ታማኝ መረጃ
853 subscribers
1.76K photos
48 videos
107 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
🚨ኤርትራ ለህወሃት የመሳሪያ ድጋፍ ማድረጓን አቁማለች 🚨

የኤርትራ መንግስት ለህወሃት ቡድን መካከለኛ የጦር መሳሪያ እና የታጣቂ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየት የሚታወቅ ነው።

አሁን ግን ቡድኑ ውስጥ ለውስጥ እያደረገ ይገኛል የተባለውን ድርድር ተከትሎ ድጋፉን ለማቆም መወሰኑ ታውቋል።

ሻዕብያ፣ ድርድሩ ከተሳካና ከፌደራል መንግስቱ ጋር ከተሰለፈ ዞሮ ራሴ ላይ ስጋት ሊሆንብኝ ይችላል በሚል ህውሃት የገዛቸው ድሮኖችን ጨምሮ ዘመናዊ መሣሪያዎች በአስመራ በኩል ወደ ትግራይ እንዳይገቡ አግዳለች።

ይህ ድርጊት በህወሃት ሰዎች በኩል ከፍተኛ ቅሬታ እየፈጠረ እንደሚገኝ ማረጋገጥ ችለናል።
👍2
ህዝብ የፋኖ ኃይልን በግልፅ መቃወም ጀምሯል

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ልጆቻችን ለተከታታይ ሶስት ዓመታት በፅንፈኛው ቡድን የጥፋት እንቅስቃሴ ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቆይቷል።

ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ጦርነት እንደሰለቸው እና ሰላም እንደሚፈልግ ቢማፀንም፣ ፅንፈኛው ቡድን ግን ከፀረ ህዝብ ተግባሩ መቆጠብ አልቻለም።

አሁን ግን የአከባቢው ነዋሪ በአንድነት፣ “ከዚህ በኋላ በዚህ መልኩ እንድትቀጥሉ አንፈቅድም ታጣቂዎች በመጠለያነት የያዟቸውን ትምህርት ቤቶች ለቀው ይውጡልን" ሲሉ በፋኖ ሃይሎች ላይ ተቃውሞ ማሰማት ጀምረዋል።

ህብረተሰቡ ይህን በማድረግ በዞኑ ትምህርት እና ሌሎች የልማት ሥራዎች በአስተማማኝ ሰላም እንዲካሄዱ ያላውን ፅኑ ፍላጎት አሳይቷል 🙌
4
“ዓባይ የትብብር እንጂ የግጭት ምክንያት ሊሆን አይገባም” የግብፅ ሚዲያ💯

ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ከግጭት ይልቅ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ያዋጣኛል የሚል ውሳኔ ላይ የደረሰች ትመስላለች።

Al_haram online የተሰኘ የግብጽ የዜና አውታር የአፍሪካ ሃገራት የናይልን ውሃ የግጭት ሳይሆን አብሮ የመልማልትና የመተባበር ምሳሌ ሊያደርጉት ይገባል ሲል ዘገባ ሰርቷል።
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ በኩል የተነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ጭምር ተገቢነታቸውን በመዳሰስ ሰፊ ጽሁፉን አስነብቧል።

ይህም የአልሲሲ መንግስት የጀመረው ሀሰተኛ ውንጀላ የትም እንደማያደርሰው ተረድቶ ወደ ሰለማዊ የውይይት መንገድ መምጣቱን የሚያስረዳ ነው።
👍1
ሰበር መረጃ🚨

ከፍተኛ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች መንፈቅለ መንግስት ሊያካሂዱ ነው

ህወሃት በሁሉም አቅጣጫ ሁለንተናዊ ውድቀትና የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ወድቋል።

በፖለቲካ ክንፉ አመራሩ መገለልና መዋከብ እየደረሰባቸው የሚገኙ የህወሃት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በህገወጡ የትግራይ ክልል አስተዳደር ላይ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ሊፈጽሙ በድብቅ መምከር መጀመራቸው ተሰምቷል።

የህወሃት ባለስልጣናት አሁን ላይ በገዛ ጥላቸዉ እንኳን ሳይቀር እየተሸበሩ ይገኛሉ፤ በዚህ ወቅት ይህ መፈንቅለ መንግስት ዕቅድ ቢካሄድ ቡድኑ ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ እንደሚቻል ጀነራሎቹ ተስማምቷል።
👍1
አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ወደ መቀሌ ሊያቀኑ ነው📌

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በአውሮፓ ህብረት፣ በአሜሪካ ተወካዮች እና በሌሎች ሀገራት የተደገፈውን የኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ጉዞ የሚያጠናክር ጉዞን ወደ መቀለ ሊያደርጉ መሆኑ ታውቋል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሰው ሥልጣን የተቆጣሩትን አካላት ለመናጋገር በወራት ልዩነት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ወደ መቀሌ ማቅናታቸው የቡድኑ አሉታዊ እንቅስቃሴ በአለማቀፍ ማህበረሰቡ ዘንድ የተሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ያመላክታል።

ህወሓት ወደ ፕሪቶሪያ ስምምነት ካልተመለስ እና የጦርነት እንቅስቃሴውን ካላቆመ በቀር ተስፋ የለውም 🤷
👍1
ኤርትራ ስለ ውጪ ጣልቃ ገብነት የማውራት ሞራል የላትም‼️❗️

ኤርትራ በአንጎላ እየተካሄደ በሚገኘው 21ኛው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ላይ ተገኝታ ’’ በአፍሪካ ለሚከሰቱ ግጭቶች ዋነኛ መንስዔ የውጭ ጣልቃ ገብነት ነው ‘’ ማለቷን ተከትሎ መነጋገሪያ ሆናለች።

በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ኤርትራ ስለ ውጭ ጣልቃ ገብነት ማውራቷን አስቂኝ ቅራኔ ነው ሲሉም በግልፅ እየተቹ ይገኛል።

ተንታኞቹ አክለውም ኤርትራ ራሷ በሱዳን ፣ በሶማሊያ ፣ በኢትዮጵያ እና በየመን ጉዳይ በተደጋጋሚ ጣልቃ በመግባት በቀጠናው እና በአፍሪካ ቀውስና አለመረጋጋትን አባብሳለች ሲሉ ከሰዋታል።

ይህ ጣልቃ ገቡነቷ ለቀጠናው ስጋት በመሆኑ በተደጋጋሚ በአለም አቀፍ ተቋማት ጭምር እንድታቆም ብትጠየቅም ፍቃደኛ እንዳልሆነች ተናግሯል።
👍1
ሞንጆሮኖ ሆስፒታል ገብታለች📌

ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር (ሞንጆሪኖ) አዲሓውሲ (ቀበሌ 18) አዲሓቂ ክፍለ ከተማ፣ ከትራፊክ መብራቱ 120 ሜትር ወረድ ብሎ በሚገኘው አሉላ የግል ሆስፒታል መግባቷ እየተሰማ ይገኛል።

ሞንጆሪኖ የጤና እክል እንዳጋጠማት ቢነገርም እውነታውና ያለው ግርግር ግን በባለፈው የድሮን ጥቃት ሳትገኝና ሳትቆስል እንዳልቀረች የሚጠቁም ነው።

የትግራይ ወጣት እንዲታፈስ በተጠናከረ መልኩ ሲሰሩ ከነበሩ የህወሃት ሰዎች ሞንጆሪኖ ዋና እንደነበረች የሚታወቅ ነው።

ለትግራይ ህዝብ የተመኘችው ጉዳት እሷ ላይ ደርሶ አሁን ማየቷ ምን ያህል እንደሚያስተምራት የምናየው ይሆናል።
👍1
ልዩነቱ ግልፅ ነው ✍️

አላማው ጥሩም ሆነ መጥፎ አላማ ብሎ ለተነሳበት የፋኖ ትግል ብዙ ዋጋ ሲከፍል የነበረው ማርሸት ጸሃዩ ውለታው ሜዳ ተበትኖ በጓዶቹ በነ ዝናቡ ልንገረው እንዳልሆነ ተደርጎ ለከፍተኛ ጉዳት ተዳርጓል።

በተቃራኒው ማርሸት በፋኖ ቤት ሳለ በከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ስራው ሲቀጠቅጠው የኖረው የፌደራል መንግስቱ ግን በፍቅር ተቀብሎ ከፍተኛ የሆነ የህክምና ዕርዳታ እየሰጠው ይገኛል።

ጽምዶን በመቃወምም ሆነ በሌላ ተቃርኖ በራሱ ጓዶች ከፍተኛ ስጋት አንዣቦበት የሚገኝ የትኛውም አመራር ቢኖር ወደ ሰላም ቢመጣ የሚደረግለት አቀባበል ይህን የመሰል መሆኑን ተረድቶ ሳያመነታ ወደ ሰላም ሊገባ ይገባዋል።

የሰላም መንገድ መከተል እራስን ለመጠበቅ ከማገዙ ጎንለጎን ለህዝብ እና ለሀገር ዘላቂ መፍትሄን ያመጣል 🙌
1
🚨ህወሃት ለውትድርና የአፈሳቸውን ወጣቶች እያስራበ ነው🚨

ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች በፅንፈኛው ህወሃት በግዳጅ ታፍሰው ወደ ጦር ካምፕ የተወሰዱ ወጣቶች በከባድ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

ቡድን የትግራይን ወጣት በገፍ እያፈሰ መሆኑን ተከትሎ የሚታፈሰውን ወጣት በአግባቡ ማሰልጠንም ሆነ መመገብ አልቻለም።

በዚህም የታፈሰው ወጣት ለከፍተኛ ርሃብ እየተዳረገ እንደሚገኝ ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ወታደራዊ ስልጠናውም ለይስሙላ የ8 ቀን ብቻ መሆኑ ከውስጥ በሚወጡ መረጃዎች ለማወቅ ተችሏል።
2
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/JOHkkcFSCXo»
“ግብፅ የኢትዮጵያን መብት ልታከብር ይገባል” አምባሳደር ቲቦር ናጊ💯

ግብፅ ኢትዮጵያ የውሃ ሀብቷን በልማት ለመጠቀም ያላትን መብት ልታከብር እንደሚገባ የቀድሞ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቲቦር ናጊ ከpeoples of Africa ጋር ባደረጉት ቆይታ አስታውቋል።

አክለውም ግብፅ በዓባይ ውሃ ላይ ሙሉ ቁጥጥር ሊኖራት የሚገባ ይመስል የምትከተለው አቋም ከቀጠናውና እየተለወጠ ካለው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ጋር የማይጣጣም መሆኑን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ከዚህ ቀደምም ግብጽ የፖለቲካ ድራማዋን ትታ ቴክኒካል በሆኑ ጉዳዮች ዙርያ ከኢትዮጵያ ጋር መስማማት እንደሚበጃት ገልፀው እንደነበር አይረሳም።
👍2
“ላለፉት 50 ዓመታት የህወሃትን ጠባብ ፍላጎት ስንገነባ ነበር” አሉላ ሰሎሞን📌

አክቲቪስቱ አሉላ ሰሎሞን “በትግራይ ለ50 ዓመታት ሙሉ ብሔራችንን እየገነባን ነው የሚመስለን ነበር ፣ እውነተኛው ትልቁ ውድቀታችን ግን የህወሓት ቡድን ጠባብ ፍላጎትን እየገነባን መቆየታችን ነው” በማለት የእስካሁን የህወሃት ጉዞ ለትግራይ ህዝብ የሚጠቅም እንደልነበር ገልጿል።

አያይዞም “ቡድኑ ሲያነጥስ እኛም አብረን ጉንፋን እንያዝ ነበር ፤ ይህም ማለት ትግራዋይ ሃይማኖቱንና ብሔሩን ትቶ አንድን ቡድን እንዲያመልክ ተደርጓል ማለት ነበር” ሲል ህወሃት በህዝቡ ስነ ልቦና ላይ ሲሰራ የነበረውን የተቀነባበረ ፕሮፖጋንዳ እንደነበር አስረድቷል።

የትግራይ ህዝቡ ከህወሃት ጋር ያለውን ቁርኝነት መበጠስ እንደሚገባው አሉላ አሳስቧል።
1
“ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም” 📌

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “ህወሓት እና ፋኖ ተስማምተው 10 ኪሎ ሜትር እንኳን አብረው መሄድ አይችሉም” በማለት"ስለ ጽምዶ" ያላቸውን ምልከታ አጋርቷል።

አክለውም በጽምዶ ስም የተሰባሰቡት አካላት መሠረታዊ የርዕዮተ-ዓለም እና የፖለቲካ ዓላማ ልዩነት ስላላቸው፣ የፈጠሩት ጥምረት የትም ሊደርስ እንደማይችልና ውጤት እንደማያመጣ አስረድተዋል።

እነዚህ ኃይሎች ወጣቶችን በማስገደድ ለእልቂት እየዳረጉ መሆናቸውን እና ቆመንልሃል የሚሉትን ህዝብ ለመከራ መዳረጋቸውን ተናግሯል።

ኢትዮጵያ በረጅም ታሪኳ በውስጥ ችግሮችም ሆነ በውጭ ጣልቃ ገብነቶች የተዳከመች ብትመስልም በጽናትና በአሸናፊነት ያለፈች ሀገር መሆኗንም ፕሮፌሰር አስታውሷል።
👍2
በመቀሌ ከተማ ሓድነት ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት ጀነራል 📌

በህወሃት ውስጥ ያለውን የስልጣን ሽኩቻ እና የውስጥ ክፍፍል ተባብሶ ቀጥሏል።

አብዛኛው የህውሃት ታጣቂና አመራር ጭምር የለውጡን ሃይል እየደገፈ ነው የሚል ፍርሃት እና ስጋት ውስጥ የገባው የህውሃት ከፍተኛ አመራር በጥርጣሬ ታጣቂዎችን በገፍ እያሰራ እና ወደማይታወቅ ቦታ እየወሰደ ይገኛል።

በዚህም ጀነራል ህንፃ ወልደጊዮርጊስ ሸዊት ቢተውን “ታጣቂዎችን ወደ ነፃ መሬት አደራጅተህ ትልካለህ " በሚል ከእነ አጃቢዎቹና ሹፌሩ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት በመቀሌ ከተማ ሓድነት ፖሊስ ጣቢያ ማሰሩ ተሰምቷል።

ሌሎች አመራሮች ስልታዊ በሆነ መንገድ የማስወገድ ዘመቻ ለማካሄድ ቡድኑ ዕቅድ እንደወጣም ከውስጥ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
👍1
አሳዛኝ መረጃ🥲

ህወሃት በከፍተኛ ሁኔታ የቆሰሉ ታጣቂዎችን ረሽኗል

የህወሃት የጦር ጉዳተኞች ለሌላ አዳዲስ ጉዳተኞች ቦታ እንዲለቁ በማሰብ ከመቀለ ወደ አክሱምና አዲግራት እንዲዘዋወሩ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

ቁሰለኛ ታጣቂዎቹ ተቋማቱን ለቀን አንወጣም በማለት ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ሰሚ ጆሮን በለማግኘቱ በኃይል ከዋናው ከተማው እንዲወጡ ተደርጓል።

ይህም ሳያንስ፣ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የጦር ጉዳተኞችን በጀነራል ምግበይ ትዕዛዝ መሰረት “እነሱን ለማሳከም የምናባክነው ወጪ አይኖርም” በሚል በመንገድ ላይ እንዲወርዱ በመደረግ መረሸናቸው ተሰምቷል ።

ህወሃት ማለት ይሄ ነው 😡
👍1
🚨ለአልቡርሃን ጦር የሚሸጡ የትግራይ ታጣቂዎች በጨለማ እየታፈሱ ነው🚨

ህወሓት የትግራይን ህዘብ ለራሱ የፖለቲካ ዓላማና ትርፍ ከመጠቀም አልፎ፣ እንደሸቀጥ ወጣቶችን ለሌላ ሀገር ጦርነት የሚሸጥ የህዘብ ጠላት ድርጅት ነው።

ቡድኑ ያጋጠመውን የፋይናንስ ዕጥረት ለመቅረፍ የትግራይ ወጣቶችን በግዳጅ በማፈስ ለሱዳኑ አልቡርሃን ጦር በዶላር መሸጡን አጦጥፎ ቀጥሏል።

አሁን ደሞ በበዛ ጭካኔ በየከተሞቹ የምሽት መብራት እንዲቋረጥ በማድረግ በየቤትና መንገዶች ወጣቶችን እያፈሰ መሆኑ ተሰምቷል ።

የትግራይ ወጣቶች ራሳቸውን ከህወሓት ለማስመለጥ በጋራ ሊቆሙ ይገባል‼️‼️‼️
2
ወጣቶቹ በፈቃዳቸው ወደ ጦር ካምፕ የገቡት በሚል የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሊሰራጭ ነው🚨

የትግራይ ወጣቶች ወደ ጦር ካምፖች ላለመግባት ከመኪና ላይ ሳይቀር እየዘለሉ ህይወታቸውን ለማዳን ሲሞክር የሚያሳይ ቪዲዩ እየወጣ ባለበት በዚህ ወቅት ህወሃት የውሸት ድራማ በማዘጋጀት ለማደናገር ሊሞክር ነው።

ስብስቡ እየፈጸመ የሚገኘውን የአፈሳ ተግባር ተከትሎ የሚቀርብበትን ተቃውሞ ለማለዘብ በአፈሳ የተያዙ ወጣቶች እና ቤተሰቦቻቸውን በፈቃዳቸው ወደ ቡድኑ እንደተቀላቀሉ እንዲገልጹ በሃይል በማስገደድ ቪድዮ ቀርጾ በሚዲያዎች ለማሰራጨት ሰፊ ስራን እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።

ይህ ድርጊት የወጣቶችን ስቃይና የቤተሰቦቻቸውን እንባ እንደ መሳለቅ ነው የሚቆጠረው‼️
በደቡብ ጎንደር ዞን ከፅንፈኛው ፀድታለች💪

በደቡብ ጎንደር ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ኮር ከነሐሴ 01 አስከ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም ባካሄደው የተቀናጀ የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 51 ፅንፈኞች ሲደመሰሱ፣ 24 ቆስለዋል፣ 32 በተለያየ መንገድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከተደመሰሱት መካከል፣ ግዜ ግርማ የተባለ የፅንፈኛዉ ቡድን የአንዳቤቴ ብርጌድ የነሱ መዋቅር ፍርድ ቤት ኀላፊ፣ ሙጨ ታምር የአንበሳዉ ጋይንት ክፍለ ጦር አደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ፣ ሽሻነዉ ጠጋ የአንበሳዉ ጋይንት ሻለቃ አዛዥ ይገኙበታል።

በተጨማሪ በዞኑ ባተካሄደው ሕግ የማስከበር እርምጃ የተለያዩ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች፣ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ ተተኳሾች፣ የመገናኛ ሬድዮዎች እና ከኅብረተሰቡ ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን በእጁ አስገብቷል።
👍2
የጅምላ እስር እንደቀጠለ ነው🚫

ሀሳብን በጠበመንጃ ብቻ ማሸንፍ የሚችለው፣ ከእራሱ ውጪ ማንንም የማይሰማው የህውሃት ቡድን ‘’ ቡድኔን ይቃወማሉ፣ የለውጥ ፈላጊ ሃይሎችን ይደግፋሉ‘’ በሚል የጠረጠራቸውን ንጹሃን ማሰርና ማንገላታቱን አጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም በማዕከላዊ ዞን ታህታይ ማይጨው እና ዓዲግራት አዲ ከተማ ቡድኑን ይቃወማሉ ያላቸውን ከ56 በላይ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ታውቋል።

ፅንፈኛው በጥርጣሬ ንፁኃን ላይ እያካሄደው ያለው የጅምላ እስር ለሚድያ ተጋላጭ እንዳይሆን በሚል በድብቅ እንደሚያካሂድ ለማወቅ ችለናል።
👍1
ሰበር መረጃ🚨

የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች የወጣ የእስር ትዕዛዝ📌

ህወሃት የሀሰት ፕሮፓጋንዳና የጦርነት ቅስቀሳ በዋነኝነት የሚያደርገው በልሳን ሚዲያዎቹ በኩል እንደሆነ ይታወቃል።

ነጻና ገለልተኛ መሆን የሚገባቸውን ሚድያዎች የፕሮፖጋንዳ መሳሪያ ለማድረግ በሚፈጽመው እንቅስቃሴ “ግዜያዉ አስተዳደሩንና ጦርነቱን ይቃወማሉ” በሚል የለያቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ባለሙያዎች ለማሰር እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተሰምቷል።

ቡድኑ በተደጋጋሚ አፈናና ዕስር እየፈጸመባቸው ለሚገኙ ጋዜጠኞች አለማቀፍ የፕሬስ ነጻነትና የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች ድርጅቶች ድምጽ ይሆኗቸው ዘንድ፣ የቡድኑ አፋኝነት ይፋ የማውጣት የንቅናቄ ስራ በተለይም በኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ዘንድ ሊሰራ ይገባል።

የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ ህዝብን ላለማደናገር የወሰኑ ባለሙያዎችን ደሞ የትግራይ ህዝብ ሊያከብራቸው ይገባል
3