ታማኝ መረጃ
853 subscribers
1.76K photos
48 videos
107 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
51 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች ተዘጋጅቷል 📌

ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ 51 ሺህ የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበራት ድርጅቶች ጥምረት አስታውቋል ።

ምርጫውን በገለልተኝነት ለመታዘብ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች መጠናቀቁን ድርጅቱ አስታውቋል።

የታዛቢዎቹ ንቁ ክትትል እስከ ሚያዝያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል እና በምርጫው ዕለትም ሂደቱ ተዓማኒና ግልጽ እንዲሆን ጥብቅ ክትትል እንደሚደርግ ተገልጿል።
የታዛቢዎችን ጥራትና ብቃት ለማረጋገጥ ጥምረቱ አዲስ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ሥራ ላይ ማዋሉን ገልጿል።

ቴክኖሎጂው የታዛቢዎችን የሥራ አፈጻጸም በብቃት መቆጣጠር እንደሚችል እና በቀጣዩ ምርጫ ላይ የታዛቢዎችን ተደራሽነትና የክትትል ጥራት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተጠቁሟል።
👍2👎1
"የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ በማንኛውም ዓይነት ጩኅት አይደናቀፍም" ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ‘’ የጀመርነው የብልጽግና ጉዞ በማንኛውም ዓይነት ጩኅት የማይናወጥ በደም መሰረት ላይ ያቆምነው ነው ’’ ሲሉ ተናግሯል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት የሕዝብን ሕይወት የሚለውጡ ተግባራትን በሙሉ ልብ እና በሙሉ አቅም ማከናወኑን እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ በብዙ ውጣ ውረድ እና መስዋዕትነት ያለፈ መሆኑን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ "ሊያደናቅፈን የሚችል ማንኛውም እንቅፋት ካለ እንደ ማንኛውም ጉቶ ነቅለን በመጣል እናልፋለን" ብሏል፡፡
👍4👎1
ጀነራል ታደሰ ወረደ ወደ እርምጃ ሊገቡ ነው🚨

ጀነራል ታደሰ ከሹመት ለማንሳት ድንጋይ የሚፈነቅለው የጽንፈኛው የህወሃት ስብስብ የሚያደርገውን መፈንቅለ መንግስት አሁን እንደቀጠለበት ነው።

አሁን ግን ጀነራል ታደሰ ወረደ ከተደጋጋሚ ትንኮሳው አልታቀብ ባለው የጽንፈኛ ስብስብስ ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ጫፍ መድረሱ እየተሰማ ይገኛል።

የትግራይ ሕዝብ ከጥፋትና ከጦርነት ይልቅ ሰላምንና ልማትን የሚሻበት በዚህ ወቅት ፅንፈኛው ህወሃት ለተራ የፖለቲካ ቁማር ህዝብን ሊያንገለታው አይገባም።

በመሆኑም የዚህ ቡድን የጥፋት ጉዞ በንቁውና አስተዋዩ የትግራይ ህዝብ ትግል እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ ህጋዊ እርምጃ ሊቆም ይገባል ‼️
👍1
🚨ምርጫን ለማደናቀፍ የተጠነሰሰው ሴራ🚨

ጽንፈኛው ፋኖ ህዝቡ ምርጫ እንዳይመርጥ ተደጋጋሚ ማስፈራሪያዎችን ሲያደርስ ቢቆይም ሰሚ ጆሮ አላገኘም።

የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች የሚመለሱት ፅንፈኛው ቡድን በመረጠው መንገድ እንዳልሆነ የተረዳው ህዝብ የምርጫ ካርዱን እየወሰደ ይገኛል🙌

በዚህም ምክንያት የዲሞክራሲ ፀር የሆነው ቡድን “የምርጫ ካርድ የሚወስዱ ዜጎችን በግዳጅ ነው” የሚል ውሃ የማያነሳ የሽንፈት ማስተባበያን ወደማሰማት ገብቷል።

በሰላማዊ እና በዲሞክራሲ መንገድ ወደ ስልጣን እንዳማይመጣ የተረዳው ስብስብ ምርጫን ለማደናቀፍ በሙሉ አቅሙ እያሴረ መሆኑን ህዝብ ሊረዳ ይገባል ‼️
👎1
ዘመነ ካሴ ለደሳለኝ ሲያስብሸዋ ያስተላለፈው ትዕዛዝ 📌

በዘመነ ካሴ መሪነት የተመሰረተው "አፋብን" የተሰኘው አደረጃጀት እየፈራረሰ እና በታጣቂዎቹ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መከፋፈል እየፈጠረ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ደሞ ከሰሞኑ የፋኖን አካሄድ ኮንነው ለሰላም እጅ የሰጡ አባላቶች ያጋለጧቸውን ሃቆች ቡድኑን አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል።

በተለይም ኮረኔል ማን ነገረው ስለዘመነ ስግብግብነት ያጋለጠውን ሃቅ ተከትሎ ዘመነ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ እንደገባና ለበቀል በመሳሳት በሸዋ የሚገኙ የኮረኔሉ ቤተሰቦች ላይ ዕርምጃ እንዲወሰድ ለኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብ ሸዋ ትዕዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል።
👎1
“የሰላም አማራጭ ይሻለናል የሚል ካለ ትግራዋይ አይደለም በሚል እየተፈረጀ ነው” 📌

የቀድሞው የፌዴሬሽን ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ እና የህዋሃት አባል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) ጋር ባድጉት ቆይታ “አሁን ላይ ትግራዋይነት በእነሱ የሚሰጥና የሚነፈግ ጉዳይ ሁኗል ፤ ጽምዶውን የሚቃወም፣ የሰላም አማራጭ ይሻለናል የሚል ካለ ትግራዋይ አይደለም በሚል ይፈረጃል ዕርምጃ ይወሰድበታል” ብሏል።

አያይዘው "የትግራይ ሁኔታ በጣም ነው እንደሚያሳዝን እና አለመግባባቶች እየተወሳሰበ ሁለት ጫፍ ላይ እንደደረሰ ገልጿል።

ከህወሃት በላይ የትግራይ ህዝብ ያንበረከከው እና ያጠፋው የለም ያሉት ወይዞሮ ኬርያ፣ አሁን ላይ ወጣቱ የሁሉንም ሴራ አውቆ እየሸሸ ነው ብሏል።
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/5P9O_CH1cNg?si=azQLdRUarw4dEIf7»
የትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት ጥሪ 📌

ኢሕአፓ ፣ መኢአድ ፣ አማራ ግዮናዊ እና እናት ፓርቲ ተዋህደው ትብብር በሚል እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ይታወቃል።

ሆኖም የትብብሩ የምርጫ ጉዳዮች ሃላፊ እንደገለጸው አንዳንድ የኢሕአፓ ሰዎች ከትብብሩ ውጭ አንድ እግራቸውን ወደ ምርጫ አንዱን ወደ ውጭ በማድረግ አጥር ላይ ተንጠልጥለው ከትብብሩ አቋም ውጭ የራሳቸውን መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።

“ይህንን እኛ እንደትብብር መጠየቅ አንችልም የህግ አካላት እንጂ” ሲሉ ፓርቲው በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን ጥሪ አቅርቧል።
ጥብቅ መረጃ🚨

የኤርትራ ወታደሮች ትግራይ ገብቷል‼️

የኤርትራ ወታደራዊ ሰራዊት አባላት በትግራይ ክልል በስፋት እየተንቀሳቀሱ መሆኑ ተጋልጧል።

ትላንት ሚያዝያ 11/2018 ዓ.ም ለሊቱን በዛላምበሳ በኩል የኤርትራ ወታደሮች እና ሳዋ የሰለጠኑ የህውሓት ታጣቂዎች በጭነት መኪናዎች ወደ ትግራይ ገብቷል።

በተመሳሳይጦርነቱን የሚመራው ማዕከላዊ ኮማንድ ፖስቱ በትግራይ ክልል የሚገኙ ሚዲያዎችን ፣ ባንኮችን እና ኤርፖርቶችን ለመቆጣጠር ትዕዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል።

ማንኛውም የትግራይ ታጣቂም ሆነ የታጣቂው አዛዦች ትግራይን ለቀው መውጣት እንደማይችሉም ትዕዛዝ ሰጥቷል ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሸኔ ሊደርስ የነበረ ሬዲዮ በቁጥጥር ስር ዋለ ‼️

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ከኦሮሚያ ክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በምዕራብ አርሲ ዞን ለሚንቀሳቀሰዉ የሸኔ ሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረን መገናኛ ሬዲዮ በቁጥጥር ስር አውሏል ።

የደህንነት መስሪያ ቤቱ መነሻዉን ከሰሜን ኬኒያ አዋሳኝ አድርጎ በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በማድረግ ምዕራብ አርሲ ዞን ለሚንቀሳቀሰዉ በሰባኢፍ ለሚመራዉ የሸኔ ሽብር ቡድን ሊደርስ የነበረን 98 መገናኛ ሬዲዮ ከነቻርጀሮቹ ከመነሻዉ ጀምሮ ብርቱ ክትትል በማድረግ ከኦሮሚያ ፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በቀን 12/08/2018 ዓ.ም በሻሸመኔ ከተማ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉ ነው የታወቀው ፡፡

በቀጣይም ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን ለመከላከልና የራሱን ሰላም ለማረጋገጥ በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የሚያደርገዉን ትብብር አጠናክሮ በማስቀጠል ፀፅንፈኞችን በትጋት እንዲዋጋ ጥሪ ቀርቦለታል ፡፡
“ህወሃት የእኛን ዕጣ ፈንታ እንዲወስኑ እስከተፈቀደለት ድረስ ሰላም አይኖርም" ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት

የህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የስምረት ፓርቲ አመራር የሆኑት ፕ/ር ክንደያ ገብረህይወት “እነዚህ ጦርነት ናፋቂዎች የእኛን ዕጣ ፈንታ እንዲወስኑ እስከተፈቀደላቸው ድረስ ሰላም አይኖርም “ ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጿል።

ህወሃት ከጦርነቱ በፊት የነበረውን የክልል ምክር ቤት ለመመለስ፣ ክልላዊ አስተዳደሩን ለማፍረስ እና ከጎረቤት አገራት ጋር ያለውን ሕገ-ወጥ ግንኙነት ለማጠናከር መግለጫ አውጥቷል ያሉት ፕ/ር ክንደያ ።

“እንዲህ ያለውን እንቅስቃሴ ሰላም ወዳድ በሆኑ ወገኖች ሁሉ ሊወገዝ እና በወንጀል ቡድን ተጠያቂ ሊደረገው ይገባል “ ብሏል።

የትግራይ ህዝብ በቃችሁ ብሎ የማይነሳ ከሆኑ ቡድኑ እስካለ ድረስ ጦርነት ከመቆስቆስ ወደኋላ እንደማይልና መከራውም እንደማያልቅ ማረጋገጫ ሰጥቷል።
በታዳሚ እጦት የተሰረዘው የገቢ ማሰባሰቢያ 📌

በአሜሪካ አትላንታ ለፋኖ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በሚል የተዘጋጀው መድረክ በጣት የሚቆጠር ታዳሚ ብቻ በመገኘቱ ሳይካሄድ መበተኑ ታውቋል።

የቡድኑ ደጋፊዎች ቡድኑ በከፍተኛ ኪሰራ ውስጥ መሆኑን እና የክልሉን ህዝብ ተቀባይነት አለማግኘቱን ተከትለው ከድጋፍ ርቋል።

ይህም ቡድኑ በውጭ ሃገር ደጋፊወቹ ጭምር እየተከዳ መምጣቱንና ዲያስፖራውም የአመራሩን ሌባነት በመረዳት መንቃቱን ያረጋግጣል።

ከዚህ በኃላ ለቡድኑ ሎጀስቲክስ ለማሟላት የተለያዩ መርሀግብሮችን ቢካሄዱ የሚኖረው ግብረ መልስ ተመሳሳይ ነው።
ዝናቡ ከጥቂት ያመለጠበት ድንገተኛ ኦፕሬሽን🙌

ደጀኑ መከለካያ ሰራዊታችን የፅንፈኛው ከፍተኛ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ኦፕሬሽን በማካሄድ የቡድኑ አመራሮችን እየደመሰሰ መዋቅራቸዉን ፍርክስክሱን እያወጣ በጀግንነት ቀጥሏል፡፡

በዚህም ሰራዊቱ በጎጃም ጃውሳ አንድ ክንፍ ላይ በወሰደው ድንገተኛ ጥቃት ራሱን የጎጃሙ ፅንፈኛዉ ሃይል ወታደራዊ አዛዥ ብሎ የሚጠራዉ ዝናቡ ልንገረዉ አጃቢ እና የቅርብ ጓደኞች ሙሉ በሙሉ መደምሰስ ተችሏል፡፡

በኦፕሬሽኑ ዝናቡ ለጥቂት በማምለጥ ከአካባቢዉ መስወሩ ተሰምቷል፤ የዝናቡ ጠባቂዎች ሞት የሰማዉ ታጣቂም ፍርሀት ወስጥ መግባቱ ተረጋግጧል።
1
የባህር በር የ130 ሚሊዮን ህዝብ ጥያቄ ነው🙌

ኢትዮጵያ በጂኦግራፊ የታጠረች ወደብ አልባ ሀገር ሆና የምትቆይበት ዘመን አክትሟል

ለብዙ ዘመናት የባህር በር ጉዳን ማንሳት እንደ ሀፍረት ተደርጎ የሚቆጠርበት ጊዜ ታሪክ ሆኖ አልፏል።

የወደብ ጉዳይ ዛሬ ላይ ለኢትዮጵያ ከንቱ ምኞት ወይም የፖለቲካ ፍጆታ ሳይሆን ፤ በቀላሉ የማይቀለበስ ከ130 ሚሊዮን በላይ ለሚሆነው የሀገራችን ሕዝብ የህልውና ፣ የኢኮኖሚ ዋስትና እና የሉዓላዊነት ጥያቄ ነው።

የባህር በር ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የህልውና መሰረት እና ጉዳይ ነው! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
👍1
የትግራይ የሰላም ኃይል ህወሃትን ለማጥፋት ተነስቷል💪

የትግራይ የሰላም ኃይል የትግራይን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከዚህ ጽንፈኛ ሃይል ለማላቀቅ በቁርጠኝነት መነሳቱን ይፋ አድርጓል።

በርካታ ቁጥር ያለው የህወሓት ታጣቂ የቡድኑን ትክክለኛ ማንነት ተረድቶ የትግራይ ህዝብ ሰላም ፀር የሆነውን ስብስብ ለመታገል ወደ ቡድኑ እየጎረፈ ነው።

በመሆኑም የትግራይ ህዝብ አሁኑኑ ትግራይን ወደሌላ ጦርነት እያንደረደረ የሚገኘውን ህውሃትን ለማስወገድ የሰላም ሃይሉን በሙሉ ልቡ መደገፉን ሊያሳይና ለለውጥ መዘጋጀቱን ሃይሉን በመደገፍ ሊያሳይ ይገባዋል 🙌
👍3
የአቶ በረከት ስምዖን የምርጫ ክርክር ትዝብት📌

አቶ በረከት ስምዖን በርካታ የምርጫ ክርክሮችን መመልከታቸውን ገልጸው፤ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ውስጥ ያሉ አንዳንድ ግለሰቦች በጫካ ሆኖ መንግሥትን ከሚፋለሙት ጋር የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች መሆናቸውን ተናግሯል።

በመካከላቸው የሚታይ ልዩነት ቢኖር እነዛ በጫካ፣ እነዚህ ደግሞ በከተማ መሆናቸው ብቻ ነው" ብሏል።

የገዛ ፖሊሲያቸውንና ተጨባጭ እቅዶችን በማቅረብ ሕዝብን ማሳመን ሲገባቸው፣ እንደ ሰካራም በስድብ ብቻ ጊዜያቸውን በማባከን ሕዝብን መናቅ እንደሆነም አክለው ገልጿል።

ሀገር ለመምራት የሚዘጋጅ ፓርቲ ወይም ግለሰብ እንዲህ ዓይነት ድርጊት እንደማይፈጽም፣ ይልቁንም ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ሕዝቡ የእርሱን ፓርቲ እንዲመርጥ ማሳመን እንዳለበት አቶ በረከት አሳስቧል።
ጀነራል ታደሰ ወረደ ህወሃትን ሊቀድሙት ይገባል‼️

ጀነራል ታደሰ ወረደ አሁን ስራቸውን በአፋጣኝ ሊጀምሩ ይገባቸዋል።

ህወሀት ካለፈው እልቂት አንዳች ትምህርት ሳይቀሰም፣ በቁም እየማቀቀ ያለን ህዝብ ለሌላ ዙር መስዋዕትነት እያዘጋጀው እና ለፖለቲካ ቁማር ሊጠቀምት እየመቻቸው ይገኛል።

ህወሀት የትግራይን ህዝብ እንደ ጋሻ በመጠቀም የራሱን እድሜ ለማራዘም የሚሄድበት ርቀት፣ ቡድኑ ለትግራይ ህዝብ ያለውን ንቀትት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ለዚህም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀነራል ታደሰ የህውሃት ስብስብ ዳግም ክልልና ህዝባቸውን ወደከፋ ጦርነት ከማስገባቱ በፊት ሊቀድሙት ይገባል የምንለው።
ከበባ ውስጥ የገባው ጃውሳ እጅ እየሰጠ ነው ‼️

በምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ ወረዳ ቢቸና አካባቢ ከሸምሽ በተባለ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ፀረ ሰላም ቡድን በሰራዊቱ ከበባ ውስጥ ገብቷል ።

በሰራዊቱ ከበባ ውስጥ የገባው ይህ ሃይል በምንም አይነት መንገድ ከበባውን ሰብሮ መውጣት እንደማይቻለው ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ታጣቂው አንድ በአንድ እጅ እየሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል ።

እጅ ለመስጠት ስጋት ያደረባቸው የተቀሩት ታጣቂወች ደግሞ እጅ ለመስጠት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት በኃማኖት አባቶች እና በሀገር ሽማግሌዎች በኩል ጥያቄ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተሰምቷል ።

ሰራዊቱ ከበባ ውስጥ ያስገባውን ይህን ሃይል ሙሉ በሙሉ ማውደም ሲችል ለታጣቂው የሰላም እድል መስጠቱ መንግስት የያዘውን ጠንካራ የሰላም ፍላጎትና ህዝባዊነቱን የሚያረጋግጥ ነው ።

በቀጥታ እጅ ከመስጠት ይልቅ በሃይማኖት አባቶችና በሃገር ሽማግሌወች እጅ መስጠትን ምርጫቸውን ያደረጉ የተቀሩ ታጣቂወችንም መንግስት በመልካም ሁኔታ እንደሚቀበላቸው የሚጠበቅ ሲሆን ፤ በሌሎች አካባቢወች የሚንቀሳቀስ የቡድኑ ክንፍ ታጣቂም በተመሳሳይ እጅ ከሰጠሁ በኋላ ምን ይደርስብኛል ከሚል ፍርሃትና ስጋት ነጻ በመውጣት እጁን ለሰላም ቢሰጥ አዋጭ እንደሚሆን ከጎጃም ጓዶቹ ሊማር ይገባል ።
👍1👎1
የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግሬስ ወደ ትጥቅ ትግል ተሸጋግሯል📌

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ኮንግረስ (EANC) የአሁኑን የኤርትራ አገዛዝ በትጥቅ ትግል ለማፍረስ ወታደራዊ ክንፍ መቋቋሙን ይፋ አድርጓል።

የኤርትራ መንግስትን ለመታገል ሰላማዊ የፖለቲካ ስልት ተጠቅሞ ሲንቀሳቀስ እንደነበረ የገለጸው የፖለቲካ ድርጅቱ አሁን ላይ አገዛዙ በኤርትራ አፋር ሕዝብ ላይ ከባድ ሰብአዊ መብት በመፈጸም ምክንያት ፓርቲውም የትግል ስልቱን እንዲቀይር ተገዷል።

ኤርትራ ውስጥ በዳንካልያ የአፋር ሕዝብ ውስጣዊ የራስን ዕድል በራስ የመወሰን ፣ የራስን በራስ የመመራት እና የራስን አስተዳደር መብቶችን መልሶ ለማቋቋም የቆመው ግንባር ቀደም የአፋር ተወላጅ ንቅናቄ በምርጫ ያልተመረጡት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አገዛዝ ላይ እርምጃ ለመዉሰድ የተቋቋመ ንቅናቄ መሆኑን አሰታዉቋል ።
4
📌 በጥቅማጥቅም ሹክቻ የሚገዳደለው የጃውሳ አመራር

በአራቱም አቅጣጫ የሚገኝ የጃውሳው ሃይል በጥቅማጥቅምና ሌሎች ምክንያቶች መነሻነት ዕርስ በርሱ እየተባላ መሆኑ ታውቋል ።

በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ጊዜያዊ መንግስት በሚል ያደራጀው አመራር እና በክ/ጦር ፋይናንሱ መካከል በግብር መልኩ ከማህበረሰቡ በተሰበሰበ ገንዘብ ግጭት ውስጥ መገባቱ ተሰምቷል።

በተመሳሳይ በሰከላ ዙሪያ አምቢሲ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው ቡድን አባላት መካከል ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የእርስ በእርስ ግጭት መፈጠሩን ፣ በዚህም ሳቢያ ታጣቂው እየከዳ መሆኑ ፤ እንዲሁም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አምባጊዮርጊስ አካባቢ በሚንቀሳቀሰው ቡድን አባላት መካከልም በተቀሰቀሰው ግጭት ጌታቸው እና ሲሳይ የተባሉ የቡድኑ አስተባባሪዎችን ጨምሮ አራት (4) ገደማ አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል ።

እንዲሁ በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ወረዳ ከሚንቀሳቀሰው ቡድን መካከል ጥርናፊ ስተው ወደ ዋጃ ፣ ጥሙጋ እና አላማጣ አካባቢዎች የገቡ የቡድኑ አስተባባሪዎች እና አባላት ግጭት ውስጥ እየገቡ በመሆኑ ከከተማው ማስወጣት እንደሚገባ በየአካባቢው የሚገኙ የቡድኑ አመራሮች ለቡድኑ አስተባባሪዎች እያሳሰቡ ይገኛሉ ።

እንግዲህ ቡድኑ በሰራዊቱ ከሚወስድበት ዕርምጃና እጅ ከሚሰጠው በርካታ ታጣቂ በተጨማሪ በውስጥ ሹክቻውም ጭምር መጥፊያውን እያፋጠነ ይገኛል ፡፡
1👎1