💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➩ክፍል ሰላሳ ሁለት ➲ ታጥቀን ተሸምረን ዛሬ ጠራናችሁ፣ መቼም ለእርዳታ ነው ጀሊል ሲፈጥራችሁ።” ➧ “እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው፣ እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው፣ እመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፣እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው፣ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፣ አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ፣በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ፣ ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር” …
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➣ክፍል ሰላሳ ሶስት

➲“ዱርር” ማለት ጉዳት ማለት ነው። ጉዳታችንን እንዲያነሳልን የምንጠይቀው አላህን ብቻ ነው። ይህ ነው የነብያት አስተምህሮት። ብዙ መከራዎችን ስላስተናገዱት ነብዩላህ አዩብ (ዐለይሂ-ስሰላም) አላህ እንዲህ ይላል፡-

۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

➩አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡



➧"ነስር” ማለት ደግሞ “ድል” ማለት ነው። ሁለቱንም የሚሰጠው አንድየው ጌታ ብቻ ነው"የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር፣ ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር፣ ተምኪን የተሰጠው ዟሂር ወባጢን፣ እኔ ያለሁበት እክጀላ በር፣
ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር፣ ስንቱን አሳደገው ገና በነዞር (በእይታ)፣ ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ ይዐጂብ ነበር፣ እንኳን ሰው መላኢካ ያደምጠው ነበር።”



➲"አንቱን የሚጠራ እሱ ልቡ ጠራ፣
የለበት መከራ አኼራ ሲጥጠራ”
ለጭንቅ ለችግር የሚጥጠራው አላህ ብቻ ነው። አላህን ትቶ ሌላን የሚጠራ ልቡ በሺርክ የቆሸሸ ነው። ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ መኖርያው እሳት እንደሆነ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ነግረውናል።



➣"እንዳንቱ የሚሆነኝ መቼም አላገኝ፣
ዘይኔ ቅረቡኝ ጣል አታድርጉኝ”
"ካንቱ ጋር የዋለ ምንኛ ታደለ፣
ነቢ ነቢ እያለ ጭንቀቱ ቀለለ፣ እኔም ልጥራዎት ጨንቆኛልና፣ ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና”። ይጣራል ይጮሃል የናንተው ለፍላፊ፣ የሊበኖቹ ልጅ ሙሀመድ ሻፊ፣ በዱንያም በአኼራም ሁኑልን ደጋፊ” እውነት ይሄ ለፍላፊ ያለመውን ያገኛል?
ሃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፡-

أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

➧“ምንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ ላይ) ያጋራሉን! ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን?!)”
[አልአዕራፍ፡ 191- 192]

"ና በሉት ኸይረል ወራ፣ ሳልሞት ሳልሄድ አኼራ፣ ያቺን ረውዳ ዚያራ፣ የጀነትዋን አርዴ” "ካልመጣሁኝ መዲና፣እኔስ የለኝም ጤና፣ እንድሆንሎት ደህና፣ ቶሎ ጥሩኝ አህመዴ፣ኒዛሙል መደዴ” "ዘይኔ ይበቃናል ኑ በሉን መዲና፣ ሀይ እንድናደርገው ሁሌ የርሶን ሱና”
"ቀልቤእኮአንቱጋርነው፣ ፍላጎቱ ረውዳ ነው፣ ዘይኔ ና በሉት ፈጥነው፣ የቀረውን ጀሰዴን” መካና መዲና በእሳትና በውሃ ቢታጠርም፣ እርሶ ይጥሩን እንጂ አንቀርም።” ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ፣ ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ፣ መዲና ና ይበሉኝ”

➲ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ወደ መቃብር ከገቡ በኋላ ይህን የማድረግ ስልጣኑ አላቸውን?በጭራሽ!! ስልጣን እና ድርሻ የላቸውም። አለምን ማስተናበር ህያው የሆነው የማይሞተው አላህ ስልጣን ብቻ ነው።

"የፍቅር ነጋሪ ዝም ብየ ልምጣ፣ “
እባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፣
ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)
◉

◉
◉✍ኢሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Kitabu Tewhid #53
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ርዕስ باب قول الله تعالى (إِنَّمَا ‌ذَٰلِكُمُ ‌ٱلشَّيۡطَٰنُ يُخَوِّفُ أَوۡلِيَآءَهُۥ فَلَا تَخَافُوهُمۡ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ)

↪️ ክፍል 5⃣3⃣↩️
〰〰〰〰〰〰

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅ اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ
◾️በእነርሱ ላይ ሸይጧን ተሾመባቸው፡፡ አላህ ማስታወስን (ዚክር) አስረሳቸው፡፡
✅ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ
◾️እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው፡፡
✅ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ
◾️ንቁ! የሸይጧን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

📚(ሱረቱ አል-ሙጀድላህ - 19)
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧አላህ ሆይ! በዲናችን ላይ እርግጠኛነትን (የቂንን) ስጠን!!

➲ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–

“አንድ ሰው በቁርኣን ላይ ያለው እምነት በጠነከረ ቁጥር አላህ በሌሎች መፅሃፎች ሊያገኘው የማይችለውን የእርግጠኛነትን ማስረጃ ይከፍትለታል፣ በመሆኑም እናንተንም ራሴንም ቁርኣንን እያስተነተኑ በማንበብ በቁርኣን በመተግበር ላይ ሙሉ የሆነን ማነሳሳትን አነሳሳለሁ፣ እሲቲ ወደ ቁርኣን ተመለስና ለልብህ ከኢማን፣ከልብ መከፈት፣ ከልብ ኑር፣ ከፊት ኑር፣ ምን እንደሚያስገኝልህ ተመልከታት፣ በዚህም ተሞክሮን ውሰድ።”

ምንጭ:– ሸርህ አልካፊየቱ ሻፊያህ 4/166

➧ውድ እህቶቼ በአሁኑ ሰአት ማሻአላህ አብዘሃኞቻች የሱና እህቶች ኪታብን ለመቅራት የምናደርገውን ጥረት ያክል ቁረአን ላይ እያደረግን አይደለም! ኪታብ መቅራታችን እንዳለ ሆኖ እያለ ከቁረአንም መራቅ የለብንም ቁረአንም ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን!

➧መሀፈዙ ቢከብደን በቲላዋ እያስተነተን መቅራት አለብን አላህ ያግራልን ሁላችንንም ቁረአን በመቅራት ላይ አደራ እላችኃለሁ ያአኽዋቲ ቁረአን የደረቀች ልብን ታረጥባለች ወደ ጌታችን ታቃርበናለች!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➣ክፍል ሰላሳ ሶስት ➲“ዱርር” ማለት ጉዳት ማለት ነው። ጉዳታችንን እንዲያነሳልን የምንጠይቀው አላህን ብቻ ነው። ይህ ነው የነብያት አስተምህሮት። ብዙ መከራዎችን ስላስተናገዱት ነብዩላህ አዩብ (ዐለይሂ-ስሰላም) አላህ እንዲህ ይላል፡- ۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ…
➭መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሰላሳ አራት
〰〰〰〰〰〰

➲ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ወደመቃብር ከገቡ በኋላ ይህን የማድረግ ስልጣኑ አላቸውን? በጭራሽ!! ስልጣን እና ድርሻ የላቸውም። አለምን ማስተናበር ህያው የሆነው የማይሞተው አላህ ስልጣን ብቻ ነው።

➴“የፍቅር ነጋሪ ዝም ብየ ልምጣ፣
እባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፣
ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)” ምንም አይነት ሃተታ፣ ምንም አይነት ውትወታ አይፈይድም።


➛ከኢስላም አምስቱ ማእዘናት አንዱ ሐጅ ነው። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ያስተማሩት “የቻለ ሰው ቤቱን ይጎብኝ” ብለው ነው እንጂ “ያልቻለ ሰው እኔን ይማፀን” ብለው አይደለም። ውትወታችን ሊሆን የሚገባው ወደ ሁሉን ቻዩ ጌታ ነው።

➴“የአላህ አፈ ንጉስ የአላህ ቢተወደድ፣
ኧረ የት ይገኛል እንደ ሙሐመድ፣


➷➷ወዳጅ የሚረዳው ሲገቡ በላህድ (በቀብር ውስጥ)”

“አንተ የጠይባው ነጋዴ፣
ሰላም በልልኝ አህመዴን፣
አንቱ የጅብሪል ጓደኛ፣
አትርሱን ቀብር ስንተኛ”

➮ቀብር ስንተኛ እራሳችን በነፍስ ወከፍ ለተጠየቅነው ጥያቄ መልስ እንሰጣለን እንጂ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለማንም ቀብር ውስጥ ምንም ማድረግ አይችሉም። እያንዳንዱ ሰው ቀብር ውስጥ መልካምም ይሁን መጥፎ የራሱን ስራ ያገኛል።


➷➷“ያሙሀመዲ ያሀቢቢ፣
ያሙሀመዱ ኩን ጠቢቢ (ዶክተሬ ሁኑ)፣
ወአጂርኒ ሚን ለሂቢ (ከሚንቀለቀለው እሳት ጠብቁኝ)፣
ኢነ አውዛሪ ሲቃል (ወንጀሎች ከባድ ናቸውና)”


➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ግን ዘመዶቻቸው ለሳቸው ባላቸው ቅርበት እንዳይሸወዱ ይልቁንም ተውሒድን በመያዝና ከሺርክ በመራቅ እራሳቸውን እንዲያተርፉ አላህ እንዲህ ሲል አሳስቧቸዋል፡-

وَأَنذِرْ عَشِيرَتَكَ الْأَقْرَبِينَ الشعراء: ٢١٤

“ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህን አስጠንቅቅ!!”
[አሽሹዐራእ፡ 214]

➲ይህቺ አንቀፅ በወረደች ጊዜ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم” (የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! ነፍሳችሁን ከአላህ ግዙ። ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም። የዐብዱል ሙጦሊብ ቤተሰቦች ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም።የዐብዱል ሙጦሊብ ልጅ ዐባስ ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይድህም። የዐብዱል ሙጦሊብ ልጅ ሶፍያ ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም። የመልእክተኛው ልጅ ፋጢማ ሆይ! ከገንዘቤ የፈለግሽውን ጠይቂኝ። ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይድሽም።” [ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
206]

➷➷ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ! ወገኖቼ ሆይ! ከሰማይ በወረደው ማሳሰቢያ መሰረት ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለኔ ባላችሁ ቅርበት እንዳትሸወዱ። በተግባር
እራሳችሁን አትርፉ እያሉ ነው። ለአብራካቸው ክፋይ ለፋጢማ ረዲየላሁ አንሃ ያልፈየዱትን ላንተ የሚፈይዱ ይመስልሃልን? ከልብ ሁነህ አስተውል
!!

➴➴“ነቢ አንቱን እያለ፣
ቀልቤ ጥሎኝ ዋለለ፣
ወዳሉበት ደወለ፣
ሄሎ በሉት አሕመዴ”

➴➴ “አንቱ ኖት ረሃቤ ጥሜ፣
ልንገሮት አስቀድሜ፣
ያላንቱ አይሞቅም ደሜ፣
ግቡልኝ በጀሰዴ”


➴➴“ሰብርም የለኝም አለሁኝ ታምሜ፣
መንገዱ ጠፍቶብኝ አልቻለም አቅሜ፣
ጉልበቴ ብርታቴም ባንቱ ነው መቆሜ”

➴➴“ሳዳቴ አደራ አሁን ለምነናል፣
ሁላችን በጅምላ አድሉን ብለናል፣
ዱስቱር ዱስቱር ብለን እዛው አፍጠናል፣
አትጨክኑብን እርሶን ለምነናል፣
ይኸው ደውለናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን፣
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
አርበዒን 41ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ ሐዲሥ ቁጥር – 4⃣1⃣

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ክሪስማስ (ገና) ❌
➖➖➖➖➖➖➖

✅ የአይሁዶችና የነሷራዎችን አመት በአል ማክበርም ሆነ በበአሉ ላይ መገኘት እንደማይቻል ኢማሙ አህመድ ይህንን የቁርአን አንቀፅ እንደ መረጃ ጠቅሷል።
☑️ وَٱلَّذِينَ لَا يَشْهَدُونَ ٱلزُّورَ وَإِذَا مَرُّوا۟ بِٱللَّغْوِ مَرُّوا۟ كِرَامًا
➡️ እነዚያም እብለትን የማይመሰክሩ፤ በውድቅ ቃልም (ተናጋሪ አጠገብ) ባለፉ ጊዜ የከበሩ ኾነው የሚያልፉት ናቸው፡፡ (ሱረቱል ፋርቃን 72)
📚مجموع الفتاوى لابن تيمية ٣٢٥/٢٥
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አምስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ▪️ሱፍያን ብን ዑየይናህ - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "من فسد من علمائنا ففيه شبه من اليهود ، ومن فسد من عبادنا ففيه شبه من النصارى" ➧“ከዑለማዎቻችን የተበላሹት ከአይሁድ ጋር መመሳሰል አላቸው። ከዓቢዶቻችን(ያለጥልቅ እውቀት አላህን…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ስድስት

➠በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ይናገሩ ነበር፡
"ليتني أنجو من علمي – يقصد من العلم الذي تعلمه – كفافا ، لا لي ، ولا علي"

“ለእኔም ሳይኖረኝ በእኔም ላይ ሳይኖር ከእውቀቴ (ሳልጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ፡፡”

➛በዚህም ፣ ሰለፎች የተስተካከለ እውቀትና ተግባር እያላቸው ምን ያክል አላህን እንደሚጠነቀቁና እንደሚፈሩ ያመላክታል፡፡

▪️ሀሰን አል'በስርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"إن المؤمن جمع بين إحسان ومخافة ، والمنافق جمع بين إساءة وأمل"

✅“ሙእሚን መልካምንና ፍርሀትን አጣምሮ ይዟል፡፡ ሙናፊቅ ደግሞ ክፉ ስራንና መልካም ተስፋን አጣምሮ ይዟል፡፡” አዝ ዙህድ ሊብኒ አል ሙባረክ፡985

▪️ዓብደሏ ብን አቢ'ሙለይካ -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
"أدركت أكثر من ثلاثين صحابيا كلهم يخاف النفاق على نفسه"

➤“ሁሉም ኒፋቅን በነፍሳቸው ላይ የሚፈሩ ከሰላሳ የሚበልጡ ሶሃቦችን አግኝቻለሁ፡፡”
ቡኻሪ በሶሂህ ታባቸው ኪታቡ አል ኢማን ባቡ ኸውፉል ሙእሚን ላይ በተዕሊቅ አውርትታል

➲ለአማኞች በአንድ ላይ ሁለት ታላላቅ ደረጃዎችን አጣምሮላቸዋል፡፡ በመልካም መታዘዝንና ያማረ ተግባርን እየሰሩ ስራችንን ከእኛ አይቀበልም ብለው አላህንእንዲፈሩ አድርጓቸዋል፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوا وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ

እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡አል ሙዕሚኑን 60

➲“እነዚህ አስካሪ መጠጥ የሚጠጡ ፣ ዝሙት የሚፈጽሙ ፣ የሚሰርቁ ናቸው?” በማለት ስለዚህ ቁርኣናዊ አንቀጽ ትርጓሜ ረሡልን صلى الله عليه وسلم ጥያቄ አቀረብኩላቸው ትላለች ዓኢሻ ረድየሏህ አንሃ ረሡልም صلى الله عليه وسلم፡ - “አይደለም፣ የ (አቡበክር) ሲዲቅ ልጅ ሆይ! ነገር ግን እየጾሙ፣ እየሰገዱ ፣ እየሶደቁ ከእነርሱ ይህን መልካም ስራችንን አላህ ላይቀበለው ይችላል ብለው ስጋት ያደረባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በመልካም የሚሽቀዳደሙ ናቸው፡፡” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡25263 ቲርሚዚይ፡ 3175ኢብኑ ማጀህ፡4198

✅አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናገረ፡

وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ

“(ኢብራሂምና) ኢስማኢልም “ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡”
አል በቀራህ፡127

➧ውሀይብ ብን አልወርድ- ረሂመሁሏህ- ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበና አለቀሰ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገረ፡-

"يا خليل الرحمن ترفع قوائم بيت الرحمن وأنت مشفق أن لا يقبل منك!"

➭“የአላህ ወዳጅ (ኢብራሒም) ሆይ! የአላህን ቤት መሰረቶች ከፍ ታደርጋለህ፡፡
እንደገና ይህን ስራየን አላህ ላይቀበለኝ ይችላል ብለህ ትጨነቃለህ
፡፡” ተፍሲር ኢብኑ ከሲር፡1/206
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ዚና የሰሩት አይሁዶች ታሪክ
Sheikh Muhammed Zeyn
➧ዚና የሰሩት አይሁዶች ታሪክ


🎙ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ሸይኽ አደም
Audio
♦️ تلاوة من سورة المؤمنون
♦️ القارئ: #صالح_الفالح
•••━══❁✿❁══━•••
✅ ማራኪ ቲላዋ
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③⑧➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🖋 قال العلامة ابن عثيمين رحمه الله :

أهم كتاب يعتني به طالب العلم كتاب الله عز وجل؛ لكن ليكن تلقيه لمعاني كتاب الله عز وجل من الكتب الموثوقة في التفسير التي قام بتأليفها علماء موثوقون في علمهم وفي دينهم وفي أمانتهم ، ثم بعد ذلك ما صح من أحاديث رسول الله صلى الله عليه وعلى آله وسلم .

📚 فتاوى نور على الدرب : (٢٣/٢).
አርበዒን 42ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ ሐዲሥ ቁጥር – 4⃣2⃣

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Forwarded from MuhammedSirage M.Noor (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ከአላህ ውጭ ሌሎች አካላት (ነቢያቶች ፣ ወሊዮች እና ሌሎችም ፍጡራን ) እንዲመለኩ ጥሪ የሚያደርግ በሙሉ መሃይም ነው!

ቁርአን ን ፣ ሐዲስን ፊቅህን እና በርካታ የዱንያ ትምህርቶችን አብዝቶ ቢያውቅና ቢሸመድድም እንኳን ፍጡራንን የሚመልክ ሁሉ መሃይም ነው!

قُلْ أَفَغَيْرَ ٱللَّهِ تَأْمُرُوٓنِّىٓ أَعْبُدُ أَيُّهَا ٱلْجَٰهِلُونَ
«እናንተ መሃይማን ሆይ! ከአላህ ሌላን እንድግገዛ ታዙኛላችሁን?» በላቸው፡፡
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➭መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሰላሳ አራት 〰〰〰〰〰〰 ➲ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ወደመቃብር ከገቡ በኋላ ይህን የማድረግ ስልጣኑ አላቸውን? በጭራሽ!! ስልጣን እና ድርሻ የላቸውም። አለምን ማስተናበር ህያው የሆነው የማይሞተው አላህ ስልጣን ብቻ ነው። ➴“የፍቅር ነጋሪ ዝም ብየ ልምጣ፣ እባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፣ ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)”…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሰላሳ አምስት
➛➛➛➛➛➛➛➛

➧ይኸው ለምነናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን”
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ከደካማ ፍጡር ዘንድ የሚያፈጥ አካል ከለማኝ ፊት እንደቆመ ለማኝ ነው።ተለማኙ የማይሰማ የማይለማ፣ በቀብር ያውም በሩቅ ያለ ሙት ሲሆንስ? አሳዛኝ ነው።ጥሪን የሚሰማ፣ ተማፅኖን የሚቀበል ጌታ እያለ ይህን ያክል ከደካማ ፍጡሮች ያውም ከማይሰሙ ጋር ይህን ያክል ሙጭጭ ማለት ክፉ በሽታ ነው። በብቸኝነት ሊለመን የሚገባው አላህ ብቻ ነበር። ባርያዎቹ ሲለምኑትም መልስ የሚሰጠው እሱ ብቻ ነውና።

አላህ እንዲህ ይላል፡

وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ

“ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ።” [ጋፊር፡ 60]

➭በጅምላም ይበሉት በችርቻሮ ከአላህ ውጭ የሚለመኑት ምንንም መስጠትም
ሆነ መከልከል አይችሉም።ነፍሱ ላይ ጨክኖ ከአላህ ውጭ እያመለከ
“አትጨክኑብን” እያለ መጮሁ
ይገርማል።

➴➴“ግቡልን በማለት ጠራ መሀይሙ፣
አንተን በመውደዱ ሄደለት ህመሙ፣
ልቡ ተሸበረ እንዳየህ በህልሙ፣
አንተ ነህ ፀሎቱ ስግደትና ፆሙ፣
መወትወት ጀመረ ቢፈላበት ደሙ”


➧እኛ ስግደታችንን፣ እርዳችንን፣ ህይወታችንን እናም ሞታችንን የነብዩም صلى الله عليه وسلم ይሁን የሌሎች ፍጡራን ጌታ ለሆነው ለአንድ አምላክ አላህ ብቻና ብቻ በእርሱም ላይ ማንንም ሳናጋራ እንድንገዛው ነው የታዘዝነው።

የፍጡራኑን ጥሪ ሰሚ አላህ ብቻ ነው።
ከአላህ ውጭ ያሉትን ማንንም ይሁን ማን ቢወተውቱት ምንም መስጠጥም ሆነ
መከልከል አይችልም።

➴➴ “ሰላም አለይኩም ነቢ ያሰይደል አለሚን ፣
እያዩ መባዘኔን ምነው ጨከኑ በእኔ”

➧ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሱን መባዘን አያዩም። አያውቁምም። እሳቸውን በመጣራቱም ከጌታው ጋር የሚያጣላው ትልቁ ሺርክ ላይ ከመውደቁ ውጭ የሚያተርፍለት ነገር የለም። እሳቸውን “ጨከኑብኝ” እያሉ ማናገርም አደበ ቢስነት ነው። “ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ
ይለቀልቃል።”


➧ በጭንቀት ጊዜ ማንን ይለምናሉ?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➠የድሮዎቹ አጋሪያን የሚታወቁት በሰላሙ ጊዜ በማጋራት እና በጭንቀት ጊዜ ለአላህ ሃይማኖትን ያጠሩ ሲሆኑ እሱን በብቸኝነት በማምለክ ነበር።

فَإِذَا رَكِبُوا فِي الْفُلْكِ دَعَوُا اللَّهَ مُخْلِصِينَ لَهُ الدِّينَ فَلَمَّا نَجَّاهُمْ إِلَى الْبَرِّ إِذَا هُمْ يُشْرِكُونَ

“በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜም አላህን መገዛትን ለእርሱ ብቻ ያጠሩ ሆነው ይጠሩታል። ወደ የብስ (በማውጣት) ባዳናቸው ጊዜም ወዲያውኑ እነርሱ (ጣዖትን) ያጋራሉ።”
[አልዐንከቡት፡ 65]

➛የዛሬዎቹ አጋሪያን ግን በሰላሙም በችግሩም ጊዜ በአላህ ላይ ያጋራሉ። በዚህ ንኡስ ክፍል ላይ ይህንን እውነታ የሚያሳዩ የመንዙማ ስንኞችን እንመለከታለን፡-

➴➴ሪጃለላህ ያሪጃለላህ፣
የአህለል በይቲ አጊሱና ቢላህ
”

➧ትርጉሙም፡- “እናንተ የአላህ ወንዶች ሆይ! እናንተ የአላህ ወንዶች ሆይ!
የነብዩ ቤተሰቦች ሆይ! በአላህ ይሁንባችሁ ከዚህ ጭንቀታችን ገላግሉን።”

➴➴“ያ ረሱለላህ አል መደድ”

ትርጉሙም፡- “አንቱ የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርዳታዎትን።”

➴➴ “ሰላሚ አላ ገውሰል ዒባዲ፣
ዳኢመን ቢላ ዐደዲ”
ትርጉሙም፡- “የባሪያዎች የጭንቅ ገላጋይ የሆናችሁት ሆይ! ሰላም በናንተ ላይ ይሁን። ዘወትር ስፍር ቁጥር የሌለው።”

➴➴ “አጊሱና ገውሱ፣ አሊዩል ጎንደሪ”
ትርሙም፡- “የጭንቅ ገላጋይ የሆኑት አሊዩል ጎንደሪ ሆይ! ከጭንቀት ገላግሉን።”

◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
‏القارئ حمزة معاذ | ما تيسر من سورة الأعراف | رمضان 1440 هـ -…
♦️ تلاوة من سورة الأعراف
♦️ القارئ: #حمزة_معاذ
•••━══❁✿❁══━•••
✅ ማራኪ ቲላዋ
✅ የቁርአን ግብዣ
18 Al-Kahf
Abdul Wadood Haneef
📖سورة الكهف
ሱረቱል ከህፍ ⤴️⤴️⤴️

🎙 ቃሪዕ _አ/ወዱድ ሀኒፍ

📌((قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين))

💢የአሏህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አሏህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል)