Holy Spirit Revival
386 subscribers
79 photos
8 videos
17 files
37 links
The End Time Holy Spirit and Gospel Revival...
Download Telegram
ሰማርያ

በአንድ ወቅት ስለ ሌሊት ወፍ ያነበብኩት ታሪክ በጣም ይገርመኛል። ሌሊት ወፍ ለምንድነው ማታ ማታ ብቻ ምትበረው ሲባል ለዚህ መልስ እንዲሆን የተፈጠረ አንድ አፈታሪክ አለ። በአንድ ወቅት በሰማይ አዕዋፋት እና በምድር አዕዋፋት መሃል ጦርነት ተነስቶ ነበር። እናም ይህ ጦርነት በጣም ከባድ ጦርነት ስለነበር ረዥም ጊዜ አሸናፊው ሳይታወቅ፥ በተለያየ ጊዜ አንዱ ሲበረታ አንዱ ሲደክም ቆየ። በስተመጨረሻ ጦርነቱ አብቅቶ እርቅ ሲፈጠር የአባላት መቆጣጠር ተጀመረ። ልክ የአባላት መቆጣጠር ሲጀመር የሌሊት ወፍ ከማን ወገን እንደሆነች ለመለየት ክርክር ተነሳ። የሰማይ አዕዋፋትም ከእኛ ወገን ናት፥ የምድር አዕዋፋትም ከእኛ ወገን ናት እያሉ ክርክር ተጀመረ። በስተመጨረሻ ነገሪ ሲደረስበት ለካ የሌሊት ወፍ የበረታ ከመሰላት ቡድን ጋር ስትወግን እና የደከመ የመሰላትን ቡድን ስትክድ ነበር። ስለዚህ ሁለቱም ወገኖች ስላወገዟት በዚህ አሳፋሪ ድርጊቷ ከአዕዋፋት ተነጥላ ሌሊት መብረር ጀመረች ይባላል።

አንዳንድ ሰዎች እንደዚህ ናቸው። በአንድ ማሊያ ለሁለት ቡድን መጫወት ይፈልጋሉ። ከእግዚአብሔርም ከሰይጣንም ወገን መሆን ይፈልጋሉ። በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ ስላሉት ስለ ሰማርያዎች ሳስብ በጣም ይገርመኛል። እነዚህ ሰማርያዎች እስራኤልም፥ አህዛብም አይደሉም። ደግሞም እስራኤልም አህዛብም ናቸው። ምን ማለት ፈልጌ ነው ድብልቅ ህዝብ ናቸው። በእስራኤል እና በአህዛብ ድንበር መሃል የተቀመጡ ቅይጥ ህዝቦች ስለሆኑ ከሁለቱም ወገን ተገለው እና እንደ እርኩስ ተቆጥረው ለረዥም ዘመናት ይኖሩ ነበር።

እኔ ስለ ዘር ላወራ አይደለም የመጣሁት። ወይም ስለ ጋብቻ ለማውራይ አይደለም የመጣሁት። የመጣሁት የእግዚአብሔርን ነገር ከሰይጣን ነገር ጋር ለመቀየጥ ስለሚሞክሩ ሰዎች ለማውራት ነው። ከእግዚአብሔርም ከሰይጣንም ወገን ለመሆን ለማጥሩ ሰዎች ለማውራት ነው የመጣሁት። ፅድቅን ከአመፅ ጋር፥ ቅድስናን ከእርኩሰት ጋር፥ ልክ እንደ ክርስቶስ ሳምራ እግዚአብሔርን ከሰይጣን ጋር በግብራቸው ለማስታረቅ ስለሚሞክሩ ሰዎች ለማውራት ነው። ሀጢያትን በጥቅስ ብዛት ፅድቅ ለማድረግ ለሚሞክሩ፥ እርኩሰታቸውን በፀጋ ስም ለመሸፈን ለሚሞክሩ ሰዎች ለማውራት ነው የመጣውት። በእግዚአብሔር ፊት መንፈሳዊ ሰማርያዊ መሆን እጅግ አፀያፊ ነው። ወገን መለየት አለብን። ከማን ወገን ነህ? ከእግዚአብሔር ወይስ ከሰይጣን? በሚመጣው ሪቫይቫል እግዚአብሔር አስቀድሞ የሚሰራው የመጀመሪያው ነገር ቤቱን ማጥራት ነው። አዲስ ኪዳን የፍቅር ብቻ ሳይሆን የጅራፍ፥ የልምምጥ ብቻ ሳይሆን የሃይል እና የፍርድ ነገርም አለው። ከሀጢያት፥ ከሰይጣናዊ እስራት ውጡ! እንውጣ! መለየት አለብን። ውስጣችን ላለው መንፈስ ቅዱስ ልንጠነቀቅ ይገባል። እርሱን ማስመረር የለብንም። ንስሐ ሚገባ ጠፍቶ እንጂ ሀጢያተኛስ ብዙ ነው ያለው ማን ነበር🤔🤔🤔
ሰው ነን እንደክማለን። ነገር በድካማችን በእግዚአብሔር ፊት ወድቀን ከማልቀስ ይለቅ፥ ለድካማችን ቲዮሎጂ ሰርተን ፅድቅ ለማድረግ መሞከር እና ለስህተታችን ጥቅስ መፈለግ ግን ያጠፋናል። ሀጢያት ሀጢያት ነው። እግዚአብሔርም እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም። በሀጢያት ውስጥ ዘወትር እንድኖር አልተጠራንም። የእግዚአብሔርን ነገር ከሰይጣን ነገር አትደባልቁ፥ ቅድስናን ከአመፅ አትደባልቁ፤ ቅድስና ለእግዚአብሔር።

Join us
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
የእግዚአብሔር መንግስት


የእግዚአብሔር መንግስት ሶስቱ መገለጫዎች
“እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።”
  — 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7
“For God did not give us a spirit of timidity (of cowardice, of craven and cringing and fawning fear), but(He has given us a spirit)  of power and of love and of calm and well-balanced mind and discipline and self-control.”
  — 2Tim 1፥7 (AMP)

ሃይል

የእግዚአብሔር መንግስት የመጀመሪያው መገለጫ ሃይል ነው። የእግዚአብሔር መንግስት በቃል ሳይሆን መንፈስ ቅዱስን እና ሃይሉን በመግለጥ የሚሆን እንጂ በሚያባብል ቃል አይደለም። በስልጣን እንጂ በመገዛት አይገለጥም። በሃይል እንጂ በፍርሀት የእግዚአብሔር መንግስት አንሰበክም።

ፍቅር

ፍቅር እግዚአብሔር ራሱን የገለጠበት ማንነት እንደመሆኑ መንግስቱ የሚገለጥበት ሌላኛው መንገድ ፍቅር ነው። ያለ ፍቅር መንፈስ ቅዱስ አይሰራም። ያለ ፍቅር የእግዚአብሔር መንግስት በሃይል አይገለጥም። የእግዚአብሔር መንግስት ሃይል የሚገለጠው በፍቅር እንጂ በጥላቻ፥ በቅናት፥ በክርክር፥ በፀብ፥ በቂመኝነት፥ በአድመኝነት አይደለም።

ራስን መግዛት

ራስን መግዛት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። በእግዚአብሔር መንግስት አገልግሎት ውስጥ ራስን መግዛት ወሳኝ ነው። ራስን ሳይገዙ በስሜት በመነዳት አይሆንም።

ራስን  መግዛት በውስጡ አራት ነገሮችን ይይዛል

calm

well-balanced mind

discipline

self control

“ከመጥምቁም ከዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማያት ትገፋለች፥ ግፈኞችም ይናጠቋታል።”
  — ማቴዎስ 11፥12
“And from the days of John the Baptist until the present time, the kingdom of heaven has endured violent assault, and violent men seize it by force(as a precious prize...a share in the heavenly kingdom is sought with ardent zeal and intense exertion  .”
  — Mat 11፥12 (AMP)
የእግዚአብሔር መንግስት በመናጠቅ ምናገኛት እንጂ በመልፈስፈስ የምትመጣ አይደለችም። የቆረጡ፥ የፀኑ፥ እስከሞት በጨከኑ የእግዚአብሔር መንግስት ሃያላን ነው በምድር የምትገለጠው እንጂ ለዓለም፥ ለሰይጣን፥ ለሰዎች በሚልፈሰፈሱ ሰዎች አይደለም። ከሞት ጋር፥ ከሰይጣን ጋር ፊት ለፊት የሚጋፈጡ፥ ለሀጢያት ባርነት እጅ የማይሰጡ፥ ከሰዎች ይልቅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ባስቀደሙ ሰዎች ነው የምትገለጠው።

https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
ፍቅር እስከ መቃብር

አንድ ጊዜ በታሪክ የሚታወቅ ታላቅ ዋናተኛ በመርከብ ሽልማቶቹን ከብዙ ወርቆች ጋር አጋብሶ ይዞ እየሄደ እያለ መርከቢቱ የመስጠም አደጋ አጋጠማት። በአለም የታዋቀ እና ሽልማቶችን ያግበሰበሰ ዋናተኛ በመሆኑ በቀላሉ ባህሩን አቋርጦ ነፍሱን ማዳን ቢችልም ያ ሁሉ ሽልማት እና ወርቅ ግን ሰጥሞ መቅረቱ እጅግ ስላሳዘነው ወርቆቹን እና ሽልማቶቹን ቀበቶው እና አንገቱ ላይ አስሮ ዋና ጀመረ። በጣም ጎበዝ ዋናተኛ ስለነበር የተወሰነ ርቀት መሄድ ቢችልም ወርቁ እና ሽልማቶቹ ብዙ ስለነበሩ ወደ ታች ይጎትቱት ጀመር። ይህን ሲያይ ወርቆቹን እና ሽልማቶቹን ፈትቶ እንደመጣል ባለ በሌለ ሃይሉ ይታገል ጀመር። በስተመጨረሻ ነፍሱንም፥ ወርቁንም ሳያድን የውሃ እራት ሆኖ ቀረ። ፍቅር እስከ መቃብር ማለት ይህም አይደል! ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ የገንዘብ ፍቅሩ እስከሞት ተከትሎት ሄደ።
ወዳጆቼ የእግዚአብሔር ቃል በ1ቆሮ11፥32 ላይ ከአለም ጋር አብረን እንዳንኮነን ብሎ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል። ቶሎ የሚከበንን ሀጢያት ልናስወግድ እና ሩጫችንን ኢየሱስን በመመልከት ልንሮጥ ይገባል እንጂ ከአለም ጋር በፍቅር መዳራት ምንም ያህል ብልህ ዋናተኛ ብንሆን ከመስጠም አያድነንም። የጌታችን መምጫ እጅግ ቅርብ እንደመሆኑ ነገርን ሁሉ በልክ አድርገን ልንኖር ይገባል እንጂ ከሀጢያት፣ ከአለም እና ከሰይጣን ጋር በአጓጉል ጨዋታ ውስጥ ገብተን፥ አለምን ወደ ልባችን አስገብተን፥ ይህችን ጠፊ አለም አዝለን ራሳችንን ለማዳን በሞከርን ቁጥር የዓለም ጥፋቷ ላይቀር እኛንም አብራ ታስጠፋናለችና በጊዜ በልባችን ያዘልናትን አለም ከልባችን ገፍትረን ልናስወጣት ይገባል። ወደ ምድር በጣም በተሳብን ቁጥር ከሰማይ እየራቅን በመምጣት ከንጥቀት እንጎድላለንና እንደዚያ ሞኝ ዋናተኛ ለዓለም ስትሉ ከጌታ ጋር ያላችሁን ህይወት እንዳታጡ ተጠንቀቁ።
ማራናታ! አሜን ጌታ ሆይ ቶሎ ና!

ትምህርቱን ከወደዳችሁት ቤተሰብ ይሁኑ!

https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom
የእግዚአብሔር ክብር

ሪቫይቫል ማለት የሰማይ አገዛዝ በምድር ላይ ሲገለጥ ማለት ነው። የሰማይ አሰራር በምድር ላይ ሲገለጥ። የሰማይ ስርዓት በምድር ላይ ሲሰለጥን ማለት ነው። የሰማይ እሴቶች በአንድ ቦታ ሲገለጡ ማለት ነው። ሁሉን ነገር መንፈስ ቅዱስ ሲገዛው ማለት። ሰማይ በምድር ላይ ሲገለጥ እና ተፅዕኖ አድርጎ አንድን አካባቢ በቁጥጥር ስር ሲያደርግ ማለት ነው። መንግስተ ሰማይ በምድር ላይ ሲገለጥ ሪቫይቫል ይሆናል።

ማዕበሉ፣ ወጀቡ፣ ድካሞች፣ ጉድለቶች፣ በጤነኛው ጊዜ፣ በሙላት፣በጥጋብ እና ሁሉ ሰላም ሆኖ ልናውቀው ያልቻልነውን የእግዚአብሔር ማንነት የሚያሳዩን ነገሮች ናቸው። ውስጥህ ያለውን መንፈስ ቅዱስ ምትተዋወቀው በምቹ ሁኔታ ሳይሆን በምድረበዳ ላይ ስትመጣ ነው።

የጎደለን ዕውቀት አይአይደለም ። የአዘማመር ቴክኒክ አይደለም። ቲዎሎጂ አይደለም። የአመራር ስልትም አይደለም ። የጎደለን የእግዚአብሔር ክብር ነው። የጎደለን ኃይማኖታዊ ዶግማው እና ስርዓቱ አይደለም። የጎደለን ጥበብ አይደለም። የጎደለን ገንዘብ አይደለም። የጎደለን የክርስትና መልክ አይደለም። የጎደለን መንፈስ ቅዱስ ነው። የእሱ ክብር ነው የጎደለን። በመልክ ብቻ እየኖርን ማንነቱን የሸፈነብን እና ያስረሳን።

የዕውቀት ብዛት ህይወትን አያመጣም። የጥበብ ብዛት ህይወትን አያመጣም። ህይወትን የሚሰጠው መንፈስ ቅዱስ ነው።
ሰውን ሊለውጠው የሚችለው የእግዚአብሔር ክብር ብቻ ነው። ሰው የእግዚአብሔርን ክብር አይቶ እንደ ቀድሞው መሆን አይችልም። የሙሴ የዕድሜ ልክ ጥያቄ ክብርህን አሳየኝ እንደሆነ ሁሉ ዛሬም የሁላችን አንገብጋቢ ጥያቄ እንጀራ፣ ዝና፣ ክብር እና ሌሎች ምድራዊ ጉዳዮች ከመሆን ወጥቶ ክብርህን አሳየኝ ወደ ማለት ማደግ አለበት። ልዩነት የሚፈጥረው የእግዚአብሔር ክብር ብቻ ነውና።
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
Channel photo updated
God is not fair???🤔🤔🤔

የሰይጣን የሁልጊዜም ስብከቱ እግዚአብሔር መልካም እንዳይደለ ለእኛ መስበክ ነው። በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እይታ በመምታት በእግዚአብሔር ላይ ጥርጣሬ ፈጥሮ ነው ከታየልን ግብ የሚያስቀረን። ሄዋን ከመውደቋ በፊት ሰይጣን ያስጣላት ትልቁ ነገር እግዚአብሔር ያጎደለባቸው ነገር እንዳለ እና መልካምን እንዳልሆነ መስበክ ነው። በአሁን ዘመንም በፈላስፋዎች ፥ አዋቂ ነን በሚሉ ምሁራን በኩል፥ የተወሰነ ያወቁ በመሰላቸው አንዳንድ አጠገባችን ባሉ ሰዎች በኩል የሚሰብከን ተመሳሳይ ስብከት "God is not fair " የሚል ነው።

በእግዚአብሔር ማንነት ላይ ሰይጣን የሚፈጥረውን ወሬ አትስሙ። በሰዎችም በኩል ሆነ በገዛ ሃሳባቹ በኩል ሆኖ ቢያወራችሁ አትስሙት። እግዚአብሔርን የሚያማላችሁ እና ራሱን መልካም አድርጎ የሚስልላችሁ ለእናንተ አስቦ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነጥሎ ሊያጠፋችሁ ነው። የሰይጣንን ሽንገላ ተቃወሙ እንጂ አትቀበሉት። እግዚአብሔር መልካም ነው። በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን እግዚአብሔር መልካም ነው። እግዚአብሔር ሉዓላዊ አምላክ ነው። ይህ ማለት ግን ነገሮችን በክፋት ደስ እንዳለው ያደርጋል ማለት ሳይሆን የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ያደርጋል ለማለት ነው። የእግዚአብሔር ማስተዋል አይመረመርም። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚሰራውን ስራ ይመዝናል። ስህተት የማያውቀውን እግዚአብሔርን ተሳስተሃል ሊል የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም። እግዚአብሔር በስራው ፃድቅ ነው አይሳሳትም። የእግዚአብሔር መንገድ አሁን ባይገባንም ሲቆይ ግን እየተረዳነው እንመጣለን። እግዚአብሔርን ለሚወዱት፥ እንደ ሃሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን። ስለዚህ እግዚአብሔርን በማመን፥ እሱን እየወደደን ወደፊት እንቀጥል እንጂ እንደ እስራኤላውያን ዘወትር በእግዚአብሔር ላይ አናጉረምርም። እግዚአብሔር መልካም ነው። እግዚአብሔር ፃድቅ ነው። የሚሰራውን ስራ ይመዝናል። ተባርካችኋል!!!

https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
ብታይ ይሆንልሃል

ምን ታያለህ?
ገንዘብ፣ ሴት፣ ዝና፣ ክብር፣ ሀብት፣ ባለጠግነት ወይስ ምን? አይኖችህ ወዴት ያማትራሉ? የልብህ ጩኸት ምንድነው? የምታየው የእግዚአብሔርን ክብር ከሆነ፣ የምትመለከተው እግዚአብሔር ያወራህን ነገር ከሆነ በእርግጥ ክብሩ ያገኝሃል። ወደ ሰሜን ተመልከት፣ ወደ ምዕራብ ተመልከት፣ ወደ ምስራቅ ተመልከት፣ ወደ ደቡብ ተመልከት፣ የምታየውን ነገር ሁሉ ትወርሳለህ። የረገጥከውን ምድር ሁሉ ትወርሳለህ። ነፍሳት ሲድኑ ካየህ፣ የእግዚአብሔር ክብር ሲገለጥ ካየህ፣ የእግዚአብሔር መንግስት ተገልጦ ሲገዛ ካየህ፣ ቤተክርስቲያን በተራሮች አናት ላይ ስትቀመጥ ካየህ፣ ሪቫይቫል ሲነሳ ካየህ ይሆንልሃል። እሱን እይ።
በምድራዊ አርቲ ቡርቲ ተጠላልፈን ዘመናችን የተበላበት ዘመን ይበቃል። አሁን እይታችን ከምድራዊ ቁሳቁስ፣ ዝና፣ ክብር እና ባለጠግነት ወጥቶ ወደ ሰማይ ሊነሳ ይገባል። የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችን እንድትገለጥ፣ የእግዚአብሔር ክብር እንዲገለጥ ሰማይን መናፈቅ እና አይናችንን ወደ ሰማይ ማንሳት ይኖርብናል። ኢየሱስ በእርግጥ ይመጣል። ከመምጣቱ በፊት ግን ይህ የመንግስቱ ወንጌል ለምስክር እንዲሆን በዓለም ሁሉ ይሰበካል፥ አለም ከዚህ በፊት አይታ የማታውቀው ታላቅ ሪቫይቫል በምድር ሁሉ ላይ ይሆናል። ይህን ካየህ ይሆንልሃል!!!

ኢየሱስ ይመጣል

https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
GOD is not fair???🤔🤔🤔 part two
ስፒኖዛ እስራኤላዊ ፈላስፋ ሲሆን እግዚአብሔር ማለት እስራኤላውያን ራሳቸው የፈጠሩት ዘረኛ የሆነ አምላክ እንደሆነ አድርጎ በማቅረብ ብዙ ሊከራከር ሞክሯል። እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ብቻ የሚያዳላ ስለተቀረው አለም ግን ግድ የሌለው አምላክ እንደሆነ ተናግሯል።
እግዚአብሔር ሞቷል በሚል ፍልስፍናው የሚታወቀው ፍሬድሪክ ኒቼ የተባለው ፈላስፋ ደግሞ እግዚአብሔር እንደሌለ ካለም ደግሞ ፍትሐዊ(just or fair) የሆነ አምላክ እንዳልሆነ ተናግሯል። ኒሂሊዝም በሚለው ፍልስፍናውም ህይወት ትርጉም የሌላት ባዶ ነገር እንደሆነችም አስተምሯል። በተለይ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በዓለም ላይ የመጣውን ሰብዓዊ ቀውስ እና ምስቅልቅል ያዩ ሰዎች በእግዚአብሔር ማንነት ላይ ብዙ ጥያቄ ማንሳት እንዲጀምሩ አድርጓቸዋል። ድህረ ዘመናዊነትም መነሻው ይኸው ጦርነት ነው።
አንዳንዶች ደግሞ በምድር ላይ ያለውን ምስቅልቅል እና ግራ መጋባት አይተው እግዚአብሔር የለም ለማለት ፈርተው "እግዚአብሔርን አለ ግን አለማትን ከፈጠረ በኋላ ከፍጥረቱ ራሱን አግልሏል፥ አለምን ማስተዳደር አቁሟል"ብለው ይሰብካሉ።
ግን በመሰረታዊነት መረዳት ያለበት አንድ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር አለ፥ ደግሞም በፍጥረቱ ሁሉ ላይ የማስተዳደር መብት የራሱ የእግዚአብሔር ነው።
ግን አንድ መሳት የሌለበት ነገር ደግሞ አለ። በምድር ላይ ይሄ ሁሉ ቀውስ የተፈጠረው እግዚአብሔር በፍጥረቱ ተሳስቶ እና በመንገዱም ደግሞ ፍትሐዊ ሳይሆን ቀርቶ ሳይሆን እግዚአብሔር ፍጹም አድርጎ በፈጠረው አለም ላይ የሰውን ልጅ ሲሾመው የሰው ልጅ የሰራው ሀጢያት ነው ይህንን ሁሉ ጥፋት ያመጣው። በዓለም ላይ ላለው ቀውስ ሁሉ ምንጩ ሀጢያት ነው። የሀጢያት ምንጩ ደግሞ ሰይጣን ነው። ሀጢያትን በገዛ ፈቃዱ ያደረገው ደግሞ የሰው ልጅ ነው። ስለዚህ በዓለም ላይ ላለው ጥፋት የሰው ልጅ በዋነኝነት ተጠያቂ መሆኑን መዘንጋት የለብንም። እግዚአብሔር በዓዳም ምክንያት የተበለሻሸውን እና በእርግማን ስር የገባውን ፍጥረት ለማስተካከል እስካሁን እየሰራ ቢሆንም አንድ የተሃድሶ ቀን አምጥቶ በዓለም ላይ ያለውን እርግማን እስካልተነሳ ድረስ ዓለም ከነምስቅልቅሏ ትቀጥላለች። ስለዚህ በወደቀች አለም ላይ የምንኖር ሀጢያት እና አመፅ የሚባል ነገር በተፈጥሯችን ውስጥ እንዳለ መቀበል አለብን። ስለዚህ በዓለም ላይ ላለው ክፋት እና አመፅ ሁሉ ተጠያቂው ሰይጣን እና የሰው ልጆች ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም ሙሉ በሙሉ ራሱን ስላላገለለ አሁንም ድረስ ጣልቃ እየገባ የሰዎችን ህይወት ይመራል። ሙሉ በሙሉ ይህች አለም በእግዚአብሔር ቁጥጥር ውስጥ ምትገባበት ጊዜ ይመጣል። ያን ጊዜ መፅሐፍ ቅዱስ የሺህ አመት መንግስት ብሎ የሚጠራው የተሐድሶ ጊዜ ነው።


የሰው ልጅ ጥፋቱን ማመን አይፈልግም። በኤደን ገነት እንኳን አዳም፥ ሄዋን እና እግዚአብሔርን ጥፋተኛ ሲያደርግ፣ ሄዋን ደግሞ እባብን ጥፋተኛ አደረገች እንጂ አንዳቸውም የንስሐ ልብ አልነበራቸውም። የመጀመሪያው ነገር ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠያቂው የሰው ልጅ እንደሆነ ማወቅ፥ እኛም ደግሞ በህይወታችን በሚፈጠሩ ነገሮች እጃችን እንዳለበት ማወቅ አለብን። ግን እግዚአብሔር በገዛ ስህተታችን አውቀንም ሳናውቅም በገባንባቸው ነገሮች እንኳን ቢሆን ጣልቃ እየገባ ነገሮችን ለበጎ እንደሚለውጥ ማወቅ ነው ትልቁ ነገር።

https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
ቅርበት(Intimacy)
It's all about intimacy...ወደ ደረቱ በመጠጋት ኢየሱስን በጥልቀት ማወቅ። ኢየሱስን አውቆ የሚጨርስ ማንም የለም። ነገር ግን ኢየሱስ ራሱን የሚገልጥበት level  ይለያያል። በቅርበታችን ልክ ነው ኢየሱስን የምናውቀው። casual ክርስቲያን ኢየሱስን በስም እና በሰላምታ፥ close የሆኑ ደግሞ በግማሽ፥ best level ያሉ ደግሞ እጅግ ያውቁታል። exceptional በሆነ መልኩ ለኢየሱስ ቅርብ የሆኑ እና ኢየሱስን የሚያውቁ ደግሞ አሉ። ከብዙሃኑ ህዝብ ይልቅ 70ው ደቀመዛሙርት፥ ከ70ው 12ቱ፥ ከ12ቱ 3ቱ፥ ከ3ቱ ደግሞ ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር ያላቸው ቅርበት እየተጠጋ የሚሄድ ሲሆን በቅርበታችው ልክ ኢየሱስን የሚረዱበት እና ስለ ኢየሱስን የሚያውቁበት ልክ ይለያያል። ከሁሉም ይልቅ ዮሐንስ የኢየሱስን ልብ ቀርቦ ያውቅ ነበር። ለሌላው ሚስጥር የሆነ ለእሱ ግን እጅግ ይገለጥ ነበር። ኢየሱስ ይወደው ነበር የተባለውም እሱ ነው። ጉዳዩ የማጋፋት እና የመጋፋት ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ደረት የመቅረብ ጉዳይ ነው። it's all about intimacy...



https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
Channel photo updated
Forwarded from Deleted Account
ሼር አርጉ ወገኖች ተቃውሞአችሁን አሰሙ ዝም አትበሉ
***********
#ሰዶማዊነትን_እቃወማለሁ_challenge_ሁላችሁም_በፈጣሪያችሁ_ስም_ልለምናችሁ_ተቀላቀሉ

👉“የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ።”
— ዘፍጥረት 13፥13

👉“እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤”
— ዘፍጥረት 19፥24
ግብረ ሰዶማዊነትን እቃወማለው 🙅‍♀️🙅‍♀️🙅‍♀️

☝️መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት በዚህ መልክ ጋብቻን አስቀምጧል ።

👉 መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ኢ-ሞራላዊና ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ ኃጢአት ይኮንናል። ሌዋውያን
18፡22 ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ርኩሰት ይወስደዋል፣ እንደ ጸያፍኃጢአት። ሮሜ 1፡26-27 የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና ድርጊትንእንደ አሳፋሪ፣ ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ፣ ሴሰኝነት፣ እና ወራዳነትአድርጎ ይገልጸዋል። አንደኛ ቆሮንቶስ 6፡9 እንደሚያስቀምጠውግብረ-ሰዶማውያን ርኩሶች ናቸው እናም የእግዚአብሔርን
መንግሥት አይወርሱም።

🤔ሁለቱም የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና
ድርጊቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተኮንነዋል፣ የግብረ-ሰዶማውያን“ጋብቻ” የእግዚአብሔር ፍቃድ አለመሆኑ ግልጽ ነው፣ እናም
በእውነቱ ኃጢአት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በሚጠቅስበት ጊዜ ሁሉ፣ በወንድና በሴት መካከል ነው። በመጀመሪያ የተጠቀሰው ጋብቻ፣ ዘፍጥረት
2፡24፣ ሰው ወላጆቹን በመተው ከሚስቱ ጋር እንደሚተባበር ይገልጻል።
ጋብቻን በተመለከተ መመሪያ የሚሰጡ ምንባቦች፣ እንደ 1ቆሮንቶስ 7፡2-16 እና ኤፌሶን 5፡23-33 ያሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ
በግልጽ ያስቀመጠው ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል መካሄዱንነው።

😥 እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አባባል፣ ጋብቻ የሕይወት ዘመንኅብረት ነው፣ በወንድና በሴት መካከል፣ በቅድሚያ ቤተሰብን ለመገንባትና ለእዚያ ቤተሰብ አመቺ የሆነ አካባቢ ለመስጠት።
ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይህንን የጋብቻ መረዳት ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል አይደለም።

የመጽሐፍ ቅዱስ የጋብቻ አተያይ
ሁለንተናዊ የሆነ የጋብቻ አተያይ ሆኗል፣ በእያንዳንዱ የሰዎች ሥልጣኔ፣ በዓለም ታሪክ ላይ። ታሪክ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ
ተቃውሞ ይሞግታል። ዘመናዊው ሃይማኖታዊ ያልሆነው ሥነ-ልቦና እውቅና እንደሰጠው ወንድና ሴት በሥነ-ልቦናም ሆነ በስሜት
የተፈጠሩት እርስ በርሳቸው እንዲቀባበሉ ነው።

ቤተሰብን በተመለከተ፣ የሥነ-ልቦና ሰዎች የሚሉት በወንድና በሴት መካከል
የሚደረግ ኅብረት፣ ሁለቱ ተጋቢዎች መልካም የሆነውን ጾታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል፣ በተሻለ ስፍራ በመልካም
የተቀረጹ ልጆችን ለማሳደግ። ሥነ-ልቦና የግብረ-ሰዶማዊ ጋብቻን ተቃውሞ ይሞግታል። በተፈጥሮ/በአካል፣ ወንድና ሴት የተፈጠሩት
በግብረ-ሥጋ ግንኙነት አንድ ላይ “እንዲገጥሙ” መሆኑ ግልጽ ነው።

🤯በግብረሰዶማውያን-ሥጋ ግንኙነት “ተፈጥሯዊ” አሠራር ልጆችንለመውለድም ፣ በግልጽ የተቀመጠው ብቸኛ መንገድ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ነው ይሄንን ዓላማ የማያሳካ።

☝️ተፈጥሮ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ ተቃውሞ ይሞግታል። ስለዚህ እኛም ኢትዮጵያን ግብረ ሰዶምን እንቃወማለን ።
Forwarded from URIM🔥 (✞ቃለ-አብ✞)
"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"

ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...።

የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል።

ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር።

እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ  ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት ፍጹማን ክርስቲያኖች ስለሆኑ  አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም    አስከባሪዎች ነበሩ።

አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!...

በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን።

ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ

@oraclekb
Forwarded from #KALTUBE
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Read Bible

“አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።”
       መዝሙር 119፥33

#read #bible #kaltube #saka
💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE