Ŋever Ĝivĕ űp
45 subscribers
172 photos
137 videos
18 links
Never give up.everyone has bad days .
Pick yourself up& keep going.

👉 quotes & facts

👉 funny videos 😀😁 & tiktok video

👉 poem

👉 best🌆 wallpapers 🌌
Download Telegram
#ዳን_አድማሱ
#ከፍቶሽ_እንዳላይ
#ሙዚቃን_በግጥም
@lyricsamh
🎹🎹🎸🎹🎸🎹🎸🎹🎸
🥁🎸🥁🎸🎸🥁🎸🥁🥁
ከፋኝ የአንቺን እንባ ከአይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካ ልብሽ ደስታ የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን አለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጪው ጭራሽ
ህይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታይ
ምንም አይኔ ከፍቶሽ ባላይ
🎸🥁🎸🎸🥁🎸🥁🥁
ጊዜን ላይገዛው ሠው ላይመልሰው
ቢያዝን ቢጨነቅ ትርጉም ላይሰጠው
ያልፋል ይሄም ቀን አንቺን ያለፋው
እስከዛው አይንሽ ማንባቱ ይብቃው
ቀኑም ቢጨልም ሰማዩ ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋን ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
🥁🎸🥁🎸🎸🥁🎸🥁🥁
🎹🎹🎸🎹🎸🎹🎸🎹🎸
ከፋኝ የአንቺን እንባ ከአይንሽ ሳየው
አዝኗል ለካ ልብሽ ደስታ የለው
እንኳን አዝነሽለት ይህን አለም
ስቆም የሚሞላ ከቶ አይደለም
ለሀዘን ፊት አትስጪው ጭራሽ
ህይወት ላትኖሪያት ደግመሽ
ለኔ ደስታዬ ነው ብታይ
ምንም አይኔ ከፍቶሽ ባላይ
🎸🥁🎸🎸🥁🎸🥁🥁
ፀሀይ ባትወጣ ቢያይል ደመናው
ቢከብሽ እንኳን እሾህ ጋሬጣው
ለቀን አለቃ ቀን አለውና
አሮጌው በአዲስ ይተካል ገና
ቀኑም ቢጨልም ሰማዩ ቢመሽ
ጠዋት ይሆናል ይነጋል አይዞሽ
ነገን ለሚያስብ ተስፋን ላዘለ
ሲያድር ከዛሬ ሌላ ቀን አለ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ.. እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
ከፍቶሽ እንዳላይ
አዝነሽ እንዳላይ
🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧
#stay_home_be_safe
#ሙዚቃን_በግጥም
@lyricsamh #share_now_please