Diinii kee Anaakara (Md Ali)
1.61K subscribers
999 photos
212 videos
217 files
1.48K links
دروس وفتاوي ومحاضرات باللغة العفرية
★Diini barittooy, fatwaa kee Daqwa Qafar afat
Tû mabul=> @Anaakar or @acmadxalol
Download Telegram
የማለዳ መልእክት (46)
~
ከአቡ ሁረ ይረህ - ረዲየላሁ ዐንሁ - ተይዞ ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

أكْملُ المؤمنينَ إيمانًا أحسنُهُم خلقًا . وخيارُكُم خيارُكُم لنسائِهِم

"ከምእመናን መካከል ኢማኑ ሙሉ የሆነው ሥነ-ምግባሩ ያማረው ነው። ከእናንተ መካከል በላጮቹ ለሴቶቻቸው (ለባለቤቶቻቸው) መልካም የሆኑት ናቸው።"

[አቡ ዳውድ (4682)፣ ቲርሚዚይ (1162) እና አሕመድ (2/ 472) የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ "ሐሰኑን ሶሒሕ" ብለውታል። (ሶሒሑ ቲርሚዚይ፡ 1162) ]

የራሳችንን ሁኔታ እናጢን፤ የተሻለ ለመሆንም እንጣር።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 01/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሙስሊም ወንድሞቼ ፣ ጊዜው ሳያልፍ እንንቃ!

ያ አላህ! ጉዳዩ እየከበደና እያሳሰበ መጥቷል። ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ ፊርቆችና አስተሳሰቦች እየተጋለጠች ነው። አንዳንድ ቡድኖችና እንቅስቃሴዎችም በሕዝቡ መካከል እየተስፋፉ ሲሆን፣ በተለይም ወጣቶችንና ሕፃናትን ማነጣጠራቸው እየጨመረ ነው።
በቅርብ ጊዜም ከአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ አስተምህሮ ፍፁም የሚለያዩ  ቡድኖች፣ ከእነሱም መካከል ሺዓ፣ አሕመዲያ እና ሌሎችም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንደሚገኙ እናስተውላለን። በተለይም በባቲና በአካባቢዋ የተለያዩ የትምህርትና የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ትኩረታችንን ይሻል።
በተለይ ልንጠነቀቅ የሚገባን ሕፃናትና ወጣቶች ላይ የሚደረገው ትኩረት ነው። አንዳንድ ወገኖች ትምህርት ቤቶችን፣ ማዕከላትንና የትምህርት ተቋማትን በመክፈት ሕፃናትን ገና ከልጅነታቸው ከ kg ጀምሮ ለማስተማር እየሰሩ ነው።

እንግዲህ ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፦
ልጆቻችን እና ወጣቶች ምን እየተማሩ ነው?
ምን ዓይነት እምነትና አስተሳሰብ እየተቀበሉ ነው?
ትምህርታቸውን የሚከታተልና አቅጣጫ የሚሰጣቸው ማን ነው?

ወንድሞቼና የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ!
ከሀገራችን  ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ፣ የአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ ተከታዮች ሆይ፣ የአካባቢያችን ሰዎች ሆይ፣ በተለይም የባቲ ነዋሪዎች ሆይ!

የልጆቻችን የወጣቶችን የራሳችንንእምነት መጠበቅና የአላህን መጽሐፍ እና የነቢዩን ﷺ ሱና ማስተማር ታላቅ ኃላፊነት ነው።
ይህንንም በዘፈቀደ ግጭት፣ በስድብ ወይም ሌሎችን በማዋረድ ሳይሆን፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በትክክለኛ ትምህርት፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ማህበረሰባችንን በቁርአን፣ በሱናና በትክክለኛ የእስልምና እምነት ማጠናከር ነው።
ማህበረሰባችንን በቅርብ ልንከታተል፣ ምን እንደሚማሩም ልናውቅ ይገባል። በራሳችን ትምህርት ቤቶችና የእስልምና ማዕከላት ውስጥም ጠንካራና ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ ልንጥር ይገባል።

ይህም ቁርአንን፣ ትክክለኛ የአቂዳ ትምህርትን፣ ፊቅህን፣ መልካም ሥነ-ምግባርንና የዓረብኛ ቋንቋን ያካተተ መሆን አለበት።
ሌሎች ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ ከፈቀድን በኋላ፣ ሐሳቦቻቸው ስለተስፋፉ ብቻ ማማረር መፍትሔ አይሆንም።
ስለዚህ ኃላፊነታችንን እንወጣ። ማህበረሰባችን ከሌሎች ዘንድ ከመማራቸው በፊት እኛ እናስተምራቸው። የተሳሳቱ አስተሳሰቦችንም በዕውቀት፣ በማስረጃና በጥበብ እንመልስ።
ኢንሻአላህ፣ እነዚህ ቡድኖች ምን እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ሐሳቦቻቸውና እምነቶቻቸው ምን እንደሆኑም በማስረጃና በታማኝ ምንጮች ላይ በመመስረት አብራራለሁ፤ ዓላማዬም ሙስሊሙ ስለ ዲኑ በቂ ዕውቀት እንዲኖረውና በጉዳዮች ላይ በግልጽ እውቀት እንዲቆም ነው።

አላህ ሆይ! ሀገራችንንና ማህበረሰባችንን ጠብቅ። እኛንና እነርሱን በቁርአንና በሱና ላይ አጽና። ዑለማዎቻችንን፣ ዳዒዎቻችንንና መምህራኖቻችንን ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ እርዳቸው። ከቀናው መንገድ የራቁትንም ወደ እውነት ምራቸው።
አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ልጆች ጠብቅ፣ እምነታቸውን ጠብቅ፣ ወደ እውነትና መልካም ሥራ የሚጠሩ ዳዒዎች አድርጋቸው።
                     አሚን!

=
አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba
የማለዳ መልእክት (46)
~
ታላቁ ሶሓቢይ ሰዕድ ብኑ አቢ ወቃስ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

إن الله يحب العبد التقي الغني الخفي
"አላህ፡ አላህን ፈሪውን፣ በራሱ የተብቃቃውን እና ድብቁን (ዝናን የማይፈልገውን) ባሪያውን ይወዳል።"

ኢማሙ ሙስሊም በሶሒሓቸው ውስጥ ዘግበውታል። [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2965]

=

ዑለማኦች የአላህን ውዴታ የሚያስገኙትን እነዚህን ሦስት ባሕርያት እንደሚከተለው አብራርተዋቸዋል፦

1. «አል-ተቂይ» (ፈሪሃ-አላህ ያለው / አላህን ፈሪ):-

ይህ ባሪያ የአላህን ትዕዛዛት በመፈጸም እና ክልከላዎቹን በመራቅ የአላህን ትእዛዝ የሚጠብቅ፣ በአላህ ትዕዛዝና ኃጢአትን እንዲሁም አጠራጣሪ ነገሮችን በመራቅ በእርሱ እና በአላህ ቅጣት መካከል ከልላይን የሚያደርግ ነው።

2. «አል-ገኒይ» (ሀብታም / የተብቃቃ):-

«ሀብት/መብቃቃት» በሚለው ትርጉም ላይ በሁለት አቅጣጫ ገልጸውታል፦

* የነፍስና የቀልብ መብቃቃት (ይህ ይበልጥ ጎላ ያለና ተመራጩ ትርጉም ነው)፦

ባሪያው አላህ በወሰነለት እና በሰጠው ሲሳይ የሚረካ፣ በሰዎች እጅ ካለው ነገር ተብቃቅቶ በአላህ ብቻ የሚብቃቃ፣ ቀልቡ በኢማን እና በየቂን (እርግጠኝነት) የሞላ መሆን ነው። ነቢዩም ﷺ፦ «ولكن الغنى غنى النفس» («እውነተኛ ሀብት ማለት ግን የነፍስ (የቀልብ) መብቃቃት ነው») ብለዋል።

* የገንዘብ ሀብት፦

ይህም ሀብቱን በበጎ አድራጎት፣ በመልካም ሥራዎች እና ሰዎችን በመጥቀም ላይ የሚያውል፣ ሀብቱ ከአላህ እገዛ እንዳይዘናጋው የአላህን ሐቅ እየፈጸመ የሚያመሰግን ሀብታም ነው።

3. «አል-ኸፊይ» (ድብቁ / ራሱን የማያገዝፈው):-

* ዝናን፣ ሥልጣንን እና በምድር ላይ ከፍ ማለትን የማይሻ፣ ይልቁንም ጌታውን በመገዛት፣ የራሱን ጉድለቶች በመመልከት እና ራሱን በማረም ላይ ብቻ የተጠመደ ሰው ማለት ነው።

* በተጨማሪም፦ ፍጹም ለአላህ ብቻ ብሎ ለመስራት (ኢኽላስ) እና ይዩልኝ ስሙልኝን (ሪያእ) በመፍራት መልካም ሥራዎቹንና አምልኮቶቹን (እንደ ድብቅ ሶደቃና የሌሊት ሶላት ያሉትን) ሰው እንዳያይበት የሚደብቅ ሰውም በዚህ ውስጥ ይካተታል።

||
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 04/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የሰዎች ህይወት እና ንብረት በሌላው ላይ ሐራም ነው!
~
ከአቡ በክረህ (አላህ ይውደድላቸው) ተይዞ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

" إِنَّ دِمَاءَكُمْ وَأَمْوَالَكُمْ وَأَعْرَاضَكُمْ بَيْنَكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا، فِي شَهْرِكُمْ هَذَا، فِي بَلَدِكُمْ هَذَا "
“ደማችሁ (ሕይወታችሁ)፣ ንብረታችሁ እና ክብራችሁ በእናንተ ላይ እርም (የተከለከለ) ነው፤ ልክ በዚህ ወራችሁ እና በዚህ አገራችሁ ውስጥ ይሄ ቀናችሁ እንዳለው ክብር።”

[ቡኻሪይ (39) ከዘገቡት ሐዲሥ የተወሰደ ነው። ሙስሊምም (2816) ዘግበውታል።]

* ቡኻሪይ (7078) ውስጥ በሚገኝ ሌላ ዘገባ ደግሞ እንዲህ የሚል አለ፦
" وَأَبْشَارَكُمْ، عَلَيْكُمْ حَرَامٌ كَحُرْمَةِ يَوْمِكُمْ هَذَا "
“አካሎቻችሁም እንዲሁ እንደዚህ ቀናችሁ ክብር የተከበሩ ናቸው።”

* በተጨማሪም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" لَا تَرْجِعُوا بَعْدِي كُفَّارًا، يَضْرِبُ بَعْضُكُمْ رِقَابَ بَعْضٍ "
“ከኔ በኋላ ከፊላችሁ የከፊሉ አንገት የሚሰይፍ ከሃዲዎች ሆናችሁ አትመለሱ።” [ቡኻሪይ (67 እና 7078] እና ሙስሊም (1679) ዘግበውታል።]

የቃላት መፍቻ፦
=
1. “ይሄ ቀናችሁ” የተባለው ዙልሒጃ አስር ሲሆን የዒደል አድሓ የመጀመሪያው ቀን ነው።
2. “በዚህ ወራችሁ” የተባለው የተከበረው የዙልሒጃ ወር ነው።
3. “በዚህ ሃገራችሁ” የተባለው የተከበረው የአላህ ቤት፣ የተከበረችዋ መካ ለማለት ነው።

ከሐዲሡ የሚወሰዱ ትምህርቶች፦
=
1. የሙስሊሞች ደም ፈፅሞ ሊደፈር የማይገባው እርም እንዲሁም በጣም የተከበረ እንደሆነ፣
2. የሰዎችን ንብረትና ክብር መዳፈር ክልክል እንደሆነ እና
3. የሙስሊም ደሙ፣ ንብረቱ እና ክብሩ ከተከበረው ሃገር፣ ከተከበረው ወር እና ከተከበረው ቀን ክብር በላይ እንደሆነ እንወስዳለን።

ዐብዱላህ ብኑ ዐምር ብኒል ዓስ (አላህ ይውደድላቸው) ባስተላለፉት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

" وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَقَتْلُ مُؤْمِنٍ أَعْظَمُ عِنْدَ اللهِ مِنْ ‌زَوَالِ ‌الدُّنْيَا "
“ነፍሴ በእጁ በሆነችው (ጌታዬ) እምላለሁ! አንድን አማኝ መግደል አላህ ዘንድ ከድፍን ዓለም መጥፋት የከፋ ነው።” [ነሳኢይ (3986) ዘግበውታል።]

* ሙስሊም ያልሆኑ አካላትም እንዲሁ ሊበደሉ አይገባም። ይህንን የሚመለከት ማስረጃ ሌላ ጊዜ አቀርባለሁ፣ ኢንሻአላህ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የማለዳ መልእክት (47)
~
ልጅ ትልቅ ሃብት ነው። እንዲያውም ከልጅ በላይ ሀብት የለም። ህንፃ ቢደረደር፣ ሃብት ቢትረፈረፍ ያለ ልጅ ጣእም የለውም። የልጅን ኒዕማ የሚያቃልለው ወይ ህይወት ያለ ልጅ ምን ያክል ባዶ እንደሆነች የሚረዳበት የእድሜ ክልል ላይ ያልደረሰ ነው። ወይ ደግሞ አእምሮው በሌሎች መጥፎ አስተሳሰብ የተበከለ አካል ነው። እንጂ በተትረፈረፈ ሃብት ውስጥ ብትሆን እንኳ ያለ ልጅ ህይወት ጣእም አልባ ናት። የአላህ ነብይ ዘከሪያ የነበራቸውን ስሜት እና የሰጣቸውን ፈረጃ አላህ እንዲህ ሲል ይገልፀዋል:-

{ وَزَكَرِیَّاۤ إِذۡ نَادَىٰ رَبَّهُۥ رَبِّ لَا تَذَرۡنِی فَرۡدࣰا وَأَنتَ خَیۡرُ ٱلۡوَ ٰ⁠رِثِینَ (89)
"ዘከሪያንም፡ 'ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ' ሲል ጌታውን በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡''

فَٱسۡتَجَبۡنَا لَهُۥ وَوَهَبۡنَا لَهُۥ یَحۡیَىٰ وَأَصۡلَحۡنَا لَهُۥ زَوۡجَهُۥۤۚ إِنَّهُمۡ كَانُوا۟ یُسَـٰرِعُونَ فِی ٱلۡخَیۡرَ ٰ⁠تِ وَیَدۡعُونَنَا رَغَبࣰا وَرَهَبࣰاۖ وَكَانُوا۟ لَنَا خَـٰشِعِینَ (90) }
"ለእርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ የሕያንም ሰጠነው፡፡ ለእርሱም ሚስቱን አበጀንለት፡፡ እነርሱ በበጎ ሥራዎች የሚቻኮሉ ከጃዮችና ፈሪዎች ሆነው የሚለምኑንም ነበሩ፡፡ ለእኛ ተዋራጆችም ነበሩ፡፡" [አልአንቢያእ፡ 89-90]

በርግጥ ትልቁ ነገር እንዲሁ ልጅ መኖሩ ብቻ አይደለም፣ አስተዳደጉ ሲያምር ነው ልጅ የዓይን ማረፊያ፣ የዱንያ ምርኩዝ፣ የኣኺራ ስንቅ የሚሆነው። ስለዚህ ልጆቻችን ከየትኛውም ሃብት በላይ ናቸውና አጥብቀን እንድከምላቸው።

ውለዱ፣ ክበዱ። አስተዳደጋቸው ላይ ትኩረት ስጡ። የሌላችሁ አላህ ልጅ ይስጣችሁ። ያልተሰካላችሁ አላህ ስብራታችሁን ጠግኖ በኣኺራ ይካሳችሁ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑል አወል 05/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
1
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
Photo
ሶሐቦች የማያውቁት ዒባዳ ዒባዳ አይደለም!
~
በየትኛውም የቢድዐ መስመር ላይ የሚገኝ አካል በሶሐቦች ግንዛቤ ሲሞገት ምቾት አይሰጠውም። ምክንያቱም ቁርኣንና ሐዲሥን እንዳሰኘው እየጠመዘዘና እየለጠጠ ነገር ሊያስረዝም ሲጣጣር በሶሐቦቹና በሰለፎቹ ግንዛቤ ተገድቦ ሲያዝ መፈናፈኛ አያገኝም። በዚህም ሳቢያ በዚህ መልኩ ሲፋጠጡ በቅድሚያ የሚያደርጉት ይህን የቀደምቶች ግንዛቤን እራሱን ከውይይት ጠረንጴዛ ላይ እንዲወርድ መታገል ነው። ለዚህም ነው “ሰለፎች ያልሰሩት ነገር ቢድዐ ነው የምትለዋ ትምህርት ከየትኛው የቁርኣን ወይም የሐዲሥ ዘገባ የመነጨች ናት?” እያሉ ልብ የሚያወልቁት።

አዎ ሰለፎች ያልሰሩትን አምልኮ ኢስላም አያውቀውም። ሶሐቦች የማያውቁት ኢስላም አለ እንዴ? ኢስላም ማለት እኮ ከነብዩ ﷺ ወደ ሶሐቦች፣ ከሶሐቦች ወደ ታቢዒዮች፣ ከታቢዒዮች ወደ መልካም ተከታዮቻቸው የተላለፈ ሃይማኖት እንጂ ማንም እየተነሳ የሚያሻሽለው ሰው ሰራሽ አስተምህሮት አይደለም። ስለዚህ እነዚያ ምርጥ ትውልዶች የማያውቁት ሃይማኖት ኢስላም አይደለም። እነዚያ ኢስላምን በቀጥታ ከመልእክተኛው ﷺ የተማሩ እንቁዎች የማያውቁት አምልኮ ዒባዳ አይደለም። ይልቁንም ቢድዐ ነው፤ ጥመት። ይሄ ሐቅ አእምሮውን ማሰራት ለሚሻ ሁሉ የሚሰወር ባይሆንም ጥቂት ማስረጃዎችን ላጣቅስ፡-


﴿ وَمَنْ يُشَاقِقِ الرَّسُولَ مِنْ بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُ الْهُدَى وَيَتَّبِعْ غَيْرَ سَبِيلِ الْمُؤْمِنِينَ نُوَلِّهِ مَا تَوَلَّى وَنُصْلِهِ جَهَنَّمَ وَسَاءَتْ مَصِيرًا ﴾
{ቅኑ መንገድ ከተገለፀለት በኋላ መልእክተኛውን የሚፃረርና #የአማኞቹ_ያልሆነን_መንገድም_የሚከተል፣ በተሾመበት (ጥመት) ላይ እንሾመዋለን፤ ጀሀነምንም እንከተዋለን። መመለሻይቱም ከፋች!} [አኒ፞ሳእ፡ 115]

የደመቀውን ሀረግ በሚገባ ያጢኑት። ቁርኣኑ በወረደበት ዘመን የነበሩት አማኞች አይነታችን የበዛው እኛ ሳንሆን በተውሒድና በሱና የተሳሰሩት ሶሐቦቹ ብቻ ናቸው። በአንቀጿ ምስክርነት የሶሐቦች ያልሆነን መንገድ የሚከተል አደጋ አለበት።


﴿ فَإِنْ آَمَنُوا بِمِثْلِ مَا آَمَنْتُمْ بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوْا وَإِنْ تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ﴾
"በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡" [አልበቀራህ: 137]

③ “ከናንተ የሚኖር ብዙ ውዝግቦችን ያያል። ያኔ ባወቃችሁት ሱና፞ዬ እና ከኔ በኋላ ያሉ ቀጥተኛና የተቀኑ የሆኑ ምትኮቼንም ሱና፞ አደራችሁን” ይላሉ ነብዩ ﷺ። [አሶ፞ሒሐ፡ 937]

④ ኢብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-

“ከናንተ ምሳሌን መያዝ የፈለገ የሞቱትን ይያዝ፡፡ ምክንያቱም በህይወት ያለ ሰው ፈተናው አይታመንምና፡፡ እነዚያ የሙሐመድ ﷺ ሶሐቦች ከዚህ ህዝብ ሁሉ ልባቸው የመጠቀ፣ እውቀታቸው የጠለቀ፣ ከማይመለከታቸው መግባታቸው የቀለለ ናቸው፡፡ አላህ ለራሱ ነብይ አጋርነት እና ሃይማኖቱን ለማፅናት የመረጣቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ሐቃቸውን እወቁ፡፡ በመንገዳቸው ተጓዙ፡፡ ምክንያቱም እነሱ ቀጥ ባለው መንገድ ላይ ነበሩና!!” [ዘምሙል ከላም፡ 88]

⑤ ሑዘይፈቱ ብኑል የማን ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላሉ፡- “የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦች አላህን ያላመለኩበትን እያንዳንዱን አምልኮት አላህን አታምልኩበት። የመጀመሪያዎቹ ለኋለኞቹ የተውት ዘርፍ የለምና። [አዙ፞ህድ፡ 47]

⑥ ዑመር ብኑ ዐብዲል ዐዚዝ እንዲህ ይላሉ፡- “ሰዎቹ (ሶሐቦች) ከቆሙበት ቁም። እነሱ ከእውቀት ነው የቆሙት። ከጥልቅ ግንዛቤም ነው የታቀቡት። በርግጥም እነሱ ከናንተ በበለጠ እሷን (መጤዋን) በመግለጥ ብርቱ ነበሩ። በሷም ላይ ትሩፋት ቢኖር ይበልጥ የተገቡ ነበሩ። ‘ከነሱ በኋላ ነው የተፈጠረው’ ካላችሁ መመሪያቸውን የጣሰ፣ ከሱናቸው የዞረ እንጂ አልፈጠረውም። ከእውቀት፡ የሚያረካን ግልፅ አድርገዋል። በቂ የሆነንም ተናግረዋል። ከነሱ በላይ የሚጥር ከንቱ ደካሚ ነው። ከነሱ ያሳጠረ ወደኋላ የቀረ ነው። የሆኑ ሰዎች ከነሱ ቀሩና ራቁ። ሌሎች ከነሱ አለፉና ፀነፉ። እነሱ ግን እዚህ መሀል ላይ ቀጥ ካለ ቅናቻ ላይ ናቸው።” [ሉምዐቱል ኢዕቲቃድ፡ 8 - 9]

⑦ አልኢማም አልአውዛዒይ እንዲህ ይላሉ፡ “እራስህን በሱና ላይ አፅና። ሰዎቹ (ሶሐቦች) ከቆሙበትም ቁም። እነሱ ያሉትን በል። እነሱ ከታቀቡት ታቀብ። የመልካም ቀደምቶችህን መንገድ ተከተል። ለነሱ የበቃቸው ይበቃሀልና!!!” [ሸርሑ ኡሱሊ ኢዕቲቃዲ አህሊ ሱና፞ ወልጀማዐህ፣ ላለካኢይ: ቁ• 315] [አሽ-ሸሪዐ፣ አልኣጁሪይ፡ 2/673]

* በድጋሚ አውዛዒይ እንዲህ ብለዋል:– "የቀደምቶችን ቅሪት ያዝ አደራህን። የሰዎችን ግላዊ እይታዎች ተጠንቀቅ፣ በቃላት ቢያሸበርቁልህም እንኳን። አንተ በቀጥተኛው መስመር ላይ ከሆንክ ነገሩ ሲገለጥ ይገለጣል።" [አሸ፞ሪዐህ፡ አልኣጁሪይ፡ 63]

⑧ ኢማሙ ማሊክ፡- “የዚች ህዝብ ቀደምቶቿ ያልነበሩበትን የሆነን ነገር የፈጠረ በርግጥም የአላህ መልእክተኛ ﷺ ተልእኳቸው ላይ ሸፍጥ ሰርተዋል ብሎ ሞግቷል። ምክንያቱም አላህ {ዛሬ ለናንተ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ} ብሏልና። ያኔ ዲን ያልነበረ ነገር ዛሬ ዲን አይሆንም።” [አት-ተምሂድ፣ ኢብኑ ዐብዲልበር፡ 10/23] [አልኢዕቲሷም፡ 2/53]

ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! ይሄ የኢማሙ ማሊክ ንግግር ለቢድዐ አራጋቢዎች ከባድ መብረቅ ነው!

* አሁንም ኢማሙ ማሊክ፡- “የዚች ህዝብ መጨረሻዋ አይስተካከልም፣ የመጀመሪያዋ በተስተካከለችበት ቢሆን እንጂ። ያኔ ዲን ያልነበረ ነገር ዛሬ ዲን አይሆንም።” ላሉ [ሐጀ፞ቱ ነ፞ቢይ፡ 103]

⑨ ኢማሙ አሕመድ፡- “እኛ ዘንድ የሱና መሰረቶች የአላህ መልእክተኛ ﷺ ሶሐቦች በነበሩበት አጥብቆ መያዝ፣ እነሱን መከተል፣ ቢድዐዎችን መተው ነው። እያንዳንዷ ቢድዐ ጥመት ነች” ይላሉ። [ኡሱሉ ሱ፞ና፞: 1]

(10) ኢብኑ ከሢር፡- “አህሉ ሱና፞ ወልጀማዐ እያንዳንዱን ከሶሐቦች ያልተገኘን ተግባርም ይሁን ንግግር ‘ቢድዐ ነው’ ይላሉ። ምክንያቱም በጎ ቢሆን ኖሮ ወደሱ ይቀድሙን ነበርና። ለምን ቢባል የመልካም ነገር ቀንዘል ሆኖ ሳይሽቀዳደሙበት የተውት የለምና።” [ተፍሲር ኢብኒ ከሢር፡ 7/256]

(ኢብኑ ሙነወር፣ ህዳር 09/2012)
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Forwarded from Kassis Faage
البدعة_في_الدين_والإحتفال_باالمولد_النبوي.MP3
55.8 MB
#Diinit Bidqa/bicso bicsaanamat tanih tan umaanee kee Mawliid Al nabawih bidqa wagsiisaak yabta Khutba
🎙Khutba lem Shekh Cuseen Acmad Cafizahullaah
Forwarded from Kassis Faage
#Repost
☝️Islaaminnah addal namma qiidiik iroh qiidittemmay tamixxigem mali, Muslimiin tassakaxxeeh leh tanim namma qiidi(qafayda) tohumuu:-
Fatri qiid( Raamadaanak edde yafturen qiid) kee
Masgaadâ qiid(Qarafah alsak taban haytoh ayro nassakaxxe qiid kinni.
Tohuuk iroh qiiditte haysitaanaah yassakaxxeenim Muslimiin kinni marak mafaxximta.
👉inah ayrooy ,
👉Kacani ayrooy ,
👉ገና/Christmas(Koros dirab kee deedalah Yallah baxi edde yooboke axcuk tassakaxxe ayrooy,
👉Sinni ubukyah ayrooy,
👉Qusba sanatih ayrooy Gorgooriyaan hinnay nanu Farangi liggidih loowol muggaaqisna loowol takkay Ityobbiyah liggidih loowol takkay,Amaaziigh loowoh qusba sanatih ayro takkay kalah faxe liggidih loowooy takkay
Taham inkih koros ayrooraa kee ken katayyoh yassakaxxen ayroora kinniimih taagah Islaam diinii kee Muslimiin ummatta mawlissam naaxigem faxximta ummaan sanat elle yadaareemil qagaaqagittam kinnuuk tannah tan umaaneenak garcite waynay garci sittah kallay inxeca .
👉Manol aabbe wayya hayneemih korosuy fatri qiid kee Qarafâ qiid tassakaxxe maabbino, keeniy deedal kee dirab diinih amol yani ni qiid inki saaku assakaxxe waah sinniimih kacanuh tannah abitan wak nanu tagideh massakaxxaa kee konnabna le diini likih ken kataynaah oson yassakaxxen ayroora ken luk nassakaxxem nee macelta meqe toobokoy.
👉Taa dagal edde yabne ayroora akke sinni ayrooray bidqâ maritte bicisseh iyya tan kaaduk Tohumuu:-
👉Mawlidû Nabawi/Nabi (ﷺ) edde yooboke ayrooy ,
👉Hiljrâ liggidih biloh ayrooy,
👉Nabi Mucammad (ﷺ) Makki masgidiik Beytal maqhdis(Masgidul- Aqhsa) fanah edde kuuleeh qaran edde yewqe barih Munaasabat wagsiisaak yassakaxxen ayrooy
Taham kaaduk isih nabsi fayxii kee Bidqâ maritte bicisse ayroora kinnuuk Islaaminna mawlissaay nassakaxxem mafaxximta bidqa yaanam sahlik tanim hinna koroosinnaak wadiril teetik gacta umaane matan.
👇Taa ayroora yassakaxeenim bidqa kah kinnim taa ciggilta sababitte:-
👉Taa ayroora Nabi (ﷺ)massakaxxinna.
👉Yallih farmoyti (ﷺ) kataysis massakaxxinna.
👉Ken maqaanel katayya hayte Islaam Qolomak num massakaxxinna.
👉Ta ayroora yassakaxxeenim maqaane takkeemil ta mari inkih nek elle aakume xaaxen ummaan maqaanel nek kah yookomen innah, tohih taagah taa ayroora yassakaxxeenim kaxxa umaaney Yallat sinam taysaamme kinnim nasmatu dudne.
👉Taa ayroora kaaduk ummaan liggidih addat tamaate ayroora kinniimih taagah garci sittah elle kalnam faxximta.
#Join ⤵️⤵️ Telegram channel
https://t.me/Kassisfaage
https://t.me/Kassisfaage
🥰1