ማንበብ ህይወት ነው 🤼‍♂️📕
216 subscribers
65 photos
279 links
ሰላም 🤚 -

📯 📯  እንኳን በደህና መጡ!  📯 📯


በዚህ ቦት አማካኝነት https://t.me/hopereding

➡️.  ትረካዎችን 🎙
➡️.  ልቦለዶችን 📖
➡️.  ኢ-ልቦለዶችን 📕
➡️.  መፅሐፍትን በpdf 📚
➡️.  ግጥሞችን 📝
➡️.  አጫጭር ትረካዎችን 🎙
➡️.  የመፅሐፍ ቻናሎችን 📌 ያገኛሉ።
አስተማሪና አነቃቅ ንግግሮች ከተለያዩ መፅሐፎች

▫️ቦቱን ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ
Download Telegram
#"አይ_እቴ"



እሷ፡-
"መልኩ ደምግባቱ ቁመናው ምን ቢያምርም 
በቁንጅናው ብቻ ሰው አይፈቀርም።
እንዴት ይፈቀራል?
እንዴት ይወደዳል?
በል እስኪ ተናገር እርግጥ ቆይ ያስኬዳል?
አይ አይመስለኝም ...
ያን ዳር የለሽ ስሜት ልብ እስካልወለደው
ስለሚያምር ብቻ አልችልም ልወደው።"


እኔ፡-
" እንዲ እንዲ እያልሺኝ አትከራከሪ
እረ እንደው አንቺ ሴት ምናለ ብታፍሪ።
አይ እቴ ...
እኔ አንቺን ማፍቀሬ እያለ ምስክር
ባይገባሽ ነው እንጂ አያሻም ነበረ በዚ ርዕስ ክርክር።"


━━━━━━━━✦
✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

Join us 
🙏
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding

"ኣደ ሰብኣያ ካብ መግዳል  ዘይተመለሰ"

ካብታ በዓል ቤታ ብሞት ካብ ዝፍለያ ጊዜ ኣትሒዛ ዕላታዊ ናብርኣ ሓደ ኳ ዝሕግዛ ዘይብላ ፡ ከልበትበት እናበለት ነቶም ክልተ ደቃ ትኣሊ ዝነበረት ኣደ ኢያ ፡፡

ሓደ ግዜ ብፍጹም ንድራር ዝኸውን መግቢ ሰኣነት ። ንሳዃ ንጥምየት ለሚዳቶ እንተኾነት ፡ ደቃ ግን ክጻወርዎ ኣይከኣሉን ፡ ኣዒንቶም ሰለምለም እንዳ ኣበሉ ፡ ኣደይ ጠሚና ጠሚና !! ንብዓት እንዳ ሓወሱ ፡ ገጽ ገጻ ክጥምቱ ኣምሰዩ ።
እታ ለባም ኣደ ናብ ፈጣሪኣ ፡ ንብዓታ ደቃ ከይርእይዎ ደጋጊማ እንዳ ደረዘት ፡ ኣንታ ለዋህ ጎይታ ኣነሲ ሓጢኣተኛ ኢየ ፡ ናብ ንብዓት ደቀይ ግን ጠምት እሞ ናይ ዕለት እንጀራና ሃበና ኢላ ብምጸላይ ፡

ተንሲኣ ዕንጨይቲ ብምንኻስ ወላሓንቲ ዘይብሉ ምሉእ ጻሕሊ ምሉእ ማይ ሰኽተተት ። ንደቓ ድማ ኣራእሶም እንዳ ሓኸኸት ፡ ስጋብ እዛ ጸብሒ ትበስል ጽንጽዋይ ክነግረኩም ኢላ ዛንታ ክትነግሮም ኣምሰየት ።

ዞምደቀይ ቀሪባ ኢያ ክትበስል እንዳ በልት ፡ ድቃስ ከም ዝወስዶም ገበረት ፡፡ ምስ ደቀሱላ ነቲ ዘናኸሰቶ ኣጥፊኣ ነቲ ሸረኽረኽ ዝብል ዝነበረ ማይ ውን ኣውሪዳ ደቃ ሓቛፋ ደቀሰት ::
ከም ኣመላ ለይቲ ኣንጊሃ ሰብ ብድቅሱ ብምትንሳእ ናብ በረኻ ከይዳ ሓምሊ ሓማሚላ ናብ ቤታ ተመልሰት ደቃ ውን ከምታ ዝገደፈቶም ደቂሶም ጸንሕዋ ፡ ከምብሓድሽ ነቲ ሓዊ ኣናኺሳ ድማ ነቲ ሓምሊ ኣብሰለቶ ፡
ንደቃ ኣተንሲኣ ትማሊ ድቃስ ወሲድኩም ምትሳእ ከኣ ኣቢኹምኒ ንዑ
ሕጂ ቁረሱ ብምባል ደቃ ኣዐንገለቶም ፡፡

ማማ ዓለም  🌍
ማማ ተፈለ እያ
ነዊሕ ዕድመ  ንኣደታታት
​​፨--•••••••••• ሞሮ •••••••••••--፨
         ፨--•••••ክፍል 39 ••••••--፨
https://t.me/hopereding

ሁለታችንም የቅዳሴው ሰአት እስኪያልቅ ዝም ተባብለን ቆየን እንዲው ማውራት ስላልፈለገች እንጂ በውኑ እያስቀደሰች አልነበረም ሃሳቧ ሌላ ቦታ ነበር ዝም ብላ እንባዋ እንደጅረት ከአይኗ ይፈሳል አንጄቴ በላችኝ በጣም አዘንኩ ላባብላትም ፈለግኩ ግን ሰምሃልን አውቃታለው ከተናደደች እሳተገሞራ ማለት ነች ማንም አይችላትም ባዝንም አቅፊያት ላባብላት ብፈልግም ዝም ማለቱ የተሻለ አማራጭ መስሎ ታየኝ። እንባዋ መቶ ግዜ ይወርዳል እሷም መቶ ግዜ ታብሰዋለች ምንም ልላት አልቻልኩም እኔ አስቀይሚያት ከሆነ ግን እንዲ የሆነችው በእውነት ቀሽም ነኝ እኔ የማንንም ልብ መስበር አልፈልግም የማንንም ስሜት መጉዳት አልፈልግም የፈለገችውን ትቅጣኝ እቀበላለው።
የቅዳሴ ሰአቱ በእንደዚ አይነት ሃሳብ ውስጥ ተውጬ ሳላስበው ገስግሶ አለቀ ድንገት ሰምሃል ፀበል ለመጠጣት ወደ ፀበል ቤቱ አቅጣጫ ስትንቀሳቀስ ነበር ከሰመመኔ የነቃሁት። ልጠይቃት አልፈለኩም እዛው ቆሜ እስከምትመለስ መጠበቅ ጀመርኩ ሳይታወቀኝ ብዙ ሰአት ስለቆምኩ ነው መሰለኝ ደክሞኝ ነበር አጠገቤ የነበረው የድንጋይ ወንበር ላይ ቁጭ አልኩ። ሰምሃልም ተመልሳ መጣች ምን እንደረፈጠረ ከተረጋጋች በኃላ ልታወራኝ ነው ብዬ ስዘጋጅ ጃኬቱን አውልቃ የድንጋዩ ወንበር ላይ አስቀምጣልኝ ልትሄድ ስትል እጇን ያዝኳት ዞራ አየችኝ ፊቷ በጣም የተቆጣች ይመስላል አስፈራችኝ ሰምሃል ስትናደድ አውቃታለው ታስፈራለች። ድምፄን አለሳልሼ አረ ሰሙ ምን እንደሆንሽ ንገሪኝ እስካሁን የጠበቅኩሽ እኮ ምን እንደተፈጠረ ትነግሪኛለሽ ብዬ ነው በማርያም ብዬሽ ሰሙ አንቺ በማርያም ተብለሽ እሚጨክን ልብ አለሽ አልኳት የተናደደችውን ለማለዘብ የተጠቀምኩት መንገድ ነበር። ናዲላንተ ማወቁ ምንም ጥቅም የለውም  ሲቀጥልም እሚመለከትህ ነገር አይደለም አለችኝ እዛው እንደቆመች እኔም ተነሳውና ቆምኩ እጇን ጠበቅ አድርጌ እየያዝኳት ለምን ሰሙ ለምን አይጠቅመኝም ለምን አይመለከተኝም ጓደኛዬ እኮነሽ በማንም በምንም የማልለውጥሽ ጓደኛዬ፤ ጓደኛ ባልነበረኝ ሰአት ጓደኛ የሆንሽኝ እኮ ነሽ ሰሙ እንዴት ነው ያንቺ ጭንቀት እማያገባኝ እንዲ እያለቀስሽ እየየሁሽ ዝም እምልሽ ይመስልሻል ሰሙ በጣም ተሳስተሻል አልኳት። አጥብቄ የያዝኩት እጇን በግድ አስለቀቀችኝና እንግዲያውስ ጓደኝነታችን እዚ ላይ ያበቃል እኔና አንተ ከዚ በኃላ ጓደኛ መሆን አንችልም አለችኝና ጥላኝ ሄደች መብረቅ የወረደብኝ ይመስል ደንግጬ ባለሁበት ደርቄ ቆሜ ቀረው መንቀሳቀስ አልቻልኩም ከቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን  ቅፅር ግቢ እስክትወጣ ድረስ ዝም ብዬ አየኃት ልከተላት አልቻልኩም ሰምሃል ንዴቷ እስኪበርድላት ድረስ ዝም ማለት አለብኝ ለግዜው ብትጣላኝም ተመልሳ ትታረቀኛለች የሚል ጭላንጭል ተስፋ በልቤ አደረ። ሰምሃል እንዲ አይነት ሴት እንዳልሆነች በደምብ አውቃለው ለግዜው ብንጣላም እንታረቃለን ስትረጋጋ ራሷ መጥታ እስከምታናግረኝ ድረስ ዝም ለማለት ወሰንኩ።
እሺሺሺ.... ሞሮ ምን ያክል ተመቻችው እስካሁን ባለው ላይክ በማድረግ አሳዩኝ በድርሰቱ ላይ ወይም አፃፃፉ ላይ ማንኛው አስተያየት ካላችው እባካችው በኮመንት ማስጫው ላይ ላኩልኝ እቀበላለው ።

    ክፍል 40       ይቀጥላል

               

🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢
​​፨---••••••••••••• ሞሮ••••••••••••--፨
          ፨--•••••  ክፍል 40 ••••••--፨
https://t.me/hopereding

አመሻሽ ላይ ከኪያር ጋር ግቢ ከተገናኘን በኃላ ሰምሃል እንደተጣላችኝ ነገርኩት ምክንያቱን ጠየቀኝ እኔም ምን እንደሆነ አላውቅም ትናንት ማታ ከተገናኘን ግዜ ጀምሮ ጥሩ ስሜት ላይ አልነበረችም አልኩት። እስኪ እኔ አግኝቻት አወራታለ እስከዛ ግን ትናንት ማታ ምን እንደተፈጠረ መለስ ብለህ አስታውስ ምናልባት አንተ ሳታስተውል ያደረከው ነገር ደብሯት ሊሆን ይችላል ብሎ የሱን መላምት እና መፍትሄ ያለውን ነገረኝ። ኪያር ስልኩን አውጥቶ ወደ ሰምሃል ጋር መደወል ጀመረ እኔም ወደ ትናንት በሃሳብ ማእበል እየተናጥኩ ሄድኩ። ትናንት ከሸገር ስንመጣ ደህና ነበረች እየተሳሳቅን እየተጫወትን ነበር የመጣነው ማታ ላይም እራት እየበላን ደህና ነበረች ትንሽ ስሜቷ መቀያየር የጀመረው እነኤቤጊያ ከመጡ በኃላ ነበር። ከኤቤጊያ ጋር የሆነ ያቀያየማቸው ነገር እንዳለ ገመትኩ ሁለቱን ምን ሊያቀያይማቸው ይችላል? ብዙ አሰብኩ ከዚ በላይ ራሴን ማስጨነቅ አልፈለግኩም። ኪያር ስልኳን አታነሳም! ሲለኝ ከሃሳቤ ነቃው አው እኔ መስለሃት ይሆናል ቴክስእ አድርግላት ወይ አልኩት። ማሰብ ባልፈልግም አእምሮዬ ማሰላሰሉን አላቆም ቆይ ከኤቤጊያ ጋር ከተቀያየመች ለምን እኔንም ተቀየመችኝ? እኔ ምን አደረኳት? በአሁን ሰአት ሰምሃልን አጊንቻት ላውራት አልችልም ኤቤጊያን  ግን አግኝቼ መጠየቅ እችላለ ወዲያው ስልኬን አወጣውና ኤቤጊያ ጋር ደውዬ አምፊ ደረጃዎቹ አከባቢ እንደንገናኝ ነገርኳት። የምሽቱ ብርድና ንፋስ ከበድ ያለ ስለነበር ልብስ ደረብረብ አድርጌ ከዶርም ወጥቼ ወደ አምፊ አከባቢ ሄድኩና ጥግ አከባቢ ያሉት ደረጃዎች ጋር ተቀመጥኩ ኤቤጊያም ትንሽ ቆይታ መጣች።
......................................................
አረ ሰሙ በማርያም ኣታልቅሺ በቃ ለምንድነው እንዲ እምትሆኚው ምን እንደተፈጠረ ሳታውቂ ነው እንዴ እንዲ እምትሆኚው አረ ራኪ ንገሪያት እኔ ከዚ በላይ አልችልም ደከመኝ ከመንገድ መግባቴ ነው አለች ሊዲያ በደከመ ስሜት ራኬብ በተራዋ ድምፃን አለሳልሳ አረ ሰሙ ይብቃሽ ምን ይባላል እንደዚ መሆን አለቻት። ሰምሃል እየተነፋረቀች መሳምስ ትሳመው እሱን ተቀብዬ መኖር እችል ነበር ግን ያኔ ሰክራ ግቢ አላስገባም ያላት ግዜ እሱ አብሯት አድሮ ነበር ያኔ አብሯት እንደተኛና ስለሱ ማሰብ እንዳላቆመች እዛውጋ ስታወራው ስምቻትልለው ከዛም በላይ ደግሞ ትናንህ ለሊት በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ እያለቀስኩ እያለ አንሶላዋን ተከናንባ ከሰክፍል ስትወጣ አይቻት ነበር እና ይህንን ነው ምንም ሳይታወቅ ምንም አላደረጉም እምትይኝ ናዲ እኮ ጥሩ ልጅ ነበር እንደዚ ያደርጋል ብዬ አላስብ ም ነበር አለቻቸው ይበልጥ እያለቀሰች። ሊዲያ እንደመናደድ እያለች ቆይ ሰሙ እኔ ያልገባኝ ነገር ያላችው ግንኙነት ጓደኝነት ብቻ ነው ሌላ ነገር እንወጀመራችው አላውቅም ናኦድ አሁን ያልሽውን ነገሮች በሙሉ እሚያደርግ አይመስለኝም አድርጎ እንኳን ቢሆን ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ! ምን አጠፋ ፍቅረኛሞች አይደላችሁም  ጓደኛሞች እንጂ ታዲያ እንደምትወጅው እስካልነገርሺው ድረስ እሱ በምን ያውቃል ጠንቋይ አይቀልብ አለቻት የሰምሃል ለቅሶ ያሰለቻት ትመስላለች ራኬብ በሊዲያ ንግግር የተናደደች ትመስላለች እንዴት ነው ጥፋተኛ እማይሆነው እስከዛሬ እኮ ዝም ብለው አይደለም የተቀመጡት ሰሙ ቃል አውጥታ ደፍራ ባትነግረው እንኳን እንደምትወደው አይደለም ለሱ ለማንም ያስታውቃል ማንም ባልነበረው ሰአት እሷ አይደለች እንዴ አብራው የነበረችው ታዲይ ይህንን እንደ አንድ ጓደኛ ብቻ ማየት አይከብድም!? ለሱ የከፈለቻቸውን ነገሮች ልብ ቢል ኖሮ በጣም እንደምትወደው ይገባው ነበር እሱ ባይወዳት እንኳን ለሷ ስሜት.ይጨነቅላት ነበር። እንዲ እየተከራከሩ እያለ ሰምሃል በመሃል በቃችችችውውው!!! ብላ ጮኀችባቸው ሁለቱም ደንግጠው ዝም አሉ።


         ይቀጥላል

               

🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
​​፨--••••••••••• ሞሮ ••••••••••••--፨
           ፨--•••••ክፍል 41•••••--፨

https://t.me/hopereding

ለተወሰነ ግዜ ዶርሙ በፀጥታ ተሞላ ሰምሃል ራሷ ላይ ባሰረችው ጥቁር ስካርቩ በእንባ የራሱ አይኗቿን አበሰቻቸው ስልኳት ጠራ አንስታ እየችውና መልሳ አልጋው ላይ ወረወረችው ስልኩ ጥሪውን ጨርሶ ድጋሚ ተደወለ ዝም ስትል ግዜ ሊዲያ ማነው ብላ ስልኩን ከአልጋዋ ላይ አነሳችውና አየት አድርጋው እንቺ አናግሪው እንጂ ኪዩ ነው አለቻት ሰምሃል ስልኩን ተቀብላት መልሳ አልጋዋ ላይ አስቃመጠችውና ኪያር አይደለም ናኦድ ነው በሱ ስልክ እሚደውለው አለቻትና በጀርባዋ ተንጋላ ተኛች። ራኬብ በረጅሙ ተናፈሰች ኡፍፍፍ... ምን አይነት እዳ ነው በጌታ ገና ከመጣታችን የጭንቅ መአት ቆይ ግን ሰሙ ለምን እንደምትወጂው ነግረሽው ቁርጡ አይታወቅም እንዲ ሆነ አልሆነም በሚል ሃሳብ ከምትጨነቂ ተንፍሰሽው ተገላገይ አለቻት።

.................................................
ኤቤጊያ እንደመጣች አምፊ ደረጃዎቹ ጋር ተቀምጠን ማውራት ጀመርን። ብዙም ግሳንግስ ሳላበዛ ከሰሙ ጋር ያቀያየማቸው ነገር ካለ ጠየቅኳት ግራ እየገባት እጇን ከንፈሯ አከባቢ አድርጋ ትንሽ ካሰላሰለች በኃላ ምን ያቀያይመናል ከሰሙጋ ብላ አሰብ አሰብ አድርጋ አረ... ምንም የለም እሚያቀያይመን ነገር ሰሙዬ ጥሩ ልጅ ናት ምንም እሚያቀያይመን ነገር የለም አለችኝ እሺ አልኳትና በሃሳብ ተዋጥኩ ግራ ገባኝ የገመትኩት ነገር ልክ አልነበረም። ምን ሊሆን እንደሚችል እያውጠነጠንኩ እያለ ኤቤጊያ ማልቀስ ጀመረች ደንገጥ ብዬ ምነው አቢጊ አልኳት ትናንት ባደረኩት ነገር ተቀይመኀኛል አይደል  በስነስርአት ሰላም ሳትለኝ እንኳን ቀጥታ ስለሰምሃል ጠየቅከኝ እኔ አጠገብህ እያለው እሷን ነው እምታየው አለችኝ አረ አቢጊ እንደዛ አይደለም አልተቀየምኩሽም ትንሽ ከሰሙ ጋር ስለተጋጨን ነው ግን አንቺም እንደዛ ማድረግ አልነበረብሽም ልክ አልሰራሽም እንደዛ አይደረግም አልኳት ጉንጮቿ ላይ ያሉትን እንባ እየጠረግኩላት እጄን ጥብቅ አድርጋ ይዛ ሳመቻቸው ናዲ አውቃለው እኔ ላንተ ጥሩ ሴት አልነበርኩም ብዙ ነገር በድዬሃለው ግን የዛኔ እንዳሁኑ አይነት ማንነት አልነበረኝም የበደልኩህ ይበልጥ ስትቀርበኝ የዋህነትህ አሸነፈኝ ሁልጊዜም ስላንተ አስባለው አብረን እንድንሄን እፈልጋለው ናዲ ታስፈልገኛለህ እባክህ አንድ እድል ብቻ ስተኝና አብረን እንሁን ሁሉንም ነገር አስተካክዬ አሳይሃለው አለችኝ። የግዜ ነገር አስገረመኝ... ከግዜያት በፊት ነገሮች ተገላቢጦሽ ነበሩ ተፈላጊ የነበረው ፈላጊ ሆነ ፈላጊ የነበረው ደግሞ ተፈላጊ ሆነ!! በተመስጦ ግዜን አደነቅኩ የነገን ሳናውቅ ዛሬ ከኛ በታች መስሎ የታየንን ሰው መበደል እንደሌለብን ታዘብኩ ምክንያቱም ነገ እኛን አልፎ ከኛ በላይ መሆን ይችላልና እንዲ በሃሳብ ተመመስጬ ስፈላሰፍ  አቢጊ ሳግ በሞላው ድምፅ ናዲ! ብላ መለሰችኝ።
አቢጊ አልችልም! አረፈድሽ! የዛሬ አመት መጥተሽ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ላይ ሌላ ታሪክ ይኖረን ነበር ግን የተምናው ናኦድ ዛሬ የለም ይቅርታ አቢጊ እኔ ስሜትሽን መጉዳት አልፈልግም እኔ እንደዛ አይነት ስሜት አሁን ላይ የለኝም ግን ከዚ የበለጠ ጥሩ ጓደኛሞች መሆን እንችላለን አልኳት ይህንን ስላት ኤቤጊያ እንባዋ መንታ መንታ እየሆነ እየወረደ ነበር አውቃለው ናዲ እንዳረፈድኩ አለችኝና ዝም ብላ ትንሽ ከቆየች በኃላ ሰምሃል ናት አይደል አለችኝ አልገባኝም አልኳት። ሰምሃልን ትወዳታለህ አይደል አለችኝ እንባዋን እየጠረገች። እንዴ ለምን አልወዳትም ጓደኛዬ አይደለች እንዴ አልኳት እንደዛ ለማለት አይደለም የፈለግኩት ሰምሃልን ታፈቅራታለህ አይደል ባትናገረው እንኳን ያስታውቅብሃል ስትለኝ ማብረቅ እንደመታው ሰው ደነገጥኩ.... ምን አስደነገጠኝ? ለምን ደነገጥኩ? ራሴን ጠየቅኩ እኔ ሰምሃልን አፈቅራታለው?
    

         ይቀጥላል
እዝጋጅ፦ "ማንበብ ህይወት ነው"
🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
        አገባህ ነበረ ……………


ቆሎ 'የቆረጠምን እኖራለን ውዴ
ልጅ በልጅ ይሆናል ቤታችን መውደዴ
አንቺ ውሀ አጣጬ የእግዜር ባለ አደራ
እሺ በይኝ ላግብሽ ፍቅራችንም ይድራ
::

አለኝ የኔ ሚስኪን..............
               አገባህ ነበረ..................

ቆሎ ባልቆረጥም እርሀብ ባይደፋኝ
ሊያውም በዚ ዘመን..........


ቆሎ ያልከው ውዴ
ዝም ብለህ ስታየኝ የኤርፎራ ዶሮ እመስላለሁ እንዴ?


ጭራሹን.................

ልጅ በልጅ ሆኜልህ
አንዱን ከኃላዬ ሌላውን ከፊቴ
ገሚሱን በግራ ገሚሱን በቀኜ
እሪ እምቧ ሲሉብኝ መንምኜ መንምኜ


የድስት ፍቅፋቂ በጋራ ስንበላ
ጎረቤት ቢረበሽ ይደብራል ኃ


እኔም ተማርሬ እግዜር ከሚከፋዉ
ቆሎህን ለብቻህ ተደብቅህ ብላው::

😂





━━━━━━✦🙏✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን
    𝚓𝚘𝚒𝚗 𝕦𝕤
https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding

​​​​◈ ━━━⸙ የታሪክ ማዕድ  ⸙━━━━ ◈


    ለምቶደው ሰው ምንም ነገር ልትሰጥ ስትፈልግ መልስ አትጠብቅ

ባንድ ወቅት ልጁ ከጎረቤታቸው ልጅ ድብን ያለ ፍቅር ይይዘዋል ታድያ የሷን ትኩረት ለመሳብ የማያደርገው ጥረት አልነበረም እሷ ያለችበት ቦታ ሁሉ ይገኛል ... ለካ ግን እሷ ነበረች ቀድማ ለልጁ ቦታ የሰጠችው እሱ የተከተላት የሚመስለው ቦታ ለካ እሷ ነበረች የምትገኘው...

ታድያ በውስጣቸው እየተፈላለጉ ሳይገላለፁ ግዜው መሮጡን ቀጠለ ይሄን የተረዳው ወንድ በድፍረት የፍቅር ጥያቄውን አቀረበ ይሄኔ ነበር ሳታንገራግር የተቀበለችው ... በዚ መልኩ የተጀመረው ፍቅር ቀጠለ...

ሁለቱም ፍቅረኛሞች ቢዋደዱም እሷ ጥርጣሬ ይገባት ጀመር ይህ የሆነው ደግሞ እሱ እወድሻለሁ አፈቅርሻለሁ የሚሉትን የቃላት ገለፃዎች ስለማይጠቀም ነበር እሷ ደግሞ ሁሌም ከሌሎች ፍቅረኛሞች የምትሰማቸውን እሷም ትጠብቅ ነበር ሲቀጣጠሩ አምራና ተውባ ትሄዳለች ብዙዎች ሲያሞግሷት እሱ ግን ምንም ሳይላት ይቀራል በዚም ፍቅሩን የማይገልፅላትና ውብ እንደሆነች የማይነግራት ስለማይወዳት ይመስላታል... ለዛም በመሀላቸው ጭቅጭቅ ይነሳ ጀመር በሆነው ባልሆነው ስለማቶደኝ ነው... እያለች ታበሳጨዋለች ይህም እየሰፋ ሄዶ እየተዋደዱ ለመለያያት በቁ...

እህቴ

➲ አንዳንዴ እኛ ሴቶች ከሚደረግልን ይልቅ የሚወራልን ይገዛናል ይህም አግባብ አይደለምና ተጠንቀቂ...

   ➲ሁሌም እኛ ሴቶች ብልህ ነን ስለዚህም ከሱ ሳትጠብቂ ያለሽን ፍቅር ስጪ ፍቅር መስጠት ከመቀበል የበለጠ ዋጋ አለውና እወቂበት...


ወንድሜ

    ➲አንተም ብትሆን ለግንኙነትህ ሀላፊነት መውሰድን አትርሳ ሁሌም ፍቅረኛህ ከሷ በላይ ማንም እንደሌለ ንገራት ምክንያቱም ደስተኛ ታደርጋታለህ ።

           
#ሼር_ይደረግ
https://t.me/hopereding

​​፨--••••••••• ሞሮ •••••••••--፨
         ፨--• ክፍል 42 •--፨

በውስጤ ለማንም ሳልናገር ሳብሰለስለው የነበረ የኔም  ጥያቄ ነበር አቢጊ እንደዚ ስትለኝ ለምን ደነገጥኩ? እውነት ስለሆነ ነው? ፊቴ በአንዴ ተቀያየረ ። አይ አቢጊ ተሳስተሻል ሰሙ ጥሩ ጓደኛዬ ናት እሷ እኔን በጓደኝነት እንጂ በፍቅር ምናምን አይን አይታኝ አታውቅም ስለፍቅር እንኳን አንድም ቀን አውርተን አናውቅም አንዴ ብቻ እምትወደው ሰው እንዳለ ነግራኛለች አልኳት።

................................................
ሰምሃል ትንሽ ከተረጋጋች በኃላ ሊዲያ ወደሷ አልጋ እየተጠጋች ሰሙዬ ወክ እናድርግ ላንቺም ጥሩ ነው ትንሽ ቀለል ይልሻል አለቻት ራኬብም ቀበል አድርጋ አው ለምን ወክ እናደርግም እንደውም አንፊ አከባቢ እንቀመጥ አየሩ ደስ ይላል እዛ አከባቢ አለቻት እሷም እየተደረበች። አረ... እኔ አልሄድም መተኛት ነው እምፈልገው አለቻቸው ሊዲያ ተናደደች ኤጭጭ.... አሁንስ አበዛሽው ብላ የለበሰችውን ብርድልብስ ገፈፈቻትና እግሯን ትጎትታት ጀመር ሰምሃል እንደመሳቅ እያለች ምን እያደረግሽ ነው አለቻት። ራኬብም ስትስቅ ስታያት እሷም ተደርባ  እግሯን ለሁለት እየጎተቱ በግድ ከአልጋው አውርደው መሬት ተቀመጠች በሁኔታው ሶስቱም ተሳሳቁ እሺ በቃ ወጣለው ፊቴን ልተጣጠብና እንሄዳለን አለቻቸው እንሱም እሺታዋን ሲሰሙ ጉትጎታቸውን ትተው ልብስ መደራረብ ጀመሩ። ራኬብ ቡኒ ባለኮፍያ ጃኬቷን እያደረገች በናታችው አምፊ ደረጃዎቹ አከባቢ ሄደን እንቀመጥ እሱ ቦታ እንቀመጥ አለቻቸው ሊዲያ ወደሷ ዞራ ከዶርም እምንወጣው እኮ  አምፊ ሄደን ልንዘፈዘፍ አይደለም ወክ ልናደርግ እንጂ አለቻት እሺ በቃ በሜይን ካፌ አከባቢ ወክ እናድርግና ሲደክመን አምፊ እንሂድ አለቻታ። ሶስቱም ጨራርሰው ነበር በይ ነው ውጪ ባክሽ  ሰሙ ነይ እንጂ  ብላ ራኬብን ሳትሰማት ሶስቱም ተነስተው ወጡ።

...............................................
ስለሷ ሳይሆን ስላንተ ነው የጠየቅኩህ እሷ ሌላ ሰው ታፍቅር አታፍቅር ሌላ ጉዳይ ነው አንተ ግን ሰምሃልን ታፈቅራታለህ አይደል? ብላ ድጋሚ ስትጠይቀኝ ልቤ ብፍጥነት ይመታ ጀመር እኔንጃ አላውቅም አልኳት እንዴት ነው እማታውቀው ትወዳትለህ..ብላ አስጨነቀችኝ ሳላውቀው ለወራት አምቄ የያዝኩት ስሜት ገነፈለ... አው እወዳታለው አፈቅራታለውው!!... ደግነቷ የዋህነቷ ቀልቤን ይገዛዋል ሁሌም ስለሷ አስባለው ሁሌም እሷን ማግኘት ለኔ ትልቅ እድል እንደሆነ አስባለው እስከዛሬ እንደሷ አይነት ሴት በህይወቴ አይቼ አላውቅም አንቺን ሳላውቅሽ ነበር እማፈቅርሽ እሷን ግን በግዜ ሂደት ስብእናዋን ሳውቅ ነበር ያፈቀርኳት ላንቺ የነበረኝን ፍቅር አስወጥታ በምትኩ የሷን ንፀህ ፍቅር በልቤ አኖረች ሁሌም ምን አይነት ሴት እንደሆነች እያሰብኩ እደነቃለው እፁብ ግሩም የሆነች ሴት!! እንደሌሎቹ ብልጭልጭ አለም እማያታልላት ሴት! አስተዋይ ሴት። አንቺን ያፈቀርኩሽ መልክሽን አይቼ ነበር እሷን ግን ስብእናዋን አይቼ ነው የወደድኳት። ውበትና ደምግባት ቁንጅና ሁሉም ፈራሽ ናቸው መልክን አይቶ ያፈቀረ ያ.. ያፈቀረው መልክንል ግፕላ ሲያረጅ ሲጠፋ ፍቅሩም አብሮ ይጠፋል ስብእና ግን አያረጅም አይጠፋም ዘላለማዊ ፍቅርን ይሰጣል... ግን.. ግን ምን ያደርጋል ብዬ በረጅሙ ተነፈስኩ በእጄ የደረጃው ላይ መሞነጫጨር ጀመርኩ ግን ምን ያደርጋል ኡፍፍፍ... እሷ ሌላ እምታፈቅረው ሰው አላት አፍቅሮ ማጣትን በደምብ አውቃለው ያፈቀሩት ሰው ሌላ ሰው ሲያፈቅር ማየት ትልቅ ስብራት ነው ባንቺ የተጎዳሁትን ዳግም በሷ መጎዳት አልገልግም ፍቅሬን ቀብሬው ብኖር ይሻላል አልኳትና አገቴን አቀረቀርኩ ኤቤጊያ አይኗ ዳግም በእንባ ተሞላ ወደኔ ተጠግታ አቀፈችኝ ናዲ ለሷ እንዲ የጠለቀ ፍቅር እንደነበረህ አላውቅም ነበር አይዞህ እኔም እንዳንተ ያፈቀሩት ሰው ሌላ ሰው ሲያፈቅር ማየት ምንያህል ቅስም እንደሚሰብር አውቃለው ስሜትህ ይገባኛል አይዞህ ሰምሃል እኔ ባላዋቂነት እንደጎዳሁህ እምትጎዳህ አይነት ሴት አይደለችም አለችኝ አይኖቼ በእንባ ተሞሉ አቢጊ እኔ ግን ለፍቅር ያልታደልኩ ሰው ነኝ  ጥሩ ፍቅር መስጠት የሚችል ልብ አለኝ ግን.... ግን.... ማውራት አቃተኝ ይበልጥ ጥብቅ አድርጌ አቀፍኳት። ኤቤጊያን ጥብቅ አድርጌ እንዳቀፍኳት
ከጀርባዬ ሶስት ሴቶች ሲመጡ ታየኝ ጨለማ ስለነበር አይኔም በእንባ ተሞልቶ ስለነበር ማንነታቸው በውል ለመለየት አልቻልኩም ምንም ሃሳብ አልሰጠኃቸውም ቀልቤን ወደ አቢጊ መለስኩ በቃ አታልቅስ ናዲ በእናትህ አታልቅስ በቃ አለችኝ የራሷንም እንባ ለመቆጣጠር እየጣረች እንባዬን ጠራረግኩ እና እንነሳና እንሂድ በቃ ከዚ በላይ አንቆይ አልኳት እሺ አለችና ተነስታ እጄን ጎተት አድርጋኝ እኔም ተነሳው እዛው እንደቆምን ድጋሚ አቀፈችኝ እኔም አቀፍኳት በጆሮዬ አይዞህ ናዲ አምላክ ላንተ ያላት ከሆነ የትም አትሄድም  አንድ ላይ ትሆናላችው አለችኝ። ሶስቱ ሴቶች ከአቢጊ ጀርባ ብርሃን ያለበት ቦታ ላይ ደርሰው ቆመው እኛን እያዩን ነበር ልብ ብዬ አይቻቸው ማንነታቸውን ሳውቅ በድንጋጤ ደርቄ ቀረው ሰምሃል? አልኩ ኤቤጊያ ከጀርባዋ ስላሉ እንዳቀፈችኝ ሳታያቸው አው ሰምሃል አለችኝ።
ሰምሃል እየሮጠች ወደኃላ ተመለሰች ሊዲያና ራኬብም ተከተሏት ሰምሃል ብዬ ጮህኩና ኤቤጊያን አስለቅቂያት ወደሷ ሮጥኩ።

       ይቀጥላል

               
ሞሮ -2-ክፍል ብቻ ቀረው እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን..
🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹
ንሓቀኛ ፍቅሪ ሞት አየፍርሖንዩ:-

. ሓደ ጊዜ  ካብ ብንአሽትኦም ዝፋለጡ ዝነበሩ እሞ ብፍቅሪ ሓቢሮም ዝነብሩ ናይ ልቢ  ፍቁራት  ሰብ ሓዳር ነበሩ :: ሓደ ንጉሆ እቲ ሰብአይ ንጉሆ ንስራሕ ክከይድ እንከሎ በዓልቲ ቤቱ ከምዚ በለቶ :-

'' ፍቅረይ ሎሚ ንጉሆ ከም ቀደምካ አይኮንካን  ገጽካ ፋሕሽዩ ዝደከምካውን ትመስል ደሓን ዲኻ? ''

    :-ደሓንየ ግን ምሉእ ለይቲ ሕማቅ ሕልሚ ርእየ  ክብህርር ክትንስእ ጽቡቕ አይደቀስኩን :: እቲ ቀንዲ ዝርብሸኒ ዘሎ ድማ ቀደም ከምኡ ክሓልም ሓዲረ ንጽባሒቱ ዝፈትዋ ወላዲተይ ብሓደጋ  ሞይታ ተፈልያትኒ :: ሕጂ ድማ ብዘይካኪ ዘፍቅሮ ሰብ የብለይን እሞ  ብአኺ  ተሻቒለ:: ካብ ስራሕ አብኪረ ምሳኪ ክውዕል ደስ ምበለኒ በላ ::

     ኖ : እንተኮነ ሕልሚ ሕልሚ ኮይኑዩ  ዝተርፍ እንተዘይኮነ ድማ ሰብ ካብ መዓልቱ አይሓልፍንዩ :: አነ እንተሞትኩውን መዓልተይ ኮይኑ እዩ :: ንስካ ካብ ስራሕካ አይትትረፍ ኢላ አፋነውቶ :: ስራሕ ውዒሉ ንገዛ ክምለስ  አብ ሓንቲ እንዳ ሻሂ የላግስ እሞ : አብ ዜና ናይ መሬት ምንቅጥቃጥ አጋጢሙ ገዛውቲ ከምዝፈረሰ : እቲ ገዛውቲውን አብቲ ንሶም ዝቅመጡሉ ከምዝኮነ ይርኢ::

   ብጉያ ንገዝኡ እንተመጸ : ኩሉ መንገዲ ብፓሊስን አምቡላንስ መሊኡ ተዓጽዩ ጸንሖ :: ነቶም አብኡ ዝነበሩ ፓሊስ በጃኩም : ብዓልቲ ቤተይ አብኡ አላ እሞ ክደልያ አሕልፉኒ ኢሉ ለመኖም : : ይኩን እምበር እቲ ህንጻ ሓደገኛ እዩ ምሉእ ብምሉእ ዓንዩ ዝተረፈውን ሕጂ ክወድቅ ስለ ዝክእል : ንሂወትካ ድማ ሓደገኛ ስለዝኮነ አይነእትወካን ኢና ኢሎም ከልከልዎ ::

    ንሳ እንተ ሞይታ አነ ብድሕሪአ ምንባር ትርጉም አይህበንንዩ : እንተመትኩ ናተይ ሓላፍነት በጃኩም ኢሉ ለመኖም:: ንሳቶም ግን ንዓናውን የሕትተናዩ ኢሎም ከልከልዎ:: ቅሩብ ጸኒሑ አዘንጊዑ ዋላ ብጥይት ቅተሉኒ ሕጂ እንዳበለ ሃዲሙ አብቲ ፍርስራስ ህንጻ አተወ :: ደድሕሪኡ ዝሰዓበ አይነበረን ::

ድሕሪ ነዊሕ ምድላይ ንአፍቃሪቱ አብ ትሕቲ  ዓቢ ፍራስ መንደቅ ተጸቂጣ ርእሳ ጥራሕ ተቀልቂላ አብ ጻዕረሞት አርከባ:: ብዙሕ በከየ : ይኩን እምበር  አፍቃሪቱ ስቅ ንክብል ተማሕጸነቶ : ስቅ ምስ በለ ድማ ቅሩባት ደቓይቕ እየን ዘለዋኒሞ ጽን ኢልካ ስምዓኒ :: በለቶ

ሂወትካ አብ ሓደጋ የእቲካ ንዓይ ክትረድእ አብዚ ስለዝመጻኻ አብ ልዕለይ ሓቀኛ ፍቅሪ ከምዘለካ አረጋጊጸ :: ክትደልየኒ እንተዘዘይትመጽእ  ከምዘይተፍቅረኒ ተረዲኤ ክልተ ሞት ምሞትኩ :: ሓደ ናይ ስጋ ሓደ ድማ ናይ መንፈስ :: ስለዚ  ናይ ስጋ ድአምበር ናይ መንፈስ ሞት አይሞትኩን ብመንፈስ ምሳኻ ክነብርየ :: ሕጂ ድማ እዘን ዝላበወካ ሓደራ እንተዘይፈጺምካ ፍቕረይ  ጠሊምካኒ ማለትዩ :

ምስተቀበርኩ ከይሓዘንካ ቀልጢፍካ ተመርዒካ ቆልዑ ከም ትወልድ ሕጂ ቃል እተወለይ እንተአቢኻ ግን ንስኻ ኢኻ ብመንፈስ ቀቲልካኒ ኢላ : አምሒላቶ ዓረፈት ::
ንሱ ድማ ቃላ አኽቢሩ ተመርዕዩ ውሉዳት ወለደ ::

ተፈጸመ::


https://t.me/hopereding
https://t.me/hopereding
[ ደስ ይላል ]

እድገት መጨረሻ ጣሪያ  ባይኖረውም
እርካታ ባይገኝ ምኞት ባያበቃም
መውጣት ያስደስታል ማደግ ያስደስታል
አንዷንም ሳይዘሉ ከመውጫው መንሰላል
ህይወት በደረጃ ሲሆን ደስ ይላል።

     
https://t.me/hopereding

ይነበብ 🙏

ወንድሜ እኮ ነው! አ ይ ከ ብ ደ ኝ ም ::

ይህ በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ታሪክ በጃፖን አገር  የሆነ እውነተኛ  ክስተት ነው :: ልጁ በጃፓን በጦርነቱ ወቅት : የሞተውን ወንድሙን በጀርባው አዝሎ አብሮት ካለው ወታደር ጋር ረዥም የእግር ጉዞ ያደርግ ነበር::

ወታደሩ ክስተቱን አስተውሎ ልጁን በጉዞው እንዳይዝልበት በማሰብ በቃ  "ወንድምህ ሞቷል : ቅብረውና ጉዟችንን እንቀጥል" ብሎ ይጠይቀዋል ::  ልጁም መልሶ ወንድሜ እኮ ነው!  ለእኔ አይከብደኝም ሲል መለሰለት:: ወታደሩም ልጁ ለወንድሙ ያለውን እውነተኛ ፍቅር  ተመልክቶ እንባውን አፈሰሰ።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ይህ ምስል በጃፓን አገር  የአንድነት ምልክት ሆኖ ይኖራል::

ምንም እንኳን ታሪኩ በጃፓን አገር የሆነ ቢሆንም :የዚህ ፎቶ እውነተኛ ታሪክ  ለእኛም የወንድማማችነትና የእህታማማችነት እውነተኛ  ፍቅር  ምልክት ነው!

"ወንድምህ ለአንተ  አይከብድህም ምክንያቱም ወንድምህ ነውና... እህትህም  ለአንተ አትከብድህም እህትህ ናትና:: ከዚህ እውነት ውጭ ተፈጥሮአዊ አይደለም
ቢወድቅ አንሳው::
ቢደክም ደግፈው::
ቢቸግረው እርዳው::
ፍትህ ቢነፈግ ስለፍትህ ድምጽ ሁንለት::
እርሱን በመሸከም ድከም::
እርሱን ለመደገፍ  ጥረት አድርግ ።
ስህተት ቢያደርግ ይቅር በለው::
ቢስት መልሰው !
ሰዎች ጀርባቸውን ቢያዞሩበት አንተ ግን በጅርባህ ተሸከመው ::
ለአንተ አይከብድህም :ወንድምህ ነውና ::
https://t.me/hopereding
​​፨--•••••••• ሞሮ •••••••••--፨
            ፨--••ክፍል•••--፨
43

ወደ ሰምሃል እየሮጥኩ ስሄድ ሊዲያ ትንሽ ወደኃላ ቀረት ብላ አስቆመችኝ ናኦድ አንተ በጣም መጥፎ ሰው ነህ እንዲ አይነት ሰው አትመስለኝም ነበር አለችኝና ጥላኝ ሄደች እዛው ቆሜ ቀረው ኤቤጊያ ከኃላዬ መጥታ ቀስ ብላ ትከሻዬን ነካ አድርጋኝ አይዞህ ናዲ ሁሉም ነገር ግዜውን ጠብቆ ይስተካከላል አለችኝ። እዛው መሬት ላይ ቁጭ ብዬ አላቀስኩ እኔ ቆይ ለምድነው ሁሉም ነገር እሚጠምብኝ!!! ኤቤጊያ አፅናናችኝ በቃ ወደ ዶርም ሂድና እረፍት አድርግ አለችኝ ው ተባብለም ተለያየን። ዶርም አከባቢ ስደርስ የዶርሜ ልጆች ሳለቅስ እንደነበር ቢያውቁ.... ደበረኝና መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ተኛው እዛው ተጋድሜ እንዳለ ለራሴ አንድ ነገር ቃል ገባው ማንንም ሴት ከዚህ በኃላ ላልቀርብ! ሴትን በማሰብ ያቃጠልኩትን ግዜ ጠንክሬ ተምሬ ላካክስ ወስንኩ። በማግስቱ ከኤቤጊያ ጋር ስንገናኝ ዶርም ሰምሃልን ለማናገር ስትሄድ እንደተጣላቻትና ከዶርሟ እንዳሶጣቻት ነገረችኝ ሰምሃልና ኤቤጊያም ተጣሉ።  ሁለት ሳምንት ሙሉ ሰምሃልን ሳላገኛት አለፈ ትምህር... ተጀመረ... ሙሉ ሃሳቤን ወደ ትምህርቴ አድረጌ መማር ጀመርኩ ቢከብደኝም ራሴን አልጥልም አልሰላችም   በራሴ ተስፋ አልቆርጥም እንደቀድሞዬ ጠንካራ እና ሰቃይ ሆንኩ። ከሰምሃል ጋር ከተጣላን በወራችን ላይብረሪ ስገባ እሷ ደግሞ ስትወጣ በር ላይ ተገናኘን ደንገጥ ብላ ቆማ አየችኝ እኔን ትንሽ ቆሜ አየኃትና ፈጠን ብዬ ወደላይብረሪ ገባው ሰምሃልም ሄደች ግዜውም ሄደ.... የፋይናል ፈተና ደረሰ ላይብረሪ ውስጥ ሁሌ አያታለው አንነጋገርም ሌላው ቀርቶ ሰላምታም የለንም ድንገት እንኳን መንገድ ላይ ብንገጣጠም እንዳልተያየ ሆነን እንተላለፋለን።
2006  የአንደኛ ሴሚስተር ግዜ አልቆ ሁለተኛ ሴሚስተር ገባ ከሰምሃል ጋር ከተጣላን ከአምስት ወር በላይ ሆነን ሁልግዜ ስልኬን አነሳና ልደውልላት አስቤ እተወው ነበር አሁን ግን በሰምሃል ተስፋ ቆረጥኩ ስልኳን ከስልኬ ላይ አጠፋሁት። የአንደኛ ሴሚስተር ውጤት ሲለቀቅ ከክላሴ ከፍተኛውን ነጥብ አስቆጠርኩ 3.98 በሚቀጥለው 4 ነጥብ ለማምጣት ወሰንኩ ሰምሃልን ረሳኃት ...
ሁለተኛውም ሴሚስተር ማንንም ሳይጠብቅ ገሰገሰ እኔም ግቢ መኖር ስላስጠላኝ ከግቢያችን ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቤት ተከራይቼ መኖርና መማሬን ቀጠልኩ ብዙ ግዜ ሲደብረኝ ወይም ብቸኝነት ሲሰማኝ ኪያር ወይም ኤቤጊያ መጥተው ያዳብሩኛል።
ሁለተኛ ሴሚስተር ሲጀምር የማታ ሌላ ትምህር ጀምሬ ስለነበር በጣም እጨናነቃለው ግዜውም ሳይታወቀኝ በትምህርት ራሴን እንደወጠርኩ ገሰገሰ የሚድተርም ፈተና ከተፈተንን በኃላ አንድ ቀን ኤቤጊያና ኪያር ቤት እንድጠብቃቸውና አስቸኳይ እሚነግሩኝ ነገር እንዳለ ነገሩኝ ምን እንደሆነ ለናወቅ ጓጓው ከአንድ ሰአት በኃላ አልጋዬ ላይ ቁጭ ብዬ መፅሃፍ እያነበብኩ ኪያር እና አቢጊ ዘው ብለው ገቡ። አቢጊ እንኳን ደስ ያለ...ህህክ ብላ እዛው አልጋው ላይ እንደተቀመጥኩ መጥታ ተጠመጠመችብኝ እየሳቅኩ ምን ተገኘ አልኳቸው ሁለቱንም እያየኃቸው። ምን ሆነ መሰለህ ብሎ ኪያር ሲጀምር እኔ አይደል እንዴ ሰምቼ የነገርኩ እኔ እራሴው ነው እምነግረው ብላ ኤቤጊያ እየሳቀች አቋረጠችው የውልህ ናዲ ቅድም እነሰምሃል ስፔስ ቁጭ ብዬ እያጠናው እያለ ሰሙ ሊዱ እና ራኪ ሆነው ሊያጠኑ መጡ እኔ ከኃላ ያጥቁሩን ባለሁዲ ጃኬት ከነኮፍያው አድርጌው ስለነበር አላወቁኝም ነበር ብዙም አላዩኝም እናም እያጠኑ እያለ በመሃል ሰምሃል ማልቀስ ጀመረች እና እነ ራኪ ምነው አሏት ናዲ ናፈቀኝ ፍቅሩ አሁንም አልወጣልሽ አለኝ ይባስ ብሎ ተጣልተን ስንራራቅ ፍቅሩ ባሰብኝ ኣረሳው አልቻልኩም አለቻቸው። ኤቤጊያ ይህንን ስትነግረኝ ደነገጥኩ እስከዛሬ እሷ ስታፈቅረው የነበረው ሌላ ወንድ አልነበረም እኔኑ ነው!? እኔኮ ፍቅሬን ያልነገርኳት እሷ ሌላ እምታፈቅር ስለመሰለኝ ነው አልኳት አቢጊም እየሳቀች አው አይገርምም  አንተን ነበር እንጂ ሌላ ሰው አልነበረም አለችኝ።  ሁለታችሁም አሁን ትዋደዳላችው አይደል አሁን ወደ ቤተክርስቲያን እየወጡ ነው ሂድና አግኛት አለኝ ኪያር አይ አይሆንም አሁን ግዜው ረፍዷል ወደ ስምንት ወር ምናምን ሆነን ከተጣላን አሁን ላይ ምን ብለን ነው እምንታረቀው በዛ ላይ እኔ በፍቅር ተስፋ ቆርጫለው ዳግም ሴት ቀርቤ መጎዳት አልፈልግም በሰምሃል  ተስፋ ከቆረጥኩ ቆየው አልኩት ኪያር ተናዶ ምን? አለኝ እኔ ከዚ በላይ ልታገስህ አልችልም ናኦድ ቻው ብሎኝ ወጥቶ ሄደ አልጋዬ ላይ ተመልሼ ዘፍ አልኩ። ኤቤጊያ ባዘነ አንደበት ለምን አለችኝ ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ አቢጊ እኔ በዚ አለም ላይ ለፍቅር ያልተፈጠርኩ ሰው ነኝ ምንም ነገር አይሳካልኝ አልኳት አቢጊ እንደዛ አትበል ናዲ አንተ ጥሩ ሰው ነህ እኔ እንኳን ብዙ ነገር አድርጌህ ይቅር ብለኀኛል ይኀው አሁን ላይ ካንተና ከኪዩ ውጪ ምንም ጓደኛ የለኝም እባክህ በፍቅር ተስፋ አትቁረጥ እኔንም ፍቅርና ይቅርታን ያስተማርከኝ አንተ ነህ አንተ ተስፋ ስትቆርጥ አይቼ እኔም ተስፋ መቁረጥ አልገልግም ብላ አቀፈችኝ። አቀፍኳት!


               
🍁ክፍል-44🍁 👈👈  ላይ ያበቃል!!

ሞሮ -1-   ክፍል ብቻ ቀረው እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን እንደ ላይክ ብዛት እንፈጥናለን..
🌹🌹🌹🌹🌹🍃🍃🌹🌹🌹🌹🌹
https://t.me/hopereding
"ታክሲ ውስጥ"
የኋላ ወንበር ላይ ተቀምጬ አጠገቤ ያሉ ሰዎች ስለመቸገር እያወሩ ነበር። በተለይ አንደኛው "እቸገር ነበር" ብሎ ስለጀመረ ጆሮዬን ወደጨዋታቸው ጣልኩኝ። ያው ችግርን "ነበር" ብሎ እንደመግለጽ ደስ የሚል ነገር የለም። ሁሉም ሰው "ነበር" እያለ የሚያወራበት ዘመኑ ላይ ያድርሰው።

"የምሬን ነው የምልህ በልጄ ፊት እንዴት እንደምሳቀቅ ሃሳቡ የለህም"

"ማለት እንዴት?"

"ከስራ ስወጣ ትደውልና 'አባዬ እንትን ይዘህ ና፣ እንትን ግዛልኝ ትላለች"

"ሳትገዛ ገብተህ 'ረሳሁት' ትላት ነበር?"

"ኧረ እሱማ ቢሆን ባልከፋ!"

"እና ምን ታደርግ ነበር?"

"ከባለቤቴ ጋር በስልክ ውስጥ በቃላት እንጠቃቀስና ወደቤት ልገባ ያልኩት ሰውዬ ሰፈር ያለ ድዳ ማስጫ ላይ ተቀምጬ አመሻለሁ"

"እንዴ፣ ለምን?"

"ባለቤቴ ደውላ፣ ልጃችን መተኛቷን እስክትነግረኝ"

............🤔
እንዳልኩት ነው፣ ሁሉም ሰው "ነበር" እያለ ለሚያወራበት ዘመኑ ያመጣልን!
​​💓💓💓💓💓 💓 💓💓💓💓💓
💓💓💓💓💓ሞሮ 💓💓💓💓💓
💓💓💓💓    ፍፃሜ     💓💓💓💓
💓💓💓💓💓 💓  💓💓💓💓💓
https://t.me/hopereding

ፀሃፊው ነኝ .... ከጥቂት ወራት በፊት በአንደኛው እለተሰንበት በእድሜ የሚበልጠኝ አንድ ጓደኛዬ ሲአምሲ አከባቢ ከሚገኘው ቤቱ እንደመጣ ጋበዘኝ እናንተ "ናኦድ" በሚለው ለፅሁፍ እንዲያመች በተቀየረው ስሙ ታውቁታላችው። እናም ግብዣውን ተቀብዬ ቤቱ ሄድኩ  ወደቤቱ እየገባን እያለ አዲሱ ትዳር እንዴት ይዞሃል አልኩት በፈገግታ እሱም እየሳቀ አሪፍ ነው በልጄም በሚስቴም ደስተኛ ነኝ አለኝ አሪፍ ነው አልኩት። እንደለመደብኝ አዲስ ቦታ ስሄድ እንደማደርገው በአርክቴክት አይኔ ቤቱን ቃኘሁት ደስ ይላል ቀለል ያለ ኮተታኮተት ያልበዛበት የባለትዳር ቤት ይመስላል።  ልክ ሳሎን ውስጥ እንደተቀመጥን ከመኝታ ቤት አንዲት ሴት ወጣች  እንዴ... አቢጊ ብዬ አቀፍኳት ረጅም ግዜ ሆኖኝ ነበር ካገኘኃት ሞቅ ያለ ሰላምታ ሰጠኃት ናኦድን ሰላም ልትለው ስትል ከመኝታ ቤት የህፃን ልጅ ለቅሶ ሰማን ኤቤጊያ ውይ እፁዬ አለቀሰች ብላ እየሮጠች ወደመኝታቤት ተመለሰች ናኦድም ተከትሏት ሄደ። ትንሽ ከቆየ በኃላ ትንሿ በጣም እምታምረው ልጁን ይዟት ወጣ ብዙ ግዜ እኔ ህፃናት ብዙም አይመቹኝም ግን እፁብን እንዳየኃት ውድድድ አደረኳት እንዴት እንደምታምር ቀይ ድንቡሽቡሽ ልጅ ሉጫ ፀጉር ትልልቅ አይን ያላት ቆንጅዬ ልእልት ናት እፁብ። ከሶፋው ላይ ተነሳውና ወደናኦድ ተጠጋው ናዲ እምታምር ልጅ አለህ በጣም ነው ምታምረው አልኩና ግንባሯን በስሱ ሳምኳት አው ባክህ ቆንጅዬ ልእልት ናት ትንሽ እንቅልፏ ሲመጣ ለቅሶዋ መከራ ነው እንጂ አለኝ ህፃኗን እፁብ እሹሩሩ እያለ እንግዲ እኔ ስለህፃናት እማውቀው ነገር የለም አልኩት እየሳቀ ባክህ አንተም አግብተህ ስትወልድ ታየዋለህ አለኝ እኔም እየሳቅኩ ኡ.... ገና አልኩት። እፁብ ማልቀስ ስትጀምር እያባበላት ወደመኝታ ቤት ይዟት ሄደና ለአቢጊ ሰጥቷት ተመለሰ። እሺ እስራኤል እና ደህና ነህ ተጠፋፋን አይደል ያው ታውቀዋለህ ትዳር ስራ ምናምን ሲደራረብ አሁን ደግሞ እፁዬ መጥታለች ተጠፋፋን አለኝ አው ተጠፋፋን አልኩትና ከመቀመጫዬ ዳግም ተነሳውና ፊትለፊቴ ወዳለው ግርግዳ ሄድኩ የናዲ እና የሚስቱ የሰርግ ፎቶ በትልቁ በፍሬም ታሰቅሏል ባዶ ቦታዎቻቸው ላይ በወርቃማ እስክርቢቶ የወዳጅ ዘመዶቻቸው መልካም ምኞት አውቶግራፍ ተሞልቷል አይኔን አጥብቤ የተወሰኑትን ለማንበብ ሞከርኩ ደስ ይላሉ። ወደ ናኦድ እየዞርኩ ሳቅ ብዬ ለሰርጋቹ ግን ሳትጠሩኝ በጣም ታዝቢያቹሃለው አልኩት ናዲም እየሳቀ እኛማ ጠርተንህ ነበር አንተ አልመጣም አልክ እንጂ አለኝ። እና መቀሌ ነበርኳ ግቢ የእህቴን ሰርግ እራሱ አንድ ቀን ቆይቼ ነው የተመለስኩት ምናለ ለእረፍት እስከምንመለስ ብትጠብቁኝ እንኳን አንድ ብሬ ብጨርስ ነው አልኩት እየሳቅኩ ናዲም እየሳቀ አይ ረም ዘንድሮም ትኮምካለህ አ አለኝ እየሳቅኩ የቴሌቭዥኑ ስታንድ ጋር ሄጄ እዛ ላይ  በፍሬም የተቀመጡትን ፎቶዎች እያነሳው ማየት ጀመርኩ ካሉት ውስጥ  የምርቃታቸውን ፎቶ በእጄ አንስቼ አየሁት ናዲ መሃል ሆኖ ሰምሃል እና ኤቤጊያ በጎና በጎን ሆነው የተነሱት ፎቶ ነበር ወደናዲ እየዞርኩ ይሄ ፎቶዋቹ ደስ ይላል አልኩት። አውው... ባክህ ጥሩ ትውስታ ነው ግዜው ይሮጣል አይደል ከተመረቅን እንኳን አራት አመት ሆነን አይ ግዜዜዜ.... አለና ትንሽ በሃሳብ ሰመመን ሄደ። እኔ ፎቶዎቹን እያነሳው አይቼ ስጨርስ አስቀምጥና ሌላ አንስቼ ማየት ጀምራለው። ናዲ እንዳጎነበሰ ሲያስብ ከቆየ በኃላ ረምሃይ ብሎ ጠራኝ እእእ ናዲ አልኩት። እስኪ ና ቁጭ በል ስለ ግቢ አንድ ታሪክ ልንገርህ አንተ አስተዋይ እንደሆንክ አውቃለው ናሆሚም ነግራኛላች ግን ምናልባት እምትማርበት ነገር ይኖራል አለኝ እኔም ሄጄ አጠገቡ ተቀመጥኩ። ትንሽ አጎንብሶ ግንባሩን እያሸ  ካሰላሰለ በኃላ ታውቃለህ ግቢ እያለው ብዙ ትዝታ ነበረኝ ብዙዎቹ መጥፎና አሳዛኝ ቢሆኑም በዛው ልክ ደግሞ ክፉውን ግዜ የሚያስረሱ ጥሩ ትዝታዎችና ምርጥ ጓደኞች ነበሩኝ። ግቢ ፍሬሽማን እና ሁለተኛ አመት ላይ በጣም ጎበዝ ተማሪ ቀለሜ ነበርኩ ብዙ ደሳስ እሚሉ ጓደኞች ነበሩኝ። ደስ የሚል ጊዜ እናሳልፍ ነበር በአስተማሪዎቼም ተወዳጅ ተማሪ ነበርኩ ግን ህይወት ልታስተምርህ ስትፈልግ ከፊትህ ፈተና ማስቀመጥ ትጀምራለች ልክ 2004 ሶስተኛ አመት እንደገባን አንዲት ሴት በፍቅር አንባረከከችኝ ሲለኝ በዚያው  ቅፅበት ኤቤጊያ ከመኝታ ክፍሉ ቀስ ብላ እያተራመደች ወደኛ ጠጋ ብላ እፁ ተኝታለች  ቀስ ብላችው ተጫወቱ እኔ ሰሙ ሳትመጣ ምሳ ልሰራራ ብላን በእግሮቿ ጣት ብቻ ቀስ ብላ እየተራመደች ከሳሎን ሄደች። ናዲ ወደኔ እያየ በእጁ አቢጊ ወደወጣችበት በር እየጠቆመ ያቺ በፍቅር ያንበረከከችኝ  ሴት አቢጊ ነበረች አለኝ በአግራሞት ምን!? አልኩት አው አቢጊ በጣም ቆንጅዬ ቀበጥባጣ ልጅ ነበረች ያኔ አሁን እንደምታያየት የተረጋጋች አልነበረችም እና ስለሷ ሳስብ  ስለሷ ሳልም ትምህርቴን እረሳው ያኔ ፍቅሯ ልቤን አውሮት በጣም እፈራት ነበር  ገና ከርቀት ሳያት መንገዴን እቀይራለ ጓደኞቼ ሁኔታዬን እያዩ ይስቁብኝ ነበር ግዜያት እየተቆጠሩ ሲሄዱ እኔም ፍቅሯ በጣም እየባሰብኝ ሄደ....
ከውስጥ ኤቤጊያ ሽንኩርት ስትከትፍ የመክተፊያው ድምፅ ይሰማናል ተመስጬ እየሰማሁት ስለነበር ብዙም ልብ አላልኩትም ነበር ናዲ ብድግ አለና መኝታ ቤቱን ከፍቶ እፁ አለመነሳቷን ካረጋገጠ በኃላ ተመልሶ መጣና ፈገግ እያለ እና.... ራሴን መጣል ጀመርኩ እሷ እኔን አትመጥነኝም እል ነበር ፍቅሬን ድፍረት ኖሮኝ ብገልፅላት  እንኳን ምሏሿ ተቀራኒ እንዳይሆን እልና እፈራለው እተወዋለው ስለሌላ ነገር ማሰብ ተሳነኝ ስልቹና ቸልተኛ ለምንም ነገር ግድ የማይሰጠኝ ሰው ሆንኩ ጓደኜቼ ለኔ ያላቸው ከበሬታ ቀስበቀስ እየቀነሰ ሄደ ይባስ ብለው ይስቁብኝና ይሳለቁብኝ ጀመር ታውቃላሃ "ሞሮ" ይሉኝ እንደነበር አለኝ አው አውቃለው ሰሙም ናሆሚም ነግረውኛል አልኩት። አው ሞሮ ማለት ምንም የማይገባው ደደብ ማለት ነበር  የሚገርምህ ይህንን ስም ያወጡልኝ የገዛ ጓደኞቼ ናቸው የልብ ጓደኞቼ እምላቸው ነበሩ ሁሉም ከዱኝ ከአንድ በስተቀር ኪያር! ኪያር አሁንም ድረስ በጣም እምወደው እና እማከብረው የልብ ጓደኛዬና የስራ ባልደረባዬ ነው ከዛም በላይ ደግሞ የእህቴ ናሆሚ እጮኛም ነው።
ሶስተኛ አመት ሙሉ ስለኤቤጊያ ሳስብና ሳልም ኖርኩ ጓደኞቼ ሸሹኝ እኔም ከትምህርት ራቅኩ መማር አስጠላኝ ቀን ከቀን ተኝቼ እውላለው የጓደኞቼ ስድብና ኤቤጊያን መቼም እንደማላገኛት ሳስብ መጠጣት ጀመርኩ ሱስ ውስጥ ተዘፈቅኩ ዶርም ተኝቼ ካልሆነ  በጠርሙስ ተደብቂያለው ወይ በሲጋራ ጭስ ራሴን ደብቂያለው ደህና የነበርኵት ልጅ በግዜ ሂደት መውጣት እማልችለው አዘቅት ውስጥ ተዘፈቅኩ ብዙ ግዜ ራሴን ላስተካክል ጣርኩ ግን አልሆነልኝም እንዲው እንደሆንኩ አራተኛ አመት ገባን የግቢው ቁጥር አንድ ጀዝባ እና ሞሮ ሆንኩ ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም። አንድ ቀን ኤቤጊያን ከአንድ ራስታ ልጅ ጋር ስትሳሳም አየኃት በጣም ተናደድኩ በማግስቱ ልጁን ሺሻ ቤት አጊንቼ ተጣላን ጓደኞቹ ማታ ላይ ጠብቀው በጩቤ ወጉኝ ያኔ... ያኔ... ነበር ህይወቴን በሙሉ የምትቀይረዋን ሴት ያገኘሁት ሰምሃል! ኣለኝ ከሰሙ ጋር የተዋወቃቹት ያኔ ነው አልኩ በመገረም። አው ያኔ በሞትና በህይወት መካከል ሆኜ ያተረፈችኝ እሷ👇👇👇
​​መቀራረብ ጀመርን ጓደኝነታችን እየጠበቀ መጣ  ብዙ ምክሮችን ትመክረኝ ነበር እያለ ናዲ ታሪኩን በሰፊው አጫወተኝ እንዴት ሰሙ እሱን እየመከረች እንዳስተካከላችው ምናምን ሁሉንም ታሪክ አንድም ሳይቀር አጫወተኝ ለሰአታትት ሳይደክመው አወራኝ እኔም በጣም ተመስጬ ሳልሰለች እየሰማሁት ነበር። እንዴት የተበላሸ ማንነቱን አስተካክሎ ከቀድሞ የበላጠ ጠንካራ እንደሆነ እንዴት በሁለት ዲግሪ  ትምህርቱን በማእረግ እንደጨረሰና ከነሰሙና ኤቤጊያ ጋር አንድላይ እንደተመረቁ እንዴት ቤተክርስቲያ ቀለብት እንዳሰረላት እና እንደተጋቡ  በቅርቡ እፁዬን እንደወለዱ በሰፊው አጫወተኝ  በጣም ደስ አለኝ ታሪኩ ከጠበቅኩት በላይ አስተምሮኛል ናዲ እውነት ፍቅርን፣ የራስ ማንነት ጥንካሬን፣ ከምንም በላይ ደግሞ ይቅርታንና መልካምነት አስተማርከኝ አልኩት። ደስ ብሎኛል ስላስተማረክ ህይወት እንዲህ ናት እንግዲ  ብዙ ውጣ ውረድ ቢኖራትም ፈተናዋን ስታልፍ ሽልማቷ ብዙ ነው አለኝ ከውጪ በር ተንኳኳ.... ናዲ እጁ ላይ ያለውን ሰአት አየት አደረገና ኦ.... ምሳ ሰአት ደርሷል ሰሙ ናት መሰለኝ አለና ከመቀመጫው ተነስቶ በር ሊከፍት ሄደ። የሳሎኑ መጋረጃ ስስ ስለነበር ውጪ ያለውን ክዋኔ በደምብ ያሳያል ናኦል በሩን ሲከፍተው አንዲት ዝንጥ ያለች ሴት ወደውስጥ ገብታ ጥምጥም አለችበት ፍቅር.... ብላ ከንፈሩን ሳመችው ሰምሃል እንደሆነች አልተጠራጠርኩም ነበር ከውስጥ ሆኜ ሁኔታቸውን አይቼ ፈገግ አልኩና ወደኮርኒሱ አንጋጥጬ አምላክ አንድ ቀን እንዲህ ለኔም..... አልኩና ተመለስኩ ሰምሃልና ናኦድ እንደተቃቀፉ ወደ ቤት ገቡ ልክ ሳሎኑ ጋር ጫማዋን አውልቃ ስትገባ ከሰሙ ጋር አይን ለአይን ተገጣጠምን ረሙ ያገሬ... ልጅ አለችኝ ሰሙዬ ብዬ ተነሳውና ተቃቀፍን። ሰምሃል ማለት ናዝሬት ሃይስኩል እማቃት በእድሜና በክፍል ትንሽ እምትበልጠኝ ጓደኛዬ ናት ቤተሰቦቿ ወደ አዲስ አበባ ጠቅልለው እስኪገቡ ድረስ የቅርብ ጒደኛሞች ነበርን እዚ ከገቡ በኃላ ግን ለረጅም ግዜ ተራረቀን በናኦድ ምክንያት ዳግም ተገናኘን የአጋጣሚ ነገር ይገርማል። እንዴት ነሽ ባክሽ ሰሙ ወፍረሻል ይሄ ትዳር ተመችቶሻል አይደል አልኳት እየሳቀች ኣው ባክህ ምን እናድርግ ብለህ ነው አላችኝ። እፁ ከእንቅልፏ ተነሳች መሰለኝ ማልቀስ ጀመረች ሰሙ የእናት አንጀት ሆኖባት እኔን ልጄ እኔን ልጄ መጥቼልሻለው መጥቼልሻለው እያለች በፍጥነት ወደመኝታ ክፍል ገባች። ኤቤጊያም የእፁን ድምፅ ሰምታ ነው መሰል እየሮጠች መጥታ መኝታ ክፍል ገባች። ሰሙና አቢጊ ለሁለት እፁን እያባበሏት ይዘዋት ወደሳሎን መጡ ሰሙ አቢጊን እያየቻት እጡዬ ኔኔ ማል አክትሽ አቢጊ በደም ተንተባተበትሻ አለቻት ጥፍጥ ባለ በኮልታፋ የህፃን አንደበት። አቢጊ እኔ የክርስትና እናቷ እያለውማ ምን ትሆናለች በደምብ አድርጌ ነው የምይዛት አለች የእፁን እጅ እየሳመች። ሁኔታቸውን ሳይ አስቀናኝ ያንን ሁሉ ግዜ አልፈው አሁን ላይ ለዚ በቅተዋል ደስ ይላል። ናዲ ከሰሙ እጅ ላይ እፁን ተቀበላትና ፍቅር ታጣጥበሽ ነይና ምሳ እንብላ አላትና ወደ አቢጊ ዞሮ አክስት ተብዬዋ ምሳ ደርሷል አይደል አላት አው ላቀራርብ እንደውም ብላ ሄደች። ናዲ እኔን ፍፁም እረስቶኝ ከእፁ ጋር ጨዋታ ጀመረ.... አይ የልጅ ፍቅር! አልኩ በልቤ።
ምሳ  ቀራርቦ ከበላን በኃላ ሰሙ ቡና አፍልታ መጨዋወት ጀመርን በመሃል ናዲ ስልኩላይ ያለውን ሰአት አየና እንዴ ኪያር አይመጣም እንዴ ቆየ አለና ደወለለት ስልኩን ስፒከር ላይ አድርጎት ነበር። ምናባክ ነው ምትጨቀጭቀኝ በር ላይ ደርሻለው ክፈት አለው ናኦድ እየሳቀ ሄዶ ከፈተለት ተያይዘው ገቡ ኪያር መጥቶ በአንዴ ቤቱን ሞቅ አደረገው! ከሰአቱን ከነሰሙና ናዲ ጋር ስጫወት አመሸው አራቱም በእድሜም ሆነ በሌላም ነገር ከኔ ይበልጣሉ ታላላቆቼ ናቸው በዛች እለት ናዲ በነገረኝ ታሪክ እና እኔም ባየሁት እውነታ ብዙ ነገር ተማርኩ! ሁሉም ያላቸው ወዳጅነትና ፍቅር በጣም ያስቀናል እኔም እንደነሱ ብሆን ብዬ ተመኘው። ግዜው እየመሸ ደንገዝገዝ ብሎ ለአይን ያዝ ማድረግ ሲጀምር እኔ ለመሄድ ተነሳው ሰሙ ቅር እያላት ልትሄድ ነው አታድርም አለችኝ አይ መሄድ አለብኝ ይቅርታ ሰሙ ባይሆን ሌላ ግዜ አድራለው አልኳት እሺ በቃ ካልክ ምን ይደረጋል አለችኝና ተሰናበትኳት ኪያርና ኤቤጊያንም ተሰናበትኳቸው እነሱ ትንሽ ይቆዩ ነበር። ከናኦድ ጋር ትንሽ ሊሸኘኝ አብረን ወጣን ከቤት እንደወጣን ወደ ታክሲ መያዣው ቦታ እየሸኘኝ እያለ ናኦድ ዛሬ ቤትህ ስለጠራኀኝ በጣም ደስ ብሎኛል ብዙ ነገር ነው ያስተማራችሁኝ አልኩ። አው ቅድም እኮ ያው በደምብ ሳልመክርህ  ሁሉም ተሰባሰበ ደስ ስላለህ እኔም ደስ ብሎኛል አየህ አይደል ፈተናህን ታግለህ ስታሸንፍ ደስታህን ትሰጥሃለች ሁሌም ጠንካራ ማንነት እና ቅን ልቦና ይኑርህ ሁሉን ታሸንፋለህ የሚበድሉህን ይቅር በላቸው ባለማወቅ በድለውህ ሊሆን ይችላል ግን ሰው ይቀየራል ሁሌም አንድ ቦታ ላይ አታገኘውም መልካምነትና ይቅርታን በልብህ ሁሌም አኑራቸው ጥለው ኣይጥሉህም እህቴ ናሆሚ ስላንተ ብዙ ነገር ነግራኛላች ለሷ ያደረክላትን ነገር በሙሉ አውቃለው ለዛም አመሰግንሃለው አስተዋይ ልጅ ነህ ብዙ ምክር አላብዛብህ አለኝ እየሳቅኩ አረ ናዲ እንደውም ብትጨምርልኝ ደስ ይለኛል እንዲ ስለህይወር እሚያስተምረኝና እሚመክረኝ ሰው ነው እምፈልገው አልኩት እሺ ብዙ እምናውራቸው ነገሮች ይኖራሉ ወደፊት አለኝ። ቦሌ... ቦሌ ቦሌ ቦሌ አለ አንድ ወያላ የታክሲውን በር እየከፈተ። ከናዲ ጋር መሰነባባት ጀመርን ስለመከረኝና ስላስተማረኝ ነገር ሁሉ ከልብ ኣመስግኜው እና ሌላም ግዜ እንዲጨምርልኝ ነግሬው ቻው ተባብለን ታክሲው ውስጥ ገባው። ጋቢናው ውስጥ ከሹፌሩ ጋር ብቻዬን ስለነበርኩ በሃሳብ ማእበል እየተናጥኩ ናኦድ የነገረኝን ታሪክ አሰብኩና ተገረምኩ ይገርማል የሰው ልጅ እንደመፅሃፍ ገልጠው እስካላነበቡት ድረስ ማወቅ አይቻልም ምን ቀን ከናኦድ ጋር እንደተዋወቅን ለማስታወስ ሞከርኩ...። ናኦድ ግቢ እያለው ከአርክ ውጪ ሌላ  ትምህርትም እድማር  መንፈሳዊ ቅናት ያሳደረብኝ  ልጅ ነው እኔም እሱ በአንዴ ሁለት ዲግሪ ስይዝ አቀናኝ እኔም በሱ ፈለግ ተከተልኩ።  ይሄ ታሪክ መፃፍ አለበት እኔ እንደተማርኩበት ብዙ ሰው ይማርበታል  አልኩ በልቤ  እፅፈዋለው! ስልኬን ኣወጣው አዲስ ኖት ከፈትኩና ትንሽ ማሰላሰል ጀመርኩ ...መጣልኝ!!!!
ከላይ ርእሱን "ሞሮ" አልኩት ክፍል አንድ ......ታክሲው እየሄደ መፃፌን ቀጠልኩ። እነሆ አንድ ብልህ አስተዋይ ወዳጄ የነገረኝ የግል ታሪኩን እኔ እንደተማርኩበት እናንተም ትማሩበት ዘንድ ፃፍኩላችው ሞሮ ተፈፀመ ፍቅር ከበቀልና ጥላቻ በላይ ናት የፅድቅ ሁሉ ፍፃሜም ፍቅር ናት ፍቅር ለዘልአለም ትኑር በመፅሃፍ መልክ ታትሞ በሰፊው ተስተካክሎና ሌሎች ያልተፃፉ ታሪኮችም ተፅፈውበት ዳግም በመፅሃፉ እንገናኝ


   ┈•✿•˚•❀•˚•✿•˚•❀•˚•✿•˚•✿•┈ ✥┈┈┈┈┈••◉ተፈፀመ◉●••┈┈┈┈┈✥
እንግዲ ሞሮ እዚ ላይ ቢያልቅም በመፅሃፍነት ታትሞ ሲወጣ ብዙ ያልተፃፉ ታሪኮች ተጨምረውበት ይመለሳል።

https://t.me/hopereding
'''የፍቅሬ ጀማሬ ''''ምርጥ በጣም ደስ የሚል ...
ኣጥር ያለ  ኣሰተማሪ ዛሬ የጀምራል..
የጭን qus
ሙሉ በሙሉ እውነተኛታሪክ
የብዙዎቹን ጓዳ የሚፈትሸ፣ በቀላሉ የማይረሳ፣ አሳዛኝና ልብ ሰቃይ ታሪክ
በተክሉ ጥላሁን
ይህ የምታዩት የቤልጂየምና የኔዘርላንድ ድንበር ነው! ከመስመሮቹ ወደዚህ ቤልጂየም ከመስመሮቸቹ ወደዛ ደግሞ ኔዘርላንድ! ወታደር የለም! ታንክ የለም! መትረየስ የለም!
...
የሰው ልጅ እንዲህ ሰልጥኖ ድንበሩን በነጭ ቀለም ብቻ በሚያሰምርበት በዚህ ዘመን አንተ እገሌ ከክለሌ ይውጣልኝ እያልክ ከገዛ ወንድምህ ጋር በገጀራ ስትከታከት ትውላለህ! ዓለም ጥሎህ ሄዷል ወዳጄ!!

👉 https://t.me/hopereding
የፍቅሬ ጅማሬ

1 ክፍል
    ጊዜው ጠዋት ነው ገና በማለዳ ፀሐዩ ቀኑን ቀትር አሥመስሎታል ሀይ ስሜ ቤዛ ይባላል የ አዳማ ዩንቨርስቲ የ ሁለተኛ አመት የ ኢንጅነሪንግ ተማሪ ነኝ
        
         ቤዚ....ቤዚ ተነሽ በጌታ ዛሬኮ የሀይሚ ልደት ነው አንቺ ቤዛ የሚል ጥሪ ነበር ከእንቅልፌ ያነቃኝ ሀዊን ተዋወቋት እሷም እንደኔ የ ሁለተኛ አመት ተማሪ ናት  እኔ ሀይሚ እና ሀዊ ከጓደኛም በላይ እህታሞች ሆነናል እና ዛሬ ለ ሀይሚ ልደት ሥጦታ ልንገዛ ልንወጣ ነው
  "ስሚ ቤዚ ያለን ብር አራት መቶ ብቻ ነው እሽ በዚ ብር ምን እንደምንገዛ እናያለን"የብሩ ትንሽነት ያሣሠባት ሀዊ በንዴት ጦፋ ነበር ያለችው

ስጦታውን ለመግዛት ፍራክኮ በሚል ታክሲ ውሥጥ ገብተናል ሀዊ ጥሎባት ጋቢና መቀመጥ ትወዳለች እኔ ደሞ በተቃራኒው በዛ ብር ምን እንደምንገዛ እያሠብኩ ነበር"ይቅርታ ትንሽ ጠጋ ቲ"የሚል ድምፅ የሰማሁት ጠይም እና የደሥ ደሥ ያለው ልጅ ፈገግ ብሎ በድጋሚ "sorry"አይ ችግር የለውም ብዬ ተጠጋሁ ፊቱ ግን አዲሥ አልሆነብኝም "ግን አቅሻለሁ ልበል "አው እኔም የሆነ ቦታ ማቅህ ይመሥለኛል "ይሆናል ማቲዎስ እባላለሁ ግን ማቲ ብለሽ ብጠሪኝ ደስ ይለኛል"ቤዛዊት "እሺ ቤዛ የት እንደማውቅሽ አስታወሥኩ የጊቢ ተማሪ ነሽ አይደል "አው አንተሥ "እኔም የጊቢ ተማሪ ነኝ እዛ ነው ማለት ነው የምንተዋወቀው "አይኔን ከጥርሱ ላይ ማንሳት አቃተኝ ፈገግታው ልብ ይማርካል ሳላውቀው ፍራንኮ ደርሠናል ወርደን ከሀዊ ጋ መንገድ ሥንጀምር "ሀዊ "የሚል ድምፅ ሠማሁ "አቤት"ብላ ሀዊ ዞረች ማለት ቤዚ ስልክችን አልሠጠሽኝም ገና ተናግሮ ሣይጨርሥ ሀዊ"09........" የሷ ነው ደውልላት ብላው ተለያየን የሆነ የደሥታ ሥሜት እየተሠማኝ ነው "አንቺ የማን ሸበላ ነው"አንቺን አይደል እንዴ ማናግረው የት ነው ምታውቂው የሀዊ ተከታታይ ጥያቄዎች ነበሩ

ጊዜው መሽቷል ሁላችንም ዶርም ውስጥ ተሰባስበናል ሀይሚ ሥጦታዋን በመክፈት ላይ እያለች ነበር ድንገት ሥልኬ የጮኸው ሄሎ "ሄሎ ቤዛ ነሽ"........
            ይቀጥላl  
https://t.me/hopereding
🙏#ሠላም_ለዕናንተ_ይሁን__ቀዳሜ📖🙏

…"በሰፊው መስታውት ወደፊት እያየን ከመጓዝ ይልቅ በጠባቧ የኋላ መስታውት አብዝተን እያየን ከኋላ ታሪካችን ጋር ግብግብ ገጥመን ከፊት ለፊት ያለውን ተስፋችንን ለማጨለም እንዳክራለን። ትንሽ የሄድን ሲመስለን ተንገራግጨን እንቆማለን ወይ ወደ ኋላ እንመለሳለን። የሠራነውን እናፈርሳለን፣ የገነባነውን እንንዳለን፣ ቁመን ያጨበጨብንለትን ቁጭ ብለን ለማየት እንጠየፋለን። በጭፍን እንደግፋለን፣ በደምሳሳው እንቃወማለን፣ ሰውን ወይ መልኣክ አለበለዚያ ሠይጣን እናደርጋለን። ሚዛናችንን ስተን እንገዳገዳለን። ከአንድ ሙሉ ሰው ብልቶች ውስጥ ከዐይን ጆሮን አቅርበን፣ ከእግር እጅን አስበልጠን አድልዎ እንፈጽማለን። ከተወለድንበት መንደር ማዶ ካለው ጋራ ወዲያ ያለውን ሰፊ ሐገርና ወገን መዋጀት አቅቶን ድክ ድክ እንላለን።…"

#ምንጭ:- "ዝጎራ" በዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር) ገጽ-41

#ፍቅር_ያሸንፋል!
#እውቀት_ነፃ_ያወጣል!

📚#በማንበባችን_እጥፍ_ብናተርፍ_እንጂ_ከቶ_አንከስርበትም!📚

🙏#መልካም_ሠናይ_ምሽት 🌃!🙏


https://t.me/hopereding
✍️ ህርፋነይ…! ኣደይ! ማማይ
https://t.me/hopereding
ስምዕኒ 'ማ ሓንሳብ!ስለምንታይ 'የ ኣብ ዕረፍቲ ግዜይ ድያረይ ክሕዝ ከለኩ፡ኣብ ኣእምሮይ ቅድሚት ቅጅል 'ትብልኒ! ህዋሳተይ፣ሓሳበይ ቀልበይ ኩሎም ስለ-ንስኪ ገለ ክብል ዓው ኢሎም ዝጭድሩ! ንኩሉ ሰብ ኣብ ህይወተይ ከከም ዝግቦኦ ቦታ ይህብ'የ፡፡ምናልባት እቲ ዝዓበየ ቦታ ናትኪ ስለ ዝኮነ ደ ይኮን! ምናልባት እታ መተካእታ ኣልቦ ልዕሊ ኩሉ ፈቃር ኣደይ ስለ-ዝኮንኪ ዶ ይኮን! ምናልባት እታ ኣብ ሕማመይ ትቅንዘ ኣብ ድካመይ ፀግዒ ትኮነኒ ሓቦ ተስነቅኒ ስለ-ዝኮንኪ ዶ ይኮን!

እወ ካምኡ ስለ-ዝኮንኪ እዩ። ስለ-ንስኪ፣ብዛዕባኪ ነዊሕ ክሓስብ ሕልፊ ክፈትወኪ ካብ ልበይ ዕቁር ፍቅርኪ ፈንዲኡ ክወፅእ ክብል ከሎ ሕግብ-ግብ ይብል ጥበበኛ ስለ-ዘይኮንኩ ኣምዕዝ ኣቢለ ከይገልፀኪ! ቃላት ፍሕ ብጭር ይብሉኒ ውሽጠይ ብእጉዱ ይሓፅሩኒ።ግን ካዓ ፋሓት-ሓት ናበልኩ ክገልፀኪ ይፍትን…

ህርፋነይ ይሃርፈኪ እምበር" ከመይ ዘይ-ሃርፈኪ ሃረር ይብል ኣዕይንቲኪ እንዳራኣኩ ዝካፈልክለይ መስዋእቲ እንዳዘከርኩ፡ ገለ ኣብ ገፀይ ፃዊዕታት ክተንብቢ ኣብ ቅድሚ ዓይነይ ክትህልዊ 'ወ ይሃርፈኪ፡፡ እምበር ኪኒኡ 'ኳ ካበይ ክመፅኦም ናዓኪ ዝገልፁ ቃላት ካምዘይ ብለይ ነጊረኪ እንድየ። ባዕልኪ ክተንብብዮ ውሽጠይ ማዕረ ክንደይ ካም-ዝፈትወኪ'ሲ ይሃርፈኪ ክረክበኪ!!

ይሃርፈኪ ግን ካዓ ክረክበኪ፣ይደልየኪ'የ ህርፍ የብለኪ፡፡ኪኖ 'ቲ ብመስመር ንዕልሎ ዕላል ኣብ ሕቅፎኪ ተሸጉጠ ክነብዕ ከለኩ ክትእብድኒ፡ ክሕጎስ ከለኩ ድማ ክትሕጎሲ ምሳይ ይሃርፈኪ'የ።ህርፋነይ ህርፍ-ሩፎት ልበይ ኣደዋይ መዋዳድርቲ ኣልቦ።
'ታ እንኮ ውሽጥካ ኣንቢባ ስሚዒታትካ ትርደአልካ ኣዴካ ጥራይ'ያ።✍️
Happy mother day🥰🙏