ታማኝ መረጃ
853 subscribers
1.76K photos
48 videos
107 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
ከአስመራ በላይ የኤርትራ ወጣቶች አዲስ አበባ ላይ ያለ ስጋት ይኖራሉ✍️

እንደሚታወቀው በኢሳያስ አገዛዝ የኤርትራ ወጣቶች ተስፋ ቆርጠው ወደ ሌሎች ሀገራት በከፍተኛ ደረጃ ይሰደዳሉ።

ከአምባገነንነት ውጪ በሥልጣን ሽግግርና በትምህርት የማያመነው የሻዕብያ አገዛዝ ሕዝብን ከሕዝብ ለመለያየትና ስልጣኑን ለማስቀጠል ሲል ኢትዮጵያን እንደ ስጋት አድርጎ ለኤርትራ ህዝብ ይስላል።

ሆኖም እውነታው ግን አገዛዙ በሚፈጥረው በደልና መከራ ምክንያት ሀገራቸውን ትተው የተሰደዱ ከ4000 በላይ የኤርትራ ወጣቶችና ቤተሰቦቻቸው ኢትዮጵያን እውነተኛ ቤታቸው በማድረግ በሰላም እየኖሩ መሆኑ ነው።

ከመንግስታቸው ያጡትን ነፃነት እና ዕድገት እዚህ በማግኘታቸው ተስፋቸው ለምልሟል።
የኦባሳንጆ ምላሽ 📌

ክቡር ኦሊሶንጆ ኦባሳንጆ በጽህፈት ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ የህወሃት ቡድን የእሳቸውን የአሸማጋይነት እና የሰላም ጥረት ጥላሸት ለመቀባት ያቀረበውን ሃሰተኛ ክስ ኮንኗል።

ቡድኑ ትኩረትን ለመሳብ ሲል ብቻ ሚስጥራዊ የሆኑ የውይይት መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረጉን “ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት” በማለት ገልጿል።

የፕሪቶሪያው ስምምነት በአፍሪካ ኅብረት ከፍተኛ የመልዕክተኞች ኮሚቴ እና በቁልፍ ዓለም አቀፍ አጋሮች የአፈጻጸም ሂደቱን በህወሃት ምክንያት አንስቷል።

አክለውም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰቡ በእኒህ ግትሮች የፀረ_ሰላም አቋም የትግራይ ህዝብ ዳግም ለስቃይ እንዳይዳረግ ሁኔታውን በቅርብ እንዲከታተል ጥሪ በማቅረብ ቡድኑን ዓለማቀፍ ጫና ውስጥ የሚያስገባ ጥብቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያን የምክክር ሂደት አድንቋል🤩

በጄኔቫ እየተከናወነ ባለው 63ተኛው የተመድ የሰብአዊ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን የተመለከተ ሪፖርት አቅርቧል።

በዚህም በሃገሪቱ የተደረገውን ምርጫም ሆነ የምክክር ሂደት አድንቋል እንዲሁም ሙሉ በሙሉ እንደሚቀበለው አሳውቋል።

ህብረቱ ምርጫው እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርቧል፤ እንዲሁም ብሄራዊ ምክክሩን ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆዩ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና አስተዳደራዊ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት በምታደርገው ጥረት ትልቅ ምእራፍ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በሃገሪቷ ካሉ የግጭት ሂደቶች ጋር ተያይዞ የፕሪቶርያ ስምምነትን አደጋ ላይ ለመጣል የሚደረጉ እንቅስቃሴወች እንዲቆሙ በመጠየቅ ፣ ከትግራይ በተጨማሪ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በሲቪሊያን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አካላት ላይ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪውን አቅርቧል ።
👍1
ሸኔ ያቃጠላቸው ነዳጅ የጫኑ ተሸከርካሪዎች

ሸኔ የኦሮሞ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት መሆኑን በተግባሩ እያረጋገጠ ነው 😡 ህዝቡን በመውጋት እና መሰረት ልማቶችን በማጥፋት አከባቢውን የሽብር ቀጠና ለማድረግም እየሰራ ነው።

ለአብነትም፣ አሸባሪው ቡድን በኦሮምያ ክልል ወለጋ በጊንቢና ቢላ አካባቢ ነዳጅ የጫኑ ብዛት ያላቸው ቦቴዎችን ማቃጠሉና 14 ሹፌሮችን አግቶ መውሰዱ ታውቋል።

ይህ ቡድን ለህዝብ አገልግሎት የሚውል በዶላር ተገዝቶ ከውጪ የሚገባን ነዳጅ ከነቦቴው ማቃጠሉ የፖለቲካ አላማ ሳይሆን የመሃይምነት እና የሽፍትነት አላማን የያዘ ጸረ_ህዝብ ቡድን መሆኑን የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም መላው የኦሮሞ ህዝብ በተለይም ወጣቶች ይህን አሸባሪ ቡድን ማጥፋት አለባቸው ብለዋል።
ቀጣይ ተረኛ እጅ የሚሰጠው ታውቋል📌

የፅንፈኛው ፋኖ አመራሮች እና ታጣቂዎች ሳይረፍድ አመለካከታቸውን ቀይረው ወደ ሰላም መንገድ እየመጡ ነው።

ከሰሞኑ የነበለጠ አዱኛን ወደ ተከዜ ዘብ መቀላቀል ዜና እንደሰማነው ሁሉ በቀጣይነት እነ አርበኛ መሳፍንት እና አርበኛ ደረጀ በላይ ታጣቂዎቻቸውን ይዘው ወደዚሁ ቡድን መቀላቀላቸውን በቅርብ መስማታችን እንደማይቀር የሚያረጋግጡ መረጃዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርገውን የሰላም መንገድ መሆኑን በመረዳት እጅ የሚሰጡ አባላትን ለመቀበል መንግስት ሁሌም ዝግጁ ነው 🙌
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/QAsvMVitfnM?si=Z6HZLujc6tNGcsZD»
እስክንድር ነጋ እየተፈለገ ነው📌

ከፅምዶ ጋር የሚሰሩት የአማራ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች ናቸው በማለት የተናገረው እስክንድር ነጋ በጥምረቱ አመራሮች እየተፈለገ ይገኛል።

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድኑ የፅምዶን ገፅታ አጠልሽቷል በማለት እስክንድር ነጋን ፈርጆታል። በዚህም የጎጃም ፋኖ ከገባበት ገብቶ በመያዝ እንዲያስረክበው መጠየቁን ከታማኝ የመረጃ ምንጭ ሰምተናል።

ቡድኑ እስክንድርን ለሻዕቢያ አሳልፎ በመስጠት በአስከፊ እስር ቤቶች እንዲማቅቅ ሊያደርገው ማቀዱንም አረጋግጠናል።

እስክንድር አዲስ የመሰረተውን አደረጃጀት ይፋ ሳያደርግ በፊት ለማፈን ጥረት እየተደረገም ይገኛል።
በህወሃት አፈሳ ምክንያት የተቀሰቀሰው ተቃውሞ 📌

ፅንፈኛው የህወሃት ቡድን የጀመረውን የወጣቶች አፈሳ አጠናክሩ በአዲስ ዓመት ዕለት አፈሳን ፈፅሟል። ይህንንም ተከትሎ በመቀለ ዙሪያ ተቃውሞ ሊቀሳቀስ ችሏል።

ጥቃት የመረረው ነዋሪ በሁለት አፋሽ የህውሀት ታጣቂዎች ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ ዕርምጃ መውሰዱ ታውቋል።

ይህ ዜና ከተሰማ ተመሳሳይ ህዝባዊ ዕርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ይቀጣል በሚል ህወሃት ጉዳዩ እንዳይናፈስ እየጣረ መሆኑንም አረጋግጠናል።

ቡድኑ የመጨረሻ የውድቀት ምዕራፍ ላይ የሚገኝ መሆኑን በዚህ ተግባሩ ብቻ ማረጋገጥ ይቻላል።
የልደቱ ብሶት 😅😂

የቀድሞ ፖለቲከኛ የአሁኑ ድምፃዊ ልደቱ አያሌው በTrack 2 ''ስደት '' የሚል ሙዚቃው '' ስደት አደረገኝ ነጭናጫ ሆደ ባሻ ፤ የማደርገውን አሳጣኝ '' እያለ ኑሮ ዳገት እንደሆነበት በዜማ ገልጿል።

ሰሞንኛው አንዴ “ሙዚቀኛ”፣ አንዴ “ዩትዩበር” ልሁን እያለ መነሳቱም የዚህ መቅበዝበዙ ማሳያ መሆኑን ግልጽ አድርጎልናል።

ከዚህ ሁሉ ብሶት ልደቱ አንድ ሰሞን ከመንግስት ጋር በራስህ ጥያቄ ጀምረህ ያቋረጥከውን ንግግር ዳግም በማነሳሳት በአመጽ ሳይሆን በሰላማዊ ትግል ለመታገል ተስማምተህ ለምን ወደ ሃገርህ አትመለስም

ይሄ ድምፃዊነት ሙያው አላወጣ ሲል ደሞ፣ ፊልም ወደ መስራት ሳትሸጋገር በፊት ሰላማዊ ውይይትን ጠበቅ አድርገ ብትይዝ ይሻልሃል🤗
ድሮንን ሽሽት ታጣቂዎች ነፃ መሬት እየወረዱ ነው📌

ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን ትግራይን ዳግም የደም መሬት ለማድረግ የሚያደርገውን አደገኛ እንቅስቃሴ በመቃወም እራሱን ከቡድኑ አግልሎ፣ ሲደራጅ የቆየው ሀይል በከፍተኛ ደረጃ የህወሃት ታጣቂዎች እየጎረፉለት ነው።

በፀጥታ ኃይላችን በተከታታይነት እየተወሰደ የሚገኘውን የድሮን ዕርምጃ ሽሽት ስፍር ቁጥር የሌለው የህውሃት ታጣቂ እየተበተነ ወደ ሃራ መሬቱ ሃይል እየተቀላቀለ ይገኛል።

ለአብነትም ለማንሳት ያህል፣ ከሰሞኑ በኮረም በተወሰደው ዕርምጃ ከጥቃቱ በተዓምር የተረፉ የአርሚ 11 በርካታ ታጣቂዎች ወደ ሀራ መሬቱ ሀይል መቀላቀላቸው ታውቋል።

ቡድኑ በየዕለቱ በሚቀላቀሉት ልምድ ያላቸው ታጣቂዎች ምክንያት ህወሓት ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመወሰድ የሚያስችለውን አቅም አካብቷል።
ሰበር መረጃ🚨

ህወሃት ኔትወርክ ለማቋራጥ ትራንስፈርመሮችን እያነሳ ነው

ፅንፈኛው የህወሃት ቡደን ትግራይን የሀዘን እና የጨለማ ማቅ ውስጥ ለመክተት ቆርጦ የተነሳ ይመስላል 😡

አሁን ከስፍራው በደረሰን መረጃ ህወሓት በሻዕቢያ ትዕዛዝ መሰረት በመላው የትግራይ ክልል የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነቶችን ሙሉ በሙሉ ለማቋረጥ የኢትዮ ቴሌኮም ትራንስፈርመሮችን ማንሳት ጀምሯል።

እንደ መነሻነት በእዳጋ ሃሙስ ፣ አቢይ አዲ ፣ ሀገረ ሰላም ፣ ራማ እና ዛጊር ማንሳቱም ተሰምቷል።

ይሄም ቡድኑ ለጦርነት በምን ደረጃ ዝግጅት ላይ እያደረገ እንደሚገኝ የሚያመለክት ነው።
የህወሃት ሚስጥራዊ ሰነድ የፋኖን ውሳኔ ሊያስቀር ይገባል‼️❗️

ከድል በኋላ እንዴት የጥምረት ሃይሎችን አጥፍቶ ብቻውን ነገሮችን መቆጣጠር እንዳለበት የሚያትት የህውሃት ሚስጥራዊ ሰነድ ሾልኮ ወጥቷል።

ሰነዱ ፅንፈኛው ፋኖ ከህወሃት የመሰረተው የባሪያ እና ገዢ ጥምረት ውድቀቱን እንጂ ስኬትን እንደማያመጣለት እንዲረዳ የሚያስችለው ነው።

በመሆኑም የዚህ ጥምረት አቀንቃኝ የሆኑት የፋኖ አመራሮች በይፋ ከጥምረቱ የማግለል ወሳኝ ዕርምጃን በአስቸኳይ ሊወስድ ይገባል በሚል በብዙሃን ደጋፊዎቹ ዘንድ ሳይቀር ሃሳብ እየተሰጠበት ይገኛል።

ህወሃት “ጓዴ” የሚላቸውን የመካድ የካበተ ልምድ ያለው በመሆኑ፣ ከፋኖ በተጨማሪ የህዝብን ስሜት ወደኃላ ጥሎ ለደብረፅዩን የተንበረከከው ኦነግ ሸኔ ሳይረፍድ ሊነቃ ይገባል።