La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–

☞ሰባት /7 አይነት ሰዎችን አላህ ከሱ ጥላ ውጭ ጥላ በሌለበት ቀን ከጥላው ያስጠልላቸዋል:–

① ☞ፍትሃዊ የሆነ መሪ፣

② ☞አላህን በመገዛት ላይ ያደገ ወጣት፣

③ ☞ልቡ በመስጂዶች ላይ የተንጠለጠለ ሰው፣

④ ⇡በአላህ መንገድ ላይ ተገናኝተው በዚያው ላይ የተለያዩ ሁለት ሰዎች፣

⑤☞ ባለ ደረጃና ባለ ውበት የሆነች ሴት (ለብልግና) ጠርታው "እኔ አላህን እፈራለሁ" ያለ ሰው፣

⑥☞ ቀኙ የሚሰድቀውን ግራው እስከማያውቅ ድረስ ደብቆ የሰደቀ ሰው እና

⑦☞ አላህን ብቻውን ሆኖ አውስቶ ዐይኖቹ እንባ ያፈሰሱ ሰው ናቸው።"⇄
ቡኻሪና ሙስሊም


" سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللَّهُ فِي ظِلِّهِ يَوْمَ لَا ظِلَّ إِلَّا ظِلُّهُ : الْإِمَامُ الْعَادِلُ، وَشَابٌّ نَشَأَ فِي عِبَادَةِ رَبِّهِ، وَرَجُلٌ قَلْبُهُ مُعَلَّقٌ فِي الْمَسَاجِدِ، وَرَجُلَانِ تَحَابَّا فِي اللَّهِ ؛ اجْتَمَعَا عَلَيْهِ وَتَفَرَّقَا عَلَيْهِ، وَرَجُلٌ طَلَبَتْهُ امْرَأَةٌ ذَاتُ مَنْصِبٍ وَجَمَالٍ فَقَالَ : إِنِّي أَخَافُ اللَّهَ، وَرَجُلٌ تَصَدَّقَ أَخْفَى حَتَّى لَا تَعْلَمَ شِمَالُهُ مَا تُنْفِقُ يَمِينُهُ، وَرَجُلٌ ذَكَرَ اللَّهَ خَالِيًا فَفَاضَتْ عَيْنَا
   




https://t.me/httpsLatahzenhttps://t.me/httpsLatahzen
ጉዙ ወደ አብሬት ብለው የሚሄዱ ሰዎች አላህን ሊፈሩ ይገባል።
የአብሬት ሸህ አይደለም ለሌላ ሊደርሱ፣ ሌላን ሊጠቅሙ እራሳቸውን ከደርግ ማስጣል አልቻሉም።
ይመጣሉ ብለው የሚያምኑም አሉ፣ እሳቸው ከነልጃቸውና ተከታዬቻቸው ሞተዋል።
አብሬትን በአላህ ላይ ማጋራት ታላቅ ወንጀል ነው።
ጉራጊኛ የምትናገሩ ዱአቶች በጉራጊኛ የሚባሉ የሺርክ ስንኞችን አደራ በቁርአንና ሱና መልስ ስጡባቸው።
Valentine`s day የፍቅረኛሞች ቀን በሸሪዓ እይታ

ክፍል ➊

የ"ፍቅር ዒድ" (የፍቅረኛሞች ቀን) ተብሎ ሰሞኑን እየተከበረ የሚገኘው በዓል በሚከተሉት ሶስት ምክንያቶች በሸሪዓ የተከለከለ ነው:–
1ኛ– በሸሪዓ መሰረት የሌለው አዲስ ፈጠራ በመሆኑ።(¹)
2ኛ– ወሰን ወዳለፈ የሴቶች ፍቅር የሚቀሰቅስ በመሆኑ።
3ኛ– ለሰለፎች ጎዳና ተቃራኒ ወደሆኑ ውድቅ ተግባራት ልቦና እንዲጠመድ የሚያደርግ በመሆኑ ናቸው።
* እያንዳንዱ ሙስሊም ይህንን ቀን በምግብ፣ በመጠጥ፣ በልብስ፣ በስጦታና በመሳሰሉ አዳዲስ ፈጠራወች ከሌሎች ቀናቶች መለየት አይገባውም።(²)
* እያንዳንዱ ሙስሊም በዲኑ የሚኮራ እንጅ የትም ተነስቶ ለጮኸው ሁሉ ተከታይ ሊሆን አይገባውም።(³)
# ግልፅም ይሁን ስውር ከሆነ ፈተና ሙስሊሙን ህብረተሰብ እንዲጠብቀውና እርሱ ብቻ ረዳታችን ወደሀቅ መሪያችን እንዲሆን አላህን እማፀናለሁ።

ሸይኽ ብን ዑሰይሚን ‐ረሂመሁላህ‐ መጅሙዑል ፈታዋ 16/199

======================
(¹) እንደሚታወቀው ዲናችን ጭማሪን የማይሻ የተሟላ እምነት ነው አላህ እንዲህ ብሏል:–
﴿ٱلْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًاۚ﴾( المائدة\٣)
{ዛሬ ሀይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ ፀጋየንም በናንተ ላይ ፈፀምኩ} (አልማኢዳህ/3)
የአላህ መልእከተኛ ﷺ አዒሻ (ረዲየሏሁዓንሃ) ባስተላለፉት ሐዲስ የሚከተለውን ተናግረዋል "በዚህ ጉዳያችን (በዲናችን) ከእርሱ ያልሆነን ነገር የፈጠረ (ስራው) ተመላሽ ነው።" (ቡኻሪ/2550 ሙስሊም/1718) በሌላ ዘገባ "ትእዛዛችን የሌለበትን ስራ የሰራ (ስራው) ተመላሽ ነው።" (ሙስሊም/1718)
ዓብደላህ ብን ዑመር (ረዲየሏሁዓንሁማ) እንዲህ ይላሉ 'ሁሉም የፈጠራ ተግባር ጥመት ነው! ሰዎች መልካም ነገር አድርገው ቢያዩት እንኳ!' (ኢብን በጠተ ፊል ኢባናህ: 205/ ወልአልካኢ: 126)

(²) ኢስላም በሌላ እምነት ተከታዬች እንዳንመሳሰል በጥብቅ አዞናል የነብዩ ﷺ ተግባርና ንግግራቸው የሚያመላክተው በጭራሽ ከነርሱ ጋር መመሳሰል እንደማይገባ ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል (ከህዝቦች ጋር የተመሳሰለ እርሱ ከነርሱ ነው) (አቡ ዳውድ 4031)
በተከታዬቻቸው ላይ ያላቸውን ስጋት ነብያችን ﷺ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል:‐ ❝ከእናንተ በፊት የነበሩትን (ህዝቦች) ፈለግ ስንዝር በስንዝር፣ ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የፍልፈል (ወከሎ) ጉድጓድ ቢገቡ እንኳ (ተከትላችሁ) ትገባላችሁ!❞ ሠሃቦችም (ሪድዋኑሏሂዓለይሂም) አንቱ የአላህ መልእክተኛ:– ‹አይሁዳውያንን እና ክርስቲያኖችን?› ነው አሉ ረሡልም ﷺ ❝(ታዲያ) ማንን?❞ አሏቸው። (ቡኻሪ/3269 ሙስሊም/6952) በጌታየ ይሁንብኝ አላህ የጠበቃቸው ሲቀሩ አብዛኛው በዚህ ፈተና ወድቋል።
እንደሚታወቀው ይህ "የፍቅረኛሞች በዓል" ("የፍቅር ዒድ") ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክርስቲያኖችና ምዕራባዊያን የሚያከብሩት በአንድ ግለሰብ የተመሰረተ በዓላቸው ነው። እኛ ሙስሊሞች በዚህ ውዳቂ በዓል ተሳታፊዎች ልንሆን አይገባም ይህ ከሌላ እምነት ተከታዬች ጋር የመመሳሰል ጉዳይ አደጋው የከፋ ነው።
አቡል ዓባስ ሸይኹል ኢስላም አህመድ ብን ተይሚያህ [ዓለይሂ ሩሃማቱ ረቢል ዓለሚን] እንዲህ ይላሉ:–
" በዓላቶች ከሸሪዓ ህግጋትና ጎዳና ክፍሎች ናቸው።
አላህ እንዲህ ብሏል:– "{ለየህዝቡ ሁሉ እነሱ የሚሰሩበት የሆነን ስርአተ ሀይማኖት አድርገናል}" (አልሐጅ: 67) በዓላት ከሸሪዓ ህግጋትነት አንፃር ከቂብላ፣ ከሶላት እና ከፆም የሚለይበት ነገር የለም። በሌሎች በዓላት ሁሉ መስማማት በክህደት ሁሉ እንደመስማማት ይቆጠራል። በተወሰኑ የቅርንጫፍ ዘርፎች መስማማት በተወሰኑ ቅርንጫፋዊ የክህደት ዘርፎች እንደመስማማት ይቆጠራል። በዓላቶች ሀይማኖቶች በተለየ ሁኔታ የሚታወቁበትና የሚገለፁበት ነው። ( ሸሪዓው ባላዘዛቸው) ባዓላት መስማማት በክህደት ልዪ መገለጫዎች እንደመስማማት ይቆጠራል። ( ሸሪዓው ባላዘዛቸው) በዓላት መመሳሰል በጥቅሉ (ሸሪዓዊ) መስፈርቶችን ተከትሎ ከክህደት ማድረሱ የሚያጠራጥር አይደለም።"።❜ (ዒቅቲዳኡ ሢራጠል ሙስተቂም/236)
(³) ሙስሊሙ ማህበረሰብ በእምነቱ ሚብቃቃ, የብልጭልጭ አለም ምንም ያክል ቢሸላለምና ቢዋብ ተወጋጅ እንደሆነ መዘንጋት አይገባም። ሌሎች ይህን የመሳሰሉ በዓላቶች ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ሰርገው እየገቡ ትእዛዛት የመጣባቸው ይመስል በቋሚነት እየተተገበሩ ይገኛሉ። ለምሳሌ:– ልደት፣ የታጨች ሴት የሰርጓ ቀን ሲቃረብ wedding shawor፣ ጥንዶች የተጋቡበትን እለት በየአመቱ ማክበር anniversary፣ 9ነኛ ወር ላይ የምተገኝ ነፍሰጡር "baby shawor" እየተባለ የሚከበረው ይገኝበታል ይህ በጣም አስነዋሪ ተግባር ነው ይህንን ፀጋ የለገሰው አላህ ሆኖ ሳል ምስጋናን ለአላህና አላህ ባዘዘው መልኩ ማድረስ ሲገባን እርሱን ማመፅ ብሎም በመጥፎ ነገር መተጋገዝ ይህ ከባድ አደጋ ነው። ለዚህ ብቸኛው መፍትሄ ወደ እምነታችን መመለስና ስለ እምነታችን ተጨባጭ ግንዛቤ እንዲኖረን መማር፣ በስራችን የምናኖራቸውን ቤተሰቦች የአላህን ትእዛዛት እንዲተገብሩና ክልክሎችን እንዲርቁ በማድረግ ሐላፊነታችን ልንወጣ ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ዑመር ብን ዓብዱልዓዚዝ (ረሂመሁሏህ) እንዳሉት "አሏህ በግለሰብ ወንጀል ማህበረሰብን አይቀጣም ነገር ግን የተጠላ (ፀያፍ) ተግባር በአደባባይ ሲሰራ ሁሎቹም ለቅጣት የተገቡ ይሆናሉ።" (አልዑቁባት ሊብን አቢ ዱንያ/55)

ክፍል 2 ይቀጥላል


https://t.me/httpsLatahzen
👉⚠️እንጠንቀቅ!!

ዝሙትም ለማስፋፋት እንዲህ የፍቅር ቀን መቁጠሪያ ተዘጋጅቶለታል

የቫላንታይን ካላንደር
🚫🚫🚫🚫🚫🚫
👉February 7-------------የአበባ ቀን
👉February 8------የመተጫጫ ቀን
👉February 9------የቸኮላታ ቀን
👉February 11 -----ቃል የመገባባት ቀን
👉February 12----የመተቃቀፍ ቀን
👉February 13-----የመሳሳም ቀን
👉February 14-----የፍቅር ቀን

👌በዚህ ተግባር የምንሳተፍ ሰለጠን የምትሉ ሙስሊሞች ራሳችሁን ጠብቁ!!

አሏህ ይጠብቀን
👌ግብዣ…!
🌸መሳጭ ቲላዋ!
#أذكار_الصباح
((يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغيثُ أَصْلِحْ لِي شَأْنِيَ كُلَّهُ وَلاَ تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ)).
🍃🌻
( لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَريكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالْحَمْدُ للَّهِ، وَلاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكبَرُ، وَلاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ الْعَلِيِّ الْعَظِيمِ، رَبِّ اغْفرْ لِي ).
🍃🌻
(أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّداً عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ..).
🍃🌻
◾️እውቀትን የሚያክል ምንም ነገር የለም‼️


ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

➧አላህ ሸሪአዊ እውቀት ከሰጠህ፦ አብሽር! ምክንያቱም ይህ ማለት አላህ መልካም ሽቶልሀል ማለት ነው።

ኢማሙ አህመድ እንዲህ ብሏል «ንያውን ለተስተካከለለት ሰው እውቀትን የሚያክል ነገር የለም» አሉ።

➧ የአብደላህ አባት ሆይ፦ እንዴት ነው ታዳ ንያውን የሚስተካከለው? ተብለው ሲጠየቁ፦ «ጅህልና (መሀይምነትን) ከራሱና ከሌሎች ለማንሳት ብሎ ማሰቡ ነው» ብለው መለሱ።

📚(شرح حلية طالب العلم / ص16)

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
#ከሀዲስ

1) «ከቀብር ቅጣት ነጃ የወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው ገር ይሆንለታል፣ ከቀብር ቅጣት ነጃ ያልወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው የበለጥ ይጠናበታል»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📔ሶሒሁል ጃሚዕ (1684)

2) ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አሉ፦
«ረሱልን በላጭ የሆነው መልካም ስራ የትኛው ነው ብየ ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ "ሶላትን በወቅቱ መስገድ" ከዛስ አልኳቸው ለወላጆች መልካም መዋል አሉኝ»።
📔ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

3) «ረሱል የሞቱ ቀን አቡበክር ሲዲቅ ወደርሳቸው መጣና ፊታቸውን ገልጦ ግምባራቸውን ሳማቸው ከዛም እንዲህ አለ"አባቴና እናቴ መስዋት ይሁኑሎትና በህይወትም ሳሉ ሙተውም ምንኛ ውብ ናችሁ»።
ምንጭ:-📔ሶሒሁል ቡኻሪ (3667)
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:

لا تكثروا الكلام بغير ذكر الله؛ فإن كثرة الكلام بغير ذكر الله تعالى قسوة للقلب! وإن أبعد الناس من الله تعالى القلب القاسي.
ነብዩ ሰ.ዐ.ወ.እንድህ ይላሉ፦ ንግግርን አታብዙ።
አሏህን ለማውሳትና ለማወደስ ካልሆነ በስተቀር።ለምን ከተባለ፦ ዝክር ያልሆነ ንግግርን ማብዛት ቀልብን ያደርቃታልና።ከአሏህ ረህመት በጣም የራቀ ሰው ማለት ደግሞ ቀልቡ የደረቀበት ሰው ነው። አሏህ ይጠብቀንና‼️

ስለዝህ በተቻለ መጠን መልካም ንግግርን ለመናገር እንሞክር ።አልያም ዝም እንበል።
👉ከተቻለ ሰዎችን ወደ ኢስላም ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሱና ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሷላት ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ እውቀት መድረክ ጋብዛቸው

👉ከተቻለ ከሀሜት እንድ ርቁ ምከራቸው

👉ከተቻለ ከውሸት ራቁ በላቸው

👉ከተቻለ ወደ ተውሂድ ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ዝክር ጥራቸው

👉ከተቻለ እርቅን እንድያሰፍኑ ምከራቸው
👉ከተቻለ ሷደቃ እንድሰጡ አነሳሳቸው

👉ከተቻለ የቲሞችን እንድረዱ አድርጋቸው

👉ከተቻለ ቁርኣንን እንቅራ እናስቀራ

⚠️ከዝህ ውጪ የሆነ ንግግር በሽታ እንጂ የቀልብ ፈውስ አይሰጥህም በደንብ ራቀው‼️

መልካም አዳር‼️

አቡ ሙስሊም ቢን ጋቼኖ
Audio
#የመጨረሻ_ክፍል
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
#የነብዩ_ዩሱፋፍ_(ዐ.ሰ)የህይወት ታሪኩ የመጨረሻ ክፍል ደርሱዋል እስከ ዛሬ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለተከታተላቹን በጣም እናመሰግናለን። ለሌሎችም #ሼር አርጉት እሀንን ጣፋጭ የነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) የህይወት ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከላያቹት በዚ ቻናል ማያት ትችላላችሁ ዉድ ye_ le tahzenቤተሰቦቼ 👉

ሁላቹንም ለአላህ ብዬ እወደቹዋለው።

#ሼር_ሼር_ሼር


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
ማንኛችሁም ሞትን እንዳይመኝ
ቢስሚላህ
አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ
አሰላሙዐለይኩም
ውዶች ፣
ሰዎች በእይታቸው ከበድ ያለ ችግር ሲገጥማቸው ምነው በሞትኩት፣ይህንን ሳላይ ብሞት ይሻለኝ ነበር።ሲሉ ይደመጣል።ሌላው ሀገራዊ ብሂል "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል
ድሀ ሞኝ ነው ሞትን ይመኛል"
በማለት ዛሬ ከበድ ያለ ችግር ቢገጥምህ ነገ ደግሞ መውጫ ስለሚኖር ተሰፋን አትቁረጥ የተሻለ ነገ ይኖራልና።
ይህን መርሕ ከ 1400 ዓመት በፈት ውዱ ነቢይ
ለ ጓዶቻቸው ሰሐባዎች በተለያዩ ዘገባዎች በገጠማቸው ችግር ሞትን እንዳይመኙ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቁ እንደነበር እንረዳለን።ከእነዚህ ዘገባዎች የሚከተለው የቡኻሪ ዘገባ ይጠቀሳል።
حَدَّثَنَا ابْنُ سَلاَمٍ، أَخْبَرَنَا إِسْمَاعِيلُ ابْنُ عُلَيَّةَ، عَنْ عَبْدِ الْعَزِيزِ بْنِ صُهَيْبٍ، عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَتَمَنَّيَنَّ أَحَدٌ مِنْكُمُ الْمَوْتَ لِضُرٍّ نَزَلَ بِهِ، فَإِنْ كَانَ لاَ بُدَّ مُتَمَنِّيًا لِلْمَوْتِ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ أَحْيِنِي مَا كَانَتِ الْحَيَاةُ خَيْرًا لِي، وَتَوَفَّنِي إِذَا كَانَتِ الْوَفَاةُ خَيْرًا لِي ‏"‌‏.‏ اللبخاري 6351

ከአነስ ቢን ማሊክ በተላለፈው ሀዲስ እንደሚከተለው ማለታቸውን ቡኻሪ ዘግበዋል
"አንዳችሁ በገጠመው ችግር የተነሳ ሞትን አይመኝ።የግድ ሞትን የሚያስመኘው ደረጃ የሚያደርሰው ከሆነ አላህ ሆይ መኖሬ ለኔ የሻለ ከሆነ በህይወት አኑረኝ።መሞቴ ለኔ የተሻለ ከሆነ
ሞትን ግጠመኝ ይበል" በማለት ምርጫውን ለአላህ ይስጥ ዘንድ አስተምረዋል።
ቡኻሪ አረብኛ እንግሊዝኛ መድበል ሀዲስ ቁጥር 6351

ከአቢሁረይራ በተወራ ሀዲስ ደግሞ " .....አንዳችሁ ሞትን እንዳይመኝ መልካም ሰሪ ከሆነ የመልካም ተግባር ኪታቡ እንዲጨምርላት መሆኑ በላጩ ነው።በተቃራኒው አመፀኛ / አጥፊ ከሆነ ደግሞ ተውበት ለማድረግ እድል ያገኛልና" ቡኻሪ ሀዲስ ቁ 5671
በሌላ ዘገባ እድለኛ ሰው ማለት እድሜው የረዘመ ነው ።ማለታቸው ተዘግቧል።
ሁላችንም አላህ ረጅም እድሜና መልካም ስራን እንዲያበዛልን እንለምነው።
እርሱ የባሮቹን ልመና ሰሚ ነው
ወሰለላሁመ ወሰሊም ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ
ወሰላም
(سُبْحانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتوبُ إِلَيْكَ).
🍃🌻
(بِسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، وَلَاَ حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ).
🍃🌻