ታማኝ መረጃ
850 subscribers
1.77K photos
48 videos
108 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
በህወሃት አፈሳ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ 📌

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን የጀመረውን የወጣቶች አፈሳ አጠናክሩ በአዲስ ዓመት ዕለት አፈሳን ፈፅሟል። ይህንንም ተከትሎ በመቀለ ዙሪያ ተቃውሞ ሊቀሳቀስ ችሏል።

ጥቃት የመረረው ነዋሪ በሁለት አፋሽ የህውሀት ታጣቂዎች ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ ዕርምጃ መውሰዱ ታውቋል።

ይህ ዜና ከተሰማ ተመሳሳይ ህዝባዊ ዕርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ይቀጣል በሚል ህወሃት ጉዳዩ እንዳይናፈስ እየጣረ መሆኑንም አረጋግጠናል።

ቡድኑ የመጨረሻ የውድቀት ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን በዚህ ተግባሩ ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል።
የልደቱ ብሶት 😅😂

የቀድሞ ፖለቲከኛ የአሁኑ ድምፃዊ ልደቱ አያሌው በTrack 2 ''ስደት '' የሚል ሙዚቃው '' ስደት አደረገኝ ነጭናጫ ሆደ ባሻ ፤ የማደርገውን አሳጣኝ '' እያለ ኑሮ ዳገት እንደሆነበት በዜማ ገልጿል።

ሰሞንኛው አንዴ “ሙዚቀኛ”፣ አንዴ “ዩትዩበር” ልሁን እያለ መነሳቱም የዚህ መቅበዝበዙ ማሳያ መሆኑን ግልጽ አድርጎልናል።

ከዚህ ሁሉ ብሶት ልደቱ አንድ ሰሞን ከመንግስት ጋር በራስህ ጥያቄ ጀምረህ ያቋረጥከውን ንግግር ዳግም በማነሳሳት በአመጽ ሳይሆን በሰላማዊ ትግል ለመታገል ተስማምተህ ለምን ወደ ሃገርህ አትመለስም

ይሄ ድምፃዊነት ሙያው አላወጣ ሲል ደሞ፣ ፊልም ወደ መስራት ሳትሸጋገር በፊት ሰላማዊ ውይይትን ጠበቅ አድርገ ብትይዝ ይሻልሃል🤗
ድሮንን ሽሽት ታጣቂዎች ነፃ መሬት እየወረዱ ነው📌

ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን ትግራይን ዳግም የደም መሬት ለማድረግ የሚያደርገውን አደገኛ እንቅስቃሴ በመቃወም እራሱን ከቡድኑ አግልሎ፣ ሲደራጅ የቆየው ሀይል በከፍተኛ ደረጃ የህወሃት ታጣቂዎች እየጎረፉለት ነው።

በፀጥታ ኃይላችን በተከታታይነት እየተወሰደ የሚገኘውን የድሮን ዕርምጃ ሽሽት ስፍር ቁጥር የሌለው የህውሃት ታጣቂ እየተበተነ ወደ ሃራ መሬቱ ሃይል እየተቀላቀለ ይገኛል።

ለአብነትም ለማንሳት ያህል፣ ከሰሞኑ በኮረም በተወሰደው ዕርምጃ ከጥቃቱ በተዓምር የተረፉ የአርሚ 11 በርካታ ታጣቂዎች ወደ ሀራ መሬቱ ሀይል መቀላቀላቸው ታውቋል።

ቡድኑ በየዕለቱ በሚቀላቀሉት ልምድ ያላቸው ታጣቂዎች ምክንያት ህወሓት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመወሰድ የሚያስችለውን አቅም አካብቷል።
ሰበር መረጃ🚨

ህወሃት ኔትወርክ ለማቋራጥ ትራንስፈርመሮችን እያነሳ ነው

ፅንፈኛው የህወሃት ቡደን ትግራይን የሀዘን እና የጨለማ ማቅ ውስጥ ለመክተት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል 😡

አሁን ከስፍራው በደረሰን መረጃ ህወሓት በሻዕቢያ ትዕዛዝ መሰረት በመላው የትግራይ ክልል የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ የኢትዮ ቴሌኮም ትራንስፈርመሮችን ማንሳት ጀምሯል።

እንደ መነሻነት በእዳጋ ሃሙስ ፣ አቢይ አዲ ፣ ሀገረ ሰላም ፣ ራማ እና ዛጊር ማንሳቱም ተሰምቷል።

ይሄም ቡድኑ ለጦርነት በምን ደረጃ ዝግጅት ላይ እያደረገ እንደሚገኝ የሚያመለክት ነው።
1
የህወሃት ሚስጥራዊ ሰነድ የፋኖን ውሳኔ ሊያስቀር ይገባል‼️❗️

ከድል በኋላ እንዴት የጥምረት ሃይሎችን አጥፍቶ ብቻውን ነገሮችን መቆጣጠር እንዳለበት የሚያትት የህውሃት ሚስጥራዊ ሰነድ ሾልኮ ወጥቷል።

ሰነዱ ፅንፈኛው ፋኖ ከህወሃት የመሰረተው የባሪያ እና ገዢ ጥምረት ውድቀቱን እንጂ ስኬትን እንደማያመጣለት እንዲረዳ የሚያስችለው ነው።

በመሆኑም የዚህ ጥምረት አቀንቃኝ የሆኑት የፋኖ አመራሮች በይፋ ከጥምረቱ የማግለል ወሳኝ ዕርምጃን በአስቸኳይ ሊወስድ ይገባል በሚል በብዙሃን ደጋፊዎቹ ዘንድ ሳይቀር ሃሳብ እየተሰጠበት ይገኛል።

ህወሃት “ጓዴ” የሚላቸውን የመካድ የካበተ ልምድ ያለው በመሆኑ፣ ከፋኖ በተጨማሪ የህዝብን ስሜት ወደኃላ ጥሎ ለደብረፅዩን የተንበረከከው ኦነግ ሸኔ ሳይረፍድ ሊነቃ ይገባል።
ኢራን የኢትዮጵያን የቀይ ባህር ጥያቄን ትደግፋለች 🇪🇹🇪🇹🇪🇹 🇮🇷🇮🇷🇮🇷

ኢትዮጵያ ያላትን ቀጠናዊ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ እና የአፍሪካን የብልፅግና ፍላጎት በማጣመር የቀይ ባህር የባህር በር ተደራሽነትን እና የጋራ ተጠቃሚነት ጥያቄዋን አጥብቃ እየጠየቀች ትገኛለች።

ሃያላን በሙሉ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ፍትሃዊ እንደሆነ በሙሉ ድምጻቸው እየመሰከሩ ይገኛሉ።

በዚህም መሰረት ኢራን የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጥያቄን እንደምትደግፍ ይፋ አድርጋለች ፤ ኢትዮጵያ በሰላማዊ ድርድር እና ሕጋዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት ለቀጠናው ሰላምና ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን ገልጻለች።
ህወሃት ኔትወርክ የሚያቋርጥበት ምክንያት ... 📌

በፅንፈኛው ህወሃት ምክንያት ትግራይ ክልል ላይ የጦርነት ስጋቶች መኖራቸው የሚታወቅ ነው።

ትላንት እንደዘገብነው ህወሃት በክልሉ የኢንተርኔትና ኔትወርክ አገልግሎት እንዲቋረጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል።

ቡድኑ ይህን ለማድረግ ዋነኛ ምክንያት የሚፈጽማቸው ግፎች ተቀርጸው እየተሰራጩ የአለማቀፍ ማህበረሰቡን ጫና እያስከተሉበት ስለሆነ ነው።

በተጨማሪም በተከታታይነት በሚወሰድው ህግ የማስከበር እርምጃ፣ ለድሮን ጥቃቱ ኢላማነት እየተጋለጥን የሚገኘውም ስልኮች ላይ በሚገኙ GPS ነው በሚል መነሻነት እንደሆነ ታውቋል።
“ህዝብን ለመካስ ዝግጁ ነን” እጅ የሰጡ ታጣቂዎች

በሰሜን ጎንደር ዞን በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 34 የፋኖ ታጣቂዎች ግጭቱ የሀገርን ኢኮኖሚ የሚጎዳ፣ የሕዝብን ሰቆቃ የሚያራዝም መሆኑን በመረዳት የሰላም አማራጭን ተቀብሏል።

የትጥቅ ትግሉ ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ጥምረት በመፍጠር የግለሰቦችን ጥቅም ለማስከበር የሚደረግ፤ በታጣቂዎች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት የጎላበት እና ዓላማ የሌለው መሆኑንም አንስቷል።
"የኛ ጫካ መግባት እርስ በርስ ከመጠፋፋትና ህዝባችንን ከመበደል ያለፈ ምንም የፈየደው የለም ፤ አሁን ተጸጽተናል ህዝባችንንም ለመካስ ዝግጁ ነን" ሲሉም ተናግሯል።

በቀጣይ ሰላምን ለማጽናት እና በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የሰላምን አማራጭ እንዲቀበሉ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጿል።
👍2
የትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ወደ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሊዘዋወሩ ነው 📌

ህውሓት በክልሉ የፈጠረውን ሁከት ተከትሎ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መቀጠል ስላልቻሉ ወደ ሌሎች ክልሎች ወደሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በጊዜያዊነት እንዲዛወሩ ተወስኗል።

ጦርነትና ግጭትን በመሸሽ ከትግራይ ክልል የወጡ ተማሪዎች በሰላም የመማር መብት ያላቸው በመሆኑ ትምህርታቸው ሳይስተጓጎል እንዲቀጥሉ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩ ተገቢ እና የሚደነቅ ነው።

ህወሃት ለከተሞቹ የንግድ እንቅስቃሴ ትልቅ አስተዋጾ ያላቸው ተማሪዎች ፣ መምህራንና ሠራተኞች ከክልሉ እንዲቀሩ በማድረግ የንግድ እንቅስቃሴውን በቀጥታ እየጎዳ፣ ዩንቨርሲቲዎችን ከትምህርታዊ ተልዕኮ ከማስተጓጎል በተጨማሪ የክልሉን ነጋዴና ኢኮኖሚ ዋጋ እያስከፈለ ነው።
👍1
አስረስ ማረ ከፅምዶ ጋር ፍቺ ሊፈፅም ነው 📌

ጽምዶ የአማራ ህዝብ ጥላቻ ያሳበደው ቡድን ነው፤ ከዚህ ኃይል ጋር አብሮ መቆም ከክህደትም በላይ ነው።

በዚህም ምክንያት የጥምረቱ ቃል አቀባይ ነው በሚል እነ እስታሊን የሚያንቆለጳጵሱትና ስለ ጥምረቱ የሚሰጡ መግለጫወች ፊት አውራሪ የነበረው አስረስ ማረ ከጥምረቱ የማፈግፈግ ምልክት አሳይቷል።

አስረስ በጎጃም አፋብን ውስጥ እየበረታ የመጣውን የጽምዶ ተቃውሞ ተከትሎ ወደኃላ ማለት መጀመሩና ስለጥምረቱ በየሚድያወች ሃሳብ ከመስጠት መቆጠቡ ታውቋል።

በዚህም ከሰሞኑ የአማራ ሃይሎች ስለጥምረቱ ያደረጉት ዝምታ ያሰጋው ህውሃት የወሎ ፈረሱን ምሬ ወዳጆን ወጥቶ ስለጽምዶው እንዲያሟሙቅ በመሰየም በአንከር ሚድያ ላይ ይዞት ብቅ ብሎ ታይቷል።
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/AYuWGcpMojY?si=UgH185xf3vp77i4S»