💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ነገሮች ከአቅማችን በላይ ሲሆኑ ምንም ማድረግ ሳንችል ሲቀር እንባ ብቻ ማፍሰስ ነዉ። ኢላሂ የመቻል አቅሙ ስጠን ።

=
«ለሱና ነው ክብሬ!»
〰➖〰➖〰➖

ያሉትንም ቢሉ እኔስ አይደንቀኝም
ለሱና አደረጉድጂ ቢዲአ አልጨመርኩም

ጥንካሬንጂ ሙገሳ አልፈልግም
የጀሊሉን ትእዛዝ መጣስ አለፈልግም

ያወሩትን ያዉሩ እኔን አይደንቀኝም
ለነብዩ መንገድ ለቀናው ጎዳና

ምንስ ብከፍል ለሰለፎች ፋና
ጉዞዬ ቀጠልኩኝ ልቤ ወደደና

በክብር ለመኖር በዱኒያ በአኼራ
የሰዎች ወቀሳ መቼዉም   አልፈራ
ክጃሎቴ ሁሉ ነፍሴ እንድትጠራ
ሽርክና ቢዲአን ከልቧ መንጥራ
አላህ እንዲወዳት ነዉ የኔ ፈጠራ!!


🖋𝐇𝐚𝐲𝐚𝐭 𝐔𝐦𝐮 𝐀𝐛𝐝𝐮𝐫𝐞𝐡𝐦𝐚𝐧

𝐓𝐞« http://t.me/HayatbintSeid
የጁሙዓኹጥባ/እሪዝቃችሁን ከአላህ ዘንድ ፈልጉ!!
አቡ ረይስ ሙሐመድ ኢብኑ ኢማም
⊱የጁሙዓ ኹጥባ ⊰
⏝⏝⏝⏝

۞ ርእስ፦ እሪዝቃችሁን ከአላህ ዘንድ ፈልጉ..!!


🎙በአቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም

t.me/abu_reyyis_arreyyis/8704
«አቡ ዱጃናህ Online ቂርአት መድረሳ»

አስተማሪያቸዉ ጎበዝ ተማሪዎቹ እንቁ፣
የጌታቸዉን ቃል ጠንቀቀዉ ያወቁ፣
በዛዛታ á‹‰áˆŹ áŒŠá‹œáŠ• ያልሰነቁ፣
በዉድ አስተማሪያቸዉ áˆáŠá‹‰áŠ˘áˆáˆ á‹Ťá‹ˆá‰áŁ

የአቡ ዱጃናህ ተማሪዎች እንቁ፣
ቁርአን በተጂዊድ አድቅቀዉ ያወቁ፣
ደግሞም  ሞደል ናቼዉ ለነዚያ ላልነቁ
፣
በርቱልን ጠንክሩ የኛ ዉድ ጀግኖች፣
የአላህን ከላም  ሁልጊዜም ቀሪዎች
፣
ነገም በአኼራ ናችሁ ተደሳቾች፣
በአላህ በእዝነቱ የጀነት ወራሾች
፣
ነዉም አስተማሪያቸዉ ብርቱና ጠንካራ፣
ጠንቃቃ ነዉ  ጎበዝ በተጂዊድ ሲያቀራ፣
ተዉሂድን ሲያስተምር  ምንም ሳያጋራ፣
አምልኮን ለጌታዉ ብቻ ሲያጥራራ
፣
እንድህም ነዉ ጎበዝ ብርቱና ጠንካራ፣
ኢስቲቃማ ይስጥህ በዱኒያ በአኼራ።

=

𝐓𝐞« t.me/Abu_Dujanah_Online_Medresa
ገጠር እያለን ነጠላ ጫማ ብርቃችን ነበር
አሁን እንድህ ሊያልፍልን ህእ¡

=
ከትዝታ ሰፈር ማነዉ ዉሀ የቀዳ በዚች ህእ...!!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት ልብ አንጠልጣይ ታሪክ...!! ⏠⏠ ክፍል  ⓸ ⏡⏡ ↱ወጣቷም ይሄን ያልታሰበ ከባድ ቁም ነገር አዘል ደብዳቤ አነበበች፡፡ ራሷን ታዘበችን ወደ ቤቷ አመራች፡፡ ግድፍቶቿን አረመች፡፡ ባህሪዋን አስተካከለች፡፡ ከተወሰነ የጊዜ ቆይታ በኋላአላህን ፈሪውን ወጣት ዳግም ማግኘት እንዳለባት ወሰንች፡፡ ↱ የአሁኑ አላማዋ ግን የመጀመሪያው አይነት ዝሙት የመፈጸም ፍላጎት አልነበረም፡፡…
አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት
ልብ አንጠልጣይ
ታሪክ.....!!

⏠⏠
ክፍል ⓹
⏡⏡
☞ይሄን ተከትሎ ከመጀመሪያዋ ለቅሶ በበለጠ መልኩ አለቀሰኝ፡፡ ለቅሶዋ ግን ዱንያዊ ጥቅምን በማጣቷ ወይም ያንን የጓጓችለትን ወጣት ባለማግኘቷ አይደለም፡፡ ይሄ እንባ የሚፈሰው አላህን በመፍራት ከሞላ ቀልብ ነው፡፡


☞ከዚች እለት ጀምሮ ያቺ መልከ መልካም፣ ቆንጆ ልጃገረድ ቤቷ ዉስጥ ዘወተረች፡፡ ጌታዋን እስከተገናኘችበት ቀን ድረስ ከወጣቱ የተሰጣትን ምክር እየተገበረች በቤቷ በመጽናት ጌታዋን አመለከች፡፡ 

☞ከሆነ ጊዜ በኋላ ይች ምክር ሰሚ እንድሁም ኋላ ላይ አላህን ፈሪ ለመሆን የበቃችው ወጣት ወደ አኺራ መሸጋገሯን ለወጣቱ ተነገረው፡፡ በሞቷ በጣም አዘነ፤ አለቀሰም፡፡

☞የወጣቱን ሁኔታ የታዘቡ ከፊል የአካባቢው ሰዎችም “በአንተ ፍቅር ምክንያት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ምንም እንዳላየሆነህ አልፈህ አሁን ለእሷ ማልቀስህ ምን ይባላል!! የምታዝንላት ቢሆንማ ኖሮ ያኔ ፍላጎቷን ታሟላላት ነበር ብለው ሊወቅሱት ሞከሩ፡፡


☞እሱም አዎ በርግጥ መጀመሪያ ላይ ልጅቷ ተጽእኖ አሳድራብኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ከጊዜያዊ አካላዊ ፍላጎቴ ይልቅ ዘላለማዊ የሆነውን የአላህን ዉዴታ መጎናጸፉ እንደሚበልጥብኝ በመገንዘብ ጌታዬን ከማስቀይም ይልቅ እሷ ብትቀየም ይሻላል የሚለውን መረጥኩኝ፡፡

☞በርግጥ በዚህም ዉሳኔዬ ከጌታዬም ይሁን ከልጅቷ ጋር ሳልቀያየም ቀረሁ፡፡ ይሄን ተግባሬንም (ወንጀል የመፈጸም እድሉ ተመቻችቶልኝ ለአላህ ስል እርግፍ አድርጌ መተዌን) ጌታዬ ዘንድ ተከማችቶ የሚገኝ መልካም ስራ ይሆን ዘንድ በማሰብ አስቀመጥኩት፡፡

☞ከዚያ በኋላ ልጅቷ ስትስተካከል ከእሷ ጋር በትዳር መተሳሰርን ያልመረጥኩበት ምክንያት ደግሞ በልጅቷ ፈተና ምክንያት ለአኺራዬ መማለጃ ይሆነኝ ዘንድ ያሰብኩት ስራ ልጅቷን ቀድሜ በዱንያ ላይ ማግኘቴ በቀጣዩ ዐለም ላይ የምጠብቀውን ምንዳ ሊያጠፋብኝ ይችላል የሚል ስጋት አድሮብኝ ነው ብሎ መለሰላቸው፡፡

«የልጁ ታሪክ እዚህ ይጠናቀቃል ተጨማሪ ለወንድሞች  ምክር  በቀጣዬ ክፍል የሚለጠፍ ይሆናል.....!!Âť

✍️ይቀጥላል.......

         ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/https_Asselefya1
ወንድሜ

يا أخي إذا عملت عملا فلا تنتظر من الناس #ثناء أو مدحا؛ لأن ذلك علامة #الرياء.

አንድን ስራ ስትሰራ ከሰወች ምስጋናም ሆነ ልቅና አትፈልግ ይህ #የሪያዕ ምልክት ነው።

https://t.me/nuredinal_arebi
📍قـال العلاّمة #صالح_الفوزان حفظه الله تعالىٰ :

قد يُكثِر الإنسان من الأعمال الصّالحة لكنه قد يهمل لسانه ويتركه يحصد فيها

مثل الذي يزرع ويترك الحصّاد يحصد في زرعه فلا يُبقي له شيئاً

شرح كتاب الكبائر (صـ ٩١ )

=
በህይወታችን የሚገጥሙን ገጠመኞች ሁሉ ጠላታችንና ወዳጆቻችንን ያሳዩናል ማን ማንን መቅረብ እና ከማን መራቅ እንዳለብን ያስተምሩናል !!

t.me/Darutewhide
ትምህርት ባትማር
ቁርአን ባትቀራ
ኪታብ ባታነብ
ደርሶችን ባትከታተል
ደዕዋዎችን ባታዳምጥ ኖሮ
ምን አይነት ሰው እንደምትሆን፣ ምን አይነት ኑሮን እንደምትኖር እና እነማንን እንደምትመስል አስበኸው ታውቃለህ?
አልሀምዱሊላህ!!


t.me/https_Asselefya1
ምንም ያክል ተደራራቢ መከራ ዉስጥ ብንሆንም በአላህ ላይ የሚኖረን ተስፋና መልካም ምኞት ግን ፍጹም ሊሸረሸር አይገባም።
ነብዩላሁ የዕቁብ عليه الصلاة والسلام  በጣም የሚወደውን ልጁን ዩሱፍን አጣ። ቀጥሎም የዩሱፍ ወንድም ጠፋበት። በሶስተኛ ደረጃ በብርቱ ሀዘን ምክንያት ዐይኖቹን አጣ።እንደዚህ አይነት ተደራራቢ ተስፋ አስቆራጭ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የዕቁብ عليه الصلاة والسلام ግን ሁሉም ወደቦታቸው ይመለሳሉ የሚል ጽኑ ተስፋ ነበረው።
"ከአላህ እዝነትማ ፍጹም ተስፋ አትቁረጡ" እያለ ያስተምር ነበር። ተስፋውም ከንቱ አልሆነበትም። ልጆቹም ተገኙ። የዐይኖቹ ብርሃንም ተመለሰ።

  وَلَا تَيْئَسُوا مِنْ رَوْحِ اللَّهِ
سورة يوسف [87]


https://t.me/https_Asselefya1
ባለህ ነገር ላይ መብቃቃት
Daru tewhid
የልብ ሀብት በእጅ ካለ ንብረት የበለጠ ነው !!

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት ልብ አንጠልጣይ ታሪክ.....!! ⏠⏠ ክፍል ⓹ ⏡⏡ ☞ይሄን ተከትሎ ከመጀመሪያዋ ለቅሶ በበለጠ መልኩ አለቀሰኝ፡፡ ለቅሶዋ ግን ዱንያዊ ጥቅምን በማጣቷ ወይም ያንን የጓጓችለትን ወጣት ባለማግኘቷ አይደለም፡፡ ይሄ እንባ የሚፈሰው አላህን በመፍራት ከሞላ ቀልብ ነው፡፡ ☞ከዚች እለት ጀምሮ ያቺ መልከ መልካም፣ ቆንጆ ልጃገረድ ቤቷ ዉስጥ ዘወተረች፡፡ ጌታዋን እስከተገናኘችበት…
አላህን የመፍራት ተምሳሌቱ ወጣት
ልብ አንጠልጣይ ታሪክ
.......!!

⏠⏠⏠⏠⏠
♨️ክፍል ⓺ የመጨረሻ!
⏡⏡⏡⏡⏡

⏣ አንተ የረጅሙ ጉዞ ጓዴ፦ይሄን አስደማሚ ታሪክ ሰማህ አይደል? አየህ!!! ይሄን ወጣት ዱንያ አላታለለችውም፡፡ ሴቷ ልጅም በዉበቷ አልፈተነችውም፡፡ ልጃገረዷም የጌታዋን ቃል አልተላለፈችም፡፡ የተሰጣትን ምክርና የተነበበላትን የቁርአን አንቀጽ በንቄት አልተመለክተችም፡፡ ይልቁንም በቀጥታ ተግባር ላይ ነበር ያዋለችው፡፡  ወንድሜ!!  የወንጀል ጣዕም ሾር የለውም፡፡ ሃጢያቱ ከተፈጸመበት ቅጽበት በኋላ የወንጀል ትርፉ ጸጸት ብቻ ነው፡፡

⏣ መልካም ተግባር ደግሞ ድካሙ አይዘወትርም፡፡ ዒባዳ ስትፈጽመው በሰአቱ ሊከብድህ ይችላል፡፡ ሲያልፍ ግን የዒባዳ ጣዕሙ ዘላለማዊ ሆኖ ታገኘዋለህ፡፡ ይህ ጀግና ወጣት ያኔ ለስሜት ተንበርክኮ የጌታውን ድንበር ተላልፎ ቢሆን ኖሮ ይሄን የመሰለ ዝና እና ክብር በኪታቦች ዉስጥ አይጻፍለትም ነበር፡፡


⏣በተለያዩ አጋጣሚዎች የአላህን ፈሪዎች ምሳሌ ተደርጎ አይገለጽም ነበር፡፡ በአኺራም ሊያጋጥመው የሚችለው ቅጣት ከሚታሰብው በላይ ከባድ ሊሆንበት ይችል ነበር፡፡ ቆንጆዋም ከመልካሙ ወጣት የተለገሳትን ምክር በቀናነት ባትቀበል ኖሮ በብልግና እና በጸያፍ ተግባር ተዘፍቃ ያንን መሳይ የዒባዳ ሂወት ሳታጣጥም ወደ አኺራ ተሸጋግራ በዉርዴትና በጸጸት ትኖር ነበር፡፡


⏢ጌታችንም በኢማን የተሳሰሩን ተዋዳጆች በቀጣዩ ዐለም እንደማይለያይ ታውቃለህ አይደል? አዎ እነዚህ ወጣቶች ምንም እንኳ አፍላ የወጣትነት ጊዜ ላይ ቢሆኑም፤ ምንም እንኳ ሁለቱም ማራኪ ዉበት ቢኖራቸውም፣ ምንም እንኳ ባልተለመደ መልኩ ዝሙት እንፈጽም የሚለው ጥያቄ ከሴቷ ቢመነጭም በስሜት ተጽእኖ በመታወር የአላህን ክልከላ መተላለፍ የለብንም በሚል ጽኑ እምነት ሃራም ቦታ ላይ አልተገኙም፡፡


⏢ስለዚህ እነዚህ ተምሳሌት የሆኑ ወጣቶች በአኺራ አብረው የመኖር እድላቸው በጣም ሰፊ ነው፡፡ አላህም በተከበረው ቃሉ ጌታው ፊት መቆምንና መተሳሰብን ፈርቶ ነፍስያውን ከስሜቱና ከዝንባሌው የከለከለ ሰው በእርግጥም እሱ መኖሪያው ጀነት ነች ብሎ ቃል ገብቷል፡፡

{ وَأَمَّا مَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ وَنَهَى ٱلنَّفۡسَ عَنِ ٱلۡهَوَىٰ }{ فَإِنَّ ٱلۡجَنَّةَ هِیَ ٱلۡمَأۡوَىٰ }

«የዚህ አይነት አማኝ አንድትን ብቻ ሳይሆን ሁለትን ጀነቶች እንደሚሸለምም ነግሮናል፡፡»

{ وَلِمَنۡ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِۦ جَنَّتَانِ }

«ለጀነት የበቃ ሰው ደግሞ የሚፈልገው ሁሉ ይሟላለታል ብሎናል፡፡»

وَلَكُمۡ فِیهَا مَا تَشۡتَهِیۤ أَنفُسُكُمۡ وَلَكُمۡ فِیهَا مَا تَدَّعُونَ }

⏢ሸይኹል ኢስላም ቢን ተይሚያህ አላህ ይዘንላቸውና ፈታዋ አል ኩብራ 5/461 ላይ እንዳሰፈሩት አንድ ሰው የሆነችን ልጅ ቢወድና በዱንያ ላይ ማግባት ሳይችል እሷም ሌላን ሳታገባ ብትሞት፤ መህሯን ከፍሎ በዘላለማዊዉ ሀገር ከእሷ ጋር እንዲያኖረው አላህን ቢለመነው በጀነት ዉስጥ ይገናኛሉ የሚል ትልቅ ተስፋ አለ፡፡


⏢ታዲያ ነገሩ እንደዚህ ከሆነ አላህን በመፍራት ላይ ሲያበረታታ ከነበረ ወዳጅ ጋር እንደመገናኘትና አብሮ እንደመኖር ምን የሚናፈቅ ነገር አለ? በርግጥ ወንድሜ እንደዚህ አይነት ፈተናዎች ሲያጋጥሙ በፈተናው ሳይንበረከኩ የጌታን ትእዛዝ በአግባቡ መጠበቅ መቻል የሙሉእ ኢማን እንድሁም የእውነተኛ ታማኝነት (ኢኽላስ) መገለጫ ነው፡፡

⏢ በርግጥ መንፈስ (ሩህ) ከአላህ ጋር ያላት ቁርኝት በጸናና ከፍ ባለ ቁጥር እምነትን ለመጠበቅ ሲባል በአካል ላይ የሚያርፈውን የተለያየ ፈተና መቋቋም ምንም አይከብዳትም፡፡ ለዚህም ነው ሩህን ማነጽ አካልን ከማስተካከል በላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል የሚባለው፡፡

«አንተ አካልን ገንቢ ሩህን ዘንጊ ሆይ ለቀጣዩ ሂወት፣ ከአካል በላይ ሩህ  ወሳኝ አይደለም ወይ!!Âť


ከዚሁ ሚድያ ካነበብኩት ለእናንተም ይጠቅማል ብዬ  ያካፈልኳችሁ አላህ ሁላችንንም ተጠቃሚዎች ያድርገን....!!

✍️ أم عثيمين بنت أراغاو الجامية

ሌሎች ተጨማሪ ለመከታተል ይቀላቀሉ
↷↷↷↷↷↷↷↷↷↷↷↷↷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1