ታማኝ መረጃ
850 subscribers
1.77K photos
50 videos
108 links
ታማኝ እና አዲስ መረጃዎች ለመግኘት ቻናላችንን ምርጫቹ አድርጉ
Download Telegram
በሰላማዊ ትግል ካባ ለፋኖ የሚታዘዘው ኢሕአፓ

ኢሕአፓ በአንደበቱ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ ቢልም፣ በተግባር ግን በሕዝብ ላይ መከራን ለሚያወርዱ የታጠቁ ኃይሎች ሽፋን እየሰጠ ነው እና የነሱን ፍላጎት ለማሞላት እየተጋ ነው።

ስድስት ከምርጫ ሂደቱ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ቅድመ ሁኔታዎች በማስቀመጥ፣ “ያስቀመጥኳቸው ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ በምርጫው ብወዳደር ከአጃቢነት የዘለለ ትርጉም አይሰጠኝም” በማለት ኢሕአፓ የፋኖ የከተማ ሴልነቱን ከቡድኑ ቀጥታ በተወሰዱ ቃላት ጭምር እያስመሰከረ ነው።

የዘፈን ዳርዳሩ እስክስታ ነው እንዲሉ ፓርቲው ቀድሞም ራሱን ከምርጫ ለማግለል የእናቴ ቀሚስ አደናቀፈኝ የሚሉ አልባሌ ሰበቦችን ሲደረድር ሰንብቶ ነበር አሁን ደሞ እሄው የመጨረሻ ፊሽካውን ነፍቷል።
1👎1
አነጋጋሪው የትግራይ ቴሌቪዥን ጋዜጠኞች ውሳኔ 📌

12 የትግራይ ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች የጦርነት አጀንዳ ላይ ብቻ አተኩሩ የሚለውን የህውሃት አመራር ጫና በመቃወምና በባለፈው ጦርነት የትግራይን ወጣት ወደ ጦርነት የሚገፋ እና የሐሰት ድል ዜናወችን በማሰራጨት ለነበረው ውድመት ራሳቸውን ተወቃሽ በማድረግ ተደጋጋሚ ስህተት አንሰራም ሲሉ ከስራ መልቀቃቸው ታውቋል።

የተቋሙ አዳዲስ አመራሮች "ሰላም የሚረጋገጠው በጦርነት ብቻ ነው" በማለት ጋዜጠኞቹ የጦርነት አጀንዳዎች ላይ ብቻ እንዲያተኩሩና የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚያጣጥሉ ዘገባዎችን እንዲሰሩ ሲያስገድዷቸው እንደነበር ጋዜጠኞቹ ገልጿል።
👍2
የግብጽ ገቢ ተቋርጧል📌

ግብጽ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ሳቢያ ከስዊዝ ካናል እንዲሁም ቱሪዝም የማገኘው ገቢ ተቋርጧል። በዚህም የግብፅ መንግስት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ታውቋል።

ይህን ሁኔታ ተከትሎ የምግብ ዋጋን እንኳን መቋቋም አልቻልኩም ስለዚህም አሜሪካ ዕርዳታ ታድርግልኝ ስትል የውጭ ጉዳይ ሚንስሯ ከአሜሪካው አቻው ጋር ባደረገው ውይይት እንዲያሳውቅ አድርጋለች።

ይሄም በሃገር ደረጃ በይፋ ልመና ውስጥ እንደመግባት ተደርጎ ተወስዷል።

ከዚህ በተጨማሪ የግብጽ ልመና ሃገሪቷ በዚህች አጭር ግዜ ውስጥ የሚናወጥ ምን አይነት የወረደ የኢኮኖሚ አቅም ላይ እንደነበረች የሚያጋልጥ ነው ።
የባዬ ቀናው ተቃውሞ🚨

ያለ ማዕከላዊ ኮሚቴው እና ስራ አስፈጻሚው እውቅና በነዘመነ እና አስረስ አዛዥነት የጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ ዕዝ ሰብሳቢ በሚል የተሾመው ዮሃንስ ንጉሱ በህውሃት ትዕዛዝ ወልቃይትን ለህውሃቶች አመቻችቶ እንዲሰጥ የተመረጠ የትግራይ ተወላጅ መሆኑ ተረጋግጧል።

ዮሀንስ ንጉሱ በጨረባ ምርጫ እንዲመራ በመመረጡ የተበሳጨው ባዬ ቀናው የሀብቴ ወልዴ ምክትሉ እኔ ሆኞ ሳለ ስልጣኑን ለዮሀንስ ንጉሱ መሰጠቱ ህወሓት ውስጣችን ምን ያህል ሰርጎ እንደገባ የሚያሳይ ስለሆነ ይህን ደግሞ እኔ በፍፁም አልቀበልም ሲል በቪዲዮ ጭምር ተናግሯል።

እሱን ተከትሎ ሙሉ ዕዙም ውሳኔውን በተመሳሳይ እየተቃወመ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል ።
2
ኢራን የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ትደግፋለች 🇮🇷🇪🇹🇮🇷🇪🇹🇮🇷🇪🇹

በኢትዮጵያ የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር አሊ አክባር ራዛኒ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድና በድርድር የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው እንቅስቃሴ ለቀጣናው መረጋጋትና ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ገልጿል።

በዚህ ምክንያት ኢራን በይፋ የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት እንደምትደግፍ አስታውቋል።
አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የኢኮኖሚ አቅምና የሕዝብ ብዛት የባሕር በር መዳረሻ እንዲኖረው የግድ የሚል መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህ የኢራን ድጋፍ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ጂኦ-ፖለቲካዊ ተጽዕኖ ለማጠናከር ለምታደርገው ጥረት ተጨማሪ ዲፕሎማሲያዊ ግብዓት ይሆናል።
👍1
ጥብቅ መረጃ🚨

የሻዕብያ ወታደር ሽራሮ ገብቷል

ህወሃት ለሚፈልገው የፖለቲካ ትርፍ ሲል የትግራይን ህዘብ ወደ ጦርነት ሊከት እያኮበኮበ ነው።

በዚህ ከቀናቶች በፊት (መጋቢት 26/2018 ዓ.ም) በፅንፈኛው ህወሃት ቡድን በመታደም ትግራይ ወጣቶች በሀይል አፈና እና አፈሳ ለማድረግ ሲባል የሻዕብያ ሰራዊት ሸራሮ ከተማ መግባቱ ታዉቋል፡፡

የአረመኔዎች ስብስብ ነው ህወሓት የትግራይ ወጣቶችን በግዳጅ በማፈስ የጦርነት ቅዥቱን ሊያሳካ ነው
የሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የአዲስ አበባ ጉዞ እና የነሞንጆሪኖ ስጋት📌

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል ታደሰ ወረደ፣ በክልሉ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ትላንት (እሁድ መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም) አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል።

ጄነራሉ የስልጣን ግዚያቸው ሊያበቃ ቀናት በቀረበት ሁኔታ በፊደራል መንስግቱ ወደ አዲስ አበባ መጠራታቸውን ተከትሎ ስልጣናቸውን ሊያራዝሙላቸው ነው በሚል በቦታው ሌላ ሰው ለመተካት ዕቅድ ይዞ በነበረው የነሞንጆሪኖ ስብስብ ዘንድ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን ሰምተናል።

በዚህም ስብስቡ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት የፌደራል መንስግቱ ይህን የሚያደርግ ከሆነ ጀነራሉ ሳይመለሱ በወታደራዊ አዛዦች በኩል መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግ መወሰናቸው ታውቋል ።
“ህወሃት መስራች መሆኔ የህይወቴ ትልቁ ስህተት ነው” ዶ/ር አረጋዊ በርሀ✔️

“ለዘመናት ትግራይን ያወደመ፤ ለዓመታት ኢትዮጵያዊያን የበላ፣ የከፋፈለ ለብዙ ሰቆቃ ያጋለጠ ህዉሓት የተባለ አረመኔ ድርጅት መስራች መሆኔ ይቆጨኛል ፣ የህይወቴ ትልቁም ስህተት ነዉ” በማለት ዶክተር አረጋዊ በርሀ ተናገሩ።

ህወሃት የትግራይን እናቶች ከልቅሶ አትውጡ ብሎ ጭካኔን ያወጀ፣ እያወጀም ያለ ፤ከስህተቱ የማይማር፣ ስልጣንና ወንበርን የሞት አፋፍ ላይ ተቀምጦ እንኳ በህዝብ ስቃይ የሚመኝ ከንቱ ድርጅች፣ ከኢትዮጵያ ጥንተ ጠላቶች ጋር አብሮ እናቱን የሚዋጋ የዚህ ድርጅት መስራች መሆኔ ሁሌም ይቆጨኛል ሲሉም ዶ/ር አረጋዊ ሀሳባቸውን ገልጿል።
1👍1
ታማኝ መረጃ pinned «https://youtu.be/fhifk206qD8»
ሚስጥረስላሴ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድት እንደማትወክል ተገለፀ📌

የኢሕአፓ እና የትብብሩ ጸሃፊ ሚስጥረስላሴ የሽግግር መንግስት ይቋቋም የሚል አቋምን በሚያንጸባርቀው በነልደቱ አያሌው ስብስብ ጥሪ ላይ በመሳተፍ ሰለማዊ ትግል እንደማትቀጥልበት ምልክት ሰጥታለች።

በትብብር በኩል ከኢሕአፓ ጋር አጋር በሆነው የእናት ፓርቲ አባሉ አቶ ጌትነት በኩል ደሞ “እኛ እንደትብብር የሽግግር መንግስት የሚሉት ቡድኖች ህገ ወጥ በመሆናቸው እንደማንሳተፍ ወስነናል ፤ እዛ ላይ የተሳተፉት የትብብሩ አባላት በግል ፍላጎታቸው ላይ ተመሰርተው ነው የተሳተፉት” በሚል ነቀፌታቸውን አሰምተዋል።

በመሆኑም ይህ የምስጥረ ከጸረ ሰላም ሃይሎች ጋር ያላት ቁርኝት የበረታ መሆኑን የሚያሳይ አካሄድና ከትብብሩ አቋም ውጭ መንቀሳቀስ የፓርቲዋንም ሆነ የትብብሩን ገጽታ የሚያጠለሽ በመሆኑ ምናልባትም ግዜው ካልረፈደ ትብብር ለኢትዮጵያ አንድት ግለሰቧን ከጸሃፊነቷ ለማንሳት እንደሚንቀሳቀስ ምንም ጥርጥር አይኖረውም ።
በርካታ አመራሮች የተደመሰሱበት ኦፕሬሽን 📌

ደጀኑ ሰራዊታችን በሰሜን ጎጃም ዞን እና በደቡብ ጎንደር ባካሄደው ስምሪት የፅንፈኛ አመራሮችን ከነግበረ አበሮቻቸው በመደምሰስ እና በመማረክ ወጤታማ አፈፃፀም አስመዝግቧል 💪

ሰሜን ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ፣ ይልማናዴንሳ ፣ በጎንጂ ቆለላና አዴት ፣ በባህር ዳር ዙርያ እና በደቡብ ጎንደር ወረዳዎች በተካሄደ የተጠና ኦፕሬሽኖች እራሱን ዘመቻና የጦር አዛዥብሎ የሚጠራው ሻለቃ ሸዋነህ ሙልጌታ፣ ሃምሳ አለቃ ዘካርያስ፣ የልዩ ዘመቻ ሃላፊ ይነገር ተገኝ እና በርካታ ታጣቂዎች አብረው መደምሰሳቸው ታውቋል።

እንዲሁም ጌትነት ተፈራ የተባለ የፅንፈኛው ሐኪም እንዲሁም ሰውአለ ምኒችል የተባለ የፅንፈኛው ሎጀስቲክስም ተማርኳል።

በተጨማሪ ፅንፈኛው ከህዝብ ዘርፎ ሲገለገልባቸው የነበሩ አራት ተሽከርካሪዎች በሰራዊቱ ቁጥጥር ስር ውሏል።
👎2👍1
በህወሃት ፍቃድ ትግራይ የገባው ሻዕብያ

ሻዕብያ ትናንት በትግራይ ህዝብ ላይ የፈፀመዉ ዘግናኝ ጭፍጨፍ ሳይበቃዉ ዛሬም በህወሃት ላይ ታዝሎ ወደ ትግራይ በመግባት የትግራይን ህዝብ ከቤት ንብረቱ እያፈናቀለዉ ይገኛል።

ለአብነትም ትላንት (መጋቢት28/2018 ዓ.ም) የኤርትራ ሰራዊት የኤርትራ አዋሳኝ በሆነው በራማ አዲ አርባተ አቅራቢያ በሚገኘው የመርብ ወንዝ ወርቅና ማዕድን በማውጣትና በሌሎች ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ኑሯቸውን የሚገፉ የትግራይ ተወላጆችን ንብረታቸውንና ከብቶቻቸውን እየዘረፈ በኃይል ከመኖሪያቸው ማፈናቀሉ ተሰምቷል።

ህወሃት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ደጋግሞ በመጣስ ከሻዕቢያ ጋር በመሆን ጦርነት ቀስቃሽ ድርጊቶች መፈፀሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቸልታ ሊመለከቱት አይገባም።
ሹፌር ያገቱ የፅንፈኛው አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ🙌

በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ አከባቢ ከጎንደር ወደ ሁመራ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ መኪና ሹፌር የጃዊሳው ቡድን አባላት አግተው ወደ ጫካ የአከባቢው ህዝብ ከረዳቱ ባገኘው መረጃ መሰረት ተባብረው በመውጣት ከእገታው እንዳስለቀቁት እና ከጸጥታ ኃይል ጋር የፅንፈኛው አባላቶች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ማድረጋቸው ታውቋል።

ይህ የህብረተሰቡ ተግባር የፅንፈኛው ተግባር እንደማመረው እና ከእንግዲህ እንደማይታገሰው ማረጋገጫን የሚሰጥ ነው።

ሌሎች ዞኖችም ከዚህ ትምህርት በመውሰድ ከፀጥታ ኃይሉ በጋራ በመስራት የአከባቢውን ሰላም ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል 👍
👍1👎1
ጀነራል አልቡርሃን ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር ፍቃደኝነቱን ገልጿል📌

ህዝባዊ ተቃውሞ የተበራከተበትና ተስፋ የቆረጠው ጀነራል አልቡርሃን ወታደራዊ መንግስቱ ዲሞክራሲያዊ ሽግግር ለማድረግ እንዲሁም ስልጣኑን ለህዝብ ለማስረከብ ዝግጁ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ይህ የጀነራሉ ንግግር የፈጥኖ ደራሽ ሃይሉን መበርታትና ወደ ስልጣን መምጣቱን አይቀሬነት የሚያረጋግጥ ነው።

በተመሳሳይ ደሞ ከፈጥኖ ደራሽ ሃይሉ በተቃራኒ ቆመወ ለከረሙት ለእነ ኤርትራና ግብጽ ደግሞ ሌላ ስጋትን የሚጭር ውሳኔም ነው።

በተለይ ህወሃት የትግራይ ወጣቶችን ለሱዳኑ ጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን ጦር በገንዘብ በመሸጡ በፈጥኖ ደራሽ ኃይል ውስጥ በጣላትነት ተመዝግቧል።
👍43
ተመልካች ያጣው የባንዳዎች ጭወኃት 📌

በሚልየን የሚቆጠር ህዝብ ያየናል በሚል የኢንተርኔት ሰልፍ ያዘጋጀው የከሰረው ፖለቲከኛ ልደቱ አያሌው እንኳን በሚልየን ሊታይና አስር ሺ የሚደርስ የህዝብ ቁጥር እንኳን ሊያገኝ አልቻለም።

ላለመታየቱ በአንከር ሚድያ ላይ እንደምክንያት ያቀረበው “የኢትዮጵያ ህዝብ ዩቱብ ከማየት ወደ ቲክቶክ ስለዞረ ነው” ነበር ያለው።

እውነታው ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በአቋራጭ ስልጣን ለመያዝ ከሚታትሩ ፣ በጠላት ሃገር ተገዝተው አመጽ እና ብጥብጥን ከሚያነሳሱ እንዲሁም የህዝቡንም ሆነ የሃገር ጥቅም አሳልፈው ከሚሰጡት ጎን እንደማይቆሙያሳዩበት መሆኑ ነው ።
👍1
ምሬ ወዳጆ እጅ ለመስጠት ሂደቱን ጀምሯል 🚨

ምሬ ወዳጆ ከስህተቱ ተምሮ ለአማራ ህዝብ ደህንነት እና ሰላም ሲል እጅ ለመስጠት መንገድ መጀመሩ ተሰምቷል።

ካፕቴን ማስረሻ ሰጤ እጅ መስጠቱን እና ወደ ሰላም መምጣቱን ተከትሎ በአስረስ ማረ ትዕዛዝ የፋኖ ታጣቂውን ወንድሙን እንደገደሉበት የሚታወስ ነው።

ታድያ ይህንን ስራቸውን ጠንቅቆ የሚያውቀው ምሬ ወዳጆ እጅ የመስጠት ሃሳብ ላይ ስላለ እሱ ከገባ በኋላ ልጁን እንዳይገድሉበት ልጁን ቀድሞ በሰራዊቱ ቁጥጥር ስር በትላንትናው ዕለት እንዲውል ማድረጉ ታውቋል።

ምሬ ህዝብን ለመታደግ ወደ ሰላም መምጣት የሚደነቅ ነው
4👎2
የጄኔራል ታደሰ ወረደ ሹመት መራዘም እና የፅንፈኛው ዕቅድ📌

የጄነራል ታደሰ ወረደ ስልጣን ተራዘመ የሚለውን ጭምጭምታ ተከትሎ ፅንፈኛው ህወሓት ትላንት (መጋቢት 29/2018 ዓ.ም) የከተማና የወረዳ ምክር ቤቶችን አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት የፕሪቶሪያ የሰላም ሥምምነት ተጥሷል ሲል የጦርነት ነጋሪቱን ጎስሟል።

ይህም በመሆኑ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፈርሶ ከጦርነቱ በፊት በምርጫ የተመረጠው ሕጋዊ የሆነ መንግስት ይመለስ የሚል ውሳኔ እያስወሰነ መፈንቅለ መንግስቱን እያወጀ እንደሚገኝ ስምተናል።

ይህን ውሳኔውኔም የዓድዋ፣ የዓብይአዲ እና ሓሓይለ ከተማ መስተዳደሮች ተቀብለው ይሁንታ መስጠታቸው ታውቋል።
ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከሚታይባቸው የምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ሆናለች 🤩

ምሥራቅ አፍሪካ እ.ኤ.አ. በ2026 አኅጉራዊ የዕድገት መሪነት እንደሚይዝና ጠንካራ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የሚታይባቸው ሩዋንዳ፣ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ዋነኛዋ የአካባቢው የዕድገት ኃይል መሆኗን፣ የአፍሪካ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ (አፍሪ ኤግዚም ባንክ) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ለውጭ ገበያ የምትልካቸውን ቡና፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ቆዳና የማኑፋከቸሪንግ ውጤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ገበያ አቅሟን ማሳደግ እንደምትችል ሪፖርቱ አብራርቷል፡፡
የሁለት አሸባሪዎች እቅድ 📌

በወለጋ አካባቢ የሚንቀሳቀሰው ራሱን የወለጋ ቢንዛሞ ብሎ የሚጠራው የጃዊሳዉ ቡድን ክንፍ ታጣቂ የኦሮሞውን አርሶ አደር ከብት እንዲዘርፉ ቤታቸውን እንዲያቃጥሉ ውሳኔ ላይ ደርሷል።

በተመሳሳይ የሸኔው ታጣቂ ደግሞ በአካባቢው ያለውን የአማራውን ሃብት ንብረት እንዲያወድሙ እና የዕርስ በርስ ግጭት በመቀስቀስ ህዝቡን ለማፈናቀል እንደተወያዩ ከውስጥ የወጣው መረጃ ያሳያል።

ሁለቱም አሸባሪዎች በየፊናቸው ተከፋፍለው ኢትዮጵያን ገሀነም ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል።
👎1
🚨 ሰበር መረጃ 🚨

የጀነራሉ ስልጣን ለአንድ ዓመት ተራዝሟል ‼️

ጀነራሉ የአስተዳደሩን አመታዊ የግምገማ ሪፖርት ለጠቅላዩና ሌሎች የፌደራል አካላት አቅርበው ባስገመገሙ ማግስት ዛሬ መጋቢት 30 ነው የጀነራሉ ስልጣን ለተጨማሪ አንድ አመት መራዘሙ ይፋ የሆነው ።

ይህን የፌደራል መንግስቱን ውሳኔ ተከትሎም ጀነራሉን አስወግዶ የራሱን ሰው መሾም የሚፈልገው የነ ሞንጆሪኖ ስብስብ ቀጣይ ዕርምጃ ጀነራሉ ወደ መቀለ ከመመለሱ በፊት መፈንቅለ መንግስት መፈጸም ሊሆን እንደሚችል ፣ ሆኖም ስብስቡ ይህን ካደረገ የሚከተለው አጸፋ የከፋ በመሆኑ ምናልባትም እሱን ግምት ውስጥ በማስገባት የሃሳብ ለውጥ ሊያደርግ ይችላል የሚለውም የሚጠበቅ በመሆኑ የቡድኑ ዕርምጃ ላይ ሃምሳ ሃምሳ የሆነ ግምት ተይዟል ።

በመሆኑም ስብስቡ የጀነራሉን ሹመት እየመረረውም ቢሆን የሚውጠው ከሆነና ጀነራሉ በሰላም ወደ መቀሌ ከገቡ ያባከኑትን አንድ ዓመት ዞር ብለው በመገምገም በተጨመረላቸው ተጨማሪ የስልጣን ዘመን እዛ እና እዚህ መርገጣቸውን ትተው ለትግራይ ህዝብ የሚበጀውን ሊያደርጉ ይገባል እንላለን ።