ደና ነኝ እላለው መድከም የት አባቱ
ገደለኝ አልልም ሰበረኝ ናፍቆቱ
ልክ እንደ ጀግና ሲዋሽልኝ አፌ
ደና ነኝ እላለው ትዝታን ታቅፌ
http://t.me/https_Aselefye
~💦
ገደለኝ አልልም ሰበረኝ ናፍቆቱ
ልክ እንደ ጀግና ሲዋሽልኝ አፌ
ደና ነኝ እላለው ትዝታን ታቅፌ
http://t.me/https_Aselefye
~💦
የሰሞን አመሌ ልቤን እየነሳ
ያደክመኝ ጀምሯል አንተን እያወሳ
ሀሳቤ ተጓዡ ከደጅህ ደራሹ
ላያመጣህ አንተን እምባዬን አፍሳሹ
እስኪ ይሁን እንዳልከው
ቢለውም ልቤን ቅር
እኔ እንዳልኩት ምንም አይሆን
አይረጋም ያንተ ፍቅር......ልል ነበር ተውኩት
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
ያደክመኝ ጀምሯል አንተን እያወሳ
ሀሳቤ ተጓዡ ከደጅህ ደራሹ
ላያመጣህ አንተን እምባዬን አፍሳሹ
እስኪ ይሁን እንዳልከው
ቢለውም ልቤን ቅር
እኔ እንዳልኩት ምንም አይሆን
አይረጋም ያንተ ፍቅር......ልል ነበር ተውኩት
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
ታገስ !
የታገሰ መልካሙን ፍሬ ይበላል፤ለጠበቀ ሰው ሁሉ መልካም ነዉ፤በጌዜው የማይሆን አንዳች ነገር ለማይኖር በችኮላ ለፀፀት የሚዳርግህ ነገር ውስጥ አትግባ ለሚያልፍ ዛሬ የማያልፍ ታሪክን አትፃፍበት ትንሽ ብቻ ታገስ ብዙ ታተርፋለህ !
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
የታገሰ መልካሙን ፍሬ ይበላል፤ለጠበቀ ሰው ሁሉ መልካም ነዉ፤በጌዜው የማይሆን አንዳች ነገር ለማይኖር በችኮላ ለፀፀት የሚዳርግህ ነገር ውስጥ አትግባ ለሚያልፍ ዛሬ የማያልፍ ታሪክን አትፃፍበት ትንሽ ብቻ ታገስ ብዙ ታተርፋለህ !
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
💯1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በዝናብ ቀጥረኝ"
የሠማይ መስኮቶች በተከፈቱበት፣
በረዶ ያዘለ ዶፍ በሚወርድበት፣
እመጣለሁ ፍቅሬ ቀጥረኝ በክረምት፣
የበረዶው ክምር ጣቶቼን ይንዘረኝ፣
የቆምኩበት ቦታ እንዳይታወቀኝ፣
ግዴለህም ፍቅሬ በዝናብ ቀጥረኝ፣
ብትቀርስ’ አትበል አልቀርም እመነኝ፣
ምንም አይመስለኝም ይጣል ዶፍ በረዶ፣
ይመጣል አይቀርም ልቤ አንተን ወዶ፣
ውሽንፍሩ ይምታኝ ጠል ይውረድ በላዬ፣
እጠብቅሃለሁ እቆማለሁ ችዬ፣
የዳመናው ኩርፊያ ቁጣ ጉርምርምታ፣
አያሸብረኝም የመብረቅ ብልጭታ፣
ቅሩ አይታወቀኝ ብርዱን መች ‘ፈራለሁ፣
ፍቅርህን እንዴ’ልባስ ተከናንቢያለሁ፣
ሳይመችህ ቀርቶ ድንገት እንኳን ብትቀር፣
አይዞህ አልከፋም አይለኝም ቅር ቅር፣
ይልቅ…
እተካክዛለሁ ዝናቡን ታድሜ…
ስሜቴን በእንባዬ አጥበዋለሁ ቆሜ…
ንዴቴ እንዲያልፍልኝ እንዳልሄድ አቂሜ…
ብቻ ስለሁሉም በዝናብ ቀጥረኝ፣
ትቀራለች ብለህ እንዳትጠረጥረኝ፣
ጭጋግ ይሸፍነኝ ይጥፋኝ ያለሁበት፣
አልቀርም መጣለሁ በመውደድህ ስበት፣
መጠለያ ታዛ ሥፍራ በሌለበት፣
አውላላ ሜዳ ላይ ቀጥረኝ በክረምት፣
ያኔ ታውቀዋለህ…
የመውደዴን ጥልቀት…
የማፍቀሬን ጽናት....ልል ነበር ተውኩት።
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
የሠማይ መስኮቶች በተከፈቱበት፣
በረዶ ያዘለ ዶፍ በሚወርድበት፣
እመጣለሁ ፍቅሬ ቀጥረኝ በክረምት፣
የበረዶው ክምር ጣቶቼን ይንዘረኝ፣
የቆምኩበት ቦታ እንዳይታወቀኝ፣
ግዴለህም ፍቅሬ በዝናብ ቀጥረኝ፣
ብትቀርስ’ አትበል አልቀርም እመነኝ፣
ምንም አይመስለኝም ይጣል ዶፍ በረዶ፣
ይመጣል አይቀርም ልቤ አንተን ወዶ፣
ውሽንፍሩ ይምታኝ ጠል ይውረድ በላዬ፣
እጠብቅሃለሁ እቆማለሁ ችዬ፣
የዳመናው ኩርፊያ ቁጣ ጉርምርምታ፣
አያሸብረኝም የመብረቅ ብልጭታ፣
ቅሩ አይታወቀኝ ብርዱን መች ‘ፈራለሁ፣
ፍቅርህን እንዴ’ልባስ ተከናንቢያለሁ፣
ሳይመችህ ቀርቶ ድንገት እንኳን ብትቀር፣
አይዞህ አልከፋም አይለኝም ቅር ቅር፣
ይልቅ…
እተካክዛለሁ ዝናቡን ታድሜ…
ስሜቴን በእንባዬ አጥበዋለሁ ቆሜ…
ንዴቴ እንዲያልፍልኝ እንዳልሄድ አቂሜ…
ብቻ ስለሁሉም በዝናብ ቀጥረኝ፣
ትቀራለች ብለህ እንዳትጠረጥረኝ፣
ጭጋግ ይሸፍነኝ ይጥፋኝ ያለሁበት፣
አልቀርም መጣለሁ በመውደድህ ስበት፣
መጠለያ ታዛ ሥፍራ በሌለበት፣
አውላላ ሜዳ ላይ ቀጥረኝ በክረምት፣
ያኔ ታውቀዋለህ…
የመውደዴን ጥልቀት…
የማፍቀሬን ጽናት....ልል ነበር ተውኩት።
http://t.me/https_Aselefye
~🌸
👍3