Diinii kee Anaakara (Md Ali)
1.61K subscribers
996 photos
210 videos
216 files
1.47K links
دروس وفتاوي ومحاضرات باللغة العفرية
★Diini barittooy, fatwaa kee Daqwa Qafar afat
Tû mabul=> @Anaakar or @acmadxalol
Download Telegram
ሌላ ትኩሳት የሆነ ጽሑፍ
================
(«እምነትህን ስትቀይር ዜግነትህና ታሪክህ ይሻራልን?» — በአሕመዲን ጀበል – በ"ሃይማኖታዊ ማንነት" ስም የሚነገድ የፖለቲካ ድንቁርና!)
||

✍️ ፖለቲካዊ ትረካዎችን በሃይማኖት ካባ እየሸፈኑ፣ የአንድን አገር ዜጎች "ነባርና መጤ" እያሉ ለመከፋፈል የሚደረገው ጥረት ዛሬም ድረስ በብዙዎች ዘንድ ይስተዋላል።

ኡስታዝ አሕመዲን ጀበል ባጋራው ድንቅና እውነተኛ ምሳሌያዊ ታሪክ አማካኝነት፣ ይህንን የደናቁርት
ርዕዮተ-ዓለም እንዴት በሎጂክና በታሪክ ማስረጃ ማፍረስ እንደምንችል የሚከተለውን ወጥና ሚዛናዊ ሃሳብ እንመልከት።

1. የአምስቱ ጓደኛሞች ውይይት (የኢትዮጵያዊነት ማሳያ)

በአንድ ትምህርት ቤት አብረው ተምረው ካደጉ አምስት የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ጓደኛሞች መካከል አራቱ በጊዜ ሂደት እምነታቸውን ይቀይራሉ። አንደኛው ሙስሊም፣ ሁለተኛው ካቶሊክ፣ ሦስተኛው ፕሮቴስታንት፣ አራተኛው ደግሞ የይሖዋ ምስክር እምነት ተከታይ ሲሆኑ፤ አምስተኛው ግን በኦርቶዶክስ እምነቱ ይጸናል።

ከዓመታት በኋላ በአካል ተገናኝተው ስለ አገርና ስለ እኩልነት ሲወያዩ፣ እምነቱን ያልቀየረው ጓደኛቸው በንዴትና በቁጣ ተሞልቶ እንዲህ ይላቸዋል፦

"እናንተ መጤዎች! ከእኛ ከነባሩ ህዝብ ጋር አገርን በእኩልነት እንጋራ ለማለት ደረሳችሁ? ኦርቶዶክስ አገር ያቆመች፣ ፊደል ቀርጻ ያስተማረች፣ እናንተ ተሰዳችሁ ስትመጡ የተቀበለች ነች።"

በዚህ ጊዜ ጓደኛሞቹ የሰጡት ምላሽ የፖለቲካዊ ማንነትን ስህተት ፍንትው አድርጎ ያሳያል፦

  የካቶሊክ እምነት ተከታዩ ምላሽ፦ "እምነትን መቀየር መጤ የሚያደርግ ከሆነ፣ ኦርቶዶክስን የኢትዮጵያዊነት ብቸኛ መለኪያ እያደረግከው ነው። ኦርቶዶክስ አገር ስትገነባ እኛም በወቅቱ ኦርቶዶክስ ስለነበርን ያንን ታሪክ አብረን የሰራነው እኛ ነን።"

የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዩ ምላሽ፦
"ከዓመታት በፊት እምነቴን ከመቀየሬ በፊት ኦርቶዶክስ ለሀገር ባበረከተችው አስተዋፅኦ ሁሉ ውስጥ እኔና አባቶቼ አለንበት። እምነቴን ስለቀየርኩ ብቻ የትናንት የታሪክ ድርሻዬና አሻራዬ ሊሻር አይችልም!"


የሙስሊም እምነት ተከታዩ ምላሽ፦
"አማኝን መጤ አድርጎ የሚፈርጀው ይህ አስተሳሰብ እያለ ያለው፦ 'አማራ ክርስቲያን ከሆነ ነባር ነው፣ አማራ ሙስሊም ከሆነ ግን መጤ ነው፤ ትግራዋይ ክርስቲያን ከሆነ ነባር ነው፣ ትግራዋይ ሙስሊም ከሆነ ግን መጤ ነው፤ ኦሮሞ ክርስቲያን ከሆነ ነባር ነው፣ ኦሮሞ ሙስሊም ከሆነ ግን መጤ ነው' እያለ መሆኑን አስተውላችኋልን? ይህ ከድንቁርና በቀር ምን ይባላል?"


የይሖዋ ምስክር እምነት ተከታዩ ምላሽ፦
"ሃይማኖትን መቀየር የውስጥ ማንነትን መገለጫ የሆነውን 'ዲ ኤን ኤ' (DNA)  ወይም የዘር ግንዱን አይቀይረውም። የተቀየረው እምነት እንጂ የአገሬው ተወላጅነቱ አይደለም።"



✒️ ከዚህ ውይይት በስተጀርባ ያሉትን መሠረታዊ የታሪክና የህግ እውነታዎች በአራት ዋና ዋና ነጥቦች እንገምግማቸው፦

ሀ) ዜግነት በሕግና በደም፣ ሃይማኖት በነፃነት!

ዜግነትና ሀገራዊ መብት የሚገኘው በደም (ከወላጆች) እና በሕግ እንጂ በሃይማኖት ምዝገባ አይደለም። አንድ ሰው እምነቱን ስለቀየረ ብቻ፣ የቀደሙ አባቶቹ ከጥንት ጀምሮ የገነቡትን አገር ባለቤትነት አያጣም። ሃይማኖት የምርጫ ጉዳይ እንጂ የሀገር ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ አይደለም።

ለ) ታሪክን በሃይማኖት ብቻ የመመዘን ስህተት

የኢትዮጵያ ታሪክ የሃይማኖት ታሪክ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ፣ የግብርና፣ የቋንቋ፣ የኪነ-ህንጻ፣ የሉዓላዊነት፣ የንግድና የባህል ታሪክ ድምር ነው። በእነዚህ ሁሉ ታሪኮች ውስጥ የተሳተፉት ደግሞ ከሁሉም እምነት የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን እንጂ የአንድ ሃይማኖት
ተከታዮች ብቻ አይደሉም።

ሐ) 99% የ"መጤነት" እውነታ!

ከውጭ አገር የመነጨን እምነት መከተል ሰውን "መጤ" የሚያደርግ ከሆነ፣ 99% የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጤ ነው! ምክንያቱም ኦርቶዶክስ፣ እስልምና፣ ፕሮቴስታንት፣ ካቶሊክ፣ ሁሉም መነሻቸው ከመካከለኛው ምስራቅና ከውጭ አገራት የመጡ እምነቶች ናቸው።

መ) "እንግዶቹ እንኳን ደህና መጡ!"

በእርግጥም መጤ የምንላቸው ከሌላ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እምነቱን ያስተማሩንን የውጭ አገር ሰባኪያን ነው። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትልቅ ስፍራ የተሰጣቸውና ታቦት የተሰየመላቸው ታላላቅ አባቶች ሁሉም ከውጭ የመጡ ስደተኞች ነበሩ [6]፦

1️⃣  አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)፦ የመጡት ከሮም [6]

2️⃣ አቡነ ጴንጤሌዎን፦ የመጡት ከሮም [6]

3️⃣  አቡነ ገሪማ (ይስሐቅ)፦ የመጡት ከሮም [6]

4️⃣  አቡነ የማታ፦ የመጡት ከሶርያ [6]

5️⃣  አቡነ አፍጼ፦ የመጡት ከቱርክ (አናቶሊያ) [6]

6️⃣  አባ ሰላማ (ከሳቴ ብርሃን)፦ የመጡት ከሶርያ

7️⃣ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፦ የመጡት ከግብፅ

እኛ ኢትዮጵያውያን እነዚህን የእምነት መምህራን (የክርስትናም ሆነ የእስልምና) በስደትና በእንግድነት ሲመጡ መቀበላችን እንግዳ
ተቀባይና ደግ ህዝቦች መሆናችንን ያሳያል። መጤዎቹ መምህራን እንኳንም መጡ፤ እኛም እነርሱን በእንግድነት በመቀበላችን እንኮራለን!



⬅️ ኢትዮጵያዊነት የጋራ ቤታችን እንጂ የአንድ ወገን ወይም የአንድ እምነት ውርስ አይደለም። እምነትን መቀየር ታሪክን፣ አሻራን እና ዜግነትን አያሳጣም።

ስለዚህ፣ ይህንን አገርን የሚከፋፍል የ"ነባርና መጤ" የድንቁርና ትረካ ወደ ጎን ትተን፣ አገራችንን በሕግ የበላይነት፣ በዜጎች እኩልነትና በጋራ እሴቶቻችን ላይ በፅኑ መሰረት እንገንባት!

ቸር እንሰንብት!


©: አሕመዲን ጀበል

||
t.me/MuradTadesse
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from Nek Baritaay; Nee Barisa
👉Rob radeek lakal aban dooqa.  👇👇👇
«  مطرنا بفضل االله ورحمته»
«Rob neh radeh nooqobeh Yallih muxxoo kee kay racmatah».  
   Iyyaana .
Qaalam gineeh mahoodobisah yam rabbih Fayla Dabaqta.
   
👉 Kassiisi 👇👇👇👇

    Roobuk radim kee wayto cutuukaay, silaytuuy, Qhubuurut xaaqimaanamaay; Sinaamat akah xaaqimaanam kee   w.w. tanim sabab abaanam kaxxa shirki kinniimih taagah akak takkawsimnam faxximta.
-Tohih sabbatah Yallih muxxooy, Barakah nooqobe Iyyaanam faxximta. Alcamdulillaah Rabbil Qaalamiin.
    
         👇👇👇👇👇
   @Nekbaritaayneebarisa
🥰4👎1
ማነው መጤው?
~
ሙስሊሙ መብቱን በጠየቀ፣ ጭቆናን በተቃወመ፣ እምነቱን ባስተማረ ቁጥር "እናንተ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ስትገቡ አክብረን በተቀበልን እንዴት ውለታችን ይረሳል?" እያሉ በቅጥፈት ለሚመፃደቁ አካላት "እንዴ! እኛ እኮ ኢትዮጵያውያን እንጂ መጤዎች አይደለንም" እያሉ በከንቱ መድከም አያስፈልግም ብዬ በፅኑ አምናለሁ። ሰዎቹ እንዲህ አይነት አመክንዮ የሚገባቸው አይደሉም። ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ ነው። መፍትሔው ማጥቃት እንጂ መከላከል አይመስለኝም። በራሱ ቋንቋ አናግረው።

በዚህ ድንቁ ^ ርና ላይ በሰፊው የሚታወቁት በዋናነት የአንድ እምነት ተከታዮች ናቸው። እነሱ ናቸው "የእስላም አገሩ መካ፣ የአሞራ አገሩ ዋርካ" የሚል ምሳሌያዊ አነጋገር ፈጥረው ድንቁርናቸውን ከትውልድ ትውልድ የሚያሻግሩት። እንዴት አድርገው እንደሚጠርቧቸው እንጃ በዚህ ዘመን እንኳ አልተቀየሩም። የለውጥ ተስፋ የሚታይባቸውም አይደሉም።

አስቂኙ ነገር ደግሞ ራሳቸውን የአይ^ሁድ ዘር አድርገው መኮፈሳቸው ነው። ሃገሪቱን ለሰባት መቶ ዓመታት በላይ የቦጠቦጠው ራሱን "ሰለሞናዊ መንግስት" ብሎ የሚጠራው መዥገር ስርአትኮ ባህር ተሻግሮ የሰሎሞን ዘር ነኝ የሚል ነው። መጤ ነኝ ማለት አይደል ይሄ? አፄ ምኒልክ "ዳግማዊ" ምኒልክ የተባለው ጥንት ከንጉስ ሰለሞን የተገኘ "ቀዳማዊ" ምኒልክ ነበር ብለው ስለሚያምኑ ነው። "የናዝሬቱ እየሱስ፣ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ቃና ዘገሊላ፣ ቤተልሄም፣ እየሩሳሌም፣ ... " እያለ እምነቱን ከባህር ማዶ ጋር የሚያይዝ አካል እንዴት ሙስሊሞችን መጤ ሊያደርግ ይዳፈራል?!

የሙስሊሙን ኢትዮጵያዊነት መቀበል የከበዳቸው ጭንቅላቶች "ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት" የሚል ያረጀ ያፈጀ ተረት ዛሬም ይተርታሉ። ለመሆኑ እነሱ ዘንድ ኢትዮጵያ ማለት የቷ ናት? ለመሆኑ ኢትዮጵያ ሲሉ አፋርን፣ ሶማሊን፣ ሀረርን፣ ስልጤን፣ ከፊል ጉራጌን፣ ሰፊውን ኦሮሚያን፣ ሀላባን፣ አብዛኛው ወሎን፣ አብዛኛውን በኒሻንጉልን፣ ድሬዳዋን፣ አርጎባን፣ ... ይጨምራል ወይ? እስኪ እነዚህን አካባቢዎች ቆርጠው ያውጡና የደሴቷን ካርታ ይመልከቱ። ካርታው ላይ የሚታየው ቀዩ ክፍል ነው የሚቀራቸው። ከዚያ የቀራችሁን የክርስቲያን ደሴት ተመልከቷት! የምትዘምሩላት ኢትዮጵያ ይቺ ናት?

ለማንኛውም "በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል የሰለሞን ዘር ነን"፣ "ነገደ ይሁዳ ነን"፣ "የይሁዳ አንበሳ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት የምታምኑበት ከሆነ መጤዎች እንደሆናችሁ በራሳችሁ ላይ መስክራችኋል። እኛ ሙስሊሞች ዐረቦች ነን አላልንም። ኢትዮጵያውያን ነን። እናንተ "የሁ^ዶች ነን" ካላችሁ እኛ ነን የተቀበልናችሁ።

"አይ" ካላችሁ "አይ^ሁድ ነን" የሚለውን የአባቶቻችሁን ተረት ውሸት እንደሆነ አስረግጣችሁ ወርውራችሁ ጣሉ። ከዚያ በኋላ ራሳችሁን የኢትዮጵያዊነት አከፋፋይና ድርጎ ሰፋሪ አድርጋችሁ ማየታችሁን አቁሙ። የነውረኝነታችሁ ዳፋ ለደካሞች ይተርፋልና ጥፍራችሁን ሰብስቡ። በዚህ ዘመን እንዲህ አይነት የከረፋ ሃሳብ ስታንፀባርቁ ታንኩም ባንኩም በእጃችሁ በነበረበት የቀደመው ዘመን ያደረሳችሁትን ማሰብም ይሰቀጥጣል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
3
የልጆች ጉዳይ
~
* ክረምቱን በምን እያሳለፉ ነው? ሙሉ ቀን ከሳምንት ሳምንት በዋል ፈሰስ እንዳይባክኑ ቁርአን በመቅራት፣ ኪታብ በመማር፣ ሌሎች ተጠቃሚ ነገሮችን በመማር እንዲጠቀሙ ትኩረት እንስጣቸው።

* ትምህርት እናስመዝገብ። በዚህ ዘመን አለመማር ተራ ነገር አይደለም። ከተማ ውስጥ እየኖሩ ሳይማሩ ማደጋቸው ተፅእኖው ከባድ ስለሆነ ኋላ በጣም ይጎዱባችኋል፣ ያዝኑባችኋልም ጭምር። ያለንበትን ሀገር፣ እንዲሁም የዘመኑንም ተጨባጭ በጥልቀት በማሰብ መወሰን ይሻላል። በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ተፅእኖ ይሉኝታ አያስይዛችሁ። ደጋግማችሁ አስቡበት።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
"የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ።

"በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما
"አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165]

"ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" ማለት አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው።

ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሁ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ።

ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦

ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት።

በነገራችን ላይ እንኳ ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ሌላ ጥግ ማድረግ። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው።

አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። እንኳን ሌላ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
አሳሳቢ የክረምት መልእክቶች
~
1. ልጆች የተሻለ ሰፊ ጊዜ የሚያገኙበት ጊዜ እንደመሆኑ ቁርኣን እንዲቀሩ፣ ኪታቦችን እንዲማሩ መስራት ይገባል።

2. በቅጡ የሚለበስ የሌላቸው ወገኖችን በዚህ በብርድ ወቅት ካለን ብናካፍል ትልቅ ሶደቃ ነው።

3. በየጎዳናውና ጉሊቱ ትናንሽ ነገሮችን ለመሸጥ ኩርምት ብለው የተቀመጡ እናቶችን የያዙትን በመግዛት፣ ከተቻለ ከዚያም አለፍ ብሎ ማገዝ ብዙ ሰዎች የሚዘነጉት ሶደቃ ነው።

4. ለቀጣይ የትምህርት ዓመት አቅመ ደካማ ተማሪዎችን በማሰብ ያለፉ ተማሪዎችን የደምብ ልብሶች (ዩኒፎርም) መሰብሰብ እና አስተባብሮ ደብተር በመግዛት ላይ በየአካባቢው ብንረባረብ ትልቅ ስራ ነው። አገሩን የሚወድ አገር ተረካቢ ትውልድ ላይ ይሰራል።

5. ብዙ የሀገራችን አካባቢዎች በዚህ ክረምት ዝናብ በመጥፋቱ ህዝብ ጭንቅ ላይ ነው። አጥብቀን ዱዓእ እናድርግ።

6. ዝናብ ባለበት አካባቢ ያላችሁ ኢማሞችና ኸጢቦች በሶላታችሁም፣ በኹጥባችሁም ታዳሚውን እያሰባችሁ፣ ወቅቱን እያገናዘባችሁ ፈጽሙ። በናንተ ያፈፃፀም ችግር ሰው ዝናብ እንዳይመታው ተጠንቀቁ። ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦች እና መሰል ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ለማህበረሰብ ግንዛቤ ስጡ። ኹጥባ ማለት ማህበረሰብን መቀየሪያ ሁነኛ መድረክ ነውና እየተጠቀማችሁበት መሆናችሁን ገምግሙ።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰበር፣ የአዛውንቶች ያለ ጧሪ ቀባሪ መቅረት፣ የሃገር መቆርቆዝ የማያስደነግጠው ልብ ከጠላት በላይ ጨካኝ ነው። ሰው ሌሎች ላይ ከደረሰው፣ ከጎረቤቱ ይማራል። እሱ ቢቀር እንዴት በራስ ላይ ከደረሰው መማር ያቅታል?!

ለማንኛውም ወጣት ሆይ! ለራስህ እወቅበት። በስምህ የሚምለው ሁሉ ተቆርቁሮልህ እንዳይመስልህ። ጀግና ጀግና የሚልህ ጀግና ስለሆንክ አይደለም። እየሸነገለህ ነው። ራሱንም ቤተሰቡንም ከእሳቱ አርቆ ነው አንተን የሚማግደው። ካንተ ሞት በኋላ ልጅህን፣ እናትህን ዞሮ አያይም። ግፋ ቢል ነገ ካንተ ሞት በኋላ የሰማእታት ሀውልት ብሎ የድንጋይ ክምር ቢያቆምልህ ነው። ይሄ ላንተም ለቤተሰብህም የሚጠቅመው ነገር የለም። ህዝብ ማደንዘዣ፣ ሌላ እልቂት ማቀጣጠያ እንጂ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ልብህን ለማን እንደምትሰጥ እወቅ!

የዱኑያ ምሽት ላይ እንደመሆናችንና የመሲሐድ'ደጃል መምጫም እንደመቃረቡ ዲኑ ላይ የሚጫወቱና እራሳቸው ተደናብረው ኡማውን የሚያደናብሩ ሰዎች በዝተዋል።

ማህበራዊ ሚዲያውም የራሱ ጥሩ ጎን እንዳለው ሁሉ ሰዎችን ማሳሳትና ግራ ማጋባት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

መችና ከማን የሸሪዓህ እውቀት እንደተማሩ የማይታወቅ ሰዎች በካሜራ (በስልክና ኮምፒዩተር) መስኮት ብቅ እያሉ የፈለጉትን ሐላል፣ የፈለጉትን ሐራም ብለው ያለ በቂ እውቀት በስሜትና በግምት በመናገር ብዙ አላዋቂዎችን ያሳስታሉ።

ከዚህም አልፎ ገና አዲስ ወደ ኢስላም የገቡ ወንድምና እህቶች እራሳቸው እንኳ ዲኑን በትክክልና በጥልቀት ሳይረዱ መደበኛ አስተማሪ ሆነው ቀርበው ኢስላምና ሙስሊሞችን ወክለው ሲናገሩና ሲከራከሩም ይታያል !!
ይህ በጣም ይገርማል፤ ያሳዝናልም! ይበልጥ የሚገርመው ደግሞ እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን እንደ ትልቅ አዋቂ ቆጥረው የሚከተሏቸውና ልባቸውን የሚሰጧቸው ሰዎች ሁኔታ ነው!!

ኢስላማዊ እውቀት የዲኑ/የእምነቱ አንድ አካል ነው፤ ከኔ ይሻላል ከሚሉት ሁሉ (ከየትም፣ ከማንም) እውቀትን ዝም ብሎ መቀበል እምነትን ሊያበላሽ፣ ማንነትና አስተሳሰብን ሊቀይር ይችላልና
ምላስና ድፍረት ስላለው ብቻ ራሱን በራሱ ጊዜ አስተማሪ አድርጎ የቀረበን ሁሉ ከመስማትና ከመከተል እንጠንቀቅ!!
ለአካላዊ ጤናችን ሃኪም ከምንመርጠው በላይ ለልብና ለእምነታችን መሪና መካሪ እንምረጥ።

ትልቁ መሲሐድ'ደጃል ከመምጣቱ በፊት ለሱ መንገድ የሚያመቻቹ ብዙ ትናንሽ ደጃሎች እንዳሉ ተነግሯል።

ቂያማ ሲቃረብ ሸይጣን በሰው ተመስሎ አስተማሪ ሆኖ እንደሚቀርብም ተገልጿልና ልብህን ለማን እንዳምትሰጥ/ጪ፣ የሸሪዓህ እውቀትን ከማን እንደምትቀስም/ሚ ጠንቅቀህ/ሽ እወቅ/ቂ።

የሸሪዓህ እውቀትን ከምንጩ ያልወሰደና በዑለሞች ያልተመሰከረለት የዩቱበር፣ የቲክቶከርና ፌስቡከር ... መጫወቻ እንዳትሆን/ኚ!!

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

ዛዱል-መዓድ
©: ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ?
~
መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ ቀደም ብየ ገልጬ ነበር። አሁን ደግሞ ለምን አላማ ጀመሩት የሚለውን ባጭሩ እዳስሳለሁ።
በግብፅ የአስዩጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶክተር ሐሰን ኢብራሂም ሐሰን እና በሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትምህርቶች ገምጋሚ የነበሩት ጦሀ አሕመድ ሸረፍ በጋራ በመሆን “አልሙዒዝ ሊዲኒላህ” በሚል ርእስ ስለ“ፋጢሚያዎቹ” ንጉስ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አንድ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ “አውደ - አመታት እና በዓላት” በሚል ርእስ ስር ያሰፈሩት ሃሳብ “መውሊድ ለምን አላማ ታስቦ ነው የተጀመረው?” ለሚለው ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡-

“(ንጉሱ) አልሙዒዝ በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ቀን፣ በነብዩ ﷺ መውሊድ ቀን፣ በረጀብ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በሸዕባን መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በረመዷን መጀመሪያ ቀን ከሚያስተዳድራቸው ህዝቦች ጋር ይካፈል ነበር፡፡ ይህን የሚያደርገው

* የሱኒ፞ዮቹን ልብ ለማረጋጋት፣
* እንዲሁም በሱኒ፞ዮች መርሆዎችና በሺዐዎች እምነቶች መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በማሰብ ነው፡፡
* በተጨማሪም ይሄ አልሙኢዝ ሊዲኒላ፞ህ የንግስና ዘመኑን ያሸበረቀባቸውን እነዚህን በዓላት የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ እምነቶችን ለማሰራጨት ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሑሰይንን ዝክር ህያው ለማድረግ የዓሹራእ ቀንን ያከብር የነበረው፡፡ ልክ እንዲሁ የበርካታ አኢማዎችን መውሊድና ስልጣን ላይ ያለውን ገዢ መውሊድ በሚልም (የራሱን ልደት) ያከብር ነበር፡፡
* ልክ በዚህ መልኩ የህዝቦቹን ትኩረት ወደሱ ለመሳብና የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ መሰረታዊ እምነቶችን ለማሰራጨት እነዚህን በዓላት እንደ መዳረሻ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡” [አልሙዒዝ ሊዲኒ'ላህ፡ 284]

ስለዚህ መውሊድ የተጀመረው ለፖለቲካዊ ትርፍና የሺዐን እምነት ለማስፋፋት ዓላማ ነው ማለት ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ ገና፞፣ ሁዳዴ፣ …፣ የሺዐዎቹ የዓሹራእ በዓል፣ ገዲር ኹም፣ …፣ የእሳት አምላኪ መጁሳዎቹ ነይሩዝ ይከበሩ ከነበሩት በዓላት ውስጥ ነበሩ፡፡ የህዝብን ትኩረት ለመሳብ፣ ቅሬታ ውስጥ ያሉ ሱኒ፞ዮችን ልብ ለማረጋጋት በሂደትም ወደራሱ የሺዐ እምነት ሰዎችን ለማስገባት በማለም ነው፡፡ ቀስ እያለ በጉልበት ወደ ሺዐ እምነት መጣራት እንደተጀመረ ይታወስ፡፡ ስለዚህ አላማቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን የህዝብ ግፊቶች በማርገብ ይከተሉት የነበሩትን የኢስማዒሊያ ሺዐ እምነት ማስፋፋት ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ ዛሬ ሱፍዮች እንደሚያስቡት “የወሃብዮች” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው የታሪክ አጥኚዎች ድምዳሜ ነው፡፡

የመውሊድ ስርኣቱ ለእኩይ አላማ የታለመ ስለነበርም ነው ሶላሑዲን አልአዩቢይ ሺ0ዎችን አስወግዶ ግብፅን ሲቆጣጠር አስቁሞት የነበረው፡፡ መቼም እሱንም “ወሃቢ ነው” እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዳግም የተጀመረው ኋላ በመምሉካውያን ጊዜ ነው፡፡ የመውሊድ ተግባር እንደገና ሲመለስ ሌሎቹ በአላት የሌላ እምነት መሰረት ያላቸው ወይም ሺዐ-ዘመም ስለነበሩ በሱኒ፞ው አለም ገበያ አላገኙም፡፡

ዛሬም የሙስሊሞችን መብት የሚጨፈልቁ የፖለቲካ ኃይሎች አጉል ተቆርቋሪ ሊመስሉ ለመውሊድ የተለየ ሸፋንና ድጋፍ ሲሰጡ ማየት የተለመደ ነው። ብልጥ የሆነ ሰው ሊያስተውል ይገባል። አላህ ማስተዋሉን ይስጠን።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
1
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል።
ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል።
ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
የማለዳ መልእክት (45)
ለኸጢቦች እና ለዱዓቶች
~
የደዕዋ እና የኹጥባ መድረክ የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መድረክ ነው። የማህበረሰብን ንቃተ ህሊና ለመቀየር፣ ዲኑን ለማስተማር፣ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለማንቃት እጅግ የላቀ ቦታ ነው። ግን እንደሚገባ እየተጠቀምነው ነው ወይ? መድረኩ ነብያዊ አማና ነውና አማናውን እየተወጣን ነው ወይ? ለመድረኩ የሚመጥን አቅምና ዝግጅትስ አለን ወይ? ሐቅን ለመናገር፣ ማህበረሰብን ለመጠበቅ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎታቸውን ተከትለን ነው የምንፈሰው ወይስ አላህን በማሰብ፣ ለሐቅ በመቆርቆር፣ ዘላቂ ጥቅምን በማስቀደም በጀግንነት እንጓዛለን? ኃላፊነትን ባለመወጣት ከመጠየቃችን በፊት ከራሳችን ጋር ሂሳብ እንስራ።

1. ወደ ህዝብ ከመቅረባችን በፊት በቂ ዝግጅት እናድርግ፣ አቅማችንን እናዳብር። ሳይዘጋጁ መቅረብ ታዳሚን መናቅ ነው። ቦታውንም ክብር ማሳጣት ነው።

2. መሰረታዊ የኢስላም ርእሶችን ቅድሚያ እንስጥ። አርካኑል ኢማን፣ አርካኑል ኢስላም፣ ተውሒድና ሺርክ፣ ሱናና ቢድዐ፣ ከባኢረ ዙኑብ፣ ስነ ምግባር፣ ኢስላማዊ ቤተሰብ፣ እንደ ኡማ ሊኖረን የሚገባ መተዛዘንና መደጋገፍ፣ ዘረኝነት፣ እንደ ጫትና ሲጋራ ያሉ ጎጂ ሱሶች፣ ወዘተ. የህዝብን ቁጣና ኩርፊያ ሳንፈራ ግን ደግሞ ባማረና በማያስበረግግ መልኩ ደጋግመን እናስተምር።

3. ርእስ መረጣ ላይ የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተልን አንፍሰስ። ትኩረታችን የሚጠቅማቸውን መስጠት ይሁን። ደዕዋ ሰው መለወጫ እንጂ መዝናኛ መድረክ አይደለም። የሰዎችን ስሜትና ፍላጎት እየተከተለ የሚፈስ አስተማሪ ፈሪና አስመሳይ እንጂ እውነተኛ ተቆርቋሪ አይደለም።

4. እንደ ዘመን በህዝብ ላይ የተጋረጡ አደጋዎች እና ወቅታዊ ክስተቶች ሲኖሩ አቅጣጫ መስጠት ያስፈልጋል። ለዚህ ደግሞ በቂ ንቃትና ዝግጅት ይፈልጋል። ንቃትና ዝግጅት ማለት እንግሊዝኛ መቀላቀል አይደለም። በሚዲያ የሰማነውን ዜና ማስተጋባትም አይደለም። የዳዒ ኃላፊነት እንደ ጋዜጠኛ ክስተቶችን ማንልበልና መተንተን አይደለም። መድረኮችን የፖለቲካ መደስኮሪያ እያደረጉ ማርከስ ንቃት አይደለም። ከዳዒ የሚጠበቀው ነገሮችን በኢስላም መነፅር በመመልከት ህዝብን ማረጋጋት፣ ሰዎችን ወደ አላህ መመለስ፣ በወቅታዊ ክስተቶች ከአቅማቸው በላይ በመግባት እንዳይዋጡ ማሳሰብ ነው።

እንዳጠቃላይ ለመድረኩ የሚመጥን ትኩረት እንስጥ፤ አቅም እናዳብር፤ ዝግጅት እናድርግ፤ ጀግንነትን እንላበስ፤ ሐቀኛ ተቆርቋሪነትን ሁሌም እናስብ። ሰላም።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 30/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor