La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
💫ጁማዕ💫

ነቢዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦
"ፀሀይ ከወጣችበት በላጩ ቀን የጁሙአ ቀን ነው በዛች ቀን ነቢዩላህ አደም ተፈጠረ፣ጀነትንም ገባ፣ከጀነትም ወጣ፣ የቂያማ ቀንም በጁሙአ ቀን እንጂ አትቆምም"
[ሙስሊም _ ዘግቦታል]
በጊዜ ወደ መስጅድ መሄድ ነቢዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦

የጁማዕ# ቀን ላይ በእያንዳንዱ መስጅዶች በር ላይ መጀመሪያ የመጣውን መጀመሪያ ላይ ቀጣይ የመጣውን በተርታ የሚመዘግቡ መላኢካዎች አሉ ልክ ኢማሙ ሚንበር ላይ በተቀመጠ ጊዜ መዝገባቸውን ዘግተው ኹጥባ ለማዳመጥ ይመጣሉ። መጀመሪያ ሰአት ላይ የመጣ ሰው ምሳሌው ልክ ግመል ሰደቃ እንዳወጣ ነው፤ከዛ ከብት እንደሰደቀ ነው፤ከዛ ሙክት በግ እንደሰደቀ ነው፣ከዛ ዶሮ እንደሰደቀ ነው፣ ከዛ እንቁላል እንደሰደቀ ነው።"
[ቡኻሪ ዘግቦታል]

فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡
وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوًا انفَضُّوا إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَائِمًا ۚ قُلْ مَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ مِّنَ اللَّهْوِ وَمِنَ التِّجَارَةِ ۚ وَاللَّهُ خَيْرُ الرَّازِقِينَ
ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡
{ጁማዓህ-10-11}

የጁማዕ# ሶላት ሁለት ረካዐዎች ያሉት ፈርድ ሶላት ነው።
አንድ ሰው" ዘግይቶ ቢመጣና ሁለተኛውን ረከዐ ከጀማዓጋር ከሰገደ ቀሪውን አንድ ረከዐ አሟልቶ መስገድ አለበት ። አንድ ሰው" በጣም ዘግይቶ በመድረሱ የጁማዓው ሶላት ሙሉ በሙሉ ያመለጠው እንደሆነ አራት ረከዐዎች ፈርድ የዙሁር ሶላት መስገድ ይኖርበታል። የጁማዓ ሶላት የዙሁር ሶላት ምትክ ናት።

የጁማዕ ቀን ሱናዎች፥- ሻወር መውሰድ
- ንጹህ ልብስ መልበስ- ሽቶ መቀባት
- ሲዋክ _መፋቂያ መጠቀም
- ቁራዕን ማንበብ
ቁርአን እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ የሚቆይ ፣
እስከ ዕለተ ሞትህ የምትከተለው ትዕዛዝ ያለበት ፣ ንጽሕናው እንደተጠበቀ የሚዘልቅ መጽሐፍ ነው። ሱረቱል ከህፍን መቅራት በጁማዕ# ቀን የተወደደ ነው

#የጁማዓ ሶላት

ጁማዓ ለመስገድ ወደ መስጅድ የሔደ (የገባ) ሰው" ፀሐይቱ ከእኩል ቀን" ወደ ምዕራብ ትንሽ ካጋደለችበት ጊዜ አንስቶ ኢማሙ ኹጥባ እስከ ሚጀምሩበት ጊዜ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የፈለገውን ያህል ነፍል "ሶላት መስገድ ይችላል።
ቢያንስ ሁለት ረካዐ ሱንና መስገድ ግን ይጠበቅበታል።

*ኹጥባ (ምክርን) በፀጥታ ማድመጥ*

ኹጥባ ከተጀመረ በኋላ ሰጋጁ ሕዝብ በፀጥታ ማድመጥ አለበት። አንድ ሰው" ኢማሙ ኹጥባ ሲያደርጉ ከደረሰ ኹጥባውን ለማድመጥ ቁጭ ከማለቱ በፊት ሁለት ረካዐ ነፍል መስገድ ይኖርበታል።

ጀቢር(ረ.ዐ.) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ኹጥባ ስያደርጉ እንደ ሚከተለው " ማለታቸውን ዘግበዋል፦ ማንኛችሁም ኢማሙ ኹጥባህ ስያደርጉ ለጁማዓ የደረሰ ሰው" የግድ ሁለት አጠር ያሉ ረካዐዎች መስገድ አለበት።

በሌላ ሐዲስም ጃቢር (ረ.ዐ)
-አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ ዐ ወ) ኹጥባ ስያደርጉ በነበሩበት ጊዜ አንድ ሰው መጣ " ከዛም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሰግደሀል እንዴ? ሲሉ ጠየቁት ፥ ሰውየውም -አይ ሲል መለሰላቸው! ከዚያም ነብዩ ( ሰ.ዐ.ወ) ተነስና ስገድ አሉት።

(ቡኻሪ -ሙስሊም-አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል።)

አንድ አንድ ሰዎች ኢማሙ ኹጥባ ንግግር እያደረጉ ሳለ ሁለት ረካዐዎች ሱንና የሚሰግድ ሰው ካዩ በጣም ይናደዳሉ ፥ ኢማሙን እንደ መናቅ ይቆጥሩታል ፦ይህ አስተሳሰብ ግን ስህተት ነው። ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተቀሰመ ልምድ አይደለም።
አቢ ቀታዳህ(ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ሚከተለው መናገራቸውን ገልፀዋል ፦ ማናችሁም ሰው" ወደ መስጅድ ሲገባ ሁለት ረካዐዎች (ተሒይቱል መስጅድ) ሳይሰግድ መቀመጥ የለበትም።
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።)
*የጁማዓ ሶላት*
የጁማዓ ሶላት ሁለት ረካዐዎች ያሉት ፈርድ ሶላት ነው።
አንድ ሰው" ዘግይቶ ቢመጣና ሁለተኛውን ረከዐ ከጀማዓጋር ከሰገደ ቀሪውን አንድ ረከዐ አሟልቶ መስገድ አለበት ። አንድ ሰው" በጣም ዘግይቶ በመድረሱ የጁማዓው ሶላት ሙሉ በሙሉ ያመለጠው እንደሆነ አራት ረከዐዎች ፈርድ የዙሁር ሶላት መስገድ ይኖርበታል። የጁማዓ ሶላት የዙሁር ሶላት ምትክ ናት።

*ከጁማዓ በኋላ የሚሰገድ ሶላት*
አብደሏህ ኢብኑ ዑመርን ጠቅሰው ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ "ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አብዛኛው ከጁማዓ በኋላ እቤት ገብተው ሁለት ረከዐ ሱና ይሰግዱ ነበር"ብለዋል።
አቡ ሁረይራን ጠቅሰው ሙስሊም አቡ ዳውድና ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ ከጁማዓ በኋላ የሚሰገድ አራት(4) ረከዐ ይስገድ" ብለዋል።
ኢብኑ ዑመር ጠቅሰው -አቡ ዳውድ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ( መስጅድ ከሰገዱ አራት(4) እቤት ከሰገዱ ሁለት ረከዐ ሱና ነበር የሚሰግዱት" ብለዋል
Audio
♦️አንድ ሰው የውመል ቂያማ ባነሳቸው ፎቶዎች ልክ ይቀጣል።

🎙الشيخ :- صالح الفوزان "حفظه الله"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
حظر الجوال على الشباب مقتطف للشيخ محمد بن عبد الله الإمام

በሰልካችን ምን እየሰራን ነው እህት ወድሞች

እስት ቆም ብለን እናሰበው ይህ ጀዋል በጃችን

ያለው በገዛ ብራችን የመጣነው ሙሲባ ምን

እያረግንበት ነው ያአላህ ያረብ ወላሂ ሲያስፈር
https://t.me/httpsLatahzen
Audio
ጥፍጥ ያለች ግብዣ እንሆ
ለቁርአን ወዳጆች
🌹ሃጅ ለመድርግ ላቃተን ሰዎች #ጁመዓ ለኛ ሃጃቺን ነውና አላህ ከመጣው በላዕ ከሚመጣው በላዕ ሁሉ ነጃህ ብሎን ሃጃቺንሁሉ የሚይወጣበት በሰላት በሰለዋት በኢባዳ ፍክት ፍክትክት ብለን ምናሸበርቅበት ምርጥዬ😍
🤲🤲ጁመዓ ይሁንልን🤲🤲
#Share_Share ለወዳጆህ
Join 👉
https://t.me/httpsLatahzen👈 Join
ልክ እንደዚህች ጎጆ አሁን ላይ መንግስት ስሙ ብቻ ነው ያለው የሚያስብሉ ክስተቶች እያጋጠሙን ነው። ትክክለኛ አሸባሪዎችና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ የጥላቻ ሰባኪዎች እነ ምህረተ አብ አሰፋ ተቀምጠው፤ ሳያጣሩ ንጹሐንን ማሰር ምን ይሉታል?
🌹

💢ከጁመዓ ቀን ሱናዎች

↩️ ‏سنن يوم الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት

📌((قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين))
🔺የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል))
📚 صحيح الجامع - رقم : (6470
. ይህ የምታዩት ውብ መስጂድ ቱርክ ወይም አረብ ሀገራት ውስጥ አይደለም ❤️ እዚው ወሎ ባቲ ከተማ ነው ❤️
ጉሉ ማሻአላህ 🥰

ጁመዓዬ 🕌 ❤️

.━─━──────༺༻──────━─━
ጋዜጠኞች በዚህ መልኩ እየተናገሩ ነው።

ዘመቻችን ፍሬው መታየት ጀምሯል ማለት ነው።
➽የፋናው ጋዜጠኛ ዶክመንተሪውን በዚህ አገላለፅ እጄ የለበትም ብሏል።

እኛ ተግባራዊ ስራችንን ስንሰራ ብቻ ነው ገለውን መልሰው እኛኑ የሚከሱ ጠላቶቻችንን እንዲህ ማርበትበት የምንችለው እላለሁ።

እናም ዘመቻችን ጠላቶቻችንን እስክናውቃቸው ድረስ ይቀጥላል...ሸር አድርጉ ሸር

https://t.me/httpsLatahzen
#የሙስሊሟ ሴት ሒጃብ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ونِساءٌ كاسِياتٌ عارِياتٌ مُمِيلاتٌ مائِلاتٌ، رُؤُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ البُخْتِ المائِلَةِ، لا يَدْخُلْنَ الجَنَّةَ، ولا يَجِدْنَ رِيحَها، وإنَّ رِيحَها لَيُوجَدُ مِن مَسِيرَةِ كَذا وكَذا.، ﴾

“ሁለት ዓይነት ሰዎች የእሳት ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም የነርሱ ዐይነት ፈጽሞ አላየሁም… ሴቶች ናቸው የለበሱ ግን እርቃን የሆኑ። የሚወለጋገዱ፣ ራሳቸው እንደግመል ሻኛ የተቆለለና የተዘነበለ ጀነትን አይገቡም! ሽታዋንም አያገኙም፡፡ ሽታዋ በዚህና በዚህ ያህል ርቀት የሚያውድ ሲሆን፡፡”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 2128

ሸሪዓዊ የሒጃብ መስፈርቶች

⒈ ሁሉንም የሰውነት ክፍል የሚሸፍን መሆን አለበት።

⒉ ከካህዲያንና ከወንድ ጋር የሚመሳሰል መሆን የለበትም።

⒊ ሰፋ ያለ መሆን አለበት። ጠባብ መሆን የለበትም።

⒋ ሽቶ የተቀባ መሆን የለበትም።

⒌ ስስ ሆኖ የሰውነት ከለርን ማሳየት የለበትም።

⒍ ዋጋው በጣም የተወደደ ዝናን ለማትረፍ የሚለበስ መሆን የለበትም።

⒎ ያሸበረቀና ዕይታን የሚስብ መሆን የለበትም።

ጆይን፡https://t.me/httpsLatahzen
ጠባይህ ከፍ ካላረገህ ሥልጣንህ ከፍ አያረግህም፣
ሥራህ ካላሳመረህ ልብስህ አያሳምርህም፣
ሕይወት ዲን ብቻ አይደለም። ሥነምግባርም አቋምም ናት።
ጥሩ ፀባይ ከሌለህ የለህም።
አቋም ከሌለህ ማንም አያከብርህም ።
"ብር ነው ጊዜ ሚሰጣችሁን ባል ነው ምትወዱት።" ተብለው ተጠየቁ አሉ ሴቶች። ብር በጊዜ ሚሰጠንን ብለው መለሱ።
ሕይወት እንዲህ ናት!
የአዚም ሰንሰለት፣የድባቴ ጉዝጓዝ፤
ቢንዱት አያልቅም፣የሸክሟ ሕብረ-ጓዝ፤
አንዱን ጭንቅ አልፎ. . .
ወደ አዲስ ጭንቅ መጓዝ!
#ጀነት_አትገኝም!

ረመዳን ወጣ፤
ሸይጧንም ተፈታ፣
ወሩን ሙሉ ሰገድኩ፤
ከእንግዲህስ ይብቃ!
ትንሽ ፈታ ልበል፤
ቀጣዩ እስኪመጣ፣
አለች ነብስያዬ፤
አሁኑኑ እንውጣ፡፡
ባንድ ወር ኢባዳ፣
ባንድ ወር ሁካታ፣
ይገኛል መስሏታል፤
የዘላለም ደስታ፡፡

ነብሴ ሆይ! ልንገርሽ፤
መሸንገልሽ ይብቃ፣
ሰው ጀነት አይገባም፣
በኼይር ስራው ብቻ፡፡
እንዲያውም ልንገርሽ፤
ስለ አንድ ደግ ሰው፣
አላህን መቶ አመት፣
ሳያርፍ ያመለከው፣
እናልሽ ይሄ ሰው፤
ሞት አይቀር ሞተልሽ፣
ስራውን ሊያስመዝን፤
አላህ ፊት ቆመልሽ፣
ከዛማ ይሄን ሰው፣
አላህ በእዝነቱ፤
ጀነት ግባ ቢለው፣
የሰራሁት ስራ፤
እጅጉን ብዙ ነው፣
ጀነትን ለመግባት፤
ስራዬ በቂ ነው፡፡
እዝነትህ ይቅርብኝ፤
አልፈልግም አለው፡፡

እናማ አምላኩ፤
እዝነቱን ሊያሳየው፣
‹‹እንደዛስ ከሆነ፤
ና ጠጋበል!›› አለው፣
‹‹ስራህን እንመዝን፤
ከበቃህ እንየው!››

መልካም ስራው ሁሉ፤
ባንድ ላይ ሆነና፣
የጌታውም ፀጋ፤
ባንድ ጎን ቆመና፣
ይነፃፀር ቢባል፤
የሰውዬው ስራ፣
እንኳንስ ለጀነት፤
ለአይኑ ምስጋና፣
ሳያደርስ አለቀች፤
አልበቃ አለችና!
እናም ውዷ ነብሴ፤
ልልሽ የፈለኩት፣
ካልታከለ በቀር፤
የአምላክሽ እዝነት፣
እንኳንስ ባንድ ወር፤
ልትገቢ ጀነት፣
ሽታዋ አይገኝም፤
ብትፆሚ ሽህ አመት፡፡
እናማ ቀጥ በይ፤
ከአመት እስከ አመት፣
ከመስጂድ አትራቂ፤
እስኪመጣብሽ ሞት፡፡
በረመዳን ብቻ፤
አላህን በማምለክ ፣
ጀነት አትገኝም፤
አንድ ወር በማሸቅ፡፡

#ሼር #share
#join
https://t.me/httpsLatahzen
ውዷ እህቴ

👑አማኝ ሴት የተረጋጋች ነች👑

✒️አነጋገሯ በዝግታ
✒️አረማመዷ በቀስታ
✒️አለባበሷ በኒቃብ በጅልባብ የደመቀ
✒️ አቂዳዋ የጠራ ነው።
👇
https://t.me/httpsLatahzen
ትንሿ ዒድ
➬➬➬➬
የኢድ ትንሽ የለ ሁለቱም ትልቅ ነው
በእስልምናችን የ ተ ደ ነ ገ ገ ው
በነብዩ ሱና የ ተ ረ ጋ ገ ጠ ው
📏📏📏📏📏📏📏📏📏
ፁሙ የተባለው 6ቀን ከሸዋል
ወይ ከመጀመሪያ ሲፈለግ ከመሀል
ለዘገየ ደግሞ ሊያልቅ ሲል ይፆማል

ታዳ ➴➘➴➷➘
ትንሿ ዒድ መጀመሪያ ላይ ናት
በናንተ ቃዒዳ ባስቀመጣችሁት
ፍልስፍስፍ አርጋችሁ ባፀደቃችሁት
📏📏📏📏📏📏📏📏📏
ያንን ቀን ያልፆመ አጅሩ አምልጦታል
ትርፉ ረሀብ ነው ሲባልም ይሰማል
የቢድዓ ነገር እጅጉን ይደንቃል
📏📏📏📏📏📏📏📏📏
እስኪ መረጃ አምጡ ከነብዩ ሀዲስ
ወይ ከአዒማወች በእውቀት ይዳሰስ
ሀቅ ከባጢሉ እንዳይድበሰበስ።




➝➝➝➝➝➝➝➝➝➝➝➝
ትንሿ ኢድ

አትቀልዱ ፋዘር የምን ትንሽ ኢድ ነው፤
በቁርአን የሌለ ሀዲስ የማያውቀው፤
በወርድ ስፋቱ ወይም በምንድነው፤
ትንሽ ትልቅ ብሎ የማበላለጫው፤

ለኢደል ፊጥሩ ያልታረደው ሙክት፤
ትንሽ ኢድ ተብሎ ያገኛል ትልቅ መብት፤

እረ ፍትህ ይኑር ህሊና ይውቀሰን፤
ቁርአን ይዳኘን ሀዲሱ ይፍረደን፤

ትንሿ ኢድ ብለህ
ትልቅ መብት ስትሰጠው፤
ለዚህ ለቢድአህ ምንድነው ማስረጃው፤

ለዚህ ለድፍረትስ ከቀደምቶች ፋና፤
ይምጣልን ደሊሉ ከኪታብ ከሱና፤

አይ ሸሆቹ አዘዋል ኢዷን ልናከብር፤
ቃላቸው ክቡር ነው ብለህ ብትደሰኩር፤
ፍፁም አይጠቅምህም ውርደቱ
ሳይመጣ ተመለስ በክብር፤
📝 Ibnu muhammed