La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ሰደቃ

አንተ ውድ ወንድሜ የሆንከው ሙዕሚን
አድምጠኝ ልምከርህ ጥቂት ምክርን

በዚ በረመዳን በከበረው ወራት
መንገድህን ጀምር ገስግስ ወደ ጀነት

በአንድ የቴምር ፍሬ ከሳት ነፃ መውጣት
አንድ ብር ሰቶ ሺ ትርፍ ማግኘት

ትፈልግ ከሆነ ከረሱሉ ጋራ ለመሆን ጎረቤት
እንዲሁም በጀነት ውብ ቤት ለመገንባት

ፈፅሞ አትዘንጋ ምስኪኖችን መርዳት
አላህ ከረዘቀህ ሰደቃ በመስጠት

ይህን ማድረግ ካልቻልክ በሀሳብ በጉልበት
ቶሎ ተሽቀዳደም ጊዜህን ስራበት

ገንዘብህም አልቆ ሳይመጣ ድህነት
እርጅናም ሳይመጣ ሳይደካክም ጉልበት

መሽቀዳደም ያሻል የጀሊሉን እዝነት
እድሜህን ተጠቀም እያለህ በሀያት

ስምህ ተቀይሮ ሳትባል ጀናዛ
በዱኒያ ንብረትህ የዓኼራ ቤት ግዛ

ታዲያ ይሄ ሁሉ ይሁን በኢህላስ
ቸር ለመባል ሳይሆን በሰው
ለመሞገስ

ከሰው አትጠብቅ ለማግኘት ውለታ
እንዲሁም ክብርን ጭብጨባ ሆሆታ

ነፍስያህን ገተህ ጥርት አርገህ ስራ
ከሳሪ እንዳትሆን ነገ በአኼራ

የሰራኸው ስራ እንዳይቀር በከንቱ
ነገ የቂያማ ቀን ስትቆም እፊቱ

#ibnu muh...
La tehzen
🌹ሑረል = ዓይን🌹 ~ ክፍል አምስት(5) የሰውነቷ ቅርጿ ፤ የቆዳ ቀለሟ ፤ ተክለ ሰውነቷ ያፈዛል ፤ የማይጠወልገውና የማይረግፍ ውበትን አላህ አጎንጽፏታል። በድንኳኖች ውስጥ የተጨጎሉ የዓይኖቻቸው ጥቁረትና ንጣት ደማቅ የኾኑ ናቸው፡፡ አል ረሕማን - 72 የሑረል ዓይኗና የዱኒያዋ እንስት ተረብ ========================= ሑረል ዓይን እናንተ የዲኒያ ሴቶች ሆይ! ቁንጅናችን የሚያፈዝ…
🌹ሑረል = ዓይን🌹

~ ክፍል ስድስት(6)

~ ለአላህ ብሎ የተወ ምርጡን ይተካዋል

መሐመድ ኢብኑ ዓብዱልባቂ ስለአጋጣሚው አንድ ክስተት በራሱ አንደበት እንዲህ ሲል ይተርክልናል።

‹የአላህ ጥበቃ በማይለያት መካ አቅራቢያ እኖር ነበር። ከእለታት በአንደኛው ቀን ከባድ የሆነ ረሃብ አጋጠመኝ። ርሃቤን የሚመክትልኝ ፣ ጉሮሮዮን የሚደፍንልኝ አንድ ጉርሻ ግን አላየሁም። ቤት ተቀምጬ አንጀቴ ከሚላወስ ወደ ውጪ ወጥቼ ብዟዟር አንዳች ነገር አገኝ ይሆናል ብዮ በማሰብ ከቤት ወጣሁ። በመንገድ ላይ ሳለሁ በሀር ጨርቅ የተጠቀለለ በውስጡም ጠጣር ነገርን ያቀፈ ከረጢት በማግኘቴ ደስ አለኝ። ወደ ኪሴ ከትቼ ምን ሊሆን ይችላል ብዮ እያሰላሰልኩ ከቤቴ ደጃፍ ደርስኩ። በሩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ገባሁ ቋጠሮውን ፈታሁ በውስጡ አይቼ የማላውቀው በጣም ውድና እንቁ ነበር።

ርሃብ ስላሽመደምደኝ እና ስላዳከመኝ ከፊሉን ሸጬ በማገኛው ገንዘብ ምግብ ለመግዛት አስቤ ከቤት ወጣሁ። መንገዴን ይዤ ሽቅብ በመጎዝ ላይ ሳለሁ አንድ እድሜው የገፋ አዛውንት ድምፅ ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ሰማሁት።

የሀር ጨርቅ ቆጠሮ ላገኝና ለምለሰልኝ አምስት መቶ ዲናር ለውለታው እከፍላለሁ በእጁም ከጨርቅ የተሰራ የገንዘብ መያዣ ከረጢት ይዞል ንግግሩን እንደሰማሁ ለነፍሴ እንዲህ አልኮት.


ርቦኛል ግን ብሩን ተቀብዮ እንቁውን ብመልስ ተጠቃሚ ነኝ ግን።ብሩንስ ለምን እቀበለዋለዋለሁ ለምን ለአላህ ብዮ አልመልስለትም በማለት አስብኩኝ ። ይዤው ወደ ቤቱ ሄድኩ የቆጠሮውን ክር አይነት የጨርቁን ቀለም የእንቁውን ልዩ ምልክት ጠይቄው መለስኩለት እሱም አምስት መቶ ዲናር ሊሰጠኝ እጁን ዘረጋ እኔ ግን የሰራሁት ለአላህ ስል ነው ብር አልፈልግም ። ወረታን አልፈልግም አልኩት ቢያስጨንቀኝም አልቀበልም ብዮ በአቆሜ ፀናሁ።


ከአመታት ቡሃላ ከመካ ወጥቼ በመርከብ ጉዞ ማድረግ ጀመርኩ። መሃል ምንገድ ላይ መርከቦ ተሰበረችና ሰዎች ሰጠሙ ብዙ ገንዘብ ወደመ። እኔም በአንድ መርከብ ስባሪ እንጨት ላይ ተንጠልጥዮ ወዴት እንደሚወስኝ ሳላውቅ ጉዞን ተያያዝኩ። በባህር ውስጥም ለትንሽ ግዜ ያህል ከቆየሁ ቡሃላ ንፋስ እያወዛወዘ ወደ አንድ መንደር ወስዶ ጣለኝ። በአንድ መስጅድ ውስጥ ገብቼ ቁርአንን በመቅራት ላይ ሳለሁ አንድ ግርማ ሞገስ ያለው ወጣት ጠጋ ብሎ ቁርአንን እንዳስቀራው ጠየቀኝ። አስተምሬው እንደጨርስኩኝ የተለያየ ይዘት ያላቸውን ፁሁፎች ከመደርደሪያ ላይ አንስቼ ማንበብ ጀመርኩ።

ወጣቱ መፅፕፍ እንደምችል ጠይቆኝ ፁሁፍ መለማመድ ጀመርኩ ብዙ አባቶች ልጆቻቸውን።እንዳስተምርላቸው ወደኔ።መምጣት ጀመሩ ጠቀም ያለም ስጦታም ይመጣልኝ ይዞል. ከወራት ቡሃላ ከማስተምራቸው ሰዎች አንዱ ጠጋ በማለት ሲል ሃሳብ አቀረበልኝ። እኛ ዘንድ የቲም ቆንጅዮ ልጃገረድ አለች። ከዱኒያ ጥቅማ ጥቅም በውርስ የያዘቺው ከበቂ በላይ ገንዘብ አላት ልናጋባህ ወስነናል ተቀበለን እኔም እሽታዮን ገለፅኩላቸው የጋብቻ ቀናችን ተቃርቦ አስተካክለውና ሞሽረው ከጨረሱ ቡሃላ ይዘዋት መጡ።

በጣም ተይዛና ተውባ ነበር። ከሶ ውበት ይልቅ አንገቶ ላይ የተንጠለጠለው እንቁ ትኩረቱን ሳበው። ሰዎቹም ታዝበውኝ ኖሮ ወደኔ ተጠግተው እይታህ ሙሉ በሙለ ከእሶ ይልቅ በአንገቶ ላይ ባጠለቀቺው ውድ ጌጥ ላይ ነው። ቀልቦ ተጠንቀቅላት እንጂ በማለት ተናገሩኝ። እኔም የዚያን ቀን እንቁ ታሪክ አጫወትኮቸው ደስታቸው እጥፍ ድርብ ሆነ ከመሃከላቸው አንዱም ድምፁን ከፍ አድርጎ የዚህ እንእቁ ባለቤት እንዲህ ይል ነበር። በዱኒያ ላይ ይህን ጌጥ ከመለሰልኝ ሰው የበለጠ እውነተኛ አላህን የሚፈራ ሙስሊም እስካሁን አላጋጠመኝም። ጌታዮ ሆይ አገናኝንና ልድጄን ልዳረው እያለ አላህን በተደጋሙሚ ሲለምን ሰምቼዋለሁ በማለት በደስታና ፈንጥዚያ ጋብቻው እንዲጠናቀቅ አደረገ።

ለአላህ ብሎ አንድን ነገር የተወ የተሻለውን በላጩን አላህ ይተካዋል።

ውዱ ነብዩ መሃመድ ( صلى الله عليه وسلم)

~ ለእኛ ለሴቶችስ

ጀነት ውስጥ ለወንዶች ሁረል ዓይን ሚስቶች እንዳላቸው ሁሉ በዱኒያ ህይወቶ ላይ መልካም የሆነች ሚስት በአኬራ ከሑረል ዓይን በላይ ትሆናለች ጠረኖም ተፈላጊነቶም ከጀነት እንስት የበለጠ ይሆናል።

በዱነያ ያላገባች ሴት ጀነት ውስጥ የምትደርስበትን የዓይን ማረፊያ የሚሆናትን ባል አላህ ይሰጣታል።


አላህ የጀነት ሰዎች ድሎትና ፀጋን አስመልክቶ እንዲህ ይላል።..

በእርሷም ውስጥ ነፍሶች የሚከጅሉት፣ ዓይኖችም የሚደሰቱበት ሁሉ አልለ፡፡ እናንተም በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናችሁ፡
ዙኽሩፍ 71

ውዷ እህቴ! የሑረል ዓይን የቁንጅና ውበት በእጥፍ ለመብለጥና በአርረህማን በአርረህማን ጀነት ውስጥ በሚደረገው የስነ ውበት ውድድር ላይ በአንደኝነት ደረጃ አማላይ ቆንጆ ለመሆን በሒጃብሽ ፣ በኢማንሽና በሀያእሽ ላይ ጠንካራ ባልሽን ታዘዚ ከአጉል ባህሪያት ራቂ።

ሙአዝ ኢብኑ ጀበል (ረ ዐ) ባስተላለፉት ሐዲስ ረሰልብ(ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል...


የዱኒያ ሚስቱ ስታስቸግር በጀነት ውስጥ የተዘጋጀላት ሑረል ዓይን ሚስቱ አላህ (ሱ ወ) ያዋርድሽ አታስቸግሪው አንቺ ጋር። በእንግድነት ነው የመጣው የሚለይሽም ቀን ቅርብ ነው። በማለት ትረገማለች።
[ቡኻሪ ዘግበውታል]

ሑረል ዓይን

በምድር ባህር ላይ አንዴ ብትተ የባህሩ ጨውነት ጠፍቶ ወደ ጥፍጥና በተለወጠ ነበር። ስትጠጋ ውበቷ ከሰባ እጥፍ በላይ ይጨምራል።
.
.
ይቀጥላል...

https://t.me/httpsLatahzen
➲ጌታችን ሆይ ልቦቻችንን!

➺ከሽርክ፣ ከቢድዓ፣
➺ከኩራት፣ ከኒፋቅ፣
➺ከውሸት፣ከእዩልኝ ስሙልኝ፣
➺ከጥርጣሬ፣ከአላማ ቢስነት
➺ከጥላቻ፣ከጭካኔ፣
➺ከደካማነት፣ከቸልተኝነት፣
➺ከዱንያ ፍቅር አጥራልን!

➻አንተ ልቦችን የምትቀያይር ጌታ ልቦቻችንን ባንተ ዲን ላይ ፅናት ስጣቸው!!
La tehzen
የዝሙት አኼራዊ ቅጣቱም የከፋ ነው! ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 2 (ዚና) ዝሙት ነው። የዝሙት አኼራዊ ቅጣት እዚህ ዓለም ላይ ከሚያስከትለው ከባድ ቅጣት የባሰ የከፋ! ነው። ለዚህም ነው አላህ (ተባረከወተዓላ) ከሌሎች ሀራም ነገሮች በተለየ መልኩ “ዝሙትን አትቅረቡት” በማለት ገና በርቀት ያስጠነቀቀው፣ ይህ ከመሆኑም ጋር ግን በአሁን ጊዜ አብዘሃኛው ማለት በሚያስችል መልኩ ወጣቱ ዘንድ እንደ ሀላል ይታያል!…
የዝሙት የቅጣት ደረጃው ይለያያል።

ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 3 (ዚና) ዝሙት ነው።

ዝሙትን በተመለከተ ሁለት ተከታታይ ፅሁፎችን አሳልፌላችሁዋለሁ፣ ይህ 3ኛው ናው፣ እሱም የዝሙት የቅጣት ደረጃው ካሳለፍናቸው አይነቶችም የባሰ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ነው!!
አላህ ይጠብቀንና አንዳንድ ሰዎች ህይወታቸውን በተለያዩ ሀራም ነገሮች አሳልፈው ሲያበቁ ቀሪ የእርጅና እድሜያቸውንም ወደ አላህ (ተባረከወተዓላ) ተውበት አድርገው ሊመለሱ ሲገባ ቀደም ሲል በለመዱት የከፋ ወንጀል ዝሙት ላይ ሲልከሰከሱ ልጆቻቸውና ዘመዶቻቸው እንኳን ሳይቀሩ አይናችሁን ላፈር እስከማለት የደረሱ በርካቶች ናቸው።
Sugermami&Sugerdadi እየተባባሉ ለዝሙት በእርጅና ራሳቸውን አዘጋጅተው ይወጣሉ፣ ይህ ደግሞ ጭራሹኑ ካሳለፍናቸው የዝሙት የቅጣት አይነቶችም ቅጣታቸውን የባሰ የከፋ የሚያደርገው ነው!።
Sugermami- ትልቅ ሴት ሆና ልጇን የሚያክል ወጣት በገንዘቧ ለዝሙት የምትጋብዝ ማለት ሲሆን
Sugerdad- ሽማግሌ ሆኖ ወጣት ሴቶችን የሚያባል/ዝሙተኛ የሚያደርግ ማለት ነው።
ወንድም እህቴ ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ አላህን ካስከፋቹና እንዲጠላችሁ ካደረጋችሁ ሁሉ ነገር እንዲጠላችሁና አይናችሁን ለአፈር እንዲላችሁ ያደርጋል!! አላህ ከወደዳችሁና ወደሱ ተውበት በማድረጋችሁ እንዲሁም መልካም ስራችሁን ከወደደላችሁ እሱም ይወዳችሁዋል! ሰዎችም መላኢካዎችም እንዲወዷችሁ ያደርጋል!!
ሁሉ ቢቀር እንኳን የአላህን ወዳጅነት ማግኘት ማለት ምንኛ መታደል ነው??? አላህ ይወፍቀን!!
ታዲያ የሽማግሌ ዝሙተኛ ነቢዩ ﷺ: አላህ በእለተ ትንሳኤ ወደርሱ አይመለከትም፣ አያነጋግረውም፣ አያጠራውምም ብለዋል:–
ከአቢ ሁረይራ ተይዞ (መ. አላህ ይውደድለትና) የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲ ብለዋል:–
{ሶስት አይነት ሰዎችን አላህ በእለተ ትንሳኤ አያነጋግራቸውም፣ ወደ እነሱም አይመለከትም፣ አያጠራቸውምም ለእነርሱም ከባድ የሆነ ቅጣት አላቸው የሽማግሌ ዝሙተኛ፣ ውሸታም መሪና የድሃ ኩራተኛ፣ (ናቸው)።} ሙስሊም 107 ነሳኢይ 5/86 ላይ ዘግበውታል።

በጎረቤቱ ሰውዬ ሚስት ላይ ዝሙት የሚሰራ።
ይህ ከከባባድ ወንጀሎች ሁሉ ከባድና ከሽርክና ህይወት ከማጥፋት ተርታ የተሰለፈው ካባድ ወንጀል ነው
ከኢብኑ መስዑድ ተይዞ (መ.ስራውን አላህ ይውደድለትና) እንዲህ አለ:–
{የአላህ መልእክተኛ ሆይ! የትኛው ወንጀል ነው? የላቀው አላህ ዘንድ ከከባባዶች ሁሉ በላይ እጅግ በጣም ከባዱ አልኳቸው፣
“አላህ እርሱ የፈጠረህ ሆኖ ሳለ ለርሱ ቢጤ ማድረግህ ነው” አሉኝ። ይህማ እጅግ በጣም ከባድ ነው! ከዚህ ቀጥሎስ? አልኳቸው፣ “ልጅህን ከአንተ ጋር እንዳይበላብህ ፈርተህ መግደልህ ነው” አሉኝ። ከዚህ ቀጥሎስ? አልኳቸው፣ “በጎረቤትህ ሰውዬ ሚስት ላይ ዝሙት መፈፀምህ ነው” አሉኝ። ይህን እውነት ብሎ በማረጋገጥ አላህ (ተባረከወተዓላ) የሚከተለውን የቁርኣን አንቀፅ አወረድ:
﴿وَالَّذينَ لا يَدعونَ مَعَ اللَّهِ إِلهًا آخَرَ وَلا يَقتُلونَ النَّفسَ الَّتي حَرَّمَ اللَّهُ إِلّا بِالحَقِّ وَلا يَزنونَ وَمَن يَفعَل ذلِكَ يَلقَ أَثامًا★يُضاعَف لَهُ العَذابُ يَومَ القِيامَةِ وَيَخلُد فيهِ مُهانًا★إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صالِحًا﴾ الفرقان ٦٨-٧٠
“እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ህግ የማይገድሉት፣ ዝሙት የማይሰሩትም ናቸው፣ ይህንንም የሚሰራ ሰው ቅጣትን ያገኛል። በትንሳኤ ቀን ቅጣቱ ለርሱ ይደራርባል፣ በርሷ ውስጥ የተዋረደ ሆኖ ይኖራል። ተፀፅቶ (ወደ አላህ) የተመለሰና ያመነ መልካም ስራንም የሰራ ሰው ሲቀር፣” አል ፉርቃን 68–70።} ሶሂህ ነው፣ ኢማሙ አህመድ 380–431 ነሳኢይ በተፍሲር 338
ቡኻሪና ሙስሊም የቁርኣን አንቀፁን ሳይጠቅሱ ዘግበውታል።

ወንድም እህቶቼ ሆይ! አላህ ይዘንላችሁና! እስቲ ልብ በሉ! ቆም ብላችሁም አስተውሉ!!
በአሁን ጊዜ ከቤተሰባችን ውስጥና ከውጭ ብዙ ወጣት እህትና ወንድሞች ኧረ! ሽማግሌዎችም እንደ ቀላልና ተራ ነገር የሚያዩትን የዝሙት ወንጀልን
አላህ ጥራት ይገባውና በርሱ ላይ ከማጋራትና ህይወትን ከማጥፋት እንዴት አድርጎ እንዳያያዘው!!

===በአላህ ፈቃድ!===ይቀጥላል…..

https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen

Share join 👆👆 share join 👆👆👆
La tehzen
የዝሙት የቅጣት ደረጃው ይለያያል። ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 3 (ዚና) ዝሙት ነው። ዝሙትን በተመለከተ ሁለት ተከታታይ ፅሁፎችን አሳልፌላችሁዋለሁ፣ ይህ 3ኛው ናው፣ እሱም የዝሙት የቅጣት ደረጃው ካሳለፍናቸው አይነቶችም የባሰ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ነው!! አላህ ይጠብቀንና አንዳንድ ሰዎች ህይወታቸውን በተለያዩ ሀራም ነገሮች አሳልፈው ሲያበቁ ቀሪ የእርጅና እድሜያቸውንም ወደ አላህ (ተባረከወተዓላ)…
ዓይንን (አጅነቢይ) ያልተፈቀደችለትን ሴት ከማየት መጠበቁ ከዝሙት ለመጠበቅ ፍቱን መድኃኒት ነው።
ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 4 (ዚና) ዝሙት ነው።

ኢስላም ምንኛ ያማርና ቀጥ ያለ ዲን ነው!! ከጎጂ ነገሮች ከመከሰታቸው በፊት መጠበቅን ያደረገለት የሆነው ዲን።
የላቀው! አምላካችን አላህ (ተባረከወተዓላ) የሰው ልጆችን ከብልግና እንዲጠበቁ ወደ ብልግና ከመድረሳቸው በፊት በርቀቱ አስጠንቅቋል! ወደዛ ነገር መዳረሻዎችን ሁሉ ዘጋግቷል። የሰው ልጅ ከተቃራኒ ፆታው ጋር ሲተያይ ነው ለዝሙት የሚከጃጀለው፣ በመሆኑም የዚህን መንገድ ወንዱንም ሴቱንም አይናችሁን ስበሩ በማለት ዘግቷል። አላህ (ተባረከወተዓላ) በዓይንን (ሀራም) ያልተፈቀደን ነገር ማየትን ብሊትን ከመጠበቅ ጋርም አያይዞታል፣ ለምን? አንድ ሰው ዓይኑን ካልጠበቀ ብሊቱን ሊጠብቅ እንደማይችል ግልፅነውና። አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:–
﴿قُل لِلمُؤمِنينَ يَغُضّوا مِن أَبصارِهِم وَيَحفَظوا فُروجَهُم ذلِكَ أَزكى لَهُم إِنَّ اللَّهَ خَبيرٌ بِما يَصنَعونَ﴾ النور ٣٠
“ለምእመናን ንገራቸው:– ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልከሉ፣ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፣ ይህ ለነሱ ልባቸውን የተሻለ አጥሪ ነው፣ አላህ በሚሰሩት ሁሉ ውስጥ አዋቂ ነው።” ኑር 30
ኢብን ከሢር ይህን አንቀፅ ሲተነትኑ “ይህ ለነሱ ልባቸውን የተሻለ አጥሪ ነው” የሚለው ቦታ ላይ፣ (ዓይንን ሀራም ከማየት መጠበቅ ለልባቸውም ለዲናቸውም አጥሪ ነው «ዓይኑን ሀራም ከማየት የጠበቀ ሰው አላህ ዓይኑ ላይ ብርሃንን ያስወርሰዋል» እንደተባለው ) ብለዋል።
ይህ ከአላህ (ተባረከወተዓላ) ዘንድ ለባሮች ሀላል ካደረገላቸው ውጪ ክልክል ያደረገባቸውን ነገር እንዳይመለከቱና ክልክል ካደረገባቸው ነገርም ዓይናቸውን እንዲሰብሩ የተላለፈ ትእዛዝ ነው። ዓይን በድንገት አላህ ከማየት ክልክል ካደረገባት ነገር ብትጋጠም እንኳን በፍጥነት ዞር ልትል ይገባል!! ይህን አስመልክቶም ታላቁ ሷሃቢይ ጀሪር ኢብን ዐብደላህ አልበጀሊ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩን ﷺ በድንገት ሀራም የተደረገን ነገር ስለማየት ጠየኳቸው አለ:– (ዓይኔን ዘወር እንዳደርግ አዘዙኝ።) ኢማሙ አህመድ በሙስነዳቸው 4/361 ሙስሊም ኪታቡል አደብ 3/1699–1700 ሌሎችም ዘግበውታል።
በሌላ ዘገባ (ዓይንህን ወደ መሬት አድርገው።) ብለውታል፣ ዛሬ ላይ በተለይ ዓይንን ወደ መሬት ማድረጉ ወደሌላ አቅጣጫ ዘወር ከማድረጉ የተሻለ ነው! ዓይንህን ወደሌላ ቦታ ዘወር ስታደርግ መጀመሪያ ከሸሸህበት የባሰ ነገር ሊገጥምህም ይችላልና! (ዓይኔን ዘወር እንዳደርግ አዘዙኝ።) ማለቱ፣ ወደ መሬትም ሆነ ወደሌላ አመላካች ነው፣ የተሻለው ግን ወደ መሬት ማድረጉ ነው።
በአሁን ጊዜ ግን አላህ ያዘነለት እንጂ በዲኑ ከሌላው የተሻለ ነው የሚባለው ወንድ እንኳን ሳይቀር በዚህ በሽታ ተጠቅቷል: ይህ በሽታ ከላጤነት ጊዜ ጀምሮዋቸው ሲያገቡ እንኳን የማይተዋቸው ሰዎች ቀላል የሚባሉ አይደሉም፣ በዚህ በሽታ የተጠቃ ሰው በተለይ ላጤ ከሆነ አላህ ይጠብቀንና ጊዜው ቢረዝምም በዋናው ዝሙት መውደቁ አይቀሪ ጉዳይ ይሆናል፣ ባለ ትዳርም ከሆነ ከሚስቱ ጋር ያለው ግንኙነት እየሻከረ ይሄዳል፣ ከሌላ ሴትም መልከስከስ ይጀምራል፣ ከባድ የሆነው ወንጀል ውስጥም ይወድቃል!!
ታዲያ በየትኛውም ቦታ ላይ ዓይናችንን እንጠብቃት! ከሀራም ነገር እናርቃት! በተለይ በዚህ ጊዜ የድብቅን ወንጀል ተጠንቀቅ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለያዩ አጅነቢይ ሴቶች ፎቶ ላይ የምታፈጥ ከሆነ አደጋው የከፋ! ነው።
ወንድሜ ሆይ! መንገድ ዳር ላይ ቁጭ ብለህ ለብልግና ራሳቸውን አዘጋጅተው የሚወጡ ሴቶች ላይ ዓይንህን አታማትር፣ አንተ ልብስህን አሳጥር ተብለህ ከታዘዝከው በላይ ቀሚሳቸውን አሳጥረው ለዝሙት የሚጣሩ ሴቶችን ቁጭ ብለህ አትላከፍ ይዘውህ ገደል ይገባሉ፣ መንገዱም እጅግ በጣም የከፋ ነውና ከገባህበት የመመለስህ ጉዳይ አደጋ ላይ የሆነበት አዘቅጥ ውስጥ ገብተህ እንዳትቀር።
ገጠመኝ ከሰዎች ጋር መንገድ ዳር ላይ ለጉዳይህ የምትቀመጠው ወንድሜ ሆይ! መንገዱ በአንተ ላይ ሀቅ አለውና ሀቁን ስጠው! በየ መንገድ ዳር ቁጭ ብለው ከሚባልጉና ጨዋ ሴቶችን ከሚያባልጉ ወንዶች ተርታ እንዳትሰለፍ ተጠንቀቅ!።
ነቢዩ ﷺ ለመንገድ ያለውን ሀቅ ነግረውሃልና እሱን አጥብቀህ ያዝ! በሚገባ ተግብርበት።
ከአቢ ሰዒድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተይዞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል አለ:–
{“መንገዶች (ዳር) ላይ መቀመጥን ተጠንቀቁ!፣” ሷሀባዎች የአላህ መልእክተኛ ሆይ መቀመጣችንማ የማይቀር ነገር ነው (ምክንያቱ) የተለያዩ ጉዳዮቻችንን እናወራበታለን፣ አሉ። የአላህ መልእክተኛﷺ እንዲህ አሉ “እንቢ ካላችሁ የመንገዱን ሀቁን ስጡት” ሷሃባዎች:– የአላህ መልእክተኛ ሆይ የመንገዱ ሀቅ ምንድነው? አሉዋቸው፣ “ዓይንን መስበር፣ ሰዎችን የሚያስቸግርን ነገር ማስወገድ፣ ሠላምታን መመለስ፣ በመልካም ማዘዝና ከተወገዘ ነገር መከልከል” ነው አሉ።) ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
===በአላህ ፈቃድ!===ይቀጥላል…
NurAhemd

https://t.me/httpsLatahzen

Share and join 👆👆👆
ሰው ሳቅ በሳቅ ሆኖ ዋለ ሲፈነድቅ

ለረጅሙ ጉዞ ትንሽም ሣይሰንቅ
እንዴት ዋልክ ሲሉት ደህና ነኝም አለ ቀብር የሚባል ሀገር ከፊቱ እያለ

እንደምን ነህ ሲሉት ሰላም ነኝም አለ

ሲራጥ ሳይታለፍ የምን ሰላም አለ

Nur
https://t.me/httpsLatahzen
አይቀርም


ቀኑ ቢጨላልም ሰማዩ ቢጠቁር

የሄድንበት መንገድ ቢያስኬድ ብዙ ዙር

ፀሀይዋ ጠልቃለች ተስፋ የለንም በቃ

አንልም! በጭራሽ በዚህም አናበቃ

ድንግዝግዝ ቢል ሌቱ አለችን ጨረቃ

ታግሰን ከሄድን መንገዳችንን ይዘን

ፈተና እንቅፋቱን ሁሉን በሆድ ችለን

የጨለመው ለሊት ይሆናል ብሩህ ቀን


By Nurahemd
https://t.me/httpsLatahzen
ማረኝ!?

በሀራም አድሬ፤ በሀራም ዘውትሬ
ያዘዝከኝን ሁላ፤ ጥሼ እስከዛሬ
ለመንጻት አቅቶኝ
ለመመለስ ዳግቶኝ
ለመውጣት አድጦኝ
ለመድረስ እርቆኝ
ተውባን አዘግይቼ፤ እስከዛሬ ኖሬ
አለመገዛቴ፤ አስለቀሰኝ ዛሬ
ለእስካሁኑ እድሜ
ላጠፋሁት ጥፋት፤ ወንጀል ማስቀደሜ
ጊዜ በማጥፋቴ፤ በዝቅጠት መክረሜ
ጸጸቱ ተሰማኝ፤ አንጻኝ ከህመሜ!?


Nurahemd
https://t.me/httpsLatahzen
▒ሱረት አል-ኢኽላስ የወረደበት ምክኒያት▒
----------------------------
ኢማም አል-በይሀቂይ - ኢብኑ አባስ ብለዋል በማለት ተናግረዋል «አይሁዶች ረሱል [ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] ዘንድ መጥተው 'አንተ ሙሐመድ ሆይ! አንተ የምታመልከውን ጌታ ግለፅልን' በማለት ሲጠይቁ፤ በዚህ ግዜ 'ሱረቱል ኢኽለስ' ለነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወረደላቸው፦
ﻗﻞ ﻫﻮ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﺪ * ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺼﻤﺪ * ﻟﻢ ﻳﻠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﻮﻟﺪ * ﻭﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﻟﻪ ﻛﻔﻮﺍ ﺃﺣﺪ *
ከዛም ረሱል [ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] «ይህ ነው የጌታዬ በህሪ» ብለው መለሱላቸው። ይህም የአይሁዶች ጥያቄ ለእውቀትና ሐቅን ለማወቅ አልነበረም። የዚህ ምዕራፍ ትርጉሙም፦
1- ﻗﻞ ﻫﻮ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﺪ
«ክፍፍልና ብዛትን የማይቀበል፤ በዛቱ (በእውኑ)፣ በበህሪውም ሆነ በድርጊቱ ምንም አጋር የሌለው። ማለትም ማንም የአሏህን በህሪ የሚመስል ያለው የለም» ማለት ነው።
2- اﻟﻠﻪ ﺍﻟﺼﻤﺪ
«ሁሉም ነገራት በእርሱ ፈለጊ ሲሆኑ፤ እርሱ ግን ከማንም ከጃይና ፈላጊ ያልሆነ ጌታ (አሏህ) ነው»።
3- ﻟﻢ ﻳﻠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﻮﻟﺪ
«አይወልድም (ከሱ ሚወጣ ነገር የለም)፤ አይወለድም (ከሌላ የወጣም አይደለም)»።
4- ﻭﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﻟﻪ ﻛﻔﻮﺍ ﺃﺣﺪ
«አርሱን በምንም አይነት የሚመስል የለም፤ አምሳያም ሆነ ቢጤ የለውም»
.
ሱረቱል ኢኽላስ ተውሒድን በአጭሩ አጠቃላ የያዘች አንቀፅ ናት። አሏህ ትርጉሟን በተገቢው ካወቁት ያድርገ።

https://t.me/httpsLatahzen

✿✿✿༺ཌ༈༈ད༻✿✿
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑨

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
~ሉቅማን~~


ዘመን ያልሸፈነው፣አባታዊ ምክሩ፤
ከቃል የዘለገ፣ወይራ ንግግሩ፤
ይነገራል ዛሬ፣ይታወሳል ትላንት፤
ይበሰራል ነገ፣ምሽት ሳይል ንጋት፤
የስነ-ቃል ጥበብ፣ ክሂል ተለግሶ፤
በሰላው አንደበት፣እውነትን አንግሶ፤
ከሰማይ የጎነ፣ አስደማሚ ድምፀት፤
ከደም የሰረፀ ፣የሰመረ ካንጀት፤
ልጄ ሆይ……የሚለው የለሆሳስ ጥሪ፤
ድንበር ያልከለለው፣ አድማስ ተሸጋሪ ፤
ይሰማል…እንዲህ ሲል ይሰማል!
ልጄ ሆይ……… ባ’ላህ አታጋራ፤
ሰማእት መላዕክት ነቢያት ላትጠራ፤
አምልኮ ፀሎትህ ፍሬ እንዲያፈራ፤
ልጄ ሆይ………ይቅር አትኩራራ፤
ጉንጭህን ከማዞር መንበጥረር በጉራ፤
እንደ ብራቅ ላትጮህ፣ ጌታህን ልትፈራ፤
እጅህ ለምፅዋት ፣ ግንባርህ ለስግደት፤
ከመጥፎ ከልክለህ ፣ሀቁን ልታዝበት፤
ጥበበኛው ሉቅማን፣ የእውነት ባለሟል፤
ተግሳፅ ቁምነገሩ ፣መንፈስን ይሞላል፤



ከ ሱረቱ ሉቅማን የተወሰደ
ክብር ለጥበበኛው ሉቅማን!

ttps://t.me/httpsLatahzen
꧁ግጥም꧂


💫ለሞትና ከሞት በኋላ ላለው ሀገር...እንዘጋጅ💫

አልሀምዱሊላሂ ምስጋና ይድረሰው

እኛን ለመፈተን ሞትን የፈጠረው

በሀቅ የሚመለክ የለም አንድም ነገር

ከአለማት ፈጣር ከአረህማን በስተቀር

ሰላት ሰላም ይውረድ የአላህ እዝነት
በሙሀመድ ላይ ለአለም በተላኩት

ከዚያም በመቀጠል ርዕሴን ሚሆነው
ስለ ደስታ ቆራጭ በሞት ዙርያ ነው


በዚች አዱንያ አይቀርም ማንም ሰው
የ ሞት መላኢኩ ስንቱን ከሰከሰው


ዱንያ አደለችም የመኖርያ ሀገር
ሁሉም ይገባታል ያችን ጠባብ ቀብር


ሞት ይበጣጥሳል ያዱንያን ደስታ
ጊዜህ ከደረሰህ አትቆይም ላፍታ

ያዱንያን ሀያት ለቀህ ትኖግዳለህ
ያጠራቀምከውን ለወራሾች ትተህ


አታለለህ እንዴ የ አዱንያ ኑሮ
በንብረት በልጆች መኖር ተፎካክሮ
መሰለህ ማይመጣ የጌታህ ቀጠሮ
ከላ ይወስድሃል ጨምድዶ ሰባብሮ
ስንት ሰዎች ሄዱ ከ አምና-ዘንድሮ


ከሞት ሊያስጥልህ ህዝቡ ቢሰበሰብ
መመለስ አይችልም ቢጮህ ቢቅለበለብ
ብትገባም አትድንም በጠንካራ ግንብ

በጣም ሀይለኛ ነው ለሞት አለው ስቃይ
ማንም ሚያድንህ አትታገኝ ገላጋይ

ኢስቲቃማ ካለህ ስትኖር በምድር
መልዓክ ይመጣሉ አንተን ለማበሰር

ለሞት አንዘጋጅ መልካም በመስራት
ነጃ እንድንወጣ ስንቆም በአላህ ፊት
ጀነት አንድንገባ በአረህማን ረህመት

አላህን ማምለክ ነው ከሽርክ ርቀህ
ቀጠሮህ ሳይደርስ ሞት
ሳይመጣብህ


ስትገባ በ አፈር ነጃ የምትወጣው
በአዱንያ ስትኖር በያዝከው ስራ ነው


ሁሉም ይመለሳል ጥሎህ በ አፈር
ዘመድ ወዳጅህም ወላጅህ ሳይቀር
መልካም ስራህ ብቻ ይሆናል ካንተ ጋር


በ አዱንያ ስትኖር ለ አኼራህ አስብ
መልካሙንም ስራ ከስበው በ ደንብ

ነገ እንድታገኝ የጌታህን(ውዴታ)ሁብ
🌹
🌿
🌻
ሰላትህን ስገድ ዘካህንም አውጣ

ነፍሲያህ ስትያዝ መልሱኝ ላይመጣ
...................... ..........................
https://t.me/httpsLatahzen
ከ ሶላት ቡሀላ ይጀምራል 👇👇

https://t.me/UstazKedirAhmed?voicechat=4504f06f79f5789530
La tehzen
🌹ሑረል = ዓይን🌹 ~ ክፍል ስድስት(6) ~ ለአላህ ብሎ የተወ ምርጡን ይተካዋል መሐመድ ኢብኑ ዓብዱልባቂ ስለአጋጣሚው አንድ ክስተት በራሱ አንደበት እንዲህ ሲል ይተርክልናል። ‹የአላህ ጥበቃ በማይለያት መካ አቅራቢያ እኖር ነበር። ከእለታት በአንደኛው ቀን ከባድ የሆነ ረሃብ አጋጠመኝ። ርሃቤን የሚመክትልኝ ፣ ጉሮሮዮን የሚደፍንልኝ አንድ ጉርሻ ግን አላየሁም። ቤት ተቀምጬ አንጀቴ ከሚላወስ ወደ…
ሑረል ዓይን

ክፍል ሰባት(7)


አንተን በመጠበቅ ላይ ነኝ
================

ኡዝትልዝ ሱለይማን ዘንድ ገባሁ። ብቻውን ይስቃል ከፊቱ ላይም ደስታ ይነበባል። ምን ተገኝ ብዮ ጠየኩት።

እሱም ለይል ተነስቼ እየሰገድኩ ሁለተኛ ረክኣ ስጁድ ላይ ሳለሁ እንቅልፍ ወሰደኝ ፤ በእንቅልፍ ልቤም ከፅሃይ የምታበራ እንስት በእግሯ እየሮጠች .. ወዳጄ ሆይ መላኢኮች ንቁ ሆነው ተሀጁድ የሚሰግዱትን ሰዎች እየመዘገቡ አንተ እኔን አጭተህ ትተኛለህ?

የአይኔ ማረፊያ ሆይ ረጅም አመታትን (ተሞሽሬ) ተጨጉዮ አንተን በመጠበቅ ላይ ነኝ አለች። የሷ ንግግር እስከ አሁን ጆሮዮ ይመላለሳል። ጣፋጭ አንደበቶ ነው ያስባለኝ። በማለት መለሰልኝ።

ሑረል ዓይን ወደ ምድር አጮልቃ ብትመለከት ፍጥረታት ሁሉ አፋቸውን ይዘው ውበቷን እያደነቁ አላህን ያጠሩ ነበር። እሷን ከማየት ውጪ ወደሌላም ፈፅሞ ባልተዘነበሉ ነበር።
.
አቡ ወዳእ የሚባል ታላቁ ታቢአይ የራሱን የትዳር ታሪክ እንዲህ ሲል ያጫውተናል...

በረሱል (ሰ ዐ) መስጅድ ውስጥ እውቀትን ለማግኝት የሸህ ሰዒድ ኢብኑ ሙሰይብን የእውቀት ማዕድ አዘወትር ነበር።..

አዝታዙ ዘንድ የሚማሩ ተማሪዎችም ቁጥር በርካታ ነው። ሆኖም ግን ጎበዝ ተማሪ ስለነበርኩኝ ከሌሎች የተለየ ቦታ ነበረኝ። የተወሰኑ ቀናቶችን ከኡዝታዜ የመማሪያ ስፍራ ራቅሁ። ኡዝታዜ የታመምኩብ ስለመሰለው የመኖሪያ አድራሻዮን ያፈላልግ ጀመር። ስለ እኔ ሁኔታ ቢጠይቅም ተገቢውን መልስ የሚሰጠው ማንንም አላገኘም። ስለደረሰብኝ ችግር እያጣራ ደርሱን ማስተማሩን ቀጠለ።

ጉዳዩ ከፈጀው የቀናት ቆይታ ቡኃላ ወደ መማሪያ ስፍራ ሄድኩ። በደንብ ሰላምታ ተለዋወጥንና በምን ምክንያት ቀናቶችን እንደቀረሁ ለምንስ እንዳልመጣሁ ጠየቀኝ። እኔም ባለቤቴ ሞታብኝ ሀዘን ላይ መቆየቴን አብራቼ ገለጵኩለት። ከነበርንበት ቦታ ገለል አድርጎ ይዞኝ ሄደና እንዲህ ሲል ጠየቀኝ <አዲስ ሚስት ለማግባት አላሰብክምን?>


እኔም .. ኡዝታዜ ለኔ ዓይነቱ የቲም ሆኖ ላደገ ፣ ደሃ ሆኖ ለኖረ ልጂን የሚድር ማን አለ?! ወላሒ አሁን ከሁለት ዲርሃም በላይ በሃብትም ሆነ ንብረት የለኝም መለስኩለት። እኔ ልጄን እድርሃለሁ በማለት ድምጱን ከፍ አድርጎ በጆሮዮ አስተጋባ።..

ታላላቅ ባለስልጣናት ልጁን ለትዳር ጠይቀውት አልሰጥም ማለቱን አውቃለሁና ይህ ቃል ከአፉ ሲወጣ ምላሴ ተኮላተፈ። ተንተባተብኩኝ። የኔን ሁኔታና ምስጢራዊ የችግር ህይወቴን ካወቅክ በኃላ ልጅህን ልትድረኝ? ሲል በተደናገጠ በተቆራረጠ ድምፅ ጠየኩት። እሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ "አዎ ልጄን እድርሃለሁ እኛ መስሊሞች ሃይማኖቱና ስነ ምግባሩ ያማረ ሰው ካገኘን ልጃችንን እንድራለን አንተ ደግሞ በእምነትህም ሆነ በስነ ምግባርህ ወደር የሌለህ መልክልም ሰው ነህ። ከዛም ለምስክርነት ሁለት ሰዎችን ከመስጅድ ጠራና ሁለት ዲርሃሙን መህር አድርጎ ዳረኝ። ልጅቱን ግን አላውቃትም። አላየኃትምም። በቦታው አልነበረችም።


ከድንጋጤና ከደስታዮ ብዛት የተነሳ የምናገረውን እንኳን ማወቅ ተሳነኝ። ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ቀኑን ፆመኛ ስለነበርኩ መስጅድ ገብቼ የመግሪብን ሶላት ሰገድኩ። ወደ ቤቴም አቀናሁ። የማፈጥርበትን ነገር ዘይትና ዳቦ ከፊት ለፊቴ አቀረብኩ። ፋኖሴን አበራሁ። ያቀረብኩትን ምግብ አንዴ ወይም ሁለቴ እንደጎረስኩ የቤቴ በር ተንኳኳ። ማን ነው? በማለት ከበሩ ኃላ የቆመውን ሰው ማንነት ለማጣራት ጠየቅኩሽ።...


ሰዒድ የሚል ድምፅ ሰማሁ። በአላህ እምላለሁ ሰዒድ በሚል መጠሪያ ስም የማውቃቸውን ሰዎች ሁሉ አሰብኩ። ሰዒድ ኢብኑ ሙሰየብ ግን በልቦናዮ ውል አላለም ነበር። ምክንያቱም አርባ አመት ሙሉ ቤቱ ወይም መስጅድ እንጂ ሌላ ቦታ ታይቶ አይታወቅምና። አወለ ሰፍ እንጂ የሰውን ጀርባ እያየ ሰግዶ አያውቅምና ነው። በሩን ከፈትኩ ። ከፊት ለፊቴ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ ቆሞል። በቃ ልጁን ለኔ ዓይነቱ መናጢ ደሃ በመዳሩ ተጸጽቶ ሀሳቡን ሊቀይር ነው የመጣው ስል አሰብኩ።


የመሐመድ አባት ሆይ! ሰው አትልክብኝም ያለህበት ቦታ እመጣ ነበር አልኩት። እሱም "በፍፁም ዛሬማ እኔ ራሴ አንተ ዘንድ ልመጣ ይገባል" በማለት መለሰልኝ ወደ ቤት እንዲገባ ጋበዝኩት። አይ አልገባም ባይሆን የመጣሁት ለጉዳይ ነው ልጄ የአንተ ሚስት ሆናለች እሷ አባቷ ቤት ብቻዋን አንተም በቤትህ ያለ አጫዋች ስለ እሷ እያሰብክ ብቻህን መሆናችሁን ጠልቼ ይዣት መጥቻለሁ አለና" ከጎኑ ቆማ ወደነበረችው መልከመልካም ውብ እንስት ዞሮ.. "ልጄ ሆይ!...


በአላህ ስምና ረድኤት ወደ ባልሽ ቤት ግቢ በማለት ትእዛዝን ሰጣት። ከእፍረቷ የተነሳ ወደ እኔ ስትመጣ ቀሚሷ አደናቅፏት ልትወድቅ ተቃረበች።


አባቷን እንኳ ሳልሰናበት ከፊት ተቀድሜ እየመራኃት ወደ ቤት ገባን። ድህነቴ ስላሳፈረኝ ዳቦና ዘይቱን ደበቅኩ። የፋኖሱን ብርሃንም አደበዘዝኩ። ጣራ ላይ ወጥቼ "ሰዒድ ልጁን ዳረኝ እቤቴ ድረስም ይዞልኝ መጣ" ብዮ ከፍ ባለ ድምጽ ጎረቤቶቼን ተጣራሁ። ከጎረቤቶቼ ሰዎች መካከል አንዲት አሮጊት እንዲህ አለች...

አንተ ሰው! ለመሆኑ የምትናገረው ታውቃለህ? ሰዒድ ልጁን ድሮህ ከቶውንም ቤትህ ድረስ ይዞልህ ሊመጣ?! የእሷ ነገር እኮ እንኳን ላንተ ለደሃው የታላቁ ባለስልጣን ልጅ ወሊድ ኢብን ዓብዱል መሊክ ሽማግሌ ልኮ እምቢ የተባለበት ጉዳይ ነው እኔም አዎ ድሮኛል ከፈለጋችሁ ግቡና ተመልከቱ። ግቡ እቤቴ ናት ያለቺው ተመልከቷት እውነተኛነቴን ታረጋግጣላችሁ በማለት መልስ ሰጠሁ።


ከእሷ ጋር ሳምንትን ከቆየሁ በኃላ ወደ ቀድሞው የእውቀት ገበታ ስፍራ ዒልምን ለመቋደስ ስነሳ "ቁጭ በል አባቴ ጋር ያለው እውቀት ሁሉ እኔ ጋርም አለ" በማለት በጆሮዮ ሹክ አለቺኝ።


የረሱልን (ሰ ዐ ወ) ሐዲስ የሃፈዘች የጌታዋን ቃል አክባሪ የያዘቺውን እውቀት ተግባሪ አላህን ፈሪ የባሏን ሐቅ ጠባቂ መልከ መልከመልካምና እጅግ በጣም ቆንጆ እንስት ሆና አገኝኃት።

ሰብሃን አላህ...

ይቀጥላል...

https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
ሑረል ዓይን ክፍል ሰባት(7) አንተን በመጠበቅ ላይ ነኝ ================ ኡዝትልዝ ሱለይማን ዘንድ ገባሁ። ብቻውን ይስቃል ከፊቱ ላይም ደስታ ይነበባል። ምን ተገኝ ብዮ ጠየኩት። እሱም ለይል ተነስቼ እየሰገድኩ ሁለተኛ ረክኣ ስጁድ ላይ ሳለሁ እንቅልፍ ወሰደኝ ፤ በእንቅልፍ ልቤም ከፅሃይ የምታበራ እንስት በእግሯ እየሮጠች .. ወዳጄ ሆይ መላኢኮች ንቁ ሆነው ተሀጁድ የሚሰግዱትን ሰዎች እየመዘገቡ…
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

🌹ሑረል ዓይን🌹

~ ክፍል ስምንት

የፊቷ ውበት ሲገለፅ ምህዋሯን ለቃ ትሄዳለች ፤ ፈገግታዋ እንደመብረቅ ብልጭታ ያበራል› ከባሏ ጋር ስትተቃቀፍ ፀሀይና ጨረቃ በጋራ ለምድር የሰጡትን ብርሃን ይመስላል።…


ጣፋጭ ህልም… ሁሁሁ

ወፍቅና ያረብ አሚን አትሉም ወይ ያ ጀምዓ…

ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ወደ ሐጅ በማድረግ ላይ ነኝ። በመንገዴ ላይ ያጋጠሙኝን ውጣ ውጣውረዶች አልፌ መካ ገባሁኝ። የአላህን ቤት በመዞር ላይ ሳለሁ አንድ ሰው ቀልቤን ሳበው። ወደ እርሱም ቀረብኩና የሚያደርገውን ዱዓ ለመስማት ጆሮዮን ቀሰርኩኝ።

«ጌታዮ ሆይ! የጓደኞቼን ሀጃ ፈፅመሃልና የኔን ጉዳይ ፈፅምልኝ። እያለ በለቅሶ ጌታውን ይለምናል። ከዚህ ውጭ ሌላ ዱዓን አይጨምርም። ምክንያቱ ምን አደሆነ ለማወቅ ብዮ ጠያቅኩት። እሱም «ከሩሞች ጋር ለመዋጋት ሰባት ጓደኛሞች ሆነን ከሀገራችን ወጣን። ሁላችን በጥላቶቻችን ተማረክን። ስለመሸ አንድ ክፍል ውስጥ አስረውን በሩን ቆልፈው ሄዱ።


በህልሜ የሰባቱ ሰማይ በሮች ተከፍተው በራፍ ላይ በእጃቸው ፎጣን የያዙ እንስቶች ቆመዋል። የጓደኞቼ አንገት ተራ በተራ በሰይፍ ሲቀላ የጀነት እንቡጥ ፅጌረዳ እንስቶች ተራ በተራ እየወረዱ በያዙት ፎጣ አንገታቸው ላይ ያለውን ደም ጠርገው ይመለሳሉ። በሩም ይዘጋል። አንድ የሰማይ በር ብቻ እንደተከፈተ ቀርቷል።


በእድሜ ከሌሎቹ አነስተኛ ስለነበርኩኝ አንድ የሮም ጦር አዛዥ አዝኖ አስለቀቀኝ። ክፋቱ የሰማይ በር ላይ ፎጣ ይዛ የምትጠባበቀኝ እንስትም እንዲህ ስትል ሰማኃት… ምነኛ ምርጥ ነገር ነው ያመለጠህ አይኔ እያየ በሩ ተዘጋ። በህልሜ ያየሁት ክስተት ጠዋት በእውን ተፈፀመ። የምታየው ዱኣም ባመለጠኝ እድል ቁጭት የተነሳ ዘወትር የሚደረገው ነው። በማለት መለሰለኝ።

ይቀጥላ ውድ የኢስላም ልጆች በአላህ መልካም መገጠም ከሆነ…

እናም ውዶቼ የመልካም ስራ ትንሽ የለውምና በመልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ይኖርብናል!!


ውድ ስጦታ ከጀነቱ ሙሽራ…

ለውድ ሚስቱ ለቆንጆዋ ንግስት ሑረል ዓይን ስጦታን ሊያበረክትላት አስቧል። ከምንም በላይ ያማረና እሷን በጣም የሚያስውባትን ውድ ጌጥ ሊሰጣት ፈልጓል።

ውድ ነገሮች ሁሉ ለውዶቻችን የተገቡ ናቸው አይደል እናማ ተከተሎኝ…

ሁለት እርምጃ እንደተራመደ አገልጋዩ ያሰበውን ከአእምሮው አንብቦ የጌጣጌጥ ማስቀመጫ የሆኑ ብዛት ያላቸው ካዝናዎችን እየከፋፈተ የሚፈልገውን እንዲመርጥ በታላቅ ትህትና ጋበዘው።

ከአልማዝ ከሉል የተሰሩት ጌጣጌጦች አፍዝዘውት ለረዥም ግዜ ሲያማርጥ ቆየ። ፈገግ አለና እፁብ ድንቅ የሆነ ከአልማዝ የተሰራ የአንገት ጌጥ በቀይና በአረንጓዴ ክፋይና ሀር የተጌጠ የፀጉር ሪቫን እንዲሁም ውብ የሆኑ ሸዋሊያና ቀለበቶችን መርጦ መያዝ ወደ ሁረል ዓይኗ ሚስቱ ሄደ።

እሷ ጋርም እንደደረሰ በስስት እየተመለከታት በፍፁም የደስታ ስሜት ተውጦ ዓይኗን እንድትጨፍን ካደረገ በኋላ ጌጣጌጦቹን አውጥቶ በአንገቷ ላይ ሐብሉን በጣቷ ላይ ቀለበቱን አጠለቀ።

ዐይኗን ልትገልጽ ስትል በእጁ ካስጨፈናት በኋላ ሸዋሊያውን አደረገላት። ምንም እንኳ ጌጣጌጦቹ በጣም ድንቅ ቢሆኑም የእርሷ ቁንጅና በቃላት ስለማይገለጽ በውበቷ የተዋጡ መሰሉ። በዕርግጥም ተውጠዋል።

አንገቷ ስር ከሳማት ቡሃላ ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ እንዲህ አላት…
«አንቺን የመሰለች ቆንጆ ሚስት ጌታዮ ስለጠኝ ምስጋና ይገባዋል።

«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው»…
አል ዙመር =74

ይቀጥላል በአላህ መልካም ፍቃድ!

~ ሉዕባ ሆይ!…

ዓብደላህ ኢብኑ መስኡድ (ረ ዐ) እንዲህ ብለዋል…

በጀነት ውስጥ ሉዕባ የምትባል የጀነት ሴቶች ሁሉ በቁንጅናዋ የሚገረሙባት እንስት አለች ፤ ትካሻዋን በእጃቸው መታ እያደረጉ እንዲህ ይሏታል «ሉዕባ ሆይ! ምነኛ እድለኛ ነሽ ፈላጊዎችሽ ቢያዩሽ ኖሮ አንቺን ለማግኘት ምነኛ በለፉ ነበር። በዓይኖቿ መሀልም ‹‹እኔ የሚፈልግ ጌታዮን በኢባዳ ያስደስት ›› የሚል ጥቅስ ተፅፏል።

እርቃን የሆኑ ሴቶችን ከመመልክት ዓይንህን የሰበርክ ከጭቃ የተሰራችውን እንስት ችላ ብለህ ከሉል የተሰራችውን ያስበለጥክ ፤ አብሽር የሉእባ ዓይነት ውድ እንስትን ታገኛለህ…።

የሑረል ዐይኗን ጉንጮች
እንደመስታወት ይጠቅማል ፤
ልብሶ አያረጅም
ወጣትነቷ አይለወጥም ፤
ጡባ ሊዘውጂሃ…›››››

ይቀጥላል… የሁረል አይን ፈላጊዎች ሆይ !

https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀 🌹ሑረል ዓይን🌹 ~ ክፍል ስምንት የፊቷ ውበት ሲገለፅ ምህዋሯን ለቃ ትሄዳለች ፤ ፈገግታዋ እንደመብረቅ ብልጭታ ያበራል› ከባሏ ጋር ስትተቃቀፍ ፀሀይና ጨረቃ በጋራ ለምድር የሰጡትን ብርሃን ይመስላል።… ጣፋጭ ህልም… ሁሁሁ ወፍቅና ያረብ አሚን አትሉም ወይ ያ ጀምዓ… ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ወደ ሐጅ በማድረግ ላይ ነኝ። በመንገዴ ላይ ያጋጠሙኝን ውጣ ውጣውረዶች አልፌ መካ ገባሁኝ።…
🌹 ሑረል ዓይን🌹

~ ክፍል (9) ዘጠኝ

~ የማይገለፀው በሰው ልጅ አንደበት
.
ሑረል የኔ ዓለም የዉበት ሁሉ ውብ ውበት ካንቺ ዘንቦ ደርሶ ሚንጠባጠብ ዓይኖችሽ ይልቃል ከሰማይ ጨረቃ አየናት በማታ ካንች ተደብቃ ፀሐይም ከፊትሽ በሚወጣው ፀዳል አየናት ስትሸሽ ራሷን ስትከልል ፀጉርሽም ዞማ ነው ማረፊያው ከዳሌሽ በጥበብ ተሰርቷል ባትሽ ተረከዝሽ ስልክክ እንዳለ ነው ቀጭኑ አፍንጫሽ ራስን ያስታል ያ ሞንዳላ ዳሌሽ ጣቶችሽ አለንጋ ጥፍሮችሽ ስላት የማገለፀው በሰው ልጅ አንደበት....

~ የመእሚን ሽልማቱ...

~ ሳቢት ኢብኑ ነዑማን ይባላል ..
.
በጣም ተርቧል ከረሃቡም የተነሳ መላ አካላቱ ተዳክሞል። በአቅራቢያው ወዳለው አትክልት ስፍራ አመራ። ዓይኑ ወደ አንድ የፍራፍሬ ዛፍ ተመለከተ። የተንጠለጠለቺውን አንድ የፓም ፍሬ እጁን ሰዶ ቀጠፈ። ግማሹን በላና በአቅራቢያው ካለው ወራጅ ውሃ ትንሽ ተጎነጨ። የሰራው ስህተት ለአእምሮው የፀፀት ምልክቱን ሰጠ። ወዮውልሽ! ባለሀቁን ሳታስፈቅጂ ያንቺ ያልሆነን የአትክልት ፍሬ ትመገቢያለሽ እንዴ ? በማለት ነፍሱን ወቀሰ።

የአትክልቱን ባለ ቤት አፈልልልጎ አግኝቶ ለተመገበው ፓም ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ወሰነ።

የአትክልተኛውን ቤት ፍለጋ ተንቀሳቀሰ። ብዙ ካጠያየቀ በኃላ ቤቱን አገኘው። ወደ ሰውዮ2 ቤት በር ጠጋ ብሎ አንኳኳ። ባለ አትክልቱ ገበሬም ከቤቱ ወጣ። በእጁ የያዘውን የተገመጠ ፓም ይዞ ያደረገውን ድርጊት መናገር ጀመረ። በጣም ተርቤ ስለነበር ከወንዙ ዳር ካለው የአትክልትህ ቦታ ይህንን ፓም በላሁ። ከተመገብኩ በኃላ የኔ ሐቅ አለመሆኑን አስታወስኩ ፤ ይቅርታ እንድታደርግልኝና ለሰራሁት ስህተት ተምጣጣኝ ቅጣት እንድትቀጣኝ በማለት መማጸን ጀመረ።


ሰውዮውም የምልህን ካላሟላህ በስተቀር በፍጹም ይቅርታ አላደረገልህም አለው። ምንድን ነው ግዴታ ያደረግክብኝ ብሎ ጠየቀ...

ዓይነ ስውር መስማት የተሳናት እንዲሁም መናገር የማትችል ልጅ አልቺኝ። እሷን እንድታገባ እፈልጋለሁ... ብሎ መለሰለት።....


የገባበትን አስቸጋሪ ጉዳይ በደንብ አጥኖት አስቦት የማይፀፅተው ውሳኔ ለማሳለፍ አሰበ።

በግማሽ ፓም ምክንያት አላህ በጀሃነም እሳት ከሚያቃጥለኝና ዘላለም ከምሰቃይ ይህችን ማግባት የተሻለ ነው፤ በዚህች አጭር የዱኒያ ህይወት መቸቸገሬ ከረጅሙ የአኬራ ህይወት ስቃይ እጅግ የተሻለ ነው ሲል ከራሱ ጋር ተማርከውና ጋብቻውን ተቀብለ።

የሰርጉ ቀን ሲደርስ ጋብቻውን ለመፈፀም ቤት ቀድሞ ተገኝ። እጅግ በጣም ተጨንቋል። ሃሳብ ገብቶታል።

ኒካህ ከተደረገ በኃላ ወደ መሽራዋ ክፍል ገባ። ሚስቱ ከተቀመጥችበት ብድግ ብላ የአላህ ሰላም ባንተ ላይ ይሁን አለቺው። ግር ብሎታል። ተሳስቶ ይሆን? ተመለከታት! የሑረል ዓይን ሁኔታ አስታውሰ ፤ ቁንጅናዋ ተመሳሰለበት።


በዝምታ ተዋጠ።....
ይህች ሴት ትናገራለች ፣ ትሰማለች ፣ !
ታያለች! ምንድን ነገሩ? ግራ ገብቶታል። እሷ ወዳለችበት ቦታ አመራ። አባቷ የተናገረውን ሁሉ አጫወታት። እርሷም....


አባቴ ያለው ሁሉ እውነት ነው አልዋሸም ፤ አትናገርም ያለህ በህይወቴ የሐራምን ንግግርን ተናግሬ ስለማላውቅ ነው፤ መስምልት አትችልም ያለህም ሃሜትም ሆነ አልባሌ ንግግርን ሰምቼ አላውቅም ፤ ዓይነስውር ናት የተባልከውም እውነት ነው ወንድን በሐራም ተመልክቼ አላውቅምና ነው.. በማለት መለሰች። አላህን በመፍራት ምክንያቱ አባቷ ለትዳር መረጠው። በተከበረው የፍቅር ህይወታቸው ውስጥ #ኢማሙ_አቡ_ሀኒፋን ወለዱ....
~ ሰብሃን አላህ.
ተፈፀመ ኑርአህመድ ሀሳብ አስተያየት ምክር ካላቹህ በዚ አድርሱኝ @Nur4843

https://t.me/httpsLatahzen
ረመዳን
ምስጋና ለአላህ አምሳያ ለሌለው
እዝነት በረከቱ ለሁሉም ሚደርሰው
አዛኝ ነው ሩህሩህ ከጉድለት የጠራ
ሰጥቶ ማያልቅበት ድህነት ማይፈራ
ለባሮቹ ክብር ካለው አዘኔታ
ፉርሳ ያመቻቻል በጊዜ በቦታ
ብዙ እድሎችን ለኛ ያመቻቻል
ነቄው ይጠቀማል ሞኙ ይሸወዳል
ከነዚህ ፉርሳዎች ከልዩ እድሎች
አንዱ አካቦናል ንቁ የአላህ ባሮች
መጥቷል ከፊትለፊት እየገሰገሰ
ታላቁ እንግዳ ሊገባ ደረሰ
ቀኑ ቆጠረና የተቀጠረበት
በጊዜው ደረሰ ሳይጎል ሳያልፍበት
ዘንድሮም እንደ አምና ያለምንም ስራ
በባዶ እንዳይሄድ አላህን እንፍራ
ከጀምዐ ጁምዐ በመስጂድ ታድመን
ለይልና ተራዊህ ሰላት ዱአ አድርገን
መስጂዶች ምልተው ሙስሊሞች ከፍ ብለው
የዒድ ሰላታቸው በድምቀት ሰግደው
የዒቲካፍ ጀምዓ ከመስጂድ ሲመለስ
ልባቸው በሀዘን ዐይናቸው ሲያለቅስ ፡፡
ትዝ ይላል ............... .....
እንዴት ነው ዝግጅት ያ ኡመተል ኢስላም
ለሲያም ለቂርኣት ለአዝካር ለቂያም
ስንቶቹ ነበሩ የአምናው የፆሙት
የዘንድሮው ሳይደርስ አኼራ የሄዱት
እኛም ካደረሰን አላህ ከወፈቀን
ከዚህ ትርፋማ ወር እንውጣ ሸምተን
ተከታታይ ፊልሞች ወይንም ድራማ
ሁሉም አስወግደህ ቁርአን ብቻ ስማ
ቀንህን በመፆም ለሊትን በመቆም
ደረጃህ ከፍ ይበል ከጌታህ ፊት ስትቆም
ፆምህ ጥርት ይበል ከሀሜት ከውሸት
አሉባልታ ወሬ እለፈው በርቀት
ቁርኣንህ ዘርግተህ አንብበው ቀን ማታ
ከዱዐ ከአዝካር አትቋረጥ ለአፍታ
ሰላትህ በመስጂድ ከሙስሊሞች ጋራ
ሁሉንም በኢኽላስ በሱና እንስራ
ዝናቡን እንዲወርድ በሽታው እንዲነሳ
እንለምን ጌታችን እጃችን እናንሳ
የተራበ አብልተን ፆመኛ አስፈጥረን
ይህን ከባድ ጊዜ እንለፍ ተባብረን
ያስቀየምነው ካለ አፉታ እንጠይቅ
ያስቀየመን ካለ ሄደን እንታረቅ
ድንበር ያለፍኩበት ካለ ያስቀየምኩት
አውቄም ይሁን ሳላውቅ ቅስሙን የሰበርኩት
ለአላህ ይበልና ሁሉም አፍው ይበለኝ
እኔም ብዬዋለሁ አላህ ይቀበለኝ
ኑርአህመድ ሼር ሼር ሼር ጀዛ ከላህ
((በአላህ ተመካ))

////

በቆላ በደጋ፣ ከወንድ ከሴቱ
ሁሉንም አዩሁ ከልጅ ከወጣቱ
ልሙት ይሰንጥቀኝ በጌታው ስም ምሎ
ላልከዳህ ላልከዳሽ ሲኖር ተዋውሎ
አንድ ቀን ይርቃል ተበደልኩኝ ብሎ
እናማ …
በስጋ በነፍሱ እዬተፈተነ፣አድሮ ከሚጠፋው ከፍጡራን ሁሉ
ሲያምኑት የማይከዳ፣
ሊያምኑት የሚበቃ፣ አንድ አላህ ብቻ ነው የሚገኝ በቃሉ
# ከፍያለሁ !
______
ለምፈልገዉ ሰዉ ልቤ ለከጀለዉ:
መዉደዴ ለኔ'ጅ ለሱ 'ማይታየዉ::
ዉለታ ሆኖበት የመዉደዴ ዋጋ:
ምላሹን ሊሰጠኝ ቢጀምር ፍለጋ::
ብየ ከጀልኩና ለልቤ ነግሬ:
ቀድሜ ከፈልኩኝ ቀብድ ለችግሬ::

___
# በዘሀራ ሰይድ