Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች
69.8K subscribers
8.47K photos
348 videos
124 files
1.29K links
The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.
Download Telegram
የዋጋ ጭማሪ የተደረገባቸው አገልግሎቶች

የአዲስ አበባ ከተማ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ የአገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ላይ ከፍ ያለ ጭማሪ አድርጓል።

ለአብነት ፦
° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ማሳወቅ አገልግሎት 500 ብር የነበረው 1,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የዋጋ ግምት ለሽያጭ አገልግሎት 2,310 ብር የነበረው 4,000 ብር ገብቷል።

° የተሽከርካሪ የባለቤትነት ስም ዝውውር አገልግሎት 3,000 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

° ለዓመታዊ ምርመራ ተለጣፊ ምልክት (ቦሎ) ግልባጭ ለመጀመሪያ ጊዜ 1,010 ብር የነበረው 2,500 ብር ተደርጓል።

° የተሽከርካሪ ባለቤት ማረጋገጫ ሊብሬ 300 ብር የነበረው 1200 ብር ተደርጓል።

° ሊብሬ  ሲበላሽ ወይም ሲጠፋ ምትክ ፣ የማደሻ ቦታው ሲያልቅ መስጠት 3,000 ብር የነበረው 3,500 ብር ሆኗል።

° መረጃ መስጠት 300 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° አዲስ መንጃ ፍቃድ መስጠት 680 ብር የነበረው 1500 ብር ተደርጓል።

° ለጠፋ መንጃ ፍቃድ ማፈላለጊያ ለፖሊስ ወይም ለፕሬስ የሚሰጥ መረጃ 100 ብር የነበረው 700 ብር ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የፅሁፍ ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት 100 ብር የነበረው 300 ተደርጓል።

° ከ3 ጊዜ በላይ የተግባር ፈተና ለወደቁ በየወሩ ለመፈተን የሚሰጥ አገልግሎት ከ300 ብር ወደ 600 ብር ጨምሯል።

° የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ እድሳት ከ620 ብር ወደ 1000 ብር ገብቷል።

° ለጠፋ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ምትክ መስጠት 620 ብር የነበረው 5,000 ብር ገብቷል።

@tikvahethiopia
የዓመታት የቤት ጥያቄ ...

" ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም ፤ ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጥ መቅረቱ አሳዝኖናል " - ቅሬታ አቅራቢዎች

ለ21 ዓመታት ኮንዶሚኒየም ይደርሰናል ብለው ሲቆጥቡ የቆዩ የኮንዶሚኒየም ነባር ተመዝጋቢዎች ዕጣ ሳይወጣላቸው፣ ቤቶቹ ለልማት ተነሽዎች በመሰጠታቸው ቅሬታ አቀረቡ፡፡

ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በዕጣ ለማግኘት ሲጠባበቁ የቆዩ በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ፣ ለልማት ተነሽዎች ቤቶች መሰጠታቸው ኢፍትሐዊ እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልጸዋል፡፡

ይህን ቅሬታ ያቀረቡት ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ነው።

" ለልማት ተነሽዎች ለምን ቤት ተሰጣቸው አንልም " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ለረዥም ዓመታት ፍትሐዊነት በጎደለው መንገድ ለእኛ ሳይሰጠን መቅረቱ አሳዝኖናል " ብለዋል።

ለልማት ተብሎ ቤታቸው የፈረሰባው ዜጎች ቤት ሲሰጣቸው የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመዝጋቢዎች ጉዳይ በዝምታ መታለፉ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል፡፡

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ እስኪያልቅ ድረስ ለምን በመንግሥት የተሠሩ ቤቶች አይሰጡንም ? ያሉት ተመዝጋቢዎቹ፣ ለሁለት አሠርት ዓመታት ቤት ለማግኘት በመጠበቃቸው በተለየ ሁኔታ በከተማ አስተዳደሩ ሊስተናገዱ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የቤት ኪራይና የልጆች ትምህርት ቤት ክፍያዎች ጣራ በመንካታቸው፣ ለችግር ተዳርገናል ያሉት ተመዝጋቢዎች፣ የኢትዮጵያ ዜጋ አይደለንም ወይ ሲሉም ቅሬታቸውን  አሰምተዋል፡፡

ለዓመታት ምላሽ በተነፈገው ጥያቄያቸው ምክንያት በመንግሥት ላይ ያላቸው እምነት መሟጠጡን ገልጸዋል፡፡

ተመዝጋቢዎቹ ለሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም፣ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትና ሌሎች ተቋማት ቅሬታቸውን ቢያሰሙም እስካሁን መፍትሔ እንዳላገኙ አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ምን ምላሽ ሰጡ ?

- አጠቃላይ የቤቶች ግንባታ ከሁለትና ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ የብድር አቅርቦት ችግር ተጨማሪ ግንባታ ማድረግ አላስቻለም፡፡

- ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ግንባታ አይካሄድም ፤ ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ውዝፍ ዕዳ እስኪከፈል ድረስም ሲያገኝ የነበረው ብድር ተከልክሏል።

- ኮርፖሬሽኑ ካለበት ዕዳ ውስጥ 36 ቢሊዮን ብር ተመላሽ አድርጓል ፤ ቀሪ 37.7 ቢሊዮን ብር ያልተከፈለ ውዝፍ ዕዳ አለበት ፤ ለመክፈልም የተለያዩ አማራጮችን እያጤንን ነው።

- በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር የሚሰጠው ለማጠናቀቂያ ሥራ ብቻ ነው። ለሰፊ የቤት ግንባታ ግን ተጨማሪ ብድር አይሰጥም።

-  ለልማት ተነሽዎች ቅድሚያ መስጠትን መመርያው የሚያዝና የሚደግፈው ነው። ነገር ግን የኮንዶሚኒየም ዕጣ ጠባቂዎችን ወደ ጎን ከመግፋት ጋር መገናኘት የለበትም።

- የቤት አቅርቦት ጉዳይ የ1997 እና የ2005 ዓ.ም. የቤት ተመዝጋቢዎች ችግር ብቻ ሳይሆን፣ በአጠቃላይ በቤት አቅርቦቱ በአማራጭ የቤት ልማት ላይ እየተሠሩ ነው።

- ከተለመዱት 40/60 እና 20/80 ቤቶች በተጨማሪ በ70/30 ፕሮግራምና በማኅበር ቤቶች አቅም ያላቸው እንዲገነቡ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል።

- ኮርፖሬሽኑ እስካሁን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ሲገነባ የነበረው በቦንድ ግዥ ነበር፤ አሁን ግን የከተማ አስተዳደሩ ካለው በጀት ላይ እየመደበ ብድሩን እየከፈለና ለኪራይ የሚሆኑ ቤቶች እየገነባ ነው።

- ከዚህ በተጨማሪ መንግሥትና ባለሀብቶች ተቀናጅተው የሚገነቧቸው ቤቶች አሉ ፤ ለዝቅተኛ የኅብረተሰብ ክፍሎች እየተሰጡ ነው።

- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎችን በተመለከተ ቁጠባ ያቋረጡ አሉ። ነገር ግን አሁንም ኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች የሉም ወይም ጨርሰን ሰጥተናል አላልንም።

- የኮንዶሚኒየም ተመዝጋቢዎች ቅሬታ ትክክል ነው። ነገር ግን ከተማው ያለበትን የቤት አቅርቦት ችግር ሲፈታ የተመዝጋቢዎቹን ችግርም በዚያው ይፈታል።

- የነባሩ የዕጣ አወጣጥ ሒደት ቆሟል ወይም አልቆመም ብለን መናገር አንችልም፤ ምናልባት የባንክ ብድር ከተመለሰ እንደገና በሌላ ብድር ቤቶች ተገንብተው ለዕጣ ጠባቂዎች ለመስጠት ጥረት ይደረጋል።

- የተመዝጋቢዎች ዕጣ የማውጣት ሒደት ይቀጥላል ወይም አይቀጥልም የሚለው በቤት አቅርቦት ሁኔታው ይወሰናል።

- ከኮሪደር ልማት ተነሺዎች በአንድም በሌላም መንገድ ቢጣራ ተመዝጋቢዎች አሉ፡፡ ለኮሪደር ልማት ተነሽዎች የ40/60 እና የ20/80 ቤቶች ተሰጥተው አልቀው ወደ ኪራይ ቤት እየተገባ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የሕግና የአስተዳደር በደል ምርመራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ መንግሥቱ ቀና በበኩላቸው፣ በ1997 ዓ.ም. ኮንዶሚኒየም ለማግኘት ተመዝግበው ዕጣ ያልወጣላቸውን በተመለከተ ኮርፖሬሽኑ በደብዳቤ መጠየቁን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ አለመገኘቱን አቶ መንግሥቱ ገልጸው፣ እንደገና በደብዳቤ ተጠይቆም ምላሽ ካልተገኘ ወደ  የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለማምራት መታቀዱን ተናግረዋል። #ሪፖርተርጋዜጣ
ውድ#የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!!
አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም እና 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም ፤
በዚህም መሰረት፡-
1ኛ. 4አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣
2ኛ.3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት=60,000 ዋት.ሰ፣
3ኛ. 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣
ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡

ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት ሲቀየር 1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡

በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢጠቀም በተቀመጠው እርከን መሰረት በ2.46 ብር ይባዛል፡፡
በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 2.46 ብር= 622.872 ብር ይመጣል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.95 እና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ 10 ብር ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ 675 ብር ከ 80 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ጥብቅ ማስታወቂያ

በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ የቤት ባለቤቶቹ የማይገቡበት ከሆነ ውል የሚቋረጥ መሆኑን ስለማስጠንቀቅ፦

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ማስተላለፉ ይታወቃል።

ይሁንና በተለያዩ ጊዜያት በሽያጭ ተላልፈው የቤት ባለቤቶች ውል የተዋዋሉባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ አሁን ነዋሪ ባለመግባቱ ምክንያት የተለያዩ ህገ ወጥ ተግባራት እየተፈፀመባቸው እና ለፀጥታ ስጋት እየሆኑ ይገኛል።

በመሆኑም ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም ድረስ ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው እንዲገቡ ኮርፖሬሽኑ እያስጠነቀቀ ነገር ግን በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ መሆኑን እና በእጣ እና በሽያጭ ለሌላ ነዋሪ የሚተላለፉ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ለመጨረሻ ጊዜ በጥብቅ ያሳስባል።

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን
ኢትዮቴሌኮም የታሪፍ ጭማሪውን ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን አስታወቀ

ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም ከነገ መስከረም 21፤2017 ዓ.ም. ጀምሮ በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ ጭማሪ የሚያደርግ መሆኑን አስታዉቋል።

ተቋሙ የሚደረገው የዋጋ ጭማሪ አብዛኛውን የህብረተሰብ ክፍል እንደማይነካ የገለፀ ሲሆን ተመጣጣኝ እና የዲጅታል አካታችነትን መርህ በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ይደረጋል ብለሏል።

ተቋሙ የሚደረገዉ ማሻሻያዉ 22 ፓኬጆችን የማይነካ እንደሆነ ቢገልፅም በምን ያህል ፐርሰንት የሚለዉን እና በየትኞቹ አገልግሎቶቹ ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ አላሳወቀም።

ካፒታል የዉጪ ምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲመራ መደረጉን ተከትሎ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የዋጋ ማሻሻያ ሊያደርግ መሆኑን መዘገቧ ይታወቃል ።
ውድ የባንካችን ደንበኞች
****
መንግስት በቅርቡ ባወጣው አዲስ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሕግ መስረት ባንኩ በሚያቀርባቸው ምርት እና አገልግሎቶች ላይ በነበረው የአገልግሎት ክፍያ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲከፈልባቸው መወሰኑ ይታወቃል።
ስለሆነም ከመስከረም 21 ቀን 2017 ዓ. ም ጀምሮ የባንካችን ምርትና የአገልግሎት ዓይነቶች ላይ በሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ ታሪፍ የተጨመረባቸው መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
የሰሞኑን የብር መዳከምን (የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን) ተከትሎ ገበያ ላይ ያልጨመረ ነገር የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም

ይህ አልበቃ ብሎ የመንግስት ተቋማት ህዝብ ላይ እልህ እየተወጡ ይመስል ተራ በተራ እስከ 700 ፐርሰንት ጭማሪ ያረጉ አሉ።

ኢሚግሬሽን፣ ንግድ ባንክ፣ ኤሌክትሪክ፣ ውሀ፣ ቴሌ፣ አየር መንገድ፣ የመኪና ቦሎ እና መንጃ ፈቃድ፣ የትራፊክ ቅጣት... ከሰሞኑ ደግሞ የዳኝነት ክፍያ እንኳን ጭማሪ ይደረግበታል። የኔ ጥያቄ:

አንደኛ፣ ጭማሪ ሲደረግ ነባራዊ የህዝብን አቅም እና ችግር ማገናዘብ የለበትም ወይ?

ሁለተኛ፣ በሌላው አለም እንደምናየው progressive የሆነ የ10%፣ የ20%... ወዘተ እያለ ጭማሪ ይደረጋል እንጂ ሲፈልግ የ150%፣ ሲያሻው የ700% ጭማሪ ማድረግ ማለት ነው?

ሶስተኛ ደግሞ አንድ ሰሞን ሲወራ የነበረውን ጥቂት የሆነ የደሞዝ ጭማሪ እንኳን ተግባራዊ ሳያደርጉ ህዝብ ላይ ሸክም መጫን ለምን ተፈልጎ ይሆን?

እውነት ይሄ ነገር አንድ ወዳጄ እንዳለኝ "መንግስት ከህዝብ ጋር እልህ ተጋብቶ እየቀጣው ነው" ያለው እውነት ይሆን እንዴ?

ዝመት ሲባል ዘምቶ ለሚቆም፣ ደግፍ ሲባል በሚሊዮኖች ወጥቶ ለሚሰለፍ፣ ሀገርህ ተደፈረ ሲባል "ኢትዮጵያን!" ብሎ ለሚዘምት ግን ይህ አይገባውም።

@EliasMeseret