La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
Forwarded from Teqwa Repi students Group (Ibnu Muhammed™️)
ያገረሻል እኮ አስቸጋሪ ነው የነሱ ነገር
አልላህ ይፋረዳቸው!!!
ብዙ ሰው መሃል ሆነን ብቸኝነት ሊሰማን ይችላል ።
ከአንድ ሰው ጋር ብቻ ሆነን ብርታትና ብሩህ ተስፋ ይሰማናል።
ቁምነገሩ በዙርያህ የሰው መብዛት አይደለም።
አይዞህ አለሁልህ የሚል አንድ ሰው አጠገብህ መኖሩ ነው።

አብሽሩ።

ሰባሐል ኸይር!
አላህ ሱብሓነሁ ወተዐላ ከእውነተኞች ጋር እንድንሆን አዞናል።


{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَكُونُوا مَعَ الصَّادِقِينَ }

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፤ ከእውነተኞቹም ጋር ኹኑ፡፡» [ተውባህ (119)]
"በኔ ኃይል የተመካን ብረት ሳይቀር እንዲታዘዝለትና እንዲለዝብለት አደርጋለሁ።" ይላል አላህ።
ሕይወት የቱን ያህል ከባድ ብትሆንም ወንድም እህቶቻችን መንፈሳቸው እንዲታደስ፣ ሳቃቸው እንዲመለስ፣ ተስፋቸው እንዲለመልም፣ ሞራላቸው እንዲያንሰራራ ዱንያ ላይ እስካለን ድረስ እንታገላለን። ኢንሻአላህ።

ይህ የ La tahzen ድምፅ ነው።
ሰባሐል ኸይር
እዚህ ቤት የገባ ሁሉ አብሽሩ የሚል ድምጽ ይጠብቀዋል።

https://t.me/httpsLatahzen
አላህ ሲወድህ ከሆነ ሰው ጋር ግንኙነት ትጀምርና ብዙም ሳትርቅ የዚያን ሰው ምንነት ይገልጽልሃል።

ለኸይር ነው፣ ከእጃችሁ በወጣ ነገር ላይ ሁሉ እንደ ሕፃን ልጅ አታልቅሱ።

https://t.me/httpsLatahzen
ስለ አደብ ከተባሉት

፨ ልጆቹን በአደብ ያሳደገ በዕድሜው አመሻሽ ላይ ይረካባቸዋል።
፨ ከዕውቀት በፊት አደብን ተማሩ።
፨ ገንዘብ ካለው አደብ ያለው ይበልጣል።
፨ አደብ ከሌለ ማክበርም መከባበርም የለም።
፨ ከስንቅ በላጩ የአላህ ፍራቻ ሲሆን ከዉርስ ደግሞ ምርጡ አደብ ነው።
፨ አደብ የሌለው ሰው አውሬ ነው፤ ያገኘዉን ሁሉ ይናከሳል።

https://t.me/httpsLatahzen
በጥቂት ሰዓታት ልዮነት ነገሮች ይቀያየራሉ።
በቅጽበት ጊዜ ዉስጥ የነበሩት እንዳልነበሩ ይሆናሉ።
ጤነኛው ይታመማል፣
የታመመው ይድናል፣
ጓደኛ ወደጠላት ይቀየራል፣
ጠላት የቅርብ ወዳጅ ይሆናል፣
ሞራላችን ይሞታል፣
ተስፋችን ያንሠራራል፣
ጥርሳችን ፈገግ ይላል፣
ዐይናችን እንባ ያፈሳል፣
እሷ ዱንያ ናት፣
ሐዘንና ደስታ አላት፣
እንባና ሳቅ የሞላት፣
በጥቂት ሰዓታት ልዩነት፣
ሞትና ሕይወት አላት፣
ቅድም ይኸው እየደረስኩ ነው መጣሁ ያለን ልጅ፣
አሁን ሞቷል ሲባል ሰማን።
ጌታዬ ሆይ አትፈትነኝ፣
ባንተ ኖሬ፣
ላንተ ኖሬ፣
የምሞት አድርገኝ።
የህይወት እውነታ

#ሁሉንም ሰው ልታስደስት አትችልም፡፡ ይህ ትልቅ እውነታ ነዉ፡፡

#የሆኑ ሰዎች ቢጠሉህ ምንም ማለት አይደለም፡፡ #የሚወዱህ እንዳሉ ሁሉ የሚጠሉህም እንደዚያው መብዛታቸው አይቀርም፡፡ #ሰዎች ስላንተ ያላቸው አመለካከት ያንተ ጉዳይ አይደለም፡፡

#የመሰላቸውን ያህል ሊገምቱ ፣ ዋጋ ሊያወጡ ሊያወርዱ ፣ ወይም ሊሰቅሉ ይችላሉ፡፡

#ሰዎች አንተ ላይ ባላቸው #አመለካከት ማንነትህን እያመቅክ እና ቀዝቀዝ እያደረክ አትኑር...

#ራስህን ሆነህ በሕይወትህ ትልቅ ዋጋ ለምትሰጣቸው ሰዎች ብቻ የሚጠበቅብህን መስዋእትነት ክፈል ፡፡
የዉስጤን ሁሉ የማወራው ከአላህ በስተቀር አንድም የለም። እንባዬ የሚገባው አንድም ከሱ ዉጭ ማንም የለም።
ጌታዬ ሆይ እርዳኝ፣
አምላኬ ሰትረኝ፣
ረቢ ኮ ሽክፈኝ፣
ፈጣሪዬ ሰብስበኝ።
>>> ውዳሴህ ቢመጣ ከሰባት ሰማይ
ቅንጣት አይጠቅምህም፣
>>>>>>>>>>>> ካልሆንክ ሱንና ላይ

🔉ሸይኽ ዐብደላህ አል-ቡኻሪ
በቀን መቶ ጊዜ ልታጠፋ ትችላለህ፣
ከጥፋቶቹም በላይ አንድ ጊዜ አስታውስህና ደንግጠህ ወደርሱ መመለስህን ግን አላህ ይወደዋል።

ሰባሐል ኸይር!!
የሚስትን በረከትነትና መልካምነት ከሚያሳዩ ጉዳዮች ውስጥ
የመጀመሪያ ልጇ ሴት መሆኗ አንዱ ነው። ምክንያቱም አላህ በቁርአኑ ላይ ለባለትዳሮች ስለሚጣቸው ልጆች የጾታ ስብጥር ሲጠቅስ ሴት ልጅ መስጠትን ከወንድ ልጅ አስቀድሞ ጠቅሷልና። ዋሲላ ቢን አስቀዕ

{ يهب لمن يشاء إناثاً ويهب لمن يشاء الذكور } الشورى

قال واثلة بن الأسقع : من يُمنِ المرأة تبكيرها بأنثى قبل الذكر ؛ لأن الله بدأ بالإناث .
التسهيل لعلوم التنزيل 51-52/4
ኢማኔ ከሚቀንስ
ኪሎዬ ይቀንስ።

አላህ ወደነበርንበት መልካም ሁኔታ መልሰን።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Sellahu alyih weselem
#አሏህ_ሆይ! ከዚህ ኡማ ውስጥ ሐቅ ላይ
እንደሆነ በማሰብ ከሐቅ ያፈነገጠን ሁሉ ከሐቅ
ሰዎች ይሆን ዘንድ ወደ ሐቅ መልሰው።"
#ኢማሙ_አሕመድ!

አሏህ ሐቁን ሁሉ ያግራልን በሐቁ ላይ
ያፅናን አሚን!
▣አቡ ሁረይራ ረድየሏሁ ዐንሁ ▣
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

ክፍል 1⃣
❒❒🌹❒❒

" አቡ ሁረይራ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ (ኡምማ ከ 5374 በላይ ሐዲሶችን ጠብቆ አቆይቷል።" (የታሪክ ሊቃውንት)

ዐን አቢ ሁረይረተ ረድየሏሁ ዐንሁ ቃለ፣ ቃለ ረሱሉሏሂ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም...."

በዚህ ሀረግ አማካኝነት ከኢስላም የመጀመርያ ታሪክ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች አቡ ሁረይራ የሚለውን ስም ሊለምዱት ችለዋል። በንግግሮችና በትምህርቶች፤ በጁምአ ኹጥባወችና በአውደ ጥናቶች፤ በሐዲስ፤ በፊቂህና በታሪክ መጽሐፍት አቡ ሁረይራ የሚለው ስም በዚህ መልኩ ይጠቀሳል።



በእሳቸው አስደናቂ ጥረቶች አማካኝነት በሺወች የሚቆጠሩ ሐዲሶች (የረሱል ሰ.ዐ.ወ ንግግሮች) ለቀጣዩ ትውልድ ተላልፏል። በሐዲስ ዘጋቢወች መዝገብ ውስጥ የእሳቸው ስም ዝርዝር ግንባር ቀደም ነው። ከእሳቸው ቀጥሎ አብደላህ ኢብን ዑመር ረ.ዐ፣ አነስ ኢብን ማሊክ ረ.ዐ፤ ኡሙል ሙእሚን አዒሻ ረ.ዐ፣ ጃቢር ኢብን ዐብደላህና አቡ ሰኢድ አልኹድሪይ ረ.ዐንሁም ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ሐዲሶችን እና ገቢር እንቅስቃሴዎች ለትውልድ አስተላልፈዋል።

አቡ ሁረይራ እስልምናን የተቀበሉት እሳቸው የሚገኙበት ደውስ የተባለው ነገድ መሪ በሆነው ጡፈይል ኢብን ዐምር አማካኝነት ነው። የደውስ ጎሣ አባላት ይኖሩ የነበሩት በደቡብ ዐረቢያ የቀይ ባህር ዳርቻን ተከትሎ ባለው ክልል ውስጥ ነው። ጡፈይል ነብዩን ሰ.ዐ.ወ ከተገናኘና በእሳቸው ተልዕኮ የመጀመርያ አመታት ውስጥ ሙስሊም ከሆነ በኋላ ወደመኖሪያ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ ጥሪውን ከተቀበሉት የመጀመሪያወቹ ሰወች አቡ ሁረይራ አንዱ ነበሩ። በድሮ እምነታቸው ላይ ለረጅም ጊዜ ችክ ብለው እንደቆዩት አብዛኞቹ የደውስ ተወላጆች አልነበሩም።



ጡፈይል በድጋሚ መካ በሄደ ጊዜ አቡ ሁረይራም ረ.ዐ ተከተሉ። እዚያም የተከበሩትን ነብይ ሰ.ዐ.ወ የማግኘት ክብርና ዕድልን ተጎናፀፉ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ "ስምህ ማነው? ሲሉ ጠየቁት እሳቸውም "ዐብዲሸምስ-የፀሀይ ባርያ ብለው መለሱ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከዚህ ይልቅ ዐብዱረህማን ብትባልስ አሉት።
"እሺ የአላህ መልእክተኛ ዐብዱረህማን ይሁንልኝ" በማለት መለሱ።

ይሁንና አብዱረህማን ይበልጥ የሚታወቁት "አቡ ሁረይራ" በሚለው ቅፅል ስም ነው። የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም "የድመት አባት" ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኙት ድመቶችን ይወዱና ከልጅነታቸው ጀምሮ አጫዋች ድመት ያረቡ ስለነበር ነው።



አቡ ሁረይራ ለበርካታ ዓመታት የቆዩት በጢሀማህ ሲሆን ከሂጅራ በኋላ በሰባተኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር ከሌሎች የጎሣቸው አባላት ጋር ሁነው መዲና የገቡት። በዚያ ጊዜ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ወደ ኸይበር ዘመቻ ሂደው ነበር። አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።

ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች።

አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች። እናታቸው ሙስሊም እንድትሆን በፅኑ ይመኙና ዱአ ያደርጉላት የነበረ ቢሆንም ማንገራገሯ አልቀረም።

አንድ ቀን በአንድ አላህ ብቻ እንድታምንና የአላህንም ነብይ እንድትከተል ሲመክሯት ስለነብዩ አንዳንድ ቃላትን ተናገረች። አቡ ሁረይራ እጅግ አዘኑ። ዐይናቸው እንባ እንዳቀረረ ወደ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሄዱ። ረሱልም " አንተ አቡ ሁረይራ ለመሆኑ ምን ያስለቅሳል?" አሉዋቸው። እናቴ እናቴ ኢስላምን እንድትቀበል ከመገፋፋት ወደ ኋላ ብየ አላውቅም። እሷ ግን ሁልጊዜ በንቀት ትቃወመኛለች። ዛሬም እንደገና ብነግራት የማልወዳቸውን ቃላቶች ከእርሷ ሰማሁ። የአቡ ሁረይራ እናት ልብ ኢስላምን ለመቀበል እንዲገራ ሁሉን ማድረግ ለሚችለው አላህ ሱ.ወን ይለምኑልኝ ሲል አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ረሱልን ሰ.ዐ.ወ ተማፀኑ



ረሱል ሰ.ዐ.ወ የአቡ ሁረይራን ጥያቄ በመቀበል ዱአ አደረጉላት። ከዚያ በኋላ ስለሆነው አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ሲናገሩ "ወደ ቤት ስሄድ በሩ ተዘግቶ አገኘሁት። የሚቀዳና የሚፈስ ውሀ ድምፅ ሰማሁ። ወደቤት ለመግባት ስሞክር እናቴ "አንተ አቡ ሁረይራ እዛው ቆይ" አለችኝ። ከዚያ ልብሷን ከለበሰች በኋላ ግባ አለችኝ ገባሁ "ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሀመድ የእሱ አገልጋይና መልእክተኛ መሆኑንም እመሰክራለሁ" በማለት ቃሏን ሰጠች።

ቀደም ብየ በሀዘንና እያለቀስኩ እንደሄድኩት ሁሉ አሁን ደግሞ የደስታ እንባ እያፈሰስኩ ወደ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ተመልሸ ሄድኩና "የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ የምስራች ዜና አለኝ። አላህ ሱ.ወ የርሰወን ዱአ ተቀብሎ የአቡ ሁረይራን እናት ወደ ኢስላም መርቷታል አልኳቸው።

አቡሁረይራ ረ.ዐ ነቢዩን ሰ.ዐ.ወ ሲበዛ ወደዷቸው። ውለታ ለመክፈልም ፈለጉ። የፀኃይን ጨረር ሁሉ የያዘ የሚመስላቸውን የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ፊት ማየትና ንግግራቸውን ማዳመጥ በጭራሽ ሰልችቷቸው አያውቅም ነበር። ላገኙት መልካም ዕድል ዘወትር አላህን ያወድሱትና ለራሳቸው "አቡ ሁረይራን ወደ ኢስላም ለመራው አምላክ ምስጋና ይገባው። ለአቡ ሁረይራ የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ጓደኝነት እንዲያገኝ ለረዳው አምላክ ምስጋና ይድረሰው" ይሉ ነበር።



አቡ ሁረይራ ረ.ዐ መዲና ከደረሱበት ወቅት ጀምሮ እውቀት ለመሰብሰብ ልባቸውን ክፍት አድርገው ነበር። የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታዋቂ ጓደኛ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት ረ.ዐ የሚከተለውን ተናግረዋል፦ አቡ ሁረይራ እኔና ሌላ ጓደኛየ መስጊድ ውስጥ ዱአ እያደረግን ሳለን ረሱል ሰ.ዐ.ወ መጡ
ኢንሻአላህ ይቀጥላል