Higher Mission Ministries (HMM)
140 subscribers
32 photos
6 links
This is the official channel of higher mission ministries. On this channel you will get motivation, idea about life purpose and missions. follow us for more insights on Life purpose. we will share timely news and informations too.
Download Telegram
“Now those who #belong to #Christ Jesus have #crucified the #flesh with its passions and desires.”
Galatians 5:24 CSB

If we are true disciples of Christ, we will #crusify our flash with its desires.
#discipleship_inspirational
“እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።”
ሮሜ 12:1 NASV
#discipleship_inspirational
“Finally, brothers, whatever is true, whatever is #honorable, whatever is #just, whatever is #pure, whatever is #lovely, whatever is #commendable, if there is any #excellence, if there is anything worthy of #praise, @THINK about these things.”
Philippians 4:8 ESV
#discipleship_motivations
#Do your #best to #present_yourself to #God as one #approved, a #worker who #does_not need to be #ashamed and who correctly handles the #word of #truth.”
2 Timothy 2:15 NIV
"ዛሬ ብዳዊት ከተማ #ምድኅን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።" ሉቃ. 2:11። የተወለደው የዛሬ ሁለት ሺህ አመት ቢሆንም #ዛሬም አዳኛችን ነው። መልካም የጌታችን ልደት መትሰቢያ በዓል ይሁንላችሁ። 🎄
"...እናንተ ግን የድካማችሁን ዋጋ ስለምታገኙ በርቱ፤ እጃችሁም አይላላ።" 2ዜና 15:7

እግዚአብሔር የመሪህ አምላክ ነው። በእርሱ ዘንድ በንጻ መድከም የለም፤ ሁሌም ድካም ያስከፍላል። ስለዚህ በእርሱ ፊት የምትተጉ የምትደክሙ ደስ በርቱ፣ ጽኑም በመጨረሻው ዋጋችሁን እግዚአብሔር ይከፍላል።
#የእለት_ስንቅ #Daily_pasture #discipleship_motivations
" ሰው #በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤ በከንፈሩም ምርት ይረካል። #አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።" ምሳሌ 18:20-21

#አንደበት በጣም ወሳኝ የህይወታችን ክፍል ናት። ራሳችንን ለመግለጽ ወይም እኛን ለማሳየት የአንበሳውን ድርሻ የሚጫወት #አንደበት ነው፤ ለምሳሌ ማን እንደሆንን፣ ምን እንደምንወድ፣ ምን እንደምችል፣ ስለሌሎች ያለን አመለካከት እና የመሳሰሉ ነገሮችን በመናገር ሰዎች ስለእኛ ያላቸውን አመለካከት እንገነባለን። ይህም የሚያሳየው በሌሎች ዘንድ ራሳችንን ለመሳል/ ለማስተዋወቅ አንደበት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ #አንደበትን መግታት/ መቆጣጠር ቀላል አይደለም። ራስን መግዛት #አንደበት መግዛትን ይጨምራል፤ ይህንን ደግሞ ማድረግ ካልቻልን ደግሞ ለብዙ ችግር ልያጋልጠን ይችላል። የምንረካውም ሆነ የምንጠግበው #በአንደበታችን ፍሬ ስለሆነ #በአንደበታችን ለምንዘራው ነገር በጣም መጠንቀቅ ያስፈልገናል፤ ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳልና።
#በአንደበታችን ህይወት ከዘራን ህይወትን እናጭዳለን፤ ሞትን ከዘራን እንዲሁ። ስለዚህ ልክ እንደልባችን ምናልባትም ከልብም በላይ #ለአንደበታችን መጠንቀቅ አለብን። ምክንያቱም #አንደበት ከእኛም አልፎ ሌሎችን ልጎዳ የሚችል ስለሆነ።

"#አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤ የሚወድዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።"
#Daily_pasture #discipleship_motivations #የእለት_ስንቅ
ለዘላለም በእግዚአብሔር መታመን
“በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ። በእግዚአብሔር ለዘላለም ታመኑ፤ ጌታ እግዚአብሔር የዘላለም ዐለት ነውና።”
ኢሳይያስ 26:3-4 አ.መ.ት

እግዚአብሔር በርሱ የሚታመኑትን ያውቃልና በመከራ ቀን እንደሚደርስላቸው በሰላም እንደሚጠብቃቸው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። ስለዚህ ለዘላለም በማንኛውም ሁኔታ በእርሱ እንታመን፤ እግዚአብሔር በችግር ጊዜ ብቻ የምንሮጥበት አይደለም፣ በደስታ ጊዜም ልንታመነው የሚገባ ነው እርሱ ታማኝ አለት ነውና። የዚያን ጊዜ ነፍሳችን ፍጹም ሰላም ታገኛለች።
#discipleship_motivations #daily_pasture #የእለት_ስንቅ
#ቃሉን ሰምቶ ማመን ይገባል

“እውነት እላችኋለሁ፤ #ቃሌን የሚሰማ፣ በላከኝም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ ከሞት ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።”
ዮሐንስ 5:24 NASV

ኢየሱስ #ቃሉ እውነት እርሱም እውነት እንደሆነ ይናገራል፡፡ ኢየሱስ ከዚህ ቁጥር ከፍ ብሎ አብ መፍረድን ለወልድ(ለእርሱ) እንደሰጠ ይናገራል፡፡ ስለዚህ እንዲፈርድ የተሰየመውን ከአመንን ማንም አይፈድብንም፤ #ቃሉ እንደሚለውም በጭራሽ ለፍርድ አንቀርብም ማለት ነው፡፡ ምክንያቱ ዳኛው ራሱ ስለሆነ ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ሳይደርስ ያስቆመዋል፡፡ ይህ ግን የሚሆነው ቃሉን ሰምተን ላመንን ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ምንን? እርሱ ወልድ ወይም ጌታ እንደሆነ፡፡ ስለዚህ #ቃሉን መስማት ብቻ ሳይሆን ማመንም ይጠበቃል ማለት ነው፤ #ቃሉ እውነት ስለሆነ፡፡

#የእለት_ስንቅ #discipleship_motivations #discipleship_inspirational #daily_pasture
ዋናው የሰንበት እረፍት ገና ይቀረናል

“ስለዚህ የሰንበት ዕረፍት ለእግዚአብሔር ሕዝብ ገና ቀርቶለታል፤ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር ዕረፍት የሚገባ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ከሥራው እንዳረፈ፣ እርሱም ደግሞ ከሥራው ያርፋል።”
ዕብራውያን 4:9-10 NASV

እያሱ እስራኤላውያንን አሳርፏል፤ ነገር ግን እረፍቱ ሙሉ አልነበርም በማለት ገና ለእነርሱም ታለቁ እረፍት/ሰንበት እንደሚቀርላቸው ይናገርና ለእግዚአብሔር ህዝብ ግን እረፍት ገና ይቀራል በማለት የደመድማል፡፡ እዚህ ላይ የተገለጸው እረፍት “Noah/ኖህ” የሀጥአት እረፍት ሳይሆን “Sabbath/ ሰንበት” ከሁሉም ነገር (ከጉልበት ስራ እስከ ሀጥአት) የሚናርፍበት እረፍት ነው፡፡ ይህም ዘላለማዊው የእግዚአብሔር እረፍት ነው፡፡ ይህም እረፍት እኛ የእግዚአብሔር ህዝብ ፍጹም የሆነ ሁሉን አቀፍ እረፍት የምናደርግበት ጊዜ፡፡ ይህንን ጊዜ በጉጉትና በናፍቆት እንጠብቃለን፡፡
#የእለት_ስንቅ
#discipleship_motivations
#daily_pasture
Forwarded from Cherinet N. Yatasa
“በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ፣ ከሰማይ ብርሃናት አባት ይወርዳሉ፤ በርሱ ዘንድ መለዋወጥ፣ ከመዞር የተነሣ የሚያርፍ ጥላም የለም።”
ያዕቆብ 1:17 NASV

እግዚአብሔር ምህረቱን አብዝቶልን ባለልጅ አደረገን። ስሟንም እርሱ ምሮናልና "ምህረት ቸርነት" ብለናታል።
1
በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ከእግዚአብሄር ብቻ

“በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ፣ ከሰማይ ብርሃናት አባት ይወርዳሉ፤ በርሱ ዘንድ መለዋወጥ፣ ከመዞር የተነሣ የሚያርፍ ጥላም የለም።”
ያዕቆብ 1:17 NASV

ብዙ አይነት ስጦታዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን በጎ የሆኑት እንዲሆን ከበረከትም ፍጹም የሆነ በረከት ከእግዚአብሄር (Exclusive) የሆኑ ናቸው፡፡ ማንም ምንም ሊባርክ ወይም ሊሰጥ ይችላል፤ ነገር ግን ፍጹም የሆነን አይደለም፡፡ ይህ ከእግዚአብሄር ብቻ ነው የሚመጣው፡፡
በረከት እንደሰጭው ማንነት ነው፡፡ እግዚአብሄር ብቻ በባህሪው ፍጹም ስለሆነ እርሱ ብቻ ነው ፍጹም የሆነ ስጦታና በረከት እንደፍቃዱ ሊሰጥ የሚችለው፡፡ በሌላ አባባል ከእግዚአብሄር የምንቀበለው በረከት ብቻ ነው ሁሌም ፍጹም የሚሆነው ሌላው ግን ባለብዙ እንከን ነው፡፡ ደስታውም አጭር ነው፡፡ ስለዚህም ለፍጹም እና ዘላቂ ደስታ የእርሱን በረከት እንደፈቃዱ እንጠብቅ፡፡

#የእለት_ስንቅ
#daily_pasture
#discipleship_motivations
መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትምሰል፡፡

“ወዳጅ ሆይ፤ መልካም የሆነውን እንጂ ክፉውን አትምሰል። መልካም የሆነውን የሚያደርግ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው። ክፉ የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።”
3 ዮሐንስ 1:11 NASV

ሶስተኛዉ የዮሃንስ ምልክት የተጻፈጽ ጋዮስ ለሚባል ሰው ሲሆን ዋናው ሀሳብም አገልጋዮችን እንዲቀበል ስለመጠየቅ ነው፡፡ ዮሐንስ ለጋዮስ በግል የጻፈለት ሲሆን ቤተክርስትያን እንዳትቀበል የሚያደርግ አንድ ዲዮጥራጥስ የሚባል ሰው እንዳለ እና እርሱም የዚያን ሰው ክፉ ስራ እንዳይከተልም ያሳስበዋል፡፡
ዮሐንስ ወዳጁን ጋዮስን ሲመክረው ክፉ ማድረግ እግዚአብሔርን አለማወቅ እንደሆነና ዲዮጥራጥስ በቤተክርስትያን በይፋ ስላደረገ ይህንን መከተል እንደሌለበት ይነግረዋል፡፡ ዲዮጥራጥስ መሪ መሆን የሚወድ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ቢሆንም እግዚአብሔርን እንደማያውቅና ጋዮስም ሊከተለው እንደማይገባ ያሳስባል፡፡
በቤተክርስትያን ብዙ አይነት ሰዎችን እናገኛለን፤ ሁሉንም በቅንነት ከሚቀበሉ ደግ ሰዎችን እስከ ሁሉንም ነገር ክፉ የሚያስመሱ እንደ ዲዮጥራጥስ አይነት ሰዎችን፡፡ ነገር ግን እኛ የተጠራነው እግዚአብሔርን ለመምሰል እንጂ ሰዎችን ለመምሰል/ ለመከተል አይደለም፡፡
እግዚአብሔርን ማወቃችን የሚለካበት ቀላሉ ሚዛን መልካም ስራ ነው፡፡ ዮሐንስ ሲያብራራ እግዚአብሔርን አይቶ/ አውቆ ክፉ የሚያደርግ ሰው የለም ይላል፡፡ ስለዚህ እንደጥቁር እና ነጭ ወይ ታውቃለህ ወይ አታውቅም ነው፡፡
በፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ እንዳለው ቃሉ ፍሬያችን ነው የሚገልጠን ማለት ነው፡፡
1🔥1
ከተመካን አይቀር በድካማችን

“እርሱ ግን፣ '#ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና' አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ። ስለ ክርስቶስ በድካም፣ በስድብ፣ በመከራ፣ በስደትና በጭንቀት ደስ የምሠኘው ለዚህ ነው፤ ስደክም ያን ጊዜ ብርቱ ነኝና።”
2 ቆሮንቶስ 12:9-10 NASV

ሐዋሪያው ጳውሎስ ከላይ ‌እርሱ ስለራሱ እንደማይመካ ያትትና ትምክቱን ለመግታት ጌታ እንደሚጠቀምበት ስለሚያምነው የስጋ መውጊያው ይናገራል፡፡ ጌታም ሁሌ #ጸጋዬ ይበቃሃል እንዲሁም ሀይሌ በድካምህ ጎልቶ ይታያል እንደሚለው በማከል ከድካሙ በቀር እንደማይመካ ይናገራል፡፡

ሐዋሪያው ጥሩ ሃላብ ያነሳል ብመካ ብዙ ትምክህት እንዳለው እና በባዶ እንዳልሆነ፤ ነገር ግን ይህ የግሉ ሳይሆን #የጸጋው ስራ ስለሆነ ሰዎች በእሱ እንዲያውቁት እንደማይፈልግ፡፡ ሊታይ የሚገባው እርሱ ሳይሆን ጌታ እንደሆነ ያምናል፡፡
ከጳውሎስ የምንማረው ምንድን ነው? #በጸጋ ምንም ነገር ማደረግ እንችላለን፤ ብዙ የምንመካባቸው ታሪኮችም ልኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በእነዚህ #የጸጋው ጀብዶች ራሳችን ልንወደስ አይገባም፤ ሰዎች በጭራሽ በእሱ ሊያውቁን አይገባም፡፡ ይልቁንም እንደእኛነታችንና እንደሰው ወይም እንደደካማነታችን ሊያውቁን ይገባል፡፡ የእኛ ማንነት #ከጸጋው አገልግሎት ውጭ ያለው የግል ህይወታችን ነው፡፡ #ጸጋ ስጦታችን እንጂ ማንነታችን አይደለም፡፡

ሌላው #ከጸጋ ጋር ጎን ለጎን መታየት አንችልም፤ ወይ ራሳችንን ደብቀን #ጸጋውን እናሳያለን ወይም #ጸጋውን ደብቀን ራሳችንን እናሳያለን፡፡ አንዱ ሲጎላ ሌላው ይደበዝዛል(inversely proportional)፡፡ ስለዚህ ማንን ነው ማሳየት ያለብን? ራሳችንን ወይንስ #ጸጋውን? ጌታ ጻውሎስን እንዳለው ሃይሉ ፍጹም የሚሆነው ወይም ጸጋው የሚደምቀው እኛ ስንደበዝዝ ነው፡፡ ለእኛ በእርሱ በኩል መታወቅ የእርሱ መሆን ብቻ ይበቃናል፡፡ በራሳችን ለመታወቅ ወይም ለመጉላት በወደድን መጠን 'እርሱ ልልቅ እኔ ደግሞ ላንስ ይገባል' የሚለውን የእግዚአብሔር ቃል መቃወም ይሆንብናል፡፡ እንደ አባቶቻችን እርሱን አተልቀን እእኛ ስናንስ የዚያን ጊዜ ይከናውንልናል፡፡ ሰዎች በክርስቶስ ስለሚያውቁን በዚያን ጊዜ ይበልጥ እንታወቃለን፡፡

በመጨረሻም ትምክህታችን ስለድካማችን (በእኛ በደካሞቹ ስለተሰራው ስራ እንዲሁም በደከምን ጊዜ በእኛ ታላላቅ ስራ ስለሰራው #ጸጋ) ሊሆን ይገባል፡፡ ደካማ ባንሆን ሃይሉ በሙላት አይገለጥም ነበር፡፡ ስለዚህ ድካማችን #የጸጋውን ሃይል ፍፃሜ ስለገለጠ በድካማችን ስንመካ ክርስቶስን እናከብረዋለን/ እናልቀዋለን፡፡ ለዚህ እንድንተጋ #ጸጋው ይርዳን፡፡

ተባረኩ!
#የእለት_ስንቅ
#discipleship_inspirational #daily_pasture
#discipleship_motivations
#higher_missions
#hmm
👍1
እረፉ፣ እረፍት

“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”
መዝሙር 46:10 NASV

በዚህ ክፍል ‘እረፉ’ ለሚለው ቃል ጥቅም ላይ የዋለው የእብራይስጥ ቃል “ራፋህ” የሚለው ሲሆን ጥሬ ትርጉሙ ጥረት ማቆም፣ መተው፣ መልቀቅ ወይም መረጋጋት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። ይህ መዝሙር የተጻፈው በጦርነት ጊዜ ይመስላል፤ መልእክቱም በራሳችሁ መጣጣር ተዉ፤ አይናችሁን ከሁኔታዎች ላይ ወደ እኔ አንሱና የእኔን መበዠት፣ የእኔን ሉአላዊነትና ልእልና እዩ የሚል ነበር። ይህ ክፍል በዘጸ 14 ላይ ሙሴ ለእስራኤል ህዝብ እንዲያርፉና እግዚአብሔር የሚያደርግላቸውን ማዳን እንዲያዩ ከአደረገው ጥሪ ጋር ተመሳሳይ ነው። በጦርነት ሰዓት ከሆነ የተጻፈው ይህ መዝሙር እግዚአብሔር ጦርነቱን ወይም የጦር ዝግጅቱን እንዲያቆሙ፣ ይልቁንም ከእርሱ ጋር ያለው አምላክ እርሱ በህዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ ያለ እንደሆነ እንዲያዩ ይጠይቃቸዋል።

ከዚህ ክፍል ምን ልንማር እንችላለን? በህይወት ስንኖር በችግር ወይም በተግዳሮት ውስጥ ስንሆን በቀላሉ እንሸበራለን፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እረፉ እኔ አምላካችሁ ከእናንተ ጎን እንዳለሁ እወቁ እኔም ሁሉንም ነገር ትክክል አደርጋለሁ ይለናል። ይሄ እርፍት ከጥረት፣ ከትግል እንዲሁም ከፍርሃት ወይም ከመሸበር የምናደርገው እረፍት ነው፤ ይህንን እረፍት ብንለማመድ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን መተማመን ይጨምራል። ምክንያቱም በእግዚአብሔር ላይ መታመን በተግባር እንጂ በቃል የሚገለጽ አይደለም። እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያለው አምላክ እርሱ የእኛ አምላክ መሆኑን የሚናየው የራሳችንን ጥረት ትተን በእርሱ ብርቱ ክንድ ብቻ ሁኔታውን ስናልፍ ነው። አለበለዚያ የእኛ ጥረት ካለበት መረዳታችን (እውቀታችን) ሙሉ አይሆንም። ጸጋው ይርዳን!
1🙏1
አይዟችሁ

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”
ዮሐንስ 16:33 NASV

ከላይ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደማያዩት ግን ደግሞ ጥቂት ቆይቶ እንደሚያዩት (ስለሞት እና ትንሳኤው) ሲነግራቸው ደቀ መዛሙርቱ በዚህ አባባሉ ግራ ተጋብተው ኣናገኛለን። ከዚህም የተነሳ ኢየሱስ ንግግሩን በደምብ አብራራላቸው፤ አመኑትም። ከዚያም ሁላቸውም ትተውት እንደሚበተኑ በመናገር ይህን ሁሉ እየነገራቸው ያለው እንዲፈሩ ሳይሆን ሰላም እንዲኖራቸው እንደሆነ ይገልጻል። በዚህ ክቁጥር ደግሞ በአለም እስካሉ ድረስ መከራ እንዳለባቸው ነገር ግን እርሱ አለምን እንዳሸነፈ በማስታወስ ደግሞ ያጽናናቸዋል።

በጊዜው ለነበረ ሰው ይሄ ግራ የሚያጋባ ነገር ሊሆን ይችላል። ስለሚያስፈራ ነገር እየነገረ እንዳትፈሩ ነው እንዴት ይላል? አዎ በጊዜው ኢየሱስ ከእነርሱ አልተለየም መከራም ገና አልደረሰበትም ነበር፤ ይህ ማለት ደግሞ ኢየሱስ ሊሆን ያለውን ትንቢት እየተናገረ ነበር። ጊዜው ሲደርስ እና ትንቢቱ ሲፈጸም እንግዳ ስለማይሆንባቸው አይፈሩም ካልፈሩ ሰላም ይኖራቸውል። ኢየሱስ ስለዚህ የውስጥ(የልብ) ሰላም ነው እያወራ ያለው።

በሁለተኛው ማሳሰቢያም በተመሳሳይ ሊሆን ስላለው ነገር እያወራ ነው። ኢየሱስ በጊዜው ሞቶ አልተነሳም ነበር ደቀ መዛሙርቱም መከራ አልደረሰባቸውም ነበር። ንገር ግን ኢየሱስ ወደፊት እርሱ ትቷቸው ሲሄድ የሚደርስባቸውን መከራ ይነግራቸዋል። እርሱ አለምን ያሸነፈ እንዲሁም በሰማይና በሚድር ስልጣን የተሰጠው አምላክ በኋላ በማቴ 28:30 ከእነርሱ ጋር እስከ አለም ፍጻሜ እንደሚሆን ቃል ስለሚገባላቸው የእርሱ አለምን ማሸነፍ ጊዜው ሲደርስ ትርጉም ያለው መጽናናት ይሆናቸዋል።

ከዚህ ምን ልንማምር እንችላለን? በአለም ሳለን መከራ አለብን ነገር ግን አለምን ያሸነፈው አምላክ ደግሞ እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ስለሆነ መከራውን በድል እናልፈዋለን። ዳዊት በመዝሙር 23 “በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳን አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንህ ክፉን አልፈራም” እንዳለው፣ እኛም በመከራ ውስጥ ብናልፍ እንኳን እርሱ ከእኛ ጋር ነውና መከራን አንፈራም። ምክንያቱም አለምን እና በእሷ ያለውን መከራ ያሸነፈው እርሱ ሁልጊዜም ከእኛ ጋር ስለሆነ እኛም መቼም አንፈራም፣ ሁልጊዜ ሰላም ይኖረናል።
ሰላሜን እሰጣችኋለሁ

“ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።”
ዮሐንስ 14:27 NASV

* በጣም የምትወዱት ሁሌም የሚመራችሁ ለሁሉም ነገር ወደርሱ ትሮጡ የነበረ የደስታችሁ ምንጭ የሆነ ሰው ሊለያችሁ እንደሆነ ስታውቁ ምን ይሰማችኋል?

በመጀመሪያ የት ነው የሚሄደው? እንዴትስ ነው የምንከተለው? ካልተከተልነውስ እንዴት ነው የምንሆነው? ህይወታችንስ እንዴት ይሆናል? እና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ይመጣሉ፡፡ መልስ ካለገኙ ደግሞ ጭንቀት ይመጣል፡፡ ጭንቀት ደግሞ ሰላማችንን ያደፈርሰዋል/ ያጠፋዋል፡፡ በዚህ ክፍለ ምንባብ የተፈጠረው ይሄው ነበር፡፡

ስለዚህ ኢየሱስ የመጨረሻ/ ultimate ማጽናኛ የሆነውን የተስፋ ቃል ተጠቀመ፡፡ ብቻችሁን አልተዋችሁም፤ ይልቁንም አጽናኙ መንፈስ ቅዱስን እንዲሁም ሰላምን እተውላቸዋለሁ እርሱም የራሴን ሰላም እሰጣችኋለሁ አላቸው፡፡

የኢየሱስን ሰላም ለሚያውቅ ይህ ታላቅ የተስፋ ቃል ነው፡፡ ተገፍቶ ወደ ገደል አፋፍ እየተወሰደ የነበረው ሰላም, ባህሩ ስናወጥ ሁሉም ሰው ተስፋ ቆርጦ እያለ የነበረው ሰላም, እናም ሁሌም በፊቱ ላይ የሚታየው ሰላም፡፡ ተስፋቸው ተሟጦ ነበር፤ ነገር ግን በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ ስለነገ ሲያስቡ በሚመጣው ጭንቀት ውስጥ እያሉ ይህን ሰላም ሊሰጣቸው ቃል ገባላቸው፡፡

ግሩም የሆነ ተስፋ፤ ኢየሱስ የራሱን ሰላም እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ ነገር ግን በሚያጭንቅ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ማስታወስ ልከብደን ይችላል፡፡ የእነርሱ ግራ መጋባት ነገን ባለማወቃቸው ሲሆን ኢየሱስ ደግሞ ነገን እንዲሁም ከነገ በኋላ ሊሆን ያለውን ያውቅ ነበር፡፡ ስለዚህ በዛሬ ግንብ ስንገደብ ነገን እና ከዚያ በኋላ ያለውንም የሚያውቅ የራሱን ሰላም እሱም አዕምሮን የሚያልፍ የልብ ሰላም ሰጥቶናል፤ በዚህ ተጽናኑ፡፡

ሁልጊዜም በእንደዚህ አይነት የጨለመ ምንም ብርሃን/ ተስፋ የማይታይበት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ይህን ማሰብ ወይም ማስታወስ ሊቸግረን ይችላል፡፡ በመሆኑም እንዲህ ብለን እንጸለይ ''ጌታ ኢየሱስ ሆይ ሰላምህን ሰጥተሄኛል አመሰግናለሁ፡፡ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር በጨለመበት ምንም ተስፋ በሌለበት ሁኔታ ላይ ነኝ፡፡ አንተ ነገዬን የሚታውቀው አምላክ በአንተ እታመናለሁ፡፡ አጽናኙ መንፈስህ ያጽናናኝ፤ በአንተ መታመን እና ከአድማስ ባሻገር ያለውን የነገን ተስፋን ማየት እንድችል ይርዳኝ፡፡''
#daily_pasture
#discipleship_motivations
#higher_missions
#hmm
4
“ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤”
ማቴዎስ 28:19 NASV

ይሄ ነው የተጠራንለት፤ ከአማኝነት የላቀው ተልዕኮ፡፡
#higher_missions
#discipleship_motivations
3