La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
◾️ሸህ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ አሉ።

➡️ ነጃ መውጣት (መዳን) የምትፈልግ ከሆነ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ አደራ፦
①) የአላህን ኪታብ "ቁርአን" አጥብቀህ ያዝ
②) ቅናቻውን "የመልእክተኛው መንገድ" ተከተል
③) ቢድአ "በዲን ላይ ጭማሬ" ተጠንቀቅ።

📚 شرح المنظومة الحائية (ص٥٦)


https://t.me/httpsLatahzen
ሙሉውን አንብበው ከዚያም መጨረሻ ላይ ያለውን ቁጥር አይተው ይወስኑ።

የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል ⇣ለምላስ ቀለል ብላ ሚዛን ላይ ከባድ ያለች አላህ ዘንድም የተወደደች ንግግር⇣
*ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም*
ቢያንስ ለ30 ሰዎች ላክ ቢሉትም (ቢያነቡትም) አምስ መቶ ቢሊዮን ሃሰናትን በአላህ ፈቃድ ታገኛለህ።
እንደዚሁ አንተ የላክላቸው ሰዎች እያንዳንዳቸው ለ30 ሰው ከላኩ አሁንም 4.680.000.000 ሃሰናት ታገኛለህ። መቼ እንደምትሞት አታቅምና ሰደቀተል ጃሪያ አድርጋት።
ለማሰራጨት ደቂቃ እንኳን አይወስድብህም።

የቅያማ ዕለት ትመሰክርልህ ዘነድ።
▪️ቢሽር ቢን አልሀሪስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አሉ።

ሰዎች ዘንድ እንድትወሳ ብለህ ምንም አትስራ። መጥፎ ስራህን (ሰዎች እንዳያውቁብህ) እንደምትደብቀው ሁሉ መልካም ስራህንም ደብቅ።

📚 [ سير اعلام النبلاء ]


https://t.me/httpsLatahzen
▪️ከሰለፎች ውስጥ አንዱ እንዲህ ብሏል።

♦️ሁለት ነገሮች፦
①) ሞትንና
②) አላህ ፊት መቆምን ማስታወስ
የዱንያን ጥፍጥና ቆርጠውልኛል፦

📚 لطائف المعارف [244]
https://t.me/httpsLatahzen
◾️ሁሉ ነገርህ በአላህ ላይ አድርግ


🌐 ሸኽ መሀመድ ቢን ረምዛን አልሀጅሪ "አላህ ይጠብቀው" እንዲህ ብሏል።

ከፍ ማለትህ በእጁ የሆነ ወይም መውደቅህ በእጁ ያለ መስሎህ ወደ ማንም ፍጡር አትዙር። የማንም ሰው ወቀሳ የሚጥልህ ወይም ውዳሴው ከፍ የሚያደርግህ አይምሰልህ። ባንተና በጌታህ መካከል ያለውን ግኑኝነት አሳምር። በፍቃዱ ከፈጠረው ፍጡር ተንኮል በሙሉ እራሱ ይጠብቅሀል። ምልከታህ ወደ ፍጡር አይሁን። መመካትህ ሙሉ በሙሉ በአላህ ላይ አድርግ። ከፍታህ፣ ሪዝቅህ፣ ደስታህ፣ አፍያህና የዱንያ ሁሉ ነገርህ በአላህ እጅ ብቻ ነው ያለው።


https://t.me/httpsLatahzen
ረሱል (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦

" ሀሳብና ጭንቀት የበዛበት ሰው ( لا حول ولا قوة إلا باللّه) [ ላ ሀዉለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ ] ማለትን ያብዛ " [ ሀዲሱን ሰሂህ
♦️ህይወት ያለው ነገር ፎቶ ከማንሳት እንቆጠብ

ምን ችግር አለው፣ እገሌ ዳኢ ፎቶ ይለቃል፣ እገሌ አሊም ፈቅዷል እያልን እራሳችንን አናታልል።

ተከተሉ የተባልነው መልእክተኛውን እንጂ ሸይኻችንን አይደለም። የአላህ መልእክተኛ የከለከሉትና የረገሙት ስራ ከመራቅ ውጪ አማራጭ የለንም።
~በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን የምታምን ሴት ፣እጌታዋ ፊት እንደምትቆም ጠንቅቃ የምታውቅ ሴት ፎቶና ቪዲዮ እየቀረፀች ሚዲያ ላይ አትለቅም ! አትፖስትም ወንድሞቿን አትፈትንም ። ዲኗ፣ የአሏህ ፍራቻዋ ባይከለክላት እንኳ ሀያዕዋ ሊከለክላት ይገባል።ሆኖም ተሳስተሽ ይህን ድርጊት ያደረግሽ ውዷ እህቴ መቶበት ይኖርብሻል የሰራሽውን መጥፎ ተግባር ማስተካከልም ይጠበቅብሽል .......

🌸ኡኽታዬ አዚዘቲ غሊየቲ ይቺ ዱንያ አጭር ነች ነገ በ 5 የከፈን ጨርቅ ተጠቅልለን አፈር ውስጥም የምንገባበት ቀን ይመጣል ስለዚ በዚች አጭር ዱንያ አትታለይ አትሸወጂ ሂጃብሽን ጠብቂ አላህ ባዘዘሽ መልኩ ልበሺው ሸርጡን ጠብቂ አትገላለጪ ተሰተሪ ።

💎 እንደዚሁም በየሚዲያው አትዝረክረኪ እራስሺን ጠብቂ በየኮመንቱ አትጐለቺ እዛ የኮመንት ማት የምታነቢበትን ሰአት ኪታብ ሞጥይበት ያለበለዛ ደግሞ የጌታችን ቃል ቁርኣንን ቅሪ ላንቺ የሚጠቅምሽ ይሄ ነው።
በየቦታው ለመታየት አትሞክሪ ልታይ ልታይ ማለት አያዋጣሽ ለሴት ልጅ የሚጠቅማት ተደብቃ አቂዳዋን ዲኗን መማሯ እንጂ እዛም እዚህ መታየቷ አይደለም ለሁሉም ነገር ፕሮግራም አበጂለት ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚበት በማይጠቅምሽ ነገር ላይ ጊዜሽን አታባክኚ ጊዜ ማለት ውድ ነው ነገ የሚቆጨን ቀን ከመምጣቱ በፊት ልንጠቀምበት ይገባል!

📌ከልብ የመነጨ ወንድማዊ ምክር ለእህቶቼ እና le bint nurhusen💎💎💎💎🌸🌸🌸
ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ የእሳት ቃጠሎ ዜናዎች በጣም በዝተዋል። እውነት ድንገተኛ አደጋዎች ናቸዉ ወይ ለማለት የሚያስጠረጥር ነው። ሁሉም በያለበት በያካባቢው የንግድ ቦታዎቹንና ተቋሞቹን ተደራጅቶ ይጠብቅ።
=
https://t.me/IbnuMunewor
🌴“በራስ ስራ መኮፈስ ራስ በራስ የሚደረግ ምቀኝነት ነው"🌴

(ዓልይ ቢን አቢ ጣሊብ)
ረመዷን
(12)
***
ዉስጤ የምሻዉን ነገር ልጠይቀው ባሰብኩ ጊዜ ሁሉ በነኚሁ ለኔና ለናንተ በምጽፋቸው ጽሑፎች ነው ወደጌታዬ ወደአላህ የምቃረበው። ነገም እነኚህኑ ይዠ ነው ጌታዬ ፊት የምከራከረው። አምላኬ ሆይ ስላንተ መልካም ነገር አልፃፍኩም ወይ?። ለባሮችህ በጎዉን መንገድ አላመላከትኩም ወይ? ... እላለሁ ።

ወዳጆቼ ! መልካም ሥራዎች መከላከያ ጋሻዎቻችን ናቸው። ዛሬ ከክፉ ፍፃሜ ይጠብቃሉ። ነገም ከአሳማሚው እሳት ያድናሉ።

የመልካም ሥራው ዘርፉ ብዙ ነዉና በገራላችሁ መንገድ ሁሉ ወደ አላህ ተቃረቡ። በአላህ በማመናችሁ፣ በሶደቃችሁ፣ በዱዓችሁ፣ በጥሩ ሥነምግባራችሁ፣በበጎ በማዘዝና ከመጥፎ በመከልከላችሁ፣ ለፍጡራን መልካም በመዋላችሁ ... በሌላም ብዙ ብዙ መንገድ ወደ አላህ ተቃረቡ።

መከላከያዎቻችሁን ያዙ።

https://t.me/httpsLatahzen
ኹጥባ_አሏህ ከአርሹ በላይ ነዉ_አቡ ረይስ
خُطْبَةُ الجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

←المَوضُوعُ↓
→ ርዕስ↓

🌐አሏህ ከአርሹ በላይ ነዉ።☝️

ﺍﻷﺩﻟﺔ ﻭﺍﻟﺒﺮﺍﻫﻴﻦ ﻋﻠﻰ ﺇﺛﺒﺎﺕ ﺍﻟﻌﻠﻮ ﻟﻠﻪ ﺭﺏ ﺍﻟﻌﺎﻟﻤﻴﻦ

ለዓለማቱ ጌታ ለአሏህ የበላይነትን በማፅደቅ ላይ ማስረጃዎች
♻️♻️እድሜ ልክህን የፈለከውን ያክል ለዱንያ ብትለፋ ተራራም ብትንድ እልፍ ኪሎሜትር ብትጓዝ እና ብደክም ካፈራህው ነብረት የፌስታል ያህል እንኳን ወደ አኬራ ይዘህ መጓዝ አችልም ።
🌲 መልካም ስራህ ሲቀር
የኒያ ታላቅነት


➡️መምሻድ አድዱሪ እንዲህ አለ:-በጉዞዬወቅት አንድ መልካም ሰው አገኘሁና 'ስንቅ የምትሆነኝ ምክር ምከረኝ'አልኩት።

እሱም እንዲህ በማለት መከረኝ:- በሀሳብ (ኒያህ)ላይ ትኩረት አድርግ።

➡️ የሰው ልጅ የልብ ሀሳቡ ከምንም ነገርበላይ ነው። ሀሳቡ የተስተካከለለት ሰው በዚህም እውነተኛ የሆነ እንደሆነ ተከትለውት የሚመጡ ነገሮችና ስራዎችሁሉ ይከተሉታል።
አንተን በመለመን፣ ላንተ በማጎንበስ፣ ላንተ በመዋደቅ...ትርፉ ደስታና ክብር ነው።

#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ
ሶላት የ ል ብ መድኃኒት፣ የስኬት መሰላል ነው። የሰው ልጅ የእድገቱና የስነ ምግባሩ ሚዛን ሶላት ነው። ሶላቱ የተስተካከለ እንደሆን ሕይወቱ ሰመሯል። በአሏህ(ሱ.ወ) መንገድ ሕይወታቸው ከሚሰምራለቸው ሙዕሚሞች መካከል ያድርገን!

አሚን 🤲
#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ
የምንፆመው ምግብ እና መጠጥ ብቻ አይደለም። በደል፣ ተንኮል፣ ዉሸት፣ ሀሜት፣ ክህደት፣ ስርቆት፣ ቅጥፈት፣ መጥፎ ንግግር ፣ የሀሰት ምስክርነት፣ ማታለል፣ የዉሸት መሃላ፣ ጥላቻ፣ ጎሚ፣ በቀል፣ ስካር፣ ... እነኚህን እና የመሳሰሉትን ካልፆምን ፆማችን ትክክል ሊሆን አይችልም።
“ሴት“

አልሀምዱሊላሂ ልጀምር በስሙ፣
ሴት ልጅን ለሰጠን ሀምድ ይግባው ረሂሙ፣

በሁሉም ዘርፍ ላይ ናት የተዋጣላት፣
ቢወራስ አያልቅም የእሷኮ ማንነት፣

ነች እኮ ወድ እናት አምሳያ የሌላት፣
ደሞ በእህትነት ለወንድሟ ምትሞት፣

እንደው ምን ልበላት ቃላት አጣሁላት፣
ጀሊሉ በቁድራው በጀነት ይካሳት፣

ሚስትም ትሆናለች የባል ተፈቃሪ፣
በጦርነት ላይም ምን ባትሆን ወራሪ፣

ወንዱን ታጅባለች ከጎን አባሻሪ፣
ተወዳጇ ሴት ልጅ አባቷን አክባሪ፣

ኧረ ማነው እስቲ ቦታዋን ሚተካ፣
አልፎ ተረማምዶ ነው ክብሯን ሚነካ፣

ነች እኮ ክብር ያላት የቤተሰብ ዋርካ፣
አላህ ይዘንላት ይሙላት በበረካ።

ልክ እንደ ዓኢሻ በእውቀት የተካቡ፣
አሉ በዘመኑም በኢማን ያበቡ፣

በኒቃብ በሂጃብ እጅግ የተዋቡ፣
ሚናቸው አያልቅም ቢከተብ ኪታቡ፣

ልምከርሽ እህቴ ምን ብዙ ባልቀራ፣
ካየሁ ከሰማሁት በጥቂቱ ላውራ፣

በዲን በክብርሽ ላይ አደራ አደራ፣
ከአላህ እንዳይገጥምሽ የስቃይ መከራ፣

እንዳይታለዪ ዘመኑ ባመጣሽ፣
ገዜ እንዳታጠፊ ምንም በማይጠቀምሽ፣

አልፎ ተገልብጦ አንቺን በሚጎዳሽ፣
እንዳትሸወጂ አደራ ልበልሽ፣

እኔም በዚው ላብቃ ግጥሙም ሳይንዛዛ፣
ራህማኑ ይክፈልሽ ሚያምረውን ጀዛ።

ኑርአህመድ

https://t.me/httpsLatahzen
‼️ዘርን ለገበሬ

ዘርን ለገበሬ ብያለሁ አምርሬ፣
ላይጠቅመኝ ሊጎዳኝ ብዬ ዘሬ ዘሬ፣

ሀገሬ ባሌ ነው ኦሮሞ ነው ዘሬ፣
እኔ ጉራጌ ነኝ ምኖረው ጉንችሬ፣
እኔ ሀደሬ ነኝ የሆንኩኝ ሀረሬ፣

ሌላም ሌላም ቢሆን ትቻለሁ አምርሬ፣
ምን ሊጠቅመኝ ነው ለዘር መቆርቆሬ፣
አደም የማን ዘር ነው እላለሁ ደፍሬ፣
ከዛ ሇላ ያለው ነው የሱ ጅማሬ፣

እስቲ ልጠይቅህ አምጣ ስልጤም ትግሬ፣

ከዛ ቅደዳቸው ውጋቸው በጩቤ፣
ሚወጣቸው ደም ነው ዋነኛ ታሳቤ፣
ደሙን ቀላቅዬ ልለየው አስቤ፣
ጭራሹን አይሆንም አይታሰብ ከቶ፣
እስካልተነቀስከው የዘርህን ታቶ፣

ሙስሊሞች አንድ ነን በተውሂዱ ገመድ፣
ምስጋና ይገባው ለጌታችን ሰመድ፣
አንድ ላደረገን በሀቂቃው መንገድ፣

እኛ እንሰግዳለን ሁለም በአንድ መሰጊድ፣
ዘሩን አንጠይቅም ከጎናችን ሚሰግድ፣

ነቢ አስጠንቅቀዋል እኛ እንድንዋደድ፣
ከጥንቧ እራቁ አንድ ሁኑ በተውሂድ፣
ጀሊል እኛን ያርገን በተውሂድ ሚዋደድ።



ኑርአህመድ🖊🖊https://t.me/httpsLatahzen
ረመዳን 1 ፣
ረመዳን 2 ፣
ረመዳን 3 ፣
ረመዳን 4 ፣
ረመዳን 5 ፣
ረመዳን 6 ፣
ረመዳን 7 ፣
ረመዳን 8 ፣
ረመዳን 9፣
ረመዳን 10፣
ረመዳን 11፣
ረመዳን 12፣
ላይመለሱ ሄደዋል!
መልካም ከነበሩ ጨምርባቸው ፣
ካልነበሩ እንደገና ጀምር
ኑርአህመድ

#ውድድሩ ከተሰጠህ ግዜ ጋ ነው።