Forwarded from ስለ ቀልባችን
ራስን በራስ ማርካት!–ክፍል 1―
~
በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ለክፉ ተጠቅሞበት በጣትህ ጫፍ በሚነካ ስክሪን አማካኝነት ወደ መኝታህ ገብቷል። ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች በድብቅ የሚያለቅሱበት፣ ከሰው ተደብቀው አንገት የሚደፉበት፣ የህሊና እረፍት ያጡበት ትልቁ በሽታ «ኢስቲምናእ» (ራስን በራስ ማርካት) አንዱና ትልቁ የወጣቱ ችግር ነው።
ይህ ተግባር ዝም ብሎ መጥፎ ልማድ ብቻ አይደለም፤ የወጣትነትን ወዝ የሚጠጣ፣ ከአላህ የሚያጣላ፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልም «የድብቅ ካንሰር» ነው። እስቲ ቆም ብለህ ተመልከት! ጌታችን አላህ የሰው ልጅን ሲፈጥር ክብር ሰጥቶታል። ስሜትንም የሰጠህ ለተፈቀደ ትዳርና ለዘር መተካት እንጂ በእጅህ ልትጫወትበት አይደለም። በቁርኣን ውስጥ አማኞችን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
«እነዚያም እነሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙት (ባሮች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚያም ወዲያ (ሌላን) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነሱ ወሰን አላፊዎቹ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 5-7)
ከዚህ አያ መረዳት እንደምንችለው ከትዳር ውጪ ስሜትን ማውጣት «ወሰን አላፊነት» ነው። ነብያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወጣቶችን አግብተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ካልቻሉ ደግሞ እንዲጾሙ አዘዋል እንጂ ራስን በራስ ማርካትን አልፈቀዱም።
ውድ ወንድሜ! ስሜትህን በተከለከለ መንገድ ባወጣህ ቁጥር፣ ከአላህ እዝነት ትርቃለህ። ዱዓህ እንዳይሰምር፣ ዒባዳህ እንዳይጣፍጥህ የሚያደርገው ይሄው የረከሰ ተግባር ነው።አላህ የሰጠህን የተከበረ አካል ማርከስ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው።
ከ አላህ ጋር ከማጣላቱ ባሻገር ይህ ሱስ ከአደንዛዥ ዕፅ ባልተናነሰ በአእምሮ ላይ ከባድ ተጽእኖ አለው። ዶክተሮች ይህን ተግባር በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚከተሉትን አደጋዎች ያስቀምጣሉ፡-
📎 1ኛ―የአእምሮ ባርነት (Addiction): ልክ እንደ ኮኬይን አእምሮህ ላይ የደስታ ሆርሞን (Dopamine) በውሸት እንዲረጭ ስለሚያደርግ፣ አእምሮህ ይደነዝዛል። ነገ ከትዳር አጋርህ ጋር የምታገኘው ተፈጥሯዊ ደስታ አይጣፍጥህም።
🕹 2ኛ―የማስታወስ ችሎታ መቀነስ እና የመርሳት ችግር፡ አእምሮ ሁሌም በወሲባዊ ቅዠት ስለሚጠመድ፣ ለትምህርትና ለቂርኣት እንድሁም ለቁምነገር የሚሆን ቦታ ያጣል። ብዙ ተማሪዎችም ሆኑ ብዙ ዒልም ፈላጊዎች ትምህርታቸውን እና ዒልም መማራቸውን የጠሉት በዚህ ምክንያት ነው።
😞 3ኛ―የጭንቀት እና የደብርት በሽታ (Depression): ድርጊቱን ከፈጸምክ በኋላ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት ራስን መጥላትና ባዶነት ወደ ድብርት ይወስዳል። "እኔ ርካሽ ነኝ" ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል።
👨👦 4ኛ―የትዳር ህይወትን ማበላሸት፡ ራስን በራስ በማርካት የለመደ ሰው፣ በትዳር ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት መፈጸም ይከብደዋል (Sexual Dysfunction)። ለወንዶች የቶሎ መጨረስ ችግር (Premature Ejaculation) ዋነኛ መንስኤው ይህ መጥፎ ልማድ ነው።
🎯 5ኛ―የሰውነት መዛል እና የጀርባ ህመም፡ የወጣትነት ጉልበትህን በከንቱ እያፈሰስክ ስለሆነ፣ ለእድገት የሚሆን ጉልበት ታጣለህ። አይንህ ይቦዝዛል፣ ጉልበትህ ይንቀጠቀጣል፣ኑርህም ይጠፋል…ከሁሉም በላይ የሚያስፈራው ግን የአኼራ ጉዳይ ነው።
ውድ ወንድሜ! እስኪ ለአፍታ ቆም ብለህ አስብ!ያ በጨለማ የቆለፍከው በር ሰዎች እንዳያዩህ ነው አይደል? ግን የዓለማቱ ጌታ አላህ እየተመለከተህ እንደሆነስ ዘነጋህን? እጅህ፣ እግርህና ብልትህ ነገ በአላህ ፊት «እንዲህ አደረገብን»ብለው ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው? ያንተ እኩዮች ቁርኣን ሲያነቡ፣ ኢልም ሲቀስሙ፣ በትዳር ሲረጋጉ፤ አንተ ግን መጸዳጃ ቤት ውስጥ ወይም አልጋህ ላይ ከራስህ ጋር ትታገላለህ። ይህ ላንተ ክብር አይመጥንም!
የወደፊት ሚስትህ ንጹህ ሆና እየጠበቀችህ፣ አንተ ግን አላህ በሐላል ላይ እንድታውለው የሰጠህን ውድ ስጦታ በቆሻሻ ቦታ እያፈሰስከው ነው። ነገ ትዳር ስትይዝ የምትሰጠው ፍቅር፣ የምትሰጠው ጉልበት ከየት ይመጣል? ጨርሰህው እኮ ነው!
ሞት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ቢመጣስ?
አላህ ይጠብቀንና፣ ያንን ቆሻሻ ቪዲዮ እያየህ ወይም ያንን ሐራም እየፈጸምክ ነፍስህ ብትወጣ፣ ከአላህ ጋር እንዴት ትገናኛለህ? ወንድሜ... እህቴ... ይሄ ጉዳይ ቀልድ አይደለም። የእሳትና የጀነት ጉዳይ ነው።
🔍 መፍትሄው ምንድን ነው?
☑ ተስፋ አትቁረጥ! አላህ መሐሪ ነው። ዛሬውኑ ቆርጠህ ከተነሳህ መመለስ ትችላለህ።ወሏሂ ከዚህ ሱስ መውጣት ከባድ እንደሆኑ ብታስቡም በ አላህ ከታገዛችሁና ከወሰናችሁ እጁግ በጣም ቀላል ነው።
☑ በንፁህ ልብ አልቅሰህ አላህን ምህረት ጠይቅ። «ጌታዬ ሆይ! ተሸነፍኩ፣ አቅም አነሰኝና እርዳኝ» በለው።
☑ ብቸኝነትን አጥፋ። ይህ ሱስ የሚመጣው ለብቻ ስትሆን ነው። ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ስልክህን መኝታ ቤት አታስገባ።
☑ የአይን ዚናን ተጠንቀቅ።እይታህን ስበር። በቲክቶክና በፌስቡክ የሚመጡ ስሜት ቀስቃሽ ምስሎችን አግድ (Block)። አይን የልብ መስኮት ናት።
☑ ጾም እና ስፖርት ስራ። ነብያችን እንዳሉት ጾም ጋሻ ነው። ስፖርት ደግሞ ትርፍ ጉልበትህን በጥሩ ነገር እንድታወጣው ይረዳሃል።
☑ ትዳርን አስብ። አቅሙ ካለህ አግብ። ካልቻልክ እራስህን ለትዳር አዘጋጅ እንጂ በሐራም አትጨርስ።
🫀 ያ አላህ! በዚህ የሱስ ሰንሰለት ተጠፍረው የሚሰቃዩ ወንድም እህቶቼን አንተ ድረሰላቸው። በወንጀል የጠቆረውን ልባቸውን በምህረትህ ብርሃን አፅዳው። የዚህን ሱስ አስከፊነትና አስጠያፊነት አሳይተህ፤ ከልባቸው ጠልተው እንዲርቁትና በምትኩ የአንተን ፍቅርና የኢማንን ጣፋጭነት አላህ ይለግሳቸው። አላህ ሆይ! ወዳንተ መመለስን ለከበዳቸው ሁሉ እጃቸውን ይዘህ ወደ ብርሃን ማውጫው መንገድ ምራቸው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
~
በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ለክፉ ተጠቅሞበት በጣትህ ጫፍ በሚነካ ስክሪን አማካኝነት ወደ መኝታህ ገብቷል። ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች በድብቅ የሚያለቅሱበት፣ ከሰው ተደብቀው አንገት የሚደፉበት፣ የህሊና እረፍት ያጡበት ትልቁ በሽታ «ኢስቲምናእ» (ራስን በራስ ማርካት) አንዱና ትልቁ የወጣቱ ችግር ነው።
ይህ ተግባር ዝም ብሎ መጥፎ ልማድ ብቻ አይደለም፤ የወጣትነትን ወዝ የሚጠጣ፣ ከአላህ የሚያጣላ፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልም «የድብቅ ካንሰር» ነው። እስቲ ቆም ብለህ ተመልከት! ጌታችን አላህ የሰው ልጅን ሲፈጥር ክብር ሰጥቶታል። ስሜትንም የሰጠህ ለተፈቀደ ትዳርና ለዘር መተካት እንጂ በእጅህ ልትጫወትበት አይደለም። በቁርኣን ውስጥ አማኞችን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
«እነዚያም እነሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙት (ባሮች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚያም ወዲያ (ሌላን) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነሱ ወሰን አላፊዎቹ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 5-7)
ከዚህ አያ መረዳት እንደምንችለው ከትዳር ውጪ ስሜትን ማውጣት «ወሰን አላፊነት» ነው። ነብያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወጣቶችን አግብተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ካልቻሉ ደግሞ እንዲጾሙ አዘዋል እንጂ ራስን በራስ ማርካትን አልፈቀዱም።
ውድ ወንድሜ! ስሜትህን በተከለከለ መንገድ ባወጣህ ቁጥር፣ ከአላህ እዝነት ትርቃለህ። ዱዓህ እንዳይሰምር፣ ዒባዳህ እንዳይጣፍጥህ የሚያደርገው ይሄው የረከሰ ተግባር ነው።አላህ የሰጠህን የተከበረ አካል ማርከስ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው።
ከ አላህ ጋር ከማጣላቱ ባሻገር ይህ ሱስ ከአደንዛዥ ዕፅ ባልተናነሰ በአእምሮ ላይ ከባድ ተጽእኖ አለው። ዶክተሮች ይህን ተግባር በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚከተሉትን አደጋዎች ያስቀምጣሉ፡-
ውድ ወንድሜ! እስኪ ለአፍታ ቆም ብለህ አስብ!ያ በጨለማ የቆለፍከው በር ሰዎች እንዳያዩህ ነው አይደል? ግን የዓለማቱ ጌታ አላህ እየተመለከተህ እንደሆነስ ዘነጋህን? እጅህ፣ እግርህና ብልትህ ነገ በአላህ ፊት «እንዲህ አደረገብን»ብለው ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው? ያንተ እኩዮች ቁርኣን ሲያነቡ፣ ኢልም ሲቀስሙ፣ በትዳር ሲረጋጉ፤ አንተ ግን መጸዳጃ ቤት ውስጥ ወይም አልጋህ ላይ ከራስህ ጋር ትታገላለህ። ይህ ላንተ ክብር አይመጥንም!
የወደፊት ሚስትህ ንጹህ ሆና እየጠበቀችህ፣ አንተ ግን አላህ በሐላል ላይ እንድታውለው የሰጠህን ውድ ስጦታ በቆሻሻ ቦታ እያፈሰስከው ነው። ነገ ትዳር ስትይዝ የምትሰጠው ፍቅር፣ የምትሰጠው ጉልበት ከየት ይመጣል? ጨርሰህው እኮ ነው!
ሞት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ቢመጣስ?
አላህ ይጠብቀንና፣ ያንን ቆሻሻ ቪዲዮ እያየህ ወይም ያንን ሐራም እየፈጸምክ ነፍስህ ብትወጣ፣ ከአላህ ጋር እንዴት ትገናኛለህ? ወንድሜ... እህቴ... ይሄ ጉዳይ ቀልድ አይደለም። የእሳትና የጀነት ጉዳይ ነው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1💯1
🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል
ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል
መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡
የጠበበ ነገር መስፋቱ አይቀርም
አንቆ የያዘህ ነገር ይረግባል
ያሳሰበህ እንደ ጉም ይተናል
ያስጨነቀህ ጉዳይ እፎይታ ይኖረዋል
አንዳንድ ጊዜ ተስፋ"አንዳንዴ ደግሞ ባዶነት
አንዳንዴ ጨለማ" አንዳንዴ ደግሞ ብርሃን እየታየን
ዕድሜያችንን በዚሁ መሃል እንጨርሳለን"
ህይወት በእየፍርጇ ለየቅል ናት" አንዳዱ የሚታከምበት ገንዘብ ሀብት ኑሮት ከማይድን በሽታ ጋር ይሰቃያል"
አንዳንዱ ደግሞ በገንዘብ እጥረት ምክኒያት ታክሞ መዳን የሚችለውን በሽታውን ተው ማረኝ እያለ አብሮት ይኖራል።

🧷قَالَ شَيِّخ الإِسَلام ابن تَيِّمَية-رَحِمَهُ اللَّه-:
«أَن حَقيقة التَوحِيد أَن تَعبد اللَّه وحدهُ ، فَلا يُدعى إِلَّا هُوَ ، ولا يَخشى إِلا هُو ، ولَا يَتقى إِلَّا هَو ، ولا يتوكل إِلَّا هُوَ ، ولا يَكُون الدين إِلا لَهُ ، وأَلا نَتخذ الملائكة والبنين أَربابًـا فكيف بالأئمة والشُيُّوخ والعُلمَاء والمُلوك وغيرهم»
مِنهاج السُّنة(٣/٤٩٠)
https://t.me/https_Aselefya

🧷
https://t.me/https_Aselefya
ትዳር ውስጥ ከመግባት በፊት"
ትዳር ምንድን ነው የሚለውን ማወቅ እና አርቆ ማሰብ ለትዳር መስተካከል ዋና መሠረት ነው።https://t.me/https_Aselefya
(رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ.)
አሁን ያላችሁበት ጥሩ ሁኔታ ወደ አላህ ፈላጊ
አላህ ሆይ ወደእኔ ለምታወርደው መልካም ነገር ሁሉ ፈላጊ ነኝ።
#ማስታወሻ
አሁን ያላችሁበት ጥሩ ሁኔታ ወደ አላህ ፈላጊ
ከመሆን አያግዳችሁ።ሁሌም ዱዓእ አድርጉ። በበራፉ ላይ ብዙ ቁሙ፣እስኪከፈትላችሁ ድረስ አንኳኩ።አላህ ሆይ ወደእኔ ለምታወርደው መልካም ነገር ሁሉ ፈላጊ ነኝ።
#ማስታወሻ
🍓1
Forwarded from 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
«وَ أعْظمُ الحُبِّ ، حُبُّ الرُوحِ لِرُّوحِ،
«
=
t.me/https_Asselefya1
«
ትልቁና የላቀው ፍቅር አንድኛው ነፍስ ለሌላኛው ነፍስ ያለው ፍቅር ነው።=
t.me/https_Asselefya1
👍2
🧷ሚስት በባል ላይ ያላት መብት ምግብ፣ ልብስና ወጪ ብቻ አይደለም።
»»ይልቁንም
~
»»ይልቁንም
የዲን_የአቂዳ_የሱና_ትምህርቶች_ርህራሄ_እንክብካቤ_ፍቅር_ስሜት_መከባበር_ሀሳቧን_መቀበል እነኚ ነገሮች ማግኘት ይበልጥ አለባት
»»ምክንያቱም ከኪስ ልግስና ይልቅ የልብ ልግስና ያማረ ነው።~
🍓4
◦ في #التوحيد غنى القلب
وفي الشرك فقره
(يَا أَيُّهَا النَّاسُ أَنتُمُ الْفُقَرَاءُ إِلَى اللَّهِ ۖ
وَاللَّهُ هُوَ الْغَنِيُّ الْحَمِيدُ)
▪️قَالَ الإمَامُ ابنُ القيِّمِ رَحِمَهُ الله
حَقِيْقَةُ غِنَى القَلبِ؛ تُعَلُّقَهُ بِاللَّهِ وَحدَهُ،
وَحَقِيْقَةُ فَقرِهِ المَذمُوْمِ؛ تُعَلُّقُهُ بِغَيرِهِ.
📓 مَدَارِجُ السَّالِكِيْن || ٤٢٠/٢ ]

የብልሆች ተግባር:-
🔖 የሌሎችን ስኬት ማክበር :ቅናት ና ምቀኝነት ማስወገድ
አእምሮን ማፅዳት :አለባሌ ግምቶችን መራቅ
በአላማ ና በፕሮግራም መንቀሳቀስ
ምስጋናን መለማመድ:በታማኝነት ና በእውነት መናገር
መጥፎ ነገሮችን መራቅ :በመልካም መብቃቃት
ከሱስ መራቅ:በየጊዜው የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ
ለሁለቱም ሀገር የሚበጅን ህይወት መምራት
ለደስታም ለሀዘን :ለምቾትም ለችግር:ለእድለኝነትም ሆነ ለእድለ-ቢስነት የመጨረሻ ህይወት አሁን ያለንበት ህይወት ብቻ እንዳልሆነ በመገንዘብ ነገሮችን በልክ መያዝ ይልቁንስ ከጌታዋ ያፈነገጠች ነፍስ እድለቢስ እና ሁል ጊዜ በሃዘንና :በመከራ ውስጥ የምትሆነው በአኸራ እንደሆነ እንድሁም ጉድለት የሌለበት የተሟላ ህይወት የሚገኘው በጀነት ብቻ መሆኑን ማመን።
https://t.me/UstazKedirAhmed