Harari COC
219 subscribers
220 photos
3 videos
2 files
4 links
Harari People Regional State Center Of Competence
Download Telegram
የነጭ ሪቫን ቀን በሀረሪ ክልል ልህቀት ማዕከል ተከበረ።

የነጭ ሪቫን ፌስቲቫል ቀን"ሠላም ይስፈን በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ይቁሙ!!"በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ እየተገበረ ይገኛል።

የነጭ ሪቫን ቀንን አስመልክቶ የተዘጋጀው ፅሁፍ በተቋሙ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር ወ/ሮ አይሻ ተማም ቀርቦ ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።
በውይይቱ ወቅትም ወ/ሮ አይሻ ተማም እንደገለፁት የነጭ ሪቫን ቀናቶቹ የሚከበሩበት ዋና አላማ በአለም እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የሰበዓዊ መብት ጥያቄ መሆኑን ግንዛቤ ለመፍጠርና መንግስት የሀይል ጥቃትን ለማስወገድ የገቡትን ቃል እንዲጠብቁ ጫና ለመፍጠር እንዲሁም በየአካባቢው የሚደረጉ የፀረ-ፆታ ጥቃት ትግሎችን ለማጠናከር እንደሆነ ተናግረዋል።
ከ240 በላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር ጥር 4/2015 ዓ.ም በሀዋሳ ይከፈታል፡፡

ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ‹‹በሀገሬ ምርት እኮራለሁ፤ ከሀገር ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ!›› በሚል መሪ ቃል ከ240 በላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር አዘጋጅቷል፡፡

ሀገር አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛሩን በማስመልከትም ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

መግለጫውን የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እንደገለፁት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከሚያደርጋቸው መንግስታዊ ድጋፎች አንዱ የገበያ ትስስር መፍጠር በመሆኑ ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ኤግዚቢሽን እና ባዛር ተዘጋጅቷል፡፡

ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ በሚካሄደው ኤግዚቢሽን እና ባዛር 246 ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉ ሲሆን ከ35 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍል ኤግዚቢሽን እና ባዛሩን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ 600 ለሚሆኑ ጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 18 ሚሊዮን ብር ያህል የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ፣ ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርት እንዲጠቀም ማስተዋወቅ እና  ኢንተርፕራይዞች ሥራ መፍጠር ብቻ ሳይሆን ሀብት እንዲፈጥሩ ዕድሎችን ማመቻቸት የኤግዚቢሽን እና ባዛሩ ዋና ዓላማ መሆኑን ክቡር ሚኒስትሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ለስድስት ቀናት በሚቆየው ኤግዚቢሽን እና ባዛር የገበያን ትስስር መፍጠርን ብቻ ሳይሆን የኢንተርፕራይዞችን ችግር መፍታትን ታሳቢ ያደረገ እና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ጥናትና ምርምሮች የሚቀርቡበት የፓናል ውይይት የሚደረግበት ይሆናል፡፡

ተቋሙ በሚኒስቴር ደረጃ ከተቋቋመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀውን ኤግዚቢሽን እና ባዛር የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ግብርና ሚኒስቴር እና የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ፣ ክህሎት  እና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ በጋራ ያዘጋጁት ነው፡፡

ጥር 2/2015 ዓ.ም፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
የሐረሪ ክልል ልህቀት ማዕከል የ2015ዓ/ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከማኔጅመንት አባላት ጋር እየገመገመ ይገኛል።

በመድረኩም ላይ ተገኝተው መድረኩን የመሩት የልህቀት ማዕከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢብሳ ኢብራሂም ሲሆኑ ባለፋት 6ወራት የተከናወኑ ተግባራትን በየዲፓርትመንቱ ባሉ ስራ ሂደቶች ቀርቦ በማኔጅመንት አባላት በኩል ሰፊ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።