Audio
"" አምላኬ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? "" (መዝ. ፳፩:፩)
"ገብር ሔር"
"በዓለ ቅዱሳን አዳም ወዳዊት"
(ሚያዝያ 6 - 2016)
🔎https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
🔎 https://t.me/zikirekdusn
"ገብር ሔር"
"በዓለ ቅዱሳን አዳም ወዳዊት"
(ሚያዝያ 6 - 2016)
🔎https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
🔎 https://t.me/zikirekdusn
✞✞✞ እንኩዋን ለታላቁ ነቢይና ሰማዕት "ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+*" ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "*+
=>ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)
*የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ 100 ደግሞ ደርሶ ነበር::
*ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ በስተእርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::
*ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::
*የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በሁዋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ 2 ዓመት ከ6 ወር በሆነው ጊዜ
ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ
ሕጻናትን
ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ
ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት
የዘጋ:
ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና
እሱንም ግደል" አሉ::
*እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን
ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል::
አረጋይት ኤልሳቤጥም
ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ3 (5) ዓመታት
ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ 5 (7) ዓመት ሲሞላው ግን
እዚያው
በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው
ቀበሯት::
*ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር
አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር
በደመና
ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው
ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት
እስክጠራው እዚህ
ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::
*ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር
ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ25 (23)
ዓመታትም
በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት
በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም
አልቀመሳትም::
*ከዚህ በኋላ 30 ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ
ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት
ስለዚህ
ነገር ተናግረው ነበርና:: (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) አባቱ
ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ
ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" (ሉቃ.
1:76) ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::
*ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ
እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት:
አከበሩት::
ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ
የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው
የሚያስፈራ
ገዳማዊ ነውና::
*ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን
አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ6 ወራት ቆይቶ
ጌታችን ወደ እርሱ
ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ
የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ::
የሚገባበትም
ጠፋው::
*"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን
"ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት
ይሔው እስከ
ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ
ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ
ለ7 ቀናት አሠረው::
*በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ
በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ
ራስ አስቆርጦ
በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ
ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው
ነበር" ይላሉ::
የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ
መዛሙርቱ ቀብረውታል:: (ማቴ. 3:1, ማር. 6:14, ሉቃ.
3:1, ዮሐ. 1:6)
*ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ
ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን
ወዳለበት ደብረ
ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያትበኋላ በአዩት
ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::
*ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ
ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው
ዓለም ለ15
ዓመታት ስትሰብክ ኑራ በዚህች ቀን ዓረቢያ ውስጥ
ዓርፋለች::
=>" አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ/ የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች"
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)
❖ጌታችን መድኃኔ ዓለም የመጥምቁ ዮሐንስን ምትረት
አስቦ ይቅር ይበለን:: ጸጋውን: በረከቱንና ክብሩንም
ያሳድርብን::
❖ሚያዝያ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት (ጸዐተ ነፍሱ)
2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ (ከ318ቱ ሊቃውንት)
3.ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
4.ቅድስት እለእስክንድርያ ሰማዕት
5.አቡነ አቢብ ጻድቅ
ወርኃዊ በዓላት
1 ቅዱስ ሚናስ
2 .ቅዱስ ማርቂርቆስ ለእሙ ኢየሉጣ
3 ቅድስት ዕንባ መሪና
4 ቅድስት ክርስጢና
5 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ
++"+ ጌታ ኢየሱስ ለሕዝቡ ስለ ዮሐንስ ሊናገር ጀመረ . .
. ምን ልታዩ ወጣችሁ? ነቢይን? አዎን እላችሁአለሁ
ከነቢይም የሚበልጠውን . . . እውነት እላቹሃለሁ ከሴቶች
ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ
አልተነሳም. .
. ነቢያት ሁሉና ሕጉ እስከ ዮሐንስ ድረስ ትንቢት ተናገሩ::
ልትቀበሉትስ ብትወዱ ይመጣ ዘንድ ያለው ኤልያስ ይሕ
ነው
::
የሚሰማ ጀሮ ያለው ይስማ:: +"+ (ማቴ. 11:7-15)
❖ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ❖
https://t.me/zikirekdusn

Telegram
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ)
በዚህ ቻናል ዲ/ዮርዳኖስ የሚያስተምራቸው ወቅታዊ እና የነገረ ቅዱሳን (ዝክረ ቅዱሳን ትምህርቶችን ከእርሱ በመቀበል እናስተላልፋለን):: "ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
Forwarded from 📖የየዕለቱ ስንክሳር የሚለቀቅበት
❤ #ዑደት_ሲጀመር_የቤተ_መቅደስ_ምስባክ፦ "ብሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ባረክናክሙ እመቤተ እግዚአብሔር። እግዚእ አስተርአየ ለነ"። መዝ 117፥26-27። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 19፥1-11።
✝ ✝ ✝
❤ #የምዕራብ_ምስባክ፦ "ተፈሣሕኩ እስመ ይቤሉኒ ቤተ እግዚአብሔር ነሐውር። ወቆማ እገሪነ ውስተ አዕፃድኪ። ኢየሩሳሌምሰ ሕንፅት ከመ ሀገር"። መዝ 121፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥1-17።
✝ ✝ ✝
❤ #የደቡብ_ምስባክ፦ "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ። በእንተ ጸላኢ። ከመ ትንሥቶ ለጸላኢ ወለገፋዒ"። መዝ 8፥2-3። የሚነበበው ወንጌል ማር 11፥1-11።
✝ ✝ ✝
❤ #የምሥራቅ_ምስባክ፦ "እምሥራቀ ፀሐይ እስከ ዓረብ። ወእምጽዮን ስነ ስብሐቲሁ። እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ"። መዝ 49፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 19፥28-48።
✝ ✝ ✝
❤ #የሰሜን_በኩል_ምስባክ፦ "ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር። ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን። እስመ አፅንዐ መናሥግተ ኆኃትኪ"። መዝ 147፥1-2። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥12-19። መልካም የሆሳዕና በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

Forwarded from ዓምደ ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት | Amde Silase Sunday School (✞ ቡሩክ ✞)
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ
#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
✨ ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
💠 በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
❇️ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦
✅ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
🌟 በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
https://t.me/amdasilase07

ዓምደ ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት | Amde Silase Sunday School
ይኽ የካራሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የዓምደ ሥላሴ ሰንበት ትምህርት ቤት የቴሌግራም አውታር ነው፡፡ የዓምደ ሥላሴ ሰንበት ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ ወቅታዊ ኹኔታዎችን የሚገልጹ መረጃዎችን እንዲኹም ማስታወቂያዎችን በዚኽ ገጽ ለተከታታዮቹ ያደርሳል።
††† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ ዓመታዊ
የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ቅዱስ ብሩታዎስ †††
††† ሐዋርያው ቅዱስ ብሩታዎስ በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው የውዳሴ ማርያም ደራሲ ነው::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፈቃዱ ሙቶ ከተነሳ ከ8 ዓመታት በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያ ያምናል:: ባመነ በ6 ዓመቱ (ማለትም ከክርስቶስ ዕርገት 14 ዓመታት በኋላ) እየሰበከ ግሪክ አቴና /ATHENS/ ደርሶ ብዙ ፈላስፎችን ወደ ክርስትና ሲያመጣ አንዱ ይህ ቅዱስ ብሩታዎስ ነበር::
ቅዱስ ብሩታዎስ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ: ሐዋርያትን ተከትሏቸው: እነሱም ቅስና ሹመውታል:: ጵጵስና እንሹምህ ቢሉት በፊታቸው ተንበርክኮ አልቅሷል:: አይገባኝም ማለቱ ነበር::
ታዲያ ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያት ስለ ድንግል እመቤታችን ሲጨዋወቱ እየሰማ "መቼ አይቻት" እያለ በፍቅሯ ይቃጠል ነበር:: አንዴ ግን ወሰነ:: "እመቤቴን ሳላያት እንቅልፍ አላይም" ብሎ በሽማግሌ እግሮቹ ከግሪክ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ::
የሚገርመው እርሱ እሥራኤል (ጽርሐ ጽዮን) የደረሰው በ49 ዓ/ም ጥር 21 ቀን እመቤታችን ልታርፍ ሰዓታት ሲቀራት ነበር:: ቅዱሱ ሽማግሌ እመቤታችንን በአካለ ሥጋ ስላያት በፊቷ እንደ እንቦሳ ዘለለ:: እየሰገደም አመሰገናት:: እመ ብርሃንም በንጹሐት እጆቿ ባረከችውና ዐረፈች::
ይሕን ጊዜ ምሥጢር ተገልጦለት ዜማና ቅኔ ያለውን የመጀመሪያውን ውዳሴ ማርያም ዕለቱኑ ደርሶ ለሐዋርያት ሰጣቸው:: እነርሱም ከምስጋናው ጣዕም የተነሳ ተደነቁ:: ከሐዘናቸውም ተጽናኑ::
ይሕ ድርሰት በዘመነ ሰማዕታት በመጥፋቱ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ አምልቶና አጉልቶ ደርሶታል::
ቅዱስ ብሩታዎስ ግን ብዙ ሃገራትን በሐዋርያነት አዳርሶ በመልካም ሽምግልና አርፏል::
††† ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቅዱስ ብሩታዎስ ላይ ያሳደረውን የድንግል እናቱን ፍቅር በእኛም ላይ ያሳድርብን::
††† ሚያዝያ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ብሩታዎስ ሐዋርያዊ
2.አባ ዕንባቆም ጻድቅ ሰባኬ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ (በትውልድ የመናዊ በጸጋና አገልግሎት ግን ኢትዮጵያዊ አባት ናቸው:: ደራሲ : ሰማዕት : ባሕታዊና ሊቀ ምኔትም ነበሩ::)
3.ቅዱስ አካክሪስ
4.ቅዱስ ይወራስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1፡ እግዝእትነ ማርያም
2፡ አበው ጎርጎርዮሳት
3፡ አባ ምዕመነ ድንግል
4፡ አባ ዓምደ ሥላሴ
5፡ አባ አሮን ሶሪያዊ
6፡ አባ መርትያኖስ
7፡ አቡነ በጸሎተ ሚካኤል
††† "ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሠጠዋል:: ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና:: ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል . . . ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጐም ይሰጠዋል:: ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደሚፈቅድለት እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል::" †††
(፩ቆሮ. ፲፪፥፯-፲፩)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

✝✝✝ እንኩዋን ለቅዱስ ፃና ሰማዕት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✝✝✝
+"+ ቅዱስ ፃና +"+
=>በቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን አሉ:: ዛሬ የምናከብረው ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና:-
*በዘመነ ሰማዕታት የነበረ:
*ቅዱስ ኤስድሮስ የሚባል ደግ ጉዋደኛ የነበረው:
*ሁለቱንም እናቶቻቸው እንደሚገባ ያሳደጉዋቸው የ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ክርስቲያኖች ነበሩ::
+በወጣትነት ዘመናቸው በድንግልና: ቅዱስ ፃና የሠራዊት አለቃ: ቅዱስ ኤስድሮስ ደግሞ የልብስ ዝግጅት ባለሙያ ነበሩ:: ከሚያገኙት ገቢ ለዕለት ጉርስ ብቻ እያስቀሩ ለነዳያን ይመጸውቱ ነበር::
+በመከራ ዘመን (ዘመነ-ሰማዕታት) ቅዱሳኑ ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው በክርስቶስ ስም መሞትን መርጠዋል:: አስቀድሞ ቅዱስ ኤስድሮስ አንገቱን ተሰይፎ የክብርን አክሊል ተቀዳጅቷል::
+ሰማዕቱ ቅዱስ ፃና ባልንጀራው ኤስድሮስ ከተገደለ በሁዋላ ለ36 ቀናት በጨለማ እሥር ቤት ውስጥ ከብዙ ስቃይ ጋር ቆይቷል:: መከራን ቢያፀኑበትም በሃይማኖቱ ጽኑ ነበርና እርሱንም በዚሕች ቀን ገድለውታል::
+ደግ እናቱ በቦታው ነበረችና መላዕክት በክብር ነፍሱን ሲያሳርጉ ተመልክታለች::
=>ፈጣሪ ከሰማዕቱ ክብር ያድለን::
=>ሚያዝያ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ፃና ሰማዕት
2.አባ ሱንቱዩ ሊቀ ዻዻሳት
3.አባ ይድራ
4.የደብረ ሲና ቅዳሴ ቤት
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
=>+"+ ልጆች ሆይ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ: አሸንፋችሁአቸውማል:: በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ታላቅ ነውና:: እነርሱ ከዓለም ናቸው:: ስለዚህ ከዓለም የሆነውን ይናገራሉ:: ዓለሙም ይሰማቸዋል:: እኛ ከእግዚአብሔር ነን:: እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል:: ከእግዚአብሔር ያልሆነ አይሰማንም:: +"+ (1ዮሐ. 4:4)
<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>