#ጓደኛዬ @Aşk
.
በጠራራ ፀሀይ ግርዶ
አጥቼ ውስጤ ተሰዶ
ከዘመድ ከወንድም በላይ
የተሰጠሽኝ ከሰማይ
ከለላ ብርታት መከታ
አጫዋች የኔ ስጦታ
ጉርብትናዬ ቤቴ ነሽ
ሚስጥሬን ሁሉ ምነግርሽ
----
ሳጣሽ መጎዳቴ ነው ካላየሁሽ ህመሜ
ደስታ ሀዘን የልቤ ረፍት ነሽ የኔ ሰላሜ
ሳላወራ የሚገባሽ የውስጤን የምትረጅኝ
ሀሳብ አካፋይ መካሪ ከልብሽ የምትወጅኝ
ታማኝ እውነተኛ ሰው ልዩ የኔ ሀቀኛ
ደህና ሁኝልኝ አካሌ የኔ ውድ ጓደኛ
…Hanita.....le migebaw sew
Join
👉 @hayutki