እማዬ___ራበኝ
* * * * ***
"እማ ራበኝኮ....
እንጀራ ወይ ቆሎ
እስኪ ስጭኝ ቶሎ!
እሽ ወይም ቂጣ
ከሞሰቡ ላምጣ?"
ልጅ እያለቀሰ
እናቱን ወቀሰ::
እናት በበኩልዋ
በአልቃሻው አመልዋ
እያለቃቀሰች
ለልጅዋ መለሰች::
አይ ልጄ...
"ከሞሰቡ ብትኖር ቁራሽ ታህል መና
እኔ ባንተ ርሃብ መች እጨክንና"
ልጅዋን በእጅዋ ዳብሳ
እንባዋን አብሳ
እህህህህህህህህ...
ልጅ እያለቀሰ መለመን ቀጥሎአል
ምግብ እንድትሰጠው
ተስፋ በእሱዋ ጥሎአል:
"እንጀራ ካልጋገርሽ ምጣድ ካልተጣደ
እሽ ቆይ ንገሪኝ ሊጡስ የለም እንዴ?
እማዬዋ ስሚኝ ራብ ውስጤን ቀጣው
በጭልፋ ልቅዳና ሊጡን ሄጄ ላምጣው?
እስከምትጋግሪ... ወይ እሱን ልጠጣው::"
እናት...
የእንባዋን ዘለላ
በእጆችዋ ከልላ
"አይ ልጄ...
ከሙሃቻችን ውስጥ ሊጥማ በኖረ
እንዲህ እስክትራብ መች ዝም እል ነበረ?
እህህህህህህህህህህህ... ህእ... ህእ... ህህህእ
እናት ውስጥዋን ከፍቶአት
የልጅዋ ጥያቄ ባዘን በትር መቶአት::
አቤት ስቃይ...
ልጅ ክፉ ጠያቂ እናት ሚስኪን መላሽ
ጥያቄው አሳዛኝ መፍትሄ አልባ ጭራሽ
የጥያቄውም መልስ መንታ ጎርፍ_ የእንባ
ከአንጀት ጠብ የማይል ከሆድ የማይገባ
ይብሱን የሚያስርብ አንጀት የሚያባባ::
እናት ምላሽ አጥታ
በሃዘን ተረታ::
ዝም ስትል ላፍታ_
ልጅዋ እያለቀሰ ያላንዲት እርፍታ
"እማዬ ሚበላ ተነሽና አቅምሽኝ
አሃ........ ለካ አሁን ነገርሽኝ
..........ምንም የለም አልሽኝ::"
ራሱው ጠያቂ እሱው ደግሞ መላሽ
መንሰፍሰፍ መንሰቅሰቅ
የእናት አንጀት ብላሽ::
ልጅ እያለቀሰ ጥያቄ አያልቅበት
ለእናት አስቸጋሪ መልሱ ክፉ አቀበት::
ለቅሶ እህህ ብቻ......
የለም ሌላ መፍቻ
እንባ እየመገበ_
የተራበን ህፃን: ከእናቱ 'ሚያስታርቅ
"እህህ"...ብቻ ነው_"እህል" ካገር ሲርቅ::
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
* * * * ***
"እማ ራበኝኮ....
እንጀራ ወይ ቆሎ
እስኪ ስጭኝ ቶሎ!
እሽ ወይም ቂጣ
ከሞሰቡ ላምጣ?"
ልጅ እያለቀሰ
እናቱን ወቀሰ::
እናት በበኩልዋ
በአልቃሻው አመልዋ
እያለቃቀሰች
ለልጅዋ መለሰች::
አይ ልጄ...
"ከሞሰቡ ብትኖር ቁራሽ ታህል መና
እኔ ባንተ ርሃብ መች እጨክንና"
ልጅዋን በእጅዋ ዳብሳ
እንባዋን አብሳ
እህህህህህህህህ...
ልጅ እያለቀሰ መለመን ቀጥሎአል
ምግብ እንድትሰጠው
ተስፋ በእሱዋ ጥሎአል:
"እንጀራ ካልጋገርሽ ምጣድ ካልተጣደ
እሽ ቆይ ንገሪኝ ሊጡስ የለም እንዴ?
እማዬዋ ስሚኝ ራብ ውስጤን ቀጣው
በጭልፋ ልቅዳና ሊጡን ሄጄ ላምጣው?
እስከምትጋግሪ... ወይ እሱን ልጠጣው::"
እናት...
የእንባዋን ዘለላ
በእጆችዋ ከልላ
"አይ ልጄ...
ከሙሃቻችን ውስጥ ሊጥማ በኖረ
እንዲህ እስክትራብ መች ዝም እል ነበረ?
እህህህህህህህህህህህ... ህእ... ህእ... ህህህእ
እናት ውስጥዋን ከፍቶአት
የልጅዋ ጥያቄ ባዘን በትር መቶአት::
አቤት ስቃይ...
ልጅ ክፉ ጠያቂ እናት ሚስኪን መላሽ
ጥያቄው አሳዛኝ መፍትሄ አልባ ጭራሽ
የጥያቄውም መልስ መንታ ጎርፍ_ የእንባ
ከአንጀት ጠብ የማይል ከሆድ የማይገባ
ይብሱን የሚያስርብ አንጀት የሚያባባ::
እናት ምላሽ አጥታ
በሃዘን ተረታ::
ዝም ስትል ላፍታ_
ልጅዋ እያለቀሰ ያላንዲት እርፍታ
"እማዬ ሚበላ ተነሽና አቅምሽኝ
አሃ........ ለካ አሁን ነገርሽኝ
..........ምንም የለም አልሽኝ::"
ራሱው ጠያቂ እሱው ደግሞ መላሽ
መንሰፍሰፍ መንሰቅሰቅ
የእናት አንጀት ብላሽ::
ልጅ እያለቀሰ ጥያቄ አያልቅበት
ለእናት አስቸጋሪ መልሱ ክፉ አቀበት::
ለቅሶ እህህ ብቻ......
የለም ሌላ መፍቻ
እንባ እየመገበ_
የተራበን ህፃን: ከእናቱ 'ሚያስታርቅ
"እህህ"...ብቻ ነው_"እህል" ካገር ሲርቅ::
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
(የ4 ስካራሞች ሀሳብ)
ከብሶት መርሻችን
ከሀሳብ መንሻችን
ማንነት ፍለጋ
እኛነት ፍለጋ
አረቄ ስንጠጣ ገፀ ባህሪ ሠፈር
የዛች ኮማሪ ቤት
መስሎ ታየኝ ጓዴ አንዲት ትልቅ ሀገር!
ያን ቀን ካስታወስከው
አራት ጓደኛሞች ከኛ በትይዩ ፊት ለፊት ተቀምጠው
በሰከረ መንፈስ ሂሳብ እያጋሩ ሀሳብ እያዋጡ
በክርክር መድረክ አረቄ ሲጠጡ
እንዲያ ሲኳሀኑ እንዲ ሲባባሉ
በሀሳብ መቃረን በመሀል ተጣሉ::
አንደኛው አወራ
"ስኖር ኢትዮጵያዊ"
"ስንሞት ኢትዮጵያ" ነን የሚለው መሪያችን
ሰው በሞተ ቁጥር
ከፋፍሎ ይቀብራል በዘር በሀይማኖት በዕምነት በቋንችን
በሞኙ ህዝባችን በእኔ በአንተ በእሱ
እየተወነብን ነው በቅቤ ምላሱ!
ይሄ ሌባ መንግስት. ...
ብሎ ...
ሀሳቡን ሳይጨርስ የልቡን ሳይቋጨው
ከአጠገቡ ያለው
ሞቅ ያለው ጀብራሬ ጓዱን አቋረጠው
አትሳሳት ጓዴ
አፉ ቅቤ ቢሆን ልቡ ነው ገራገር
ብዙ ነገር ሰርቷል ለዚች ምስኪን ሀገር!
በርግጥ
በሱ ስልጣን ዘመን
ስቃይ ሞት በርክቶ መንግስቱን ቢያሳጣው
አይግረማችሁ ጓዴ
ከሞት በሁላ ነው ትንሳኤ 'ሚመጣው!
ቢሆንም ቢሆንም....ብሎ ሊቀጥል ሲል
ሶስተኛው ስካራም
የሚያወራው ወሬ ያመልጠው ይመስል
እንዲ ስል ጀመረ...
ትውልድ እየሞተ ካህን እየታረደ
መንገድ እየተዘጋ
መስጊድ እየፈረሰ ደብር እየነደደ
ዴሞክራሲ ይገነባል!
ነፃነት ይታወጃል!
ፍትሀዊ አሰራር ይቀጥላል!
ሰላም ያንሰራራል!
ሞት ሟችን ያጣል!
ትንሳኤ ይመጣል እያሉ መወትወት
እስቲ በል ንገረኝ እውነታ ነው ዘበት?
ብታምንም ባታምንም
ፍትህ ለእውነት ቁማ ጃዋር ካልታሰረ
ስቃይ ይቀጥላል ሞት እየዳበረ..
አሁን በአብይ ዘመን እንደሚታወቀው
በቄሮ እጅ ነው ወገኔ የሚያልቀው
ድንገት አራተኛው እንዲ ሲል ጠቀየው
'ሚመራው ከጠፋ ሚገራው ከጠፋ
በል እስቲ ንገረኝ
ለምን ነው 'ሚታሰር "ጃዋር" ምን አጠፋ
ብሎ ቢጠይቀው
ሶስተኛው ስካራም እልህ ተናነቀው
መታሰር አለበት ሲል አፈጠጠበት
ያም እልህ ተጋባው
ለምን ይታሰራል ብሎ ደገመለት
ክርክሩ ጦፈ
እልህ ተጧጧፈ
ወደ ጠብ አለፈ
ከዛች ኮማሪ ቤት ዱላ ተደገሰ
ጠርሙስ ተሰበረ ብዙ ደም ፈሰሰ
ገላጋይ ጠፋና በለው ሚለው በዛ
ማስተዋል ጎደለ ስሜት ጥልን ገዛ
ጠቡን ማን ያብርደው ብትሩን ማን ይተው
ተመልከት ወዳጄ
ሰው በማያገባው ነው ገብቶ የሚሞተው!
አንተና እኔ ብቻ እንዳናገላግል
ከጠብ ጫሪ ይልቅ
ገላጋይ ነው ሚሞት የሚል ተረት ሰምተን
ግጥም ነው የፃፍነው መገላገል ትተን
ሳኖር መሞት ፈርተን!
ሳኖር መሞት ሰግተን!
ለዛም ነው ወዳጄ
አረቄ ስንጠጣ ገፀ ባህሪ ሰፈር
መስላ የታየችኝ
የዛች ኮማሪ ቤት አንዲት ትልቅ ሀገር::
✍Abu
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
ከብሶት መርሻችን
ከሀሳብ መንሻችን
ማንነት ፍለጋ
እኛነት ፍለጋ
አረቄ ስንጠጣ ገፀ ባህሪ ሠፈር
የዛች ኮማሪ ቤት
መስሎ ታየኝ ጓዴ አንዲት ትልቅ ሀገር!
ያን ቀን ካስታወስከው
አራት ጓደኛሞች ከኛ በትይዩ ፊት ለፊት ተቀምጠው
በሰከረ መንፈስ ሂሳብ እያጋሩ ሀሳብ እያዋጡ
በክርክር መድረክ አረቄ ሲጠጡ
እንዲያ ሲኳሀኑ እንዲ ሲባባሉ
በሀሳብ መቃረን በመሀል ተጣሉ::
አንደኛው አወራ
"ስኖር ኢትዮጵያዊ"
"ስንሞት ኢትዮጵያ" ነን የሚለው መሪያችን
ሰው በሞተ ቁጥር
ከፋፍሎ ይቀብራል በዘር በሀይማኖት በዕምነት በቋንችን
በሞኙ ህዝባችን በእኔ በአንተ በእሱ
እየተወነብን ነው በቅቤ ምላሱ!
ይሄ ሌባ መንግስት. ...
ብሎ ...
ሀሳቡን ሳይጨርስ የልቡን ሳይቋጨው
ከአጠገቡ ያለው
ሞቅ ያለው ጀብራሬ ጓዱን አቋረጠው
አትሳሳት ጓዴ
አፉ ቅቤ ቢሆን ልቡ ነው ገራገር
ብዙ ነገር ሰርቷል ለዚች ምስኪን ሀገር!
በርግጥ
በሱ ስልጣን ዘመን
ስቃይ ሞት በርክቶ መንግስቱን ቢያሳጣው
አይግረማችሁ ጓዴ
ከሞት በሁላ ነው ትንሳኤ 'ሚመጣው!
ቢሆንም ቢሆንም....ብሎ ሊቀጥል ሲል
ሶስተኛው ስካራም
የሚያወራው ወሬ ያመልጠው ይመስል
እንዲ ስል ጀመረ...
ትውልድ እየሞተ ካህን እየታረደ
መንገድ እየተዘጋ
መስጊድ እየፈረሰ ደብር እየነደደ
ዴሞክራሲ ይገነባል!
ነፃነት ይታወጃል!
ፍትሀዊ አሰራር ይቀጥላል!
ሰላም ያንሰራራል!
ሞት ሟችን ያጣል!
ትንሳኤ ይመጣል እያሉ መወትወት
እስቲ በል ንገረኝ እውነታ ነው ዘበት?
ብታምንም ባታምንም
ፍትህ ለእውነት ቁማ ጃዋር ካልታሰረ
ስቃይ ይቀጥላል ሞት እየዳበረ..
አሁን በአብይ ዘመን እንደሚታወቀው
በቄሮ እጅ ነው ወገኔ የሚያልቀው
ድንገት አራተኛው እንዲ ሲል ጠቀየው
'ሚመራው ከጠፋ ሚገራው ከጠፋ
በል እስቲ ንገረኝ
ለምን ነው 'ሚታሰር "ጃዋር" ምን አጠፋ
ብሎ ቢጠይቀው
ሶስተኛው ስካራም እልህ ተናነቀው
መታሰር አለበት ሲል አፈጠጠበት
ያም እልህ ተጋባው
ለምን ይታሰራል ብሎ ደገመለት
ክርክሩ ጦፈ
እልህ ተጧጧፈ
ወደ ጠብ አለፈ
ከዛች ኮማሪ ቤት ዱላ ተደገሰ
ጠርሙስ ተሰበረ ብዙ ደም ፈሰሰ
ገላጋይ ጠፋና በለው ሚለው በዛ
ማስተዋል ጎደለ ስሜት ጥልን ገዛ
ጠቡን ማን ያብርደው ብትሩን ማን ይተው
ተመልከት ወዳጄ
ሰው በማያገባው ነው ገብቶ የሚሞተው!
አንተና እኔ ብቻ እንዳናገላግል
ከጠብ ጫሪ ይልቅ
ገላጋይ ነው ሚሞት የሚል ተረት ሰምተን
ግጥም ነው የፃፍነው መገላገል ትተን
ሳኖር መሞት ፈርተን!
ሳኖር መሞት ሰግተን!
ለዛም ነው ወዳጄ
አረቄ ስንጠጣ ገፀ ባህሪ ሰፈር
መስላ የታየችኝ
የዛች ኮማሪ ቤት አንዲት ትልቅ ሀገር::
✍Abu
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
Forwarded from የደምቢ ልጆች ጥበብ ስራዎች via @like
ቀድሜሽ_ከሞትኩኝ
ውዴ ቃል ልግባልሽ እውነት የማረገው፤
የማስመሰል ሳይሆን ደርሶ የምታይው።
እኔን ካንቺ በፊት ወደሱ ከጠራኝ፤
ውዴ የኔ ፍቅር ቀድሜሽ ከሞትኩኝ።
ሄጄ በሰማዩ ባማረው ስፍራ ላይ፤
በወርቅ ፅፈዋለው ስምሽን ኮኮብ ላይ።
ስለምን መሰለሽ ውዴ ይሄን የማደረገው??፤
ላንቺ ያለኝን ፍቅር መላዕክት እንዲያዩት ነው።
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
ውዴ ቃል ልግባልሽ እውነት የማረገው፤
የማስመሰል ሳይሆን ደርሶ የምታይው።
እኔን ካንቺ በፊት ወደሱ ከጠራኝ፤
ውዴ የኔ ፍቅር ቀድሜሽ ከሞትኩኝ።
ሄጄ በሰማዩ ባማረው ስፍራ ላይ፤
በወርቅ ፅፈዋለው ስምሽን ኮኮብ ላይ።
ስለምን መሰለሽ ውዴ ይሄን የማደረገው??፤
ላንቺ ያለኝን ፍቅር መላዕክት እንዲያዩት ነው።
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
Forwarded from የደምቢ ልጆች ጥበብ ስራዎች via @like
ብሩህ ቀን ይመጣል
በርግጥ አሁንም ብሩህ ነው…
ግን ከዚህ የተሻለ ብሩህ ቀን ይመጣል
ብቻ ፈጣሪ የዛ ሰው ይበለን…
❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤
ስለጥበብ
join us
👇👇
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
በርግጥ አሁንም ብሩህ ነው…
ግን ከዚህ የተሻለ ብሩህ ቀን ይመጣል
ብቻ ፈጣሪ የዛ ሰው ይበለን…
❤❤❤❤❤
❤❤❤❤❤
ስለጥበብ
join us
👇👇
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
@siletibeb
(ህሊና ደሳለኝ)
........"ፍቅር ማለት ........
የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቃል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤
......ፍቅር ማለት ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንተ ነን ።
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
........"ፍቅር ማለት ........
የተራ ሆሄያት ባዶ ጥርቃሚ ፤
የሶስት ፊደል ጥምረት የቃል ልቅምቃሚ ፤
የደቂቃ ስሜት.......
ወይ ጊዜያዊ ጥቅም አይደለም ምስጢሩ ፤
......ፍቅር ማለት ...
በአንዲት ውብ ማሳ ውስጥ..
ከአረም ከቁጥቋጦ ፈፅሞ በራቀች ፤
ከአንድ ገበሬ እጅ..
በፅናት ተዘርታ በዕምነት የበቀለች ፤
........... .............ፍቅር ቡቃያ ነች ፤
የአለምን ሃይሎች አጣምሮ ያደላት ፤
የተንኮል ገሞራ .....
የሃሜት አውሎ ንፋስ ገፍትሮ ማይጥላት ፤
ገንዘብ ጎርፍ ሆኖ.....
ስሯን ቢያጥለቀልቅ ፈፅሞ ማይነቅላት ፤
ፍቅር ቡቃያ ናት..........."
"ገበሬው አምላክ ነው ማሳዋ ልባችን ፤
ዘሩ የፍቅር ቃል ቡቃያው ልጃችን ፤"
እንዲያውም እንዲያውም....
ከተራ ቃላት ጋር ምን አፈታተነን ፤
ፍቅር ማለት ውዴ!!!! በቃ እኔና አንተ ነን ።
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
ቆንጆ ነኝ
=============
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ
ውበትሽን አግንኜ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ
አንዳች ቀን እንኳን ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ
እርግጥ ነው ብዙዎች
ስለኔ ሳወራ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ
እርግጠኛ ሆኖ ሌላ እንዴት ያውቀኛል
እናም እኔ ማለት
ቁመቴ ከአክሱም በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ
መስማት ለተሳነው ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ
እንኳን መንገደኛን መንገድን ያቆማል
የከንፈሬ ወዙ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው
ሺ ሟች ላለማየት ኗሪ ፊት አልስቅም
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ በፍቅር ይወድቃል
የገላዬ ጠረን ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ
አለ ባሉት ስፍራ እኔ አለሁ ማለት ነው
ፀባየ ትሁት ነኝ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን
ብዙም ስለራሴ የማውቀው የለኝም
እንደውም እንደውም
አልጎርርም እንጂ
ያፈር ሰውነቴን በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ራሴን ነው ማየው
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ
---------------------------------
ከ(በላይ በቀለ ወያ)
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
=============
ስላንቺ ቁንጅና
ስላንቺ ቁመና
ከንፈር እና ዳሌ
ጥርስና ተረከዝ ፀጉር ገለመሌ
ለጡት ለወገብሽ ለፀባይሽ ጭምር
በግጥም በዝርው ባድናቆት ስዘምር
እስከዛሬ ድረስ
ውበትሽን አግንኜ ሰርክ መለፈፌ
እኔ ስለራሴ
አንዳች ቀን እንኳን ግጥም አለመፃፌ
ሲትጠዪኝ ቆጨኝ
ቢሆንም ቆንጆ ነኝ
እርግጥ ነው ብዙዎች
ስለኔ ሳወራ ድንገት ያኮርፉኛል
ያንተን ሌሎች ያውሩ ብለው ይነግሩኛል
እኔን ከኔ በላይ
እርግጠኛ ሆኖ ሌላ እንዴት ያውቀኛል
እናም እኔ ማለት
ቁመቴ ከአክሱም በእጥፍ ይረዝማል
ጣፋጭ አንደበቴ
መስማት ለተሳነው ለስልሶ ይሰማል
ውብ አረማመዴ
እንኳን መንገደኛን መንገድን ያቆማል
የከንፈሬ ወዙ ጥፍጥናው አያልቅም
ጥርሴ ሺ ገዳይ ነው
ሺ ሟች ላለማየት ኗሪ ፊት አልስቅም
ከአይኔ ብሌን ውስጥ ብርሐን ይፈልቃል
አይኔን ያየ ሁሉ
ልቡን አሳውሮ በፍቅር ይወድቃል
የገላዬ ጠረን ከሽቱ እጥፍ ነው
መልካም ጠረን ሁሉ
አለ ባሉት ስፍራ እኔ አለሁ ማለት ነው
ፀባየ ትሁት ነኝ ምጡቅ ነው እውቀቴ
ግርማ ሞገሳም ነው ተክለ ሰውነቴ
ያየኝ ይወደኛል
የወደየኝ ሁሉ መቼም አይጠላኝም
ከዚ በላይ እንኳን
ብዙም ስለራሴ የማውቀው የለኝም
እንደውም እንደውም
አልጎርርም እንጂ
ያፈር ሰውነቴን በቁንጅና አብየው
ቆንጆ ማየት ሲያምረኝ ራሴን ነው ማየው
ብቻ ግን ቆንጆ ነኝ
---------------------------------
ከ(በላይ በቀለ ወያ)
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
........... #አጀብ !
ስብራት አካሚ ፥ የፍቅር ወጌሻ
አናቱ ተቆርጦ ፥ ልክ እንደ እብድ ውሻ
ጥንብ
እርኩስ ተደርጎ
ካገር ጠፋ መሰል
ከጥላቻ ቅዠት ፥ መንቃት የተሳነን ፥ መፋቀር ቸልሰል
በአፅም የሾረ ፥ እንዝርት እያጦዝነ
ሀገር ይሉት ካባ ፥ በጋራ ለብሰነ
ከምቾቱ በላይ
እንደ ሱፍ ላይ ጭገር ፥ የኮሰኮሰነ
ምን ነካው ዘመኑ ?
እኛስ ምን ነካነ ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
ስብራት አካሚ ፥ የፍቅር ወጌሻ
አናቱ ተቆርጦ ፥ ልክ እንደ እብድ ውሻ
ጥንብ
እርኩስ ተደርጎ
ካገር ጠፋ መሰል
ከጥላቻ ቅዠት ፥ መንቃት የተሳነን ፥ መፋቀር ቸልሰል
በአፅም የሾረ ፥ እንዝርት እያጦዝነ
ሀገር ይሉት ካባ ፥ በጋራ ለብሰነ
ከምቾቱ በላይ
እንደ ሱፍ ላይ ጭገር ፥ የኮሰኮሰነ
ምን ነካው ዘመኑ ?
እኛስ ምን ነካነ ?
✍ #አብርሀም_ተክሉ
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
#በድጋሚ ከመሸ ብንከሰት ማን ከልካይ አለን ?....አንዳንዴ በማታ ሳታስበው ከሰማከው በጣም ረጅም ጊዜ የሆነክ #ሀሳብ ብቅ ይልልሃል ....... እንዴት ትዛለህ ዛሬ..?ለምን አትለኝም.? እሱን ለኔ ተወዉ ዝም ብለህ ወደ ሀሳቡ ግባ እልሃለው!
በድሮ ግዜ ነው አሉ(ድሮ የሚባለው ከመቼ በኋላ እንደሆነ ባይገባኝም)....እናም አንዲት
እናት የስለት ልጅ ነበራት... በስንት ልመና በስንት ስለት የወለደችው ...ከቤት ወጣ ሲል
ምን ይሆንብኝ ይሆን እያለች የምትሳሳለት ፤ ወደሆነ ነገር ልካው ባይዘገይም የዘገየ
እየመሰላት .... ምነው ቆየብኝ ምን አጋጥሞት ይሆን እያለች የምትጨነቅለት ልጅ ነበራት
።... እናም ይህ የስለት ልጇን በድንገት ይሞትባታል .... በጣም አዘነች እንዴት ፈጣሪ
ለሌላው ሰው አስር ፣ ዘጠኝ ልጅ ሰጥቶ ምንም ሳያደርግ እንዴት አንድ ልጄ የነጥቀኛል
በማለት በፈጣሪዋ ፍርድ መዛባት አዘነች። እናም ሀዘኑን ሲበረታባት ሙሾ ለማውረድ
አስገደዳት....
እንዲህም አለች
አስሩ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ዘጠኙ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ስምንቱ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
መቼስ የሴት ልጅ ነህ መች ፍርድ ታውቃለህ
አለችው በምሬት
.... አጠገቧ የነበሩት የንስሀ አባትዋም "ተይ ልጄ አይባልም እሱ ሰጠ እሱ ነሳ" ብለው
አወገዟት ....
እሷም እንዲህ በማለት መለሰችላቸው ...
እርሷ እማ ምን ሊሉ
ቄሴ እማ ምን ሊሉ
ለምን አያደሉ
እርሱ እየገደለ ተዝካሮ ሊበሉ.....
ናካይታ💚!
በድሮ ግዜ ነው አሉ(ድሮ የሚባለው ከመቼ በኋላ እንደሆነ ባይገባኝም)....እናም አንዲት
እናት የስለት ልጅ ነበራት... በስንት ልመና በስንት ስለት የወለደችው ...ከቤት ወጣ ሲል
ምን ይሆንብኝ ይሆን እያለች የምትሳሳለት ፤ ወደሆነ ነገር ልካው ባይዘገይም የዘገየ
እየመሰላት .... ምነው ቆየብኝ ምን አጋጥሞት ይሆን እያለች የምትጨነቅለት ልጅ ነበራት
።... እናም ይህ የስለት ልጇን በድንገት ይሞትባታል .... በጣም አዘነች እንዴት ፈጣሪ
ለሌላው ሰው አስር ፣ ዘጠኝ ልጅ ሰጥቶ ምንም ሳያደርግ እንዴት አንድ ልጄ የነጥቀኛል
በማለት በፈጣሪዋ ፍርድ መዛባት አዘነች። እናም ሀዘኑን ሲበረታባት ሙሾ ለማውረድ
አስገደዳት....
እንዲህም አለች
አስሩ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ዘጠኙ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
ስምንቱ ተቀምጠው አንዱን ትገድላለህ
መቼስ የሴት ልጅ ነህ መች ፍርድ ታውቃለህ
አለችው በምሬት
.... አጠገቧ የነበሩት የንስሀ አባትዋም "ተይ ልጄ አይባልም እሱ ሰጠ እሱ ነሳ" ብለው
አወገዟት ....
እሷም እንዲህ በማለት መለሰችላቸው ...
እርሷ እማ ምን ሊሉ
ቄሴ እማ ምን ሊሉ
ለምን አያደሉ
እርሱ እየገደለ ተዝካሮ ሊበሉ.....
ናካይታ💚!
የሻማ ሰሪው አቤቱታ(ልዑል ሀይሌ)
ፅልመት ናፋቂ ልብ
በሆዴ አድለኸኝ፤
አጨልም እላለሁ
ባልቸገረ ስራ ሻማ እያሰራኸኝ።
፲፱-፪-፳፻፲፩ ዓ.ም.
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
ፅልመት ናፋቂ ልብ
በሆዴ አድለኸኝ፤
አጨልም እላለሁ
ባልቸገረ ስራ ሻማ እያሰራኸኝ።
፲፱-፪-፳፻፲፩ ዓ.ም.
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
Forwarded from Quality Button [SCAM]
👉 በከፍተኛ ሚስጥር የተያዘ አጀንዳ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ ይሀውም ከዛሬ 70 አመት በፊት ነው "ኒው ሜክሲኮ" በተባለች የUSA ግዛት ውስጥ ልዩ ስሟ ሮዝቤል በተባለ ስፍራ ላይ አንድ ከሌላ አለም የመጣ መንኮራኩር ወድቆ እንደተገኘ ይነገራል፡፡ ይህ መንኮራኩር ጥብቅ በሆነ ሚስጥር ኔቫዳወደ ተባለች የአሜሪካ ግዛት ልዩ ስሙም ኤርያ 51 በተባለ ሚስጥራዊ ቦታ ላይ ጥልቅ ምርምር እና እና ጥናት ከተደረገለት በሇላ ሳይንቲስቶች የህዋ ቴክኖሎጂን ጥበብ እና እውቀት ሊቀስሙ እንደቻሉ በድብቅ ይወራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከዚህ መንኮራኩር ውስጥ የተገኙ እስካሁን ድረስ ለሰው ልጅ ይፋ ያልተደረጉ ጥብቅ ሚስጥራት እንዳገኙበት የሚገልፅ ሹክሹክታ አለ፡፡ ይህ ሚስጥር እንዳይወጣ ግን እጅግ በጣም ረቂቅ እና ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ አንዳንድ ህትመቶች ይገልፃሉ!
ሙሉውን ለማግኘት Open
ሙሉውን ለማግኘት Open
➖➖➖➖ ሐሰት ➖➖➖➖
መች ተገዛሁ ብዬ ስሸልል ሳቅራራ ነበረ የኖርኩት
እንደ ጉም ሲያጠለኝ ድክመቴንም አይቶት
ሐሰት መራሽ ዜና የኔን ምድር ወሮት
አድፍጦ አጠቃኝ አወየው ዝንጉነት
አካሌን ወሮታል ከምድሬም ተሻግሮ
አባልቶ አጫረሰኝ ጉድ ነዉ የዘንድሮ
መፍትሔ ያሻኛል ሳይነጋ ሳይሰልስ
ተላቅቄ እንድኖር ከዚህ እርኩስ መንፈስ
ጭንቀቴን ተረጂኝ ቅበሪኝ ቻይና
ዋን ቤልት ሮድን ለግዜው ግቺና
ከጆሮ ተገጥሞ መንፈስ የሚያቀና
ላኪልኝ ተጠበሽ ሐሰት የሚያጣራ ፊልትሮ ስሪና።
🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷
🔷 👉Written by: 🔶
🔶Ibrahim Mohammed (Ibro)🔷
🔷 ➖➖➖➖Join➖➖➖➖🔶
🔷 🔶
🔶 👉Sponsored by: 🔷
🔷 Nuredin Burka (Holly) 🔶
🔶 ➖➖➖➖Join➖➖➖➖ 🔷
🔷 @hollypoem 🔶
🔶 @hollypoem 🔷
🔷 @hollypoem 🔶
🔶 🔷
🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶
መች ተገዛሁ ብዬ ስሸልል ሳቅራራ ነበረ የኖርኩት
እንደ ጉም ሲያጠለኝ ድክመቴንም አይቶት
ሐሰት መራሽ ዜና የኔን ምድር ወሮት
አድፍጦ አጠቃኝ አወየው ዝንጉነት
አካሌን ወሮታል ከምድሬም ተሻግሮ
አባልቶ አጫረሰኝ ጉድ ነዉ የዘንድሮ
መፍትሔ ያሻኛል ሳይነጋ ሳይሰልስ
ተላቅቄ እንድኖር ከዚህ እርኩስ መንፈስ
ጭንቀቴን ተረጂኝ ቅበሪኝ ቻይና
ዋን ቤልት ሮድን ለግዜው ግቺና
ከጆሮ ተገጥሞ መንፈስ የሚያቀና
ላኪልኝ ተጠበሽ ሐሰት የሚያጣራ ፊልትሮ ስሪና።
🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷
🔷 👉Written by: 🔶
🔶Ibrahim Mohammed (Ibro)🔷
🔷 ➖➖➖➖Join➖➖➖➖🔶
🔷 🔶
🔶 👉Sponsored by: 🔷
🔷 Nuredin Burka (Holly) 🔶
🔶 ➖➖➖➖Join➖➖➖➖ 🔷
🔷 @hollypoem 🔶
🔶 @hollypoem 🔷
🔷 @hollypoem 🔶
🔶 🔷
🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶🔷🔶
❤እወድሻለሁ😘
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ድርሰቴ
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ
እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ/ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ
ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የፍቅር አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ
የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ባትረጂኝ ብታስከፊኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እኔነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ
የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!
የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባትረጂኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው።።።
ዘላለም አፈቅሬሽ አብሬሽ እሞታለሁ
ይሄን ያህል ነው ፍቅሬ ላንቺ ምንም እሆናለሁ።❤️
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ድርሰቴ
እንደ ሰውነቴ
ልክ እንደ አቦጊዳ ልክ እንደ ቃላቴ
ሀሳብ እንደ ሞላው እንደ ልብ ምቴ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ሀረጌ
ልክ እንደ ስንኜ ልክ እንደ ማረጌ
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ ልብወለድ
አስቦ አሰላስሎ ግጥም እንደመውለድ
እኔ እወድሻለው ቤት እንደመምታት
ሀያ መፅሀፎች ፃፍኩ እንደማለት
ደራሲ ነህ ተብሎ እንደመጠራት
እኔ እወድሻለው ለእናት እንደመግጠም
ዶ/ር አብይ አንገት ልክ እንደመጠምጠም
እኔ እወድሻለው ልክ እንደ በውቀቱ
እንደ ታገል ግጥም እንደወረቀቱ
ልክ አንደራዕዬ ልክ እንደሎሬቱ
እያልኩኝ እያልኩኝ ምሳሌ ደርድሬ
ሀሳበ መውደዴን በፅሁፍ አስፍሬ
ላስጨነቀኝ መውደድ ላላወቅሽው ፍቅሬ
የፃፍኩት ደብዳቤ ከዚሁ አስፍሬ
ደግሜ ባነበው ደግሜ ባነበው ሆነብኝ አሰልቺ
ፍቅሬን ለማስረዳት አልቻልኩም አይበጅ
የፍቅር አምሮቴን ተናገርኩት እንጂ
የትም ብትሆኚ ከአጠገቤም እሩቅ
አፍቃሪሽ ልቤ ነው መውደዱ የማያልቅ
ባትረጂኝ ብታስከፊኝ መውደዴ አይቀንስ
አንቺን ገና ሳይሽ መንፈሴ የሚታደስ
ፍቅር ትሩፋቴ መላ እኔነቴ
ያንቺው ነው ብያለው ተረጂልኝ እቴ
የልቤ ምት እንኳን ስላንቺ ሲመቱ
ብታዳምጪልኝ ምን ነበረ እቱ!
የመውደዴን ምላሽ ካንቺ ሳልጠብቀው
ባትረጂኝ እንኳን ሳፈቅርሽ ኖራለው።።።
ዘላለም አፈቅሬሽ አብሬሽ እሞታለሁ
ይሄን ያህል ነው ፍቅሬ ላንቺ ምንም እሆናለሁ።❤️
JOIN US
HERE
👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👆👆👆👆👆👆
SHARE & JOIN
ዜና የገለፀው ህልፈት!?
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።
ህልሜ ላይ ተኝቼ ፥ አንድ ቀስቃሽ ሳጣ
ውል ፍቺው ተስቶኝ ፥ ከቀረሁ በሌጣ
ህላዌዬ ላንዱ...
እርኩስ መንፈስ ሆኖ ፥ አበሳን ካመጣ
ሞት ማለት ይሄ ነው ፥ የህይወት ቆረጣ።
ስሚኝ እታለሜ!
አለሁ ለማለቱ ፥ ቆሞ ለመሄዱ
ዘርን ለመተካት ፥ ልጅን ለመውለዱ
ለአንድ ራስ ለመኖር ፥ እህል ለመቅመሱ
ዝግ ብሎ ለመጓዝ ፥ ለመለሳለሱ
ለጥሉ ለውጊያው ፥ ፍቅር ለመንሳቱ
ለአንዲት ጭብጥ መና ፥ ለመቀራመቱ
ለግፊያ ለጡጫው ፥ ለመሙላት በመንገድ
ለስሪያ ለሴሱ ፥ ከእንስት ለመላመድ
ለዚህ ለዚህ ላለው የተፈጥሮ እውነት
ሰው መሆን ባላሻ ከእንስሳ መለየት !
አዎን!
ለቅኔዋ ህይወት ...
ህብረ ቃል መስጥሬ ወርቁን ሳላወጣ
በትንፋሼ ወበቅ ...
ዉርጩ ላየለበት ...ለተገፋ ነዳይ ሙቀት ሳላመጣ
በጉብዝና ወሬ ፥ እየተናነስኩኝ ፥ ሳልቆም ለምስጋና
ጥላቻ አዝሞት ...
ላዘነበለ ዳስ ፍቅር ማገር ሆኖኝ ጎጆ ሳላቀና
ሚስማር እያቀበልሁ ፥ ለመሲህ ስቅላት
መልካሙን ሳልዘራ በፀሎት በሶላት
ህልሜን ሳልፈታ ፥ በቀናቴ ንጋት
በስንፍና ገበር ፥ ስጋዬን ለብጬ
ለምስር ወጥ አምሮት ፥ ብኩርና ሽጬ
ቀልቤን እየነሳሁ ለሰላሳ ዲናር
አቅሌን እየሳትሁኝ በእስክስታ በስካር
ንግስናዬን ሽሬ ፥ ከአዳም ተናንሼ
ኖሬያለሁ አልልም ፥
የዝምታው ዳኛን፥ መልኩን በመውረሴ።
አዎን !
ይኸው ባንቺ ዘመን ...
ሰው መሆን ተስኖን ፥ የሰው ስጋ ወርሰን ፥ ሳንኖር እንደሰው
ሞተዋል ሲሉን ነው ፥ አልሞትንም እያልን ፥ መግለጫ ምንሰጠው ።
👉ተቀላቀሉና👇
👍👍👍🙏👇🙏👇👍👍👍
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
👌👌✍ ☝️👆👇👇✍👌👌
👉Join us👇👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👍👍👍☝️🙏👆🙏👍👍👍
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።
ህልሜ ላይ ተኝቼ ፥ አንድ ቀስቃሽ ሳጣ
ውል ፍቺው ተስቶኝ ፥ ከቀረሁ በሌጣ
ህላዌዬ ላንዱ...
እርኩስ መንፈስ ሆኖ ፥ አበሳን ካመጣ
ሞት ማለት ይሄ ነው ፥ የህይወት ቆረጣ።
ስሚኝ እታለሜ!
አለሁ ለማለቱ ፥ ቆሞ ለመሄዱ
ዘርን ለመተካት ፥ ልጅን ለመውለዱ
ለአንድ ራስ ለመኖር ፥ እህል ለመቅመሱ
ዝግ ብሎ ለመጓዝ ፥ ለመለሳለሱ
ለጥሉ ለውጊያው ፥ ፍቅር ለመንሳቱ
ለአንዲት ጭብጥ መና ፥ ለመቀራመቱ
ለግፊያ ለጡጫው ፥ ለመሙላት በመንገድ
ለስሪያ ለሴሱ ፥ ከእንስት ለመላመድ
ለዚህ ለዚህ ላለው የተፈጥሮ እውነት
ሰው መሆን ባላሻ ከእንስሳ መለየት !
አዎን!
ለቅኔዋ ህይወት ...
ህብረ ቃል መስጥሬ ወርቁን ሳላወጣ
በትንፋሼ ወበቅ ...
ዉርጩ ላየለበት ...ለተገፋ ነዳይ ሙቀት ሳላመጣ
በጉብዝና ወሬ ፥ እየተናነስኩኝ ፥ ሳልቆም ለምስጋና
ጥላቻ አዝሞት ...
ላዘነበለ ዳስ ፍቅር ማገር ሆኖኝ ጎጆ ሳላቀና
ሚስማር እያቀበልሁ ፥ ለመሲህ ስቅላት
መልካሙን ሳልዘራ በፀሎት በሶላት
ህልሜን ሳልፈታ ፥ በቀናቴ ንጋት
በስንፍና ገበር ፥ ስጋዬን ለብጬ
ለምስር ወጥ አምሮት ፥ ብኩርና ሽጬ
ቀልቤን እየነሳሁ ለሰላሳ ዲናር
አቅሌን እየሳትሁኝ በእስክስታ በስካር
ንግስናዬን ሽሬ ፥ ከአዳም ተናንሼ
ኖሬያለሁ አልልም ፥
የዝምታው ዳኛን፥ መልኩን በመውረሴ።
አዎን !
ይኸው ባንቺ ዘመን ...
ሰው መሆን ተስኖን ፥ የሰው ስጋ ወርሰን ፥ ሳንኖር እንደሰው
ሞተዋል ሲሉን ነው ፥ አልሞትንም እያልን ፥ መግለጫ ምንሰጠው ።
👉ተቀላቀሉና👇
👍👍👍🙏👇🙏👇👍👍👍
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
👌👌✍ ☝️👆👇👇✍👌👌
👉Join us👇👇👇👇
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
@HOLLYPOEM
👍👍👍☝️🙏👆🙏👍👍👍
ማነ በር???
ማን ነበር ያለኔና አተ
ፍቅርን አቶ የተከራተተ
ላይናችን ማረፊያ አተን
ስገባ ስኖጣ
አተም ላንተ እኔም ለኔ
የምንለው ስናጣ ተያይተን ነበረ በሩቅ በሩቁ
አተም እኔም ጠፍቶን የፍቅር መረቁ
ለየብቻ መዋተት በዝቶብን መከራተቱ
ማነው ውዴ???
ግራቢገባኝ ቀባዠርኩ ለፍልፌ
እደማጣህ ሳስብ ድገት ተክለፍልፌ
✍️ አይኖቼን ካይኖችህ ሰክቼ
ጣቶችህኝ እየዳሰስኩ በጣቶቼ
ማነበር በጎናችን ማንስ ሰማ ሚስጥራችን
በነፍስ በሰረገላ የመጣ
ሁሉ ነገራችንን በይፍ ሊያወጣ
ማነው ...ውዴ??
ፅጌሬዳ አበባዋ ሰምታ ይሆን እዴ
እዲያ እየተማማልን ላንለያይ ውዴ
በወረቀት ቀለበት ቃል ኪዳን ስናስር
ቤት ማገር ምሰሶ ለማቆም ስንጥር
ማነው... ውዴ???
አይንሽን ላፈር እድትል ያረገው
ከኔ መለየትክን መራክን የወደደው
አተስ እደማቶን እኔስ አውቀዋለሁ
ቃልህ ቃሌ እዲሆን በደብ አጥንቻለሁ
✍️ያኔ እኔና አተ ቁጭ ብለን ስናወራ
መርጠን ስንቀመጥ የቦታ ዘዋራ
ሚስጥራችንን ማንም እንዳሰማ
እየተንሾካሸክን በፀጥታ ስናወራ
ያዩን ስለኛ የሰሙ ካይን ያውጣችሁ ብለው ሲመርቁ
ካይን ያውጣችሁ ባለው አንደበታቸው
ቱቱ ባለው ከፈራቸው
ይሄው ዛሬ ፊታቸውን አዙረው ተቀመጡ
ምክንያታችንን ለመስማት ጊዜ አጡ::
ተፈፀመ
👉 ከ ርብቂ
ጥበባዊ ንግግሮችን share በማድረግ የድርሻዎን ያበርክቱ
👇👇👇👇🙏👇👇👇👇👇
👉 ለጥበብ ልባቹን ክፍት አድርጉ👈
☝️☝️☝️☝️✌️👆👆👆👆👆
👉ተቀላቀሉና👇
👍👍👍🙏👇🙏👇👍👍👍
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
👌👌✍ ☝️👆👇👇✍👌👌
ማን ነበር ያለኔና አተ
ፍቅርን አቶ የተከራተተ
ላይናችን ማረፊያ አተን
ስገባ ስኖጣ
አተም ላንተ እኔም ለኔ
የምንለው ስናጣ ተያይተን ነበረ በሩቅ በሩቁ
አተም እኔም ጠፍቶን የፍቅር መረቁ
ለየብቻ መዋተት በዝቶብን መከራተቱ
ማነው ውዴ???
ግራቢገባኝ ቀባዠርኩ ለፍልፌ
እደማጣህ ሳስብ ድገት ተክለፍልፌ
✍️ አይኖቼን ካይኖችህ ሰክቼ
ጣቶችህኝ እየዳሰስኩ በጣቶቼ
ማነበር በጎናችን ማንስ ሰማ ሚስጥራችን
በነፍስ በሰረገላ የመጣ
ሁሉ ነገራችንን በይፍ ሊያወጣ
ማነው ...ውዴ??
ፅጌሬዳ አበባዋ ሰምታ ይሆን እዴ
እዲያ እየተማማልን ላንለያይ ውዴ
በወረቀት ቀለበት ቃል ኪዳን ስናስር
ቤት ማገር ምሰሶ ለማቆም ስንጥር
ማነው... ውዴ???
አይንሽን ላፈር እድትል ያረገው
ከኔ መለየትክን መራክን የወደደው
አተስ እደማቶን እኔስ አውቀዋለሁ
ቃልህ ቃሌ እዲሆን በደብ አጥንቻለሁ
✍️ያኔ እኔና አተ ቁጭ ብለን ስናወራ
መርጠን ስንቀመጥ የቦታ ዘዋራ
ሚስጥራችንን ማንም እንዳሰማ
እየተንሾካሸክን በፀጥታ ስናወራ
ያዩን ስለኛ የሰሙ ካይን ያውጣችሁ ብለው ሲመርቁ
ካይን ያውጣችሁ ባለው አንደበታቸው
ቱቱ ባለው ከፈራቸው
ይሄው ዛሬ ፊታቸውን አዙረው ተቀመጡ
ምክንያታችንን ለመስማት ጊዜ አጡ::
ተፈፀመ
👉 ከ ርብቂ
ጥበባዊ ንግግሮችን share በማድረግ የድርሻዎን ያበርክቱ
👇👇👇👇🙏👇👇👇👇👇
👉 ለጥበብ ልባቹን ክፍት አድርጉ👈
☝️☝️☝️☝️✌️👆👆👆👆👆
👉ተቀላቀሉና👇
👍👍👍🙏👇🙏👇👍👍👍
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
@hollypoem
👌👌✍ ☝️👆👇👇✍👌👌
የፊሊሞን ደብዳቤ ቁጥር 120💌
📩 28/03/2012 (እሁድ)📩
አዋ… ዛሬም መጠጥ ቤት ነኝ… በግራ እጄ አረቄ በቀኝ እጄ ደሞ ሲጋራዬን ይዤ… ስክርም ብያለው… እኔ መስከሬን አልጠላውም… እንደውም እራሴን እንድሆን ይረዳኛል… ሂሳቤን ከፈልኩ…ከምጣሁ በጣም ቆይቼ ነበር… እየተንገዳገድኩም መንገዴን ጀምርኩ…ጥንዶችም ሁለት ሁለት ሆነው ሌላ አለም ውስጥ ናቸው…አቦ እግዛብሔር ይባርካቸው… ከልቤ ተመኝቼላቸውም መንገዴን ቀጠልኩ…
ለአንቺ… ልነግርሽ እማይገቡ ብዙ ሚስጥሮቼን ነግሬሽ ነበር…ማንም እማያውቀውንም እውነቴን ጨምሮ… አሁን ላይ እሱን ሳስብ ያመኛል…ምን አለስ ባልነገርኳት እላለው… ቢሆንም ግን…አሁን ላይ በህይወቴ ምን እየሆነ እያለ እንደሆነ እኔም አላውቅም… ግን አላማርርም…የፈለገው ቢሆንም ዛሬም ተመስገን … አንተ እንዳልከውዛሬም ይሁን እላለው… ግን አንዳንዴ መተኛት እፈራለው… ደግሜ ባልነሳስ ስል እፈራለው…ስለዚ ብዙ ጊዜ አልተኛም… ተኝቼ ብዙ ነገር አልፎኛል… አለመነሳትን ደሞ እፈራለው…ካልተነሳሁ ብዙ ነገሮች ጥሩ አይሆኑም…
መኖር ማለት ላካ ስያኖሩ መኖርን ጨምሮ ነው… አሁን ላይ የገባኝ ነገር ቢኖር እሱ ነው… ደስታን ለማግኘት መከፍት የግድ ነው… ለመድረስ የግድ መጓዝ አልብን… ልብ ይለያያል ይህን አምናለው… የወደድነው ሁሉ አይወደንም… ያሰብነው ሁሉ አያስበንም… ትላንት በቃ ትላንት አለፈ… ለዛ ነው ዛሬን እየሰከርኩ ነገን በተስፋ እምጠብቀው…
እህቴ …አንድ ምክር ልምከርሽ… ያው እሚያውቅ ሰው ሆኜ ሳይሆን እንዲሁ ልነግርሽ ስለወደድኩ ነው… ልክ የሆነ ወንድ በህይወትሽ እስኪመጣ አትጠብቂ… ልክ የሆነ ሰው የለም… ልክ እምታደርጊው በፍቅር ነው… እንጂ ያልበደለ የለም…ስትወጂው ልክ እንዲሆን አትጠብቂው… በመስፈርት እሚውደድ ቢሆን እማ ኖሮ ጌታ እኛን ባልወደደን… እሱ እኛን የወደደን መመለሳችንን አይቶ ነው… እናም ጌታ እምትወጂውን ህይወት ይስጥሽ 😊
እቤቴ ደረስኩ… እማ በር ላይ ቆማለች… የለ ለምን? የወደደቺኝ ሴት… እምኖርላት …መሞትም ካለብኝ እምሞትላት ሴት… አቅፌ ሳምኳት… ወደውስጥም አብረን ገባን…ቆየህ እኮ አለቺኝ አይን አይኔን እያየች… እኔም… የመጠሁትም እኮ አንቺ ስላለሽ ብቻ ነው ብዬ ደግሜ ሳምኳት…የእማን አይኗን ሳይ የደፋሁትን አንገቴን ቀና አደርጋለው… ለመተው ያሰብኩትን ደጋሜ እጀምራለው… እማ እውነት ናት… እንደሷ አይነት ሚስት ይሰጠኝም ዘንድ ወዳጆቼ በፀሎታቹህ አስቡኝ… አሜን🙏🏾
* ዛሬም ተመስገን *
😊…ለአንቺ ዛሬም ቢሆን ጥሩውን ብቻ ነው እምመኝልሽ…ከምትወጃቸው ሰዋች ጋር ሰላምሽ ይብዛ…😘
✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ ✍🏽
ጥበባዊ ንግግሮችን #Share በማድረግ የድርሻዎን ያበርክቱ
👇👇👇👇🙏👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 #ለጥበብ_ልባቹን_ክፍት_አድርጉ 👈
☝️☝️☝️☝️✌️👆👆👆👆👆👆👆👆
👉ተቀላቀሉና👇👇👇👇
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
📩 28/03/2012 (እሁድ)📩
አዋ… ዛሬም መጠጥ ቤት ነኝ… በግራ እጄ አረቄ በቀኝ እጄ ደሞ ሲጋራዬን ይዤ… ስክርም ብያለው… እኔ መስከሬን አልጠላውም… እንደውም እራሴን እንድሆን ይረዳኛል… ሂሳቤን ከፈልኩ…ከምጣሁ በጣም ቆይቼ ነበር… እየተንገዳገድኩም መንገዴን ጀምርኩ…ጥንዶችም ሁለት ሁለት ሆነው ሌላ አለም ውስጥ ናቸው…አቦ እግዛብሔር ይባርካቸው… ከልቤ ተመኝቼላቸውም መንገዴን ቀጠልኩ…
ለአንቺ… ልነግርሽ እማይገቡ ብዙ ሚስጥሮቼን ነግሬሽ ነበር…ማንም እማያውቀውንም እውነቴን ጨምሮ… አሁን ላይ እሱን ሳስብ ያመኛል…ምን አለስ ባልነገርኳት እላለው… ቢሆንም ግን…አሁን ላይ በህይወቴ ምን እየሆነ እያለ እንደሆነ እኔም አላውቅም… ግን አላማርርም…የፈለገው ቢሆንም ዛሬም ተመስገን … አንተ እንዳልከውዛሬም ይሁን እላለው… ግን አንዳንዴ መተኛት እፈራለው… ደግሜ ባልነሳስ ስል እፈራለው…ስለዚ ብዙ ጊዜ አልተኛም… ተኝቼ ብዙ ነገር አልፎኛል… አለመነሳትን ደሞ እፈራለው…ካልተነሳሁ ብዙ ነገሮች ጥሩ አይሆኑም…
መኖር ማለት ላካ ስያኖሩ መኖርን ጨምሮ ነው… አሁን ላይ የገባኝ ነገር ቢኖር እሱ ነው… ደስታን ለማግኘት መከፍት የግድ ነው… ለመድረስ የግድ መጓዝ አልብን… ልብ ይለያያል ይህን አምናለው… የወደድነው ሁሉ አይወደንም… ያሰብነው ሁሉ አያስበንም… ትላንት በቃ ትላንት አለፈ… ለዛ ነው ዛሬን እየሰከርኩ ነገን በተስፋ እምጠብቀው…
እህቴ …አንድ ምክር ልምከርሽ… ያው እሚያውቅ ሰው ሆኜ ሳይሆን እንዲሁ ልነግርሽ ስለወደድኩ ነው… ልክ የሆነ ወንድ በህይወትሽ እስኪመጣ አትጠብቂ… ልክ የሆነ ሰው የለም… ልክ እምታደርጊው በፍቅር ነው… እንጂ ያልበደለ የለም…ስትወጂው ልክ እንዲሆን አትጠብቂው… በመስፈርት እሚውደድ ቢሆን እማ ኖሮ ጌታ እኛን ባልወደደን… እሱ እኛን የወደደን መመለሳችንን አይቶ ነው… እናም ጌታ እምትወጂውን ህይወት ይስጥሽ 😊
እቤቴ ደረስኩ… እማ በር ላይ ቆማለች… የለ ለምን? የወደደቺኝ ሴት… እምኖርላት …መሞትም ካለብኝ እምሞትላት ሴት… አቅፌ ሳምኳት… ወደውስጥም አብረን ገባን…ቆየህ እኮ አለቺኝ አይን አይኔን እያየች… እኔም… የመጠሁትም እኮ አንቺ ስላለሽ ብቻ ነው ብዬ ደግሜ ሳምኳት…የእማን አይኗን ሳይ የደፋሁትን አንገቴን ቀና አደርጋለው… ለመተው ያሰብኩትን ደጋሜ እጀምራለው… እማ እውነት ናት… እንደሷ አይነት ሚስት ይሰጠኝም ዘንድ ወዳጆቼ በፀሎታቹህ አስቡኝ… አሜን🙏🏾
* ዛሬም ተመስገን *
😊…ለአንቺ ዛሬም ቢሆን ጥሩውን ብቻ ነው እምመኝልሽ…ከምትወጃቸው ሰዋች ጋር ሰላምሽ ይብዛ…😘
✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ ✍🏽
ጥበባዊ ንግግሮችን #Share በማድረግ የድርሻዎን ያበርክቱ
👇👇👇👇🙏👇👇👇👇👇👇👇👇
👉 #ለጥበብ_ልባቹን_ክፍት_አድርጉ 👈
☝️☝️☝️☝️✌️👆👆👆👆👆👆👆👆
👉ተቀላቀሉና👇👇👇👇
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
🙏🏾 @hollypoem @hollypoem 🙏🏾
ምነው ታዲያ?
መርሳት ቀላል ነው እንዴ?… ሁሉንም ነገር መተውስ?… አዲስ ነገር ለመጀመር ያለፈውን ማርሳት ያስፈልጋል እንዴ?…ምነው ታድያ?… ይሄ ለአንቺ ቀለለሽ… እኔ እመቤቴን አላውቅም…
እየሄድሽ እያየሁ አልሄደችም እላለው… እየረቅሺኝ እያየሁ እረ በፍፁም ብዬ እከራከራለው… አንዳንዴ እመርቅሻለው… አንዳንዴ ደሞ አብዛቼ እረግምሻለው… ምን እየሆንኩ እያለሁ እንደሆነ እኔም አላውቀውም…ግራው ከቀኙ ይጠፋብኛል…
አንቺ እኮ አልገባሽም… እኔንም ቢሆን አልተረዳሺኝም… ከልብሽ ያልቅ ያን ማረጋገጥ እማያውቀውን ጆሮሽን ነው እምታምኚው… ከእንግዲህም እኔ እንዲ አደለሁም ማለት አልፈልግም… ውሸታም ነህ፣ ሀጥያተኛ ነህ፣አስመሳይ ነህ እና የፈለግሺውን ማለት ትቻያለሽ …እንደፈለግሺውም ማሰብ ትችያለሽ…ለምን አልልሽም…ብቻ አንቺ እንደፈለግሽ…
ግን ደስ እሚለው ምን መሰለሽ?… ዛሬም እወድሻለው… ዛሬም ጥሩሽን ነው እምመኘው… በርግጥ የሆነ ቀን በህይወት አጋጣሚ መገናኘታችን አይቀርም…ትልቅ ሰዋች ሆነን እና የራሳችን ህይወት ኖሮን…እስከዛ ግን… ድንገት ስለ እኔ ካሰብሽ… ዱርዬ መሆኔን፣ የሰውን መውደቅ እንደማልመኝ፣ማንም ላይ እንደማልፈርድ እና ከለፈው ማንነቴ ለመሻሻል ሁሌም እንደምለፋ እንዳትረሺ… እና እግዛብሔር እምትወጂውን ህይወት ይስጥሽ …አሜን፡
ደሞ አሁን ላይ በጣም ደስተኛ ነኝ… እንዴት እና በማን እሚለውን ግን አሁን ላይ ሳይሆን ወደ ፊት በስፊው እነግርሻለው… የወደቁት ይነሳሉ…የበደሉም ይክሳሉ…
አቦ እናተ ግን ተስፋ እንዳትቆርጡ… የፈለገ ህይወት ከባድ ብትሆንም ቀና ብለን እንታገላታለን መውደቋም አይቀርም… ሰላም ለእናተ ይሁን።
✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ ✍🏽
… 6/4/2012…
✨ ሰኞ✨
😉👉 @HOLLYPOEM
👕👉 @HOLLYPOEM
👖👉 @HOLLYPOEM
መርሳት ቀላል ነው እንዴ?… ሁሉንም ነገር መተውስ?… አዲስ ነገር ለመጀመር ያለፈውን ማርሳት ያስፈልጋል እንዴ?…ምነው ታድያ?… ይሄ ለአንቺ ቀለለሽ… እኔ እመቤቴን አላውቅም…
እየሄድሽ እያየሁ አልሄደችም እላለው… እየረቅሺኝ እያየሁ እረ በፍፁም ብዬ እከራከራለው… አንዳንዴ እመርቅሻለው… አንዳንዴ ደሞ አብዛቼ እረግምሻለው… ምን እየሆንኩ እያለሁ እንደሆነ እኔም አላውቀውም…ግራው ከቀኙ ይጠፋብኛል…
አንቺ እኮ አልገባሽም… እኔንም ቢሆን አልተረዳሺኝም… ከልብሽ ያልቅ ያን ማረጋገጥ እማያውቀውን ጆሮሽን ነው እምታምኚው… ከእንግዲህም እኔ እንዲ አደለሁም ማለት አልፈልግም… ውሸታም ነህ፣ ሀጥያተኛ ነህ፣አስመሳይ ነህ እና የፈለግሺውን ማለት ትቻያለሽ …እንደፈለግሺውም ማሰብ ትችያለሽ…ለምን አልልሽም…ብቻ አንቺ እንደፈለግሽ…
ግን ደስ እሚለው ምን መሰለሽ?… ዛሬም እወድሻለው… ዛሬም ጥሩሽን ነው እምመኘው… በርግጥ የሆነ ቀን በህይወት አጋጣሚ መገናኘታችን አይቀርም…ትልቅ ሰዋች ሆነን እና የራሳችን ህይወት ኖሮን…እስከዛ ግን… ድንገት ስለ እኔ ካሰብሽ… ዱርዬ መሆኔን፣ የሰውን መውደቅ እንደማልመኝ፣ማንም ላይ እንደማልፈርድ እና ከለፈው ማንነቴ ለመሻሻል ሁሌም እንደምለፋ እንዳትረሺ… እና እግዛብሔር እምትወጂውን ህይወት ይስጥሽ …አሜን፡
ደሞ አሁን ላይ በጣም ደስተኛ ነኝ… እንዴት እና በማን እሚለውን ግን አሁን ላይ ሳይሆን ወደ ፊት በስፊው እነግርሻለው… የወደቁት ይነሳሉ…የበደሉም ይክሳሉ…
አቦ እናተ ግን ተስፋ እንዳትቆርጡ… የፈለገ ህይወት ከባድ ብትሆንም ቀና ብለን እንታገላታለን መውደቋም አይቀርም… ሰላም ለእናተ ይሁን።
✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ ✍🏽
… 6/4/2012…
✨ ሰኞ✨
😉👉 @HOLLYPOEM
👕👉 @HOLLYPOEM
👖👉 @HOLLYPOEM
#ከንቱ #ትውልድ
==
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
=======
እንዲህ ነው ይህ ትውልድ.....
ያጎረሰውን እጅ በእሳት የሚያነድ፣
የራሱን ሰው ገሎ የሚያወራ አንደ ጀብድ፣
በፌስቡክ መንደር ላይ መደስኮር የሚወድ፣
ሀገር ስትሞት አይቶ ቆሞ የሚቀልድ።
አልጨረስኩም....
የእከሌ ብሄር ነው ብየ አልከፋፈልኩም፣
የነ እከሌ ቡድን ብየም አልጠቀስኩም።
ከሁሉም ስመርጥ.....
ሀገር ስራ ሲባል ለማፍረስ የሚሮጥ፣
የወገኑን ሰርቆ ለራሱ የሚያጌጥ፣
ሀገሩን ጨቁኖ ቤቱን የሚያስበልጥ፣
የኀላን ዘንግቶ ታሪክን የሚልጥ፣
የአስተሳሰብ ደነዝ አለ ከሁሉም ውስጥ።
ምን ይሄ ብቻ.....
ያገባኛል ብለህ ለሰው ቤት ጉልቻ፣
እውነት ስትናገር ሲደርስብህ ዛቻ፣
እሱን ተቋቁመህ ብትወጣ ዘመቻ፣
አብሮ ሚቆም የለም ላንተ መመከቻ።
ይህ ትውልድ እንዲህ ነው..........
ለሀገሩ ቀርቶ ስለራሱ የማያውቅ፣
የጎረቤቱን ቤት በጠራራ ሚሰርቅ፣
ሀገር አልማ ሲባል ቆሞ የሚሳለቅ፣
የሰፈሩን ድንጋይ በቅምጥ የሚያሞቅ፣
የሴቶችን ዳሌ ባይኑ የሚያሳቅቅ፣
ባነበብከው እውነት በማይካድ ሀቅ፤
ከቆሻሻ ጥላቻ ራቅ ባሸናፊዉ ፍቅር ላቅ!!
ወንድም እህቴ አንቺም አንተም ታረቅ
ሁላችንም እንታረቅ🙏
.
🇪🇹🇪🇹ፈጣሪ ሆይ,,,,, #ኢትዮጵያዬን አስባት🇪🇹
ከጥላሁን ጋሹ ግጥም
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·. @hollypoem @hollypoem
•════•••🍃🌺🍃•••════•
==
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
=======
እንዲህ ነው ይህ ትውልድ.....
ያጎረሰውን እጅ በእሳት የሚያነድ፣
የራሱን ሰው ገሎ የሚያወራ አንደ ጀብድ፣
በፌስቡክ መንደር ላይ መደስኮር የሚወድ፣
ሀገር ስትሞት አይቶ ቆሞ የሚቀልድ።
አልጨረስኩም....
የእከሌ ብሄር ነው ብየ አልከፋፈልኩም፣
የነ እከሌ ቡድን ብየም አልጠቀስኩም።
ከሁሉም ስመርጥ.....
ሀገር ስራ ሲባል ለማፍረስ የሚሮጥ፣
የወገኑን ሰርቆ ለራሱ የሚያጌጥ፣
ሀገሩን ጨቁኖ ቤቱን የሚያስበልጥ፣
የኀላን ዘንግቶ ታሪክን የሚልጥ፣
የአስተሳሰብ ደነዝ አለ ከሁሉም ውስጥ።
ምን ይሄ ብቻ.....
ያገባኛል ብለህ ለሰው ቤት ጉልቻ፣
እውነት ስትናገር ሲደርስብህ ዛቻ፣
እሱን ተቋቁመህ ብትወጣ ዘመቻ፣
አብሮ ሚቆም የለም ላንተ መመከቻ።
ይህ ትውልድ እንዲህ ነው..........
ለሀገሩ ቀርቶ ስለራሱ የማያውቅ፣
የጎረቤቱን ቤት በጠራራ ሚሰርቅ፣
ሀገር አልማ ሲባል ቆሞ የሚሳለቅ፣
የሰፈሩን ድንጋይ በቅምጥ የሚያሞቅ፣
የሴቶችን ዳሌ ባይኑ የሚያሳቅቅ፣
ባነበብከው እውነት በማይካድ ሀቅ፤
ከቆሻሻ ጥላቻ ራቅ ባሸናፊዉ ፍቅር ላቅ!!
ወንድም እህቴ አንቺም አንተም ታረቅ
ሁላችንም እንታረቅ🙏
.
🇪🇹🇪🇹ፈጣሪ ሆይ,,,,, #ኢትዮጵያዬን አስባት🇪🇹
ከጥላሁን ጋሹ ግጥም
.........
JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
`·. @hollypoem @hollypoem
•════•••🍃🌺🍃•••════•
እባክህ አምላኬ
ዘረኛ ቀማኛ ሰላም እንዳያገኝ፡
የፍቅር የአብሮነት ጠባቂህ አድርገኝ፡
ካዘዝክብኝ ቦታ ታዛዥ ሆኘ እንድገኝ፡
እባክህ
የምድር ባለቤት የሰዉ ልጅ ፈጣሪ፡
አድርገኝ እባክህ የሰላም ተቆርቋሪ፡
በዕውቀት አንፀኝ እዉነት እንድናገር፡
መረጃውን ሁሉ አርግልኝ ገርበገር፡
እባክህ
ጠማማውን ሁሉ በሁጃ አንበርክኬ፡
በጣፋጭ አንደበት እውነትን ሰብኬ፡
ከጠላቶች ሴራ ቃልህ ጋሻ ሆኖኝ፡
በደሊል ስናገር ሱው ሁሉም አምኖኝ
………
አንተን የምዘምር በጧትም በማታ፡
ሰወች ከበዙበት ጭር ካለም ቦታ፡
ግሩም ፍጥረትህን እያስተነተንኩኝ፡
በሰጠኸኝ ፀጋ እየተመሰጥኩኝ፡
ሀጢያቴን አስቤ ላንተ እያለቀስኩኝ፡
ባሪያህ በመሆኔ እየተደሰትኩኝ፡
አንተን በማመፄ በራሴ እያፈርኩኝ፡
አይኔን ላክ አድርጌ ወደ ግዙፍ ሰማይ፡
እንባየን ዘርግፌ ከሰውነቴ ላይ፡
እባክህ ልበልህ ጭንቀቴን እንድታይ፡
የላይ ገፅታየን የውስጤንም ሚስጥር ታውቀዋለህና፡
ከጨለማው አውጣኝ የአለማት ጌታ አዛኙ ረበና፡
የወደፊት ህልሜን
የቀብር አለሜን አንተ አሣምርልኝ፡
አንተ ፊት የሚቆም አንድም ነገር የለኝ፡
በጠፊዋ አለምም ልታገል ለምነቴ፡
ተውሒድ ለሱና ይሁን መሰዋዕቴ፡
ሸሒድ ሆኖ መሞት ነውና ምኞቴ፡
ምንም አንተን ባምፅ ከወንጀል ላይ ብሆን፡
መምራት ባንተ እጂ ነው አርገኝ እንደምሆን፡
ያንተንም ትዕዛዝ ሣላሟላ ብጥስ፡
አላከብርም ብየ ህግህን ብበጥስ፡
በተቻለኝ አቅም ወዳንተ ተመለስኩ፡
ያላንተ መድሀኒት እንደሌለኝ አወኩ፡
ያ አሏህ እባክህን !!??
ቅናቻውን ስጠኝ ከማያልቀው ባንክህ፡
የአለም ፈጣሪ ማርታህን እባክህ፡
ሁሌም ልማፀንህ ቆሜም ተንበርክኬ፡
ጀነትን ለግሰኝ እባክህ አምላኬ፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 ተቀላቀሉን 🙏
👌👌👌👌👌👌👌
👌 JOIN_US 👌
👌👌👌👌👌👌👌
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
ዘረኛ ቀማኛ ሰላም እንዳያገኝ፡
የፍቅር የአብሮነት ጠባቂህ አድርገኝ፡
ካዘዝክብኝ ቦታ ታዛዥ ሆኘ እንድገኝ፡
እባክህ
የምድር ባለቤት የሰዉ ልጅ ፈጣሪ፡
አድርገኝ እባክህ የሰላም ተቆርቋሪ፡
በዕውቀት አንፀኝ እዉነት እንድናገር፡
መረጃውን ሁሉ አርግልኝ ገርበገር፡
እባክህ
ጠማማውን ሁሉ በሁጃ አንበርክኬ፡
በጣፋጭ አንደበት እውነትን ሰብኬ፡
ከጠላቶች ሴራ ቃልህ ጋሻ ሆኖኝ፡
በደሊል ስናገር ሱው ሁሉም አምኖኝ
………
አንተን የምዘምር በጧትም በማታ፡
ሰወች ከበዙበት ጭር ካለም ቦታ፡
ግሩም ፍጥረትህን እያስተነተንኩኝ፡
በሰጠኸኝ ፀጋ እየተመሰጥኩኝ፡
ሀጢያቴን አስቤ ላንተ እያለቀስኩኝ፡
ባሪያህ በመሆኔ እየተደሰትኩኝ፡
አንተን በማመፄ በራሴ እያፈርኩኝ፡
አይኔን ላክ አድርጌ ወደ ግዙፍ ሰማይ፡
እንባየን ዘርግፌ ከሰውነቴ ላይ፡
እባክህ ልበልህ ጭንቀቴን እንድታይ፡
የላይ ገፅታየን የውስጤንም ሚስጥር ታውቀዋለህና፡
ከጨለማው አውጣኝ የአለማት ጌታ አዛኙ ረበና፡
የወደፊት ህልሜን
የቀብር አለሜን አንተ አሣምርልኝ፡
አንተ ፊት የሚቆም አንድም ነገር የለኝ፡
በጠፊዋ አለምም ልታገል ለምነቴ፡
ተውሒድ ለሱና ይሁን መሰዋዕቴ፡
ሸሒድ ሆኖ መሞት ነውና ምኞቴ፡
ምንም አንተን ባምፅ ከወንጀል ላይ ብሆን፡
መምራት ባንተ እጂ ነው አርገኝ እንደምሆን፡
ያንተንም ትዕዛዝ ሣላሟላ ብጥስ፡
አላከብርም ብየ ህግህን ብበጥስ፡
በተቻለኝ አቅም ወዳንተ ተመለስኩ፡
ያላንተ መድሀኒት እንደሌለኝ አወኩ፡
ያ አሏህ እባክህን !!??
ቅናቻውን ስጠኝ ከማያልቀው ባንክህ፡
የአለም ፈጣሪ ማርታህን እባክህ፡
ሁሌም ልማፀንህ ቆሜም ተንበርክኬ፡
ጀነትን ለግሰኝ እባክህ አምላኬ፡
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 ተቀላቀሉን 🙏
👌👌👌👌👌👌👌
👌 JOIN_US 👌
👌👌👌👌👌👌👌
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
ስለ መጽሐፍት
----------~~---------
★ በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መጽሀፍቶች ውስጥ አሉ።
የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መጽሐፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።
((አብርሃም ሊንከን))
.
★ መጽሐፍን ከማቃጠል የባሰ በርካታ ወንጀሎች አሉ። ከነዚህ መሃል መጽሀፍትን አለማንበብ አንዱ ትልቁ ወንጀል ነው።
((ጆሴፍ ብሮድስኪ))
.
★ የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መጽሀፍ በማንበቤ ነው።
((ቤል ሑክስ))
.
★ መጽሀፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።
((ሬኔ ዴካርቴሥ))
.
★ እዚህ ምድር ላይ ግዜ የማይሽረው ደስታን የሚሰጠን ብቸኛው ነገር መጽሐፍ የማንበብ ልምድ ነው። ሁሉም ደስታዎቻችን በወረት ከእኛ ሲለዩን መጽሀፍ የማንበብ ልምዳችን ግን ዘወትር ደስተኞች ያደርገናል።
((አንቶኒ ትሮሎፔ))
.
★ አዎ! የሚታኘክ ማስቲካ ለማምረት ከምናወጣው ወጪ በላይ ለመጽሀፍቶች ብዙ ወጪን ባናወጣ ኖሮ ይህች ሀገራችን እንዲህ የሰለጠነችና የዘመነች አትሆንም ነበር።
((አልበርት ሀባርድ - አሜሪካዊ))
.
★ አላዋቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሳሪያ ማንበብ ነው።
((ሌኖርድ ቤይንስ ጆንሰን))
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 ተቀላቀሉን 🙏
👌👌👌👌👌👌👌
👌 JOIN_US 👌
👌👌👌👌👌👌👌
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
----------~~---------
★ በህይወቴ ማወቅ የምፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ መጽሀፍቶች ውስጥ አሉ።
የኔ ምርጥ ጓደኛ ብዬ የምቀርበው ሰው ያላነበብኩትን መጽሐፍ “እንካ አንብብ” ብሎ የሚሰጠኝ ነው።
((አብርሃም ሊንከን))
.
★ መጽሐፍን ከማቃጠል የባሰ በርካታ ወንጀሎች አሉ። ከነዚህ መሃል መጽሀፍትን አለማንበብ አንዱ ትልቁ ወንጀል ነው።
((ጆሴፍ ብሮድስኪ))
.
★ የኔን የግል ህይወት ብቻ ሳይሆን በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን ህይወት መለወጥ የቻሉ ሀሳቦችን መተግበር የቻልኩት መጽሀፍ በማንበቤ ነው።
((ቤል ሑክስ))
.
★ መጽሀፍትን በሚገባ ማንበብ ማለት በድሮ ዘመን ይኖር ከነበረ በጣም አስተዋይ ሰው ጋር መወያየት ማለት ነው።
((ሬኔ ዴካርቴሥ))
.
★ እዚህ ምድር ላይ ግዜ የማይሽረው ደስታን የሚሰጠን ብቸኛው ነገር መጽሐፍ የማንበብ ልምድ ነው። ሁሉም ደስታዎቻችን በወረት ከእኛ ሲለዩን መጽሀፍ የማንበብ ልምዳችን ግን ዘወትር ደስተኞች ያደርገናል።
((አንቶኒ ትሮሎፔ))
.
★ አዎ! የሚታኘክ ማስቲካ ለማምረት ከምናወጣው ወጪ በላይ ለመጽሀፍቶች ብዙ ወጪን ባናወጣ ኖሮ ይህች ሀገራችን እንዲህ የሰለጠነችና የዘመነች አትሆንም ነበር።
((አልበርት ሀባርድ - አሜሪካዊ))
.
★ አላዋቂነትንና ችኩልነትን የምንዋጋበት ብቸኛው ወሳኝ መሳሪያ ማንበብ ነው።
((ሌኖርድ ቤይንስ ጆንሰን))
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 ተቀላቀሉን 🙏
👌👌👌👌👌👌👌
👌 JOIN_US 👌
👌👌👌👌👌👌👌
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM
👉 @HOLLYPOEM