Higher Mission Ministries (HMM)
140 subscribers
32 photos
6 links
This is the official channel of higher mission ministries. On this channel you will get motivation, idea about life purpose and missions. follow us for more insights on Life purpose. we will share timely news and informations too.
Download Telegram
ከተመካን አይቀር በድካማችን

“እርሱ ግን፣ '#ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና' አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ። ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በመከራ፣ በስደትና በጭንቀት ደስ የምሠኘው ለዚህ ነው፤ ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።”
2 ቆሮንቶስ 12:9-10 NASV

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከላይ ‌እርሱ ስለራሱ እንደማይመካ ያትትና ትምክቱን ለመግታት ጌታ እንደሚጠቀምበት ስለሚያምነው የስጋ መውጊያው ይናገራል፡፡ ጌታም ሁሌ #ጸጋዬ ይበቃሃል እንዲሁም ሀይሌ በድካምህ ጎልቶ ይታያል እንደሚለው በማከል ከድካሙ በቀር እንደማይመካ ይናገራል፡፡

ሐዋሪያው ጥሩ ሃላብ ያነሳል ብመካ ብዙ ትምክህት እንዳለው እና በባዶ እንዳልሆነ፤ ነገር ግን ይህ የግሉ ሳይሆን #የጸጋው ስራ ስለሆነ ሰዎች በእሱ እንዲያውቁት እንደማይፈልግ፡፡ ሊታይ የሚገባው እርሱ ሳይሆን ጌታ እንደሆነ ያምናል፡፡
ከጳውሎስ የምንማረው ምንድን ነው? #በጸጋ ምንም ነገር ማደረግ እንችላለን፤ ብዙ የምንመካባቸው ታሪኮችም ልኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በእነዚህ #የጸጋው ጀብዶች ራሳችን ልንወደስ አይገባም፤ ሰዎች በጭራሽ በእሱ ሊያውቁን አይገባም፡፡ ይልቁንም እንደእኛነታችንና እንደሰው ወይም እንደደካማነታችን ሊያውቁን ይገባል፡፡ የእኛ ማንነት #ከጸጋው አገልግሎት ውጭ ያለው የግል ህይወታችን ነው፡፡ #ጸጋ ስጦታችን እንጂ ማንነታችን አይደለም፡፡

ሌላው #ከጸጋ ጋር ጎን ለጎን መታየት አንችልም፤ ወይ ራሳችንን ደብቀን #ጸጋውን እናሳያለን ወይም #ጸጋውን ደብቀን ራሳችንን እናሳያለን፡፡ አንዱ ሲጎላ ሌላው ይደበዝዛል(inversely proportional)፡፡ ስለዚህ ማንን ነው ማሳየት ያለብን? ራሳችንን ወይንስ #ጸጋውን? ጌታ ጻውሎስን እንዳለው ሃይሉ ፍጹም የሚሆነው ወይም ጸጋው የሚደምቀው እኛ ስንደበዝዝ ነው፡፡ ለእኛ በእርሱ በኩል መታወቅ የእርሱ መሆን ብቻ ይበቃናል፡፡ በራሳችን ለመታወቅ ወይም ለመጉላት በወደድን መጠን 'እርሱ ልልቅ እኔ ደግሞ ላንስ ይገባል' የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል መቃወም ይሆንብናል፡፡ እንደ አባቶቻችን እርሱን አተልቀን እእኛ ስናንስ የዚያን ጊዜ ይከናውንልናል፡፡ ሰዎች በክርስቶስ ስለሚያውቁን በዚያን ጊዜ ይበልጥ እንታወቃለን፡፡

በመጨረሻም ትምክህታችን ስለድካማችን (በእኛ በደካሞቹ ስለተሰራው ስራ እንዲሁም በደከምን ጊዜ በእኛ ታላላቅ ስራ ስለሰራው #ጸጋ) ሊሆን ይገባል፡፡ ደካማ ባንሆን ሃይሉ በሙላት አይገለጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ድካማችን #የጸጋውን ሃይል ፍፃሜ ስለገለጠ በድካማችን ስንመካ ክርስቶስን እናከብረዋለን/ እናልቀዋለን፡፡ ለዚህ እንድንተጋ #ጸጋው ይርዳን፡፡

ተባረኩ!
#የእለት_ስንቅ
#discipleship_inspirational #daily_pasture
#discipleship_motivations
#higher_missions
#hmm
👍1
እረፉ፣ እረፍት

“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
መዝሙር 46:10 NASV

በዚህ ክፍል ‘እረፉ’ ለሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የእብራይስጥ ቃል “ራፋህ” የሚለው ሲሆን ጥሬ ትርጉሙ ጥረት ማቆም፣ መተው፣ መልቀቅ ወይም መረጋጋት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ይህ መዝሙር የተጻፈው በጦርነት ጊዜ ይመስላል፤ መልእክቱም በራሳችሁ መጣጣር ተዉ፤ አይናችሁን ከሁኔታዎች ላይ ወደ እኔ አንሱና የእኔን መበዠት፣ የእኔን ሉአላዊነትና ልእልና እዩ የሚል ነበር። ይህ ክፍል በዘጸ 14 ላይ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ እንዲያርፉና እግዚአብሔር የሚያደርግላቸውን ማዳን እንዲያዩ ከአደረገው ጥሪ ጋር ተመሳሳይ ነው። በጦርነት ሰዓት ከሆነ የተጻፈው ይህ መዝሙር እግዚአብሔር ጦርነቱን ወይም የጦር ዝግጅቱን እንዲያቆሙ፣ ይልቁንም ከእርሱ ጋር ያለው አምላክ እርሱ በህዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ ያለ እንደሆነ እንዲያዩ ይጠይቃቸዋል።

ከዚህ ክፍል ምን ልንማር እንችላለን? በህይወት ስንኖር በችግር ወይም በተግዳሮት ውስጥ ስንሆን በቀላሉ እንሸበራለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እረፉ እኔ አምላካችሁ ከእናንተ ጎን እንዳለሁ እወቁ እኔም ሁሉንም ነገር ትክክል አደርጋለሁ ይለናል። ይሄ እርፍት ከጥረት፣ ከትግል እንዲሁም ከፍርሃት ወይም ከመሸበር የምናደርገው እረፍት ነው፤ ይህንን እረፍት ብንለማመድ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን ይጨምራል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ላይ መታመን በተግባር እንጂ በቃል የሚገለጽ አይደለም። እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው አምላክ እርሱ የእኛ አምላክ መሆኑን የሚናየው የራሳችንን ጥረት ትተን በእርሱ ብርቱ ክንድ ብቻ ሁኔታውን ስናልፍ ነው። አለበለዚያ የእኛ ጥረት ካለበት መረዳታችን (እውቀታችን) ሙሉ አይሆንም። ጸጋው ይርዳን!
1🙏1
አይዟችሁ

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
ዮሐንስ 16:33 NASV

ከላይ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደማያዩት ግን ደግሞ ጥቂት ቆይቶ እንደሚያዩት (ስለሞት እና ትንሳኤው) ሲነግራቸው ደቀ መዛሙርቱ በዚህ አባባሉ ግራ ተጋብተው ኣናገኛለን። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ንግግሩን በደምብ አብራራላቸው፤ አመኑትም። ከዚያም ሁላቸውም ትተውት እንደሚበተኑ በመናገር ይህን ሁሉ እየነገራቸው ያለው እንዲፈሩ ሳይሆን ሰላም እንዲኖራቸው እንደሆነ ይገልጻል። በዚህ ክቁጥር ደግሞ በአለም እስካሉ ድረስ መከራ እንዳለባቸው ነገር ግን እርሱ አለምን እንዳሸነፈ በማስታወስ ደግሞ ያጽናናቸዋል።

በጊዜው ለነበረ ሰው ይሄ ግራ የሚያጋባ ነገር ሊሆን ይችላል። ስለሚያስፈራ ነገር እየነገረ እንዳትፈሩ ነው እንዴት ይላል? አዎ በጊዜው ኢየሱስ ከእነርሱ አልተለየም መከራም ገና አልደረሰበትም ነበር፤ ይህ ማለት ደግሞ ኢየሱስ ሊሆን ያለውን ትንቢት እየተናገረ ነበር። ጊዜው ሲደርስ እና ትንቢቱ ሲፈጸም እንግዳ ስለማይሆንባቸው አይፈሩም ካልፈሩ ሰላም ይኖራቸውል። ኢየሱስ ስለዚህ የውስጥ(የልብ) ሰላም ነው እያወራ ያለው።

በሁለተኛው ማሳሰቢያም በተመሳሳይ ሊሆን ስላለው ነገር እያወራ ነው። ኢየሱስ በጊዜው ሞቶ አልተነሳም ነበር ደቀ መዛሙርቱም መከራ አልደረሰባቸውም ነበር። ንገር ግን ኢየሱስ ወደፊት እርሱ ትቷቸው ሲሄድ የሚደርስባቸውን መከራ ይነግራቸዋል። እርሱ አለምን ያሸነፈ እንዲሁም በሰማይና በሚድር ስልጣን የተሰጠው አምላክ በኋላ በማቴ 28:30 ከእነርሱ ጋር እስከ አለም ፍጻሜ እንደሚሆን ቃል ስለሚገባላቸው የእርሱ አለምን ማሸነፍ ጊዜው ሲደርስ ትርጉም ያለው መጽናናት ይሆናቸዋል።

ከዚህ ምን ልንማምር እንችላለን? በአለም ሳለን መከራ አለብን ነገር ግን አለምን ያሸነፈው አምላክ ደግሞ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ስለሆነ መከራውን በድል እናልፈዋለን። ዳዊት በመዝሙር 23 “በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳን አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንህ ክፉን አልፈራም” እንዳለው፣ እኛም በመከራ ውስጥ ብናልፍ እንኳን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና መከራን አንፈራም። ምክንያቱም አለምን እና በእሷ ያለውን መከራ ያሸነፈው እርሱ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ስለሆነ እኛም መቼም አንፈራም፣ ሁልጊዜ ሰላም ይኖረናል።
ሰላሜን እሰጣችኋለሁ

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።”
ዮሐንስ 14:27 NASV

* በጣም የምትወዱት ሁሌም የሚመራችሁ ለሁሉም ነገር ወደርሱ ትሮጡ የነበረ የደስታችሁ ምንጭ የሆነ ሰው ሊለያችሁ እንደሆነ ስታውቁ ምን ይሰማችኋል?

በመጀመሪያ የት ነው የሚሄደው? እንዴትስ ነው የምንከተለው? ካልተከተልነውስ እንዴት ነው የምንሆነው? ህይወታችንስ እንዴት ይሆናል? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ይመጣሉ፡፡ መልስ ካለገኙ ደግሞ ጭንቀት ይመጣል፡፡ ጭንቀት ደግሞ ሰላማችንን ያደፈርሰዋል/ ያጠፋዋል፡፡ በዚህ ክፍለ ምንባብ የተፈጠረው ይሄው ነበር፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ የመጨረሻ/ ultimate ማጽናኛ የሆነውን የተስፋ ቃል ተጠቀመ፡፡ ብቻችሁን አልተዋችሁም፤ ይልቁንም አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን እንዲሁም ሰላምን እተውላቸዋለሁ እርሱም የራሴን ሰላም እሰጣችኋለሁ አላቸው፡፡

የኢየሱስን ሰላም ለሚያውቅ ይህ ታላቅ የተስፋ ቃል ነው፡፡ ተገፍቶ ወደ ገደል አፋፍ እየተወሰደ የነበረው ሰላም, ባህሩ ስናወጥ ሁሉም ሰው ተስፋ ቆርጦ እያለ የነበረው ሰላም, እናም ሁሌም በፊቱ ላይ የሚታየው ሰላም፡፡ ተስፋቸው ተሟጦ ነበር፤ ነገር ግን በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ ስለነገ ሲያስቡ በሚመጣው ጭንቀት ውስጥ እያሉ ይህን ሰላም ሊሰጣቸው ቃል ገባላቸው፡፡

ግሩም የሆነ ተስፋ፤ ኢየሱስ የራሱን ሰላም እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ ነገር ግን በሚያጭንቅ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ማስታወስ ልከብደን ይችላል፡፡ የእነርሱ ግራ መጋባት ነገን ባለማወቃቸው ሲሆን ኢየሱስ ደግሞ ነገን እንዲሁም ከነገ በኋላ ሊሆን ያለውን ያውቅ ነበር፡፡ ስለዚህ በዛሬ ግንብ ስንገደብ ነገን እና ከዚያ በኋላ ያለውንም የሚያውቅ የራሱን ሰላም እሱም አዕምሮን የሚያልፍ የልብ ሰላም ሰጥቶናል፤ በዚህ ተጽናኑ፡፡

ሁልጊዜም በእንደዚህ አይነት የጨለመ ምንም ብርሃን/ ተስፋ የማይታይበት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ይህን ማሰብ ወይም ማስታወስ ሊቸግረን ይችላል፡፡ በመሆኑም እንዲህ ብለን እንጸለይ ''ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሰላምህን ሰጥተሄኛል አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር በጨለመበት ምንም ተስፋ በሌለበት ሁኔታ ላይ ነኝ፡፡ አንተ ነገዬን የሚታውቀው አምላክ በአንተ እታመናለሁ፡፡ አጽናኙ መንፈስህ ያጽናናኝ፤ በአንተ መታመን እና ከአድማስ ባሻገር ያለውን የነገን ተስፋን ማየት እንድችል ይርዳኝ፡፡''
#daily_pasture
#discipleship_motivations
#higher_missions
#hmm
4
“ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤”
ማቴዎስ 28:19 NASV

ይሄ ነው የተጠራንለት፤ ከአማኝነት የላቀው ተልዕኮ፡፡
#higher_missions
#discipleship_motivations
3
“የእግዚአብሔርን ቃል የነገሯችሁን መሪዎቻችሁን አስቡ፤ የኑሯቸውን ፍሬ ተመልከቱ፤ በእምነታቸውም ምሰሏቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።”
ዕብራውያን 13:7-8 NASV

የዕብራውያን ጸሃፊ የእግዚአብሔር ቃል ያስተማሯችሁን ሰዎች እነርሱ ክርስቶስን እንደሚመስሉ (የማይመስሉትን አይጨምርም) ምሰሏቸው(ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደሚመስል እነን ምሰሉኝ እንዳለው ማለት ነው) ፡፡ ክርስቶስ ትላንትም ዛሬም ያው ነው፤ አልተቀየረም ለዘላለምም አይቀየርም፡፡ ክርስቶስ ሌላ መገለጫ የለውም አንደውኑ እስከዘላለም ተገልጧል እያለን ነው፡፡
4
ከእኔ የተማራችሁትን ማንኛውንም ነገር አድርጉ

“ከእኔ የተማራችሁትን ወይም የተቀበላችሁትን፣ የሰማችሁትን ወይም ያያችሁትን ማንኛውንም ነገር አድርጉ፤ የሰላም አምላክም ከእናንተ ጋራ ይሆናል።”
ፊልጵስዩስ 4:9 NASV

ጳውሎስ ይህንን ያለው የፊልጵስዩስ መልክት ስጨርስ አከባቢ ነው፡፡ እንግድህ እርሱ ሲያደርግ የነበረውን ሁሉንም፤ ማለትም መድረክ ላይም ከመድረግ ውጭም ያደረገውን በሙሉ አድርጉ እያላቸው ነው፡፡

ጥያቄው እኛስ ዛሬ እንደ ጳውሎስ እንደዚህ በድፍረት ከእኔ ያያችሁትን ማንኛውንም ነገር አድረጉ የማለት ድፍረቱ አለን ወይ ነው? መቸም ጳውሎስ እንደእኛ ሰው ነው፤ ነገር ግን እንደዚህ በድፍረት የሚናገረው በትክክል የክርስቶስ ደቀ መዝሙር ስለሆነ ነው፡፡ በዚህም እርግጠኛ ነው፡፡

ይሄ ለእኛ ጥሩ challenge ነው፡፡ ለምንመራቸው ሰዎች ክርስቶስን ወይም ጳውሎስን ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለን ገጸባህሪ ሳይሆን እራሳችንን ነው ማሳየት ያለብን፡፡ እኔ እንደማደርገው አድርጉ፤ እንደ እኔ ሁኑ ነው ማለት ያለብን፡፡

ዛሬ ከጳውሎስ ህይወት የምንማረው ደቀ መዝሙር ሆነን ደቀ መዝሙር ማድረግ እንደሚገባን ነው፡፡ ደቀ መዝሙር የምናደርገው ደግሞ በማውራት ብቻ ሳይሆን አድርጎ በማሳየት ጭምር ነው፡፡

ይህንን ምሳሌ እንድንከተል ጸጋው ያስፈልገናል፤ የእግዚአብሔር ጸጋ ይብዛልን፡፡
“በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል። እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።
መዝሙር 91:1-2 NASV
#discipleship_motivations #higher_missions
#daily_pasture
#የእለት_ስንቅ
“ለእኔ፣ መኖር ክርስቶስ ነው፤ ሞትም ማትረፍ ነው።”
ፊልጵስዩስ 1:21 NASV

ይላል የክርስቶስ ደቀመዝሙር የሆነ ሰው፡፡
#discipleship_motivations
#higher_missions
“በዚህ ጊዜ አንቺ ዝም ብትዪ፣ ለአይሁድ ርዳታና ትድግና ከሌላ ስፍራ ይመጣላቸዋል፤ አንቺና የአባትሽ ቤት ግን ትጠፋላችሁ፤ ደግሞስ አንቺ ንግሥት ለመሆን የበቃሽው ለዚህ ጊዜ እንደ ሆነ ማን ያውቃል?””
አስቴር 4:14 NASV
ዛሬ ያለንበት ቦታ ያለነው ለምንድን ነው? እግዚአብሔር ለሆነ አላማ አስቀምጦን ይሆን ብለን አስበን እናውቃለን? የጌታ ደቀመዝሙር የሆነ ሰው እንዲህ ያስባል፡፡
#discipleship_motivations
#higher_mission
#daily_pasture
ቃል

“በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። እርሱም በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋራ ነበረ። ሁሉ ነገር በርሱ ተፈጥሯል፤ ከተፈጠረው ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም። ሕይወት በርሱ ነበረች፤ ይህች ሕይወት የሰው ብርሃን ነበረች።”
ዮሐንስ 1:1-4 NASV
ይህ ቃል ወደ ዘፍጥረት አንድ ይጠቁመናል፡፡ በዚያ ምዕራፍ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ከሰው ውጭ በቃሉ(በክርስቶስ) ነው የሰራው፡፡ እርሱ ቃል እራሱ የሰው ብርሃን ነበር ይለናል ዮሐንስ፤ ይህ ማለት በእርሱ በክርስቶስ የሄደ ብቻ ወደ እውነት ወይም ቀጥተኛው (orthodox) ህይወት መድረስ ይችላል ማለት ነው፡፡ ከእርሱ ውጭ ብርሃን የለም ብርሃን ከሌለ መድረሻ የለም እያለን ነው ሐዋርያው፡፡
በእርሱ ብርሃን ተመርተን ከዘላለም ህይወት መድረስ እንድንችል ፀጋው ይርዳን፡፡
#higher_mission
#daily_pasture
#discipleship_motivations
“በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።”
1 ቆሮንቶስ 10 : 13 NASV

“The temptations in your life are no different from what others experience. And God is faithful. He will not allow the temptation to be more than you can stand. When you are tempted, he will show you a way out so that you can endure.”
1 Corinthians 10 : 13 NLT
#discipleship_motivations
#higher_mission
#daily_pasture
“እንደማያፍርና የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያስረዳ የተመሰከረለት ሠራተኛ፣ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ልታቀርብ ትጋ። እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ ራቅ፤ በዚህ ነገር የተጠመዱ ሰዎች ከእግዚአብሔር እየራቁ ይሄዳሉና።”
2 ጢሞቴዎስ 2:15-16 NASV
ጵውሎስ እራስን ለእግዚአብሔር ስለማቅረብ ሮማውያንን ራሳቸውን እንዲያቀርቡ ሲያሳስባቸው ነበር። አሁን ደግሞ ጥሞተዎስን በተመሳሳይ እንደተመሰከረለት የቅሉ ሰባኪ ራሱን ለእግዚአብሔር እንዲያቀርብ፣ ወይም ራሱን እንከን የሌለበት ለማድረግ እንዲሰራ ያሳስበዋል። እርሱም እንዴት እንደሚቻል ሲያስረዳ እግዚአብሔርን ከማያስከብር ንግግር ራሱን በማራቅ ቁጥብ በመሆን እንደሆነ ያረጋግጥለታል። በነገራችን ላይ የተመሰከረለት ሲል በሰዎች የተመሰከረለት ነው እያለ ያለው።

እኛስ ዛሬ ቁጥብ ህይወት በመምራት እንደተመሰከረለት ሰራተኛ ራሳችንን እያቀረብን ነው፡፡ ይሄ አቀራረብ የተወሰነ ዋጋ መክፈልን ይጠይቃል፡፡ ይህንን የማናደርግ ከሆነስ ለማድረግ ዝግጁ ነን?
#daily_pasture #discipleship_motivations #higher_mission
“ፍቅር ይህ ነው፤ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው ሳይሆን እርሱ እንደ ወደደንና ስለ ኀጢአታችን ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን መላኩ ነው። ወዳጆች ሆይ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፣ እኛም እርስ በእርሳችን መዋደድ ይገባናል።”
1 ዮሐንስ 4:10-11 NASV
ዮሐንስን የሚወደው እንቅጩን ስለምናገር ነው፤ በተለይ በተግባራዊ እምነት ጉዳይ፡፡ ስለፍቅር ስናገር 'ይገባናል' አለ ግዴታ አለብን ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ለእኛ በልጁ ለምናምን መውደድ ምርጫ አይደልም እርሱ ያለቅድሜ ሁኔታ እንደወደደን እኛም ሌሎችን እንዲሁ መውደድ ይገባናል፡፡

ጸጋው ይብዛልን!
#higher_mission
#discipleship_motivations
2
“ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።””
ሐዋርያት ሥራ 4:12 NASV

ለመዳን የተሰጠን አንድ Original ስም ብቻ ነው፤ እርሱም ኢየሱስ ነው፡፡ የቀሩት high copy ናቸው፡፡ ስለዚህ ከእነዚህ አስመሳይ ስሞች መጠንቀቅ ያሻናል፡፡

ጸጋው ይርዳን!
#discipleship_motivation
#discipleship_motivations
#daily_pasture
“ወንድሞቼ ሆይ፤ ነጻ እንድትሆኑ ተጠርታችኋል፤ ነጻነታችሁን ግን ሥጋዊ ምኞታችሁን መፈጸሚያ አታድርጉት፤ ይልቁንም አንዱ ሌላውን በፍቅር ያገልግል።”
ገላትያ 5:13 NASV

ነጻነት ሁሌም መዘዝ አለው። የሆነ ነገር ነጻ ከሆነ በጥንቃቄ አይያዝም፤ የነጻ ውሃ፣ ምግብ፣ የመሳሰሉትን ማሰብ እንችላለን። በእርግጥ ርካሽ ከሆነም ይቃጣናል እንደንጻ ባይሆንም። ጳውሎስ ይህንን ስለተረዳ እንዲህ ይለናል። ነጻነታችንን ለማይገባው አንጠቀም። በጣም ግልጽ እና አንገብጋቢ፤ ጸጋው ይርዳን!
#discipleship_motivation
#daily_pasture
ከዛሬ የሚጀምር የ50 ቀናት ቋሚ የወንጌል ስርጭት ስላለን ብትቀላቀሉን ደስ ይለናል፡፡
“ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ። የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።”
1 ቆሮንቶስ 16:13-14 NASV

ጳውሎስ የመጀመሪያው የቆሮንቶስን መልዕክት ሲጨርስ ነበር ይህን የተናገረው፡፡ በመጨረሻም እንደማለት ነው፤ ንቁ እምነታችሁን ለማጥፋት የሚፈልጉ ሃይላትን እንዲታውቁ፤ በእምነታችሁ ጽኑ ብዙ የሚያሰናክሉ ነገሮች ቢኖሩም እናንተ ግን ጽኑ (እንዲጸና የሚነገረው ጽናቱ ለተፈተነ ሰው ነው)፤ በርቱ ለመንቃት እንዲሁም ለመጽናት ብርታት ይጠይቃል፤ ጠንክሩ በቦታ ለመቆየት እንዲሁም ለመጽናት ጥንካሬ ያሻል፡፡

የምናደርገውን ሁሉ ደግሞ በፍቅር እንድናደርግ ይመከራል፤ ምክንያቱም ፍቅር የሁሉም ነገር ማሰርያ ነው፡፡ ያለፍቅር የምናደርገው ነገር መጨረሻው ጥሩ እንደማይሆን ሁሉ በፍቅር የምናድርገው ነገር ውጤቱ ሁልጊዜም ጥሩ ይሆናል፡፡

#discipleship_motivation
#higher_mission
👏3
“የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።”
2 ቆሮንቶስ 1:3-4 NASV

ሐዋሪያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች ሁለተኛውን ደብዳቤ ስጽፍ በመጽናናት ይጀምራል፡፡ ከምንም በላይ የመጽናናት ሁሉ ምንጭ የሆነውን እንዲሁም በመከራ ሁሉ ያጽናናቸውን እግዚአብሔርን በማመስገን ይጀምርና እነርሱ የተጽናኑት ለሌችን ለማጽናናት እንደሆነ በመናገር በጣም ቁልፍ መሪህ ያነሳል፡፡ እኛ የምንጽናናው ሌሎችን ለማጽናናት ነው፡፡ ይሄ ማለት የተጽናናን ሰዎች በሙሉ የማጽናናት አቅሙም ሆነ አላፊነቱን አለን ማለት ነው፡፡
#daily_pasture
#higher_mission
#discipleship_motivation
🙏2