መገላለጥ መመላለጥ
ይቅርብሽ መሎጣሎጥ
አይሆንሽም አጀብ አጃብ
ለምለሜ ሆይ ነይ በሂጃብ ...
ውብዬ ሆይ ፍቀጅ
ልብየ ተነጥፏል ስገጅ
ባይንሽ ዓይኔን ላጥራ
ፊደለ-ውበትሽን ልቅራ
ከከንፈርሽ ፍሬ ልቃም
ከነፍስያሽ ልሁን ግጣም
ግን ውብዬ ...
ስለ ጉንጭሽ ብርራ ቀለም
ስለ አይኖችሽ ኪነ-መስ-ለምለም
መቼ ነው ...
ግል-ገላሽን በጥቼ
(በአላህ በፍጥረቱ ኮርቼ)
በደመ-ነፍስሽ (ትኩስ) ቀለም ...
እልብሽ ላይ ምፅፍ ሥነ-ግጥም
✍ዳዊት
ይቅርብሽ መሎጣሎጥ
አይሆንሽም አጀብ አጃብ
ለምለሜ ሆይ ነይ በሂጃብ ...
ውብዬ ሆይ ፍቀጅ
ልብየ ተነጥፏል ስገጅ
ባይንሽ ዓይኔን ላጥራ
ፊደለ-ውበትሽን ልቅራ
ከከንፈርሽ ፍሬ ልቃም
ከነፍስያሽ ልሁን ግጣም
ግን ውብዬ ...
ስለ ጉንጭሽ ብርራ ቀለም
ስለ አይኖችሽ ኪነ-መስ-ለምለም
መቼ ነው ...
ግል-ገላሽን በጥቼ
(በአላህ በፍጥረቱ ኮርቼ)
በደመ-ነፍስሽ (ትኩስ) ቀለም ...
እልብሽ ላይ ምፅፍ ሥነ-ግጥም
✍ዳዊት
❤2
* የልማት ጥያቄ *
"
ውዴ እኔ ያልኩት፣
ከላይ በርዕሱ ልክ እንደጠቀስኩት፣
በድፍረት ቀርቤ አንቺን የጠየኩት፤
ከጭኖችሽ መሃል… ያለውን ለም መሬት ለልማት ፈለኩት፡፡
ድንግሉ መሬትሽ በዝናብ የራሰው ፍቀጂልኝና ክረምቱን ልረሰው፡፡
መንግስት ሳይገባበት ፣ደላላ ሳይሰማ፤
በውል አልባ ፍቅር ፣እኛው እንስማማ ፡፡
መቼም በኛ ሀገር…ታውቂያለሽ አውቃለው፤
ከማንም ከምንም ፣ልማት ነው የሚቀድመው ፡፡
ደግሜ ልነገርሽ… የኔናንቺን ወሬ ፣የኔናንቺን ደባ፤
ሌላ ሰው አይስማው ፣ መንግስት ጆሮ አይግባ ፡፡
ነገሬ እስኪገባሽ ፣ ታዲያ ምን ይሻላል፤
ጠንካራ ገበሬ ፣ ባመት ይሸለማል ፡፡
ይሄንን ቢያውቅ አይደል ፣ ምድረ ዲያስፖራ፤
ሀገር ሸሽቶ ሄዶ ፣ ሀገር የሚያኮራ ?!
ወደፊት ለመጓዝ ፣ ለማደግ ስንዳዳ፤
አንዳንዴም ይሆናል ፣ ጠላትም እንግዳ፡፡
በዚህ በኛ ሀገር ፣ እንኳን ድንግል መሬት፤
በሊዝ ከተገዛ ፣ ይፈርሳል የሰው ቤት ፡፡
እስቲ አሁን በኔ ሞት፣ ይሄ ይጠፋሻል ?
‹‹ልማት›› ከተባለ ፣ ድንበርም ይሸሻል ፡፡
በዚህ በኛ ሀገር…
እኔም አንቺም ሁሉም ፣ቀድሞ እንደምናውቀው፤
ከማንም ከምንም ፣ ልማት ነው ሚቀድመው ፡፡
‹‹ሙስና ነው›› ሳንል ፣ መንግስት ሳንፈራ፤
እስኪ እሺ በይና ፣ ሻጥር እንስራ ፡፡
ደግሜ ልንገርሽ ፣ ጥያቄዬ ይህ ነው፤
በውኔም በህልሜም ፣ እኔ እንደማልመው፤
ከጭኖችሽ መሀል… ያለውን ለም መሬት ፣ ፍቀጅልኝ ላልማው ፡፡
እንዲ በቀላሉ… ‹‹እሺ›› ብሎ መስጠት ፣ አውቃለሁ ይከብዳል፤
ግን ደሞ ልማት ነው…
ይህ ድንግል መሬትሽ ፣ ለሚያለማ ሀብታም ፣ ሊሰጠው ግድ ይላል ፡፡
ምክንያቱም….
በዚህ በኛ ሀገር ፣ እኔም አንቺም ሁሉም ፣ በወል የምናውቀው፤
ከማንም ከምንም ፣ልማት ነው ሚቀድመው፡፡
-------------///-------------
(ኤፊ ማክ)

👍6❤1
ጉም አዝሎ ጋራ ላይ እጥላል ላመዳይ፤
ሲያስፈራ ክረምቱ አቤት ኖረሽ ብታይ።
ገብቼ ከእልፍኙ ገሉን ብለኩሰዉ፤
ለካ ቢነድ እሳት አይሞቅም ያለ ሰዉ።
"
@hollypoem
t.me/hollypoem
ሲያስፈራ ክረምቱ አቤት ኖረሽ ብታይ።
ገብቼ ከእልፍኙ ገሉን ብለኩሰዉ፤
ለካ ቢነድ እሳት አይሞቅም ያለ ሰዉ።
"
@hollypoem
t.me/hollypoem
Telegram
ግጥም ፍቅር ቅኔ
ለማንኛዉም አስተያየት👉 @hollynba
ግጥም
ቃላትን በንዝረት በምትሃት በዉበት እና በእዉነት አበጃጅቶ እፈጥርልናል
ቁስልን ማከም ተስፋን ማለምለም አቅም አለዉ
ፍቅር
ዉበት እንደ ተመልካቹ እንደሆነዉ ሁሉ ፍቅርም በዚዉ ሊገለፅ የሚችል በተለያየ አንደበት በተለያየ ትሩጋሜ ሊገለፅ የሚችል ረቂቅ የፈጣሪ ልግስና ነዉ
ቅኔ
ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ።

👍1
"የት እንገናኝ? "
የተመቸህ ቦታ ሆነህ ጠብቀኝ
" ኮፊ ሀውስ ልጠብቅሽ ?"
ይመቸኛል መጣሁ
ለመጀመሪያም ለመጨረሻም ከእርሱ ጋር ብቻ የገባሁበት ካፌ ነበር።
እሱ ሁለት ብረጭቆ ቡና እኔ ደግሞ አንድ ነጣ ያለ ማኪያቶ ጠጣን።ሰአቱን ማስቆም ብችል አብሬው እዛችው ወንበር ላይ መሽቶ ቢነጋ ምን ያህን ደስ ባለኝ ነበር።
ኮስታራ የመሰለ ፊቱ ላይ አይኔን ጥዬ ቀረሁ ልቤንም ያለጥርጥር ጣልኩበት።
ለመጀመሪያ ጊዜ የራሴ ሰው እንዳገኘሁ ተሰማኝ።
አንዳንዴ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የምትሸነፋለት ሰው ይኖራል።
አንዳንዴ ስለነገ ሳታሰላስሉ ዛሬን ጨርሳችሁ የምትንበረከኩለት ሰው ይኖራል።
አንዳንዴ ፍርሀትን ጥሳችሁ ድንበር የምትሻገሩለት ሰው ይኖራል።
በቃ እሱ እንደዚህ ነው ድንበሬን ጥሼ የሄድኩለት ፍርሀቴን አሸንፌ የተንበረከኩለት ።
ማረፊያዬ ነበር ሮጬ የምደበቅበት
አንገቱ ላይ ተወሽቄ ሀዘኔን የምጥልበት
ነፃነቴ ነበር አንዳች የማልሳቀቅበት
"ታውቂያለሽ ?"
ምኑን ?
"አይኖችሽ መሀል አይደለም መኖር መሞት ይናፈቃል "
ተዋ
"የእውነት ባንቺ ልክ እናቴ እንኳን አይታኝ ማወቋን እጠራጠራለሁ ፤ ለምንድነው ግን እንደዚህ የምታይኝ ? "
ፈገግ እላለሁ ውስጤ በታመቀው ፍቅር ልክ ንግግሬ ሊገልፅልኝ ያቃተውን በአይኖቼ ቋንቋ ልነግረው እሞክራለሁ።
"እንዳትረሺ ከአይኖችሽ ብዙ ጉዳይ አለኝ "
ይገርማል ጊዜ ዛሬ ይሄ ሁሉ ትዝታ ሆኗል። እኔም
በአይኖቼ ካስቀረሁት ምስሉ ጋር ዛሬም ድረስ በትዝታዬ ውስጥ እናፍቀዋለሁ።
ይሄ ሁሉ ትዝታ ሆኖ የቀረ ታሪክ የተጀመረው ግን እዚህ ካፌ አሁን ሁለት ጥንጆች ተቀምጠው ከሚያወሩባት መቀመጫ ነበር።
በዚህ መንገድ ማለፍ አልወድም፤ ሆድ ይብሰኛል የፍቅሬን አጭር እድሜ ይበልጡን ያስታውሰኛል ።
ከሄድኩበት የሀሳብ መአበል የአንድ ታክሲ ክላክስ አባነነኝ ፤ ዞሬ ገላመጥኩት ፍቅሬን የነጠቀኝ ይመስል ከትዝታዬ ስላባነነኝ እየተበሳጨኹ ወንበሩንም ካፌውንም በአይኔ እየተሰናበትኩ አይኖቼ ያቀረሩት እንባ ሰው መሀል እንዳይዘረገፍ ዋጥ አድርጌ ወደፊት መንገዴን ቀጠልኩ።
ትዝታዬ ነው በአይኖቼ ምስል ውስጥ የተቀረፀ፤ ትዝታዬ ነው በልቤ ነግሶ የቀረ ፤
አንዳንዴ እንዲህ ነው ፍቅር ቆይታው ያጥርና የትዝታው እድሜ እስከዘመን ያህል ይረዝማል ‼️
ታሪክ ወደኋላ ሲጎተት ከትዝታ በቀር ከቶውንስ ምን አለ? ‼️
💜

(ሚካኤል ኤርሚያስ)
"እጠብቅሻለው"
**
(ሚካኤል ኤርሚያስ)
በቀለመ ቀንዲል ፍቅርሽን ሳማስል
ከዝርጉ ብራና መዉደድን ሳንጓልል
ለአፍታ ሳይደክመኝ አንዴም ሳይሰለቸኝ
እቴ አንቺን እንዳልኩኝ ላንቺ እንደማሰንኩኝ
ጀንበሯ ጠለቀች
ጨረቃ መንገሧን በሰማይ አወጀች
አላፋት ከዋክብት አብረዋት ወገኑ
ስትደሰት ስቀዉ ስታለቅስ አዘኑ
ይሄ ሁላ ሲሆን
የተስፋ ሽዉታ አንዳችም ሳይቃኘኝ
ጨረቃዋ ፀልማ ፀሀይ ወጣችብኝ
ንጋት ተበሰረ
መኖር እንደገና ባንቺ ተቀመረ
....... አንቺ ግን የለሽም ......
....እኔም ተስፋ አልቆርጥም.........
ዳግም እንደገና
በጨረቃ ሹመት ከዋክብቱ ደምቀዉ
እ..ጠ..ብ..ቅ..ሻ..ለ..ዉ ::
ግና ውዴ
አንቺ ስትመጪ ......
ጥቁር የጉም
ብርድ ልብስ ከሰማይ ላይ ይጠልላል
አፈሩ በካፊያ ሽቶ ርሶ አየሩን ያውዳል
ዛፎች እና ቅጠሎች የዛር ዳንኪራ ይረግጣሉ
አበቦች
ባንቺ ፀዳል ፍንጣቂ ዳግም ህይወት ይዘራሉ
አንቺ ስትመጪ
ይብላኝ ለኔ እንጂ
ጨረቃዋስ ጉም ውስጥ ገብታ ትደበቃለች
ፀሀይስ ብትሆን
ልማዷ ነው ስለክብርሽ ታረግዳለች
አንቺ ስትመጪ
ይብላኝ ለኔ...
እንደ በጋ ዝናብ
እንባዬ በወፍራሙ ለሚንጠባጠብ
አቅሌን አቅበዝብዤ ሌት'ና ቀን አንቺን ለማስብ
ህይወት
መንጋጋዋ መሀል ሰልቃ ለምታላምጠኝ
በልቤ ድውድውታ አሀዝ
መምጫ ቀንሽን ለቆጠርኩኝ
ይ ብ ላ ኝ ለ ኔ
ምንም ሆይ
አልገባሽ ብሎ'ንጂ
እንደ ባህር ሞገድ ተስፈን በሚሰቅዝ
በሲቃ እንጉርጉሮ ሌት'ተቀን ምተክዝ
መናገር ሚጨንቀኝ ማድመጥ ሚሰለቸኝ
ባማተረኝ ሁሉ እብድ ነው ያሰኘኝ
አልገባሽም እንጂ
አንቺ የሄድሽ ለታ ያኔ ነው የጀመረኝ
አየሽ.. ያ ኔ..
መለየትሽ እውን ሲሆን ብቻ መቅረቴ ሲመጣ
መኖር ከሚሉት ፅዋዬ እሬት አንቆርቁሬ ስጠጣ
እንደማይቀር የሆነ ቀን መመለስሽ
ያ ፅገሬዳ እንቡጥ መሣይ ከንፈርሽ
ነግሮኝ ነበር ስትስሚኝ ነግሮኝ ነበር ስስምሽ
እናም ....
ያቺ ቀን መቼ ትሆን
ብዬ ልበ ኦናሽን በልቦናዬ ብጠይቀው
ልክ አንደ እለተ ምፀዐት እሱም ቢሆን አላወቀው
ታዲያ ምንም
መምጫ ቀንሽን ጣኦት ልብሽ ካልተረዳው
ምናልባት
ህቃቆቱን እግዜሩ ይሆን የደበቀው ...?
ልጠይቀው ...?
ወይስ ልተው.....?
እንጃ...
ብቻ አንቺ ስትመጪ ....
ይብላኝ ለኔ እንጂ.....
:
#ሚካኤል ኤርሚያስ
"እጠብቅሻለው"
**
(ሚካኤል ኤርሚያስ)
በቀለመ ቀንዲል ፍቅርሽን ሳማስል
ከዝርጉ ብራና መዉደድን ሳንጓልል
ለአፍታ ሳይደክመኝ አንዴም ሳይሰለቸኝ
እቴ አንቺን እንዳልኩኝ ላንቺ እንደማሰንኩኝ
ጀንበሯ ጠለቀች
ጨረቃ መንገሧን በሰማይ አወጀች
አላፋት ከዋክብት አብረዋት ወገኑ
ስትደሰት ስቀዉ ስታለቅስ አዘኑ
ይሄ ሁላ ሲሆን
የተስፋ ሽዉታ አንዳችም ሳይቃኘኝ
ጨረቃዋ ፀልማ ፀሀይ ወጣችብኝ
ንጋት ተበሰረ
መኖር እንደገና ባንቺ ተቀመረ
....... አንቺ ግን የለሽም ......
....እኔም ተስፋ አልቆርጥም.........
ዳግም እንደገና
በጨረቃ ሹመት ከዋክብቱ ደምቀዉ
እ..ጠ..ብ..ቅ..ሻ..ለ..ዉ ::
ግና ውዴ
አንቺ ስትመጪ ......
ጥቁር የጉም
ብርድ ልብስ ከሰማይ ላይ ይጠልላል
አፈሩ በካፊያ ሽቶ ርሶ አየሩን ያውዳል
ዛፎች እና ቅጠሎች የዛር ዳንኪራ ይረግጣሉ
አበቦች
ባንቺ ፀዳል ፍንጣቂ ዳግም ህይወት ይዘራሉ
አንቺ ስትመጪ
ይብላኝ ለኔ እንጂ
ጨረቃዋስ ጉም ውስጥ ገብታ ትደበቃለች
ፀሀይስ ብትሆን
ልማዷ ነው ስለክብርሽ ታረግዳለች
አንቺ ስትመጪ
ይብላኝ ለኔ...
እንደ በጋ ዝናብ
እንባዬ በወፍራሙ ለሚንጠባጠብ
አቅሌን አቅበዝብዤ ሌት'ና ቀን አንቺን ለማስብ
ህይወት
መንጋጋዋ መሀል ሰልቃ ለምታላምጠኝ
በልቤ ድውድውታ አሀዝ
መምጫ ቀንሽን ለቆጠርኩኝ
ይ ብ ላ ኝ ለ ኔ
ምንም ሆይ
አልገባሽ ብሎ'ንጂ
እንደ ባህር ሞገድ ተስፈን በሚሰቅዝ
በሲቃ እንጉርጉሮ ሌት'ተቀን ምተክዝ
መናገር ሚጨንቀኝ ማድመጥ ሚሰለቸኝ
ባማተረኝ ሁሉ እብድ ነው ያሰኘኝ
አልገባሽም እንጂ
አንቺ የሄድሽ ለታ ያኔ ነው የጀመረኝ
አየሽ.. ያ ኔ..
መለየትሽ እውን ሲሆን ብቻ መቅረቴ ሲመጣ
መኖር ከሚሉት ፅዋዬ እሬት አንቆርቁሬ ስጠጣ
እንደማይቀር የሆነ ቀን መመለስሽ
ያ ፅገሬዳ እንቡጥ መሣይ ከንፈርሽ
ነግሮኝ ነበር ስትስሚኝ ነግሮኝ ነበር ስስምሽ
እናም ....
ያቺ ቀን መቼ ትሆን
ብዬ ልበ ኦናሽን በልቦናዬ ብጠይቀው
ልክ አንደ እለተ ምፀዐት እሱም ቢሆን አላወቀው
ታዲያ ምንም
መምጫ ቀንሽን ጣኦት ልብሽ ካልተረዳው
ምናልባት
ህቃቆቱን እግዜሩ ይሆን የደበቀው ...?
ልጠይቀው ...?
ወይስ ልተው.....?
እንጃ...
ብቻ አንቺ ስትመጪ ....
ይብላኝ ለኔ እንጂ.....
:
#ሚካኤል ኤርሚያስ
❤2👍2
#አንቺ እና ግጥም
....(ሚካኤል አስጨናቂ)
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!
....(ሚካኤል አስጨናቂ)
ልማዴ እንዲህ ነው ...
ከጀምበር መግለጥ ጋር
አንቺንና ግጥምን ስንቅ ነው 'ምውለው።
.
#ግጥም ያስጠላኛል!
አንድ ሀሳብ ለመግለፅ መዞር ዙሪያ ጥምጥም
ቃላት ማሰካካት ... ምኑም እኮ አይጥምም።
እወድሻለሁ ለማለት
መመሰል በፀሀይ... ማሞገስ ጨረቃ
እዬዬ ማለት ነው ... ማውረድ ልቅሶ ሲቃ
በቃ !
.
#ግጥም!
ለመግለጥ ቁንጅናን ...
ሰውን ማድረግ መልዐክ...ማጋነን ...መጨመር
መወጠር.. .መቆለል ... ቅኔያት መከመር
ከዚህ ሁሉ ስቃይ
ቁንጅናዋን ነግሮ ወደድኩሽ እያሉ በዝርው መናገር
አይቀልም ማሳጠር?
ስከርቭን ጠምጥሞ ጠቢብ ነኝ እያሉ ጉራ ከመቸርቸር?
እያልኩ አስባለሁ ...
.
አንቺም እንደዚያው ነሽ !
እንደ ግጥም ሁሉ በኔ ትጠያለሽ
ሁሉንም አልወድም ያንቺን ነገራቶች
ጨዋታና ሳቅሽ እንዲሁም ቃላቶች
መስማት ይቀፈኛል የድምፅሽን መውጣት
ቅብጥብጥ ዓመልሽ ይመስለኛል መዓት
ጠጉርሽ ዞማ ቢሆን ቢመስል ፀሀዳ
ከብዶኛል እንደ እዳ!
.
ይብላኝልሽ ላንቺ
ቁንጅና በሚሉት ሰንሰለት ለታሰርሽ
ራስን በመውደድ ኩራት ለተጠመድሽ
እንጂ እኔ ሳይገርመኝ የውበትሽ ግርማ
ጠልቼሽ አለሁኝ
ታምራለች ከሚሉኝ ሰዎች ሳልስማማ ።
.
እያልኩኝ ቢሆንም ...
እንደዚህ ባስብም...
ግጥምን እየጠላሁ መግጠም ግን አልተውም።
.
አንቺም እንደዛው ነሽ
ቅኔ ነሽ ወርቅ ያለሽ
ጠላኋት እያልኩኝ.. .
አደባባይ መሀል ቆሜ ብፎክርም
አንቺን ላለማሰብ ሞልቶልኝ አያውቅም።
.
#ግጥምና አንቺ
አንቺ እና ግጥም
የልክፍት ጥርቅም
አቃጣይ ተብለው እጅን ለመሰብሰብ
ማባያም ተብለው ደርሶ ለመንገብገብ
እንደማይመቹት ...
አዋዜ ፣ ሰናፍጭ ... ዳጣ አይነት ናችሁ
አቃጣይ ቢሆንም ቅመም ነው ፍቅራችሁ
ጠልቼ አልጠላችሁ!
❤2
#ለምን እንደረከስኩ.. . !
(ሚካኤል አስጨናቂ )
በቀልዴ ስትስቂ.. . ፈገግታሽ ሲገለጥ
ለኔ ደስታ የለም ከዚህ ገኖ 'ሚበልጥ
ስትስቂ ግን ድንገት
ሄጄ በሀሳብ ዥረት.. .
ተመልሼ ድሮ.. . አምናና ካቻምና
ከሌላ ወንድ ጋር አብረሽ ነበርሽና
ለሱም ስቃ ነበር ...በቀልዱ ተገርማ
ብዬ አኮርፋለሁ ... ደስታዬ ሲቀማ ።
.
እንዲሁ እንደ ዘበት
አንዳንድ ቀን ድንገት
በአልጋ ላይ ጨዋታ
ነፍሳችን ተረታ ...
አንገትሽ ስር ባለች.. . መዓዛ ሰክሬ
ሸሽቼ ከቅጥሬ.. .
ስቤ በምምገው ... ቃናሽ ሳልረካ
ሌላም ሰው ደርሶታል ይሄ ሽታም ለካ !
የሚል ሞጋች ሀሳብ እያንገበገበኝ
አንቺን አቅፎ ማደር ገላዬን ሸከከኝ።
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ማሽን ያተኮሰው
እኔ የምወደው.. .
የፀጉርሽ ሽታ
ደርሷል ሌላ ቦታ ...
.
ከፍቶሽ ስታነቢ እንባሽ ሲወርድ ቁልቁል
ሌላም ሰው እንደኔ አፅናንቶሻል እኩል
.
መስታወት ፊት ቆመን
የተንጋደደው የሸሚዝ ኮሌታ
ሲቃና በጣትሽ
ትናንት የሌላ ወንድ ኮሌታ ላይ አርፏል
ይሄ የጣት ፍቅርሽ
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ወይን እየጠጣን የተጨዋወትንበት
ይሄ ቦታ ድንገት
ከሌላ ወንድ ጋር በፊት ነበርሽበት ...
.
መውደድን ያየሁት ባንተ ነው ፍቅሬ
የሚል አፅናኝ ወሬ ...
አይደለም የዛሬ
.
ፅጌረዳ መሳይ አበባው ከንፈርሽ
እንቡጥ ሳለ ድሮ ተስሟል ባፍቃሪሽ
.
ይህን ጊዜ ታድያ ...
ካንቺ ኋላ መጥታ ላወኳት ሌላ ሴት
በቅናት በንዴት ...
ቀልዱን አጋርቻት አየሁ የሷን ሀሴት
አንገቷ ስር ገባሁ... ሳብኩት መዓዛዋን
የተከዘች ጊዜ ክንዴ ስር አቅፌ አበስኩኝ እንባዋን
.
ማሽን ያተኮሰው ጡገሯን አሸተትኩኝ
(ሽታሽ ይብልጣታል .. )
ሸሚዜን ላቃና ከሷ ፊት ዘንድ ቆምኩኝ
ጠጣን አብረን ወይን በኔና አንቺ ቦታ
ከንፈሯን ጎረስኩት ካላንዳንች ይሉኝታ
.
ረከስኩ
ረከስኩ
ለሌላ ሴት ወደኩ!
ከክብር ተናነስኩ!
.
ከዛ ግን ተቃናሁ ... በገላዬ ርኩሰት
ዛሬ አንቺን አቅፌ ... እንዲሁ በድንገት
"ሌላ ወንድ አቅፏታል" የሚል ክፉ ሀሳብ
ውስጤን ሲሞግተኝ...
"እኔ ማን ሆኜ ነው የሌላ ሰው ሀጥያት
ቀድሞ የሚታየኝ ?"
የሚል ምላሽ አለኝ!
(ሚካኤል አስጨናቂ )
በቀልዴ ስትስቂ.. . ፈገግታሽ ሲገለጥ
ለኔ ደስታ የለም ከዚህ ገኖ 'ሚበልጥ
ስትስቂ ግን ድንገት
ሄጄ በሀሳብ ዥረት.. .
ተመልሼ ድሮ.. . አምናና ካቻምና
ከሌላ ወንድ ጋር አብረሽ ነበርሽና
ለሱም ስቃ ነበር ...በቀልዱ ተገርማ
ብዬ አኮርፋለሁ ... ደስታዬ ሲቀማ ።
.
እንዲሁ እንደ ዘበት
አንዳንድ ቀን ድንገት
በአልጋ ላይ ጨዋታ
ነፍሳችን ተረታ ...
አንገትሽ ስር ባለች.. . መዓዛ ሰክሬ
ሸሽቼ ከቅጥሬ.. .
ስቤ በምምገው ... ቃናሽ ሳልረካ
ሌላም ሰው ደርሶታል ይሄ ሽታም ለካ !
የሚል ሞጋች ሀሳብ እያንገበገበኝ
አንቺን አቅፎ ማደር ገላዬን ሸከከኝ።
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ማሽን ያተኮሰው
እኔ የምወደው.. .
የፀጉርሽ ሽታ
ደርሷል ሌላ ቦታ ...
.
ከፍቶሽ ስታነቢ እንባሽ ሲወርድ ቁልቁል
ሌላም ሰው እንደኔ አፅናንቶሻል እኩል
.
መስታወት ፊት ቆመን
የተንጋደደው የሸሚዝ ኮሌታ
ሲቃና በጣትሽ
ትናንት የሌላ ወንድ ኮሌታ ላይ አርፏል
ይሄ የጣት ፍቅርሽ
.
ሸከከኝ
ሸከከኝ!
.
ወይን እየጠጣን የተጨዋወትንበት
ይሄ ቦታ ድንገት
ከሌላ ወንድ ጋር በፊት ነበርሽበት ...
.
መውደድን ያየሁት ባንተ ነው ፍቅሬ
የሚል አፅናኝ ወሬ ...
አይደለም የዛሬ
.
ፅጌረዳ መሳይ አበባው ከንፈርሽ
እንቡጥ ሳለ ድሮ ተስሟል ባፍቃሪሽ
.
ይህን ጊዜ ታድያ ...
ካንቺ ኋላ መጥታ ላወኳት ሌላ ሴት
በቅናት በንዴት ...
ቀልዱን አጋርቻት አየሁ የሷን ሀሴት
አንገቷ ስር ገባሁ... ሳብኩት መዓዛዋን
የተከዘች ጊዜ ክንዴ ስር አቅፌ አበስኩኝ እንባዋን
.
ማሽን ያተኮሰው ጡገሯን አሸተትኩኝ
(ሽታሽ ይብልጣታል .. )
ሸሚዜን ላቃና ከሷ ፊት ዘንድ ቆምኩኝ
ጠጣን አብረን ወይን በኔና አንቺ ቦታ
ከንፈሯን ጎረስኩት ካላንዳንች ይሉኝታ
.
ረከስኩ
ረከስኩ
ለሌላ ሴት ወደኩ!
ከክብር ተናነስኩ!
.
ከዛ ግን ተቃናሁ ... በገላዬ ርኩሰት
ዛሬ አንቺን አቅፌ ... እንዲሁ በድንገት
"ሌላ ወንድ አቅፏታል" የሚል ክፉ ሀሳብ
ውስጤን ሲሞግተኝ...
"እኔ ማን ሆኜ ነው የሌላ ሰው ሀጥያት
ቀድሞ የሚታየኝ ?"
የሚል ምላሽ አለኝ!
🔥2
ገራሚ ታሪክ
አንድ ባል አለ እና በየቀኑ ማታ ማታ ከስራ ሲመለስ ሚስቱን ይደበድባታል። ይሄ ድብደባ ምርር ያላት ሚስት ወንድሟን ስለጉዳዩ ነገረችው። ወንድሟም፦ “ጓሮ ካለው ምንጭ ውሃ በጠርሙስ ቀድተሽ አምጪልኝ” አላት። እሷም ቀድታ ይዛለች መጣች። ወንድሟም ለጥቂት ደቂቃ ውሃውን አተኩሮ አየና እንዲህ አላት፡- “ባልሽ ከስራ በገባ በቁጥር ከዚህ ጠርሙስ ትንሽ ጠጪ ነገር ግን ውሃውን ፈጽሞ እንዳትውጪው።”
እሷም እንደተባለችው አደረገች። ባሏም እንደልማዱ ሳይመታት ቡናውን ጠጥቶ አልጋው ላይ እንደ ህፃን ልጅ ጥቅልል ብሎ ተኛ። ሚስት በዚህ በጣም ተገረመች። አንድ ወር ሙሉ በጊዜ ወደቤቱ ይገባል። አይመታት አይጨቃጨቃትም። በሰላም አውርቷት እራቱን በልቶ ይተኛል። ነገር ግን ባሏ በገባ ቁጥር በየቀኑ አፏ ላይ የምትይዘው ውሃ ከጠርሙሱ አለቀ። ይሄኔ ወደ ወንድሟ ጋር ተመልሳ፦“ሌላ የውሃ ጠርሙስ እፈልጋለሁ። እና ደግሞ እባክህ በእናትችን ይዥሃለሁ ንገረኝ፤ ከምንጭ የቀዳውት ውሃ ምን አይነት መለኮታዊ ምስጥር ነው ያለው?”
የእህቱን አመል የሚያውቀው ወንድም ተረጋግቶ መለሰላት፦“ምንም የመለኮት ሆነ የመተት ሚስጥር የለውም። ባልሽ ደክሞት ከስራ ወደቤት ሲገባ ቢያንስ ዝም በማለት አፍሽን(ምላስሽን) ጠብቂ!” 🤲🏼 🤐
ስለሚያስተምር ደገምኩት

❤1
፠፠የእልሜ፠፠
በህልም አለም ጉዞ እየተገላበጥኩ ፤
ክንዴ ላይ ተኝታ ስፈልጋት አደርኩ ።
እንደ ልማዱ መሽቶ ልተኛ ነው ዛሬ ፤
የህልሜ ጓደኛ ካአንቺው ነው አዳሬ ፤
ምን መሄጃ አለኝ በፍቅርሽ ታስሬ ፤
የማወራው ሁሉ ስለአንቺ ነው ወሬ ፤
በህልሜ እንዳትቀሪ የምወድሽ ፍቅሬ።
{{{{{{{➍☞}}}}}}}
come back
በህልም አለም ጉዞ እየተገላበጥኩ ፤
ክንዴ ላይ ተኝታ ስፈልጋት አደርኩ ።
እንደ ልማዱ መሽቶ ልተኛ ነው ዛሬ ፤
የህልሜ ጓደኛ ካአንቺው ነው አዳሬ ፤
ምን መሄጃ አለኝ በፍቅርሽ ታስሬ ፤
የማወራው ሁሉ ስለአንቺ ነው ወሬ ፤
በህልሜ እንዳትቀሪ የምወድሽ ፍቅሬ።
{{{{{{{➍☞}}}}}}}
come back
👍1
#ምክር_ከሉቅማን_ለልጁ
#ልጄ_ሆይ 👉ጥበብ (እውቀት) ምስኪኖችን የነገስታት ደረጃ አድርሳለች፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉አደራህን በብድር ላይ ብድር የቀን ውርደት የማታ ጭንቀት ነው ፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉የማይረዳን ከማስረዳት ቋጥኝን ከቦታው ማንሳት ይቀላል ፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉ባወከው ነገር እስከምትሰራ ያላወከውን አትማር ፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉መጥፎ ጎረቤት ከከባድ ብረት በላይ ይከብዳል መራራነገሮችን ሁሉ ቀምሻለሁ ከድህነት በላይ መራራ ነገር አልቀመስኩም፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉አንድን ሰው ወንድም ለማድረግ ከፈለክ መጀመሪያ አስቆጣው በቁጣው ጊዜ ካለፍክ …ካልሆነ ተጠንቀቀው ፡፡
#ልጄ_ሆይ 👉በሰው ቤት ውስጥ ከሆንክ አይንህን ጠብቅ፤ በስብስብ መካከል ከሆንክ ምላስክን ጠብቅ ፤ በሰላት ውስጥ ስትሆን ልብህን ጠብቅ ፡፡
በእናንተ ፍላጎት #ይቀጥላል
#እንቀጥል ??

🔥1
በፍለጋ
በፊት እንደቀላል አይቼ እንደዋዛ ፤
ማንም ያልከፈተው ልቧን ለኔ ይዛ ።
ከላይ በተሰጣት የማፍቀርን ፀጋ ፤
የሷን ድርሻ አጉድላ የኔን ሙሉ አድርጋ።
የፍቅር አቦጊዳ ፊደል አስቆጥራኝ ፤
ሊያውም ፍቅርን ሆና አፍቅራ አሳይታኝ ፤
ሙሉ አፍቃሪ አድርጋኝ ድንግል ልቧን ከፍታ ኑርበት ባለችኝ።
እኔ የፍቅሯ ምሩቅ እኔ የሷ ተማሪ ፤
ማፍቀር ቻልኩኝና ልሆን አስተማሪ ።
ሁሉንም አውቄ ሙሉ አፍቃሪ ስሆን፤
ህሊናዬን ስቼ ገፋሁ ንፁህ ፍቅሯን።
ወጣሁኝ ፍለጋ ተማሪ ናፍቄ ፤
መሰረቴን ትቼ መነሻዬን ርቄ።
ብ...ዞ...ር ብ...ዞ...ር ብ...ዞ...ር በፍለጋ ብ..ጦ..ዝ ብ..ጦ..ዝ ብ..ጦ..ዝ ፤
የሚሰርቀው እንጂ በአፍዝ አደንግዝ ፤
ልብ የሚሰጥ አጣው ቀርቦ እኔን እሚያግዝ፡፡
ወይ የቀን ጎደሎ አወይ ስህተት ክፉ! ፤
የፊት እርምጃዬ ድካም ሆኖ ትርፉ! ።
እንደው የሞት ሞቴን ሀፍረቴን ከልዬ ፤
ድንገት ፊቴን ባዞር ክብሬን የትም ጥዬ።
በረገጥኳት ዱካ ሮጣ በእርምጃዬ ፤
ፍቅር አስተማሪዬ ስህተቴን ስታርም አለች ከጀርባዬ ።
እዛው ድርቅ! እንደመታው መብረቅ... ምን አንደበት አለኝ ምን ቃል ካፌ ይውጣ ፤
ፀፀት እንደ ሰማይ ከፊቴ ተጋርጣ ።
በንስሀ እንባ ታጥቦ የማይፀዳ ፤
ይኸው በገዛ እጄ ለዘልአለም ፀፀት ሆንኩለት ባለዳ ።
(ስ ነኝ ከ...)

አንዲት ሴት ፕሮፈሰር ስለ "አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶችን ማግባት" በተሰኘ አርእስት በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ሴቶች እና ወንዶች ገለፃ እንድታደርግ ትጋበዛለች።
ፕሮፈሰሯ የተጠቀሰውን አርእስት ገለፃ ለማድረግ እራሷ ነበረ የመረጠችው።
ፕሮፈሰሯ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ ለሴት ልጅ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር አስረዳች።
ሴቶችም ይህን የጋብቻ ልምድ ተቀብለው ቢፈፅሙት ያለውን ጠቀሜታ አስተማረች።
ጥቅሙ ለእራሷ ለሴቷ እንደሆነና መቃወም እንደሌለባት አዳራሽ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች አስረግጣ ገለፃ አደረገች።
በአዳራሹ የፕሮፈሰሯን ገለፃ ስትከታተል የነበረች አንዲት ሴት እጇን አውጥታ ለፕሮፈሰሯ እንዲህ በማለት አስትያየት ትሰጣለች ።
"በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ ስላደረግሽልን አመሰገናለሁ!"
"ከባለቤትሽ ጋር አንቺ ሳታውቂ ፣ አብረሸው እያለሽ ከተጋባን አሁን አራት አመታችን ነው ፣ መንታ ልጆችም አለን አለቻት።"
ፕሮፌሰሯ ከሴትየዋ ይህንን ስትሰማ በአዳራሹ ውስጥ እራሷን ስታ ወደቀች ፣ሆስፒታልም ተወሰደች።
ፕሮፌሰሯ ሆስፒታል ከአልጋ ላይ ሆና ስትነቃ ያቺ አዳራሽ ውስጥ አስተያየት የሰጣቻት ሴት ከአልጋዋ አጠገብ ሆና አየቻት ።
ሴትየዋ ለፕሮፌሰሯ እንዲህ አለቻት:-
"ባለቤትሽን እንኳን ላገባው በአይኔም አይቼው አላውቅውም ይህን ያልኩት ልፈትንሽ ነበረ፤ ፈተናውን ወድቀሻል።"
"ለሌላ ግዜ ስለ አንድ አስተሳሰብ ተቀበሉና አድርጉት ብለሽ ሌሎችን ስታስተምሪ ፣መጀመሪያ አንቺ ራስሽ አምነሽና ፣ ተቀብለሽ መሆን አለበት" በማለት ለፕሮፈሰሯ ነገረቻት።

ብርጭቆው ከባድ ነው ወይስ ቀላል?
አንድ አሰልጣኝ እንዲህ ሲል ለሰልጣኞቹ በመጠየቅ አንዲትን ቀላል የምትመስል፣ ነገር ግን እጅግ ወሳኝ ቁምነገር አስተላለፈ፡- “አንድ ብርጭቆ ውሃ በእጃችሁ ብትይዙት ከባድ ነው ወይስ ቀላል?”
ሁላችንም እንደምንጠብቀው ሰልጣኞቹ በአብዛኛው ቀላል እንደሆነ በመስማማት ገለጹ፡፡ አሰልጣኙም በመመለስ፣ “መልሳችሁ ትክክልም፣ ስህተትም ነው” በማለት ሲያብራራ፣ “ይህንን ውኃ የተሞላ ብርጭቆ ለአንድ ደቂቃ ከያዛችሁት ቀላል ነው፡፡ ለአንድ ሰዓት ከያዛችሁት ደግሞ እየከበዳችሁ ይሄድና እጃችሁን የሕመም ስሜት ሊሰማችሁ ይችላል፡፡ ነገር ግን አንድ ቀን ሙሉ ከያዛችሁት እጃችሁ ይደነዝዛል፣ ይዝላል፣ እንዲያውም ብርጭቆውን ልትለቁት እስከምትደርሱ ድረስ ልትደክሙና ሊከብዳችሁ ሁሉ ትችላላችሁ”፡፡
መልእክቱ ይሄ ነው፡- የዚህ ብርጭቆ ክብደት ልክ በመጀመሪያ እንደነበረ፣ ከአንድ ደቂቃ በኋላ፣ ከአንድ ሰዓት በኋላና፣ ከአንድ ቀን በኋላ ያው ነው፡፡ እዚህ ጋር ልዩነት ያመጣው ብርጭቆውን በእጃችን የያዝንበት የጊዜ ርዝመት ነው፡፡ የስሜትም ጉዳይ እንዲሁ ነው!
ማንኛውም እንደ ጭንቀት፣ መረበሽና ፍርሃት የመሳሰለ ቀላል የተባለ የስሜት ሁኔታ ለጊዜው ምንም ችግር ላይኖረው ይችላል፣ ሆኖም ስሜቱን ለረጅም ጊዜ ስንይዘው ግን መዛላችን፣ መድከማችን፣ መታመማችንና ሕይወት ከአቅማችን በላይ እየሆነ መምጣቱ አይቀርም፡፡
ምናልባት የመኖር ጣእም ያጣችሁት፣ ድብርት የሚጫጫናችሁና የውስጥ (የስሜት) ህመም የሚሰማችሁ አንዳንድ ስሜቶችን ለረጅም ጊዜ እየያዛችሁ ሊሆን ይችላልና አላስፈላጊ ስሜቶችን ገና በትንሽነታቸው ቶሎ ቶሎ ለማራገፍ ሞክሩ!
ተጨማሪ ምክሮች
1. ቢቻል ስሜታዊ ከሚደርጓችሁ አካባቢዎች ለመራቅ ሞክሩ
2. ቢቻል በስሜታችሁ ላይ ጫና ከሚደርጉ ሰዎች ጋር ያላችሁን ንክኪ ቀንሱ
3. ቢቻል ምንም ነገር ብትነግሩት የማይንቃችሁና የማይፈርድባችሁ ወዳጅ ጎናችሁ በማድረግ ስሜታዊ ያደረጋችሁን ነገር አዋዩት
4. በተቻችሁ መጠን ስሜታዊ የሚያደርጓችሁን ሃሳቦች በአዎንታዊ ሃሳቦች ለመቀየር የራስ በራስ ቋንቋን ልመዱ
© ዶክተር እዮብ ማሞ
ከመፅሐፍት አለም
#share

የውሸት ተስፋ
✍️ ዮናታን በጋሻው
ተስፋ ለሕይወት ትርጉም ይሰጣል። ግን ሁልጊዜ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ተስፋ ሰዎችን ዝም ለማሰኘት ይጠቅማል። ከመናገር ይልቅ እንዲጠብቁ ለማድረግ። ከመቃወም ይልቅ እንዲጸኑ ለማድረግ ይውላል።
በብዙ ሥርዓቶች ተስፋ ስጦታ አይደለም፤ ማሰሪያ ነው።
ሰዎች “የተሻሉ ቀናት እየመጡ ነው” ተብለዋል። "እግዚአብሔር ያስተካክለዋል" ተብለዋል። "ጠንካራ ሆነህ ከቆየህ ገሮች ይለወጣሉ" ተብለዋል። ግን በደል እንደቀጠለ ነው። ድህነት ቀጥሏል። ዝምታው ቀጥሏል። በስልጣን ላይ ያሉት ደግሞ በስልጣን ላይ እንዳሉ ናቸው።
የውሸት ተስፋ ሰዎች ዛሬ ላይ ያለውን እውነት እንዳይመለከቱ ያውራቸዋል። መከራን እንደ ፈተና እንጂ ችግር አድርጎ አያሳይም። ህመምን እንደ ቅዱስ እና ጥርጣሬን እንደ አደገኛ ነገር አድርጎ ይስላል።
ኃይማኖቶች ስቃይ የአንድ ትልቅ እቅድ አካል ነው ሲሉ ይደመጣሉ ግን ያንን እቅድ በጭራሽ አያብራሩትም። መንግስታት ለፍትሃዊነት ቃል ይገባሉ ነገር ግን ለበርካታ አስርት ዓመታት ያዘገዩታል።
እና አፈታሪክ፣ ተረት በዚህ አፈና ውስጥ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ታዛዥነትን ክቡር የሚያስመስሉ ታሪኮችን ይናገራሉ። ሰዎች እንደ ጀግኖች እንዲጸኑ ያስተምራል— ፅናት ስለሚረዳቸው ግን አይደለም ስርዓቱን እንዲቀጥል ስለሚያደርግ እንጂ።
ፓንዶራ ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ናት። አማልክቱ ሰዎችን ለመቅጣት ባሰቡ ጊዜ ጥፋቱን የሚያላክኩባት ሴት ፈጠሩ እና “አሁንም ተስፋ አለ” አሉ። ነገር ግን ያ ተስፋ የመጣው ከህመም በኋላ ነው። እና ፈውስን ፈጽሞ ቃል አልገባም። ሰዎችን እንዲቀጥሉ ብቻ አድርጓል።
ስለዚህ ጥያቄው: ተስፋ እንድንኖር የሚረዳን መቼ ነው እና መቼ ከእንድናንቀላፋ የሚያደርገን?
መልሱ አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም እውነተኛ ተስፋ ታዛቢ አያደርገንም። ወደ ተግባር ይገፋፋናል። በግልጽ ለማየት እና ለመናገር ድፍረት ይሆነናል። የውሸት ተስፋ “ቆይ ዝም በል” ይላል። እውነተኛ ተስፋ ግን “ተመልከት፣ አስተውል እና ተንቀሳቀስ” ይላል።
የእናንተ ተስፋ ጠባቂ ነው ወይስ ታጋይ ያደረጋችሁ? ራሳችሁን ጠይቁ!!!