Ŋever Ĝivĕ űp
45 subscribers
172 photos
137 videos
18 links
Never give up.everyone has bad days .
Pick yourself up& keep going.

👉 quotes & facts

👉 funny videos 😀😁 & tiktok video

👉 poem

👉 best🌆 wallpapers 🌌
Download Telegram
🌺🌹 #እኔ_እወድሻለው🌹🌺

ባማሩት ዜማዎች በቅኔ ተቀኝተው
እንደገጠሙልሽ ብዕሩን አድምተው
ማታን በጨረቃ ቀን በፀሃይ መስለው
ውበት ከሚለኩት በሸራ ላይ ስለው
የእውነት ልንገርሽ፤
ከነሱ አስበልጬ እኔ እወድሻለው

ዝምታ አሸንፎኝ በፍቅርሽ ተይዤ
የምልሽ ሲጠፋኝ አንቺን ሳይ ፈዝዤ
እገጥምልሻለው በሃሳቤ ጓዳ ምናብ ተመርኩዤ

ከተራራው ማዶ ከአድማሷ ባሻገር
ከደመናው በላይ ስላንቺ ስናገር
ብትኖሪ እላለው ብትሰሚው ጬኸቴን
ዝም ያልኩትን ፍቅር የመውደድ እውነቴን
በምናልባት ተስፋ በፍርሃት ታምሜ
ታድያ እንዴት ልናገር ፊት ለፊትሽ ቆሜ
የውሸቴን አይደለም እውነት እልሻለው
ከራሴ አግዝፌ እኔ እወድሻለው🌹♥️

<<<Join and Share>>>

@fikrhn
@fikrhn
@fikrhn
... #Jolly