✨ዜና✨
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
አዲስ ዓመት በመምጣቱ ጫማዎች ደስተኛ መሆናቸውን ተናገሩ፡፡
ከተለያየ ዓይነት ከኤርጌንዶ እስከ አንበሳ ጫማ ያሉ ጠቅላላ ጫማዎች ባካሄዱት ስብሰባ እና ባወጡት የአቋም መግለጫ እንደገለጹት ከሆነ የአዲስ ዓመት በዓል በመምጣቱ በጣም ደስተኞች ነን ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የስብሰባው አስተባባሪ የሆኑት ሸራ ጫማ ጉባኤውን ለማካሄድ ያነሳሳችሁ ዓቢይ ዓላማ ምንድነው ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ ማብራሪያ ሲሰጡ እኛ ይህን ስብሰባ እንድናካሂድ እና ደስታችንን እንድንገልጽ ያደረገን ዋናው ምክንያት ወደ ቤተ እግዚአብሔር የምንመጣበት ጊዜ የለንም አለቆቻችን ከፅድቅ ይልቅ ኃጢአትን ወደ ቅድስና ስፍራ ከመሄድ ወደ ጭፈራ መሄድን ስለሚመርጡ እኛ አምላካችንን የምናመሰግንበት ጊዜ አጥተን ጨንቆን ነበር፡፡ነገር ግን በዚህ በሚመጣው አዲሱ ዓመት ምእመናኑ በወረት ወደ ቤተ ክርስቲያን ስለሚመጣ እኛም በዚያው በረከት ስለምናገኝ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡በስተመጨረሻም አቶ ሸራ በሰጡት አስተያየት እባካችሁ የሰው ልጆች አምላካችሁን አትዘንጉ ቅድስናችሁን አታርክሱ እግሮቻችሁም እኛን ተጠቅመው ወደ ቤተ እግዚአብሔር ይገስግሱ ከኃጢአት ይሽሹ ለኛም በረከት ይትረፈን ሲሉ አስተያየታቸውን አጠናቀዋል፡፡
🌻

++ የመስቀል ሥነጽሑፍ !!
( መስቀል ኃይላችን ነው )
የነገር መስቀሉን መነሻ
የታሪኩን መዳርሻ
መርምራ ለማወቅ ብትሻ
እመቆስጠንጢኖስ ንግስት እሌኒ
ተደብቋት መቼ ቀረ
ምስጢር ሆኖ እንደተቀበር፡፡
በባዕድ ሃገር በኢየሩሳሌም
ሐይማኖቷን ደብቃ
ለእውነት ተነስታ ፀንታ ታጥቃ
ተራ ሰው መስላ ራሷን ንቃ
መስቀሉን አስቀድማ
ስታስፈልግ በገጠር በከተማ
ኪራኮስ እስራኤላዊው
በአምላክ ቃል እያፅናናት
የመስቀሉን ቦታ እየመራት
ደመራውን ደምራ
የዕጣኑ ጢስ ምልክት ሆኖ
መስቀሉ ተገኘ ተቆፍሮ
ምቀኞችን አሳፍሮ፡፡
ደውያንን እየፈወሰ
አንካሶችን እየረታ
ጎባጣዎችን እያነፃ
ዕውራንን እያበራ
ሙታንን እያስነሳ
ዜናው ተሰማ በዓለም ዙርያ፡፡
ጥበበኞች ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
መጎብኘታቸውን ያላወቁ
ሰላማቸውን የናቁ
መዳኛቸውን የርሱ
በስራቸው የረከሱ
መስቀሉን ቢቀብሩትም
አልቻሉም ሊሰውሩት
ከእሌኒ ንግስት ሊሸሽጉት
ዝናውን ከቁስጠንጥንያ
ከዚያም አልፎ በኢትዮጵያ
እየተባለ ሃሌ ሉያ፡፡
እስኪ እኛም ይመርብን
የመስቀሉን ቃል እንዲያድርብን
በአዲስ ምስጋና በዝማሬ
ደመራውን እንደምር
ተሰባስበን በመስቀሉ ዙርያ
መስቀል ኃይላችን ነው
መስቀል ፅንአችን ነው
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
እየተባለ እያሰተጋባ
እየተበተነ አደይ አበባ፡፡
🌻🌼🌻🌻🌼🌻🌻🌼🌻
( መስቀል ኃይላችን ነው )
የነገር መስቀሉን መነሻ
የታሪኩን መዳርሻ
መርምራ ለማወቅ ብትሻ
እመቆስጠንጢኖስ ንግስት እሌኒ
ተደብቋት መቼ ቀረ
ምስጢር ሆኖ እንደተቀበር፡፡
በባዕድ ሃገር በኢየሩሳሌም
ሐይማኖቷን ደብቃ
ለእውነት ተነስታ ፀንታ ታጥቃ
ተራ ሰው መስላ ራሷን ንቃ
መስቀሉን አስቀድማ
ስታስፈልግ በገጠር በከተማ
ኪራኮስ እስራኤላዊው
በአምላክ ቃል እያፅናናት
የመስቀሉን ቦታ እየመራት
ደመራውን ደምራ
የዕጣኑ ጢስ ምልክት ሆኖ
መስቀሉ ተገኘ ተቆፍሮ
ምቀኞችን አሳፍሮ፡፡
ደውያንን እየፈወሰ
አንካሶችን እየረታ
ጎባጣዎችን እያነፃ
ዕውራንን እያበራ
ሙታንን እያስነሳ
ዜናው ተሰማ በዓለም ዙርያ፡፡
ጥበበኞች ነን ባዮቹ
የአይሁድ ካህናት ግብዞቹ
መጎብኘታቸውን ያላወቁ
ሰላማቸውን የናቁ
መዳኛቸውን የርሱ
በስራቸው የረከሱ
መስቀሉን ቢቀብሩትም
አልቻሉም ሊሰውሩት
ከእሌኒ ንግስት ሊሸሽጉት
ዝናውን ከቁስጠንጥንያ
ከዚያም አልፎ በኢትዮጵያ
እየተባለ ሃሌ ሉያ፡፡
እስኪ እኛም ይመርብን
የመስቀሉን ቃል እንዲያድርብን
በአዲስ ምስጋና በዝማሬ
ደመራውን እንደምር
ተሰባስበን በመስቀሉ ዙርያ
መስቀል ኃይላችን ነው
መስቀል ፅንአችን ነው
መስቀል ቤዛችን ነው
መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
እየተባለ እያሰተጋባ
እየተበተነ አደይ አበባ፡፡
🌻🌼🌻🌻🌼🌻🌻🌼🌻
፨መስቀሉ በፊቴ፨
=======✞========
የቀራኒዮ አርማ የፍቅር ሰሌዳ
የሰላም ብራና ቀለሙን የቀዳ
የድህነት ማህደሯ ጠቋሚ መሪዋ
እንቅፋት ነቃፊ አዳኝ ጠባቂዋ
የሰማዩ ንጉስ ስጋው ቆርሶባት
ደሙን አፍስሶ ላቡን ደቅኖባት
የትውልድን አረም ሊነቅል ከስሩ
ባሪያውን መስሎ ወረደ ከክብሩ።
ኤሎሄ ብሎ ጮኸ አምላክ ሆኖ ሳለ
የጠላትን መንግስት ንዶ እየጣለ
ደብዳቤውን ደምስሶ በችንካሩ ፋቀው
የዕዳው ፅሕፈት በደሙ ጠረገው።
በመስቀል የዋለ ጎልጎታ ያደረ
እባቡን ቀጥቅጦ አዳምን የማረ
ሄዋንን ከጭንቀቷ ጎትቶ ያወጣት
ልጆቿን ከሲኦል አትርፎ ከእሳት
በመስቀሉ ገፅ በችንካሩ ጫፍ
በእሾህ አክሊል ብሳት በከሳሾቹ አፍ
መከራው ሲፀና ስቃዩ ሲበረታ
ፊቱን በጥፊ ሶስት ጊዜ ሲመታ
የአምላካችን ፍቅር ከልብ የፈለቀ
ቢሆን ነው እንጂ ይቅርታው የላቀ።
በቃ!
ታዲያ ከመስቀሉ ወዲያ መገለጫ ለእኔ
ከወዴት ይገኛል ማረፊያ ለአይኔ?
ኧረ ከየት ይመጣል ተግዳሮቱን ሚያክል
የዕዳዬን ጣጣ በነፍሱ ሚከፍል።
ትምክህቱ ይራቅ ከጌታዬ መስቀል በቀር
አይኔ ሌላ አያይም ከቀራኒዮ መንደር
የመስቀሉን ፍቅር የሚያደንቀው አለ
ልቤ ላይ ከትሞ ነፍሴ እየነዋለለ።
የክርስቶስ መስቀል በፊቴ ተስሎ
እኔ እንድጠነክር እርሱ ስለኔ ዝሎ
የምሸከመውን እርሱ ተሸክሞ
ለኔ እንዲበራ እርሱ ላይ ጨልሞ
መስቀሉን ደረሰው ፍቅሩን እየፃፈ
የአመፃን ማዕበል በምሕረት ቀዘፈ
ቸርነቱ በዝቶ ቅጣቱ አለፈ።
➴ከእህተ ማርያም
መጋቢት 10 የጌታችንና የመዳኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀል የተገኘበት ቀን ነው። ቀኑ በጾም ወረ ስለሆነ ወደ መስክርም17 እንዲከበር ተደርጓል ይህም ቁፋሮ የተጀመረበት ቀን ማለት ነው።

የደመራ ዓመት
መስቀል የከበረው ትናንት መስሏቸው
ያዩ ተገረሙ ክብሩ አስደንቋቸው
ትናንትና አይደለም የበራው ደመራ
ዘንድሮ ዓመት ፈጀ የመስቀሉ ሥራ
ስንት አይሁድ ተነሥተው መስቀሉን ቀበሩ?
ስንትስ እሌኒዎች ሊያወጡት ቆፈሩ?
ጅጅጋ ሲዳማ ውጡ ተናገሩ
ቤተ ክርስቲያን ልክ እንደ ደመራ
በእሳት ተለኩሳ ደምቃ ስታበራ
ካህናት ምእመናን እንደ ችቦ ነድደው
ስንቴ አከበሩት ለመስቀሉ ታርደው?
ስንት ጊዜ አፏጨ ዲያቢሎስ ተቆጣ
ስንት ሟርት ተሰማ ስንት ቁጣ መጣ?
በዕጣን ያልተገኘ ጌታ ያልሞተበት
ቅርፁ መስቀል ሆኖ መዳን የሌለበት
የወንበዴው መስቀል መስቀሉ መስሏቸው
ስንቶች ትተው ሔዱ ከእሌኒ እናታቸው?
ዓለም የዳነበት መስቀሉን ጨብጦ
ስለዘር የሚሰብክ እጅግ ተመስጦ
የተቃጠለውን መቅደስዋን እያየ
"ራስሽን አድኝ" ሲል ሲስቅ የታየ
ዘንድሮ አይደለም ወይ አይሁዱ የለየ?
ዘንድሮ ከበረ ለአንድ ዓመት ደመራ
በማያቆም ጥቃት በማያቆም ሴራ
ቅድስት ተዋሕዶ በጭንቅ ተወጥራ
አባቶችዋን ከፊት እንደ ጦር ሰድራ
በልጆችዋ ጩኸት በገና ደርድራ
በሰማዕታትዋ ደም ተረጭታና ርሳ
በየአደባባዩ ምሕላን አድርሳ
በፓትርያርክዋ ዓይን በምሬት አልቅሳ
እንደ ራሔል ለአምላክ ዕንባዋን አፍስሳ
ለመስቀሉ ቀን ግን ነጭ ልብስዋን ለብሳ
እንደ ቆስጠንጢኖስ በድል ልትነሣ
አምላክዋን ከፍ አድርጋ ኀዘንዋን ልትረሳ
ተስፋ ያደረገችው በመስቀል ታድሳ
ዘንድሮ ነው በዓል ዘንድሮ ደመራ
በዚህ ዓመት ተገኘን ከመስቀሉ ሥፍra
✍እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን መልካም በዓል 🕯
✍ ቡሩክ Ashebir

#በተለይ_ለኦርቶዶክሳውያን
አምልኮ/ምስጋና/ ማለት ክርስቶስ ራስ ለኾነላት ቤተ ክርስቲያን ለተባለችው አንዲት አካል ብልት ለመኾን የምንጋደልበት ሰማያዊ ሥርዓት ነው። ኦርቶዶክሳውያን በአምልኮ ጊዜ እርስ በእርሳችን ብቻ ሳይኾን ከመላእክትም ጋር ረቂቅ አንድነት አለን። "በሰላም ማሠሪያ (ይህን) የመንፈስ አንድነት ለመጠበቅ እንድንተጋም" ታዘናል። (ኤፌ.4÷3)።
ወደዚህ ሰማያዊ ኅብረት ይመጡ ዘንድም ለዓለም ኹሉ እንደ ሐዋርያቱ እንጮኃለን፤ "ወደ ክርስቶስ ኅብረት በሃይማኖት ኑ" እንላለን። "እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው " እንዲል ሐዋርያው።
(1ኛ ዮሐ. 1÷3)።
ይህን በማድረግ ፈንታ ግን በማይመች አካሔድ ከማያምኑ ጋር መሰለፍ በሃይማኖታችን አይፈቀድም። ስለዚህ ማንም ኦርቶዶክሳዊ በሌላ ማኅበረሰባዊ ጉዳይ እንጂ በሃይማኖት ከማያምኑ ጋር ቢተባበር ራሱን ለካህን ያሳይ፣ በንስሐ ይመለስ።
ወንጌላችንም የሚለው የሚከተለውን ነው:-
"ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው?" (2ኛ ቆሮ. 6÷14-15)።
እኔም እላለሁ - ኦርቶዶክሳዊ ከኢሬቻ/ዋቄፈና ጋር ምን ኅብረት አለው?
+ የኢሬቻና የኢኩሜኒዝም አካሔድ መመሳሰል - ሌላው ሥጋት?
የዓለማዊነት (Secularism) አቀንቃኞች ከፖለቲካ ዲሞክራሲን ፣ ከምጣኔ ሀብት የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ፣ ከሃይማኖት ፕሮቴስታንቲዝምን ይመርጣሉ፣ ይደግፋሉ። እነዚህ ሦስቱም በዓለማዊነት አቀንቃኞች መደገፋቸው: ለአንድ ማኅበረሰብ በኹሉም መልክ ለዘብተኝነትን ( Liberalism) ስለሚያለማምዱ ነው። አንድ ማኅበረሰብእ ለዘብተኛ ከኾነ ደግሞ ቸልተኝነቱ ይጨምርና ኹሉን ችላ በማለት በእነርሱ ቁጥጥር ሥር ለመዋል ምቹ ይኾናል። ስለዚህ ለዚህ አካሔድ ወግ አጥባቂ (Conservative) ኾነው የሚያስቸግሯቸው ኦርቶዶክሶች ኹሉ (Orthodox Christians, Orthodox Jews, Orthodox Muslims) ጥርስ ውስጥ የገቡ ናቸው። በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የመሰሉ በሥርዓትና በዜማ የደመቁ አብያተ ክርስቲያናትን ለዘብተኛ ለማድረግ በተሐድሶ እንቅስቃሴና በተለያዩ መንግሥታዊ ተጽዕኖዎችም ጭምር እንዲጎዱ ተደርጓል።
ለዚህ ለዓለማዊነት እንቅስቃሴ የተሸረበው ሌላው ሴራ ደግሞ (ምንም እንኳን ጠቃሚ ጎን ቢኖረውም) የኢኩሜኒዝም (Ecumenism) እንቅስቃሴ ነው። ይህን እንቅስቃሴ በቅርቡ እነ ዶክተር ወዳጄነህን የመሳሰሉት እንደሚከተሉት በግልጽ አስረድተው ነበር። በዚሁ እንቅስቃሴ ስም የሚንቀሳቀሱት አንዳንዶች ታዲያ "ከኹሉም ሃይማኖት ጥሩ ጥሩውን ፣ የጋራውን እንውሰድ" በሚል መርሕ ሌላ ዓይነት ፕሮቴስታንቲዝምን ይዘውና ሃይማኖትን በልካቸው አበጅተው ብቅ ብለዋል። ይህንን የሚደግፉት በዋናነት ግላዊነትን የሚያበረታቱት ፕሮቴስታንቶችና ዓለማውያን ናቸው።
ኢሬቻም የዚሁ ኮፒ እየኾነ ነው። በኦሮሞ ፕሮቴስታንቶችና በፕሮቴስታንታዊው ኦዲፒ ከሞላ ጎደል ካለ ምንም ማንገራገር ይደገፋል። ኢኩሜኒዝም በክርስትና ስም የሚንቀሳቀሱትን ማዕከል ያደረገ ቢሆንም፣ ኢሬቻ/ዋቄፈና ደግሞ ሙስሊሙንም፣ ኦርቶዶክሱንም ፣ ፕሮቴስታንቱንም ማዕከል አድርጓል። ይህም በተለይ ኦርቶዶክሱን በኦሮሙማ ስም ከኦርቶዶክሳዊነት ለማለዘብ የተነደፈ ሴራ ይመስላል።
"ምን ችግር አለው?" የሚል ለዘብተኛ ኦርቶዶክስ ደግሞ በስም እንጂ በግብር የቤተ ክርስቲያን ሊኾን አይችልም። ስለዚህ በተለይ የኦሮሞ ኦርቶዶክሳውያን ትልቅ አስተዋይነትን የሚጠይቅ ጊዜ ላይ እንዳላችሁ ልትገነዘቡት ይገባል። ከኦርቶዶክሳዊነትና በተወዳጅ ባሕል ስም ከመጣ ሌላ እምነት መካከል ያላችሁ የምትወስኑበት ጊዜ እንደኾነ ይሰማኛል።
ኹለቱንም መኾን አይቻልም። ወይ ከጊዜ በኋላ በቅርቡ የሚበርደውን የወቅቱን ሞቅታ መምረጥ ወይም ደግሞ ካለችበት ከፍታ ላይ ሳትወርድ ለዘመናት የኖረችውን ተዋሕዶን መምረጥ ያሻል።
እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንንና ምዕመኖቿን፣ ሀገራችንንና ዜጎችን ይጠብቅልን። አሜን።

የከበሮ ምሳሌ
~ቤተክርስቲያናችን በዘፈቀደ የምትመራ አይደለችም
ስርአቷን ጠብቃ በሚስጥርና በማስተዋል በመመርመር
የምትተዳደር ናት እንጅ።
==>የከበሮ አመታት፦ ከበሮ ሲመታ ቀጥ ተብሎ
አይመታም፤ መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ይመታሉ
ይህም ጌታ ከሐና ቀያፋ ፤ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ
ያደረገውን እንግልት ያስታውሰናል።
==>ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ ይመታና በፍጥነት
ይዘዋወራል ይህም ጌታችንን አይሁድ እንደያዙት
መጀመሪያ በቀስታ እየዘበቱ ይመቱት ነበር፤ በኋላ ግን
ጲላጦስ ተመራምሮ ነፃ ሳያወጣው የሰንበት ቀንም
ሳይገባብን ኑ እንደብድበው የማለታቸው ምሳሌ ነው።
==>በማሕሌት ላይ ከበሮው መሬት ላይ ተቀምጦ ሲመታ
ጌታችን መሬት ላይ ወድቆ መንገላታቱን ለማሳየት ነው።።።
።።።።። ።።።።።።።የከበሮ 2 ክፍሎች
==>ከበሮ ስታስቀምጡ ሁልጊዜ ሰፊው አፍ ወደ ላይ
መሆን አለበት፤ ትንሹን ክፍል ወደ ላይ ካስቀመጥን ግን
ስህተት ነው።
==>ሰፊው የከበሮ ክፍል የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ይህም
የጌታችንን የባህርይ አምላክነትና ምሉዕ በኹለሄ መሆኑን
ለሥልጣኑ ወሰን ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው።
==>ጠባቡ የከበሮ ክፍል ደግሞ የትስብእት ምሳሌ ነው፤
ይህም ጌታችን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ
ሥጋን ተዋህዶ መገለጡንና የዮሐንስ ወንጌልን
ያስታውሰናል
==>በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ “ቃልም እግዚአብሔር ነበረ … ቃልም ሥጋ
ሆነ” [ዮሐ. 1-14]
==>ከበሮ የሚለብሰው ልብስ አይሁድ ጌታችንን በእለተ
አርብ ያለበሱት የቀይ ከለሜዳ አና እንዲሁም አይኑን
የሸፈኑበትና በጥፊ እየመቱ ትንቢት ተናገር ማን መታህ
በማለት የዘበቱበት ምሳሌ ነው።
==>በከበሮው ላይ የተጠላለፈው ጠፈር በጌታችን ጀርባ
ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። የከበሮው
ማንገቻ አይሁድ ጌታን የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው።
(ልብሱን ገፍፈው ቀይልብስ አለበሱት ማቴ 27፥28)።።።
==>ከበሮ ውስጥ የሚደረጉ 3 ወይም 5 ጠጠሮች፦
*3* ከሆኑ ምስጢረ ስላሴን *5* ጠጠሮች ከሄኑ ደግሞ
አምስቱ አእማደ ምስጢራትን ያስረዳል።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ
ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች
ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለችና!!
~ቤተክርስቲያናችን በዘፈቀደ የምትመራ አይደለችም
ስርአቷን ጠብቃ በሚስጥርና በማስተዋል በመመርመር
የምትተዳደር ናት እንጅ።
==>የከበሮ አመታት፦ ከበሮ ሲመታ ቀጥ ተብሎ
አይመታም፤ መዘምራን ግራና ቀኝ እያሸበሸቡ ይመታሉ
ይህም ጌታ ከሐና ቀያፋ ፤ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ
ያደረገውን እንግልት ያስታውሰናል።
==>ከበሮ መጀመሪያ በርጋታ ይመታና በፍጥነት
ይዘዋወራል ይህም ጌታችንን አይሁድ እንደያዙት
መጀመሪያ በቀስታ እየዘበቱ ይመቱት ነበር፤ በኋላ ግን
ጲላጦስ ተመራምሮ ነፃ ሳያወጣው የሰንበት ቀንም
ሳይገባብን ኑ እንደብድበው የማለታቸው ምሳሌ ነው።
==>በማሕሌት ላይ ከበሮው መሬት ላይ ተቀምጦ ሲመታ
ጌታችን መሬት ላይ ወድቆ መንገላታቱን ለማሳየት ነው።።።
።።።።። ።።።።።።።የከበሮ 2 ክፍሎች
==>ከበሮ ስታስቀምጡ ሁልጊዜ ሰፊው አፍ ወደ ላይ
መሆን አለበት፤ ትንሹን ክፍል ወደ ላይ ካስቀመጥን ግን
ስህተት ነው።
==>ሰፊው የከበሮ ክፍል የመለኮት ምሳሌ ነው፤ ይህም
የጌታችንን የባህርይ አምላክነትና ምሉዕ በኹለሄ መሆኑን
ለሥልጣኑ ወሰን ድንበር እንደሌለው የሚያስታውሰን ነው።
==>ጠባቡ የከበሮ ክፍል ደግሞ የትስብእት ምሳሌ ነው፤
ይህም ጌታችን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ
ሥጋን ተዋህዶ መገለጡንና የዮሐንስ ወንጌልን
ያስታውሰናል
==>በመጀመሪያ ቃል ነበረ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ
ነበረ “ቃልም እግዚአብሔር ነበረ … ቃልም ሥጋ
ሆነ” [ዮሐ. 1-14]
==>ከበሮ የሚለብሰው ልብስ አይሁድ ጌታችንን በእለተ
አርብ ያለበሱት የቀይ ከለሜዳ አና እንዲሁም አይኑን
የሸፈኑበትና በጥፊ እየመቱ ትንቢት ተናገር ማን መታህ
በማለት የዘበቱበት ምሳሌ ነው።
==>በከበሮው ላይ የተጠላለፈው ጠፈር በጌታችን ጀርባ
ላይ የታየው የግርፋት ሰንበር ምሳሌ ነው። የከበሮው
ማንገቻ አይሁድ ጌታን የጎተቱበት ገመድ ምሳሌ ነው።
(ልብሱን ገፍፈው ቀይልብስ አለበሱት ማቴ 27፥28)።።።
==>ከበሮ ውስጥ የሚደረጉ 3 ወይም 5 ጠጠሮች፦
*3* ከሆኑ ምስጢረ ስላሴን *5* ጠጠሮች ከሄኑ ደግሞ
አምስቱ አእማደ ምስጢራትን ያስረዳል።
ቤተክርስቲያን ከጣራዋ እስከ መሬቷ ሁሉም ሥርዓቷ
ያስተምራል ፤ ባህረ ጥበብ ቤተክርስቲያን እየተናገረች
ታስተምራለች ሳትናገር ዝም ብላም ታስተምራለችና!!
በእንድ ወቅት አንድ ገበሬ አህያው ጉድጎድ ውስጥ ትገባበታለች፡፡ ጉድጓዱ ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ አህያዋ በራሷ ለመውጣት በእጅጉ ተቸገረች በጣምም መጮህ ጀመረች ባለቤቱም አህያዋን ለማውጣት ብርቱ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለተ አልቻለም፡፡
አህያዋም ብዙ ያገለገለችና ያረጀች ስለሆነች እንዲሁም ሌሎች እንስሳትም ወደ ጉድጓዱ እንዳይገብበት በማሰብ ጉድጓዱ ውስጥ ሊቀብራት ወሰነ፡፡
ጎረቤቶቹንም አስተባብሮ ጉድጓዱን በአፈር መሙላት ጀመረ አህያዋ ይህን ስትመለከት እየቀበራት መሆኑነ ተረዳችና በሰቀቀን አለቀሰች፡፡ይሁን እንጂ አህያዋ አፈር ሲደፋባት አንድ ነገር ታደርግ ጀመር፡፡ አፈሩ በተደፋባት ቁጥር አፈሩን እያራገፈች ከአፈሩ ውስጥ ብቅ ትል ጀመር፡፡በተደጋጋሚ ከሚደፋባት አፈር ላይ መቆምም ትጀምራለች፡፡
በሂደት ውስጥ በአፈሩ ላይ በቆመች ቁጥር ከነበረችበት ጉድጓድ ከፍ እያለች ከፍ እያለች በመጨረሻም ጉድጓዱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ መውጣት ቻለች፡፡
በሚገርም ሁኔታ አህያዋን ሊቀብሯት የሞከሩት ሰዎች በአህያዋ አወጣጥ በእጅጉ ተደነቁ፡፡
ሰው ያስባል ፈጣሪ ይፈፅማል!

አባቶቻችን እንዲህ አሉ፦
"እሳትና ውኃን ማዋሐድ እንደማይቻል በሌሎች ኃጢአት መፍረድም በራስ ኃጢአት ከመጸጸት ጋር አብሮ አይሔድም።"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
"የማያማትብ እጅ ቀኙም ግራውም አንድ ነው።"
አባ ፓስዮስ ዘደብረ አቶስ
"እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያለው ፍቅር ጻድቅ ሰው ለእግዚአብሔር ካለው ፍቅር ይበልጣል።"
አባ አርሳኒ
"ሕፃን ልጅ እናቱ ስታጥበው ያለቅሳል:: ሕፃን እምነት (ትንሽ እምነት) ያላቸው ሰዎችም ነፍሳቸውን የሚያጥብ መከራ ሲመጣባቸው እግዚአብሔርን ያማርራሉ።"
አባ ስምዖን
"ዕለትን የሠጠህ እርሱ ለእለት የሚበቃህንም ይሠጥሃል።"
ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
"እጅግ ምርጡ ጸሎት "ጌታ ሆይ አንተ ሁሉን ታውቃለህ የፈቀድከውን አድርግልኝ" ማለት ነው።"
ባሕታዊ ቴዎፋን
"ሲያመነዝር ያየኸውን ሰው አንተ ንጹሕ ብትሆንም አትናቀው። ምክንያቱም አታመንዝር ያለው ጌታ አትፍረድም ብሏል።"
አባ ቴዎዶር
"አንድ ሰው ኃጢአት ሲሠራ ብታይ እንኳን አትፍረድበት:: አንዳንዴ ዓይንህም ሊሳሳት ይችላል።"
ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰዋስው
"ለኃጢአተኛው ክንፍህን ዘርጋለት:: ኃጢአቱን ልትሸከምለት ባትችል እንኳን ሸፍንለት።"
ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ
ከአበው አንዱን ትሕትና ምንድርን ነው? ብለው ጠየቁት:: እርሱም "ትሕትና ማለት ወንድምህ በበደለህ ጊዜ እርሱ ይቅርታ ሳይጠይቅህ በፊት ቀድመህ ይቅር ማለት ነው" አለ።
"ይቅር ካላልክ ገነትም ይቅርብህ።"

እመቤታችን ሆይ የሚለው ፀሎት ከየት መጣ!!
👉አንድ እህቴ እንዲህ በማለት ጥያቄ
ጠየቀቺኝ እናተ ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ
አባታችን ሆይ ካላቹ ቡሀላ እመቤታችን
ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት
ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው
ስለዚህ መፀለይ የለበትም አለቺኝ!!
እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን
የተወደደች እናታችንን
እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን
እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦
👇👇👇👇
እመቤታችን ንፅህት
ቅድስት ድንግል (ማቴ1:23)
ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2)
በመልአኩ በቅድስ ገብርኤል ሰላምታ
ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28)
በሀሳብሽ ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2
ንፅህት )
በሥጋሽም ድንግል ነሽ(ማቴ1:23)
(ህዝ44:2)
ያሸናፊ የልዑል እናት ሆይ (ሉቃ1:35)
ሰላምታ ላንች ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ
(ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32)
የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32)
ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ
ልዑል እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና
(ሉቃ1:28-30)
ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ
ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን
በቆሮ5:20
#በፅድቅ #ስራ #የኖሩት #ይለምኑ #ዘንድ
#ተሰጥቷቸዋልና
#ሃጢአታችንም #ያስተሰርይ #ዘንድ #ለዘላለሙ
#አሜን
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን
የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን
ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሔር ልቦና
ይስጣቸው፡፡ አሜን፫
👉አንድ እህቴ እንዲህ በማለት ጥያቄ
ጠየቀቺኝ እናተ ኦርቶዶክሶች ስትፀልዩ
አባታችን ሆይ ካላቹ ቡሀላ እመቤታችን
ብላቹ እምትፀልዩት ፀሎት
ፍፁም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ ነው
ስለዚህ መፀለይ የለበትም አለቺኝ!!
እንግዲህ እኛም ተዋህዶ እንዳስተማረችን
የተወደደች እናታችንን
እንዲህ እያልን ከቃሉ ሳንወጣ በፀሎታችን
እንጠራታለን
እንዲህም እንላለን፦
👇👇👇👇
እመቤታችን ንፅህት
ቅድስት ድንግል (ማቴ1:23)
ማሪያም ሆይ(2ቆሮ11:2)
በመልአኩ በቅድስ ገብርኤል ሰላምታ
ሰላም እንልሻለን (ሉቃ1:28)
በሀሳብሽ ድንግል ነሽ (2ቆሮ11:2
ንፅህት )
በሥጋሽም ድንግል ነሽ(ማቴ1:23)
(ህዝ44:2)
ያሸናፊ የልዑል እናት ሆይ (ሉቃ1:35)
ሰላምታ ላንች ይገባሻል
ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንች የተባረክሽ ነሽ
(ሉቃ1:28 ናሉቃ1:32)
የማህፀንሽ ፍሬ የተባረከ ነው (ሉቃ1:32)
ፀጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ
ልዑል እግዚአብሔር ካንች ጋር ነውና
(ሉቃ1:28-30)
ከተወደደው ከልጅሽ ከጌታችን
ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ
ይቅርታና ምህረትን ለምኝልን
በቆሮ5:20
#በፅድቅ #ስራ #የኖሩት #ይለምኑ #ዘንድ
#ተሰጥቷቸዋልና
#ሃጢአታችንም #ያስተሰርይ #ዘንድ #ለዘላለሙ
#አሜን
እኛም ይህን ከመፀለይ ቸል ብለን
የእናታችንን ውለታ አንረሳም፡፡
ነገር ግን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ተዋህዶን
ሊተቹ የሚነሱትን እግዚአብሔር ልቦና
ይስጣቸው፡፡ አሜን፫
Forwarded from Safaricom Ethiopia
🎁Safaricom ethiopia ሽልማት🎁
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
🎁ለእርስዎ እና ለ2 ጓደኛዎ የ 3000 ብር ስጦታ
🎁smart phone( s21 ultra)
🎁Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ
ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ ◔͜͡◔ BirukAshebir 19 ◔͜͡◔ ብቻ ነው
https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r08649280900

Blog
>
2019>
January>
16>
Biblical Teachings>
ከሞት በኋላ ምን ይሆናል?
ከሞት በኋላ ምን ይሆናል?
Post author:admin
Post published:January 16, 2019
Post category:Biblical Teachings
ክፍል ሁለት
“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው” ዕብራውያን 9.27
በዕብራውያን መልእክት ውስጥ የሚገኘውና ከዚህ በላይ የተቀመጠው ጥቅስ የሚያሳየው ስለ ሞት ነው፡፡ ለሰዎች አንድ የማይቀር ነገር መሞት ተመድቦባቸዋል፡፡ ሞት እውነትና በፍፁም ሊቀር የማይችል ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሞት ወደዚህ ዓለም እንዴት እንደመጣ በምን ምክንያት እንደመጣ እና የሰው ልጅ የተባለ በሙሉ ለምን እንደሚሞት ይናገራል፡፡ ሞት የሚለው ቃል በመጀመሪያ የተነገረው ወደዚች ዓለም ከመግባቱ በፊት ነበር የተነገረውም ወደ ዓለምና ወደሰዎች ልጆች ታሪክ ውስጥ እንዳይገባ ለማድረግ ነበር፡፡ ይህም እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን በሰጠው የመጀመሪያው ትዕዛዝ ውስጥ ተቀምጧል፡ “እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው። እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው። ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።” ዘፍጥረት 2.15-17፡፡
ይህ ትዕዛዝ ከተሰጠ ብዙ ሳይቆይ ትዕዛዙ ተጣሰ አዳምና ከዚያም ዘሩም ሁሉ ሞትን የሚሞቱ ሆኑ፡፡ ይህንን በማወቅ ነው ሐዋርያው በሮሜ ምዕራፍ 5 ውስጥ ከቁጥር 12 ላይ “ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት ለሰው ሁሉ ደረሰ፤” በማለት የሞትን ምክንያትና ሞት ለሰው ሁሉ እንዴት እንደደረሰ ይነግረናል፡፡
ከሞት በኋላ ምን ይሆናል? በሚል ርዕስ የቀረቡት እነዚህ ሁለት ተከታታይ ጽሐፎች ሐሳብ ከሞት በኋላ ምን እንደሚሆን ትንሽ እይታን በመስጠት አንዳንዶችን ለማንቃት ነው፡፡ እናም በክፍል አንድ ካያነው ቀጥሎ የሚከተለውን እስኪ እንመልከት፡
ከሞትኩ በኋላ የምሰራው ምንድነው?
የምድር ስራዬ እንደጌታ ፈቃድ ከሆነ!
አሁን ሳልሞት በፊት በሕይወት እያለሁ የምሰራው ነገር ምንድነው? ጌታ ኢየሱስ የእኔ ጌታ ሆኖ እርሱን በማስቀደም እየኖርኩ ነውን፣ የእርሱ አገልግሎት የእኔ ደስታዬ ነውን፣ የእርሱ ክብር የእኔ ፍፃሜ ነውን? አሁን እኔ የምኖረው ለእግዚአብሔር ከሆነ፣ የምራመደውም ከእግዚአብሔር ጋር ከሆነ፣ የምኖረው እርሱን ለማስደሰት ከሆነ፤ በዓለም ውስጥ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ በጣም እድለኛ ሰው ነኝ ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ከሞትሁ በኋላ የምሰራው በጣም አስደናቂና ግሩም ስለሆነ ነው፡፡ ከሞትሁ በኋላ ዋናው ስራዬ እርሱን ለዚያ የመንግስተ ሰማይ ክብር ያበቃኝን የወደኝንና የወደድኩትን ጌታ ማክበር፤ ስሙን ማክበር ይሆናል፡፡ እርግጥ ነው ስራዬ ፍቅሩን ማድነቅ ይሆናል፣ ከዚህም በላይ የእርሱን ክቡር ፍፁምነት ከፍ ከፍ ማድረግ ይሆናል፡፡ በእዚያ በመንግስተ ሰማይ የእኔ ሌላው ስራዬ የሚሆነው ደስታዬ ነው፣ መደሰት ሐሴት ማድረግ ሌላው አግልግሎቴ ነው፣ ያም የማያልቅ እና ገደብ የሌለው የየዕለቱ ተግባሬ ነው፣ ሌሊትም ቀንም በእርግጥ እንደዚህ የሌሊትና የቀን ገደብ በዚያ ባይኖርም ለማለት የፈለግሁት ሁልጊዜ መደሰት ስራዬ ነው፡፡ በዳኑት መካከል እቆማለሁ፣ ነጭ በነጭ ለብሼም ከክርስቶስ ጋር እመላለሳለሁኝ የእርሱንም ስም የወርቅ በገናዬን ይዤ ለዘላለም በዘላለም እውነተኛ ዜማዎች ማክበር ይሆናል፡፡
እነዚህን ከላይ የጠቀስኳቸውን ስራዎቼን ሳከናውንም እዚያ ለእኔ የማይኖሩኝን ነገሮች መጥቀስ ይኖርብኛል እነዚህም፡
እዚያ በመንግስተ ሰማይ የተከፋፈለ ሐሳብ (ሁልጊዜ የሚዞር ሐሳብ) አይኖረኝም፣ የተምታታ ሃሳብና የማይጨበጡ ግምቶችና ስጋዊ የቀን ህልሞች አይኖሩኝም፡፡ ልቤን ለመከፋፈል የሚፈትነኝ የሰይጣን አሰራር አይኖርም፣ ልቤ ንፁህ ስለሚሆን የተበላሸ ሐሳብ ምኞትም ሁሉ አይኖረኝም፣ ስለዚህም የምሰራቸው ስራዎች ሁሉ ንፁሃን ይሆናሉ፡፡
ቅዱስ ያልሆነ ህብረትና ጓደኝነት እዚያ ያለኝን አገልግሎት ሊያቋርጠው ሊረብሸው ወይንም ሊያደናቅፈው አይችልም፡፡ እዚያ የሚኖረው ሁሉ እንደ ብርሃን ንፁህ ነው፣ እንዲሁም ልክ እንደ እግዚአብሔር እቅፍ ሰላም የሞላበት ነው፣ በእግዚአብሔር ህልውና ትክክለኛ እውቀት ውስጥ ስለሚደረግ ሰላምና ደስታ የሞላበት ነው፡፡ እዚያ ስለማንኛውም ነገር ጭንቀት እንዲሁም ሐዘን የሚባል ነገር አይኖረኝም

Arif gitim NW anbibut y silase lijoch
✝ምንድን🤔 ነው ድርሻዬ✝
ሰው ሆይ እስቲ ዕወቅ
ዕዋቂውን ጠይቅ
ምንድን ነው ድርሽዬ
ንገረኝ ጌታዬ!
ድርሻህን ሳትለየው
ጉዞ አትጀምር
እንዲያው በግርግር
ምንድን ነው ሥራዬ
ንገስኝ ጌታዬ
በልና ጠይቀው
በጸሎት አሳስበው
ሥራህን ዕወተው
ድረሻህን ተረዳው
ልከተል ጊዮርጊሰን
ቅድስት ኢየሉጣን
ሕፃኑ ቂርቆስን
ሠለስቱ ደቂቅን
የሰማዕቱን ሕይወት
ዋጋ እንዳገኝበት
በኃይልህ በረከት
ወይስ በዓለም ልዙር
ወንጌልን ላስተምር
ላልሰሙት ልናገር
የልደትሁን ምሥጢር
ለልምድ ተመላላሽ
በአካል ብቻ ገሥጋሽ
በማያውቁት መኻል
ልናገር ያንተን ኃይል
ላስተምር ጥምቀትን
እንዲሁም ስቅለትን
ልናገር ስለዕርገት
ስለ ዳግም ምፅዓት
ወይንስ ጌታዬ
መካሪ አለኝታዬ
በበአት ልወሰን
በጸሎት ልለምን
ያልተከተለህን
ያላወቀ ሕግን
እንድታሳውቀው
በፍቅር እንድትቀርበው
ከግባበት ዓለም
እንዲድን በአንተ ደም
መካሪ አለኝታዬ
የሆነውን ለእኔ
ባለችኝ ዘመኔ
በልና ጥይቀው
ድርስህን ዕወቀው
ለእኛ የሆነውን
ባለን ዘመናችን
የምንፈጽመውን
እንድታሳውቀን
ቸር ፍቃድህ ይሁን
ማለቱ ይሻላል
እርሱም ይመራናል።
መንፈሳዊ ግጥም
https://t.me/httpbiruk
✝ምንድን🤔 ነው ድርሻዬ✝
ሰው ሆይ እስቲ ዕወቅ
ዕዋቂውን ጠይቅ
ምንድን ነው ድርሽዬ
ንገረኝ ጌታዬ!
ድርሻህን ሳትለየው
ጉዞ አትጀምር
እንዲያው በግርግር
ምንድን ነው ሥራዬ
ንገስኝ ጌታዬ
በልና ጠይቀው
በጸሎት አሳስበው
ሥራህን ዕወተው
ድረሻህን ተረዳው
ልከተል ጊዮርጊሰን
ቅድስት ኢየሉጣን
ሕፃኑ ቂርቆስን
ሠለስቱ ደቂቅን
የሰማዕቱን ሕይወት
ዋጋ እንዳገኝበት
በኃይልህ በረከት
ወይስ በዓለም ልዙር
ወንጌልን ላስተምር
ላልሰሙት ልናገር
የልደትሁን ምሥጢር
ለልምድ ተመላላሽ
በአካል ብቻ ገሥጋሽ
በማያውቁት መኻል
ልናገር ያንተን ኃይል
ላስተምር ጥምቀትን
እንዲሁም ስቅለትን
ልናገር ስለዕርገት
ስለ ዳግም ምፅዓት
ወይንስ ጌታዬ
መካሪ አለኝታዬ
በበአት ልወሰን
በጸሎት ልለምን
ያልተከተለህን
ያላወቀ ሕግን
እንድታሳውቀው
በፍቅር እንድትቀርበው
ከግባበት ዓለም
እንዲድን በአንተ ደም
መካሪ አለኝታዬ
የሆነውን ለእኔ
ባለችኝ ዘመኔ
በልና ጥይቀው
ድርስህን ዕወቀው
ለእኛ የሆነውን
ባለን ዘመናችን
የምንፈጽመውን
እንድታሳውቀን
ቸር ፍቃድህ ይሁን
ማለቱ ይሻላል
እርሱም ይመራናል።
መንፈሳዊ ግጥም
https://t.me/httpbiruk
Telegram
🌻🌻ደ/ታ ቅ/ሥ ሰ/ት/ቤ መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ከ ብሩክ🙏🌻🌻
የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መንፈሳዊ ስነ-ጽሁፍ፣ስነ-ግጥም፣ትረካ፣አጫጭር ጭውውቶች...የተለያዩ ኪነ-ጥበብ የሆኑ ነገሮች አሏችሁ? በሉ ገባ ገባ በሉ
ምን አይነት ዕድለኛ ነህ?!
እሳትን የሚያበርደው ውሀ ነው፣ አልጫን የሚያጣፍጠው ጨው ነው፣ ያንተን ህይወት ጣዕም የሚሰጠው ፈጣሪ ነው። ደስታን ለማግኘት ማንኛውንም ዋጋ ልትከፍል ትችላለህ፤ ብዙ ነገር አሳክተው ደስታን የጨበጡ የመሰላቸው ሰዎች ዘግይተውም ቢሆን ንፋስ እንደዘገኑ አውቀዋል።
እውነተኛ ደስታ ከፈለክ ፈጣሪ እስከዛሬ ባደረገልህ፣ አሁን ባለህ ነገር አመስግን፤ "ምን አይነት ዕድለኛ ነኝ?" በል፤ ገና በሚመጣው ሳይሆን አሁን ህይወትህ ላይ ያለውን እይና ተደሰት! አበቃ!

ዳዊት, [1/1/23 11:27 PM]
[ተክለአብ.docx]
ዳዊት, [1/1/23 11:29 PM]
የአቡነ ተክለሀይማኖት ታሪክ
ከአባታቸው ከጸጋ ዘአብ(ዘርአ ዮሃንስ) እና ከእናታቸው ከቅድስት ዘሃርያ(ሣራ) በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት በመጋቢት 24 1196 ተጸንሰው በዕለተ ሰኞ ታህሳስ 24 1197 ዓ.ም በቡልጋ፣ ሸዋ በዘመነ ዛግዌ ሥርወ መንግሥት ተወለዱ ። እንደተወለዱም ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመሰገኑ። በ3ተኛውም ቀን ደግሞ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስም ብለው አመስግናዋል። ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍስሐ ጽዮን አሏቸው።ይህም የጽዮን ደስታ ማለት ነው:: ከአባታቸው ጸጋ ዘአብ ሥርዓተ ቤ/ክ እየተማሩ በ15 እና በ22 ዓመታቸው በዘመኑ ከነበሩት ጳጳስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ዘእስክንድሪያ ዲቁና እንዲሁም ቅስና ተቀበሉ።
ከጓደኞቻቸው ጋር ለአደን ወደ ጫካ በወጡ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል ተገልጦላችው፣ "እኔ እናትና አባትህን ስለአንተ ከውሃ ስጥመትና ከምርኮ ያዳንኩኝ ቅዱስ ሚካኤል ነኝ" አላቸው በታላቅ ብርሃን ተገልጦላቸው ባዩት ጊዜ አላወቁትም ነበርና። ደግሞም እንዲህ አላቸው "ከእንግዲህ ሙታንን ታስነሳለህ፣ ደውያንንም ትፈውሳለህ፣ አጋንንትም ከአንተ ይሸሻሉ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ፍስሐ ጽዮን አይሁን ተክለሀይማኖት እንጂ" ብሏቸው ከአጠገባቸው ተሰወረ (ተክለሀይማኖት ማለት ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈስ ቅዱስ ወይንም የሥላሴ ተክል ማለት ነው) ። ጌታችንና አማላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ከሐዋርያቱ ጋር ተገልጦላቸው "ባንተ ብዙ ተአምራትን ያደረግሁብህ በእናት በአባትህም ቤት ረሃብ በነበረበት ጊዜ ምግብ እንዲመላ በእጅህ ሀብተ በረከትን ያሳደርኩብህ እኔ ነኝ" ብሎ ነስሀ መንፈስ ቅዱስ ብሏቸው የሹመት ሀብትን ሰጣቸው። እንደ ሀዋርያቱም "በምድር ያሰእከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል በምድርም የፈታኽው በሰማይም የተፈታ ይሆናል፤ አንተን እምቢ ያለ እኔን እምቢ አለ ወንጌል በሌለበትም ቦታዎች ሕዝብን አስተምረህ ታጠምቃለህና ስምህን ተክለሀይማኖት ብየዋለሁ። ቅዱስ ሚካኤልም በሰብከው ነገር ሁሉ ረዳትህ ይሆንሃል እኔም ከአንተ አልለይም" ብሎ የክህነትን ስልጣን ሰጥቷቸው ከአጠገባቸው ተሰወረ።
አገልግሎት እና ተአምራቸው
ጻድቁ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአገልግሎት የወጡት በከተታ ነበር። በዚያም ከ1219-1222 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ዓመት ወንጌልን ሰበኩ። ለ9 ወራት ያህልም ደግሞ በቡሂፋት እንዲሁ ወንጌልን አስተማሩ።
ከ1222-1234 ዓ.ም በወላይታ ለተከታታይ 12 ዓመት በማስተማር ህዝቡን ከጣዖት አምላኪነት አውጥተው አጥምቀዋል። ይህም በዚያ ስፍራ ይኖሩ የነበሩት ሰዎች ሰይጣን በዛፍ ተመስሎ እኔ አምላካችሁ ነኝ እያለ ከእውነተኛው መንገድ አስወጥቶ እርሱን እንዲያመልኩት ያደርግ ነበርና። በዚያም ስፍራ ጻድቁ ቤተክርስቲያንን አንጸዋል።
ከ1234-1244 ዓ.ም ወደ አማራ ሳይንት ወሎ ተጉዘው ከአባ ጸሎተ ሚካኤል ሥርዓተ ምንኩስናን እየተማሩ ተአምራትንም እያደረጉ ቆዩ።
ከ1244-1254 ዓ.ም አባ ኢየሱስ ሞአ ወደ ሚገኙበት ሀይቅ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በመጓዝ ሳሉም ሀይቁን እንደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግራቸው ሄዱ። የአባ ኢየሱስ ሞአ የንጽህና ምልክት የሆነውን ቀሚሳቸውንም ተቀብለዋል።
ከ1254-1266 ዓ.ም ወደ ትግራይ አቅንተው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው ከአባ ዮሃኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ12 ዓመታት በተጋድሎ፣ በትሩፋት እና በተአምራት መንፈሳዊ ትግላቸውን ቀጠሉ። ቅዱስ ሚካኤል ወደ ሌላ ገዳም እንዲሄዱ ባዘዛቸውም ጊዜ አባ ኢየሱስ ሞአ እና መነኮሳቱ አብረው ሊሸኟቸው በወጡ ጊዜ ጻድቁ በገመድ ከገዳሙ እየወረዱ ሳለ ሰይጣን መጥቶ ገመዱን ቢቆርጠውም እግዚአብሔር የመረጣቸው ታላቅ አባት ናቸውና 6 የብርሃን ክንፍን ሰጥቷቸው እንዲሄዱ አደረገ። ከዚያን ተመልሰው ከአባ ዮሃኒ የተቀበለቱን ቆብና አስኬማ ለአባ ኢየሱስ ሞአ ሰጧቸው። ወደ ዋሊ ገዳምም ገብተው እንደገና በትሩፋት፣ በመጋደል እና በተአምራት ቆይተዋል።
ከ1266-1267 ዓ.ም ወደ ግብጽና ኢየሩሳሌም ሄደው ካሉት ከቅዱሳን አባቶች ጋር ተገናኙ። በዚያን ጊዜም ዳዳ የተባለውንም 75ክንድ የሚረዝመውን ጣዖት በጸሎትና በተአምራት ገድለዋል። በቦታውም ቤተክርስቲያን አንጸው በውስጧ ታቦትን አስገብተዋል። በቤተክርስቲያኒቱም 3000 ህዝብንም አጥምቀው አቁርበዋል።
ከ1267-1289 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ አሰቦት ዋሻ ገብተው 2ጦር ከፊታቸው፣ 2ጦር ከኋላቸው፣ 2 ጦር ከቀኝ እንዲሁም 2 ጦር ከግራ አድርገው እጃቸውንም በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የጌታችንን የመስቀል ህማምና ሞት በማሰብ በጾምና በጸሎት ሌትና ቀን በአርምሞ ተወስነው ለ22 ተከታታይ አመታት በሁለት እግራቸው ቀጥ ብለው በጽናት ቆመው ጸለዩ። ከጸሎት ብዛትም የተነሳ ጥር 4 1389 ዓ.ም በቀኝ በኩል ያለችው የእግራቸው አገዳ ተሰበረች።
ከ1289-1296 ዓ.ም እግራቸው ከተሰበረ ቡሃላ ሳይበሉ ሳይጠጡ ቆመው ስለ ሰው ልጆች ድህነትን ለመኑ። በአራተኛውም አመት ነበር ጥቂት ውሃ ቀምሰው የነበረው። ጌታችን ተገልጦም ታላቅ የመንግሥት አዳራሽን ሰጥቷቸው የመለኮትን ነገር የሚያሳይ የእሳት አንደበት ያላቸውን ልብስ አለበሳቸው። በመስቀል ያጌጡ 7 የመስቀል አክሊሎችንም አቀዳጀቸው። ዝክርህን የዘከረ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ ገድልህን የሰማ ያሰማ፣ ባንተ ስም በታነጸው ቤተክርስቲያን ሄዶ ለተሳለመና ለጸለየ ሁሉ እስከ 10 ትውልድ እምርሃለሁ እባርክልሃለሁም የሚል ታላቅ ቃልኪዳን ሰጣቸው። በዚህም ዋሻ ለ57 አመት ከተቀበርክ ቡሃላ ይህ ገዳም ፈርሶ ልጆችህ ሥጋህን በዚያ አፍልሰው ያኖሩታልም ብሎ ነገራቸው።
በመጨረሻም በተስህቦ ህመም ለአስር ቀን ከቆዩ ቡሃላ ጌታቸው የገባላቸውን ቃልኪዳን ለመነኮሳት መንፈሳዊ ልጆቻቸው ካስተማሩ ቡሃላ በዕለተ ሰኞ ነሐሴ 24 1396 ዓ.ም በታላቅ ክብር አረፉ። ጻድቁ በህዳር 24 ከ24ካህናተ ሰማይ ጋር 25ተኛ በመሆን የሥላሴን መንበር ለማጠን በቅተው ነበር። ከማረፋቸውም ጥቂት አስቀድሞ ልጆቻቸውን እየባረኳቸው ሲሰናበቷቸው ሳለ አንዲት ሴት መጥታ "በቃሉ የታሰሩ እንዳሉ ይፍቱ" ስትላቸው ከሰው እስከ እንስሳ የታሰሩ የዱር አራዊት ሁሉ የተፈቱ ይሁኑ አሉ። በቃለ ግዝታቸው መሰረት ለ18 አመታት ታስረው ነበርና። ይህም ደቀመዝሙሯቸው የሚተክሉትን እያበላሹና እየነቀሉ ስላስቸገሯቸው ነበር። ይህንንም ለጻድቁ ቢነገሯቸው ተውአቸው እነርሱንወደ ቤታቸው መጡ እንጂ እኛ እነርሱ ወደ እኛ አልመጡም አለቻቸው።ከዚህም ቡሃላ አንዲት ሴት የያዘችውን ምግብ አንድ ዝንጀሮ መጥቶ ነጠቃት እጅግም ደበደባት። ያን ጊዜም ነበር አባታችን አራዊቱን ያወገዟቸው::
አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር ከጻድቁ ረድኤትና በረከቱን ይከፍለን ዘንድ ቅዱስና መልካም ፈቃዱ ይሁንልን አሜን።
የአቡነ ተክለሃይማኖት ዓመታዊ በዓላት: -
ህዳር 24 ከሱራፌል ጋር 25ተኛ ካህን ሆነው መንበረ ሥላሴን ያጠኑበት
ታሕሳስ 24 ልደታቸው
ጥር 4 የቀኝ እግራቸው አገዳ በጸሎት ብዛት የተሰበረችበት
መጋቢት 24 ጽንሰታቸው
ግንቦት 12 አጽመ ፍልሰታቸው
ነሐሴ 24 ዕረፍታቸው ይታሰባል።
አምላከ ቅዱሳን ከጻድቁ ረድኤትና በረከት ጸሎቱንና ምልጃውን በእኛ ላይ ያሳድርብን አሜን !!! https://t.me/http7kidist

🌻🌻የሥላሴ ልጆች⛪️💒👨👩👧🇪🇹🌼🌼
፨የዚህ ግሩፕ ዋንኛአላማ መንፈሳዊ የሆኑ ጥያቄዎችን በመጠያየቅ ያለን እውቀት ማዳበር ነው።
http7kidist የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መንፈሳዊ ስነ-ጽሁፍ፣ስነ-ግጥም፣ትረካ፣አጫጭር ጭውውቶች...የተለያዩ ኪነ-ጥበብ የሆኑ ነገሮች አሏችሁ? በሉ ገባ ገባ በሉ
http7kidist የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች መንፈሳዊ ስነ-ጽሁፍ፣ስነ-ግጥም፣ትረካ፣አጫጭር ጭውውቶች...የተለያዩ ኪነ-ጥበብ የሆኑ ነገሮች አሏችሁ? በሉ ገባ ገባ በሉ
✟"ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጠመቁ ምክንያት ከብሉይ ወደ ሐዲስ፥ ከኦሪት ወደ ወንጌል አሻገረን፤ የመንግሥተ ሰማያትን ደጅ ከፈተልን፤ ወደ ሀገራችን (ወደ ሰማይ) ይጠራን ዘንድ ብቻ ሳይኾን ሊነገር በማይችል ክብር ያከብረን ዘንድም ቅዱስ መንፈሱን ላከልን፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
መልካም በዓል!!!
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ።
❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖❖
መልካም በዓል!!!
ከኃጥያተኛው ድንኳን
ከኃጥያተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመኃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገሀል
አንተ ስላለኸኝ ቀሏል መከራዬ /፪/
ለእኔ ያደረከው ብዙ ነው ጌታዬ /፪/
እንኳንስ አድርገኸኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲሁም ይሄን ነው ልቤ ሚናፍቀው
የዘመናት ሸክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፋውን ድሪም አግኝተኃልና
አዝ------------
ባገኘኸኝ ግዜ ሸፍናኝ በለሷ
ከፊትህ ያነበብኩት ፍፁም አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታያለኽ ምትለኝ
አይንህ ይናገራል እንደማትረሳኝ
አዝ-------------
ምን አለኝ ብለህ ነው ደጃፌን ምትመታው
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲህ አላርስም ምንጣፌን በእንባ
መንጦላዕቴን ከፍተህ በምህረትህ ግባ
አዝ-------------
እኔ እኮ አውቅሀለሁ ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስትን ጉድጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኘው ውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግቤ እና መጠጤ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ከኃጥያተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመኃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገሀል
አንተ ስላለኸኝ ቀሏል መከራዬ /፪/
ለእኔ ያደረከው ብዙ ነው ጌታዬ /፪/
እንኳንስ አድርገኸኝ ጌታዬ ሙሉ ሰው
እንዲሁም ይሄን ነው ልቤ ሚናፍቀው
የዘመናት ሸክም ቀረ ጉስቁልና
የጠፋውን ድሪም አግኝተኃልና
አዝ------------
ባገኘኸኝ ግዜ ሸፍናኝ በለሷ
ከፊትህ ያነበብኩት ፍፁም አይረሳ
ከዚህ የበለጠ ታያለኽ ምትለኝ
አይንህ ይናገራል እንደማትረሳኝ
አዝ-------------
ምን አለኝ ብለህ ነው ደጃፌን ምትመታው
እኔ ደካማ ነኝ አንተ ቅዱስ ጌታ
ከእንግዲህ አላርስም ምንጣፌን በእንባ
መንጦላዕቴን ከፍተህ በምህረትህ ግባ
አዝ-------------
እኔ እኮ አውቅሀለሁ ሁሉን ስታፈቅር
የአናብስትን ጉድጓድ የሞት አዋጅ ስትሽር
እንዲህ እያለ ነው የሚቀኘው ውስጤ
ኢየሱስ ክርስቶስ ምግቤ እና መጠጤ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ተዋህዶአትፈርስም
ድርጅት አይደለም በሰዉ የታነጰ
ፖለቲካም አይደል ዘርን ያጣቀሰ
ሚስጥሩ ፍቅር ነዉ ቃላቶች ማይበቃዉ
እኛን ስለመዉደድ በፍቅር ተስቦ
መስቀል ላይ የወጣዉ
በደም ታንጰናል በማይጠፋ ቀለም
ለኛ ብሎ እርሱ ቢሰቀልም
መሰረቱ እየሱስ ነዉ
ግርግዳዉ ቅዱሳን
ግንቦቹ እኛ ነን የእርሱ ምእመናን
ልንወድቅ አንችልም በእርሱ ፍቅር ጰንተናል
እግዚአብሔርን ይዘን ማንስ ይንደናል
ማሃመዳዊም ሁን ወይም ጆቫዊትነስ
ፕሮቴስታንትም ሁን ወይ ደሞ ካቶሊክ
አለቱን ላታፈርስ የሰዉ ደም አታፍስስ
ምንጩንም ላታደርቅ ከመቅደሱ እራቅ
ካህኑ ቢታረድ መቅደሱ ቢቃጠል
እንበዛለን እንጂ የለም የሚጎድል
ስንሞት እንበዛለን
መከራዉ ሲበዛ በፍቅር እንጰናለን
በእሳት ስንቃጠል እንለመልማለን
ከማይደክም አባት ተፈጥረናልና
አርዮስ አትልፋ እንላለን ቀና
ሰልፉ የእኛ ነዉ ድልም የኛ ብቻ
እንደ አሸዋ የበዛን እስካለም ዳርቻ
ካህኑን ግደሉ መቅደሱን አቃጥሉ
ቅጥሩንም አፍርሱ ልጆቹን በትኑ
እናንተ ስትጠፉ እነሱ ቀና ብለዉ
ባባታቸዉ እቤት ይሰበሰባሉ
ይህ ነዉ ክርስትና የማይጠፋ ቀለም
በፍጱም ማይጨልም ሁሌ ሚሰጥ ብርሃን
እናማ አርዮስ ቁርጥህን እወቀዉ
ድል ላታደርግ እንደዉ ነብስህን አታስጨንቀዉ
ሃሰት እዉነትን እስኪ የቱጋር ነዉ አሸንፎየሚያቀዉ
ባንድነት ተነሱ የእምነትን ሰይፍ ያዙ
በፍቅር ማርኩና የዲያቢሎስን
በእምነታችሁ ናዱ
በእምነት እንሞላ በጱናት እንቁም
በተስፋ እንዉጣ
ጠላት አፍሮ እንዲቀር መድረሻ እንዲያጣ
የጦር እቃችሁን ልበሱ እንደ ካባ
ዘመቻዉን አጵኑት ቅድስት ምድር
አርዮስ ሳይገባ
የጦርሰልፍ አንሻም ቀስት አንወረዉርም
ደም እያፈሰስን እርሱ የፈጠረዉን እኛ አንገድልም
ቀስትና ጦር ይዘን አንወጣም ዘመቻ
ጠጠርም አንለቅምም አሳዳጁን መምቻ
ድርጅት አይደለም በሰዉ የታነጰ
ፖለቲካም አይደል ዘርን ያጣቀሰ
ሚስጥሩ ፍቅር ነዉ ቃላቶች ማይበቃዉ
እኛን ስለመዉደድ በፍቅር ተስቦ
መስቀል ላይ የወጣዉ
በደም ታንጰናል በማይጠፋ ቀለም
ለኛ ብሎ እርሱ ቢሰቀልም
መሰረቱ እየሱስ ነዉ
ግርግዳዉ ቅዱሳን
ግንቦቹ እኛ ነን የእርሱ ምእመናን
ልንወድቅ አንችልም በእርሱ ፍቅር ጰንተናል
እግዚአብሔርን ይዘን ማንስ ይንደናል
ማሃመዳዊም ሁን ወይም ጆቫዊትነስ
ፕሮቴስታንትም ሁን ወይ ደሞ ካቶሊክ
አለቱን ላታፈርስ የሰዉ ደም አታፍስስ
ምንጩንም ላታደርቅ ከመቅደሱ እራቅ
ካህኑ ቢታረድ መቅደሱ ቢቃጠል
እንበዛለን እንጂ የለም የሚጎድል
ስንሞት እንበዛለን
መከራዉ ሲበዛ በፍቅር እንጰናለን
በእሳት ስንቃጠል እንለመልማለን
ከማይደክም አባት ተፈጥረናልና
አርዮስ አትልፋ እንላለን ቀና
ሰልፉ የእኛ ነዉ ድልም የኛ ብቻ
እንደ አሸዋ የበዛን እስካለም ዳርቻ
ካህኑን ግደሉ መቅደሱን አቃጥሉ
ቅጥሩንም አፍርሱ ልጆቹን በትኑ
እናንተ ስትጠፉ እነሱ ቀና ብለዉ
ባባታቸዉ እቤት ይሰበሰባሉ
ይህ ነዉ ክርስትና የማይጠፋ ቀለም
በፍጱም ማይጨልም ሁሌ ሚሰጥ ብርሃን
እናማ አርዮስ ቁርጥህን እወቀዉ
ድል ላታደርግ እንደዉ ነብስህን አታስጨንቀዉ
ሃሰት እዉነትን እስኪ የቱጋር ነዉ አሸንፎየሚያቀዉ
ባንድነት ተነሱ የእምነትን ሰይፍ ያዙ
በፍቅር ማርኩና የዲያቢሎስን
በእምነታችሁ ናዱ
በእምነት እንሞላ በጱናት እንቁም
በተስፋ እንዉጣ
ጠላት አፍሮ እንዲቀር መድረሻ እንዲያጣ
የጦር እቃችሁን ልበሱ እንደ ካባ
ዘመቻዉን አጵኑት ቅድስት ምድር
አርዮስ ሳይገባ
የጦርሰልፍ አንሻም ቀስት አንወረዉርም
ደም እያፈሰስን እርሱ የፈጠረዉን እኛ አንገድልም
ቀስትና ጦር ይዘን አንወጣም ዘመቻ
ጠጠርም አንለቅምም አሳዳጁን መምቻ
+ ሩፋኤል ይቅር በለኝ +
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
አሳድገኝ ብዬህ ሮጬ
ከልጆች ጋር ተሯሩጬ
በጠበልህ እየታጠብኩ
የውኃ ጨው እየቀመስኩ
ሩፋኤል አሳድገኝ
እንደ ታላቆቼ አድርገኝ
ብዬ እየጮህኩኝ ስጣራ
ሰምተኸኛል ከልጅ ተራ
ዘንድሮን ግን ተጠለልኩኝ
ጠበል ሲወርድ ተሸሸግሁኝ
ከበረከትህ ሸሸሁኝ
ከቡራኬህ አመለጥኩኝ
ሩፋኤል ሆይ ይቅር በለኝ
ስላበቃ ልጅነቴ
በቆሸሸ ሰውነቴ
በረከሰ ማንነቴ
እንዳላረክስ ጠበልህን
ተጠለልኩት ጥምቀትህን
ጥያቄ :- ሰላም እንዴት ናችሁ?
ጥያቄ ለመጠየቅ ነበር መናፍቃን እኛ ኦርቶዶክሳውያንን አንዲት ጥምቀት ተብሎ ተጽፎ ለምን በየዓመቱ ትጠመቃላችሁ? ብለው ይጠይቃሉ ቢያብራሩልን።
መልስ
👉 ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሚለው መጽሐፋቸው የዚህን ጥያቄ መነሻና ምላሹን እንዲህ ብለው ጽፈዋል። "የጠበሉን መረጨት አይተው በቀድሞ ዘመን ወደ ሀገራችን መጥተው የነበሩ ኢየሱሳውያን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ታጠምቃለች ብለው ጽፈዋል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በያመቱ ይህን የምትፈጽመው ጌታችን ለእኛ ብሎ ያሳየውን ትህትና ለመመስከር ለምዕመናን በረከተ ጥምቀትን ለማሳተፍ እንጂ የተጠመቁትን ምዕመናን እየመላለሰች በየዓመቱ አታጠምቅም። ጥምቀት አሐቲ [አንዲት] መሆኗን ታውቃለችና። [የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ታሪክ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ገጽ.126]
ዲያቆን ብርሃኑ አድማስም በዓላት በሚለው መጽሐፉ በጥምቀት የምንጠመቀው ለሥርየተ ኃጢአት ጭምር መሆኑን ሲገልጽ እንዲህ ብሎአል። "የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያንም ለዚሁ አንጽሖተ ማይ (ውሃውን ለመቀደስ) እና ምእመናኑም በጥምቀት (በልጅነት) የቀደመ ኃጢአታቸው የተሠረየላቸውን ያህል በዚህ ዕለትም የሠሩት ኃጢአት ይሠረይላቸዋል ትላለች። [በዓላት፤ ዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ገጽ ገጽ.71] ስለዚህም በረከተ ጥምቀቱን ለምዕመናን በማድረስ ማሳተፍና ሥርየተ ኃጢአትን መስጠት እንጂ መላልሶ ማጥመቅ አይደለም። ልጅነት አንድ ጊዜ ብቻ ነውና።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ልጅነትን የምታሰጠዋ ጥምቀት አንዲት ናት። ኤፌ.{ 4:5። ልጅነትን የምታሰጠዋ ጥምቀት አንዲት ናት አትደገምም። በጸሎተ ሐይማኖት ላይም "ኃጢአት በሚሰረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን" ይላል። ጥምቀት ከምናከብራቸው ከጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ ነው። ጌታችን በቅዱስ ዮሐንስ ሊጠመቅ መሄዱን የምናስብበት በዓል ነው ከጌታችን ጥምቀትም በረከትን የምንሳተፍበት በዓል ነው። ጥምቀት ሊደገም ይቅርና ይህን የጌታን ጥምቀትን በማሰብ የምናከብረውን በዓል ለማክበር መብቱ እንኳ ያላቸው ከማሕጸነ ዮርዳኖስ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ በጥምቀት የሥላሴ ልጅነትን ያገኙ ክርስቲያኖች ናቸው። ስለዚህ በረከተ ጥምቀትን ለመሳተፍ እንጂ ልጅነት የምታሰጠዋ ጥምቀት የምትደገም ሆና አይደለም።
ጌታችን በወንጌል " የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ ጽዋ ውኃ የሚያጠጣችሁ ሁሉ፥ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኋለሁ።" ማር.9:41 እንደተናገረ ስሙን አስበን የምናደርጋቸው የምንዘክራቸው የጌታን ዓበይትና ንዑሳን በዓላትን ማሰብ መዘከር ስለ እርሱም ብሎ ነዳያንን በምሕረት መጎብኘት ዋጋ የማያሳጣ ተግባር ነው።
✍ ተክለ ማርያም [ጅማ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት]

በዜሮ ይባዛል!
*ፆም × 0/ሐሜት/= 0 ውጤት
*ስግደት × 0 /ፀብ/=0 ውጤት
*ጸሎት × 0/ስስት/=0 ውጤት
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
#ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
#ጸሎት×ምጽዋት= 60ያማር ፍሬ
#ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ ያፈራል።
*ፆም × 0/ሐሜት/= 0 ውጤት
*ስግደት × 0 /ፀብ/=0 ውጤት
*ጸሎት × 0/ስስት/=0 ውጤት
ተግቼ ብጸልይ እጆቼን ዘርግቼ
ቤቴ ባዶ ቢቀር ያለኝን መጽውቼ
ቀኑን ሙሉ ብጾም እስኪቆረጥ አንጀቴ
ዘወትር ብሰግድ እስኪዝል ጉልበቴ
በቀድስ ባስቀድስ በመቅደሱ ግርማ
ብዘምር ባወድስ የሚጣፍጥ ዜማ
ወንጌልን ብሰብክ ምስጢር አመስጥሬ
ብናገር ባስተምር ትርጉሙን ዘርዝሬ
ጥልና ክርክር ካሉ በህይወቴ
ሐሜት ክርክር ካልጠፉ ከቤቴ
በዜሮ ይባዛል ፍቅር በማጣቴ።
ስብሐት ለእግዚአብሔር!
#ፆም×ፍቅር= 30 ያማር ፍሬ
#ጸሎት×ምጽዋት= 60ያማር ፍሬ
#ስግደት× ትህትና= 100ያማረ ፍሬ ያፈራል።