​قَـــنَـــاةُ أُمِّ حَـــفْـــصَـــةَ الـــسَّـــلَـــفِـــيَّـــة
1.78K subscribers
936 photos
159 videos
7 files
732 links
العَقَباتُ وَالانْكِساراتُ لَيْسَتْ نِهايَةَ الطَّريقِ بَلْ هيَ جُزءٌ مِن رِحْلَةِ النَّجاحِ.
እንቅፋቶችና ስብራቶች የመንገዱ መጨረሻ አይደሉም ይልቁንም ወደ ስኬት ከሚያደርሰን ጉዞ አካል ናቸው

https://t.me/htt_Aselefy
Download Telegram
Forwarded from ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ!
ጥያቄ ?   📮📮  

ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል።

📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ።

ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ነብዩሏህ ሱለይማን ነው ።
Forwarded from 
ቲክቶክ «አምስት ደቂቃ ብቻ ልይ» ብላችሁ ከፍታችሁት ሳይታወቃችሁ ሰዓታትን የሚውጥ አደገኛ ወጥመድ ነው።አፕልኬሽኑ ራሱ የተሰራው አእምሮን በፈጣን ደስታ እያደነዘዘ ሰውን ስክሪን ላይ ጠፍሮ ለማስቀረት ነው።

ትልቁ አደጋው ጊዜ ማባከኑ ብቻ ሳይሆን፦
- አእምሮ ረዘም ላሉና ትዕግስት ለሚጠይቁ ሥራዎች እንዳይዘጋጅ ያደርጋል።

- የሌሊት እረፍትን በማዛባት የቀን ንቃትን ያጠፋል።
- የሌሎችን የተጋነነ ኑሮ እያሳየ በራስ ሕይወት ላይ ስንፍናን ይዘራል።

በማይረቡ ቪዲዮዎች ላይ በከንቱ የሚፈሰው እያንዳንዱ ሰከንድ ነገ የማይመለስ የዕድሜያችሁ ውድ ካፒታል ነው። ስልኩን እናንተ ካልገዛችሁት፣ እሱ ሕይወታችሁን በከንቱ ይገዛዋል፤ ስለዚህ ወይ ገደብ አበጁለት፣ አለበለዚያ ሙሉ በሙሉ ሰርዛችሁ በሰላም ኑሩ!
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
👍1
Forwarded from 
🌹 ወንድሜ ለባለቤትህ “እወድሻለሁ” በላት! 🌹
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
💌 ጀግናው ባል ሁሌም ሚስትህን እንዲህ በላት፦ «እወድሻለሁ!»

🌸 ሴቶች መታቀፍን፣ መንከባከብን፣ በፍቅር መታየትንና ፍቅርን በግልጽ ቃላት መስማትን ይወዳሉ። ስለዚህ ይህንን ከባለቤትህ አትንፈጋት!

ፍቅርህን በቃላት ለመግለጽ ከተቆጠብክ፣ በአንተና በእሷ መካከል የመራራቅ ግርግዳ ልትገነባ ትችላለህ፤ የፍቅራችሁም ጣዕም ሊቀንስ ይችላል።

🌹 “እወድሻለሁ” የሚለው ቃል ምንም አያስከፍልህም፤ በሚስትህ ዘንድ ግን ከዓለምና ከውስጡ ካለው ሁሉ የሚበልጥ ዋጋ ሊኖረው ይችላል!

ይህ ቃል ቁጣዋን ሊያረግብ፣ ልቧን በደስታ ሊሞላና ወደ አንተ ያላትን ቅርርብ ሊያጠናክር ይችላል።

🌹 በስሜትህ ለጋስ ሁን!

ሴት ፍቅርን መስማት አትሰለችም፤ ሺህ ጊዜ ቢደገምላትም እንኳን ከልብ የመጣ የፍቅር ቃል ለእሷ ደስታ ሊሆን ይችላል!

🌹 ፍቅር ዝምተኛ ተግባራት ብቻ አይደለም።

ፍቅር ልብን የሚያረካ፣ ነፍስን የሚያነቃቃ፣ በሁለታችሁ መካከል ያለውን የፍቅር ቃል ኪዳን እንደገና የሚያድስ ጣፋጭ ቃልም ጭምር ነው።

🥀 ጀግናው ባል ሆይ! ሚስትህን በድርጊትህ ብቻ ሳይሆን በቃልህም አፍቅራት። አመስግናት፣ አበረታታት፣ አስደስታት፤ እናም ከልብህ፦

🌹 «እወድሻለሁ፣ የሕይወቴ ውድ ሰው ነሽ!» 🥀በላት!
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🌹 አላህ በትዳራችን መካከል ፍቅርን፣ ርህራሄንና መተሳሰብን ያብዛልን። 🌹
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ያለሽበት ሁኔታ ምንም ያህል
አስቸጋሪ ቢሆንም አላህ ምን
ያህል ታላቅ እንደሆነ አትርሺ !!
🍓8✍5👍1
Forwarded from 
03 «ምክር ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት ላሰቡ»
አቅራቢ፦ አቡ ሱፍያን
◎ አድስ የኪታብ ደርስ!

ስኬታማ የትዳር ቁልፎች! (ክፍል 03)

​📚 የኪታቡ ስም፦
«رسائل للمقبلين على الزواج»
​📖 «ምክር ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት ላሰቡ»
◎ ለወንዶች፡ 5 ወርቃማና ወሳኝ ነጥቦች እንድሁም
◎ ለሴቶች፡ 9 ወርቃማና ወሳኝ ነጥቦች በዚህ ትምህርት ውስጥ ተዳሰዋል።

​🎙 አቅራቢ፦ አቡ ሱፍያን
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
ክፉ ሰዎች ማለት ጥለው የሄዱ ሳይሆኑ ነገለመሄድ እያሰቡ ዛሬ ትልቅ ተስፋ የሚሰጡ ናቸው::

https://t.me/htt_Aselefy
https://t.me/htt_Aselefy
👍7🎉1🍓1
የሰዎች ምኞትና የአሏህ ውሳኔ

​በሂይወታችን ለብዙ ነገሮችን እንጓጓለን እንመኛለን ቀናትና ወራትን እንቆጥራለን። አንዳንዴም የምንፈልገው ነገር ሲዘገይ ወይም ሲቀር እናዝናለን እንከፋለን። ነገር ግን እውነታው ያለው እኛ በጓጓንለት ልክ ሳይሆን አሏህ ሲፈቅድ ብቻ ነው ሚሆነው።ምናልባት የምንፈልገው ነገር የዘገየው ከኋላው መልካም ነገር ይዞ ይሆናል ኢንሻአሏህ


https://t.me/htt_Aselefy
https://t.me/htt_Aselefy
🍓3👍2
Forwarded from 
ስለ"አስከፊው ጀሀነም
በአቡ ኢምራን"
✅ ሙሀደራ🎙️

:- በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ሶባ ቢላል መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ የተደረገ።

➡️ በ"ወንዲም አቡ ኢምራን 🕋◾️

ርዕስ:-ስለ አስከፊው ጀሀነም

https://t.me/sobabilelmesjide
https://t.me/sobabilelmesjide
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የተውሂዱ አርበኛ ቢላል ኢብኑ ረባህ ማነው⁉️
በ"ኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ
✅ ሙሀደራ😀

:- በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ ሶባ ቢላል መስጅድ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ የተደረገ።

💌 በ"ኡስታዝ አቡ አምር ኑርየ ጎቤ 🎙️

ርዕስ:-የተውሂዱ አርበኛ ቢላል ኢብኑ ረባህ ማነው🤪

https://t.me/sobabilelmesjide
https://t.me/sobabilelmesjide
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔊 الســــلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ዉድና የተከበራችሁ እዉቀት ፈላጊ ወንድሞች እና እህቶች እነሆ ታላቅ ብስራት ይዘን ብቅ ብለናል።

➡️ የሚጀመረዉ ኪታብ:
-📔 سفينة النجاة 
📒 ሰፊነቱ-ነጃህ
 
↗️ የደርስ ሰዓት:- ከቀኑ 8:30pm በኢትዮ።
ደርሱ በአላህ ፈቃድ ከ2️⃣"ቀን በሗላ ይጀመራል።
ከምንም አይነት ክፍያ ነፃ ነው።

ሸርርር አርጉት ባረከላሁ ፊኩም✉️

ደርሱ የሚተላለፍበት ጉርፕ/ቻናል
🔽🔽🔽🔽🔽
https://t.me/Yesuna_brhen
https://t.me/Yesuna_brhen
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የሸሪዓው ውበትና የሴት ልጅ ክብር
​"ሴትን ልጅ እረግጠው ሲይዟት ነው መስመር ውስጥ የምትገባው" የሚሉት አባባሎች የድንቁርናና የዱርዬዎች ምክር ናቸው። እስልምና (ሸሪዓው) ግን የመከረውና የዘዘው ሌላ ነው

እዘኑላቸው በጥሩም ያዟቸው ነው ያለው።
​ሴት ልጅ በተፈጥሮዋ ስትታይ የምታሳዝን ልቧ ቶሎ የሚነካና ጥበቃን የምትሻ ንፅህት ፍጥረት ነች። ከጎን አጥንትህ መፈጠሯ ራሱ በእርጋታና በጥበብ እንጂ በኃይልና በጭካኔ ሊያስተካክሏት እንደማይቻል ትልቅ ማሳያ ነው።
​
​መልካምነት የላቀ ወንድነት ነው፦ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ከእናንተ ውስጥ በላጩ (ምርጡ) ለቤተሰቦቹ (ለሚስቱ) መልካም የሆነው ነው" ብለዋል። ወንድነት ጡንቻን ማሳየትና ሴትን ልጅ ማስፈራራት ሳይሆን፣ ደካማነቷን አይቶ የሚራራላትና ጥላ የሚሆናት ደግ ልብ ነው።

​የፍቅር እንጂ የጭቆና ቦታ አይደለም፦ ትዳር በአላህ ቃል ኪዳን መሠረት "እዝነትና ፍቅር" የሚሰፍንበት ቦታ እንጂ አንዱ ሌላውን ረግጦ የሚገዛበት ወህኒ ቤት አይደለም።

​ደግነት መስመር ያስይዛል፦ ሴት ልጅ በፍቅር በደግነትና በትህትና ከተያዘች ከራሷ በላይ ለትዳሯና ለባሏ ትታዘዛለች መስመር የሚያስገባት ጭካኔ ሳይሆን ክብርና እዝነት ነው።
Forwarded from 
አስቸኳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕርግራም

<< ክፍል ❷ >>

የኒቃብና ጅልባብ ባንክ አድሚን የሆነች እህታችን በገጠማት ህመም ምክንያት ለህክምና የምያስፈልጋትን ገንዘብ ለማግኘት በትላንትናው እለት አስቸኳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ማድርጋችን ይታወቃል።

በመሆኑም የሚፈለገውን ገንዘብ ግማሹን እንኳን ባለማግኘታችን ዛሬ ምሽት ዳግም የገቢ ማሰባሰቢያው እንዲቀጥል ተደርጓል። የእህታችን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነውና በምንችለው ሁሉ ከጎኗ ልንቆምና ልናግዛት ይገባል።

🎙ተጋባዥ ኡስታዞችም ይኖራሉ

🗓ዛሬ ማክሰኞ ምሽት
⏱ከ 3:00 ጀምሮ

አካውንት ቁጥር
1000587296784
ዘይነባ ወርቂዬ

https://t.me/nikab_jilbab_group
Forwarded from 
የምትማሪው እውቀት ጠቃሚ መሆኑን የምታውቂው  ባወቅሽው መስራት ስትችይ ነው  የአሏህ ፍራቻ ከልብሽ ሲኖር ነው

ልብሽ ንፁህ ሲሆን አነጋገርሽ አረማመድሽ ለሰው ልጅ ያለሽ አመለካከት ያማረ ይሆናል!!
🎉3👍1
Forwarded from 
🍂ሲደክማችሁ ሲያማችሁ፣ ግራ ሲገባችሁ … ወደማንም ዘንድ ከመሄዳችሁ በፊት ወደሱ ሂዱ፡፡ ለአንድም ሰው ችግራችሁን ከመንገራችሁ በፊት ለሱ ንገሩ፡፡ ለማንም በሽታችሁን ከመግለጣችሁ በፊት እሱ ዘንድ ታከሙ፡፡ ችክ ብላችሁ ለምኑት፤ ከልብ ሆናችሁ ጠይቁት፡፡ ድህነታችሁን፣ ፈላጊነታችሁን፣ አቅመቢስነታችሁን በራሣችሁ ላይ መስክሩ፡፡

ይኸው ሁሉን ትቼ አንተ ጋ መጣሁ የኔ ጌታ!
Forwarded from 
🧷ሰዎች ቢበድሉሽ ፍትሕሽን ከአሏህ ዘንድ ፈልጊ
ቢተዉሽ በአሏህ ተማመኚ"


ቢያሳዝኑሽ ሀዘንሽን ለአሏህ አውሪ
ምክንያቱም ሰዎች የማያውቁትን የልብሽን ህመም አሏህ ያውቃል።


https://t.me/https_Aselefya
🍓4
ሂዎት ሁሌ እደምንፈልጋት አትሆንም ግን ሁሌም የምታስተምረን ነገርአላት::
🎉2👍1
📖 የቁርአን እውቀታቹን ፈትኑ

የቁርአን እናት (ኡም አል-ኪታብ) በመባል የምትታወቀው ሱራ የትኛዋ ናት?
Forwarded from 
◎«ትዳር በራሳችሁ ወዳችሁት እና ፈቅዳችሁ የምትገቡበት እንጂ በቤተሰብ ግፊት እና ቤተሰብን ለማስደሰት ተብሎ የሚገባበት መንገድ አይደለም»

◎ «ሰውን ለማስደሰት እና በሰው ግፊት የተጀመሩ ብዙ ትዳሮች ፈርሰዋል »

◎ «ትዳር ኢስቲሻራም እስቲኻራም የሚስፈልገው ትልቅ የሂወት ጉዞ ነው »
tps://t.me/OmuAdnan55
🎉2