La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
#أذكار_المساء
أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيطَانِ الرَّجِيمِ
﴿اللَّهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لاَ تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلاَ نَوْمٌ لَّهُ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلاَّ بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلاَ يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلاَّ بِمَا شَاء وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلاَ يَؤُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ﴾.
🍃🌻
ረመዷን
(5)
**
ሰዎች ድምፃችንን ይሰማሉ፣ አንተ ግን ዉስጣችንን ትሰማለህ።
የልባችንን ለቅሶ የምትሰማ፣ የዉስጣችን መሻት የምታውቅ አምላካችን ሆይ! በፆመ አንጀታችን ለመንንህ፣ በደረቅ ጎሮሮኣችን ተማፀንንህ። መሻታችንን ሁሉ ሙላልን፣ ሓጃችንን ሁሉ ፈጽምልን፣ የምንፈልገዉን ሁሉ ስጠን።
ያ ረብ!
ረመዷን
(5)
***
እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።
ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ የመላእክት ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።
እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።
እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።
"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን ያክብር።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ።

ፆመኛን ያስፈጠረ የሱን ያህል እኩል ምንዳ ያገኛል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
(4)ከረመዷን ጋር ተያያዥ የሆኑ ፈታዋ በዛዱል መዓድ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም @እድል መዓድ
ረመዷን
(5)
****
አንድ አባት ስልክ ጠጋኝ ዘንድ ሄዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ።" አሉት።
ጠጋኙም "አረ ይሠራል ችግር የለበትም።" አላቸው።
"ታድያ ልጆቼ ለምን አይደዉሉልኝም?" ።
ብለው ጠየቁት።
ስልካቸው መሥራት አለመሥራቱን የሚያውቁት ልጆቻቸው ቶሎ ቶሎ ሲደዉሉላቸው ነው። ሲቆዩ ጊዜ የተበላሸ መሠላቸው።
እንዲህ እንዳይጠራጠሩ ለወላጆቻችሁ ሳትሰለቹ ደዉሉላቸው።
ረመዷን በልጅ ወላጅ ትዝታ ዉስጥ ትልቅ ቦታ አለው። ቤተሰብ ቢኖረዉም ዛሬም ድረስ እናቱ ደዉላ የምትቀሰቅሰው በድምጿ የሚነቃ ሰው አውቃለሁ።
አላህ ሆይ በልጅነታችን ወላጆቻችን በመልካም ሁኔታ አሳድገዉናል፣ እዝነትህ አይለያቸው።
ጾም ነፍስን ለመቆጣጠርና አቅጣጫ ለማሳየት ግዙፉ መንገድ ነው። ነፍስ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞ ላይ መሰናክል የምትሆነው ክፉ ስትሆን ነው። በባሕሪዋ ደግሞ ደስ የሚላትን ማድረግና ግዴታ ከተደረጉባት ተግባራት መሸሽ ትመርጣለች። ይህን ባሕሪዋን ለማረም ደግሞ ጾም ምርጡ አምልኮ ነው። በዚህ መንገድ መጠቀም የፈለግን እንደሆነ በጾሙ ክፍለ ጊዜ አብዛኛውን በእንቅልፍ ልናሳልፈው አይገባም። ስናፈጥርም የምንወስዳቸውን ምግቦችና መጠጦች ማመጣጠን ይኖርብናል። የምግብ ዓይነታዎችንም ማብዛት ተገቢ አይደለም። አንድ ወይም ሁለት ዓይነት በቂያችን ነው።
አል-ሐሊሚይ እንዲህ ይላሉ፦ ‹‹ሐላል ስለሆነ ብቻ ለአንድ ሰው አብዝቶ መመገቡ ትክክል አይደለም። ምግብ በብዛቱ ሰውነቱን ይከብደዋል፤ ወደ እንቅልፍ ይገፋዋል፤ አምልኮ ይከለክለዋል። ስለዚህ ረሐቡን በሚያስረሳ ሁኔታ ይመገብ። የሚመገብበትን ዓላማም በአምልኮ ለመበርታትና ለመጠናከር ይሁን።›› ሹዐብ አል-ኢማን አልበይሀቂ 5/22

ከምግብና ከመጠጥ ከመጾም በተጨማሪ ከማይጠቅሙ ንግግሮች እንዲሁም ከሳቅም ጭምር መጾም ይገባናል። ‹‹ምላስህን ያዝ!›› መፈክራች ሆኖ ከአላስፈላጊና ካልተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ መራቅ ይገባናል።

ጥቂት የረመዷን ቀናት
ረመዷን
(6)
የማያውቁ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ ንገሯቸው፡፡ ሶላት በአንድ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ የትም በምንም ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን መስገድ ይኖርበታል፡፡ ያለ ሶላት ፆምም ትርጉም የለዉም፡፡

ሶላት - ለመልካም ሥነምግባር
ሶላት - ዓላማ ላለው ትውልድ
ሶላት - መልካም ዜጋ ለማፍራት
ያለ ሶላት ሕይወት የለንም፡፡
ልጆቻችንን ሶላት አትከልክሉ፡፡
አምና፣ ካቻ-አምና የሰሑርና የፊጥር ማዕድ ላይ የነበሩ፣ ዘንድሮ ግን የሌሉ ወዳጆችና የቤተሰብ አባላት ይኖራሉ። የዘንድሮውንም ጀምረው ሳይጨርሱ ወደ ማይቀረው አገር የሄዱ አይጠፉም። እኛ ያገኘነውን ዕድል አላገኙምና ዱዓ እናድርግላቸው፣ ኢስቲጝፋር እንስደድላቸው፣ ሶደቃ እናውጣላቸው... በኸይራት እናስባቸው።
﴿ هُوَ الَّذي خَلَقَكُم مِن تُرابٍ ثُمَّ ﴾ .
# ኢፍጣረ_ሳዒም # ኻሊድ_መሰጂድ # ከሚሴ
አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቹው ለቀጣይ ሁለት ቀን የሚሆን ውሃ አግኝተናል።
በቀን 25 ደርዘን ያሰፈልገናል። የአንድ ደርዘን 0.40 L ዋጋ 80 ብር ነው።
ተሳተፉ ባረከላሁ ፊኩም @Faysul
የአንድ ቀን የውሀ ፊጥር 2ሺ ብር ነው ከዛም በላይና በታች መነየት ይቻላል።
25 ሰወች እያንዳንዳቸው 2ሺ ብር ቢያዋጡ ቀላል ነው ነገሩ ኸይር ስራ ለሚቀናው🤗
*⃣ታላቅ የደዕዋ ዝግጅት በታላቁ በድረል ኩብራ መስጅድ

ተጋባዥ እንግዶች
_______________
👉በሸይኽሙሀመድ ኑር
ርእስ የእውቀት አስገላጊነት
እና
👉 በኡስታዝ አብዱረህማን ዐባስ
ርእስ አላህን መፍራት
እሁድ ሚያዚያ 02/08/14 አ/ል ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ አድራሻ ወለቴ ቴሌ ገባ ብሎ
ለሴቶችም በቂ ቦታ አዘጋጅተናል

አዘጋጅ የበድረል ኩብራ ወጣቶች ጀመዓ
Forwarded from Deleted Account
የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል;- አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው።

﷽ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يصلون عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمنوا صَلُّوا عليه وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ በጁምዓ ቀን በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድን አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።
La tehzen
Photo
ለሀገራችን ትልቁ ነቀርሳ አስመሳይነት ነው !
ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የአዲስ አበባ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ
ሃላፊ ከ5 ቀናት በፊት ረመዷን ሲገባ ረመዷን ከሪም ብለው በፌስቡክ ገጻቸው
የፖሰቱት ነው ። የሙስሊም ጀለብያ እና ኮፍያ ለብሶ ረመዷን ሙባረክ ከማለት
ይልቅ የሙስሊሙ ልጆችን ከትምህርት እንዳይሰናከሉ ከማድረግ መቆጠብ
ትልቅ ጨዋነት፣ሀገር ወዳድነት ነበር ።
ረመዷን ከገባ ጀምሮ በእርሳቸው ትእዛዝ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች
የሚማሩ ሙስሊሞች በፖሊስ እየተሳደዱ፣ሶላት እንዳይሰግዱ እየተከለከሉ ነው

የሚገርም ነገር ልንገራችሁ ምንም አይነት ችግር ያልነበረባቸው ፣ከርእሰ
መምህራኑ ጋር በመወያየት በረፍት ሰዓት ጭምር እየወጡ ይሰገድባቸው የነበሩ
ትምህርት ቤቶች ነበሩ ። ነገር ግን በትላትናው እለት አቶ ዘላለም እነዚህን ርእሰ
መምህራን በመሰብሰብ ውጭ ወጥተው የሚሰግዱትን ጭምር እንዲከልክሉ
ትእዛዝ አስተላልፈዋል። አንዳንድ ትምህርት ቤቶችም ምን እናድርግ ከላይ
የመጣ ትእዛዝ ነው በማለት ምላሽ ሰጥተዋል ።
ከትላንት ወዲያ ከለሚ ኮራ ትምህርት ቤት ወላጆች ተወክለው ያነጋገሯቸውን
ሰዎች ትላንት ቃለመጠይቅ አድርጌ ነበር ። አቶ ዘላለም በፍጹም ሊያዳምጡ
እንኳን ፍቃደኛ እንዳልሆኑ፣እዚያው ገና ንግግር ስንጀምር 'ብሎክ 'ያደርጉን ነበር
ሲል በሰፊው አብራርቶልኛል። አሳፋሪው ነገር በለሚ ኮራ ኮሚኒኬሽን ፔጅ
ስምምነት ላይ ተደረሰ ብለው ነው የፖሰቱት ።
ለማንኛውም ወገኖቼ ! ውድ ተማሪዎች ! ምሁራኖች ሁላችን ሁላችን
በጋራ በአንድነት በመቆም መብታችንን እናስከብራለን
መብታችን ከማንም በችሮታ የሚሰጠን ሳይሆን ራሳችንን የምናስከብረው ነው ።
በውስጣቸው ያለው የኢስላም ጥላቻ የሚፈነቅላቸው፣የርስበርስ ያላቸውን
ፖለቲካ ሽኩቻ እኛ ላይ ለማራገፍ ለሚፈልግ አራሙቻ ወደ ኋላ የምንልበት
አንዳችም ምክኒያት የለም ። ስለ ሴኩላሪዝም እያነሳን ለእናንተ አናስረዳም ።
እንዲያውም ጥያቄ መጠየቅ ያለብን እኛ ሁነን እያለ ስላነቃችሁን
እናመሰግናለን !
(አብዱረሂም አህመድ )
ረመዷን ሱሑር
(7)
***
ከትናንት ወድያ ኮልፌ ላይ ሦስት ሰዎችን ቀበርን። በረመዷን ወር፣ በእዝነቱ ቀናት ዉስጥ ነዉና የሞቱት ኸይረኞች ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን።
ይገርመኛል ኮልፌ ገበያዋ ሁሌም ክፍት ነው። በረመዷንም ከረመዷን ዉጭም። ክረምትም በጋም። ጠዋትም ማታም። ከሟቾቹ መካከል ሁለት የረመዷን ቀናትን የፆመ አለ። በሦስተኛው ቀን ላይ ድንገት ተያዘና በቃህ ተባለ። አጀል ማለት እንዲህ ነው እንግዲህ።
ረመዷንን 'ጌታዬ ሆይ አድርሰኝ' ብሎ አምላኩን የተማፀነ ሁሉ አልደረሰበትም። ወሩን የደረሰበት ሁሉ አልፆመዉም።
አሁንም ከኛ መካከል ሱሑርን በልተው የማያፈጥሩ ብዙ ናቸው። ወሩን የማይጨርሱም በርካቶች ናቸው። ማን ማን እንደሆነ የሚያውቀው ግን አላህ (ሱ.ወ.) ብቻ ነው። ለዚህ ነው ትልቅ ዕድል ነዉና ረመዷንን በትክክል እንጠቀምበት የሚባለው።

ወሩን ሙሉ በሐቅ ከሚፆሙት፣ ተቀባይነትንም ከሚያገኙት ያድርገን።
የጁመአ ተወዳጅ ሱናዎች
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❪ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ❫

" اَللَّهُمَّ صَلِّ علىٰ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ وَعَلىٰ آلِهِ وَصَحْبِهِ وَسَلِّمْ "
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد

الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد ٍﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ
اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ