🧷ኢብኑ ዑሰይሚን አሏህ ይዘንለትና እንዲህ አሉ:-
➹" انظُر إِلَىٰ المَرأَة المُتخَمّرة المُغطِّية لِوجهِها، تَجِد أنَّها فِيٰ سَلامةٍ، وَفِيٰ أمَانٍ، وَفِيٰ حِشمَةٍ وَوَقَارٍ، لَا يَطمعُ فِيهَا الطَّامِعونَ"
➹ወደ ተሸፋፈነችዋ ፊቷን ወደ ሰተረችዋ ተመልከትማ እሷ ሰላም ውስጥ ሆና አማን ውስጥ ሀያዕ መረጋጋት ውስጥ ሆና ታገኛታለህ! በሷ ጎምዢ አይጎመዥም።
📚 سِلْسِلةُ فَتَاوَىٰ نُورٌ عَلَىٰ الدَّرْبِ (٢٦٨)
https://t.me/https_Aselefya

🍓1
የኔ ውድ እህት👒
አንዳንዴ......ልብሽን ረስተሽ የሚገባሽን
ነገር አስታውሽ" አንድን ሰው ስለወድሽው
ብቻ ደካማ እንዲያደርግሽ አትፍቀጂለት።
https://t.me/https_Aselefya
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
تعصي الإله وأنت تزعم حبه
هذا لعمري في القياس شنيعُ
لو كان حبك صادقاً لأطعته
إن المحب لمن أحب مطيعُ
هذا لعمري في القياس شنيعُ
لو كان حبك صادقاً لأطعته
إن المحب لمن أحب مطيعُ
"ከሴት ልጅ ተፈጥሮ አንዱ፤ ብታፈቅርም እንኳ (ፍቅሯን ለመግለጽ) ጀማሪ ከመሆን መቆጠቧ ነው።
በኢስላም ሴት ልጅ የምትፈለግ እንጂ ፈላጊ አይደለችም። ወደ እርሷ ይኬዳል (ይደከማል) እንጂ፤ እርሷ ወደ ማንንም አትሄድም። ለእርሷ ሲባል ሺህ ማይሎች ይጓዛሉ፤ እርሷ ግን ፈላጊ ሆነህ እስክትመጣት ድረስ (ካለችበት ክብር) ንቅንቅ አትልም።
(ስትመጣ ግን) እርምጃህን በመሰለ እርምጃ ትቀበልሃለች። እንዲያውም በበጎ ውሎ፣ በርህራሄና በእዝነት ከአንተ ልቃ ልትገኝ ትችላለች። በዚህም ረገድ ከወንዶች ይልቅ ልዩ ደረጃ (ብልጫ) አላቸው።"
ይህ ማለት ግን አንዲት ሴት ዲኑንና ስነ-ምግባሩን የወደደችውን ወንድ ለትዳር (ለሀላል) ብትጠይቅ ወይም ፍላጎቷን በጨዋ መንገድ ብትገልጽ ክብሯ ይቀንሳል ማለት አይደለም።
የምእመናን እናት የሆነችው ታላቋ ኸዲጃ (ረድየሏሁ ዐንሀ) ለረሱል (ሰለሏሁ.ዐለይሂ ወሰለም) የነበራትን ክብርና ፍላጎት ቅድሚያ በመግለጽ የትዳራቸው ሰበብ ሆናለች። ይህ ድርጊቷ የሴትነት ክብሯን አልቀነሰውም፤ እንዲያውም ለራሷና ለልጆቿ የምትመኘውን መልካም መሪ ለመምረጥ ያላትን 'አስተዋይነትና ብልህነት' ነው ያሳየው።
ክብር የሚለካው በመንገዱ ንፅህና ነው። ሴት ልጅ ፈላጊ መሆኗ ነውር አይደለም፤ ፈላጊነቷ ለአላማ (ለትዳር) እና በጨዋነት እስካለ ድረስ፥ መልካምን ባል መፈለግ የብልህ ሴቶች መገለጫ ነው።"
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

Forwarded from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ ተክፊሪይ & ለተሚይ
ዛሬ ለተሚዮች ያመጡት የ(ኢልዛም) ቢድዓ ትላንት ሐጁሪዮች ያመጡትን ራሱኑ ነው። የዛሬ ተክፊዮች የትላንት ሓጁሪዮች አባታችን የሕያ አልሓጁሪይ ሙብተዲዕ ያለውን ካላልክ ብለው ሀገር ሲበጥብጡ ነበር።
የለተሞው መንጋ ደግሞ አባታችን ዓብዱልሐሚድ የለከፈውን ካለከፍክ ሱኒይ አይደለህም ይልሃል። ወደድክም ጠላህም የሕያ እና ዓብዱ በስም እንጅ በጥፋት አይራራቁም። ተከታዮችም ስማቸው እንጅ የተለያየው ተግባራቸው ኮፒ ነው።
ለማንኛውም የመንሃጅ ቂብላ የጠፋበት የተክፊሩ ጎርፍ እና የለተሞው መንጋ ሁኔታ ባጭሩ ሲገለፅ እንዲህ ነው። ከሱፊያ ወይም ከኢኽዋን ወጣሁ ይልና አንድ ሁለት ወር ይቀራል። ከዚያ "አሊፍ" እና "ባ"ን የለየ ሲመስለው ተክፊሪዩ "ጀምዒዮዮዮች፣ ሙርጅኣዎች..." እያለ መጮህ ይጀምራል።
ለተሚዩ ደግሞ "እነፉላን አዲሶቹ ሙመይዖች፣ ኢኽዋን ሁነዋል...ያዙን ልቀቁኝ" እያለ ይቀደዳል። ኢኽዋን ዳቦ ይሁን ቂጣኮ አያቀውም። እስኪ መጀመሪያ ቁርአን በትክክል ቅራ። ከዚያም አደብ ይዘህ ኪታብ ተማር አንብብ አጥና።
ዝም ብለህ "ሲሉ ሰማሁ ብየ እላለሁ ነቢየ" ነገር አትሁን። በጎተቱህ አትጎተት ሰው ነህ በግ አይደለህም። ያለ ዕውቀት አስሩን እየጨረገድክ ነገ አላህ ፊት ማንም አብሮህ አይቆምም ለነፍስህ ስትል አላህን ፍራ።
▫️ ታላቁ ዓሊም ሙሐመድ አማን አልጃሚይ
ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ኡሱሉ ሰላሳን ብቻ ትማርና ክፍልህን ዘግተህ በሰዎች ላይ ብይን ትሰጣለህ። እገሌ ጣኦት፤ እገሌ ጃሂል፤ እገሌ ሙብተዲዕ፣ ሙብተዲዕን ሙብተዲዕ ያላለ እራሱ ሙብተዲዕ ነው። ከነዚህ ምንም ካልተማሩ መሃይሞች በየመስጂዶችና ቤቶች በየአቅጣጫው ፈትዋዎች ይፈበረካሉ። እባካቹህ ለሰዎች እዘኑ። አረ ለነፍሳቹህ እዘኑ።"
t.me/Abu_lmran_Alaseriy

ውድ እህቴ ሆይ!
በመጀመሪያ፣ ይህንን ነገር በግልፅ ስትናገሪ "አደብ ማጣት" ሳይሆን፣ ነፍስሽን ለማዳንና ወደ አላህ ለመመለስ የምታደርጊው ሙጃሀዳ መሆኑን እወቂ። በልብሽ ውስጥ ያለው ፀፀት አላህ እንደወደደሽና እንደመረጠሽ ምልክት ነው። ልብሽ ቢሞት ኖሮ፣ ወንጀሉን እየሰራሽ ሰላም ይሰማሽ ነበር። ነገር ግን አላህ ከዚህ አዘቅት እንድትወጪ ፈልጎ ነው ይህንን የጸጸት እሳት በውስጥሽ የለኮሰው። የኔ ምክሬ፦
1ኛ―"ላለመገናኘት መወሰን" ብቻ በቂ አይደለም፤ መንገዱን መዝጋት እንጂ!
"እንፀፀታለን፣ ላለመገናኘት እንወስናለን፣ ግን ተመልሰን እንገናኛለን" ያልሽው ነገር በጣም የተለመደ የሸይጣን ወጥመድ ነው። ችግሩ ያለው ውሳኔው ላይ ሳይሆን አፈፃፀሙ ላይ ነው።አንቺና እሱ ብቻችሁን በሆናችሁ ቁጥር እናንተ እሳትና ቤንዚን ናችሁ። "አንነካካም" ብሎ መገናኘት፣ እሳት እያቀጣጠሉ "አትቃጠል" እንደማለት ነው።
ስለዚህ የመጀመሪያው መፍትሄ፤ ግንኙነቱን ሙሉ ለሙሉ ማቋረጥ ነው። ሃላል እስክትሆኑ ድረስ ስልክ መደዋወል፣ ቻት ማድረግ፣ እና በአካል መገናኘት መቆም አለበት። "በቀስ በቀስ እተዋለሁ" የሚባል ነገር በዝሙት መንገድ ላይ አይሰራም። ቆራጥ ሁኚ! ቁጥሩን ብሎክ አድርጊ፣ ይህ የሚከብድሽ አሁን ብቻ ነው፤ በኋላ ግን ነፃነት ይሰማሻል።
2ኛ― "ተማሪዎች ስለሆንን አንጋባም" የሚለው አስተሳሰብ በብዙ ወጣቶች ላይ ያለ የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።ቤተሰብን በማማከር፣ ወጪን ሳታበዙ፣ ተማሪዎችም ሆናችሁ ኒካህ ማሰር ትችላላችሁ። የግድ አብሮ መኖር፣ ትልቅ ቤትና ሰርግ አያስፈልግም። ኒካህ ካሰራችሁ በኋላ እራሳችሁን ችላችሁ እስክትኖሩ ድረስ በቤተሰብ ቤት እየኖራችሁ እንደ ባልና ሚስት መገናኘት ትችላላችሁ። ይህም ግንኙነታችሁን "ሃላል" ያደርገዋል፤ ከአላህም ቁጣ ያድናችኋል።ነገር ግን ይህንን አማራጭ አቅርበሽለት "አይ አሁን ላይ ለ ትዳር ዝግጁ አይደለሁም" ካለ፣ እመኚኝ ይህ ወንድ ለጊዜያዊ ስሜቱ እንጂ ለአንቺ ክብርና ለዲንሽ አይጨነቅም። በዚህ ጊዜ እሱን ማጣት ለህይወትሽ ትርፍ ነው።
ቁርኣን ላይ አላህ "ዝሙትን አትስሩ" ሳይሆን ያለው "ወደ ዝሙት አትቅረቡ" ነው። ምክኒያቱም አንዴ ከተጠጋሽ በኋላ መመለሱ እጅግ ከባድ ስለሆነ ነው።
አሁን የምትሰሩት ነገር "ለዝሙት የቀረበ" እንጂ ዋናው አይደለም ብለሽ እንዳትጽናኚ። ነገሩ እንደ ቁልቁለቱ መንገድ ነው፤ ፍሬን የለውም። ዛሬ የጀመራችሁት ንክኪ፣ ነገ ወደማይመለስ የከፋ ወንጀል እና እርግዝና ወይም በሽታ ሊመራ ይችላል። ያኔ ፀፀቱ የከፋ ይሆናል።
ውድ እህቴ፣ አንቺ የአላህ ውድ ባሪያ ነሽ። አካልሽ የተከበረ ነው። ለጊዜያዊ ስሜት ተብሎ በየሳምንቱ የሚደረግ ንክኪ ክብርሽን ይነካል። "በሃላል እስክንገናኝ ድረስ እኔን ማግኘት አትችልም" በይው። ይሄ ወንድ እውነት የሚያከብርሽ ከሆነ ውሳኔሽን ያከብራል፤ ካልሆነ ግን መንገዱን ጨርቅ ያድርግለት።
ስለዚህ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ «አላህ ሆይ! ለአንተ ብዬ ይህንን ነገር ተውኩት፣ አንተ የተሻለውን ስጠኝ!» ብለሽ ቃል ግቢ። አሁንኑ ተውበት አድርገሽ በኢስቲግፋር እና በዱዓ ተመለሺ። ለአላህ ስትይ ስሜትሽን መተውሽ በራሱ ትልቅ ኢባዳ ነው።
የመጨረሻ መልዕክቴ!
ይህ ግንኙነት ወይ ወደ "ሃላል ጋብቻ" መቀየር አለበት፣ ወይም ሙሉ ለሙሉ መቆም አለበት። መሃል ላይ የሚባል ነገር የለም። መሃል ላይ መሆን ነፍስያሽን እያደማሽ እንድትኖሪ ያደርግሻል። ለአላህ ብለሽ የምትተይው ነገር ሁሉ፣ አላህ በሌላ በተሻለ ነገር እንደሚተካልሽ አስቢ።
አላህ ልብሽን ያጽናልሽ፣ ከዚህ ፈተና በሰላም ያውጣሽ! ጠንካራ ሁኚ!
✍ደካማው ወንድምሽ አቡ ሱፍያን―
t.me/Sle_qelbachn1

🧷كان مالك بن دينار رحمه الله يقول
ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር
« إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ »
ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው"
ወንድም እህቶቸ,,ኸይር ለመሥራት በላጩና የሚያምረው በወጣትነታችን ነውና"
በወጣትነታችን መልካም ስራወችን አብዝተን እንስራ።
https://t.me/https_Aselefya
ኢማም ማሊክ ቢን ዲናር እንድህ የል,ነበር
« إِنَّمَا الْخَيْرُ فِي الشَّبَابِ »
ጡሩ ነገር ያለው በወጣትነት ውስጥ ነው"
ወንድም እህቶቸ,,ኸይር ለመሥራት በላጩና የሚያምረው በወጣትነታችን ነውና"
በወጣትነታችን መልካም ስራወችን አብዝተን እንስራ።
https://t.me/https_Aselefya
🍓2
መልካምነት!
መልካምነት ሰው ለራሱ የሚያስፈልገውን መልካም ነገር ለሌላው እንድሆንለት መፈለግ ለእርሱ ያለውን ማካፈል:-
ኢስላም ባዘዘው መሠረት ለማንኛውም አካል ዘር :ቀለም:ፆታ:ማንነት........ሳይለይ በጎ መዋልን ይጠቀልላል"
መልካምነት ከሰው ልጆች አልፎ ለእርድ በቀረበች እንስሳ ላይ መልካም መፈፀም እንዳለብን ኢስላም ይጠቁማል:
መልካምነት የውለታ መመለስን ቀመር አይተካም:
መልካም ስትሆን ፊትህ በፈገግታ ይሞላል:
መልካም ስትሆን ልቦነህ በደስታ ይሞላል:
መልካም ስትሆን በተግባርህ ላይ ነሻጧ ይኖርሀል።
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/UstazKedirAhmed
أشغلي نفسكِ بما ينفعكِ في الدارين، تزودي بالعلم النافع والعمل الصالح ولا تكوني من الغافلين في ثوب العابدين.
https://t.me/https_Aselefya
https://t.me/https_Aselefya