💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ ብሎ ሲደሰት" እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ። በነገራችን ላይ ይሄ "የጌታ መውሊድ" ብለው የሚያከብሩት የገና በአል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ በቅድመ-ክርስትና ከነበረው የጣኦታውያን እምነት የተኮረጀ ነው። በዚያ ላይ ዛሬ የጎርጎሮሳዊውን አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት December 25ም ሆነ "የኢትዮጵያውን" አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት ታህሳስ 29ም በርግጠኝነት ዒሳ (እየሱስ) የተወለዱበት ቀን አይደለም።
-
መነሻ ሃሳቡ ዋትሳፕ ላይ ያገኘሁት 0ረብኛ ፅሁፍ ነው።
==
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊ የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል አራት ➻➻➻➻➻➻ ➧“ሙስነድ ኢማም አህመድ” ኪታብ ላይ በራእ ብን ዓዚብ ረድየላህ አንሁ ካስተላለፈው ረጅም ሐዲስ ውስጥ የሚከተለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ንግግር ይገኝበታል፡- ▪️"ويأتيه رجل حسن الوجه حسن الثياب طيب الريح، فيقول: أبشر بالذي يسرك هذا يومك الذي…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል አምስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➠ይህ አትራፊ የሆነው ንግድ እንጅ ተወጋጅ ፣ ከሳሪ ፣ ጸጋዋና መልካሟ የሚቋረጥ ፣ባለቤቷ በቅርብ እርሷን ትቷት የሚጓዝ የሆነችው ዱንያ ንግድ አይደለም፡፡ባሪያው ከዚህ ከሳሪ የንግድ ውልና ቃልኪዳን ባለቤቶች ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡

▪️ኢማም አሽ'ሻጢቢይ ረሂመሁላህ ዑለሞች ለዚህ ጉዳይ ምሳሌ እንዳደረጉ ገልጸዋል፡- እድሜ የተሰጠው ሰው “ረእሰል ማል” (አንጡራ ሐብት) አላህ ሰጦታል፡፡ ይህ አንጡራ ሐብት በዱንያ ላይ አንድም የማይመዝነው ወይም አንድም እርሱን የማይተካ እንቁ የሆነ ሐብት ነው፡፡ “የሰው ልጅ አንጡራ ሐብቱ እድሜውና ሰዓታቱ ነው፡፡ ይህ ሐብት ፣ የሰው ልጅ ከተሰጠው ነገር ሁሉ ውድ የሆነው ሐብት ነው፡፡ ይህን ውድ የሆነ
ሐብት አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - በከሐዲዎች ላይ እንደሚከተለው ትልቅ ማስረጃ አድርጎ አቅርቦታል፡፡


➧አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

أَوَلَمْ نُعَمِّرْكُم مَّا يَتَذَكَّرُ فِيهِ مَن تَذَكَّرَ

➭“በእርሱ ውስጥ ያስታወሰ ሰው የሚገሰጽበትን ዕድሜ አላቆየናችሁምን?
አስጠንቃቂውም መጥቶላችኋል፡፡” ፋጢር፡37

➲እድሜ የተሰጠው አዋቂና ጮሌ (ብልህ) የሆነ ሰው ይህን አንጡራ ሀብት -እድሜውን ፣ ሰዓቱን ፣ ቀናቶቹን - አላህ ለሚወደው ነገር እንዴት መጠቀም
እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ሰከንዶች ፣ ቀናቶች ፣ ሌሊቶች ፣ ደቂቃዎች በማይረባ
ነገር ወይም ከአላህ ትዕዛዛ ውጭ እንዳይባክኑ ይጠነቀቃል፡፡ ወቅቱን አላህን በመታዘዝላይ ያሳልፋል፡፡


➧ ወቅቱን ለሶላት ፣ ለሐጅ እና ለመሳሰሉ አላህ ለሚወዳቸው ተግባራት ባማረ ሁኔታ ያውለዋል፡፡ ክፍት የሆኑ ወቅቶችን ሀራም ነገሮችን ከመፈጸም ይቆጠባል፤ በእነዚህ ወቅቶች አላህን ይፈራል፡፡ በቻለው ያክል መልካም ነገሮችን ያበዛል፡፡

➧ይህን አንጡራ ሐብቱን በመልካም ነገር በመጠቀም ከዓለማት ጌታ ጋር አትራፊ ንግድ ከነገደ የማይጠፋና ዘውታሪ የሆነ ሀብት ባለቤት ይሆናል፡፡ ሁረል አይንን ያተርፋል ፤ ጀነቶችን ያተርፋል ፤ የጀነት አገልጋይ ወጣቶችን (ዊልዳኖችን) ያተርፋል ፤ ያለቁጣ ከጌታው መጎራበትን ያተርፋል ፤ የተከበረውን የአላህን ፊት መመልከትን ያተርፋል፡፡

➧ይህን አንጡራ ሐብት ማንቀሳቀስን አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - (በይዕ) ፤
(ሽራእ) ፤ (ቲጃራ) እና (ቀርድ) በሚሉ ስያሜዎች ሰይሞታል፡፡ምክንያቱም የዚህ አንጡራ ሀብት ባለቤት -የእድሜውን ቀናቶች- ባማረና በተስማማ ሁኔታ አንቀሳቅሶታል፡፡


▪️በዚህ ምክንያት አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا هَلْ أَدُلُّكُمْ عَلَىٰ تِجَارَةٍ تُنجِيكُم مِّنْ عَذَابٍ أَلِيمٍ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከአሳማሚ ቅጣት የምታድናችሁ የሆነችን ንግድ
ላመላክታችሁን?”
(በላቸው) አስ ሶፍ፡10

➧ይህ ከአላህ ጋር የሚደረግ ንግድ እንደሆነ ግልጽ አደረገ፡፡

يَرْجُونَ تِجَارَةً لَّن تَبُورَ

“በፍጹም የማትከስርን ንግድ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡” ፋጢር፡29

۞ فَاسْتَبْشِرُوا بِبَيْعِكُمُ الَّذِي بَايَعْتُم بِهِ ۚ وَذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

“አላህ ከምእመናን ነፍሶቻቸውንና ገንዘቦቻቸውን ገነት ለእነርሱ ብቻ ያላቸው በመሆን ገዛቸው… በዚያም በተሻሻጣችሁበት ሽያጫችሁ ተደሰቱ፡፡ ይህም እርሱ ታላቅ ዕድል ነው፡፡” አት ተውባ፡111

مَّن ذَا الَّذِي يُقْرِضُ اللَّهَ قَرْضًا حَسَنًا فَيُضَاعِفَهُ لَهُ أَضْعَافًا كَثِيرَةً ۚ

“ያ ለአላህ መልካም ብድርን የሚያበድርና ለእርሱ (አላህ) ብዙ እጥፎች
አድርጎ የሚያነባብርለት ማነው?
” አል በቀራህ፡245
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➧አንብብ! ያነበበ ተጠቀመ ።በጣም ቆንጆ መፅሃፍ ናት አብባችሁ ተጠቀሙበት ሀቂቃ እውነተኛ ንግድ ማለት በዱኒያ ላይ ያለው ሰይሆን ሀያል ከሆነው ጌታችን ጋር ያለን ግንኙነት ምን አይነት ነው? ሁላችንም እራሳችንን እንጠይቅ!? ✍

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ ለሌሎችም ሺርርር አድርጉላቸው
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ዘረኝነት ጥምብ ናት ተዋት

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሰላሳ አምስት ➛➛➛➛➛➛➛➛ ➧ይኸው ለምነናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን” ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ከደካማ ፍጡር ዘንድ የሚያፈጥ አካል ከለማኝ ፊት እንደቆመ ለማኝ ነው።ተለማኙ የማይሰማ የማይለማ፣ በቀብር ያውም በሩቅ ያለ ሙት ሲሆንስ? አሳዛኝ ነው።ጥሪን የሚሰማ፣ ተማፅኖን የሚቀበል ጌታ እያለ ይህን ያክል ከደካማ ፍጡሮች ያውም ከማይሰሙ ጋር ይህን ያክል…
➧መንዙማ
➬➬➬➬

➲ ክፍል ሰላሳ ስድስት

➩አንዳንዶች የዚህ ስንኝ መልእክቱ “በቂያማ ቀን ስለሚኖረው ትልቁ ሸፈዐ እንጂ እነሱ በአሁኑ ሰዓት ድረሱልን እያሉ አይደለም” ይላሉ፡፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ፡-

➲በመጀመሪያ ነገር የሚሉት ነገር ውሸት ነው፡፡ እንኳን ነብዩን እና ሌሎች ስንት ፍጡሮችን እየተማጸኑ አይደለምን?

➧እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ፍጡሮችን ለዱንያዊ ጭንቅና ችግሮች የሚማፀኑባቸው በርካታ ስንኞችን እዚሁ መፅሐፍ ላይ ተመልክተናል፡፡

3. በተረፈ ሸፈዐውም ቢሆን ዛሬ ዱንያ ላይ እያለን የምንጠይቀው አላህን ብቻ ነው፡፡

➳ገውሱን ተድራ ገውስ ወልዳ ነገሰች፣
ኑሩን በኑሩ ላይ ደራርባ ለበሰች”
በመጀመሪያው ላይ ገውስ ተብለው የተገለፁት (የቃጥባሪ ሸይኽ) ሲሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አቡል ጀበልን ነው። ገውስ ማለት የጭንቅ ገላጋይ ማለት ነው። የጭንቅ ገላጋይ ደግሞ አላህ ብቻ ነው።
ኢስቲጋሳ ማለት ደግሞ በጭንቅ ጊዜ የሚደረግ ፀሎት ማለት ነው። በጣም የሚያሳዝነው ነሷራዎች እንኳን መርየምን “የጭንቅ አማላጇ” እንጂ የጭንቅ ገላጋዩዋ አላሏትም።

➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) በድር ዘመቻ ላይ በጠላት ተከበው ጭንቅ ብሏቸው የጭንቀት ዱኣ አላህን ለመኑት። አላህም መልስ ሰጣቸው፡-

إِذْ تَسْتَغِيثُونَ رَبَّكُمْ فَاسْتَجَابَ لَكُمْ أَنِّي مُمِدُّكُم بِأَلْفٍ مِّنَ الْمَلَائِكَةِ مُرْدِفِينَ

➩ ከጌታችሁ ርዳታን በፈለጋችሁ ጊዜ «እኔ በሺህ መላእክት ተከታታዮች ሲኾኑ እረዳችኋለሁ» ሲል ለናንተ የተቀበላችሁን (አስታውሱ)፡
፡ [አልአንፋል፡ 9]

أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَـٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ

➲ ወይም ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደረጋችሁ፤ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትንም አትገሰፁም።
” [አንነምል፡ 62]

➳ምልጃን ከማን እንጠይቅ?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

በቅድሚያ ሊታወቅ የሚገባው ነገር ቢኖር ምልጃ ሁሉ የአላህ መሆኑ ነው። በመቀጠል አማላጆች ለተማላጆች ማማለድ የሚችሉት አላህ ለአማላጅ እንዲያማልድ ሲፈቅድለት ለተማላጅም እንዲማለድለት ሲወድለት ብቻ ነው። ይህን ምልጃ ዱንያ ላይ የሚጠየቀው በቀጥታ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ ውጭ ያለን አካል ነብይም ይሁን መላኢካ ምልጃን መጠየቅ ሺርክ ነው። ምክንያቱም ይሄ እነሱን መለመን ነውና። ልመና ወይም ዱዓእ ደግሞ ዒባዳ ነው። ዒባዳን ለሌላ መስጠት ደግሞ ሺርክ ነው።

➲ ከዚህ በታች የምታነቡት የአገራችን መንዙማዎች ይሄው ከአላህ ሌላ በቀጥታ ነብዩ ሙሐመድን (صلى الله عليه وسلم) አማላጅ ሁኑን ሲሉ በአላህ ላይ የሚያጋሩበት ነው።"ያረሱለላሂ ሸፈዐ ይሁኑና፣ የቢላል እኮ ነን በዲኑ የፀና” እባኮት ሙሂየ:ሁኑልኝ ሸፈአየ።”

➲ ከአላህ ውጭ መመኪያ አለን?
በአላህ ላይ መመካት የአምልኮ ቁንጮው ነው። አላህ የሁሉ መጠጊያ ነው።

رَّبُّ الْمَشْرِقِ وَالْمَغْرِبِ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا هُوَ فَاتَّخِذْهُ وَكِيلًا
➳ (እርሱም) የምሥራቅና የምዕራብ ጌታ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ መጠጊያ (መመኪያ) አድርገህም ያዘው።
” [አልሙዝዘሚል፡ 9]

ባለመንዙማዎች ጋር ያለው ግን ሌላ ነው። ጥቂት ምሳሌ እንመልከት፡-

➩አንቱ የገደፉት ማን ነው የወደቀው?” ያቀመረል መካ አሰላሙ አለይካ፣ልቤ ባንቱ በእርሶ ተመካ”
ነብዩ صلى الله عليه وسلم በጠላት ተከበው ከፊታቸው ብዙ አደጋ በተደቀነበት ሰኣት እንዲህ ሲሉ መለሱ:-

الَّذِينَ قَالَ لَهُمُ النَّاسُ إِنَّ النَّاسَ قَدْ جَمَعُوا لَكُمْ فَاخْشَوْهُمْ فَزَادَهُمْ إِيمَانًا وَقَالُوا حَسْبُنَا اللَّهُ وَنِعْمَ الْوَكِيلُ

➳እነዚያ ሰዎቹ ለእነርሱ፡- «ሰዎች ለእናንተ (ጦርን) አከማችተዋልና ፍሩዋቸው» ይሉዋቸውና (ይህም) እምነትን የጨመረላቸው «በቂያችንም አላህ ነው ምን ያምርም መጠጊያ!» ያሉ ናቸው
፡፡[ሱረቱ አሊ-ዒምራን -173]

وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا

በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ።” [አል ፉርቃን፡ 58]

➧እነዚህ መንዙማ ባዮች ህያውን ፈጣሪን ትተው የሞቱት ነብዩ ሙሐመድን(صلى الله عليه وسلم)በአላህ ላይ ባላንጣ አድርገው ታላቁን መመካት የተባለውን አምልኮ አሳልፈው ይሰጧቸዋል። ይህ ታላቅ በደል ነው። አሳዛኙ ይህ አጥፊ መንዙማ በብዙ ሙስሊም ቤት የኢስላም አካል እየመሰላቸው ህፃናት ሳይቀሩ ሲያቀነቅኑት ይታያል።
◉

◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③⑨➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አርበዒን 43ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ ሐዲሥ ቁጥር – 4⃣3⃣

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ወጣቶች ሆይ!
"አግቡ፣ አግቡ፣ አግቡ
"

#ትዳርን የመሰለ ነገር የለም!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬ ➲ ክፍል ሰላሳ ስድስት ➩አንዳንዶች የዚህ ስንኝ መልእክቱ “በቂያማ ቀን ስለሚኖረው ትልቁ ሸፈዐ እንጂ እነሱ በአሁኑ ሰዓት ድረሱልን እያሉ አይደለም” ይላሉ፡፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ፡- ➲በመጀመሪያ ነገር የሚሉት ነገር ውሸት ነው፡፡ እንኳን ነብዩን እና ሌሎች ስንት ፍጡሮችን እየተማጸኑ አይደለምን? ➧እሳቸውን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ፍጡሮችን ለዱንያዊ ጭንቅና ችግሮች የሚማፀኑባቸው…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሰላሳ ሰባት

➲ስንታመም የሚያድነን ማን ነው?
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➠የሚከተለው የሺርክ መንዙማ ደግሞ በጉራጊኛ ቋንቋ ከአላህ ውጭ አቡል ጀበል የሚባለው ግለሰብ የእግርም ሆነ የእጅ ቁስላችንን ያድነናል ብለው የሚያምኑበት እና እሱን ሰውየውን በቀጥታ የሚለምኑበት ነው።

➴➴“አቡል ጀበል ሺሊላህ አቡል ጀበል ሺሊላህ፣
አሁን ትሆኝ እና መላ፣

➧የእግርም ጭዛ የእጅም ጭዛ (የእግርም የእጅም ቁስላችንን አዳኝ) አሁን ትሆኝ እና መላ (እናንተ ናችሁ የምታሽሩኝ
)”

➭የሚከተሉትም በአማርኛ መንዙማ ስንኞች ከአላህ ውጭ በሺታን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲያድኑ አድርገው ያቀረቡበት ነው ።

➴➴ “መሻር ባንቱ ነው ያደዋኡና፣
ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና”።
“የጀሊል ባለሟል የሆኑት ሃቀኛ፣
ምነው ብታሽረው ያንን በሽተኛ፣
ሙሃባው ተነጥቆ የሆነ ደመኛ፣ ሀቢቢ ሀቢቢ ሀቢቢ”


➧አላህ ፍጹም ወዳጅ አድርጎ የያዛቸው ኢብራሂም (ዐለይሂ-ስሰላም) ግን አላህን አስመልክተው ለአጋሪያን ሲየስረዱ እንዲህ ይላሉ


الَّذِي خَلَقَنِي فَهُوَ يَهْدِينِ⓼⓻وَالَّذِي هُوَ يُطْعِمُنِي وَيَسْقِينِ ⓽⓻وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ ⓪⓼وَالَّذِي يُمِيتُنِي ثُمَّ يُحْيِينِ ⓵⓼وَالَّذِي أَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لِي خَطِيئَتِي يَوْمَ الدِّينِ⓶⓼رَبِّ هَبْ لِي حُكْمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ⓷⓼

“(እርሱ) ያ የፈጠረኝ ነው። እርሱም ይመራኛል። ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው። በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል። ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው። ያም በፍርዱ ቀን ኀጢአቴን ለእኔ ሊምር የምከጅለው ነው። ጌታዮ ሆይ! ዕውቀትን ስጠኝ! በደጋጎቹም ሰዎች አስጠጋኝ።”

[አሽሹዐራእ፡ 78 _83]

➧ በአላህ እና መልክተኛው ላይ መዋሸት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭በአላህ እና በመልክተኛው ላይ መዋሸት ከባድ ወንጀል ነው። እስልምና ሃይማኖት የተገነባው ከአላህ ቃል ቁርኣን፣ ከነብዩ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم ሀዲሶች ነው። ስለዚህ አላህ እና መልክተኛው صلى الله عليه وسلم ያላሉትን ብለዋል ብሎ ማውራት በተለይ እንዲህ
የሀይማኖት ሰዎች ናቸው እየተባሉ አላህ እና መልክተኛው صلى الله عليه وسلم ላይ መዋሸት ኢስላምን መናድ እና ሙስሊሞችን ማወናበድ እና እምነታቸውን ማጭበርበር ነው።

➠ጥቂት ለትዝብት ያክል፡-
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

“መጀን በኑር ሁሴን በአሩሲው ኑር፣
የአውሉያዎቹ ሻምበል የበርም የባህር፣
ከራማው ይፋ ነው አይደለም መስቱር
እጣው እንደ ነቢይ በርዳዳው ገበር፣
የሪጃሎች አባት የነዚያ ያብራር፣
የነአህመድ ኑረላህ ዚልፈይዲል ሚድራር፣
ተብሏል አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር፣
ጌታየ ኑር ሁሴን በለኝ የኔ አሽከር፣
በዱንያ በአኼራም እንዳልቸገር፣
በናንተ የሸሸ እንዲሁም አይቀር፣
አላህ ሰጥቷቸኋል ሳይሰፍር ሳይቆጥር
።”

➴➴“ሸህ መሀመድ ፈቂህ ባለመነጠር፣
የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር”
“ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር፣
ሲፈቱ መለኪይ ዛቱ የበሸር፣
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሺር ወአንዚር፣
ጎራ እማይጋርደው ይዟል መነጠር፣
ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር፣
ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ኸጢር”
“ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር፣
እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር፣
ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር
።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ

«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡አል ተውባህ 51
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ስድስት ➠በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ይናገሩ ነበር፡ "ليتني أنجو من علمي – يقصد من العلم الذي تعلمه – كفافا ، لا لي ، ولا علي" “ለእኔም ሳይኖረኝ በእኔም ላይ ሳይኖር ከእውቀቴ (ሳልጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ፡፡” ➛በዚህም ፣ ሰለፎች የተስተካከለ እውቀትና ተግባር እያላቸው ምን…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሰባት
➛➛➛➛➛➛

➲ሶስተኛው፡- በእውቀቱ ለማይሰራ ሰው የተላለፈ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ባወቁት የማይሰሩ ሰዎች ዛቻና ውግዘት በቁርኣንና በሐዲስ ደርሶባቸዋል፡፡ አላህበተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ◆كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሰሩትን
ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡”
አስ ሶፍ፡2_3

۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

“እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን?
ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን
?” አል በቀራህ፡44
▪️ስለ ሹዓይብ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል


وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ عَنْهُ

“ከርሱ ወደከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡” ሁድ 88

▪️በዚህ ርዕስ ዙሪያ የቁርኣን ማስረጃዎችን ካቀረብን በኋላ ከሐዲስ ማሰረጃዎችደግሞ የሚከተለውን እናቅርብ፡-

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ኡሳማ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ አስተላልፏል፡- “የትንሳኤ ቀን አንድ ግለሰብ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል፡፡ አህያ እየዞረ ወፍጮውን እንደሚያንቀሳቅሰው ይህ ሰው በአንጀቱ እየተጎተተ በጀሀነም እሳት ይዞራል፡፡
የእሳት ሰዎች ይመጡና “እከሌ ሆይ! ምን ሆነህ ነው?! በመልካም ስታዘን ከመጥፎ ስትከለክለን አልነበርክም እንዴ?!” ይሉታል፡፡ ግለሰቡም “አዎ! በመልካም አዝዣችሁ እኔ አልፈጽመውም ነበር፡፡ ከመጥፎ ከልክያችሁ ደግሞ እፈጽመው ነበር” በማለት ይመልስላቸዋል
፡፡ ቡኻሪ፡3267 ሙስሊም፡ 2989

▪️በኢማም አህመድ “ሙስነድ” ኪታብ አነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

➲“ነብዩ صلى الله عليه وسلم ኢስራእ በተጓዙበት ሌሊት ሰዎች ከእሳት በሆነ መጋዝ አፋቸውና ከንፈራቸው ሲተለተል ተመለከቱ፡፡ “እነዚህ እነማን ናቸው?” በማለት ረሡል ጠየቁ፡፡(ሁለቱ መላኢካዎች) “እነዚህ ከኡመትህ (ከተከታዮችህ) ኸጢቦች (ምክር
ሲመክሩ የነበሩ) ናቸው፡፡ የአላህን ኪታብ ያነባሉ ሰዎችን በበጎ ነገር ያዛሉ ነፍሳቸውን ግን ይረሳሉ፡፡
…” አህመድ፡13515 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡291

➧በእውቀታቸው ስለማይሰሩ ፤ ሰዎችን ጥሪ እያደረጉ ስለማይተገብሩ ሰዎች በቁርኣን እና በሐዲስ በርካታ ዛቻዎች መጠዋል፡፡ በእውቀታቸው ሰውን የሚጠቅሙ ነገር ግን እነርሱ ምንም የማይጠቀሙ በርካታ ሰዎችም አሉ። የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ ልክ እንደሻማ ነው ፤ ሻማ ለሌላው እያበራ እራሱን ያቀልጣል፡፡

➛ይህን አስመልክቶ አላህን ተገዥና ታማኝ የሆነው ታላቁ ታብዒይ ሙጦሪፍ ብን ዓብዲላህ ብን አሽኺር -ረሂመሁሏህ- ከዚህ ነገር በአላህ ይጠበቅ ነበር፡፡

▪️በዱዓው ውስጥ የሚከተለውን ይናገር ነበር፡-
"اللهم إني أعوذ بك أن يكون أحد أسعد بما علمتني مني، وأعوذ بك أن أكون عبرة لغيري"

“አላህ ሆይ! አንድ ሰው ለእኔ ባሳወከኝ እውቀት ከእኔ የበለጠ እድለኛ ሆኖ ለሌሎች መመከሪያ ከመሆን በአንተ እጠበቃለሁ” ኢማሙ አህመድ ፊዙህድ፡1358

➠ይህ ታላቅ ዱዓ ነው፡፡ ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - ይህን ዱዓ “ከዱዓዎች ሁሉ ምርጥ ዱዓ” በማለት ያወድሱት ነበር፡፡ መጅሙዕ አል ፈታዋ፡14/307
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📍 قال الشيخ/ سليمان الرحيلي وفقه الله:

فمن تمسك بالحق، فوجدت الذي عنده: قال الله، قال رسوله ﷺ، قال الصحابة، يقرر ما قرره الأئمة، فهؤلاء أهل الحق، ولو كانوا قلة.

📌قناة فوائد الشيخ أ.د. سليمان الرحيلي
Audio
🔹 تلاوة من سورة الزخرف
🔹 القارئ: #سيد_كمال
•••━══❁✿❁══━•••

🔹«وَإِذَا قُرِئَ ٱلْقُرْءَانُ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُون»
«ቁርኣንን በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡»
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ④∅➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ኢማም አልአውዛእይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ ሙስሊሞች ሆይ አላህ ፍሩ። የመካሪዎችን ምክር ስሙ። የገሳጮች ተግሳፅ አዳምጡ። ይህ እውቀት ዲን እንደሆነ እወቁ። በዚህ እውቀት ምን እንደምትሰሩ፣ ከማን እንደምትወስዱት፣ ማንን እንደምትከተሉና በዲናችሁ ጉዳይ ላይ የምታምኑት ማን እንደሆነ ተመልከቱ (አጢኑ)። ምክንያቱም የቢድአ ባለቤቶች ሁላቸውም አበላሾች፣ ቀጣፊዎችና አመፀኞች ናቸውና።

📚تاريخ دمشق [6/362]
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አምስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ➠ይህ አትራፊ የሆነው ንግድ እንጅ ተወጋጅ ፣ ከሳሪ ፣ ጸጋዋና መልካሟ የሚቋረጥ ፣ባለቤቷ በቅርብ እርሷን ትቷት የሚጓዝ የሆነችው ዱንያ ንግድ አይደለም፡፡ባሪያው ከዚህ ከሳሪ የንግድ ውልና ቃልኪዳን ባለቤቶች ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡ ▪️ኢማም አሽ'ሻጢቢይ ረሂመሁላህ ዑለሞች ለዚህ ጉዳይ ምሳሌ እንዳደረጉ ገልጸዋል፡…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ስድስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የዚህ አንጡራ ሐብት ባለቤት ከአላህ የተሰጠውን ይህን ውድ ጸጋና እውነታ
የማያውቅ
፣ ውስጡ በወህይ ኑር ያላበራ ፣ ምስኪንና ቂል ሆኖ እድሜውን በእንቶ
ፈንቶ የሚያሳልፍ ከሆነ ወደቀብር ዜሮ ሆኖ ተጎትቶ ይገባል፡፡
ወንድሞቸ ሆይ! አኼራ መልካም ስራ ለመስራት ፉክክር የሌለባት ፣በመልካም ስራ ድሓ ለሆኑ ሰዎች የማትመች አገር ነች፡፡

በውስጧ ያስቀደመው መልካም ስራ እንጅ ሊያግዝ የሚችል ውድ የሆነ
ጓደኛ የለም ፣ መዋዋስ የለም ፣ ሶደቃ የለም፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ የመልካም ስራ ድሃ ሆኖ ከጌታው ጋር መገናኘት የለበትም፡፡
ውድ የሆነውንና አላህ የሰጣቸውን የጊዜ አንጡራ ሐብት መልካም ስራ በመስራት ይጠቀሙበት፡፡

▪️ለእርሱም ክብር ይስጡ፡፡

إذا كان رأس المال عمرك فاحترز
عليه من الإنفاق في غير واجب


➧“ተጠንቀቅ! እድሜህ ከሆነ አንጡራ ሀብትህ ፤ ዋጅብ ከሆነው ውጭ አታባክን እባክህ)) ነፍሱን መካሪ የሆነ ሙስሊም አላህ የሰጠውን እድሜ ነገ አላህን ሊያስደስት በሚችል መልካም ስራ ብቻ ያሳልፍ፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን
ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡” አል ሐሽር 18

➧የመልካም ስራ ምንነትና ማረጋገጫ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲በዚህ ክፍል መልካም ስራ ምንድን ነው? አንድ ስራ እንዴት ነው መልካም ሊሆን የሚችለው? ለሚሉ ተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና ማብራራቱ የግድ ይሆናል፡፡

➛መልካም ስራ ፡ ማለት ግዴታም ይሁን ግዴታ ያልሆነ አላህና ረሡል صلى الله عليه وسلم ያዘዙትና የሚወዱት ተግባር ነው፡፡ ይህ ሰፊ ሜዳና ሁሉን የሚያስተናግድ በር ነው፡፡ የንግግር እና የተግባር ፤ የውጭና የውስጥ መልካም ስራዎች ሁሉ በዚህ ክፍል ይካተታሉ፡፡

➭ ይህ የንግድ ሜዳ የውድድር
ሜዳ ነው
፡፡ በዚህ ሜዳ ላይ የአላህን ረህመት የሚከጅሉ ፣ ታላቁን ምንዳ ፣ ተጸጽተው በመልካም መመለስን የሚፈልጉ ሁሉ ይሽቀዳደሙ ፣ይወዳደሩ!አንድ ስራ ፍጹም አምልኮ ለሚገባው አምላካችን አላህ እስካልሆነና አፈጻጸሙ
የረሡልን صلى الله عليه وسلم መንገድ እስካልተከተለ ድረስ መልካም ሊሆን አይችልም፡፡


➠ስራን ፍጹም ለአላህ ማድረግ የሁሉም መልካም ስራ መሰረት ነው፡፡ ሁሉም በእርሱ ላይ ነው የሚገነቡት፡፡ መልካም ስራዎች አይነታቸው ቢለያይም ቁጥራቸው ቢበዛም በኢኽላስ
ላይ (ፍጹም ለአላህ በሆነ መልኩ) ካልቆሙ ሰሪው ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡


➻በተመሳሳይ ኢኽላስ ኖሮት ነገር ግን በረሡል صلى الله عليه وسلم መመሪያ መሰረት ካልተፈጸመ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚ የሚሆነው ሁለቱንም - ኢኽላስና ሙታበዓን - አጣምሮ ሲጓዝ ነው፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ

“ስራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ..” አል ሙልክ፡2
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➛ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➧ፅሁፉን በተከታታይ ለማገኘት #Join
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w