Holy Spirit Revival
373 subscribers
81 photos
8 videos
17 files
37 links
The End Time Holy Spirit and Gospel Revival...
Download Telegram
Asfaw dnk zemari....
ብዙ ዘመን | Asfaw Melese
ተወዳጁ የደስታዬ እልልታ
. ብዙ ዘመን | አስፋዉ መለሰ
🕑-6:31Min◦💾-6.0MB
@yedestaye_elilta
@yedestaye_elilta
△Join Us△
ጊዜ
“እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።”
— መክብብ 9፥11
በህይወት ሳለን በደንብ ልንረዳው የሚገባን ነገር ቢኖር ጊዜ የሚለው ነገር ነው። እግዚአብሔር በጊዜ የማይያዝ እና በዘላለም ውስጥ የሚኖር አምላክ ቢሆንም ነገሮችን በምድር ላይ የሚሰራው ግን በጊዜ ውስጥ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉም ጊዜ አለው ይላል። በምድር ላይ ሁሉም ነገር ጊዜ አለው። በጊዜ ውስጥ ታናናሾች ታላላቅ ይሆናሉ። በጊዜ ውስጥ ታላላቆች ታናናሽ ይሆናሉ። በጊዜ ውስጥ የወደድነውን እንጠላለን። በጊዜ ውስጥ የጠላነውን እንወዳለን። በምድር ላይ ቋሚ የሆነ ነገር የለም። ሁሉም ነገር በጊዜ ውስጥ ይለዋወጣል። የማይለዋወጠው አንድ ነገር ግን ለውጥ የሚባለው ነገር ነው።
እግዚአብሔር ሁልጊዜም ለሰው ልጅ ጊዜ(Season) ይሰጣል። ጊዜን ሲሰጥ ደግሞ ከጊዜ ጋር አብሮ ዕድልን ይሰጣል። ጊዜ እና ዕድል ሁሌም የማይነጣጠሉ እና አንዱ ከአንዱ ማይቀዳደሙ ነገሮች ናቸው።
እግዚአብሔር ጊዜን እና ዕድልን ሲሰጠን መጠቀም ካልቻልን እና ካባከነው ያንን ዕድል ደግመን ብንፈልገውም ላናገኘው እንችላለን። ጊዜ የሚባለው ጉዳይ በጣም ወሳኝ እና አንገብጋቢ ነገር ነው።
በልፋት፣ በጥረት እና ብዙ በመሞከር የሚመጣ ነገር የለም። እርግጥ ጠንክሮ መስራት እና መዘጋጀት መልካም ቢሆንም ሁሉም የሚሆነው ግን በእግዚአብሔር ጊዜ እና አቆጣጠር መሰረት ነው።
አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም፤ አጋጣሚ የሆነው ለእኛ እንጂ ነገሩ ሰማይ አቅዶበት የሰራው ነው። ጊዜንም ሆነ ዕድልን የሚሰጠው እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች እድል በሚሉት ነገር የሚመጣ ነገር ዕድል የለም። እግዚአብሔር የሚሰራው በጊዜ ውስጥ ነው። ያንን ጊዜ ማወቅ እና መረዳት እንዴት ያለ ዕድለኝነት ነው።
ስለ ጊዜ ማወቅ ያለብን 3 ነገሮች
1.ጊዜ ለአንዱ ሲሰጠው ከአንዱ ይወሰድበታል። ከሳዖል ጊዜ ሲወሰድበት ለዳዊት ደግሞ ያ ጊዜ ተሰጥቶታል።
2.አንዳንዶች ጊዜን(Season) ይሰጣቸዋል። ልክ እንደ ኤልያስ እና ሙሴ ከእነሱ በፊት በዛ መንገድ የሄደ ባይኖርም አዲስ ጊዜ ይሰጣቸዋል።
3.አንዳንዶች ጊዜን(Season) ይቀበላሉ። ልክ እንደ ኤልሳእ ከኤልያስ፣ ኢያሱ ከሙሴ እንደተቀበሉት ከእነሱ በፊት ካሉት ሰዎች እንደ ዱላ ቅብብል ጊዜን ይቀበላሉ።
እንግዲህ ጊዜ እንደዚህ ከሆነ ጊዜን ተቀባይ አልያም ጊዜ ሚሰጠን እንጂ ሚወሰድብን እንዳንሆን የእግዚአብሔርን ጊዜ ነቅተን እየጠበቅን እንዘጋጅ። ሪቫይቫል በደጅ ስለሆነ በዛ ሪቫይቫል ተካፋይ ለመሆን አሁን በሚገባ እንዘጋጅ። ኢየሱስ ይመጣል!!!!
Join us on
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
Channel photo updated
The Spirit realm
Spirit realm is more real than the natural. The Spirit realm creates the natural realm so you need to see yourself in the Spirit how God says you are and then eventually it will manifest in the natural.
If you want a change in your normal life, you should have to change your spiritual realm. Don't struggle with the physical realm, just make focus on spritual realm.

When things get tiring you, start praying and go deep in the presence of God. Get intimated with the Holy Spirit. Then all things will be changed instantly.

To far away and resist satan is not the only solution. To far away from satan is good by itself. But to far away from satan is not good enough to solve your problem. You need also to come closer with God. When you come closer with God, God will come closer to you and if God will come closer to you, devil will flee from you by default.
In order to come closer to God, the only way is through Jesus christ. But after believing in christ, you have to
1.get your hands clean and
2.purify your hearts.
Jam 4 (AMP)
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁷ So be subject to God. Resist the devil , and he will flee from you.
⁸ Come close to God and He will come close to you. sinners, get your soiled hands clean; wavering individuals with divided interests, and purify your hearts .

Join us@
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
"ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ" የጊዜው_ድምፅ_ሰምተው_የማይጠግቡት_PRESENCE_#GospelMission
ዘላለማዊ - @Zelalemawi Telegram Channel
ለጌታ መምጣት መንቃት ይሁንልን!!!! ኢየሱስ በደመና ሆኖ ከመላዕክቱ እና ቅዱሳኑ ጋር በክብር የወጉት እያየለት ይመጣል!!!🙏🙏🙏
Track 10
Derge Kebede 7
ወሬው ሁሉ የሚያስፈራ.....original song
የፍፃሜው ሪቫይቫል
ሰዎች ሁሉ በዚህ ሰዓት ልናስተውለው የሚገባ እና ሁላችን እየተጠባበቅን እየመሰለን ግን የዘነጋነው አንድ ጉዳይ አለ። እሱም የፍፃሜው ሪቫይቫል ነው። ላለፉት 60 እና ከዛ በላይ ዓመታት ሲጠበቅ የነበረው ከዛሬ 100አመት በፊት የአዙዛ ጎዳናን ሪቫይቫል የመራው ጆሴፍ ሴይሞር ትንቢት የተናገረለት አሁንም ሆነ ላለፉት ብዙ አመታት ትንቢት ሲነገርለት የቆየው ከኢትዮጵያ የሚነሳው ሪቫይቫል ዛሬም ብዙ ትንቢት እየተተነበየለት እና እግዚአብሔር በብርቱ ልጆቹን በተለያዩ መንገዶች ለዚህ ሪቫይቫል እያዘጋጀ እንዳለ ለሁላችንም ግልፅ ነው።
ዳሩ ግን ለሚመጣው ሪቫይቫል እግዚአብሔር ብዙዎችን እያዘጋጀ እንዳለ እሙን ቢሆንም ግን በብዙዎች ዘንድ ተመሳሳይ የሆነ መዘናጋትን እያየሁ ነው። ሪቫይቫሉን ከአንድ ሀገር ልማት ጋር ብቻ አልያም ቤተክርስቲያን ውስጥ ከሚደረግ መነቃቃት እና ኃያል የሆነ የመንፈስ ቅዱስ እንቅስቃሴ አንፃር ብቻ የሚያዩ የበዙ ሰዎችን እያየሁ ነው። እርግጥ ነው የዌልስ ሪቫይቫል፣ የአዙዛ ጎዳና ሪቫይቫል፣ የመጀመሪያው ታላቁ መንቃት፣ ሁለተኛው ታላቁ መንቃት፣ ሶስተኛው ታላቁ መንቃት፣ የማንቺስተር ሪቫይቫል፣ የደቡብ ኮርያው ሪቫይቫል እና ሌሎችንም ሪቫይቫሎች ስናይ ሪቫይቫሉ የሀገራቱን ሁኔታ ፍፁም እንደቀየረው እና ዛሬ ላሉበት ብልፅግና እና የከፍታ ማማ መሰረቱ ያ የመንፈስ ቅዱስ ጉብኝት እንደሆነ ግልፅ ነው። ሪቫይቫል ሲነሳ ተሐድሶ መምጣቱ የማይቀር በመሆኑ በሪቫይቫል ውስጥ ሪቫይቫሉ የተነሳበት ማህበረሰብ ፍፁም የሚባልን ለውጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ በሞራል፣ በአስተሳሰብ፣ በእርስ በርስ ግንኙነት፣ በመንፈሳዊነት እና በሁሉም መስክ ለውጥ ያመጣል። ስለዚህም ከኢትዮጵያም የሚነሳው ሪቫይቫል ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት ውጥንቅጥ በሞራል፣ በኢኮኖሚ፣ በመንፈሳዊ ህይወት፣ በፖለቲካ፣ በአስተሳሰብ እና በሁሉም መስኮች ድንገቴ የሚባል ለውጥን ያመጣል ብለን ብናምን አንሳሳትም። ግን ይህ ለ60 አመታት የተጠበቀው ሪቫይቫል ልክ እንደከዚህ በፊት እንደተነሱት ሪቫይቫሎች የሆነን ማህበረሰብ ቀይሮ እና ቤተክርስቲያንን አነቃቅቶ ብቻ የሚሄድ ሳይሆን በይዘቱ አለም አቀፋዊ የሆነ፥ የአንድን ሀገር ቤተክርስቲያን ሳይሆን የአለም አቀፋዊቷን ቤተክርስቲያን መልክ የሚያድስ እና ለዓለም ሁሉ የሚሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ነው።
ይህ የሚመጣውን ሪቫይቫል ሰው ሁሉ በአንክሮ እና በትኩረት ሊከታተለው ደግሞም ከሪቫይቫሉ ጋር አብሮ ሊፈስ ይገባዋል። ይህን ሪቫይቫል እግዚአብሔር ለዓለም የሚልክበት 2 ዋና ምክንያቶች አሉት።
1.በቤተክርስቲያን ውስጥ ታላቅ የሆነን የመንፈስ ቅዱስ አውሎ ንፋስ አንፍሶ አሁን የተኛችውን ቤተክርስቲያን በማንቃት የቤተክርስቲያንን መልክ በማደስ የፊት መጨማደዷን አስወግዶ እድፈት እና እንከን የሌለባት ቅድስት የሆነችን ቤተክርስያን ለበጉ ሠርግ ለማዘጋጀት፤
2. የመንግስቱን ወንጌል በታላቅ ኃይል እና ክብር በዓለም ሁሉ እንዲሰበክ በማድረግ ዓለምን ለታላቁ መከራ ለማዘጋጀት ነው። ይህም ስንል ከእግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የሚሆን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደመሆኑ በዚህ ሪቫይቫል ተጠቅሞ ጌታን የተቀበለ ከታላቁ መከራ የሚድንበት ያላመነ ሁሉ ደግሞ ከሚመጣው ከበጉ ቁጣ ተካፋይ እንዲሆን የሚደረግበት ነው።
ይህ ሪቫይቫል እግዚአብሔር 2000 አመት ሙሉ አለምን በትዕግስት ሲጠባበቅ ኖሮ ወንጌልን አሻፈረኝ ያለውን አለም በ7አመቱ መከራ ሊቀጣ በወሰነበት (ከእሱ በፊትም ሆነ ከእሱ በኋላ አቻ በሌለው በታላቁ መከራ) መሃል የገባ የእፎይታ ጊዜ ነው።
ስለዚህ ይህ ሪቫይቫል ለተጠቀመበት በረከት ለናቀው መርገም ስለሚሆን ልክ እንደበፊቶቹ በቀልድ ምናልፈው ጉዳይ ስላልሆነ ነቅተን ልንጠባበቀው ይገባል። ከቤተክርስቲያን ፊት ንጥቀት ከትውልዱም ፊት ታላቁ መከራ አቆብቁቦ ባለበት በዚህ የዘመን ፍጻሜ ላይ ያለን አማኞች ሁሉ የሚመጣው ሪቫይቫል የፍጻሜ ሪቫይቫል በመሆኑ ለዚያ ሪቫይቫል በብርቱ እንድትዘጋጁ እና በመንፈስ ንቁ ሆናችቱ እንድትጠብቁት ከወዲሁ ላሳስብባችሁ እወዳለሁ። አንድ መዘናጋት ብዙ ዋጋ ያስከፍላልና!!!
ተባርካችዃል
ይቀጥላል.........

ከላይ ያለውን ፅሐፍ የወደዳችሁት እና የተጠቀማችሁበት ቻናሉን ለሌሎች ማጋራት እና መቀላቀልን አትርሱ።
Join us
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
ጊዜው
ኢየሱስ በምድር በነበረበት ጊዜ ፈሪሳውያንን የተቸበት እና የተቃወመበት ዋነኛው ምክንያት እነሱ የሰማይን መልክ እያዩ ዛሬ ይዘንባል አልያም ዛሬ ሞቃት ይሆናል እያሉ ሲናገሩ እንዳሉትም እየሆነላቸው ሳለ ነገር ግን ዘመኑን መመርመር እና ማወቅ ባለመቻላቸው ኢየሱስ ነቅፏቸዋል። እንደ ይሳኮር ልጆች ዘመኑን የሚረምሩ ብልሆች መሆን ሲገባቸው ቅዱስ ቃሉ በእጃቸው እና በአይምሯቸው እያለ፥ ለዘመናት መሲሑን እየተጠባበቁት ኖረው መሲሑ ሲመጣ ግን ለሞት አሳልፈው ሰጡት።
ዛሬም በዚህ ዘመን የምንገኝ ቅዱሳን ሁሉ ዘመኑን እና ጊዜው በእግዚአብሔር ቃል መነፅር እና በመንፈስ ቅዱስ አብርሆት ልንመረምር ደግሞም ልንነቃ ያስፈልገናል። ልክ እንደ ፈሪሳውያን ለዘመናት መሲሑን ጠብቀን መሲሑ ሲመጣ ለሞት አሳልፈን እንዳንሰጥ እንጠንቀቅ።
ጊዜውን በደንብ ላስተዋለ ይህ ጊዜ የዘመን ፍጻሜ ነው። አለም ልትጠቀለል እና የእግዚአብሔር ፍርድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊዘንብ አኮብኩቦ ያለበት ጊዜ ሲሆን ግን እግዚአብሔር ከቁጣው በፊት ምሕረቱን ያስቀድማልና ምድራችንን በቁጣው ከመጎብኘቱ በፊት ሪቫይቫልን ለምድራችን ይልካል። የሚመጣው መከራ እና ቁጣ አለም አቀፍ እንደመሆኑ የሚመጣውም ሪቫይቫል አለም አቀፍ የሚሆን ይሆናል።
ሪቫይቫል እየመጣ በደጅ ነው። ሁሉም ሰው ሊነቃ ያስፈልጋል። በቅዱስ ቃሉ እና በቅዱስ መንፈሱ ሁሉን እየመረመርን ራሳችንን ለሚመጣው ሪቫይቫል እናዘጋጅ። የእግዚአብሔር ጉብኝት ለዓለም ሁሉ እየመጣ ነውና በደንብ ነቅታችሁ ተዘጋጁ።
ኢየሱስ በእርግጥ ይመጣል!!!!!

Join us @
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
Forwarded from Deleted Account
📜 ምህረትና እውነት ተገናኙ!!

🚧እኛ ሁላችን ኃጢአተኞች የነበርን ፍርድ የሚጠብቀን፤ በራሳችን ጥረት ከሚመጣው ፍርድ ልናመልጥ እስከማንችል ድረስ በጨለማ ውስጥ ነበርን፡፡ሰው ሁሉ ኃጢአትን ሰርትዋል ስለዚህ ለሰራው ስራ የሚገባውን ፍርድ ከእግዚአብሔር ማግኘት አለበት፡፡ሰው ላጠፋው ጥፋት ከሰማይ ፍርድ መቀበል ነበረበት፡፡

🚧ሰይጣን እኛ ለሰራነው ኃጢአት ተሎ ተፈርዶብን እለት እለት በጽድቅ ወደሚፈርደው አምላክ የክስ ወረቀትን ይዞ በመሄድ ሲከስ ነበር፡፡ልክ አንድ ሰው ሰውን ሲገድል እንደሚከሰስና ወደፍርድ ቤት ቀርቦ ላጠፋው ጥፋት ከተከበረው ዳኛ ፍርድ እንደሚጠብቅ፣ እኛም እንዲው ለሰራነው ኃጢአት ፍርድ ተጠባባቂዎች ነበርን፡፡

🚧ነገር ግን እግዚአብሔር በጣም ስለሚያፈቅረን፣ እኛም እንድንጠፋ አልፈለገም፡፡በዚህ ደግሞ ሰይጣን ሁሌ የክስ ወረቀቱን ይዞ ፍርድ ለሰው ልጅ እያለ ክሱን ያቀርብ ነበር፡፡እግዚአብሔር በባህሪው እውነተኛ አምላክ ነው፡፡ፍርዱን ሟጓደል አይችልም፡፡አሁን ያለምንም ቅጣት እንዲው ይቅር ቢለን፥ የእርሱ ባህሪ አይፈቅድለትም፡፡

🚧ለምሳሌ ሰውን የገለው ሰው ፍርድ ቤት ቀርቦ ዳኛው፣ እእ በቃ ገድለህዋል ግን ነፃ ለቀንሃል ቢለው! ዳኛው ታማኝነቱ ያጣል፡፡ፍትህ ይጓደላል፡፡እንዴት ሰውየው አጥፍቶ ያለምንም ቅጣት ነፃ ይባላል? የሚል ጥያቄ ያስነሳል፡፡ስለዚህ ጉዳዩ መቋጫ አይኖረውም፡፡እግዚአብሔር አለመፍረድ አይችልም፡፡ደግሞ ምህረት ሊያደርግልን ፈለገ፡፡ስለወደደን ብቻ፡፡

🚧እውነት በአንድ ጎን ቁማ፣ ምህረት ደግሞ በሌላ ጎን ቁማለች፡፡እውነትና ምህረት አንድ ማድረግ በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡እውነት እንዲህ አለች፤ ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ ይሰጠው ስትል፤ ምህረት ደግሞ በተራዋ ይቅርታ ይደረግላቸው፡፡አሁን የእግዚአብሔር ትልቁ አጀንዳው ምህረትና እውነትን አንድ ማድረግ ነበር፡፡

🚧አንድ እንዲሆኑ የሁለቱም የምህረትና የእውነት ጉዳይ መፈጸም አለበት፡፡የምህረት ብቻ ቢፈጸም፣ እውነት ዘላለም ጥያቄዋን ማቅረብ አታቆምም፡፡ እውነት ሰው ለሰራው ኃጢአት ፍርድ እንዲሰጠው፣ ምህረት ደግሞ ይቅርታ እንዲደረግላቸው፡፡ታድያ ይሄን አንድ ማድረግ የሚችል ሰው ሆነ መልአክ አልነበረም፡፡በምድር ሲታይ ጻዲቅ ሰው አልተገኘም ነበር፡፡እኛ ላይ ከተፈረደ በቃ መጥፋታችን ነው፤ እኛ ለማዳን የግድ አምላክ ስጋ ሁኖ መምጣት ነበረበት፤ አለበለዝያ እውነትና ምህረት ሊዋደዱ፣ ሊገናኙ አይችሉም፡፡

🚧ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው ካልሆነ በቀር ሊያድነን የሚችል ማንም አልነበረም፡፡ኃጢአት የሌለበት ሰው፣ ሰው ብቻ ሳይሆን አምላክ የሆነ ነው እኛን ማዳን የሚችለው፡፡መልአክት ኃጢአት ባይኖርባቸውም እኛን ማዳን አይችሉም፡፡የእነርሱ ጽድቅ ለራሳቸው እንጂ ለእኛ አይደለም፡፡ምክንያቱም ስጋ ለባሽ ስላልሆኑ፡፡ስለዚህ እግዚአብሔር ልጁን ሰጠን፡፡ከስላሴ አንዱ የሆነው ወልድ የአብን ፍቃድ ለመፈጸም ወደምድር በስጋ ተለገለጠ፡፡

🚧እግዚአብሔር እውነትና ምህረትን ለማዋደድ አንድያ ልጁን ሰጠን፡፡ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስም የአባቱን ፍቃድ በፍቅር ለመፈጸም ታዛዥ ሆነ፡፡አብ ወልድን አንተ ሂድ ብሎት አስገድዶት እንዳይመስላችሁ! ፍቅር አስገድዶት ነው፡፡በአባትና በልጅ መካከል ያለው ስልጣን ሳይሆን ፍቅር ስለሆነ፡፡ኢየሱስ በስጋ ሲገለጥ ከኃጢአት በቀር እኛን ሁኖ ነው የተገለጠው፡፡

🚧በውስጡ ኃጢአት አልነበረበትም፡፡በእኛ ላይ ያለውን ኃጢአት ተሸክሞ ፍርዱን ሊቀበል ነፍሱን ስለእኔና ስለእናንተ አሳልፎ ለመስጠት ፈቀደ፡፡ኢየሱስም በመስቀል ላይ ለእኛ የሚገባውን ፍርድ ተቀበለ፡፡አባት ሆይ ስለምን ተውከኝ እስኪል ድረስ አብ ፊቱን አዞረበት፡፡ታድያ ከልጁ ፊቱን ያዞረው እኔና እናንተን ሊያይ ስለወደደ ነው፡፡የምህረት አይኑ ወደእኛ አደረገ፡፡ሰይጣን በዚህ ሰዕት እንዴት ግራ እንደተጋባ ልገልጽላችሁ አልችልም፡፡የክስ ወረቀቱን ነው ከእጁ ቅጣቱን ፍጽሞ የነጠቀው፡፡ላቀረብከው ክስ ይሄው ተፈጸመ፡፡እንደማለት ነው፡፡

🚧ሰይጣን ያኔ እንዲህ የሚል ይመስለኛል! ታድያ ኃጢአት የሰሩት ሰዎች እንዴት አልጠፉም! ኢየሱስ! ለሰሩት ኃጢአት እኔ ዋስ ሁኜ ፍርዱን ተቀብየ አዳንክዋቸው፡፡አሜን! ታውቃላችሁ ኢየሱስ ሲሞት ሰይጣን እንደዛን ቀን ተደስቶ አያውቅም ነበር፡፡ምክንያቱም ኢየሱስ ሙቶ ቢቀር መዳናችን ስለማይፈጸም፡፡ግን ኢየሱስ ሞትን ድል አደርጎ ተነሳልን፡፡ሰይጣን ምን ያድርግ የሆነው ሁሉ ከአቅሙ በላይ ሆነበት፡፡

🚧በመጨረሻም እውነትና ምህረት በመስቀል ላይ በክርስቶስ ሞት ተገናኙ፡፡እውነትም ያለቺው ተፈጸመላት፡፡ምህረትም እንዲሁ ተፈጸመላት፡፡ምህረት በእነርሱ ላይ አትፍረድ ይቅር በላቸው ብላ፣ በልጁ ላይ ፍርዱን አደረገው፡፡እውነትም፥ ቅጣት ያስፈልጋል ብላ ነበር፤ ቅጣቱም ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ተቀጣልን ሞተልን፡፡አይገርምም እነዚህን ያወደደ ጥበበኛ አምላክ፡፡ምን አይነት አምላክ ነው ያለን! ድንቅ አምላክ፡፡ምን እንለዋለን!ከምስጋና በቀር!!

🚧ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ ጽድቅና ሰላም ተስማሙ።መዝሙር 85፥10 በምሕረትና በእውነት ኃጢአት ትሰረያለች፥ እግዚአብሔርንም በመፍራት ሰው ከክፋት ይመለሳል።ምሳሌ 16፥6 ይሄም ቃል በልጁ ሞት ተፈጸመልንንን፡፡ክብር ለእርሱ ብቻ፡፡

✳️✳️ @Yezelalemhiywet✳️✳️
✳️✳️ @Yezelalemhiywet✳️✳️
✳️✳️ @Yezelalemhiywet✳️✳️

🖲Share
Channel photo updated
Forwarded from Joshua
5 ESSENTIAL DOCTRINES

1. The Absolute Supremacy of Holy Scripture

Show us anything, plainly written, in that Book, we will receive it, believe it, and submit to it. Show us anything contrary to that Book, and however sophisticated, plausible, beautiful and apparently desirable, we will not have it at any price.

2. THE DOCTRINE OF HUMAN SINFULNESS AND CORRUPTION
Man is radically diseased. I believe that ignorance of the extent of the Fall, and of the whole doctrine of original sin, is one grand reason why many can neither understand, appreciate, nor receive Evangelical Religion.

3. THE WORK AND OFFICE OF OUR LORD JESUS CHRIST
The eternal Son of God is our Representative and Substitute. We maintain that people ought to be continually warned not to make a Christ of the Church. We hold that nothing whatever is needed between the soul of man the sinner, and Christ the Savior, but simple child-like faith.

4. THE INWARD WORK OF THE HOLY SPIRIT
We maintain that the things which need most to be pressed on men’s attention are those mighty works of the Holy Spirit–inward repentance, faith, hope, hatred of sin, and love to God’s law. We say that to tell men to take comfort in their baptism or church membership when these all-important graces are unknown, is not merely a mistake, but positive cruelty.

5. THE VISIBLE WORK OF THE HOLY SPIRIT IN A PERSON
We maintain that to tell a man he is “born of God” or regenerated, while living in carelessness or sin, is a dangerous delusion. It is the position we assign to these five points which is one of the grand characteristics of Evangelical theology. We say boldly that they are first, foremost, chief and principal things in Christianity.

5 GOSPEL WARNINGS

1. Substitute anything for Christ, and the Gospel is totally spoiled!

2. Add anything to Christ, and the Gospel ceases to be a pure Gospel!

3. Put anything between a person and Christ, and that person will neglect Christ for that very thing!

4. Spoil the proportions of Christ’s Gospel, and you spoil its effectiveness!

5. Evangelical religion must be the Gospel, the whole Gospel and nothing but the Gospel!

J.C. Ryle
ወደ መስቀሉ ተመልከቱ

የክርስቶስ መስቀል የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ዕቅድ ነው። አለምን እግዚአብሔር የሚያድነው በክርስቶስ መስቀል ስራ ብቻ ነው።
በመስቀሉ
• ሰይጣን የተሸነፈው
• የጥል ግድግዳ የፈረሰበት (ኤፌ2፥13-16)
• የዕዳ ፅሕፈት የተደመሰሰበት(ቆላ2፥4)
• እግዚአብሔር ሲኦልንና ሞትን የሻረው
• የህግ እርግማን የተሻረበት(ገላ3፥13)
• የሀጢያት ስርየት የመጣው
• ቤዛነት የተገኘው
• አለም የሚድነው
• የእግዚአብሔር ፅድቅ የሆነው(2ቆሮ5፥21)
• የሰው ህይወት ሚቀየረው በክርስቶስ መስቀል ነው። የክርስቶስ መስቀል ማለትም የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ማለት ነው።
ጨለማንና ብርሃንን፥ ኩነኔንና ፅድቅን የሚከፍላቸው የክርስቶስ መስቀል ነው። ሰማይ እና ምድርን፥ ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀ የክርስቶስ መስቀል ነው። (ቆላ1፥19፥20) የክርስቶስ መስቀል ማለት ወንጌል ነው (ሮሜ1፥1-4፤1ቆሮ15፥1-4)። ወንጌል ማለት መልካም ወሬ፥ የምስራች ማለት ነው።
የብሉይ ኪዳን መልዕክታቸው የክርስቶስ መስቀል ነው። (ሉቃ24፥25-27፤44-47)
የሪቫይቫሎች መልዕክታቸው ከክርስቶስ መስቀል ሌላ ሊሆን አይችልም።
ለሰዎች ፅድቅንና ቅድስናን፣ ሠላምንና ዕረፍትን፣ ጤናንና ብልጥግናን የሚሰጣቸው እርሱ ነው።
ከፀሐይ መውጫ እስከ መጥለቂያ ድረስ የዘላለም ወንጌል። (ማር 16፥8)
ወደ መስቀሉ ምንመለከተው እና ወደ እሱ ምንገሰግሰው በእምነት ነው።
ከኢየሱስ ጋር መጠጋትና መጣበቅ ካልቻልን ሌላው ከእኛ ጋር ወይም እኛ ከሌላው ጋር እንጣበቃለን።
ብዙዎች እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ ሰዎችን እንዴት ገሃነም እሳት እንዲገቡ ይፈቅዳል? ይላሉ። ግን ይህ ጥያቄ ስለ እነዚህ 3 ነገሮች ሙሉ መረዳት ካለመኖር የተነሣ የሚመጣ ነው። ይህም
• የእግዚአብሔር ተፈጥሮ
• የሰው ተፈጥሮ
• የሀጢያት ተፈጥሮ
እርግጥ ነው እግዚአብሔር ደግ፣ ቸር፣ መሃሪ እና ፍቅር ነው። ነገር ግን እሱ ፍፁም ቅዱስ እና ፃድቅ አምላክ ነው።
ስለዚህ ቅዱስ ነው ማለት ሀጢያትን ሳይቀጣ ማለፍ አይችልም ማለት ነው። ሀጢያት በእግዚአብሔር ላይ ማመፅ ስለሆነ እሱ ሀጢያትንና አለመታዘዝን ሳይቀጣ አይቀርም(ኢሳ5፥25፤ሆሴ8፥5፤ዘካ10፥3)።
እሱ ሚያፈቅር አምላክ ብቻ ሳይሆን፥ ሀጢያትን የሚጠላም አምላክ ነው።
እሱ በምህረት የተሞላ አምላክ ነው፤ ቢሆንም ምህረቱ ገደብ አለው።
እግዚአብሔር ዘላለማዊ አምላከ ነው። በዚህም ምክንያት ሀጢያት ሁሉ ቅጣቱ ዘላለማዊ ነው። ይህን በገሃነም ካለ ሰው በስተቀር ማንም ሊረዳ አይችልም።
ሀጢያታችን በእግዚአብሔር ፊት ዘላለማዊ ስለሆነ የሱን ቅድስና ለማርካት ዘላለማዊ ፍርድ የግድ አስፈልጓል።
የሰው ተፈጥሮ፦ ሰው ከእግዚአብሔር ፍቅርን፣ ፅድቅን፣ ቅድስናን ሙሉ በሙሉ ሲካፈል ዕውቀትን ደግሞ በከፊል ተካፍሏል። አምላክነትን ደግሞ ፈፅሞ አልተካፈለም። የእግዚአብሔር ፍጥረት በመጀመሪያ ፍፁምና መልካም የነበረ ሲሆን ሀጢያት ግን ውድመትን ፈጠረ። ሀጢያት ተፈጥሮን ይቀይራል። ስለዚህ አዳም ሀጢያት ሲሰራ ተፈጥሮው ተቀይሮ ሀጢያተኛ፣ የቁጣ ልጅ እና እርኩስ ሆኗል። ያቺን የህይወት ዛፍ ፍሬ እንዳይበላ የተከለከለው ለዛ ነው። ምክንያቱም ሀጢያተኛ ሆኖ ለዘላለም እንዳይኖር። ስለዚህም ከገነት ተባረረ። የሚገርመው ደግሞ ተመልሶ እንዳይገባ የምትገለባበጥ ሰይፍ እና ኪሩብ ተደረገ። ካህኑ እራሱ የኃጢአት ስርየት አቅርቦ ቀና ሲል ኪሩቡን ያየዋል፥ ያ ኪሩብ አዳም ከገነት ሲባረር የተደረገው ኪሩብ በመሆኑ ሀጢያተኝነቱን ያስታውሰዋል።

By the way ዮሐንስ በጣም ቁጡና ጨካኝ ነበር። ምክንያቱም አንድ ጊዜ ኢየሱስን ጌታ ሆይ እንደ ኤልያስ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዲያጠፋቸው እንዘዝን ሲለው ኢየሱስ የተቀበልከውን መንፈስ አታውቅም። የሰው ልጅ ለማዳን እንጂ ለማጥፋት አልመጣምና ብሎታል። በሌላ ስፍራ ደግሞ በመንግስትህ ስትመጣ በቀኝና በግራ አስቀምጠን በማለት ራስ ወዳድነቱን ገልጧል። ነገር ግን ይህ ቁጡ፣ ጨካኝ እና ራስ ወዳድ የነበረው ሐዋርያ እንዴት የፍቅር ሐዋርያ ሊባል ቻለ ስንል ዮሐንስ ኢየሱስ ሲሰቀል ከመስቀሉ ስር ነበር። ኢየሱስ ለሰቀሉት፣ ለገረፉት፣ ለተፉበት ሰዎች የሰጠውን መልስ ይሰማ ስለነበር የዛኔ ከመስቀሉ ላይ ነው ፍቅር ማለት ምን ማለት እንደሆነ የተማረው። ለዛም ነው ከዛን በኋላ በመልክቶቹ ሁሉ ስለ ፍቅር ብቻ በማውራት የፍቅር ሐዋርያ የተባለው። ስለዚህ ሰው መስቀሉን ተመልክቶ፣ ክርስቶስ የከፈለውን ዋጋ አይቶ ጨካኝ፣ ቁጡና ራስ ወዳድ አይሆንም። በተቃራኒው ሩህሩህ፣ ቸር እና ሰው ወዳድ ይሆናል። መስቀሉን ተመልከቱ!
የሰውን ተፈጥሮ የመቀየር አቅም ያለው የክርስቶስ መስቀል እና መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው።


የተገዛህበት ዋጋ ሲገባህ ለክርስቶስ መኖር ትጀምራለህ። በዋጋ ስለገዛህ የእሱ እንጂ ያንተ አይደለህም።
የቤተክርስቲያን መሠረት አንድ ነው። እሱም ኢየሱስ ነው። ይህም ደግሞ የተመሠረተው በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በመስቀሉ ላይ ነው።
በግሪክም ሆነ በሮም የተከበረ ሰው በመስቀል ላይ ሊሰቀል አይችልም። ስለዚህ የተሰቀለው ሰው ወንጀለኛ እንጂ አዳኝ እና ንጉስ ነው ለማለት ለግሪኩም ሆነ ለሮም ዘበት ወይም ሞኝነት ነው። ለእኛ ግን ማያሳፍረን ህይወት ያገኝንበት እውነት ነው።(1ቆሮ1፥18)

Join us @
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/Thegospelofthekingdom
https://t.me/Thegospelofthekingdom