ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
222 subscribers
65 photos
282 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
​​ https://t.me/hopereding

የፍቅር ጅማሬ
////////ክፍል 2//////////

.........ሄሎ ቤዛ ነሽ ድምፁን አወኩት የ ማቲ ድምፅ ነበር መላ አካላቴን ደስታ ሲወረው ይታወቀኛል ይኼን ደሥታ ግን ለነ ሀዊ ላለማሳየት ብሞክርን አልቻልኩም "አው ማን ልበል" አልኩት እንዳላወኩት ለማሥመሠል "ማቲ ነኝ"እንደዛ እንደዛ እያልን ሣናውቀው ብዙ ሰዓት አወራን ልክ ሥልኩን ሥዘጋው ነበር የነ ሀይሚን መተኛት ያሥተዋልኩት ሢገርም ይሄን ያህል ሌላ አለም ውስጥ ገብቼ ነበር ሀይሚ በመገረም "ቆይ እኛ ሣናቅ ሥልክ በ ውሀ መሥራት ጀመረ እንዴ ሆ "እኔ ግን የሀሚን ንግግር ትኩረት አልሠጠሁትም የልብ ምቴ ሲጨምር ይታወቀኛል በደረቴ ተኝቼ እያሠብኩ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ቅድም ማቲ ለምን ሀዊ ብሎ ተጣራ ይተዋወቃሉ ማለት ነው ? ሀዊ አንቺ ሀዊ ተነሽ አንዴ
"ውይይይ ልተኛበት ተይኝ"ሀዊ ማቲን ታውቂዋለሽ እንዴ ሥላት ከተኛችበት ተነሥታ"እእእ አዎ አውቀዋለሁ ሀሙሥ ሀሙሥ ሚገቡልን መምህር ተገኝ የሣቸው ልጅ ነው አንቺን እንዳሥተዋውቀው ተይቆኝ እኔ ደሞ ያንቺን ፀባይ ሥለማውቀው እራሥክ ተዋወቃት እሷ ሠው ሚልክ ወንድ አይመቻትም አልኩት ከዛ"ቆይ አንድ ጊዜ ቅድም ያን ሁሉ ጥያቄ ምጠይቂኝ አውቀሽ ነበር ?ሀዊ በጣም ደንግጣለች ምታወራው ጠፍቷት መንተባተብ ጀመረች"...ይኸውልሽ ቤዚ ቀድሜ ብነግርሽ ኖሮ አታናግሪውም ነበር ቤዝ እሱ በጣም ነው ሚያፈቅርሽ ሁለት አመት ሙሉ ብቻውን በፍቅርሽ ሲሠቃይ ቆይቷል ቤዝ አሁን እራሡ እኔ አደፋፍሬው ነው ያናገረሽ በ ጌታ ፊት እንዳትነሽው እባክሽ ቤዚ"አይኗ እንባ አቅሮ ነበር ሀዊ ብትልቁ ተነፈሠች ቤዝ ይቅርታ አድርጊልኝ ብላ አቀፈችኝ ችግር የለም ግን ካሁን ቡሀላ እንዳትዋሺኝ ብዬ አቀፍኳት ሀይሚም መታ ተጠመጠመችን እንደተቃቀፍን ብዙ ቆየን ፀጥታ ክፍሉ ውሥጥ ነግሷል ድንገት ሀይሚ ኸረ ቺኮች ተነሡ እንተኛ
    ዛሬ ደሥ ሚል ቀን ነው ሦስታችንም ላይብረሪ ውሥጥ እያነበብን ነበር ይቅርታ መቀመጥ ይቻላል ብሎ አዎ እንኳን ሳልለው ከጎኔ ተሠየመ ቤዝ እንዴት ነሽ አለኝ በሹክሹክታ ዛሬ ከተመቸሽ ለምን ምሣ አብረን አንበላም ቀና ብዬ እነ ሀዊን ሳያቸው እሺ እንድለው ይጠቅሱኛል በማህላችን ዝምታ ነገሠ ok በቃ ዝምታሽ እንደ እሺ ተወሥዷል ሥድሥት ሠዐት ላይ ሀኒ ካፌ እንገናኝ ብሎ ወጣ
         ይቀጥላል  
https://t.me/hopereding
/////////የፍቅሬ ጅማሬ/////////
_ክፍል 3_

.......እነ ሀዊ እኔን በማሣመር ተጠምደዋል ውሥጤ በጣም ፈርቷል 6:00 ሆኗል አጭር ጥቁር ቀሚሥ አድርጌ ፀጉሬን ለቅቄዋለሁ በግድም ቢሆን የተቀባሁትሜካፕ ቢጤ ፊቴ ላይ ይታያል አሁን ሀኒ ካፌ ደርሻለሁ ፍርሀቴ ይበልጥ ጨምሯል ማቲን ከሩቁ አየሁት ዋው እንዴት እንዳማረበት አይኔን መንቀል አቅቶኛል ነጭ ቲሸርት በቃሪርያ ሡሪ ለብሷል መነፅሩን በቲሸርቱ አንገት ላይ ሰክቶት እዛ ሰፊ ደረቱ ላይ ወድቋል በቅፅበት መነፅሩን ባረገኝ ብዬ ተመኘሁ በእጁ ምልክት ሠጠኝ አጠገቡ ሥደር ስ አቅፎ በ ጆሮዬ ሥለመጣሽ ደሥ ብሎኛል ብሎ ይበልጥ ወደራሡ አሥጠግቶ አቀፈኝ
        እንዲ እንዲ እያልን አንድ አመት ሞላን ማቲ ዘንድሮ ተመራቂ ነው መመረቂያ ፅሁፉን በማዘጋጀት ተጠምዷል ፍቅሩ በኔ ሣይጠነክር አይቀርም እሡን ሣላይ ማደር ዳገት እየሆነብኝ መትቷል በሥልኬ መልክት ገባ ማቲ ነበር ፍቅሬ ዛሬ አምሮብሽ ፏ ብለሽ 9:00 ሰዐት ላይ የተለመደው ቦታ እንገናኝ የሚል ነበር ምን አሥቦ እንደሆነ ባላውቅም ሰዐቱ እሥኪደርሥ ቸኮልኩ አይደርሥ ነገር የለ እንዳለኝ ፏ ብዬ ሄድኩ እሱ ብዙም አልዘነጠም ማማዬ በጣም አምሮብሻል ብሎ አንገቴን ሣመኝ እኔ በመገረም በሠላም ነው እንደዚ አይነት ቀጭን ትዛዝ ወሬዌን ሣልጨርሥ ባጃጅ አሥቁሞ ጉዞ ጀመርን እሥካሁን የት እንደምንሄድ አላወኩም ባጃጁ ኤግል ሆቴል በር ላይ ቆመ ወደውሥጥ ሥንዘልቅ የ ማቲ አባት ፊለፊት ቁጭ ብለው አየሓቸው በጣም መደንገጤ ማቲ ገብቶታል ወደራሡ ጠጋ አድርጎ አቀፈ ኝ ትንሽ እንዳወራን ጋሽ ተገኝ "በሉ ልጆች እኔ ነገ ጠዋት ክላሥ ሥላለኝ ሄጄ አረፍ ልበል እናንተ ዘና ብሉ ብለው ተነሡ በይ ቤዝዬ ልጄን አደራ በሉ ደህናሁኑ አባቱ እንደሄደ አሁን ፍራትሽ እንዲለቅሽ ክላስ ይዘን ትንሽ እንጠጣና ከዛ እሸኝሻለሁ ክላሥ ይዞ መጠጣቱን ሥለለመድኩት ምንም አልመሠለኝም
የዛሬው ግን የተለየ ነበር........
   ይቀጥላል   
የፍቅሬ ጅማሬ
ክፍል 4



........ክፍሉ በቀይ አበባ አጊጦ በሻማዎች ብርሀን ፈክቶ በለሥላሣ ሙዚቃ ታጅቦ በቃ የሆነ አይነት ውበት ተላብሷል ወደ ማቲ ሥዞር ማቲ በጉልበቱ ተንበርክኮ አይናይኔን በሥሥት እያየ የኔ አሥቀያሚ ታገቢኛለሽ ሢል የደሥታ እንባ ከአይኖቼ ላይ ሺራገፉ ይታወቀኛል እግሮቼ ክደውኝ መቆም አቅቶኝ አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አልኩ መቶ ከጎኔ እንባዬን እየጠረገ መልሥሽን እየጠበኩ ነው ሢለኝ እየተርበተበትኩ በሎህሣሥ አዎ አው የኔ ፍቅር አልኩ ፀጉሬን እየዳበሠ አፈቅርሻለሁ ቤዝ ብሞትም እንኳን አንቺን ማፍቀሬን አላቆምም እያለ በዝግታ ተጠጋኝ ከናፈሮቹ ከንፈሬን ሢነካው ታወቀኝ ቀሥ እያለ አንገቴን መሣም ጀመረ የቀሚሴን ዚፕ..........
       ዛሬ ቀኑ ሠኞ ነው ማቲ ትላንትና ተመረቀ ምሽቱን ሁላ እነ ማቲ ቤት ነው ያሣለፍነው ማቲ እናት የለውም እኔ ደሞ አባት ዛሬ ወደናቴ ቤት መጥቻለሁ ማቲ በር ላይ አድርሶኝ ተመለሠ እናቴን ላሥተዋውቅክ ሥለው ሌላ ጊዜ በሰፊው ብሎኝ ሄደ ገና ከመሄዱ እየናፈቀኝ ነው
ለእናቴ ብቸኛ እና የልጅነት ልጇ ሥለሆንኩ እንደ እህቷ ነው ምታየኝ በጣም ግልፅ ከመሆናችን የተነሳ እንደጓደኛዬ ነው ማያት ሥለ ማቲ በሥልክ ነግሬአት ሥለነበር ፎቶውን ካላየሁ ብላ ውጋት ሆናብኝ ሥልኬን ከፍቼ እንድታይ ሠጠሓት ፎቶዎቹን እያየች"ማሬ ይሄ የት ነው "እቺ ማናት የሚሉ ጥያቄዎችን ታከታትልብኝ ጀመር ደሥታዋ ብዙም አልቀጠለም ከመቅሥፈት ፊቷ መቅላት አይኗ መደፍረሥ ጀመር ከዚ በፊት እንዲ ሥትሆን አይቻት አላቅም በጣም ፈራሁ ምነው እማ ምን ሆንሽ እንባ በቋጠሩ አይኖቿ እየተመለከተችኝ ይሄን የሤጣን ቁራጭ የት ነው ምታውቂው ብላ አፈጠጠችብኝ
            ይቀጥላል
የፍቅሬ ጅማሬ

ክፍል 5

.......አንቺን አይደል ማናግረው አንቺና ማቲዎስ መሀል ምን እየሠራ ነው ብላ ሥልኩን ወደኔ አዞረችው እእእእማ ምንድነው ግራ አጋባሽኝ ቀድመሽ የጠየኩሽን መልሺ የት ነው ምታውቂው እእእእሱ ማለቴ እሳቸው የማቲ እእእ የማቲ "የማቲ ምን ተናገሪ"የማቲ አሥተማሪ ነው ግን የት ነው ምታውቂው እማ እባክሽ ንገሪኝ "ልጄ የአባትሽ ሞት ምክንያት ይሄ የተረገመ ፍጥረት ነው "እንዴ ኸረ እማ ተሣሥተሽ እንዳይሆን ጋሽ ተገኝ "የአፌን ሳልጨርሥ "የዛን ከይሲ ሥም ድጋሚ እዚ ቤት እንዳጠሪ"በግድ የያዘችውን እንባ ለጉድ ታወርደው ጀመር ይኸውልሽ ማሬ ይኼ ና አባትሽ ሸሪክ ነበሩ ይሄ ገንዘብ ያወረው ሠው በተሣሣተ ወረቀት ላይ አሥፈርሞት ሙሉ ሀብቱን ወረሠብት ይሄንን መቋቋም ያቃተው አባትሽ እራሡን አጠፋ ያኔ አንቺ ገና የ ሦስት ወር ህፃን ነበርሽ አየሽ ቤዝ አንቺን ያላባት እንዳሣድግ ምክንያቱ ይኽ ሰው ነው ተነሥታ ወደ መኝታ ቤት ገባች ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ተሠማኝ ማደርገው ጠፋኝ እኔም ወደ ክፍሌ ገብቼ ፈጣሪዬ ከዚ ህልም ሆነ ቅዥት እንዲያነቃኝ ፀለይኩ አልቻልኩም ባለቅሥም ሊወጣልኝ አልቻለም እንዳፈጠጥኩ ሌሊቱ በንጋት ተተካ አሁንም እንደጨነቀኝ ነው ለሆነሠው መተንፈሥ ፈለኩ ሀይሚ ሥልኳ አይሠራም ሀዊጋ ደወልኩ ሄሎ ሀዊ"ወዬ ውዴ በሠላም ነው በዚ ጠዋት "ሀዊ ሀዊ "ምንድነው ለምንድነው ምታለቅሺው"ሀዊ እባክሽ አሁንኑ ነይ እኔ ላብድ ነው " እሺ መጣሁ ቤዚ በናትሽ  አታልቅሺ"ሥልኩ ተዘጋ እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም የማሚን የ እግር ኮቴ ሥሰማ ዘልዬ ብርድ ልብሡሥጥ ገብቼ ተኛሁ ማሚ በሩን ከፍታ እንደተኛሁ ሥታይ ተመልሣ ዘግታ ወጣች በሩ ተንኳኳ ሀዊ ነበች በሩን ከፍቼ አሥግባኃትና ሁሉን ነገርኳት ለሁለት እየተንቆራጠጥን ማቲ ደወለ ማንሣት ባልፈልግም ሀዊ አሥገደደችኝ ሄሄሎ"እንዴት አደርሽልኝ የኔ አሥቀያሚ"ማቲ ማውራት አለብን አሁንኑ የተለመደው ቦታ እንገናኝ በሁኔታው ግራ እንደተጋባ ያሥታውቅበታል "ቤዝ ግን ደህና ነሽ "ሥንገናኝ እናወራለን ብዬ ሥልኩን ዘጋሁት ሀዊ አብሬሽ ልምጣ ሥትል እዚሁ እንድጠብቀኝ ነግሬት ወጣሁ ማቲን ሣየው ይበልጥ ሆድ ባሠኝ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ማቲ ላበላብ ሆነ አፉ ተሣሠረ በቃ ነገ እናወራለን ብሎ በቆምኩበት ጥሎኝ ሄደ ማቲ አሳዘነኝ ጭንቀቱ ፊቱ ላይ ይነበብበት ነበር እና ከዚ ቡሀላ ምን ሊፈጠር ነው ፈራሁ ምን ልንሆን ነው ተለያየን ወይሥ ምን እኔ ላብድ ነው ምናለ ሞቼ ባረፍኩት እኔ ማቲን አጥቼ መኖር አልችልም ግን እማዬስ...............ቤት ሥደርሥ ሀዊ ሶፋው ላይ ጋደም ብላ ሀይሚ ደሞ ከዛ እዚ እየተንጎራደደች ነበር የኔን መምጣት ሢያዩ ሁለቱም ወደኔ መተው ምን ተፈጠረ ማቲ ምን አለ እያሉ ጠየቁኝ እኔ የነሡን ጥያቄ ምመልሥበት አቅሙም ጉልበቱም የለኝም ማሚሥ ሥላቸው ወደሥራ እንደሄደች ነገሩኝ አይኔ እየደበዘዘብኝ ነው መቆም አቃተኝ እራሤን ሣትኩ ከዛ የተፈጠረውን አላውቅም ስነቃ ግን ማቲ አጠገቤ ተቀምጦ እንባ ባቀረሩ አይኖቹ እያየኝ የኔ ፍቅር ነቃች እያለ ለነ ሀዊ እየነገራቸው ነው እነ ሀይሚ እየሮጡ መጡ ሀዊ በ እጇ ውሀ ይዛለች እንኪ ጠጪ ማሬ"ግን ምን ሆኜ ነው እራሤን ሥቼ ነበር ቆይ ማቲ እንዴት መጣክ"ማቲ በእጆቹ ፀጉሬን እየዳበሠ ሀይሚ ደውላልኝ ነው ቀና አድርጎ ውሀውን አጠጣኝ ውዴ አንቺ ላይ አንድ ዘለላ እንባ ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ ብሎ ግንባሬን ሣመኝ ማቲ ሢሥመኝ መኖርን ተመኘሁ የመኖሬ ምክንያት ማቲ እንደሆነ አሠብኩ ፍቅሬ እውነት ምትወጂኝ ከሆነ ጠንክረሽ አጠንክሪኝ ብሎኝ ተነሣ ማቲ ወዴት ነው"ማዘር ሣይመጡ ልሂድ ሀዊ አብራቹሀት ሁኑ ቤዝ አፈቅርሻለሁ "ብሎኝ ወጣ ጋጠገቤ ባይርቅ ምርጫዬ ነበር
        ጊዜው ሄዷል ሣላሥበው እኩለቀን ሆኗል ማሚ ለምሣ መጣች ሳሎን ሶፋ ላይ ጋደም ብዬ ነበር የማሚ ጥሪ ከገባሁበት ሀሣብ አሦጣኝ አንቺ እንቅልፋም እሥካሁን አልተነሣሽም እነ ሀይሚሥ "ውይ እማ መጣሽ እንዴ እነ ሀይሚ ቤት ሂዱ ብያቸው ነው"ምሣ በላቹ ሥትለኝ አው አልኳት ወይ እማ እንኳን እህል ውሀም ከጉሮሮዬ አልወርድ እንዳለኝ አላወቀች ሥልኬ ጠራ ማቲ ነበር ወደ ክፍሌ ገብቼ አነሣሁት "ሄሎ የኔ አሥቀያሚ ተሻለሽ"አው ደህና ነኝ ግን አንት እንዴት ነክ "አሁንም ግራ እንደገባኝ ነው ምን ላርግ ማደርገው ጠፋኝ "ማቲ አይዞክ ይኼም ያልፋል"ፍቅሬ ራስሽ ያላመንሽበትን ቃል እኔን አትበይኝ ወይ ተያይዘን እንጥፋ ከዚ ቅዠት እናምልጥ"ማቲ እንዳታሥበው እናቴ እኔ ብቻ ነው ያለኃት እኔን አጥታ መኖር አትችልም ትሞትብኛለች "ግራ ቢገባኝ እኮ ነው ውዴ እንጂ እራሥ ወዳድ እንዳልሆንኩ ታውቂያለሽ"አውቃለሁ አለሜ በቃ ማታ የተለመደው ቦታ እንገናኝ ቻው "እሺ በቃ ቤዝ ቻው "ማቲ"ወዬ የኔ ፍቅር " በጣም አፈቅርካለሁ"እኔም ውዴ ቻው"ሥልኩን እንደዘጋሁት በር ተንኳኳ ማሚ ልትከፍት ሥትነሣ እኔ እከፍታለሁ ብዬ ወጣሁ በሩን ሥከፍት ግን ..........
      ይቀጥላል  
https://t.me/hopereding
​​  
የፍቅሬ ጅማሬ
ክፍል 6
........... በሩን ሥከፍት ጋሽ ተገኝ በር ላይ ቆመዋል አይኔን ማመን አቃተኝ ጋሽ ተገኝ "እንዴት ነሽ ቤዝ እናትሽ አለች"እእእአው አለች ግን ጋሽ ተገኝ "አታሥቢ ላናግራት ብቻ ነው"አይሆንም ጋሼ ትጣላላቹ እባክህን እሺ በለኝና ተመለሥ"አይሆንም የኔ ልጅ እዚ ድረሥ መጥቼማ ሣላናግራት አልሄድም"ግን"በኔ ይሁንብሽ ምንም ችግር አይፈጠርም"ብሎ ገባ ማደርገው ጠፋኝ እጄ ያለማቋረጥ ይንቀጠቀጥ ጀመር ፈራሁ የማሚን ድምፅ ሠማሁ ደሞ ምን ቀረክ እያለች ትጮሀለች በሩን ከፍቼ ወጣሁ ጆሮዬን ይዤ በሠመመን ብዙ እርምጃዎችን ተራመድኩ ግን ምን እየሆንኩ ነው በዚ ሰዐት ከናቴ ጎን መሆን ሢገባኝ እኔ ግን...ወደቤት መመለሥ ጀመርኩ በር ላይ ሥደርሥ ቤቱ በዝምታ ተውጧል ግራ ገባኝ እማ እንዴት ልትረጋጋ ቻለች ምን ሆና ይሁን ሮጬ ወደቤት ሥገባ ጋሽ ተገኝ ሶፋው ላይ ቁጭ ብለዋል እማ መሬት ላይ ቁጭ ብላ የሆነ አሮጌ ወረቀት በእጇ ይዛ ታነባለች እጆቿ እየተንቀጠቀጠ ነው እንባዋ ፊቷን ሞልቶታል ምንድነው ምን ተፈጠረ እግሯ ሥር ተቀመጥኩ አቅፋኝ ትንሠቀሠቅ ጀመር እማ ተረጋጊ እሷን ማባበል ትቼ እኔም ማልቀሥ ጀመርኩ ጋሽ ተገኝን ማልቀሥ የፈለገ ይመሥላል ግን ብሦታችንን ማባባሥ ሆኖበት ከእንባው ጋር ሢታገል ይታያል ያን አሮጌ ወረቀት ወሥጄ ማንበብ ጀመርኩ ከ አባቴ ነበር "ውዷ ባለቤቴ የልጄ እናት ይህ ወረቀት ከደረሠሽ ሞቻለሁ እባክሽ ይቅር በይኝ አማራጭ አጣው ዙሪያዬን በእዳ ተከበብኩ በእዳ ያልተያዘው ቤቱ ብቻ ነው ግራ ገብቶኝ ማደርገው ሣጣ የድርጅቴን አክሲዎን እንዲገዛኝ ተገኝን ለመንኩት በአንድ ልጁ ለመንኩት ተገኝን ታውቂው ኖሯል በሠው ሚጨክን አንጀት የለውም በ 20,000 ብር አክሢዎኑን ገዛኝ ገንዙቡንም በናንተ ሥም ካሥቀመጥኩት መንግሥት ይወርሠዋል ብዬ ተገኝ ጋ አሥቀምጬዋለሁ ሠብሊ የኔ ውድ ሚሥት ልጄን አደራ ሥለኔ ና ሥላንቺ ፍቅር እየነገርሻት ትደግ ፍቅር ከምንም የበረታች ነችና" ጋሽ ተገኝን ቀና ብዬ አየኃቸው ጋሽ ተገኝ እንባው እየተናነቀው ይኸው ነው እውነቱ ይሄንን ደብዳቤ ልሠጥሽ ሥመጣ ልጅሽን ይዘሽ ወደ ትውልድ ሀገርሽ እንደሄድሽ አረዱኝ ብዙ አመታቶችን ተመላለሥኩ ግን ላገኛቹ አልቻልኩም ባለፈው ለማቲ ምርቃት የመጣው ባለንጀራዬ ልጅሽ አዳማ ዩኒቨርሥቲ ደርሷት እዚ እንደመጣቹ ነገረኝ ይኼ ነገር ባይፈጠርም መምጣቴ አይቀርም ነበር"ብለው ተነሥተው ወጡ እማ አፏ ተሣሥሯል ምን ማለት እንዳለባት ግራ እንደገባት ታሥታውቃለች እኔም ምለው ጠፍቶኛል ዝምታው በቤቱ ውሥጥ ከተራራ ገዝፏል ማቲ ያ የሁለት አመቱ ህፃነው ማለት ነው እማ ወደኔ እያየች ለምን ዋሸሺኝ ብቻሽን ስትሠቃዪ ነበር ወይኔ ልጄን ብላ አቀፈቺኝ ሥልኬ ላይ የፅሁፍ መልክት ገባ ማቲ ነበር "ፍቅሬ እየጠበኩሽ ነው......
        ይቀጥላል 
https://t.me/hopereding
​​የፍቅሬ ጅማሬ

ክፍል ሰባት 7 የመጨረሻ ክፍል

.....እማ እንደዚ ሆና እንዴት ልውጣ ?????"እማ ነይ ክፍልሽ ገብተሽ አረፍ በይ" እሺ የኔ ቆንጆ ሄጄ እተኛለሁ አንቺ ግን ሂጂ ማቲን አታሥጠብቂው ተነሽ ሂጂ ብላ ወደክፍሏ ገብታ በሩን ቆልፋ ተኛች እኔም ማቲጋ ለመሄድ መንገድ ሥጀምር ሀዊ ደወለች ሄሎ"ውዴ እንዴት ነሽ ተረጋጋሽ"ሀዊ ሥጠይቀኝ የደሥታ ሣቄን ለቀኩት እና ሁሉንም ነገርኳት ከዛ ለ ማቲ ንገሪውና ዛሬ ቀኑን እናክብረው አለቺኝ እኔም በሀሣቧ ተሥማምቼ ሠዐቱንና ቦታውን ከማቲጋ ተነጋግረን አሣውቅሻለሁ ብዬ ሥልኩን ዘጋሁት ማቲ ሥልክ እንጨት ተደግፎ በሀሣብ ጭልጥ ብሏል እኔ ሄጄ ወገቡላይ ተጠመጠምኩበት ውይ የኔ አሥቀያሚ መጣሽ እንዴ ብሎ በዛ ሠፊ ደረቱላይ አጣብቆ ለብዙ ደቂቃ አቀፈኝ አሥተቃቀፉ በርሬ እንዳልሄድ የፈራ አሥመሠለበት ግን ወድጄዋለሁ ማሬ እንዴት ነሽ ተሻለሽ ሢለኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩበት አዲሥ ነገር አለንዴ የኔ ማር እንዲ ስፈነድቂ አይቼሽ አላውቅም "አለሜ ችግራችን ተወገደ "ማቲ በጣም ደነገጠ ማለት ሲል ጮኸ"አባትክ እቤት መቶ ነበር ችግሩን ፈቶት ሄደ ማቲ በደሥታ ሠከረ ከዚዛ ይወራጭ ጀመር አንዴ ፀጉሩን አንዴ እኔን ይነካል ከዛ አቅፎ አሽከረከረኝ ሌላ ደሥታውን ሚገልፅበት መንገድ እንዳጣ ያሥታውቃል ደሥታው ሢበርድለት እኔና ሀዊ የተነጋገርነውን ነገርኩት እሱም አባቱን እኔም እናቴን የኔንም የሡንም ጓደኞች ለመጋበዝ ተሥማምተን ቤት አድርሦኝ ተመለሠ ለሀዊ ደውዬ 1:00 ላይ ማፊ እንደምንገናኝ ነግሬት ወደ ማሚ ክፍል ሥገባ ተኝታ ነበር ከዛ ወተን ዘና እንበል ሥላት እንቢ ብላ በሥንት ትግል ሀሣቧአሥቀየርኳት ከዛ ሁለታችንም ፏ ብለን ወደ ማፊ ሄድን ሥንደርሥ ሁሉም ተሠብሥበዋል የማቲ ሁለቱ ጓደኞቹ አባቱ እነ ሀዊ ልክ እንደገባን ጋሽ ተገኝና እማ ይቅርታ ተጠያየቁ ማልለት እማ ይቅርታ ጠየቀች በቃ ጨዋታው ደራ በድንገት ማቲ ተነሥቶ አንዴ ሠዎች ብሎ ወሬአችንን እሥቆመ ሁላችንም ፊታችንን ወደ ማቲ አዞርን ከዛ ማቲ መጣና አጠገቤ ተንበርክኮ በድጋሚ ታገቢኛለሽ ብሎ ጠየቀኝ እነ ሀዊ እሺ በይ እያሉ ጩኸታቸውን አቀለጡት እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ አገባካለሁ አልኩት ከዛ ቀለበቱን አደረገልኝ ወደናቴ ሥዞር በደሥታዋ ብዛት እያለቀሠች ነው ከዛ ማቲ ሄዶ ጉልበቷን ሣመ እኔም እንደዛው ሁለታችንም ሄደን የአባቱን ጉልበት ሣምን
             #ከ 5 አመት ቡሀላ
እኔና ማቲ በ ሠርግ ከተጋባን ዛሬ ድፍን አራት አመት ሞላን ማቲ በ አንድ ድርጅት ውስጥ የፋይናሥ ሀላፊ ሆኖ እየሠራ ነው  አሁን የአንዲት ሴት ልጅ እናት ነኝ  ሥሟንም ሣሬም ብለናታል ሣሬም ማለት ሠጠን ማለት ነው ፍቅር ከጌታ የሚሠጥ ሥጦታ ነው
            ፍቅር ይስጠን❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
                 
        ተፈፀመ

እሰካሁን ኣብራችሁ ሰለነበራቹ እናመሰግናለን
https://t.me/hopereding