ከኢብሊስ ወታደሮች መካከል አንዷ ልትሆንና ምድርን በማበላሸት ላይ ለእርሱ አጋዥ ልትሆን እንደወጣች ነው በአላህ ያመኑ ሰዎችን ፈተና ውስጥ ለመጣልና የጥፋት (ዝሙት) አዘቅት ውስጥ ለመዝፈቅ ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ነው።

➲አል ሙተኸዩላህ "المتخيلات"
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

➧አል ሙተኸዩላት" አል ኹየላ ከሚለው ቃል የመጣ ሲሆን ኩራት(በራስ መደነቅ፣መጠባረርና ትምክህት)ማለት ነው ።

እዚህ ጋ በመገላለጥና በመኩራት መካከል ያለውን ቁርኝት ለማጤን እንሞክራለን። አንዲት እንስት ተገላልጣ፣ ተዋውባ፣ በሺቶ ታጥባ እና ተሺቀርቅራ ወደ ጎዳናዎችና ሱቆች ስትወጣ ለአላህ የተናነሰች ጭምት ሆና አይደለም። ይልቁኑ ተኩራርታ ራሷን ሰቃቅላና ከፍ ከፍ አድርጋ ነው የምትወጣው በዚህ ተግባር ውስጥ ታድያ ኩራት በራስ መደነቅ በተክለ ሰውነቷ በማራኪነቷ መደመም ይኖራል።

➠በመሆኑም በኩራትና በመገላለጥ መካከል ቁርኝት አለ ልክ በመሸፋፈን (በሂጃብ) እና በሀያዕ ጥምረት እንዳለ ሁሉ።

በአግባቡ ሂጃብ የለበሰች እንስት በሃያዕ የተዋበችና ልቧ በእርሱ የተሞላ ነው። የተገላለጠች እንስት ደግሞ የሃያዕ ጅልባቧን አሺቀንጥራ ጥላ በምትኩ የኩራት፣ በራስ የመደመም፣ ራስን የማታለልና የመጠባረርን ካባ ደርባለች። ይህም የሚጎዳው የትዳር ህይወቷን ብቻ ሳይሆን ሙሉ ሂወቷን ምስቅልቅል ያደርግባታል።

➲ለዚህም ሲሉ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የዚህ አይነት መገለጫ ባህሪ ያላትን ሴት ከመጥፎዎቹ ሴቶች እንደምትመደብ ገልፀዋል። የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
:-

▪️وَشَرُّنِسَائِكُمُ الْمُتَبَرِّجَاتُ الْمُتَخَيِلَاتُ وَهُنَّ الْمُنَافِقَاتُ لا يَدْخُلُ الْجَنَة مِنهُنَّ إِلَا مِثْلُ الْغُرَابِ الأَعْصَمِ

➧ከሴቶቻችሁ መካከል መጥፎዎቹ (ከባሎቻቸው ውጪ ላሉ አካላት ) የሚገላለጡ፣ የሚኮሩ(እብሪተኞቹ) ናቸው፤ እነርሱ ሙናፊቆች ናቸው፤ ከእነርሱ መካከል ጀነት የሚገቡት እንደ አልጉራቢል አዕሰም በጣም ጥቂት ናቸው።

➲አል ጉራቢል አዕሰም ማለት በክንፎቹ (ጀርባ) እና በእግሮቹም ላይ ትንሺ ነጭ ያለበት (የቁራ ዝርያ) ነው እና እንደት ነው ከጥቋቁር ቁራዎች መካከል የዚህ አይነቱን የቁራ ዝርያ ለይተን ማየት የሚቻለን? በጣም በትግል አልፎ አልፎ ነው "ጉራቢል አዕሰምን" ማገኘት የሚቻለው ይሉቁኑ በአብዘሃኛው ሁሉም ክፍሎቻቸው ጥቁር የሆኑ ቁራዎች ነው የምንመለከተው።

➲ለዚህ ሲሉ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ

▪️لا يَدْخُلُ الْجَنَّةَ مِنْهُنَّ إِلا مِثْلُ الغُرَابِ الأَعصَمِ

"ከእነርሱ መካከል ጀነት የሚገቡት እንደ" አልጉራቢል አዕሰም"በጣም ጥቂት ናቸው።

➲ይህን ሲሉ የፈለጉት ከእነዚህ አይነት ሴቶች መካከል ጀነት የሚገቡት ጥቂት መሆናቸውን ለማመልከት የተጠቀሙት ምሳሌያዊ (ዘይቤያዊ) ገለፃ ነው ምክንያቱም ከጊርባኖቹ (ቁራዎቹ) መካከል የዚህ አይነት መከለጫ ባህሪ ያላቸው እጅግ በጣም ጥቂት መሆናቸው ነው
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

➧የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

🖊ام فاروق
➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
سورۃ الرَّحمن
Abu Useymin
✅የምሽት ጣፋጭ ቂርአት

🎙በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

➧https://t.me/tilawaAbu_Useymin
❍قال الله تعالى

﴿ما كانَ إِبرٰهيمُ يَهودِيًّا وَلا نَصرانِيًّا وَلٰكِن كانَ حنيفًا مُسلِمًا وَما كانَ منَ المُشرِكين﴾

صدق الله ،، وكذب دعاة الدِّين الإبراهيميِّ المزعوم ..

🏷الشيخ صالح العصيمي

➧https://t.me/https_Asselefya1
➛ከነ ጉድለትሽ አንቺ ጋር ብቻ የሚቆዩ አንቺን ከልባቸው የሚፈልጉሽ ብቻ ናቸው!
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል 1⃣1⃣3⃣➰
〰〰〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ከተውሂድ አርማዎች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➧ክፍል አስራ ሁለት ➻➻➻➻➻➻➻ ➲እነዚህ በሁለቱም ክፍል ያሉ ተውሂድን አረጋጋጭ ሰዎች - ሙቅተሲድና በመልካም ተሸቀዳዳሚዎች - የትንሳኤ ቀን ያለምንም ሂሳብና ቅጣት ጀነትን ይገባሉ፡፡ ➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡ ▪️ثُمَّ أَوْرَثْنَا الْكِتَابَ الَّذِينَ اصْطَفَيْنَا مِنْ…
➧ከተውሂድ አርማዎች
➛➛➛➛➛➛➛➛

➻ክፍል አስራ ሶስት
〰〰〰〰〰〰

➲ይህ አይነቱ ማጋራት አራት አይነት ክፍሎች አሉት

➧አንደኛው አይነት፡ የተማጽኖ ወይም የጥሪ ማጋራት

ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው፡

▪️فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ ◊◊لِيَكْفُرُوا بِمَا آتَيْنَاهُمْ وَلِيَتَمَتَّعُوا ۖ فَسَوْفَ يَعْلَمُونَ

➲“በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል፡፡ ወደየብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ፡፡ በሰጠናቸው ጸጋ ሊክዱና ሊጠቃቀሙ (ያጋራሉ)፡፡ወደፊትም (የሚጠብቃቸውን) ያውቃሉ፡፡”( አል ዓንከቡት፡65___66)

➲ሁለተኛው አይነት፡ - በሀሳብ በፍላጎትና በአላማ ማጋራት ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው የአላህ ቃል ነው።

▪️مَن كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ ◊◊ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ

➲“ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ስራዎቻቸውን (ምንዳዋን)በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን፡፡ እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም፡፡ እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው፡፡ የሰሩትም ስራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ፡፡ (በቅርቢቱ ዓለም)ይሰሩት የነበሩትም በጎ ስራ ብልሹ ነው፡፡” ሁድ፡15___16

➠ሶስተኛው አይነት፡ የመታዘዝ ማጋራት
ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው

▪️اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ

“ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለውን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸውን ፣ የመርየምን ልጅ አልመሲህንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፡፡ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው፡፡”( አት ተውባህ፡31)

➲ይህን ቁርኣናዊ አንቀጽ አስመልክቶ ረሡል صلى الله عليه وسلم ለዓድይ ብን ሀቲም ረድየላህ አንሁ የሰጡት
ትንታኔ ምንም አይነት ችግር የሌለበት ተስማሚ ትንታኔ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم ለዓድይ ጥያቄ አቀረቡ “እኛ እኮ አንገዛቸውም” የሚል ምላሽ ሰጠ፡፡ ረሡልም እነሱን በመማጸን ብቻ ሳይሆን ክልክል በሆኑ ነገሮች እንኳ እውቀት ያላቸውንና ያለእውቀት አላህን እንገዛለን የሚሉ ባህታውያንን መታዘዝ አምልኮት እንደሆነ ለዓድይ ግልጽ
አደረጉለት፡፡


➧አራተኛው አይነት፡ በፍቅር ማጋራት
ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው።

▪️وَمِنَ النَّاسِ مَن يَتَّخِذُ مِن دُونِ اللَّهِ أَندَادًا يُحِبُّونَهُمْ كَحُبِّ اللَّهِ ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ وَلَوْ يَرَى الَّذِينَ ظَلَمُوا إِذْ يَرَوْنَ الْعَذَابَ أَنَّ الْقُوَّةَ لِلَّهِ جَمِيعًا وَأَنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعَذَابِ

➲“ከሰዎችም ከአላህ ሌላ ባላንጣዎችን (ጣዖታትን) አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው የሚይዙ አልሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ (ከእነርሱ) ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡ እነዚያም የበደሉት ሰዎች ቅጣትን (በትንሳኤ ቀን) ባዩ ጊዜ ሃይል ሁሉ ለአላህ ብቻ መሆኑንና አላህም ቅጣቱ ብርቱ መሆኑን (በዚህ አለም) ቢያውቁ ኖሮ (ባላንጣዎችን በመያዛቸው በተጸጸቱ ነበር)፡፡”( አል በቀራህ 165)

➛ሁለተኛው የማጋራት አይነት ፡ ትንሹ ማጋራት የሚለውን ቀጣይ ክፍል እናየዋለን◉ ◉ ◉ ◉ ◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

تأليف: فضيلة الشيخ عبدالرزاق بن عبد المحسن البدر

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】

🖊ام فاروق

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1