ታማኝ መረጃ
854 subscribers
1.76K photos
48 videos
107 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
🚨ህወሃት ለውትድርና የአፈሳቸውን ወጣቶች እያስራበ ነው🚨

ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች በፅንፈኛው ህወሃት በግዳጅ ታፍሰው ወደ ጦር ካምፕ የተወሰዱ ወጣቶች በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

ቡድን የትግራይን ወጣት በገፍ እያፈሰ መሆኑን ተከትሎ የሚታፈሰውን ወጣት በአግባቡ ማሰልጠንም ሆነ መመገብ አልቻለም።

በዚህም የታፈሰው ወጣት ለከፍተኛ ርሃብ እየተዳረገ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ወታደራዊ ስልጠናውም ለይስሙላ የ8 ቀን ብቻ መሆኑ ከውስጥ በሚወጡ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።
2
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/JOHkkcFSCXo»
“ግብፅ የኢትዮጵያን መብት ልታከብር ይገባል” አምባሳደር ቲቦር ናጊ💯

ግብፅ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በልማት ለመጠቀም ያላትን መብት ልታከብር እንደሚገባ የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ከpeoples of Africa ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውቋል።

አክለውም ግብፅ በዓባይ ውሃ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖራት የሚገባ ይመስል የምትከተለው አቋም ከቀጠናውና እየተለወጠ ካለው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ጋር የማይጣጣም መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ግብጽ የፖለቲካ ድራማዋን ትታ ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ ከኢትዮጵያ ጋር መስማማት እንደሚበጃት ገልፀው እንደነበር አይረሳም።
👍2
“ላለፉት 50 ዓመታት የህወሃትን ጠባብ ፍላጎት ስንገነባ ነበር” አሉላ ሰሎሞን📌

አክቲቪስቱ አሉላ ሰሎሞን “በትግራይ ለ50 ዓመታት ሙሉ ብሔራችንን እየገነባን ነው የሚመስለን ነበር ፣ እውነተኛው ትልቁ ውድቀታችን ግን የህወሓት ቡድን ጠባብ ፍላጎትን እየገነባን መቆየታችን ነው” በማለት የእስካሁን የህወሃት ጉዞ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅም እንደልነበር ገልጿል።

አያይዞም “ቡድኑ ሲያነጥስ እኛም አብረን ጉንፋን እንያዝ ነበር ፤ ይህም ማለት ትግራዋይ ሃይማኖቱንና ብሔሩን ትቶ አንድን ቡድን እንዲያመልክ ተደርጓል ማለት ነበር” ሲል ህወሃት በህዝቡ ስነ ልቦና ላይ ሲሰራ የነበረውን የተቀነባበረ ፕሮፖጋንዳ እንደነበር አስረድቷል።

የትግራይ ህዝቡ ከህወሃት ጋር ያለውን ቁርኝነት መበጠስ እንደሚገባው አሉላ አሳስቧል።
1
“ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም” 📌

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም” በማለት"ስለ ጽምዶ" ያላቸውን ምልከታ አጋርቷል።

አክለውም በጽምዶ ስም የተሰባሰቡት አካላት መሠረታዊ የርዕዮተ-ዓለም እና የፖለቲካ ዓላማ ልዩነት ስላላቸው፣ የፈጠሩት ጥምረት የትም ሊደርስ እንደማይችልና ውጤት እንደማያመጣ አስረድተዋል።

እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን እና ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግሯል።

ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗንም ፕሮፌሰር አስታውሷል።
👍2
በመቀሌ ከተማ ሓድነት ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት ጀነራል 📌

በህወሃት ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻ እና የውስጥ ክፍፍል ተባብሶ ቀጥሏል።

አብዛኛው የህውሃት ታጣቂና አመራር ጭምር የለውጡን ሃይል እየደገፈ ነው የሚል ፍርሃት እና ስጋት ውስጥ የገባው የህውሃት ከፍተኛ አመራር በጥርጣሬ ታጣቂዎችን በገፍ እያሰራ እና ወደማይታወቅ ቦታ እየወሰደ ይገኛል።

በዚህም ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ሸዊት ቢተውን “ታጣቂዎችን ወደ ነፃ መሬት አደራጅተህ ትልካለህ " በሚል ከእነ አጃቢዎቹና ሹፌሩ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት በመቀሌ ከተማ ሓድነት ፖሊስ ጣቢያ ማሰሩ ተሰምቷል።

ሌሎች አመራሮች ስልታዊ በሆነ መንገድ የማስወገድ ዘመቻ ለማካሄድ ቡድኑ ዕቅድ እንደወጣም ከውስጥ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
👍1
አሳዛኝ መረጃ🥲

ህወሃት በከፍተኛ ሁኔታ የቆሰሉ ታጣቂዎችን ረሽኗል

የህወሃት የጦር ጉዳተኞች ለሌላ አዳዲስ ጉዳተኞች ቦታ እንዲለቁ በማሰብ ከመቀለ ወደ አክሱምና አዲግራት እንዲዘዋወሩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ቁሰለኛ ታጣቂዎቹ ተቋማቱን ለቀን አንወጣም በማለት ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰሚ ጆሮን በለማግኘቱ በኃይል ከዋናው ከተማው እንዲወጡ ተደርጓል።

ይህም ሳያንስ፣ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የጦር ጉዳተኞችን በጀነራል ምግበይ ትዕዛዝ መሰረት “እነሱን ለማሳከም የምናባክነው ወጪ አይኖርም” በሚል በመንገድ ላይ እንዲወርዱ በመደረግ መረሸናቸው ተሰምቷል ።

ህወሃት ማለት ይሄ ነው 😡
👍1
🚨ለአልቡርሃን ጦር የሚሸጡ የትግራይ ታጣቂዎች በጨለማ እየታፈሱ ነው🚨

ህወሓት የትግራይን ህዘብ ለራሱ የፖለቲካ ዓላማና ትርፍ ከመጠቀም አልፎ፣ እንደሸቀጥ ወጣቶችን ለሌላ ሀገር ጦርነት የሚሸጥ የህዘብ ጠላት ድርጅት ነው።

ቡድኑ ያጋጠመውን የፋይናንስ ዕጥረት ለመቅረፍ የትግራይ ወጣቶችን በግዳጅ በማፈስ ለሱዳኑ አልቡርሃን ጦር በዶላር መሸጡን አጦጥፎ ቀጥሏል።

አሁን ደሞ በበዛ ጭካኔ በየከተሞቹ የምሽት መብራት እንዲቋረጥ በማድረግ በየቤትና መንገዶች ወጣቶችን እያፈሰ መሆኑ ተሰምቷል ።

የትግራይ ወጣቶች ራሳቸውን ከህወሓት ለማስመለጥ በጋራ ሊቆሙ ይገባል‼️‼️‼️
2
ወጣቶቹ በፈቃዳቸው ወደ ጦር ካምፕ የገቡት በሚል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሊሰራጭ ነው🚨

የትግራይ ወጣቶች ወደ ጦር ካምፖች ላለመግባት ከመኪና ላይ ሳይቀር እየዘለሉ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሞክር የሚያሳይ ቪዲዩ እየወጣ ባለበት በዚህ ወቅት ህወሃት የውሸት ድራማ በማዘጋጀት ለማደናገር ሊሞክር ነው።

ስብስቡ እየፈጸመ የሚገኘውን የአፈሳ ተግባር ተከትሎ የሚቀርብበትን ተቃውሞ ለማለዘብ በአፈሳ የተያዙ ወጣቶች እና ቤተሰቦቻቸውን በፈቃዳቸው ወደ ቡድኑ እንደተቀላቀሉ እንዲገልጹ በሃይል በማስገደድ ቪድዮ ቀርጾ በሚዲያዎች ለማሰራጨት ሰፊ ስራን እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።

ይህ ድርጊት የወጣቶችን ስቃይና የቤተሰቦቻቸውን እንባ እንደ መሳለቅ ነው የሚቆጠረው‼️
በደቡብ ጎንደር ዞን ከፅንፈኛው ፀድታለች💪

በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር ከነሐሴ 01 አስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ባካሄደው የተቀናጀ የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 51 ፅንፈኞች ሲደመሰሱ፣ 24 ቆስለዋል፣ 32 በተለያየ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከተደመሰሱት መካከል፣ ግዜ ግርማ የተባለ የፅንፈኛዉ ቡድን የአንዳቤቴ ብርጌድ የነሱ መዋቅር ፍርድ ቤት ኀላፊ፣ ሙጨ ታምር የአንበሳዉ ጋይንት ክፍለ ጦር አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ፣ ሽሻነዉ ጠጋ የአንበሳዉ ጋይንት ሻለቃ አዛዥ ይገኙበታል።

በተጨማሪ በዞኑ ባተካሄደው ሕግ የማስከበር እርምጃ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ ተተኳሾች፣ የመገናኛ ሬድዮዎች እና ከኅብረተሰቡ ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በእጁ አስገብቷል።
👍2
የጅምላ እስር እንደቀጠለ ነው🚫

ሀሳብን በጠበመንጃ ብቻ ማሸንፍ የሚችለው፣ ከእራሱ ውጪ ማንንም የማይሰማው የህውሃት ቡድን ‘’ ቡድኔን ይቃወማሉ፣ የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን ይደግፋሉ‘’ በሚል የጠረጠራቸውን ንጹሃን ማሰርና ማንገላታቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም በማዕከላዊ ዞን ታህታይ ማይጨው እና ዓዲግራት አዲ ከተማ ቡድኑን ይቃወማሉ ያላቸውን ከ56 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል።

ፅንፈኛው በጥርጣሬ ንፁኃን ላይ እያካሄደው ያለው የጅምላ እስር ለሚድያ ተጋላጭ እንዳይሆን በሚል በድብቅ እንደሚያካሂድ ለማወቅ ችለናል።
👍1
ሰበር መረጃ🚨

የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች የወጣ የእስር ትዕዛዝ📌

ህወሃት የሀሰት ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ በዋነኝነት የሚያደርገው በልሳን ሚዲያዎቹ በኩል እንደሆነ ይታወቃል።

ነጻና ገለልተኛ መሆን የሚገባቸውን ሚድያዎች የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለማድረግ በሚፈጽመው እንቅስቃሴ “ግዜያዉ አስተዳደሩንና ጦርነቱን ይቃወማሉ” በሚል የለያቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች ለማሰር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ቡድኑ በተደጋጋሚ አፈናና ዕስር እየፈጸመባቸው ለሚገኙ ጋዜጠኞች አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች ድምጽ ይሆኗቸው ዘንድ፣ የቡድኑ አፋኝነት ይፋ የማውጣት የንቅናቄ ስራ በተለይም በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ዘንድ ሊሰራ ይገባል።

የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ ህዝብን ላለማደናገር የወሰኑ ባለሙያዎችን ደሞ የትግራይ ህዝብ ሊያከብራቸው ይገባል
3
በአልጀዚራ የወጣው የሰላማዊት ጌታቸው ዘገባ✍️

ፀሐፊ ሰላማዊት ጌታቸው አማረ በአልጀዚራ የዜና አውታር ላይ ባወጣችው ጥልቅ ትንታኔያዊ ዘገባ፣ እ.ኤ.አ. በ2022 የተፈረመው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የትግራዩን ጦርነት ቢያስቆምም፣ ህወሓት መዋቅሩን ዳግም እንዲያደራጅ እና የፖለቲካ ቅርጹን እንዲቀይር ሰፊ ክፍተት መፍጠሩን ገልፃለች።

ሰላማዊት በአልጀዚራ ዘገቧ ላይ እንዳብራራችው ስምምነቱ ወታደራዊ ምልመላን እና የጦርነት ዝግጅትን በአንቀጽ ሰባት መሰረት በጥብቅ የሚከለክል ቢሆንም፣ በተግባር ግን ከ2024 ጀምሮ በትግራይ ውስጥ አዳዲስ ወታደራዊ ምልመላዎች እየተካሄዱ መሆኑን አንስታለች።

የኤርትራ ባለስልጣናት እና የህወሓት አመራሮች በዱባይ እና በዛላምበሳ አካባቢዎች ሚስጥራዊ ግንኙነቶችን ማድረጋቸውን ዘገባዋ አመላክቷል።
3
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/EUY5FShy1mk?si=KWhKGoN2bQuB1Yfb»
👉ትናንት “ኢትዮጵያ ተነሥታለች” ስንል ምኞት ሳይሆን ዛሬ በተጨባጭ ያረጋገጥነው እውነት ነው! ከታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማማ እስከ ዘመናዊው የኮሪደር ልማት፣ ከቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ እስከ ማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም ድረስ ሀገራዊ መነቃቃታችን በተግባር ተመስክሯል።

ይህ ለውጥ በዜጎቻችን የኑሮ ደረጃ፣ በከተሞች መዘመንና የሥራ ዕድል ላይ እውነተኛ ብርሃን ከመሆኑም በላይ ለልጆቻችን የነገ ብሩህ ተስፋን የሚሰንቅ ታላቅ ርዕይ ነው።

ከእንግዲህ ወደኋላ አንመለስም! በጀመርነው ታሪካዊ የማንሠራራት ጉዞ የልማት ኃይላችንን ይበልጥ በማፋጠን የኢትዮጵያን ትንሣኤ ወደ ዘላቂ ብልጽግና ከፍ እናደርጋለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍2
#ሰበር

በፅምዶ ተቃዋሚዎች የተመሰረተው አዲሱ የፋኖ አደረጃጀት ይፋ ሊሆን ነው

ለገቢ ማሰባሰቢያና በመፈራረስ ላይ የሚገኘውን የቡድኑን አቋም አንድ እናረጋለን ለህወሃት እንታተዝ በሚል የህልም እንጀራ የተመሰረተው የፅንፈኛው ፋኖ ድርጅቱ ውሎ ሳይዳር መፈራረስ እንደአጋጠመው ይታወቃል።

በዕልልታ የተመሰረተው የነ ዘመነ ኃይሉ ለበርካታ ታጣቂዎች መርገፍ እና እጅ መስጠት ምክንያት ሆኖ እንዲሁም ለብዙ የውስጥ ጦርነት አጋልጧ ሙሉለሙሉ ፈርሷል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ በነ እስክንድር ነጋና ሌሎች ፀረ_ጽምዶ አቋም በያዙ የፋኖ አባላት የተመሰረተው አዲሱ የፋኖ አደረጃጀት በቀጣይ ሳምንት በጎንደር የመጀምሪያ ጉባኤውን እንደሚያደርግና ምስረታውንም ለህዝብ እንደሚያበስር ተሰምቷል።
1
300 የትግራይ ወጣቶች ለአልቡርሃን ጦር ተልኳል📌

አልቡርሃን በአስመራ ቆይታቸው ወቅት የፈጥኖ ድራሹ ሃይል ባደረገው ሰፊ የማጥቃት እንቅስቃሴ በርካታ የህውሃት ታጣቂ በውግያ ማለቁን በመግለፅ ተጨማሪ ታጣቂን ጠይቋል።

ፅንፈኛው ህወሃት በተሰጠው ትዕዛዝ መስረት ተጨማሪ ከ300 በላይ የሚሆኑ ታጣቂዎችን ወደ ሱዳን መላኩ ታውቋል ።

አሁን ያላካቸውን ታጣቂዎች ከሱዳኑ ዉጊያ ጎን ለጎንም በዛው ሀገር ከመሸገዉ የአርሚ 70 ታጣቂ ቡድን ጋር በማዋሀድ ለቀጣይ የጦርነት ዝግጅት ሊጠቀመዉ ዕቅድ ማውጣቱን ከታማኝ ምንጭ ሰምተናል።
👍1
የትግራይ ሰላም ኃይል ታጣቂዎችን አስመርቋል🚨

የትግራይ ህዝብ በፕሪቶርያው ስምምነት ያገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለመንጠቅ የሚንቀሳቀሰውን ፅንፈኛውን የህወሃት ቡድኑ ለማጥፋት ነራመሬት የወረደው ኃይል በከፍተኛ ሁኔታ እራሱን እያደረጃ ነው።

በዚህም የትግራይ ሰላም ሃይል ግንባር ሶስት 50ኛ ዙር ሰልጣኞችን ነሃሴ 30/2018 ዓም በብቁ ሁኔታ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠና ሰጥቶ ማስመረቁ ተሰምቷል።

በተጨማሪ ኃይሉ በየቀኑ እየጎረፈ በሚገኘው የትግራይ ወጣት እና የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አማካኝነት እጅግ በጣም ጠንካራ የሚባል የተዋጊ ሃይልን እየገነባ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
👍2
በህወሃት ታንኮች ላይ እርምጃ ተወስዷል💪

ደጀኑ መከላከያ ሰራዊቱ የአየር ኃይል የድሮን ጥቃት በመጠቀም በህወሃት ጦር መከማቻዎች ላይ አርምጃ መውሰዱ አጠናክሯል።

በዚህም ሽሬ እንዳ ባጉና መውጫ ላይ በተወሰደ የተጠና የድሮን ጥቃት የቡድኑ ወታደራዊ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ (ኦራል) እና ታንኮች ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

ቀደም ሲል በራያ አዘቦ አካባቢ ከተካሄዱት ወታደራዊ (እንቅስቃሴዎች) ጋር ተዳምሮ፣ ይህ እርምጃ ለጦር አደረጃጀቶች ይደረጉ የነበሩ የሎጂስቲክስና የጦር መሳሪያ ዝውውሮችን ያወደመ ነው።

ይህ የድሮን ዕርምጃ ለ"ሴንትራል ኮማንድ" ስምሪት የሚያደርጉ የትኛውም የጦር መሳሪያ እና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴዎች ላይ በቀጣይነት የሚወሰድ እንደሆነም ታውቋል ።
👍2