ቅዱሳን ኅሩያን የዲ°ን ዮርዳኖስ ትምህርቶች
4.68K subscribers
700 photos
5 videos
13 files
228 links
የዲ.ን ሄኖክ ሀይሌን ስብከት በድምጽ እንለቃለን
ለአስተያየት @EMNE_TSYON @unitte_bot
በቴሌግራም ከፈለጉን @henokhailee
በfacebook ከፈለጉን https://www.facebook.com/tewahidosewhone/
በyoutube ከፈለጉን https://youtube.com/channel/UCq2ueVG6O3ZuKHJ485y7hfg
Download Telegram
#ቀዳም_ሥዑር_የተሻረች_ቅዳሜ

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከተሰቀለበት ዕለት ማግሥት ያለው ቅዳሜ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል:-

#ቀዳም_ሥዑር፡-

💠 በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ሥዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

#ለምለም_ቅዳሜ፡-

❇️ ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ሥዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

🩷 (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

#ቅዱስ_ቅዳሜ፡-

🌟 ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

💫 (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)

እንበለ ደዌ ወሕማም ፤እንበለ ጻማ ወድካም
   ዓመ ከመ ዮም ፤ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ     
       እግዚአብሔር ለብርሃነ ትንሣኤሁ
                 በፍስሓ ወበሰላም

        https://t.me/amdasilase07
Audio
እንኳን አደረሳችኹ

"" በመስቀሉ ሰላምን አደረገ "" (ቆላ. ፩:፳)

"የቀዳም ስዑር ትምህርት"

(ሚያዝያ 26 - 2016)

➡️https://www.youtube.com/@ZikereKedusan

➡️https://t.me/zikirekdusn
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ሥርዓተ ማኅሌት ዘትንሣኤ
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

ደወል እንደተደወለ ከሁሉ አስቀድሞ ነቢያት ተደግሞ ውዳሴ ማርያም በዜማ ይደርሳል።
@EOTCmahlet
"ተፈሥሂ ማርያም ለአዳም ፋሲካሁ" ይባላል። መልክአ ስዕል አይባልም።
@EOTCmahlet
ከዚያም ተአምረ ማርያም እና ተአምረ ኢየሱስ ይነበባል። ቀጥሎም ወተንሥአ ይሰበክና ከአራቱ ወንጌላት 3ቱ ተነበው "አርያም" በተባለው ምስጋና ማኅሌቱ ይጀመራል።
@EOTCmahlet
ይ.ዲ ምስባክ መዝ: ፸፯ : ፷፭

ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፤
ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን፤
ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።

@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አርያም፦
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ ቀዳሚ ዜማ ግበሩ በዓለ  በትፍሥሕት እስከ አቅርንቲሁ ለምሥዋዕ፤ ዛቲ ፋሲካ ቀዳሚት ሕግ።
ሃሌ ሉያ ለአብ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ፤   ይገብሩ በዓለ ሰማያት፤ ይገብሩ በዓለ ደመናት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ምልጣን፦
ዮም ፍሥሃ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፤ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን፤ ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል አልዓላ፤ አማን ተንሥአ እምነ ሙታን።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
'አማን በአማን'/፪/ ተንሥአ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ተንሥአ እምነ ሙታን/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን/፪/
ቀደሳ ወአክበራ እምኲሎን መዋዕል/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለዓለም፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ፤ ብርሃንከ ፈኑ ዲቤነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ትንሣኤከ ለእለ አመነ/፪/
ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ/፪/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ከእስመ ለዓለሙ ጋር ተያይዞ  ሰላም ይፃፋል
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ይእቲ ማርያም እምነ፤ ወእሙ ለእግዚእነ፤ ሰአሊ በእንቲአነ፤ ከመ ይምሐረነ ወይሣሐለነ፤ ያስተርኢ ኂሮቶ ላዕሌነ፤ ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ ፍሥሐ ወሰላም ለእለ አመነ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበት ለዕረፍተ ዚአነ/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ኪዳንን ከተደረሰ በኃላ
መዝሙር በ፩፦
ሃሌ ሉያ ይትፌሣሕ ሰማይ ወትትኃሠይ ምድር፤ ወይንፍሑ ቀርነ መሠረታተ ሕምዝ፤ ወይወውኡ አድባር ወአውግር፤ ወኲሉ ዕፀወ ገዳም ወዮምሰ ዓባይ ፍሥሐ በሰማያት፤ ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
አመላለስ፦
ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ፤/2/
ተሐጺባ በደመ ክርስቶስ/4/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ሰላም
ፍጹመ ንጉሠ ኮነንዎ አይሁድ፤ ተካፈሉ አልባሲሁ ሐራ ሠገራት፤ ወኮርዕዎ ርእሶ በኅለት፤ ረገዝዎ ገቦሁ በኲናት፤ ትንሣኤሁ ገብረ በሰንበት፤ ሰላመ ይጸጉ ለነገሥት፤ ለአሕዛብ ወለበሐውርት።


ከዚህ በኃላ ወደ ስርዓተ ቅዳሴ

በዚህ አጋጣሚ የ YouTube ቻናላችንን subscribe ያላረጋችሁ ካላችሁ subscribe በማድረግ አበረታቱን

ያደረጋችሁም እናመሰግናለን 🤲

👉YouTube channel👇
https://www.youtube.com/@EOTCmahlet/featured#

አስተያየት ካለ @eotcmahletawian ላይ ጻፉልን

የቻናሉን ባለቤትና አድሚኖች ለማግኘት
@Yaredaweyan_bot ያናግሩን

እናመሰግናለን 🙏❤️

👉Telegram channel👇
     @EOTCmahlet

    #Join & #share


🇪🇹👇👇👇👇👇👇🇪🇹
👉@EOTCmahlet👈                 
👉@EOTCmahlet👈
👉@EOTCmahlet👈
🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & #share

 
Forwarded from ኖላዊ ነሄር
⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️
🕯"ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤"
    
   📖ወደ ሮሜ ሰዎች 6:5

🕯ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል
በእውነት ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቷል🕯
💐መልካም የትንሣኤ በዓል
     ⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️⚜️
ከትንሣኤ በኋላ ያሉ ዕለታት
    ሰኞ
ሰኑይ ማእዶት
ይባላል
እንደ ቤተክርስቲያን ይትባሕል ከትንሣኤ እስከ ዳግማዊ ትንሣኤ ያለውን ሳምንት እንደ አንድ እሁድ እናከብራለን። ለዚህም ነው ዕለታቱን እንደ ሰንበት እናከብራቸው ዘንድ በፍትሐ ነገሥት ላይ አባቶቻችን ትእዛዝ የቀረጹልን።
ማእዶት ማለት መሻገር ማለት ነው። አደወ ማለት ተሻገረ ማለት ሲሆን ማእዶት መሸጋገሪያ ማለት ሊሆን ነው።
ማእዶት የትንሣኤ እሑድ ማግስት ጌታ ክርስቶስ በትንሣኤው ምዕመናንን ከሞት ወደ ሕይወት ያሻገረበት ቀን የትንሣኤው ማሳሰቢያ ነው። (ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የአማርኛ መዝገበ ቃላት ገጽ ፻፶)
መሻገር በዕብራይስጥ ፓሳሕ ከሚባለው ቃል ይመሳሰላል ትርጉሙም ፋሲካ መሻገር ማለፍ የሚል ትርጉም ይሰጣል። ሁላችን እንደምናውቀው እስራኤላውያን ከሚያክብሯቸው አበይት በዓላት አንዱም ፋሲካ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እግዚአብሔር ከሞተ በኩር ያሳለፋቸውን ዕለት ያስቡበታል።
ቤተክርስቲያናችንም ይህንን በዓለ ትንሣኤን የፋሲካ በዓል የማክበሯ ምሥጢር ወይም የትንሣኤው ምሥጢር ነፍሳት በአምላካችን ትንሣኤ ከሞት ወደ ሕይወት ፣ ከአሳር ወደ ክብር ፣ ከሲዖል ወደ ገነት መሻገራቸውን በማሰብ አማናዊው ፋሲካ ወይም አሸጋጋሪው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብላ ታምናለች። እናምናለን።
ቅዱስ ጳውሎስ በብሉይ ኪዳን በታረደው የፋሲካ በግ (ዘዳ፲፮:፮) ምትክ አማናዊው ክርስቶስ እንደታረደልን እና ሞት ላያገኘን በሕይወት ለሕይወት እንዳሸጋገረን ሲገልጥ እንዲህ ብሏል:-"" እንግዲህ ያለ እርሾ እንዳላችሁ
አዲሱን ሊጥ ትሆኑ ዘንድ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ። ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤" (፩ ቆሮ ፭:፯)
ቅዱስ ጳውሎስ ስለ እርሾም ሆነ ስለ አዲሱ ሊጥ በምሳሌ የሚነግረን እስራኤላውያን የእግዚአብሔርን ፋሲካ ሲያከብሩ ያደርጉት የነበረ ስርዓትን ነው።
ይኸውም ፋሲካን ያከበሩት ገና ከነጻነት በፊት ነው። ምክንያቱ ደግሞ ከላይ እንዳየነው ከሞተ በኩር መቅሰፍት ለመዳን እና ከእግዚአብሔር ፍርድ ለመዳን ነበር።
በአዲስ ኪዳንም ያለን ክርስቲያኖች በተለይ ይህንን ዕለት ወይም ማእዶትን ስናስብ አምላካችን ከሞት ወደ ሕይወት እንዳሻገረን ፣ ከአሳር ወደ ክብር እንዳሳለፈን ፣ ከድካም ወደ ኃይል እንዳሻገረን ፣ ሁላችን ወደ መንግሥተ
ሰማያት ፋሲካችን በሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደተሸጋገርን በማመን ሊሆን ይገባል።
የፋሲካው ጌታ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞት ላይ እንድንዘባበትበት ሞትን ፣ ፍርሃትን ፣ ጭንቀትን ፣ ተስፋ መቁረጥን ፣ ሐዘንን ፣ ለቅሶን ፣ ትካዜን ፣ ድካምን ፣ ሥጋትን እና መቃብርን ሁሉ አጥፍቶ አሻግሮናል። ክብር ማዕዶታችን
ለሆነ ለእርሱ ይሁን። አሜን ክብር ይግባውና አምላካችን የሰው ልጅ ሞትን እንዲሻገር ሁለት ነገሮች(እምነት እና ምግባር ) እንደሚያስፈልጉት በመዋለ ስብከቱ እንዲህ ሲል አስተምሮናል:-
"እውነት እውነት እላችኋለሁ ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።" (ዮሐ፭:፳፬-፳፭)
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም ዕለቷ ፋሲካ እንደሆነችና እንደሰትባት ዘንድ የተገባች እንደሆነች እንዲህ ሲል በመዝሙሩ አዚሞታል:- " ፋሲካ ዛቲ ዕለት ቅድስት ይእቲ (ይህቺ የፋሲካ ዕለት ልዩ ናት) ፣ ዛቲ ዕለት ንትፈሳሕ በቲ (በዚህ ዕለት ሐሴት እናድርግባት)..."
  ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ ፳፰ ❖

❖ ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ሜልዮስ ሰማዕት +"+

=>ቅዱስ ሜልዮስ ልጅነቱን በመንፈሳዊ ትምሕርት
ያሳለፈ:
በጉብዝናው ወራት ፈጣሪውን ያሰበ ደግ ክርስቲያን ነው::
ይሕችን
ዓለም ከነ ክፋቷ ንቆ ኮራሳት ወደሚባል በርሃ ሔዶ
በተራራውና በደኑ ውስጥ በጾምና በጸሎት: በትሕርምትም
ለበርካታ ዓመታት
ተጋድሏል::

+በነዚህ የብሕትውና ዘመናቱ ልብሱን ፀሐይና ብርድ
ቆራርጦ ስለ ጨረሳቸው ፈጣሪው ጸጉርን አልብሳታል::
የአባ ሜልዮስ
ጸጉሩ እስከ እግሩ: ጽሕሙ እስከ ጉልበቱ ነበር::

+እድሜው ገፍቶ ሲያረጅ እንዲያገለግሉት እግዚአብሔር
ሁለት ወጣት ምስጉን ክርስቲያኖችን ላከለት:: እነርሱም
አባ ኢያሱና
አባ ዮሴፍ ይባላሉ:: 2ቱ ቅዱሳን አምላካቸውን
እግዚአብሔርንና አባታቸው ቅዱስ ሜልዮስን በፍጹም
ቅንነት አገልግለዋል::

+ከቆይታ በኋላ ግን በአካባቢው የነበሩ ጣዖት
አምላኪዎች አራዊት እናጠምዳለን ብለው በዘረጉት
መረብ ቅዱስ ሜልዮስን ያዙት::
ክርስቲያን መሆኑን ሲያውቁ "ለፀሐይ ስገድ" ብለው
ደበደቡት::

+ደቀ መዛሙርቱ ተሯሩጠው መጥተው አባታቸውን
በመከራ መሰሉት:: ክርስቶስን አንክድም ስላሉ ሁለቱንም
በሰይፍ አንገታቸውን
መቷቸው:: ቅዱስ ሜልዮስን ግን ለ15 ቀናት ካሰቃዩት
በኋላ በዚህች ቀን በቀስት በተደጋጋሚ ወግተው
ገድለውታል:: ጻድቅና
ሰማዕት ቅዱስ ሜልዮስ ብዙ ተአምራትን አድርጓል::

+ገዳዮች ግን ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ የሜዳ አህያ
ሊያድኑ የወረወሩትን ቀስት የእግዚአብሔር መልአክ
ወደነርሱ መልሶባቸው
ልብ ልባቸውን ተወግተው ሙተዋል::

❖ቸር አምላክ ከቅዱሱ ሜልዮስና ከደቀ መዛሙርቱ
በረከትን ያካፍለን::

❖ሚያዝያ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ሜልዮስ ዘደብረ ኮራሳን (ጻድቅና ሰማዕት)
2.አባ ኢያሱና አባ ዮሴፍ (ደቀ መዛሙርቱ)
3.ቅዱስ ብስጣውሮስ ሰማዕት (ተንባላት የገደሉት)

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አምላካችን አማኑኤል
2፡ ቅዱሳን አብርሃም ፡ ይስሐቅ ፡ ወያዕቆብ
3፡ ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
4፡ ቅዱሳን እንድራኒቆስ ወአትናስያ
5፡ ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ
6፡ ቅዱሳን አባዲር ወኢራኢ
7፡ ቅድስት ሶስና

++"+ ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ:: እነሆ
እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ
ሊያገባችሁ
አለው:: አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ:: እስከሞት
ድረስ የታመንህ ሁን:: የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ::
+"+
(ራዕይ. 2:10)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ ፴ ❖

❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖

❖ሚያዝያ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

=>እንዲህ ኃጢአታችን ጽዋዑን ሞልቶ በተረፈበት በዚህ
ዘመን አንዲት ሰዓትም ውድ የሆነች የንስሃ ዕድሜ ናት::
እግዚአብሔር
ግን ደግ ነውና ይሔው ሚያዝያን አስፈጸመን::

+ባይገባን ነው እንጂ በዚሕች ወር ውስጥ:-
*ሚሊየኖች በደዌ የአልጋ ቁራኛ ሁነዋል::
*ሚሊየኖችም ለንስሃ ሳይበቁ እንዲሁ አንቀላፍተዋል
(ሙተዋል)::

+እስኪ እርሱ አምላካችን ቀሪዋን ዘመን ደግሞ ለንስሃና
ለመልካም ሥራ ባርኮ ይስጠን::

+"+ ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ +"+

+በዚሕች ዕለት ከ72ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ:
ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ
ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ግብፅ ውስጥ ዐርፏል::

+ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ
ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ
በሚገባ ተምሮ
ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል::

+የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ120ው ቤተሰብ
በእድሜ በጣም ትንሹ (20 ዓመት) እርሱ ነበር:: ለ3
ዓመታት ከጌታ
እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን
ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል::

+በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው::
ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና:: ቅዱስ ማርቆስ 16 ምዕራፍ
ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ
ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር::

+ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር
ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ
አካባቢ በዚህ ቀን [በ60 ዓ/ም አካባቢ]
አረማውያን ገድለውታል::

=>ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን
እናስባቸው ዘንድ ይገባል::

❖ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ) የጌታ ቅን አገልጋይ
የነበረ፡፡

❖ቅድስት ማርያም (እናቱ)
*ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ:
*ጌታችንን ያገለገለች:
*ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት
ናት::

+ቤቷም (ጽርሐ ጽዮን) የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን
ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል::
የእመቤታችን ግንዘትም
ተከናውኖባታል::

❖እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን
ያድለን::

=>ሚያዝያ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ አርስጥቦሎስ (አባቱ)
3.ቅድስት ማርያም (እናቱ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
2.አባ ሣሉሲ ክቡር
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት

=>+"+ . . . እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ
ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ
ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ
ባንኩዋኩዋ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ
ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ
ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ
ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::
+"+ (ሐዋ. 12:12-15)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" 🌷ልደታ ለማርያም ድንግል🌷 "*+

ኢያቄም ወሐና ወለዱ ለነ ሰማየ:
ሰማዮሙኒ አስረቀት ለነ ፀሐየ::
" ኢያቄምና ሐና ሰማይን ወለዱልን:
ሰማያቸው ደግሞ ፀሐይን አወጣችልን (ወለደች-አስገኘችልን) "

=>የዓለማችን ወላጆች ነቢያት ሐዋርያትን: ጻድቃን ሰማዕታትን ወልደው ከብረዋል: ተመስግነዋል:: ኢያቄምና ሐና ግን ፍጥረት ሁሉ በአንድነት ቢሰበሰብ በእግሯ የረገጠችውን ትቢያ እንኩዋ መሆን የማይችል: የሰማይና የምድር ንግሥት: የእግዚአብሔርን እናት: እመቤታችን ማርያምን ወለዱልን::

+ኢያቄም ወሐና ለእግዚአብሔር የሥጋዌ አያቶቹም ተባሉ:: እስኪያረጁ ድረስ በመካንነት አዝነው ፀልየዋል:: ንጽሕናቸውና ደግነታቸው ተመስክሮላቸው ድንግል ማርያምን አግኝተዋል::

+እመቤታችን ከአዳም ስሕተት በሁዋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተወለደች የመጀመሪያዋ ሰው ድንግል ማርያም ሆናለች:: (ኢሳ. 1:9)

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ቀን: በሊባኖስ ተራራ ከ2,022 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

"ሙሽራዬ ሆይ! ከሊባኖስ ከእኔ ጋር ነይ" (መኃልይ. 4:8)

=>ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ (አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች ልጅ የላችሁም በሚል ይናቁ ነበር::

+ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ::
እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

+የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን እርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን ሳይቀር በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

+ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለ40 ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በ40ኛው ቀን 2ቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጀሮ ገብታ: በማሕጸኗ ስትደርስ አየ::

+እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለ7 ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

+በ7ኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

+እንደ ሥርዓቱም አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ . . .
ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: (ቅዳሴ ማርያም)

+"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማሕጸን ቅዱስ . . ."
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማሕጸንም ቅዱስ ነው . . ." (መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9)

+እመቤታችን ነሐሴ 7 ቀን ተጸንሳ ግንቦት አንድ ቀን ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን የዘር ሐረግ:-
*አዳም-ኖኅ-አብርሃም-ይስሐቅ-ያዕቆብ=
*በእናቷ:-
-ሌዊ-ቀዓት-እንበረም-አሮን-ቴክታና በጥሪቃ-ሔኤሜን-ዴርዴን-ቶና-ሲካር-ሔርሜላና ማጣት-ሐና::
*በአባቷ በኩል:-
-ይሁዳ-ፋሬስ-ሰልሞን-ቦኤዝ-እሴይ-ዳዊት-ሰሎሞን-ሕዝቅያስ-ዘሩባቤል-አልዓዛር-ቅስራ-ኢያቄም ይሆናል::

+ለጨለማው ዓለም የብርሃን መቅረዝ ሆና ትጠቅመን ዘንድ: አንድም ትንቢቱና ምሳሌው ይፈጸም ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም: በሊባኖስ ተራራ ከ2,026 ዓመታት በፊት ተወልዳለች::

=>የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟ: ፍቅሯ: ጸጋዋና በረከቷ ይደርብን::

=>ግንቦት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም (ልደታ)
2.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
3.ቴክታና በጥሪቃ
4.አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ (የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር

=>+"+ መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው::
ከያዕቆብ ድንኩዋኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::
በውስጧም ሰው ተወለደ::
እርሱም ራሱ ልዑል መሠረታት:: +"+ (መዝ. 86:1-6)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn